የገጣሚያን ማኅበር @ye_getamian_mahiber Channel on Telegram

የገጣሚያን ማኅበር

@ye_getamian_mahiber


እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
👉መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን👉መነባነብ
👉ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber
Group👉 @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር (Amharic)

ምንም እንደሚያሳያ ለአለም የሚፈልጉ ጌጣጌሚ ሴቶችና እስከ ታላቅ ዘሪቃን ሰዎች ላይ ያተማሩት 'የገጣሚያን ማኅበር' ባህሪ ሁሉ በስነ-ጽሁፍ እና ግጥም የሚመስል ሰውየሚካተቱበት ትምህርትን ለማግኘት፣ እና ለማወቅ። በዚህ ማኅበር ወይም በሌሎች ቲሮ በትምህርት ለሚተዳደሩ ጥመን የሚያሳዝኑ ናቸው ለማኅበረሰብ ለሚረዱት ከሆነ እናትሪክ ይሆናል። የዚህ ማኅበር በኢትዮጵያ የገንዘብ እና ትንሽ እንቅስቃሴ በመስራት የሚገኙት ሴቶች እና ዘራችን አስተማሪ የገጣሚነት የሚካተቱ ግጥሞችን ለመያዝ እና ባህርን ለመውጣት ያስባል። እንደሚለይ ያሉትን የገጣሚያን ዘሮች ከፋይረስትራል ተኮኒክ ወደ ዋቴሪየም ለማምረት፣ እና እናትሪክ ለማታበቅ፣ የመነባነብን ለማሳሰብ ስለሚያመላለሱ እና በኢትዮጵያ ተማሪዎቹን የሚወቅ ማኅበርዎ ከእርምጃው እንደተከተሉ ባህር ያስተምሩታል።

የገጣሚያን ማኅበር

22 Jan, 17:13


......የትናንትናን እንጂ ነገን ማን ያውቃል? ዘርህን ከምትይዝ እግዚአብሔርን ያዝ ለክፉ ቀን ገንዘብ ጥሩ ነው.... ግን ይገርምሃል ገንዘብ ካርድ ያመጣል እንጂ ጤና አይሰጥም። አልጋ ይገዛል እንጂ እንቅልፍ አይገዛም።
ጥሩ ነው ብር መያዝ።ከብር በላይ ግን የሚያዋጣው እግዚአብሔርን መያዝ ነው። ታርክህ ይቀየራል እግዚአብሔርን አጥብቀህ ያዝ።😍

ዮናታን አክሊሉ
ሰናይ ምሽት

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

22 Jan, 13:30


አዲስ ግጥም በዩቲዩብ ቻኔል ተለቋል።
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
https://youtu.be/oUkJjf0a-Vg?si=FfqR0cw--CwDfKeM

የገጣሚያን ማኅበር

22 Jan, 06:05


ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?”
— ማቴዎስ 6፥26

👀 ❤️


like and subscribe🙏
https://youtube.com/shorts/Q0-K6Pjr-fc?si=95cFCSgk0uvA9YpD

የገጣሚያን ማኅበር

21 Jan, 12:45


የገጣሚያን ማኅበር pinned «አዲስ የግጥም Video በዩቲዩብ ቻኔላችን ተለቋል ገብታችሁ ተባረኩበት❤️ ለቻኔሉ አዲስ ከሆናችሁ Subscribe በማድረግ በተሰብ ይሁኑ።🙏 ርዕስ፦እዩትማ ውዴን ገጣሚት፦እየሩስ ተፈሪ Link https://youtu.be/oUkJjf0a-Vg»

የገጣሚያን ማኅበር

21 Jan, 12:44


አዲስ የግጥም Video በዩቲዩብ ቻኔላችን ተለቋል ገብታችሁ ተባረኩበት❤️
ለቻኔሉ አዲስ ከሆናችሁ Subscribe በማድረግ በተሰብ ይሁኑ።🙏

ርዕስ፦እዩትማ ውዴን
ገጣሚት፦እየሩስ ተፈሪ

Link
https://youtu.be/oUkJjf0a-Vg

የገጣሚያን ማኅበር

21 Jan, 10:37


የቸኮለች አፍሳ ለቀመች
አገኛለሁ ብላ ዘርግፋ አፈሰች
ሳትፀልይ ወጥታ ፈቃዱን ሳታውቀው
የእግዚአብሄርን ሳይሆን የሰውን ሰብስባው
ተንጦልጡላ ጠፋች እየተጣደፈች
ያላትን ሳታየው ሌላ እየፈለገች
ሸክሟን ሳትቋጥረው ለማንሳት ማጎንበስ
ያላትን ዘርግፋ ሌላውን ለማፈስ
ትርፉ ባዶ መሆን አይሞላ ጆንያው
ሁሉም ተዘርግፎ ፈሷል በየሜዳው
እጅ ላይ ያለውን ቀድሞ ነው መረዳት
ከመባከን አርፎ ከሌላ አለም ዙረት ።

                     ✍️ ተፃፈ በእየሩስ ተፈሪ

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

21 Jan, 09:34


አብ ባለሞያ ነው ድግስ ያውቅበታል
አንድ በግ ሰውቶ ዓለም ጠግቦበታል❤️

ሰናይቀን😍

የገጣሚያን ማኅበር

20 Jan, 18:34


ትንሽዬ ምክር

አቅም እንዳለህ በወሬ አታውራ
በማድረግ እንደምችል አሳይ በስራ
ለምን ስባል....🤔

ይሄ ትውልድ በሽለላ ሳይሆን
በተግባር ይገንባ፥
ካልሆነ ያን አወዛጋቢ ምላስህን
ይዜ ወደ ቤት ግባ።

የኔ ትዝብት..

አንዳንድ ሰዎች ምላሱ የዓለም
ካርታ ስያክል፣ተግባሩ ደግሞ
ስንዝር እንኳን አይሞላም።

ለማንኛውም...

አውራ አውራ አውራ አሁንም አውራ፣
ብልህ ከሆንክ ያወራሄውን ሁሉ ስራ፣
ካልሆነ የማትሰራውን ፍጽሞ አታውራ።


             ተጻፈ በሶለን
      ጥቅምት 18/2016
                ወ.ሶ

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

20 Jan, 11:18


እግዚያብሔር ሕያው አምላክ ነው❤️‍🔥

የገጣሚያን ማኅበር

20 Jan, 11:13


የሚወደኝ ጌታ

የሚወደኝ ጌታ
የፈጠረኝ ለታ
በዛ በውብ ገነት
ልንፈላሰስበት
ሁሉን አመቻችቶ
ረዳት አበጅቶ
እንድኖር በድሎት
የሞት ሞት እንዳልሞት
ይቺን ዛፍ አትብላት
ብሎ ቢነግረኝ
እያስጠነቀቀኝ
የአምላክ ተቀናቃኝ
ዲያቢሎስ አታሎኝ
በምኞቴ ገብቶ
በአይኔ አስጎምጅቶ
አሰወደቀኝና
ይነዳኝ ጀመረ ወደሞት ጎዳና

የሚወደኝ ጌታ
ህጉን የጣስኩ ለታ
እያፈላለገኝ
አዳም የት ነህ አለኝ
ኃጢአት መሃል ገብቶ
ግድግዳ ገንብቶ
እኔና እግዚአብሄር
አንድ ላይ እንደኖር
በኔው ስተት ውድቀት
ተለያየንና
እራመድ ጀመረ በሲኦል ጎዳና

የሚወደኝ ጌታ
በኃጢአት ስረታ
ስቆም ከሞት ተርታ
ብዙ በድዬውም
ትዛዙን ብጥስም
ፍቅሩን አልቀነሰም
ኃጢያትን ቢጠላም
እጅግ ቢጠየፍም
ኃጢያቴን ሊሸከም
አላንገራገረም
እንደበግ ተነድቶ
በመስቀላይ ሞቶ
በቀኙ አስቀመጠኝ
ሰማይ አስገብቶ

ሼር አድርጉ via @YIKIRTAYEE

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

20 Jan, 05:53


“በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤”
— ፊልጵስዩስ 4፥8

like and subscribe🙏
https://youtube.com/shorts/Q0-K6Pjr-fc?si=95cFCSgk0uvA9YpD

የገጣሚያን ማኅበር

19 Jan, 18:05


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌለ
ኃይማኖት ራሱ ገዳይ ነው። ሰሞኑ ብዙ ነገሮችን እያየሁ ነበረ። ይገርማል ብዙ ወድቀትና ክስረት ሊኖር ይችላል ኢየሱስ ክርሰቶስን እንደማጣት ያለ ወድቀት የለም.... በሕይወትህ ወስጥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትልቁን ድርሻ ስጥ።❤️

በክብር እደሩ😍

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

19 Jan, 13:52


.    💒ዛሬ ቸርች ሄዳቹዋል⛪️ ?

ቸርች ለሄዳቹም ላልሄዳቹም ዛሬ አሪፍ መንፈሳዊ ቻናል ልጋብዛቹ☺️


አዎ ሄጃለው😊 ወይም እረ አልሄድኩም😔 በማለት መልሱ

ታዲያ መዋሸት አይቻልም

የገጣሚያን ማኅበር

19 Jan, 09:02


እኔ አርኤል ነኝ!!!!!!!!

በደም ዋጋ የተገዛሁ
በልጁ ሞት የተቤዤሁ
ከጨለማ ብርሃን ያየሁ
  አምላክ ተሰቅሎ ያዳነኝ
  እኔ አርኤል ነኝ።


     ላየሁት ሁሉ የማልሽነፍ
     ለአለም አክልል ማልሰለፍ
  ይልቁንም ለአለም ሁሉ የምተርፍ
  ፍቅር በቀራንዮ የወለደኝ
  እኔ አርኤል ነኝ።



  እንደ ጥበበኛ የምመላለስ
ጉጉቴ የሆኔ ክርስቶስን መልበስ
  ራዕይ ያለኝ የጠፉትን የመመለስ
  እግ/ር በልጁ ያወቀኝ
  እኔ አርኤል ነኝ።


  ለአለም የማዳርስ ወንጌሉን
ለተጨነቁት የማበስር ምሥራቹን
ለታሰሩትም የማዉጅ መፈታትን
  ልዑል ለራሱ የመረጠኝ
  እኔ አርኤል ነኝ።


     የቀራንዮ ፍቅሩ የማይቀልብኝ
      የመስቀሉ ሥራ ያረከሰብኝ
     ዘላለማዊነቱ የገባኝ
   በእምነት ሞኝነት ያመንኩኝ
   እኔ አርኤል ነኝ።


ግብዝነት በሌለዉ 💕ወዳጄን ምወድ
ወደ ክፎች ምክር ፍፁም የማልወርድ...
በመልካምነት ጎዳና ምራመድ
እሩህሩህ አባት እርህራሄን ያስተማረኝ........
እኔ አርኤል ነኝ።


........የክብሩ መንፀባረቅያ
         የልጁ መልክ መታያ
  የመንፈሱ መዋያ ማደርያ
  በ አዶናይ የማልደራደር
... . 


🔥.. . . . . እኔ አርኤል ነኝ.. . .🔥
🔥.. . .. .እኔ አርኤል ነኝ.. . . 🔥
🔥.. . . እኔ አርኤል ነኝ.. . 🔥
🔥. . እኔ አርኤል ነኝ.. . .🔥
🔥 እኔ  አርኤል ነኝ.. . .🔥

📥Group👇
  🌿
@yegetamianmahiber 🌿
📥 Channel👇
🌿
@Ye_Getamian_Mahiber 🌿

Subscribe our YouTube channel
.
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

18 Jan, 16:33


አበዛክ ይሉኛል!..
አላዩም አጢሀቴን...
መስቀል ላይ ሲሰቅልህ
አላዩም በደሌን ...
በየዕለት ሲያዝልህ
አላዩም ህይወቴን ..
እንዴት እንዳሰብከው
አበዛክ ይሉኛል...
   ሞንልህን አይተው።
አላዩም ዐይንህን ..
ስለእኔ ሲያነባ
በጭንቀትህ ሌሊት:
ደብረዘይት አምባ
አላዩም እግርህን :
ሚስማር የበሳውን
አበዛክ ይሉኛል አይተው ምሆነውን።


ይበዛል ወይ ሽቱ ከእግር ያፈሰስኩት
ይሉኛል ማይገባ በፊት የሆንኩት
ያደነቁኝ ሁሉ ናርዶሴ ሲሰበር
ያየሁትን ቢያዩ በእነሱ ይብስ ነበር።

አልፈርድም በእነሱ አንተን   ባልቀመሱት
እግር አሉት እንጂ
ክብር ነው ያቀፍኩት።
አልል ለምን አሉ
ትልቅለእሱ ሰጠ።
ፊትን ስለሚያዩ ካንተ የእኔ በለጠ።

ይሆኑ ነበረ ..
እንደ መቅደላዊት
  ወይም እንደ ዳዊት
ይሰጡክ ነበረ ...
ውዱን ውዳቸውን
ይሰዉ ነበረ..
በኹር ልጃቸውን
አንዴ ቢያዩ ኖሮ የሆንክላቸውን።


@የሱመልስ

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

18 Jan, 13:22


“Behold my hands and my feet, that it is I myself: handle me, and see; for a spirit hath not flesh and bones, as ye see me have.”
  — Luke 24፥39



“እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።”
  — ሉቃስ 24፥39

like and subscribe🙏
https://youtube.com/shorts/Q0-K6Pjr-fc?si=95cFCSgk0uvA9YpD

የገጣሚያን ማኅበር

17 Jan, 19:08


እሱን ስሙት🙏

🔥 ሳለ ለዛዉም ፍም
   እንጨት  አልቆ ቢነጥፍም
  ግንዱ  አብነዉ  ያዉም አባት
   ያዘጋጀ  የልጅ  መስዋት።

   ሰዉ ለምኑ  አጠመመዉ
   ገነት  ሳለ  ሲኦል  ጣመዉ


???????...............

   እሱን ስሙት ዛሬም ህያዉ
    እየሱስነዉ  በሩ መግቢያዉ።
   
   
ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

16 Jan, 17:22


የአንተ/ቺ መልእክት ነው አንብቡው

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።”
  — መዝሙር 27፥14

እግዚአብሔር ተስፋዬ ነው
እግዚአብሔር ያበረታኛል
እግዚአብሔር ልቤን ይፀናልኛል
እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ

subscribe the channel 🙏🙏❤️❤️
https://youtube.com/@jesus_smri?si=jH9uuYfHkdVq2zOK

የገጣሚያን ማኅበር

15 Jan, 18:27


ያዝናት.....

አምላክ ውበት ነስቶ
ሰራኝ አበላሽቶ
ያለች ይቺ ሴት ናት...

እግዚአብሔርም መለሰ...

".....ልቀቋት
ልንገራት
እኔ እንደምወዳት🥰

የገጣሚያን ማኅበር

15 Jan, 16:55


መዝሙር 91


subscribe the channel 👇👇❤️❤️
https://youtube.com/@jesus_smri?si=jH9uuYfHkdVq2zOK

የገጣሚያን ማኅበር

15 Jan, 04:25


አንተማለት ለኔ....

የፍቅር ወኔ
እኔ ሰሌዳ አንተ ጠመኔ
የተፃፈብህ  ሙሉ ዘመኔ

ጌታ  ወዳጅ አባት
ስትሆንስ  እንደናት


አንተማለት ለኔ
ቋቋየነህ  አንደበቴ
መዉጫ መግቢያ
ሀይል ጉልበቴ

ጌታ ወዳጅ አባት
ወንድምም ነህ እህት


አንተማለት ለኔ....

እዉነቴ ነህ ማትቀየር
የሰላም ቤት የፍቅር
ሀገር

መሬቴነህመቀመጫ
ሰማይ አክሊል
ምድር ዋንጫ።

እየሱሴ.........

ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

የገጣሚያን ማኅበር

14 Jan, 17:45


ቺርስ🥂.....

ምንም ሳናሳብቅ ምንም ሳንል ዘመም😞
በጥርስ እየሳቅን ለደበቅነው ህመም።🥹


ቺርስ ከኔ ጋር😭

የገጣሚያን ማኅበር

14 Jan, 06:22


መቼ ይከፋኛል በህልውናው ሆኜ
ከሁኔታም በላይ ከሁሉም ተንኜ
መኖር ነው ስራዬ ማውራት ነው ፅድቁን
በመንፈሱ ሆኜ እያሰብኩት እሱን
ሁሌ ይናፍቀኛል የሰማዩ ቤቴ
እጅጉን ጓግቶኛል ፊቱ የአባቴ!!
❤️🔥ህልውናዬ🔥❤️     .
📥Group👇
  🌿 @yegetamianmahiber 🌿
📥 Channel👇
🌿 @Ye_Getamian_Mahiber 🌿

Subscribe our YouTube channel
.https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

14 Jan, 04:33


አስተውል_ወገኔ

ሀያል የተባሉት መንግስታት ተናውጠው
ለውድቀት ሲዳዱ ዝለው ተንኮታክተው
ተመክተው ከርመው በ"አለን" "አለልን"
ከእጃቸው ሲያጡ የተማመኑትን
ኪሳቸው ሲራቆት ገንዘብ ሲሄድ በኖ
ውድቀት ድካማቸው ሲሰማ እጅግ ገኖ



አስተውል ወገኔ ከሁሉ የገነነ እንዳለ ገናና
ማይናወጥ መንግስት ዙፋኑ የፀና፡፡


በመጠላላት ላይ ክፋት ሲገነባ
የሰው ነፍሱ ቀሎ ሲረግፍ እንደ አበባ
ዝሙት እርኩሰቱ እንደ ባህል ታይቶ
መንግስት አንቱ ሲባል ሴት ከሴት አጋብቶ
ወንድን ከወንድ ጋር ሲድር ባደባባይ
እንደ ስልጣኔ እንደ እድገት ሲታይ

አስተውል ወገኔ
        በመሠልጠን ሽፋን ተከናንቦ ሲያምር
        ፍፁም እንዳትረሳ ሞት እንዳለ ከስር፡፡


ትውልድ በራሱ አለም ፋኖ እንደልቡ
ፍፁም ሲምታታበት መነሻና ግቡ
እግዜር የለም ብሎ ሲክድ ፈጣሪውን
ጌታንም ሲያስቆጣ አድርጎ ያሻውን



አስተውል ወገኔ
        በዚህ ማይደሰት እንዳለ የበላይ
        ፍቃዱን ሚፈፅም የሌለበት ከልካይ፡፡

አስተውል ወገኔ
          ለይቅርታ ፈጥኖ ለቁጣው ሲዘገይ
         የምህረቱን ብዛት እንደ ቀልድ እንዳታይ፡፡
                   ምንም ቢምርህም
          ሺህ ጊዜ ይቅር ብሎ ቢያባብልህም
ሊቀጣ ሲነሳ ማንም ተሰውሮ ከቁጣው አይድንም፡፡


ቀኑ እየጨለመ ዘመኑ ሲከፋ
አለም ግራ ገብቷት ፍፁም ስቆርጥ ተስፋ
ለችግሮች ሚሆን መፍትሄ ሲጠፋ
ሞትና ጭንገፋ ያለ ልክ ሲስፋፋ
አስተውል ወገኔ የመጣው ማዕበል ይዞህ እንዳይጠፋ፡፡

        ይልቅ ስማኝ ወገን ተላላ አትሁን
        ለስጋህ ስትኖር አታጉድል ነፍስህን፡፡


ነፍሱን አሳልፎ ለአለም የሰጠ
በእርሱ ሚያምኑትን ከሞት ያስመለጠ
የበጎቹን ህይወት የማይተው ለተኩላ
ኃጢያትን እንጂ ኃጢውን ማይጠላ
ታታሪ ጠባቂ የታመነ እረኛ
አንተን ሚጠብቅህ ሌት ተቀን ሳይተኛ
እንዳለ እንዲገባህ የለም ያልከው እርሱ
ይበጂሀል ጓዴ ፈጥነህ መመለሱ፡፡


አስተውል ወገኔ ፍፁም አትዘንጋ
ፈጥነህ ግባ እቅፉ መዝጊያው ሳይዘጋ፡፡


       📝selam_fikadu

📥Group👇
  🌿 @yegetamianmahiber 🌿
📥 Channel👇
🌿 @Ye_Getamian_Mahiber 🌿

Subscribe our YouTube channel
.https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

13 Jan, 04:54


ልኩ ማይታወቅ የጨለማ ባህር
ሞት የነገሰበት የአጋንቶች ህብር
ህይወቴን ጠምጥሞ ጠፍንጎ ጠፍሮ
ነፍሴን አስጨንቆ መንፈሴን አማርሮ
ውበቴን አጥፍቶ ኑሮዬን አናግቶ
ውስጠቴን አራቁቶ ደንግባቴን በልቶ
በከንቱ አስቀመጠኝ ካለሁበት አለም
እየሱስ ራርቶልኝ ሊተወኝ አልቻለም
አልሄድኩም እሱጋ ከቶ አልመረጥኩትም
ፈልጎኝ መጣ እንጂ እኔ አልፈለኩትም
የኔ አሳቢ ነው ከልቡ የወደደኝ
ክብሩን ሁሉ ትቶ ህይወቱን የሰጠኝ!!
      #የኔ ፈላጊ#...

የገጣሚያን ማኅበር

12 Jan, 18:37


20k😳❤️❤️
Tanx y'all

የገጣሚያን ማኅበር

12 Jan, 11:32


የገራፊው ማስታወሻ!

ፈቅዶ ማነስ ነው ፍቅር!

በክፉ ዕለት፤ በቀን ግማሽ አጋጣሚ፤
የአዳም ሐይል አሸንፎ፤ ሲበረታ ተቃዋሚ፤
ባለስልጣን በሚባሉት ፤ግራ ቀዳጅ ቀኝ ሰፊ፤
እኔም በዳይ ቀጪ ሆኜ፤አደረጉኝ ሰው ገራፊ።
፧፨፧፦
ሰጡኝ ሙያ አወዳድረው በቀጣሪ፤
አርገው ሾመው እንድገርፈው
እኔን በዳይ አንዱን ማሃሪ።
፧፨፧፦
እኔ እንደሆን ሙየዬ ነው፤
ሰውን ማስጮ በሰው ጅራፍ።
ቆይ ግን ይኽ ሰው
ምን ቢያውቅ ነው ሚገረፈው በሰው ምዕራፍ ??
ብሎ ማሠብ አልችልበት ማሰላሰል፤
ግረፍ ብለው የሰጡኝን በግርፋት ማቆሳሰል፤
እኔ እንደሆን አይሰለቸኝ፤
ስስ ጀርባውን አመቻቸው ለመግረፍም እንዲመቸኝ፤
አጣበቁት በደረቱ ወደ ግንዱ ሳብ አረኩት፤
እያቆሰልኩ የምገለው ለእኔ እንደሆነ መች አወኩት።

መች ተረዳው መቼ ገባኝ
ባሪያ መልኩ መች አባባኝ
መች አየሁት ሲያዜሙለት
እነ ገብርኤል ሲሰግዱለት
የዮርዳኖስ ጉድ ሲገለጥ
በአለት ውሃ ጥም ሲቆረጥ
በእስትንፋሱ ቀኔን ሲስል
መቼ ገባኝ እኔነኝ ሲል
መች ተረዳሁ  እኔ ጅሉ
በጭካኔ ምበድለው ቀኑን ሙሉ
ባላውቅ አይደል ስላልገባኝ ፍቅር ቅሉ?

Qባላውቅ አይደል በፍቅሩ ቀን የሆንኩበት ርጉም ክፉ፤
ሚስማር ስለቅም የዋልኩኝ እንዲበሳ ስስ መዳፉ፤
ባላውቅ አይደል
እንደሁ እስቲ
ምናለበት ቅዱስ መፅሐፍ ትንሽ ብማር
ለነገሩ ምን ያደርጋ፤ ለብረት ቤት የእንጨት ሚስማር
ብዬ ኖሬ ባለመማር ፤እንደ ይሁዳ ጅል ከምሆን
ሞቶ ሚያድን ልጅ ለማየት፤ በተጋሁስ እንደ ስምሆን

ከአዳም እንኳ በሰማሁት  ጥረ ግረ ብላ እንዳለኝ፤
በጥረትም እንዳላመልጥ  ያለመማር ቀኔ ጣለኝ።
ይኸው አሁን በዚህ ዘመን መጨረሻ፤
የእርሱን መንግስት ለሚሻ፤
ተምሮ አምኖ ለሚቀበል የፅድቅ ጥሩር ሲሰፋ፤
የኔ ሚዛን ተገልብጦ የስምሆ ሚዛን ደፋ።
ፀፀት መልካም!
ፀፀት ደጉ! ድንጋይ መሬቴን አረሰው፤
ለኔ እንደሆነ እያሳየኝ ንፁህ ደሙን ያፈሰሰው፤
አፈረሰው!!
ድንጋይ ልቤን ያልነበረ እስኪመስል፤
በሩሩህ ፍቅሩ ትውስታ መላ አካሌ እስኪቆስል፤
አስታወሰኝ ያን ሰመመን
አስታወሰኝ የኔን ዘመን
ትዝ ይለኛል ያ ጅራፌ
ትዝ ይለኛል ረጋሚ አፌ
እንደ ቀላል እንደ ዘበት
በደም በወዛ ገፅታው፤ ምራቄን ስደርብበት
ክብሩን ሳቀል ተስገብግቤ
ሊገድለው ሲጨክን ልቤ
አንዴ ከቆጥ አንዴ ከባጥ
ስሙን ላጠፋ ስሯሯጥ
አየሁት ራሴን ታዘብኩት ራሴን አገኘሁ ቀልዬ
ራሴን ስል እሱን ጥዬ ተገኘሁ ቀልዬ
አሁን ገባኝ ፍቅር ልኩ
ሚያድግም ቢሆን የማያድግ ሰው አትንኩ
ሰው ይሁን ለሰው ጥቅሙ
መውደድ ነው ፍቅር ትርጉሙ
ለሌላው መውደቅ አትልፉ
የገፉትን ሰው እቀፉ
ቀን ሲከፋ  ሲጠቁርበት
ቦታ ጠፍቶት ሚሄድበት
ሚገባበት የሚያድርበት
ባጣ ሰው ላይ
አትፍረዱ ቤት አለሁ mንግስተ ሰማይ

ደግሞም..
ለጎሳ ነፃነት በአደባባይ ሰው ሲበደል
ውሸት በሉ ሰው ለፍቅር ሰውን ሲገል
ውሸት በሉ!
አይቻለው እኔ ገዳይ የፍቅርን ጫፍ
ለገረፉት ለሰቀሉት ሲማልድ አፍ
አይቻለሁ እኔ ገዳይ! እኔ ጠላት! እኔ አጥፊ!
ሎሌውን ለማዳን ብሎ ንጉስ ሲመታ በጥፊ
አይቻለሁ እኔ ጠላት!

አሁን ገባኝ! ምን እንደሆነ ያደረሰው
ለሰው መስቀል እስኪሸከም
ጉልበት ነው ለካ ለመቆም
እያወቁ ለሰው መድከም።
ለካስ
ከልብ እንድትገባ እውነት ሳትዛባ
ጉልበት ነው ለፍቅር ።፤መሆን ጉልበት አልባ።
፨፧።፦፧፦፨፨፨፧፦፥፥፧፨፧፦፥፤፤፤፥፦፧፨፨፨፨፨፨፨፨

ⒹⒹ➫➫የሱመልስ🔥

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

12 Jan, 06:15


1ኛ ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።
¹⁰ ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤
¹¹ ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።

Like and subscribe the channel 👇👇❤️❤️
https://youtube.com/@jesus_smri?si=jH9uuYfHkdVq2zOK

የገጣሚያን ማኅበር

11 Jan, 18:31


.              ጥያቄ
ዳዊትን ለ ንግስና የቀባው ነብይ ሳሙኤል ነው?
   እውነት✔️ ወይስ ሀሰት✖️

ይህን ጥያቄ በትክክል ከመለሳቹ ገራሚ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ።

የገጣሚያን ማኅበር

11 Jan, 18:07


ቀለሜ አለቀ
ልፅፍ ሞከርኩ እና ስለ ፍቅርህ ጥናት
ልገልፀው ሞክሬ የቃልህን ጥምረት
ፅፍ አላልቅ አለ የአንተ ማንነት
አንዱን ሳልጀምረው ሞላብኝ ወረቀት
አትብራራም ለካ በትርክት በንግርት
ከቃላት በላይ ነህ አይገልፅህ መዛዝርት
ብዕሬ አይተርክህ ፁሁፌ አይበቃህ
ሰፋህብኝና ምኔ ይተርክህ
የትኛው መዝገቤ ሰፍቶ ይተንትንህ
መዛግብትም ቢሆን ምን ላይ ያስቀምጥህ
አለማትም ቢሆን ይበቃሀል ብልህ
ውሸት ነው ያንስሀል አየሁኝ ሲጠብህ
ብራናው ላይ ቢፃፍ አንዱ ለምህረትህ
ሌላኛው ለፍቅርህ ያኛው ለውለታህ
ቢባል መከፋፈል ለያንዳንዱ ስራህ
አልደርስብህ አለ ኧረ ምኑ ይብቃህ
ብዕሩ እንኳን ፈርቶ ስላንተ ለማውራት
ይንቀጠቀጥ ጀመር ቀለሙን ለማውጣት
ብራናውም ቢሆን አሻፈረኝ ብሎ
ስምህ ተልቆበት ቢታይ ተጠቅልሎ
ገዝፈህ ልቀህበት በዝተህ ጎልተህበት
አቃተው መገለጥ አንተ ረቀህበት
ታዲያ በዚህ መሀል እንዴት ገልፅሀለሁ
ልፃፍ እንኳን ብልህ ከየት ጀምራለሁ
እንደው ልሞክር ብል ባወጣ ወረቀት
ብእሬን ብስላት ቀለም ብነክርባት
ቋንቋዬ ከሰመ ቃላቴ ደቀቀ
ፅፌ ሳልጨርስህ ቀለሜ አለቀ ።

✍️ተፃፈ በእየሩስ ተፈሪ
25 ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።

'የዮሐንስ ወንጌል 21:25'

የገጣሚያን ማኅበር

11 Jan, 15:50


🎤ከወንድ ዘማሪዎች ውስጥ ማንን ታደንቃላቹ ?

በመዝሙሮቹ የተባረካቹ እና የምትወዱትን ዘማሪ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

የገጣሚያን ማኅበር

11 Jan, 07:11


Yida:
.........በልቤ ተወለድ..........

ማያልፉ የሚመስሉ የመከራ ጊዜያት
የመርገም ጨርቅ ሆኖ እድፍ በደል ሀጥያት
ቃሉ ከሚታጠፍ ሰማይና ምድር ሊያልፍ ለሚቀለው
ለጥፋቱ ዋጋ የአዳም ሲሰላ ደም ብድራቱ ነው።
ቢዘገይ ማይቀደም!አልፋና ኦሜጋ
ምድርን ያለ ባላ ሰማይ የዘረጋ።
አንድ መልኩ ያማረ ከምድር ወገኖች ከቶ የማይመስል
አትፍሩ!እንዳለን የምስራች!እንዳለን ሳስታውስ ምትሀት ይመስል
በልጅነት ልቦና በመታዘዝ ስሌት
እንደ ማለዳ ብርሀን ቀን ሆኖልን ምሽት
ለብርዱ ማብረጃ ከበን ተቀምጠን ባነደድነው እሳት
እንዲ ሲል ተሰማ በሚያምር አንደበት።
.........ሉቃስ ወንጌል 2:11(ይነበባል)
ከንጉስ በላይ ንጉሰ ነገስታት
እንደ መልከፀዴቅ ዘላለማዊ ክህነት
የፍቅር ድንበር ጥግ የፍቅር ጥበባት
የአብ ቀኝ እጅ የነፍሳችን ሰሰት
ህይወትና መንገድ መተላለፊያችን
ወደ ሰማይ መንግስት መሸጋገሪያችን
የሰርጉ ቤት ፍሪዳ ደግሞም ሙሽራችን
ተድላ ገነታችን ፍሬው የህይወት ዛፍ
የንግስናው ስልጣን ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ።
መቀደስ ፅድቃችን ቅዱሰ ቅዱሳን
ህያው የሆነ ህብስት አርኪ የህይወት ጥምን።
ያንገታችን እንቁ የፍላፃን ቀንበር ስሙ ድል መንሻችን
እረፋት በዓላችን ቅዱስ ሰንበታችን
ሞገስ ግርማ ፀጋ የእውነት ጥግ
አምሳል አቻ የለህ በአለም ቢፈለግ
በዙፍን ሲጠበቅ በባለ ጠጋ ቤት
በጨርቅ ተጠቅልሎ አደረ ከበረት
እሰይ ደስ ይበለን በዳዊት ከተማ
ንጉስ!ክርስቶስ ኢየሱስ ተወልዱዋል ለአለም ይሰማ።
በበጎቹ እስትንፍስ በእሳቱ ሙቀት
እረኞችም መተው ህፃንና እናቱን በግርግም ውስጥ አዩት
ሰብአ ነገስታት ኮከብ ተመልክተው
የህፃኑን መወለድ በጥበብ አስልተው
እጣንለክህነቱ ለክብር ማሳያ
ወርቅን ለንግስናው ለንጉስ መለያ
ከርቤን ለሞቱ ፍርድ የውሃን ጥም ማርኪያ።

የትዕግስት ልኬት ሚዛን መደምደሚያ
የፍቅር መልክ ውበት የእውነት መታያ
የሀቅነት ባህር የመታዘዝ አባት
ንጉስ ተወለደ ጌታ ተወለደ
መርገሜን ሊሽረው ህይወትን ሊያበስር ሞቴን የሚገድል
ንጉስ ተወሐደ ጌታ ተወለደ።
የፈርኦን ጭንቀት ህፃን እስከ መፍጀት
የነፍሱ ላይ ነፍስ ያለ መኖር ስስት
የዘማሪው መዝሙር የሰባኪው ስብከት
የትዕግስት ልኬት ሚዛን መደምደሚያ
የፍቅር መልክ ውበት የእውነት መታያ
የሀቅነት ባህር የመታዘዝ አባት
የነብያት ትንቢት ንጉስ  ተወለደ እሰይ ደስ ይበለን።
አምሮትማ ወግ ነው የኔ አልሆነም እንጂ..
  ቢሆንማ ኖሮ ቢቻልማ ኖሮ
ከእረኞች እንደ አንዱ አድርገኸኝ ቢሆን
   ቢሆንማ ኖሮ ቢቻልማ ኖሮ
ከበጎች እንደ አንዱ ተቆጥሬ ቢሆን
   ቢሆንማ ኖሮ ቢቻልማ ኖሮ
ከሰብአ እንደ አንዱ ተገኝቼ ቢሆን
እንደ ግርግሙ አፈር እንደ ተጠቀለልክበት ጨርቅ
       እንደ ስምዖን ተገኝቼ ባቅፍህ
እል ነበር እኔም ማዳንህን አየው ባርያህን አሰናብት።

.... አቤት አቤት አቤት አንደበተ ውሸት
ከአመታት ወዲህ በጊዜ ዘመን ቁጥር
የአንተን መወለድ ቀን ከወሩ ደምሬ ስዘክር ሳከብር
ልክ እንደቀደመው ይህ ልቤ ዛሬ ቦታ የለው
ከበረት ቆሸሸ ማደሪያ አልሆነው።
ከአመታት ወዲህ በጊዜ ዘመን ቁጥር
የአንተን መወለድ ቀን ከወሩ ደምሬ ስዘክር ሳከብር
ልክ እንደቀደመው እንደ እረኞች ምስራች ሳልሰማ
ንጉስ ሳይወለድ በልቤ ክፍል ኤፍራታ።

አቤቱ ልቤን ክፈተው  ይሁን ያንተ ማደሪያ
አቤቱ ገፄን እጠበው አንተን ይሁን ማሳያ!!
አታንኳኳ ደጄን ጆሮዬን ይዤብህ ባልሰማ ስነግድ በጨለማ አለም ወደ ኤማውስ ስሰደድ
በአለም ለባከነች ለጠፋችው ህይወት ምስራች ላክላት:
ከረግረግ አውጥተህ መንገዴን ጠርገኸው ቃልህን ሙላባት:
በኤሶጱ እርጨኝ ከበረዶ ልንፃ
ስበርልኝና ልቤን ፍታው ከአመፃ
ቃልህን ጠብቀህ ከዙፋንህ ወርደህ ለኔ እንደመጣኸው
ምኞቴ ይሄ ነው አንተ የኔ ህይወት
አምሮቴ ይሄ ነው አንተ የኔ መንገድ
ልክ እንደቀደመው ልቤ ማደርያ ይሁን በልቤ ተወለድ!!
        
             ..... 🙏.....

     ለይ ግጥም!
     ይዲድያ&ለምለም

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

09 Jan, 12:58


የአሜሪካ ፊልም ማምረቻዋ ሆሊውድ መገኛ ሎስአንጀለስ በከባድ የሰደድ እሳት እየነደደች ትገኛለች ።
እስካሁኗ ሰዓት ድረስ 57 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሀብትና ንብረቶች ወደ አመድነት የተቀየሩ ሲሆን ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል በአራት አቅጣጫ የተነሱትን እነዚህን አውዳሚ እሳቶች ለመቆጣጥ ከአቅም በላይ የሆኑ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ተለያየ አቅጣጫ እየተዛመቱ ይገኛሉ።

መዝሙር 39
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እነሆ፥ ዘመኖቼን አስረጀሃቸው፤ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሕያው የሆነ ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ብቻ ነው።
⁶ በከንቱ ይታወካል እንጂ በእውነት ሰው እንደ ጣላ ይመላለሳል፤ ያከማቻል የሚሰበስብለትንም አያውቅም።


መክብብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድር ነው?
⁴ ትውልድ ይሄዳል፥ ትውልድም ይመጣል፤ ምድር ግን ለዘላለም ነው።


#የመጨረሻ_ዘመን__ሰደድ_እሳት_CHRSTIAN_NEWS
Boost 👁️
/
#ንጥቀት_አለ //#እየሱስ_ይመጣል/

ክርስቲያናዊ ዜናዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን

@RAPTURE_TUBE
@RAPTURE_FAMILY

የገጣሚያን ማኅበር

09 Jan, 07:18


ጸሎት እንደስካር
ኤልያስ ሽታኹን
~    ~     ~     ~    ~

ሀና  በእግዚአብሔር ፊት አለቀሰች።
በደጁም ተንበረከከች።

ካህኑ ኤሊ
የአፏን እንቅስቃሴ አይቶ  "ሰክራለች" አለ።

ያውም ካህን ነው።
ሲሆን ተጠግቶ ነው  "ምነው" ሊላት ሲገባ ፈረደባት።
እንዲያውም ተናገራት "ወይን መጠጣት አቁሚ" አላት

ልክ ከዚህ በፊት  ሰክራ የሚያውቃት ይመስል
"ስካርሽ እስከመቼ  ነው" አላት

ይሄ በኛ ቢደርስ  ይሄን ብንባል 
አኩርፎ ለመውጣት ሀይማኖት ለመቀየር ሁለቴ ባላሰብን ነበር።

ሀና ግን አስረዳችው።

ታጋሽ ናትና እግዚአብሔር ባርያውን እንዲያየኝ ነው የምለምን አለችው።

አንዳንዴ እኮ
የናንተ ሀዘን የናንተ ለቅሶ ለአንዳንዶች ስካር ነው። ጤና ማጣትም ነው። ምን አልባትም ለብዙዎችም "ፋራነት" ነው።
ግን እንዲህ በሉት

"እኔስ ልቧ ያዘነበኝ ሴት ነኝ።  ጠጅና የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት  ነፍሴን አፈስሁ"

መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
1:15

📥Group👇
  🌿
@yegetamianmahiber 🌿
📥 Channel👇
🌿
@Ye_Getamian_Mahiber 🌿

Subscribe our YouTube channel
.
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

09 Jan, 03:28


     ቃልህ
***

ተይዘህ ያልታሰርክ ተሰ
ብከህ ያላለክ
ዘመናትን የቆጠርክ ጅማሬ የሌለክ
በነቢያት ያለፍክ በትንቢት የተነገርክ
ዘመናትንና ጊዜአትን ሁሉንም ያቀፍክ

ቃልህ.....

እንደ ማር ጣፈጠኝ ሳጣጥመው
በሀሴት ይሞላዋል ልቤን ሲነካው
በቃልህ አልፈህ ውስጥ ልቤን ስትነካው
ውስጥ ማንነቴን በእጅህ ስትዳስሰው
አይኔ ይሞላል በደስታን እንባ
ጥርሴ እየሳቀ አይኔ እያነባ

አንተን ስትናገረኝ.....

ውስጤ ሚሰማው ደስታ
ለከት የሌለው እፎይታ
ገደብ የሌለው እርካታ

በቃ....


ሁሉ ነገሬ በአንተ ተሰውሮ
ሀሳብ ጭንቀቴ በድምፅህ ታውሮ
መሻት ፍላጎቴ በቃልህ ተቀብሮ
አእምሮዬ ከአንተ ተምሮ
የልቤ ጆሮ ከደጅህ ተደግፎ
ያዳምጥሀል አርፎ

ደግሞ......

መርኩዝ ነህ ለውድቀቴ ሀይል ነህ ለድክመቴ
እረፍት ለጭንቀቴ ሙላት ነህ ለጉድለቴ
አፅናኝ ነህ ለሃዘኔ አማላጅ ነህ ለፀሎቴ
ውዱ ስጦታዬ እስትንፋስ ህይወቴ

የአንተን ቃል ምንም አይተካውም
በዘመናት መካከል ምንም አይመስለውም
የትኛውም የሰው ቃል እሱን አይተካውም
የትኛውም ከልካይ ከመሄድ አይገታውም

ትዝታዬ ሁሉ በአንተ ውስጥ ተደብቆ
ሁሌ ይኖራል ልቤ በአንተ ተሰርቆ
በቃልህ ተመርቆ

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

Kebata(KB)



📥Group👇
  🌿
@yegetamianmahiber 🌿
📥 Channel👇
🌿
@Ye_Getamian_Mahiber 🌿


.
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

08 Jan, 19:21


✍️✍️ቀርሜሎስ✍️✍️
በቃ ቻው ልሄድ ነው
ችግሬን ሰብስቤ በሻንጣ ይዛለው
ቀጠሮ አለኝና ጉዞ ጀምሬአው
አደለም መቅረት ማርፈድ ነው ማልችለው
የቀጠረሽ ማነው እያላቹ እንዳይሆን
ሁሉንም የሚወድ የማይጥል ነው ማንን
በቀርሜሎስ እንገናኝ ያለኝ
ከነችግሮቼ ቀጠሮ ያስያዘኝ
ደግሞም እንደልቀር ደጋግሞ የጠየቀኝ
ከነሸክሜ ነው ዛሬ የፈለገኝ
በተራራው ላይ ቆሞ እየጠበቀኝ ነው
እንዳላረፍድበት ቻው ልሂድ ብያለው
ሸክሞቼ ከብደው እያንገዳገደኝ
እንደምንም ብዬ ልቃረብ ደረስኩኝ
የተሸከምኩት በጣምም ቢያደክመኝ
እየተንፏቀኩ መውጣትን መረጥኩኝ
በተራራው ላይ እየጠበቀኝ ነው
ዛሬማ ግድ ነው ውዴን አገኘዋለው
ቄርሜልዮስ ወጣው እየተንፏቀኩኝ
አገኘውት ውዴን በዛም ላይ አረፍኩኝ
ለካ ሊያራግፍ ነው ቀጠሮ ያስያዘኝ
ገና እሱን ሳየው ሸክሜ ቀለለኝ
ተቀብሎ ጣለው ያስጎበጠኝን
በዘመናት መሀል ያስለቀሰኝን
አምላኬ አሳረፈኝ ሆነልኝ መከከታ
እናም ላመስግነው በልልታ በሆታ
    ✍️ ይዲድያ ተሾመ✍️

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

08 Jan, 12:49


መናፍቅ ነች አሉኝ!!

  በሀጥያቴ ብዛት ከቤትህ ተነፍቄ
   ከጉያህ ከእቅፍህ ከፊትህም ርቄ
    አመት ቢቆጠርም ቢፈጠርም ዘመን
    ቃል ግን ገብቶልኛል እኔን እንደሚያድን::
    በድንግል ማህፀን በሆዷ ውስጥ አድሮ
     ሊሽርልኝ ደዌ ስብራቴን ቀብሮ
   መጣ ወደ በረት ከብቶች በሞሉበት
   ህዝቡን ሁሉ ሊያድን ከሀሳብ ከጭንቀት
    ቢጠመቅም ጥምቀት ቢፈተን ፈተና
      እኔን ለማዳን ሁሉንም ቻለና
   ... ደግሞ ተሰቀለ እስኪከፋው ጥሙ
  ኤሎሄ...ኤሎሄ አለ ቢበዛ ህመሙ ::
   ነፍሱም አረፈች ፀሀይ ደበዘዘች
     ጨረቃ አለቀሰች እንዴት አምላኬን እያለች
     እኔን እና ጌታዬን የጋረደው ቆሞ
     አልቻለም መቆየት ተቀደደ ፈጥኖ
     መሬት ተናወጠች ቀኑም ጨለመ
      በእየሱስ መሞት አማኝ ሁሉ ታመመ
      
    ቢያስገቡት መቃብር በጨርቅም ጠቅልለው
   በድንጋይ ቢያትሙት መዉጫውንም ፈጥነው
   ሞትን ግን ድል ነሳ ይህም አልገደበው

     ያኔ ብቻ አይደለም ዛሬም ቀኝ ተቀምጦ
         እኔን ከሞት ከሲኦል አዉጥቶ
      ዘዉትር ሲተጋልኝ ሆኖልኝ አማላጅ
      በደሙ አስታርቆ አርጎኛል የ እግዜር ልጅ
      ሀጥያቴ ቢሸት ቢገን እንደ ደም ፈልቶ
       ያጠራ የለም ወይ ልክ እንደ ባዘቶ
       

        ታዲያ....ዛሬ በየአደባባዩ
        አማላጄ ጌታ ብል እሱን እዩ
        አፌን አውጥቼ ብሰብክ በመድረክ
      መካከለኛዬ እያልኩ ጉባኤ ባስመልክ
               ...ከሀዲ ናት አሉኝ                                         
       ጌታ ባወደስኩት መናፍቅ ተባልኩኝ
       ምን አጠፋሁ እኔ የቱስ ነው ኩነኔ
        ጌታ መማለዱ መቆሙ ስለኔ
        ይልቅ ንገራቸው መናፍቅ ተብዬ    
ጌታን አስከብሬደግሜ ብሰደብ አይደንቀኝምእኔ
    መሲሁን አስቀድሜ እኔ በወረድኩኝ
ሌሎች ነፍሳት ግን መናፍቅ ነች አሉኝ
     አሁንም እላለሁ አማላጄ ጌታ
   ለኔ የተሰቃየው የሞተው ጎልጎታ
  አደራ...አደራ... ጌታ ሆይ አደራ
  መናፍቅነቱ ስድቡ አስጠልቶኝ
ከቤትህ ሸሽቼ ከጉያህም ርቄ ርዳኝ እንዳልገኝ


      ግጥም እየፃፍኩኝ በቅኔ ሳስቀምጥ
      መዝሙር ተቀብዬ በዜማ ብሰጥ
    ትምህርት አዘጋጅቼ ወጥቼ ባስተማርኩ
     ጌታን የካደች መናፍቅ ነች ተባልኩ!!!


      ለአለም ለመቀር ከጌታ ለመታሰር
      በደሙ በመዳን በቃሉ መፈወስ
      ስሙን እየጠሩ እሱን ብቻ ማውደስ
      ለጌትነቱ ዘላለም በፍቅሩ ለመኖር
      መገኘቱን ናፍቀው ለክብሩ መዘከር
         ናፈኩት ከጀልኩት ያንን ክብር
      ሀሳቡ ሲገለጥ እውነቱ ሲፈካ
     በፈራጁ ሚዛን ፍጡሩ ሲለካ
    ተነጋሪ ተናጋሪ በተግባር ሲለካ
  ያኔ እናወራለን ማን እንደ ነበር መናፍቅ
    ከጌታ መንገድ ቀርቦ የሆነውን ሩቅ

    ይፈርዳል ፈራጁ ሚዛን አያዛባም
    ከሱ አይን ቁጥጥር ስር የወጣ የለም
    
    ብዬ ብዘጋውም የጀመርኩትን ቅኔ
    አስተውለህ አዉራ በል ንቃ ወገኔ


  .....ዘመኑ ተገባዷል ሰከንዳት ቀርተዋል...
ልብህን አዘጋጅእንደተናገረውመሲሁ ይመጣል


        React ❤️


ዳግማዊት ፍቃዱ


Subscribe Our YouTube Channel
https://youtube.com/@Poetscouncil8394?si=obaDUsZ_w6dHxKaL

የገጣሚያን ማኅበር

07 Jan, 10:29


መንፈሳዊ የሆኑ አዳድስ ዜናዎችን ለመስማት ከፈለጉ ወደዝህ ቻኔል ጎራ ይበሉ @Rapture_Tube

መልካም በዓል

የገጣሚያን ማኅበር

07 Jan, 05:58


#በመወለዱ

ወራት ተቀምረው - ከአመት ሲወዳጁ
ወቅቶች ተፈራርቀው -ዘመንን  ሲያበጁ
ያለጊዜ ወደር - ልእልናን የያዘው
ፍጻሜና ጅምር - ገደብ ያልነበረው
ፍጥረቱ ዘንድ ወርዶ - በሰውነት ዋጋ
የኪዳን ደም ኖሮት - ሚቸነከር ስጋ
ግድ ብሎት ታዝዞ - ፍቅሩ የገነነ
በሰው አምሳል ሲገኝ - ባለጊዜ ሆነ !

#አቤንኤዘር_ጥላሁን
ታህሣሥ - 2017 ዓ.ም የተጻፈ


Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

07 Jan, 05:48


ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።🎂🎂🎂

መልካም በዓል ይሁንላችሁ❤️

የገጣሚያን ማኅበር

07 Jan, 04:58


ተወለደ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️እልልልልልልልልልልልልልልል

የገጣሚያን ማኅበር

07 Jan, 03:34


😘 ልኡል ተወለደ😘
የምስራች አሉ መላእክቶች ወርደው
በሜዳ ለነበሩ ለእረኞች ተገልጠው
ካህናቶች እያሉ ስሙን ሚያስተምሩ
ቀድመው የሰሙት ግን እረኞች ነበሩ
ህጻን ተወለደ በቤተልሔም
የነገስታት ንጉስ መድሃኔዓለም
ያለ ወንድ ፈቃድ በድንግል መሀጸን
በመንፈስ አደረ መድሀኒት ሊሆነን
እነሱ የጠበቁት በነገስታት ቤት
እሱ ግን መረጠ የከብቶችን በረት
ዝቅ ብሎ መጣ ሁሉን ድል ሊያረግ
ሊሆንልን ፈቅዶ የመሰዋት በግ
የምስራች ስሙ አዳኝ ተወለደ
የነገስታት ንጉስ ሁሉን የወደደ
ምስጋና ምስጋና አሁንም ምስጋና
የተወለው ህጻን ገናና ነውና
እልልታ እልልታ አሁንም እልልታ
መስዋዕት ሊሆን ተወለደ ጌታ
ጭብጨባ ጭብጨባ ለስሙ ጭብጨባ
ዝቅ ብሎ መጣ ሊያብስልን እንባ
ዝማሬ ዝማሬ ለስሙ ዝማሬ
ሊያስመልጠን መጣ ሊያተርፈን ከአውሬ
ስለዚህ አመስግኑ ዘምሩ በልልታ
ተወልዶልናልና የነገስታት ጌታ
     ✍️✍️ይዲድያ ተሾመ✍️✍️

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

06 Jan, 03:43


የአብ አቻ ሰው ተባለ
መድህን ልሆን ለኮበለለ

ሀና ተክለ
መልካም ቀን❤️❤️

የገጣሚያን ማኅበር

04 Jan, 18:56


🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
የባህር መከፈል፤ መሸሽ ወደ ኋላ
ከጠፈር መዝነቡ፤ ድርጭት የምበላ
የሰው በሬ መሆን: ንጉስ ሳር መጋጡ
በአንደበት ተጩኾ፥ ግንብን መገልበጡ
የእቶኑ እሳት፤ መሆኑ መዝናኛ
አንበሳን ተንተርሶ፤ ዳንኤል ስተኛ
  ...........ግን እንዴት.........
እንዴት ግን ያስብላል፤ ይጭራል ግርምት
ከአዕምሮ ገዝፎ፤ የብሉይ እውነት
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
ንጉስ በሬ ስሆን፤ ከሰውነት ወጥቶ

ገደብ ሳይበጅለት፤ ባህር ስቆም ጸንቶ
ስያንስበት ነው እንጅ፤ ግነት አይበዛበት፤ ድንቅ ብባል ከቶ
😳😳ግን ደግሞ ......
ግን ደግሞ ሌላ አለ፤ ከብሉይ የላቀ
የድንቆቹ ሁሉ ድንቅ፤ ድንቁን ያስደነቀ
አሉባልታ መሰል፤ ደግሞ ግን እውነታ
የብዙሃንን ልብ፤ ዓለምን የረታ

.....እስክ መልሱልኝ...
በአንድት ነጠላ ቃል፤ ምድርን መስርቶ
ያለ አንዳች ምሶሶ፤ ጠፈርን አጽንቶ
መላ ፍጥረታትን፤ በውስጧ ያኖረ፤ በ"ሁን" አበጅቶ
ፈጥሮ ሚያስተዳድር፤ ግሩም የሰውን ልጅ
ከሸክላ አፈር፤ ጠፍጥፎ በእጅ
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
ገደብ ለስልጣኑ፤ ወሰን ለግዛቱ
ሳይኖረው ዳርቻ፤ ክልል ለመንግሥቱ
ከ..እስከ የማይባል፤ ሹመት ተጎናጽፎ፤ ስኖር በክብር
አምላክ የነበረ፤ ከኃጥ ብቆጠር፤ ከአመጸኛው ዘር
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
     እኮ! እኮ እንዴት ይሆናል ..??
ፈጣሪ ብመስል፤ ራሱን ዝቅ አድርጎ፤ ከእጁ ፈጠራ
ከመንበሩ ጎድሎ፤ ከሰው ልክ ልካፈል፤ የዓለምን መከራ
በአንድት እንስት ማህጸን፤ እራሱን ገድቦ
የባሪያን መልክ ልይዝ፤ ውርደቱን አንግቦ
እንደ ሰው ብወለድ፤ አምላክ ሆኖ ስጋ
በዉርጭ በሃሩሩ፤ ክፍሎ ልኖር ዋጋ
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
🤔ኧረ እንዴት? እኮ እንዴት ይሆናል..?
.....ሆነ ግን ለጌታ!!
የሞት ጣሪ ብከበን፤ ስኦል አፉን ከፍቶ
የበደላችን ልክ፤ ጽዋ፤ ከጫፍ ሞልቶ
ተስፋችን ተወስዶ፤ ተቅበዝባዦች ሆነን፤ ስንዋትት በመና
በኃጥአት ቀንበር ስር፤ ተቃኝተን ስንዝል፤ ለሞት ስንቃና
እጅግ ተጎሳቁለን፤ ብያየን ከሰማይ
ፍቅር አስገደደው፤ ማቃችንን ልወስድ፤ እንድወርድ ከላይ
  🤷እሱስ ወድያ ይሁን
እርጉም አፈር መርገጥ፤ ከዙፋን ላይ አንሶ
በሰው መልክ መወለድ፤ አፈር ጭቃ ለብሶ
ከቶ ሳያንስበት፤ እንድያው ለውርደቱ
ደግሞ ያስደመመኝ፤ ለላኛው ድርግቱ
    .... ነገሩ ወድህ ነው
ናፍቆት ሆኖ ሳለ፤ የመስህ ውልደት
አልጋ ተነጥፎለት፤ በክብር ስጠበቅ፤ ከቤተመንግሥት
እንደ በግ በበረት፤ በተናቀ ቦታ
መወለድ ማደሩ፤ እንደ መጻተኛ፤ የፍጥረታት ጌታ
  🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂
ለምን?...ግን ለምን፤ ስያብሰለስል ልቤ
ከአርያም..በረት፤ የውርደቱን ስፋት፤ ጥልቀቱን አስበ
ለካ የኔም ድንኳን፤ መጠለያ ጎጆዬ
እዛው ሰፈር ሆኖ፤ ወትሮ መገኛዬ
ቁልቁል አዘቅት፤ ሸለቆን መውረዱ፤ ለክብሩ ሳይሳሳ
እህ አስተዋልኩኝ፤ ከልኩ ማነሱ፤ ነው እኔን ልያነሳ።
ስመጥሩ ስሆን፤ የልዑል አምላክ ልጅ፤ እንደ ነውረኛ
ያልተገባው ሆኖ፤ በበረት ስወለድ፤ መስሎ መጻተኛ
ከወርቅ ብያገጡለት፤ አልጋቸውን ትቶ፤ በግርግም ስተኛ
ለካ ልያከብረን ነው፤ ራሱን ዝቅ አድርጎ፤ ተዋርዶ ስለ እኛ
  እናም  🤩 የምስራች አለኝ....
የምስራች አለኝ፤ ምን ዘመን ብቆጠር፤ የማይሽረው ዜና
ከቶ ማይደበዝዝ፤ ደምቆ የተጻፈ፤ ዘላለም የፀና
በጉ ብርሃናችን፤ የዓለም ሁሉ ንጉስ፤ የፍጥረታት ደስታ
በዛችን ክርስቶስ፤ ኢየሱስ ተወልዷል፤  የጌቶቹ ጌታ!!!
        ክርስስቶስ ተወልዷል

                    by Erkata S.


Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

04 Jan, 17:52


ኢየሱስ ሊመጣ በደጅ ነው አላቅም እሄን ስናገር ነገር ግን ሁሌም ንቁ ሁኑ
እየሱስ ሊመጣ በደጅ ነው ♥️♥️♥️♥️♥️

የገጣሚያን ማኅበር

04 Jan, 13:42


ተወለደ ❤️

የገጣሚያን ማኅበር

04 Jan, 11:57


እሰይ የምሳራች

ዛሬም ሰበር ዜና
ከሰማይ የመጣዉ
ዘላለም ነዉና

እልል ...በይ ተነሽ ያኔም ቤተልሄም
ብስራትነዉ። ዉልደቱ ዛሬም
ቢሆን ለአለም

እልልልልል......!


እኛም በተራችን
አንዴነዉ ዉልደቱ
ሁሌም ነዉ ደስታችን

የእግዚአብሄር ሙልአት
ለሰዉ የተብራራዉ
እየሱስ ሲወለድ
አምላክ ሰዉ ሲሆነዉ ።


ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

04 Jan, 05:12


https://youtube.com/shorts/Q0-K6Pjr-fc?si=95cFCSgk0uvA9YpD

like and subscribe🙏

የገጣሚያን ማኅበር

02 Jan, 09:39


❝...'Break up' አደረግን ...❞

በጣሙን የሚፋቀሩ 'ፍቅረኛሞች' አሉ። አንዳቸው ለአንዳቸው ያላቸው መሰጠት ድንቅ ነው። መደዋወል፣ መልእክት መጻጻፍ፣ በአካል አብሮ ጥሩ የፍቅር ጊዜ ከማሳለፍ ጀምሮ የሚደንቅ ህብረት አላቸው። በብርቱ ይተሳሰባሉ። ጥቂት እንኳን ነፋስ የማይገባበት የፍቅር አይነት! እጅግ ያስቀናሉ! አቤት ፍቅር ያሰኛል!!! ታዲያ ግን ይህ የፍቅር ጊዜያቸው እንደሞቀ ቢቀጥል እነርሱም የውጪውም አለም የሚመኘው ቢሆንም Break up ማድረግ ይጀምራሉ። Break up እንዳደረጉ ማሰብ ባይፈልጉም ግን ደግሞ Break up አድርገዋል። Break up ማለት 'መለያየት' ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ በአንደበታቸው እንለያይ የማለት ድፍረትን ባያገኙም በተግባራቸው ግን በየጊዜው ጮኸው ይናገራሉ። የትላንትናው የመተሳሰባቸው የመፈቃቀራቸው ውጤት የሆነው፡ መደዋወል፡ መልእክትን በፍጥነት መመላለስ ፡ መገናኘት እየቀነሰ ይመጣል። እነርሱ በአንደበታቸው አውጥተው ባይሉትም ተግባራቸው ግን ይህንኑ ይናገራል። ምንም እንኳን የፍቅር ቃላትን ለመጠቀም ቢሞክሩም አንደበታቸው ላይ ያሳብቅባቸዋል። የትላንትናው ሙቀት ይጠፋል። ታዲያ እነዚህ ተለያይተው የከረሙ ፍቅረኛሞች በአንዳች የመለያየታቸው ውጤት በሆነው ምክንያት በገሃዱ ይለያያሉ። ሁለቱንም side ለምን ተለያያችሁ ተብለው ቢጠየቁ :- ልጁ :- እንዲህ ማግጣብኝ: እንዲህ cheat አድርጋብኝ፡ ስልኬን አታነሳም ይላል። ልጅቷም ጊዜ አይሰጠኝም፡ አይወደኝም፡ cheat አድርጎብኝ በማለት ሁለቱም ምክንያታቸውን ያሰፍራሉ። ነገር ግን ከሁለቱ አንዱም ይሁን፡ ሁለቱ ፥ የተለያዩት አሁን ሳይሆን ትላንት ላይ ነው። አሁናቸው የትላንትናቸው ውጤት ነውና። ታዲያ እኛ አማኞች ከጌታ ጋርም Break up የማድረጋችን ማሳያው ከባባድ(በእኛ ዕይታ) ኃጢአት ማድረጋችን ሳይሆን የየዕለቱን የቃል ጥናት፡ አሰላስሎት እና ጸሎት መጣላችን ነው። ኃጢአቱ የየዕለቱን የቃል ጥናት፡ አሰላስሎት እና ጸሎትን የመተው ውጤት ነው። ወዳጄ ሆይ ከጌታ ጋር ያለህን መለያየት ኃጢአት እስኪነግርህ አትጠብቅ፤ ነገር ግን የየዕለቱን ለቃሉ ያለህን ጊዜ፡ በነገሮች መሃል የሚያጠፋህን አሰላስሎትህን እና ጸሎት ከጣልኽ እነግርሃለሁ፡ ከጌታ ጋር ተለያይተሃል። ስለዚህ ኃጢአት እስኪያጠምድህ አትጠብቅ እነዚህ ምልክቶች ከታዩብህ ቶሎ ጌታን ታረቀው ቅዱስ ቃሉን አንሳ፡ ወደ አሰላስሎትህ ተመለስ እናም ተንበርከክ።

👉 👉 👉“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል...”👈👈👈
— ያዕቆብ 4፥8

Tesfatsion Feleke

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

01 Jan, 06:27


ይገርማል

አምላክ በከብቶች በረት ተወልዶ
ክብሩን ተወ አለምን ወዶ🤔🤔

የገጣሚያን ማኅበር

01 Jan, 05:09


ይገርማል

አምላክ በከብቶች በረት ተወልዶ
ምክንያት ሆነ ለመዳናችን።

የገጣሚያን ማኅበር

31 Dec, 09:40


ወንጌል  እየሱስነዉ።🙏


ሰማይና ምድርን.. .ቢማሩ.. .ቢማሩ
ፍጥረትን አጢነዉ  ቢያስተምሩ
ቢጠና  የሰዉ ዘር   ቀለሙ
ቢተረክለት  ስራ  አለሙ።
   
ግን ይሄ

ወንጌል አደለም።

ታሪክ  ቢናገሩ  ካብርሀም  ጀምረዉ
ቅኔን  ቢዘርፋለት  ከዳዊት ተምረዉ
ትምቢት  ቢናገሩ  ከብሉ  ነቢያት
ህግ  ቢመዙበት  ከሙሴ  ዘፀአት
   
   ይሄም!

    ወንጌል  አይደለም።🙄

ቃሉነዉ።  የእግዚአብሔር  እስትንፋስ
ይሄን  አጠናቆ ካዲስ  ኪዳን ቢደረስ።

በወንጌላት  ትምህርት
ያዉም  የየሱስን
ከሞት  እያስነሳ
ሲሰጥ ብዙ ፈዉስን

ቢያስተምሩም
ወንጌልን  አላሉም።🙄

ደቀ መዛሙርቱ  አላስተዉል ሲሉት
ፈሪሳዊያኑ  እንዲህ እንዲያ  እያሉት
አይሁድ  ሲያደቡ  ዘወትር  ሊገሉት

ቢባልም
ወንጌልን አደለም🙄

መረዳት መልካምነዉ
ማወቅም  ጠንቅ ቆ
የትና እንዴትም  እንደሆነ አዉቆ

ሀዋርያት  ሁሉ የሰሩት  በተርታ
የፃፋትን   መልክት  አዉቆለተፈታ
በግዚያብሄር ቃል  ጉልበት
ሰዉ ከመሆን እዳ  ከሀጢያት ሰንሰለት
ታሞለመታከም  ለመዳነዉ  ከሞት።

    ለታደለሰዉነዉ ጌታ ለወደደዉ
   ቃሉ እየቆረጠ  አስሮ ለገመደዉ

አብግን እንዲወራ
ሁሌ ሚፈልገዉ
ምንም   ማንም  ሳይሆን
ወጌል  እየሱስ ነዉ።

ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ
Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

30 Dec, 09:50


የአለሙ ቤዛ

ቀድሞ በነብያት ፤ለህዝቡ እንደማለ
እቤዣችኋለው ፤አይዟችሁ እንዳለ
እንደተናገረው ፤እንደተስፋ ቃሉ
ቤዛችን ተወልዷል ፤ሃሌሉያ በሉ

እሰይ የምስራች ፤ሆነልን ደስታ
በጨለማ ስኖር ፤ሆነን የሞት ሽታ
በደዌ ተይዘን ፤በኃጢአት በሽታ
በዲያቢሎስ ቀንበር ለምንንገላታ
መዳኒት መቷል ፤መዳኒአለም ጌታ

ያ የስቃይ ዘመን ፤የአመተ ፍዳ
የሰው ልጅ ሲቀጣ ፤በኃጢአቱ እዳ
የመከራው ዘመን ፤አመተ አለም
ልንፀድቅ ስንሞክር ፤በኮርማዎች ደም
የጨለማው አመት ፤አመተ አመት
አይናችን ታውሮ ፤በከንቱ ስንዋትት
ከሰማያት ሆኖ ፤ሁሉን ሲመለከት
አላስችልህ ቢለው ፤ይሄ ሩሩ አባት
የፍዳውን ዘመን ፤ቀይሮ በምህረት
ዛሬስ ሆኖልናል፤ አመተ ምህረት

የሰው ልጅ እንዲሁ ፤በቃ ተወደደ
አምላክ ስጋ ለብሶ ፤ራሱን አዋረደ
ከገናናው ዙፋን ፤ከክብሩ ወረደ
ሰማይ ሊያገባን ፤በረት ተወለደ

የሰማይ ሰራዊት ፤ሆነው በአንድነት
ስለ ታላቅ ስራው ፤ወድቀው ሰገዱለት
አሜን ሃሌሉያ እኛም ደስ ብሎናል
አለምን የሚያድን ፤መስፍን መቶልናል


ቤቴልሄም ኤልያስ

Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

29 Dec, 14:13


የገጣሚያን ማኅበር pinned «የገና ግጥም ያላችሁ ቅዱሳን በውስጥ መስመር አናግሩን @S_o_L_e_N_y ተባረኩ።❤️»

የገጣሚያን ማኅበር

29 Dec, 14:13


📢 አዳኙ ተወለደ 📣

በሞት ሀገር የተሰማ ፣
የምስራች ድንቅ ዜማ ፣
በቤተልሔም በበጎች ግርግም ፣
ተወለደ የሚያድን አለም ፣
በሞት ከተማ ላይ ህይወትን ሊዘራ ፣
በጨለማ ላይ ብርሃኑን ሊያበራ ፣
ተወለደ አዳኙ የሀጥያት ስርየት ፣
የመዳን አሌንታ የህይወት መሰረት ፣
የሞትን መውጊያ ሊሰብረው ፣
በፍቅር ጥሎ ሊያሸንፈው ፣
ቀኑን በመናፈቅ በተስፋ ለተጠባበቁት ፣
ተወለደ አዳኙ በቃሉ መሰረት ፣
ላዘኑት ደስታን ሊሰጥ ለሞቱት ሂወትን ፣
መጣ ንጉስ አዳኝ የሆነው ፣
መልአክት ዘመሩ በአርያም ሆነው ፣
አንተ ቅዱስ ሀያል ንጉስ ክበር ብለው ፣
በላይ በሰማያት ቅኔ የፈሰሰበት ፣
አዳኙ ተወልዶ ምስራች ተነጋግሮበት ፣
ፍጥረት ደስ አለው ሰምቶ መልካም ዜና ፣
ምድሪቷ በራች ፀዳልም ሞላባት ፣
ብርሃኗ ተወለደ በዳዊት ከተማ ፣
ንጉስ ተወለደ በዳዊት ከተማ ፣
ፍጥረት ደስ ይበለው አለም ሁሉ ይስማ ፣
ቅኔ አምጡለት ለዚህ ንጉስ ፣
ሰላምን ለሚያፈስ ፣
ምስጋና አምጡለት ፣
ለዚህ ንጉስ ለሰላም አለቃ ፣
ለሚያደርገው ሞት እንዲያበቃ ፣
ሀሌሉያ ሀሌሉያ... እኛን ለወደደ ፣
ሀሌሉያ ሀሌሉያ...አዳኙ ተወለደ።


@Betsitaye

➡️Join and share 👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️
  🌿 @yegetamianmahiber 🌿
  🌿 @yegetamianmahiber 🌿
  🌿 @yegetamianmahiber🌿
✿❖✿❖✿❖✿❖✿❖✿❖✿
           🔺🔺🔺🔺
           ✿፧፨✿፧፨✿
          |፧ይ🀄️🀄️ሉን|፧
✿፧፨✿፧፨✿፧፨✿፧፨✿፧፨✿፧፨✿፧

የገጣሚያን ማኅበር

29 Dec, 14:10


(ግጥም ስለ ጌታ ልደት)

የዓለሙ መድሀኒት የዓለሙ ጌታ
አዳምን ሊያድነው ከእስራት ሊፈታ
ከባርነት ዓለም ከጨለማው ቦታ
በመስቀል ተሰቅሎ ሞትን በሞቱ ሊረታ
ለአዳም የገባውን ቃልኪዳን ሊያፀና
የሰውን ልጅ ሊያድን ከሲኦል ፈተና
ተወለደ አምላክ እኛን ወደደና

እራሱን ዝቅ አርጎ ተወለደ በግርግም
ሀጥያትን ደምስሶ ለሰው ሊሰጥ ሰላም
አምላክ ወልደ አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ
አደረ በማርያም የሰውን ልጅ ወዶ
ሀብታም ሆኖ ሳለ እራሱን ዝቅ አርጎ
እኛ እንድናገኝ ድነትን ጌታችን ፈልጎ
በከብቶቹ ግርግም ተወለደ አምላክ
ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላምን ሊሰብክ
ጌታችን ሲወለድ በከብቶቹ በረት
በአንድነት ዘመሩ ሰውና መላዕክት
ምስጋና ለእግዚአብሔር
በሰማይ ደግሞ በምድር
እያሉ ዘመሩ ሰውና መላዕክት
ነገስታት መጡና ወድቀው ሰገዱለት
አምላክ ስለሆነ እጅ መንሻ ሰጡት
ጌታችን ክርስቶስ በከብቶቹ ግርግም ስለተወለደ
ምስጋናን አቅርቡ እኛን ለወደደ።

 

ዮም ፍስሀ

📥Group👇
  🌿 @yegetamianmahiber 🌿
📥 Channel👇
🌿 @Ye_Getamian_Mahiber 🌿

የገጣሚያን ማኅበር

28 Dec, 19:06


ራእይ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
²¹ እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።

የገጣሚያን ማኅበር

07 Dec, 16:04


የገራፊው ማስታወሻ!

ፈቅዶ ማነስ ነው ፍቅር!

በክፉ ዕለት፤ በቀን ግማሽ አጋጣሚ፤
የአዳም ሐይል አሸንፎ፤ ሲበረታ ተቃዋሚ፤
ባለስልጣን በሚባሉት ፤ግራ ቀዳጅ ቀኝ ሰፊ፤
እኔም በዳይ ቀጪ ሆኜ፤አደረጉኝ ሰው ገራፊ።
፧፨፧፦
ሰጡኝ ሙያ አወዳድረው በቀጣሪ፤
አርገው ሾመው እንድገርፈው
እኔን በዳይ አንዱን ማሃሪ።
፧፨፧፦
እኔ እንደሆን ሙየዬ ነው፤
ሰውን ማስጮ በሰው ጅራፍ።
ቆይ ግን ይኽ ሰው
ምን ቢያውቅ ነው ሚገረፈው በሰው ምዕራፍ ??
ብሎ ማሠብ አልችልበት ማሰላሰል፤
ግረፍ ብለው የሰጡኝን በግርፋት ማቆሳሰል፤
እኔ እንደሆን አይሰለቸኝ፤
ስስ ጀርባውን አመቻቸው ለመግረፍም እንዲመቸኝ፤
አጣበቁት በደረቱ ወደ ግንዱ ሳብ አረኩት፤
እያቆሰልኩ የምገለው ለእኔ እንደሆነ መች አወኩት።

መች ተረዳው መቼ ገባኝ
ባሪያ መልኩ መች አባባኝ
መች አየሁት ሲያዜሙለት
እነ ገብርኤል ሲሰግዱለት
የዮርዳኖስ ጉድ ሲገለጥ
በአለት ውሃ ጥም ሲቆረጥ
በእስትንፋሱ ቀኔን ሲስል
መቼ ገባኝ እኔነኝ ሲል
መች ተረዳሁ  እኔ ጅሉ
በጭካኔ ምበድለው ቀኑን ሙሉ
ባላውቅ አይደል ስላልገባኝ ፍቅር ቅሉ?

Qባላውቅ አይደል በፍቅሩ ቀን የሆንኩበት ርጉም ክፉ፤
ሚስማር ስለቅም የዋልኩኝ እንዲበሳ ስስ መዳፉ፤
ባላውቅ አይደል
እንደሁ እስቲ
ምናለበት ቅዱስ መፅሐፍ ትንሽ ብማር
ለነገሩ ምን ያደርጋ፤ ለብረት ቤት የእንጨት ሚስማር
ብዬ ኖሬ ባለመማር ፤እንደ ይሁዳ ጅል ከምሆን
ሞቶ ሚያድን ልጅ ለማየት፤ በተጋሁስ እንደ ስምሆን

ከአዳም እንኳ በሰማሁት  ጥረ ግረ ብላ እንዳለኝ፤
በጥረትም እንዳላመልጥ  ያለመማር ቀኔ ጣለኝ።
ይኸው አሁን በዚህ ዘመን መጨረሻ፤
የእርሱን መንግስት ለሚሻ፤
ተምሮ አምኖ ለሚቀበል የፅድቅ ጥሩር ሲሰፋ፤
የኔ ሚዛን ተገልብጦ የስምሆ ሚዛን ደፋ።
ፀፀት መልካም!
ፀፀት ደጉ! ድንጋይ መሬቴን አረሰው፤
ለኔ እንደሆነ እያሳየኝ ንፁህ ደሙን ያፈሰሰው፤
አፈረሰው!!
ድንጋይ ልቤን ያልነበረ እስኪመስል፤
በሩሩህ ፍቅሩ ትውስታ መላ አካሌ እስኪቆስል፤
አስታወሰኝ ያን ሰመመን
አስታወሰኝ የኔን ዘመን
ትዝ ይለኛል ያ ጅራፌ
ትዝ ይለኛል ረጋሚ አፌ
እንደ ቀላል እንደ ዘበት
በደም በወዛ ገፅታው፤ ምራቄን ስደርብበት
ክብሩን ሳቀል ተስገብግቤ
ሊገድለው ሲጨክን ልቤ
አንዴ ከቆጥ አንዴ ከባጥ
ስሙን ላጠፋ ስሯሯጥ
አየሁት ራሴን ታዘብኩት ራሴን አገኘሁ ቀልዬ
ራሴን ስል እሱን ጥዬ ተገኘሁ ቀልዬ
አሁን ገባኝ ፍቅር ልኩ
ሚያድግም ቢሆን የማያድግ ሰው አትንኩ
ሰው ይሁን ለሰው ጥቅሙ
መውደድ ነው ፍቅር ትርጉሙ
ለሌላው መውደቅ አትልፉ
የገፉትን ሰው እቀፉ
ቀን ሲከፋ  ሲጠቁርበት
ቦታ ጠፍቶት ሚሄድበት
ሚገባበት የሚያድርበት
ባጣ ሰው ላይ
አትፍረዱ ቤት አለሁ mንግስተ ሰማይ

ደግሞም..
ለጎሳ ነፃነት በአደባባይ ሰው ሲበደል
ውሸት በሉ ሰው ለፍቅር ሰውን ሲገል
ውሸት በሉ!
አይቻለው እኔ ገዳይ የፍቅርን ጫፍ
ለገረፉት ለሰቀሉት ሲማልድ አፍ
አይቻለሁ እኔ ገዳይ! እኔ ጠላት! እኔ አጥፊ!
ሎሌውን ለማዳን ብሎ ንጉስ ሲመታ በጥፊ
አይቻለሁ እኔ ጠላት!

አሁን ገባኝ! ምን እንደሆነ ያደረሰው
ለሰው መስቀል እስኪሸከም
ጉልበት ነው ለካ ለመቆም
እያወቁ ለሰው መድከም።
ለካስ
ከልብ እንድትገባ እውነት ሳትዛባ
ጉልበት ነው ለፍቅር ።፤መሆን ጉልበት አልባ።
፨፧።፦፧፦፨፨፨፧፦፥፥፧፨፧፦፥፤፤፤፥፦፧፨፨፨፨፨፨፨፨

ⒹⒹ➫➫የሱመልስ🔥

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

06 Dec, 19:01


ሌላው ሀሳብ ለእሷ ብሎ ወይም ለእርሱ ብላ ጌታን መቀበል  ትክክል አይደለም ምክንያቱም ድንገት ቢጣሉ እንኳን ጌታን ይተዋል ለእሷ ብሎ ስለተቀበለ የሚል ሀሳብም አለ ነገር ግን ጳውሎስ
“ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርስዋ ጋር ሊቀመጥ ቢስማማ፥ አትተወው።”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 7፥13

እንዲህ በማለት መሆን ያለበትን ተናግሯል።

በሀገራችን አባባል ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም እንዲሉ.... ምናልባት ቢለያዩ ያንን ጌታ ሊተው ስለሚችል አንድ ለይ መሆን የለባቸውም ማለት ተገቢ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

የገጣሚያን ማኅበር

06 Dec, 18:49


2ኛ ቆሮ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?

🙏 ነገር ግን እኛ እራሳችን ጨለማ ነበርን እንዴት እግዚአብሔር ከኛ ጋር ህብረትን ለማድረግ መጣ? እንዴትስ ወደደን?

“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”
  — ሮሜ 3፥23

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
  — ዮሐንስ 3፥16

የገጣሚያን ማኅበር

06 Dec, 18:41


አብዛኞቻችሁ የመለሳችሁት መልስ ትክክል አይደለም የሚል ነው ።🙏
መልሳችሁን ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር ብታገናኙት የተሻለ ነው👍🙏🙏

የገጣሚያን ማኅበር

06 Dec, 18:11


ጥያቄውን ጀምረናል ፆታዊ ፍቅር ተፈጥሯዊ እንደሆነ እናውቃለን  አንድ ክርስትያን በጌታ ካልሆነ ሰው ጋር እንዴት ፍቅር ይጀምራል?

የገጣሚያን ማኅበር

06 Dec, 17:02


ሰላም እንዴት አመሻችሁ 👋👋
ዛሬ ምሽት 3:00 ለይ የመወያያ ጥያቄ ይኖረናል ሁላችሁም ተሳተፉ በጌታ ፍቅር🙏🙏


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

05 Dec, 13:51


📔 የእረፍት ሕይወት

📍 ክርስትና የሚጀምረው ከእረፍት ነው ።
📍 በክርስቶስ ተሰርቶ ያለቀውን የፅድቅ ህይወት ዕረፍት እያደረግን ነው የምንንኖረው።

📖ክርስቲያኖች ልታነቡት የሚገባ መፅሀፍ ነው ጋበዝኳችሁ።

@worlds_light
@worlds_light

የገጣሚያን ማኅበር

05 Dec, 04:48


መንፈስ ቅዱስ 🔥

ስዝል  .. ስተክዝ
ሳዝን  .. ስቆዝም
ይመሻል .. ይነጋል
ሳልሰራ .. ምንም😒

ስንፍናዬ በዛ አቤት!
የእንቅልፌ ጊዜ
ታዲያ ማን አነቃኝ?
ከዚያ ድንዛዜ🤔


እራሴን ሳገኘው
እያልኩኝ..
"ሄሎሂም...ሄሎሂም
ኃይል የሌለውን ሰው
ምነኛ እረዳኸው😭"


በደስታ እንባ አይኖቼ
ታጥበዋል
እግሮቼም ዝለዋል🧎‍♀‍➡️


ድንገት ግን ስነሳ ያ
ጉልበት በረታ
የጨለማው ስልጣን
ከላዬ ተመታ🤗


ከፈጣኖች ሰፈር ከብልዎች
ጋራ
ሆኜ  ተገኘው  ማዕድን
ስጋራ😄


አውቀዋለሁ በእኔ ኃይል
ሳይሆን በብርታቴ
መንፈስ ቅዱስ አንተ
ነህ ፍጥነቴ🔥🔥

“ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”
    የሐዋርያት ሥራ 1፥8

      Reyni Tamiru

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

03 Dec, 18:52


........እጠብቅሀለሁ
መች ተማምነህ በእኔ ችሎታ
ሁሉን ስታሳምር የፍጥረቱ ጌታ
በራስህ ስላለህ ብቸኛ ችሎት
በሰው አትመካ ባለው ጉልበት
ይሄንን አውቄ ራሴን ሰጥቻለሁ
መጣለሁ ያልከኝ ቦታ እጠብቅሀለሁ
ቃልህን አትበላ ሀሩሩ ጠንቶብህ
ርዕሰ አትቀይርም መንገዱ ርቆብህ
እመጣለሁ ስትል ስትሄድ አሸንፈህ
መሆንን አልረሳሁም ከሞት ተነስተህ
ታዲያ ምን ያግድህ ይከለክል ብዬ
ለምን እፈራለሁ ስጋት አስከትዬ
በወጀቡ መሀል መንገድ ታበጅ የለህ ??
በደረቅ በረሀ ዉሃም ታፈልቃለህ
መካኒቱም ሆነች ወልዳ ሰባት መንታ
የትውልድ እናት አድርገሀል ጌታ
በደረቁ ምድር ኖኅ ከሰራ መርከብ
ታምኖ ከታዘዘ በዉሃ መድር አንድትከብ
ከሙት ስጋ መሀል ሳራም ወልዳለች
የሌለን ለማኖር አያቅትህ አንዳች
በዚህ ሁሉ አየሁ ሁሉን ቻይነትህን
ሁኔታው ያወራል ኤልሻዳይ መሆንህን
እኔም አምኛለሁ ትመጣልኛለህ
እጠብቅሀለሁ በቃልህ ታማኝ ነህ

በ ጌታሁን አናሞ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

03 Dec, 05:04


Aridrop መስራት ለምትፈልጉ በሙሉ ይህ Finch Coin የተሰኘው Aridrop እንዳያመልጣችሁ፡፡

ቶሎ ስሩበት ብዙ ገንዘብ መስራት ትችላላችሁ፡፡

5 ቀን ብቻ እስከ 2000 ETB ብር ወደ Wallet ገብቶልኛል፡፡ጠቃሚ የሆነ መረጃ ነው ሁላችሁም ተጠቀሙ።ምናልባት ብር የቸገራችሁ ወገኖች በትንሹ ታተርፉበታላችሁ🤝


ለመጀመር👇👇👇👇
https://t.me/FinchAirdropBot?start=85287
https://t.me/FinchAirdropBot?start=85287

የገጣሚያን ማኅበር

02 Dec, 09:59


የማይሰለች ዜና
ወርዶ ከዙፋኑ፤ ብውል፤ ንጉስ ተራ ስፍራ
በተናቁት መንደር፤ ከድሀ አደጎች ጋራ
እህላቸውን በልቶ፤ ቀምሶ መጠጣቸውን፤ ብያድር ከአልጋቸው
ምንኛ ውርደት ነው? ድሪቶውን ልብሶ፤ ካባ ብያለብሳቸው
        ታድያ እንዴት ይሆናል??
በአንድት ነጠላ ቃል፤ ምድርን መስርቶ
ያለ አንዳች ምሶሶ፤ ጠፈርን አጽንቶ
መላ ፍጥረታትን፤ በውስጧ ያኖረ፤ በ"ሁን" አበጅቶ
ፈጥሮ ሚያስተዳድር፤ ግሩም የሰውን ልጅ
ከሸክላ ከአፈር፤ ጠፍጥፎ በእጅ።
መንግስቱ ያለገደብ፤ ስልጣኑ ማይሻር
አልፋና ኦመጋ፤ ከዘላለም እስከ፤ ዘላለም ነዋር
ከ..እስከ የማይባል፤ ሹመት ተጎናጽፎ፤ ስኖር በክብር
አምላክ የነበረ፤ ከኃጥ ብቆጠር፤ ከአመጸኛው ዘር
      እኮ  እንዴት ይሆናል
ፈጣሪ ብመስል፤ ራሱን ዝቅ አድርጎ፤ ከእጁ ፈጠራ
ከመንበሩ ጎድሎ፤ ከሰው ልክ ልካፈል፤ የዓለምን መከራ
በአንድት እንስት ማህጸን፤ እራሱን ገድቦ
አጥንት ደም ልሸከም፤ የባሪያን መልክ ልይዝ፤ ውርደቱን አንግቦ
ሰው ሆኖ ብገለጥ፤ አምላክ ለብሶ ስጋ
ልራብ ልጠማ፤ በውርጭ በሀሩሩ፤ ክፍሎ ልኖር ዋጋ
  እኮ! እንዴት ይሆናል..?....... ሆነ ግን ለጌታ!!
የሞት ጣሪ ብከበን፤ ስኦል አፉን ከፍቶ
የበደላችን ልክ፤ ጽዋ፤ ከጫፍ ሞልቶ
ተስፋችን ተወስዶ፤ ተቅበዝባዦች ሆነን፤ ስንዋትት በመና
በኃጥአት ቀንበር ስር፤ ተቃኝተን ስንዝል፤ ለሞት ስንቃና
እጅግ ተጎሳቁለን፤ ብያየን ከሰማይ
ፍቅር አስገደደው፤ ማቃችንን ልወስድ፤ እንድወርድ ከላይ
      እሱስ ወድያ ይሁን
እርጉም አፈር መርገጥ፤ ከዙፋን ላይ አንሶ
በሰው መልክ መወለድ፤ ነውር ስጋ ለብሶ
ከቶ ሳያንስበት፤ እንድያው ለውርደቱ
ደግሞ ያስደመመኝ፤ ለላኛው ድርግቱ
      ነገሩ ወድህ ነው
ናፍቆት ሆኖ ሳለ፤ የመስህ ውልደት
አልጋ ተነጥፎለት፤ በክብር ስጠበቅ፤ ከቤተመንግሥት
እንደ በግ በበረት፤ በተናቀ ቦታ
መወለድ ማደሩ፤ እንደ መጻተኛ፤ የፍጥረታት ጌታ
   ለምን...???
ለምን?...ግን ለምን እያልኩኝ፤ ስማከር ከልቤ
ከአርያም..በረት፤ የውርደቱን ስፋት፤ ጥልቀቱን አስበ
ለካ የኔም ድንኳን፤ የተጠለልኩበት፤ መኖርያ ጎጆዬ
እዛው ሰፈር ሆኖ፤ ወትሮ መገኛዬ
ቁልቁል አዘቅት፤ ሸለቆን መውረዱ፤ ለክብሩ ሳይሳሳ
ገባኝ ተረዳሁኝ፤ ከልኩ ማነሱ፤ ነው እኔን ልያነሳ።
ስመጥሩ ስሆን፤ የልዑል አምላክ ልጅ፤ እንደ ነውረኛ
ያልተገባው ሆኖ፤ በበረት ስወለድ፤ መስሎ መጻተኛ
ከወርቅ ብያገጡለት፤ አልጋቸውን ትቶ፤ በግርግም ስተኛ
ለካ ልያከብረን ነው፤ ራሱን ዝቅ አድርጎ፤ ተዋርዶ ስለ እኛ
   የምስራች አለኝ......
የምስራች አለኝ፤ ምን ዘመን ብቆጠር፤ የማይሰለች ዜና
በፍቅር መሰረት፤ በግብር ታንጾ፤ ላይሻር የፀና
በጉ ብርሃናችን፤ የዓለም ሁሉ ንጉስ፤ የፍጥረታት ደስታ
በዛችን ክርስቶስ፤ ኢየሱስ ተወልዷል፤ የዘላለም ጌታ!!!
        ክርስስቶስ ተወልዷል

                               Written by Erkata S.
Like share react❤️😘😍
Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

01 Dec, 17:26


ጌታዬን ጠርቼው መች ዘገየ ተራራዬን ናደው አይኔ እያየ የዘላለም አምላክ መኖሪያዬ ባንተ ጥላ ስር ነው ማረፊያዬ የሚመካ  በእግዚአብሔር ይመካ የሚመካ በአምላኬ 🔥🔥🙆‍♀🙆‍♀🙆‍♀🙆‍♀ይመካ



share😍 share 🥰share


https://t.me/+TfsXHRGblWBkYWQ0

የገጣሚያን ማኅበር

01 Dec, 06:50


ልቤን ስበርልኝ

****

እግሬ እርቆ እንዳይሄድ፣ጥሎ እንዳይጠፋ
መሸነፍ አቅቶት፣በሀጥያቱ ፀንቶ አንተ እንዳይስከፋ
ውጭው በመናፈቅ፣ወጥቶ እንዳይጎዳ
ፍቅርህ እንዳጣጥም፣እንዳበዛ፣ጓዳ
ልቤን ስበርልኝ

ልቤን ስበርልኝ

ሁሉም ጥሎኝ ይሂድ፣እያለው እግርህ ስር
ሰአታቶች ይንጎዱ፣ቀንም ቀን ይጨምር
መምህሬ ልምሰል፣መልክህ ይሁን መልኬ
ብልጭልጭ ያምልጠኝ፣ከእግርህ ተንበርክኬ

ልቤን ስበርልኝ

ፍቅርህ በውል ይግባኝ፣ምላሽ ይኑረኝ ላንተ
ሊለምድህ አይሻም፣ካንተ እየሰነበተ
ልመስክር ልናገር ትውልድ ድኖ እንዲቀር
እኔ አጥፋኝና፣ልጅህ በእኔ ይክበር
በሚቀረኝ ዘመን፣ኢየሱስ ይታይ ጎልቶ
ፍጥረት አሜን ብሏል፣ይሄ ፀሎት ሰምቶ

ኤርሚያስ ክፍሌ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

30 Nov, 06:14


የእየሩሳሌም_ምጥና_መከራ  !
#የጎግ_ማጎግ ጦርነት#

🇷🇺 🇱🇾 🇮🇷 🇵🇫 🇵🇸 🇱🇧 🇾🇪 🇮🇶 🇸🇾 🇪🇹 🇾🇪 🇬🇪
ፓስተር አስፋው በቀለ ከሰባት አመታት በፊት ባስተማሩት ትምህርት ላይ እየሩሳሌም ያልኖረችበት ምጥ እና መከራ የለም ሲሉ አስተምረው ነበር።ታድያ በዚያን ወቅት መፅህፍ ቅዱሳቸውን ገልጠው ለመግቢያ የ ራዕይን መፅሃፍ ምዕራፍ ሰባትና አስራ አራትን እንደ መግቢያ ተጠቅመው
እየሩሳሌም ያልኖረችበት ምጥ የለም ። አራት መቶ ሰላሳ ዓመታት በግብፅ ምጥ ውስጥ ኖራለች። በባቢሎን ሳባ አመታት ምጥ ውስጥ ኖራለች። በአሦራውያን ተገዝታ እየሩሳሌም ምጥ ውስጥ ኖራለች። በቱርክ ኢምፖየር ተገዝታ እየሩሳሌም ምጥ ውስጥ ኖራለች። በእንግሊዝ ተገዝታ እየሩሳሌም ምጥ ውስጥ ኖራለች።አሁንም እየሩሳሌም ጭንቅ ውስጥ ናት ያሉት መጋቢው አስፋው በቀለ፥በቀጣይ ስለሚሆነውም ነገር ፤ስለ እየሩሳሌም እጣ ፈንታ እና የጎግ ማጎግ ጦርነት እንዲሁም የአርማጌዶን ጦርነትን ከመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ሰላሳ ስምንት እና ሰላሳ ዘጠኝን አንብበው ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል ።
በቀጣይ እሳቸው ያቀረቡትን ማብራሪያ ከነ ሙሉ መረጃው አጠናቅረን የምናቀርብ ይሆናል። እስከዚያው

SHARE በማድረግ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንወጣ !
      Join our Telegram
#የጎግ_ማጎግ_ሰልፍ
#የእየሩሳሌም_መከበብ
SHARE/@RAPTURE_TUBE
SHARE/@RAPTURE_FAMILY

የገጣሚያን ማኅበር

29 Nov, 16:53


💕ጓደኝነት

ጓደኝነት ማለት የዕድሜ ጉዳይ አይደለም የገንዘብ ወይም አብረን ስለተማርን እኩያሞች ስለሆንን አይደለም ጓደኝነት ማለት በዓንድ ሀሳብ መስማማት ነው።

መጋቢ : ዮናታን አክሊሉ

@worlds_light
@worlds_light

የገጣሚያን ማኅበር

29 Nov, 10:53


ሠላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን😊🙌
ቃል የለለው ቃል የተሰኘ የግጥም መድብል በህዳር ስምንት ተመርቆ በገበያ ላይ ውሏል።በተጨማሪ ነገ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በGMM TV WORLD WIDE  INTERVIEW ከፕሮግራም አዘጋጅ ታምራት ሞቲ ጋር  በቀጥታ መከታተል እንደሚትችሉ በታላቅ ደስታ እንገልፃለን። በመቀጠልም በድጋሚ እሁድ 6:00 እና ሰኞ 11:00 ይተላለፋል።

    መፅሐፉን ለመግዛት የሚትፈልጉ
+251 90 570 6915 መደወል ትችላላችሁ።

የገጣሚያን ማኅበር

29 Nov, 08:58


ስሙት እና ፍሰሱ😭😭😭
https://t.me/+TfsXHRGblWBkYWQ0 share share🚨💥

የገጣሚያን ማኅበር

29 Nov, 05:05


የሚናገር አውልት
አፅም አዝሎ ከስሩ
አንዴ ሰው የነበር
ባቀፈው መፈክር ይሞግተኝ ጀመር።
አቶ እገሌ በ 1940 ተወለደ
አደገ፣ አገባ፣ ወለደ፣ ከበደ
2011 ሞተ።
ይኸው ነው ሰው አፈር
ሰቅል አይመዝንም ዘመኑ ቢሰፈር።
ሰባ ነው ሰማንያ የዕድሜ ጥግ ልኩ
በተሰጣቹ ቀን ታሪክን ፈብርኩ።

ታሪክ አትሰራም ወይ
መስማት አይበቃም ወይ
የተሰራ ጀብዱ የተሰራ ገድል
የት ነው ያንተስ ዕድል?
የት ነው ያንተስ ዝና ?
ምን ሰራክ ገናና?
ለትውልድ የሚቀር?
ምን ታሪክ አበጀ በአመት የሚዘከር?
ቆመ ከምትውል ልክ እንደ ጅብራ
በል ሂድ ታሪክ ስራ
እየሱስን ንገር ስለወንጌል አውራ።
አለኝ!

የሱመልስ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

28 Nov, 17:56


አላሰችልህ ስለው

ከተከታዮቹ ራቅ አለ ተለየ
በፍርሃት ስጣጣር አፅንቶ ፀለየ።

የቂጣው በዓል ምሽት የትካዜ ሆኖ
በሳቅ ቀን የሳቅ ምንጭ በሀዘን ተከድኖ🙇‍♂
አስቆሮቱ ይሁዳም ልቡን አደንድኖ
ሰው ሆኖ እያለ በሰው እንዲህ ጨክኖ
አብሮት የበላ በማዕድ ተቀምጦ
አሳልፎ ሰጠው በገንዘብ ለውጦ

አላስችልህ ስለው የኔ የኛ ጉዳይ
እንደሚታረድ በግ ዝም ብሎ ኤልሻዳይ
በከፈለው እንጂ ተወዳጅ መሆኔ
እንደኔማ ቢሆን ክህደት ነበር የኔ።

የህዝብ ሽማግሌዎች የካህናት አለቆች
እያዩ እውሮች አዋቂዎች ነን ባዮች
በሊቀ ካህኑ ቀያፋ ግቢ ውስጥ
አንድ ላይ ታድሞ ተማክሮ ልይዙት
ሰይፍና ጎመድን ይዞ ደረሱበት
መቱት ደበደቡት ደግሞም ዘበቱበት
ሳቁ ቀለዱበት ሁሉም አሾፉበት
አሉት እንዳሻቸው ተጠቃቀሱበት።

እርሱ ግን በመሀል በዚህ ድካም ሁሉ
እያለው ቁጣው እያለው አመሉ
ወንጌል መስበኩን ወንጀል ስያስመስሉ
በእውነት መቃብር ላይ ወጥተው ስዘሉ

አላስችልህ ስለው የኔ የኛ ጉዳይ
እንደሚታረድ በግ ዝም ብሎ ኤልሻዳይ
በከፈለው እንጂ ዛሬ ነፃ መሆኔ
እንደኔማ ብሆን ክሱ ነበር የኔ።

ከአስራ ሁለት ጭፍራ የሚበልጥ እያለው
እንዳሻቸው ስያደርጉት ለኔ ነው ዝም ያለው።

አብሮት የነበሩ ለራሳቸው ፈሩ
ሁሉም ጥለውት ጠፉ ብቻውን አስቀሩ።

እርሱ ግን በጅራፍ በተራ ሲገርፉት
ሲገፉት ስያጋፉት ስያክለፈልፉት
ፊቱንም ሸፍነው በጥፊ ሲመቱት
አሁን ማን መቶሀል እስኪ ንገረን ስሉት

አላስችልህ ስለው የኔ የኛ ጉዳይ
እንደሚታረድ በግ ዝም ብሎ ኤልሻዳይ
በከፈለው እንጂ ዛሬ በእረፍት መሆኔ
እንደኔማ ብሆን ድካም ነበር የኔ።

በውሸት ሲከሱት በሸንጎ ሲያቆሙት
ሲመረምሩትም ደግሞ ሲጠይቁት
ንቀው ሲተፉበት ነቅፈው ሲሰድቡት
ሁሉም እንደሌባ በመጥፎ አይን ሲያዩት
አንዴ በእየሩሳሌም አንዴ በገሊላ
ጵላጦስ ሄሮድስ ስያደርጉት ጎስቋላ
አንዱ ሲያፌዝበት ሲስቅበት ሌላ
ፍርዱ ተወስዶበት በሁሉም ሲጠላ

አላስችልህ ስለው የኔ የኛ ጉዳይ
እንደሚታረድ በግ ዝም ብሎ ኤልሻዳይ
በከፈለው እንጂ ዛሬ ነፃ መሆኔ
እንደኔማ ብሆን ፍርዱ ነበር የኔ።

ገዢዎች ወሰኑበት ህዝቡም ጨከኑበት
ይሰቀል እያሉ ጬኼት አበዙበት🙅‍♂🙅🙅‍♀
ታዋቂ ገዳይ እንኳን ሲፈታ ወንበዴ
የዘላለም ቅዱስ ለሞት ተገደደ።

ልብሱን ሁሉ ገፍፎ ቀይ ልብስ አልብሶ
በእሾኽ አክሊል ራሱን ነቃቅሶ
ሲመቱት ደጋግሞ ሲገርፉት መላልሶ
ባምላክ ሲዳፈሩ ትዕቢትን ተላብሶ
የፌዝ ስያሞግሱት በክፋት ተክነው
ሁሉ አንድ ሆነውበት ስያዋርዱት ጨክነው
ያለፉትን ጌታ ነገስታት👌 አምልከው
'ሰላም ላንተ ይሁን' ሲሉት ተንበርክከው

አላስችልህ ስለው የኔ የኛ ጉዳይ
እንደሚታረድ በግ ዝም ብሎ ኤልሻዳይ
በከፈለው እንጂ ክቡር ሰው መሆኔ
እንደኔማ ቢሆን ስላቅ ነበር የኔ።

ለኔ የሚገባኝን መስቀል ተሸከመ
ቁስሌን ልፈውስ ህመሜን ታመመ
ወዝ ደም ግባት አጣ እንደተረገመ
ፀሀይ ኋላ ዞረች ቀን ለብርሃን ጨለመ።
🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑

እንደ ርኩሳን ወግ በመስቀል ሲሰቅሉት
ያለልብስ ራቁቱን ስያንጠለጥሉት
በጦርም ሲሰወጉት ሆምጣጤውን ስያጠጡት
እጁንና እግሩን በእንጨት ሲመቱት
ሌሎችም ራሳቸውን እየነቀነቁ
'ከመስቀል አይወርድም?' ብለው ሲሳለቁ

አላስችልህ ስለው የኔ የኛ ጉዳይ
እንደሚታረድ በግ ዝም ብሎ ኤልሻዳይ
በከፈለው እንጂ በቤቱ መሆኔ
እንደኔማ ብሆን ስቅለት  ነበር የኔ።

ባህርን የሚያዝዝ አፍ ስለኔ ተዘጋ
አለምን የሰራ እጁ በሚስማር ተወጋ
የምድር የሰማይ ጌታ በሰው ልጅ ተናቀ
ቀና ደፋ አለ ተነሳ ወደቀ
ለፋ ተሰቃየ ከፋው ተጨነቀ
ድውያችንን አዝሎ በግርፊያ ደቀቀ።

እጆቹን መሠረ ያ ትልቅ ምስማሩ
ሀሞቱን ቀደደ በጎን ገብቶ ጦሩ
ጀርባውን ለጠለጠ የሽቦ ጅራፉ
የውቅያኖስ ሰሪ በጥም ደርቋል አፉ
እንደሰራ ክፉ እንዲያ መጠፍጠፉ
ለሌላ አይደለም እኔ ሆንኩኝ ትርፉ።

ፀሀይ ብርድ ፈጀበት ከሰው ይልቅ ቀለለ
ገመቱት ተመኑት ረከሰ ዝቅ አለ
ወገኖቹ ከዱት በሁሉ ተገለለ
አላስችልህ ስለው በስቃይ ሁሉ ቻለ።

'ኤሎሂ ኤሎሂ ለማ ሰባቅታኒ'
ሲል 'እየጠራ ነው' ሲሉ 'ኤልያስን'
'ስለምን ተውከኝ?' ብሎ አባቱን
በታላቅ ድምጽ ጮኾ ተለያት ነፍሱን።

አልፋው ያ ኦሜጋው ያለ የነበረ
ስሾም ስሽር ሳይሻር በዙፋን የኖረ
አለምን እንዳልሠራ ሰውን እንዳልፈጠረ
ሰዎቹ ስቆጥሩት እንደተቸገረ

አላስችልህ ስለው የኔ የኛ ጉዳይ
እንደሚታረድ በግ ዝም ብሎ ኤልሻዳይ
በከፈለው እንጂ ዛሬ ህያዉ መሆኔ
እንደኔማ ብሆን ሞቱ ነበር የኔ።

አሁንማ ዳንኩኝ የለብኝ ኩኔኔ
በጎልጎታው ሥራ ለኔ መዳን ሆነ።

በራ ለኔ በራ🌕 በጎልጎታው ሥራ
አሮጌው አለፈ ያ ግዙፍ መከራ
ዛሬ ይሄው ቆምኩኝ በፅዮን ተራራ
ለአብ ላጥን በቃሁ ጨለማዬ በራ
🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕

አንድ ምስኪን ድሀ ከሲኦል ተነጠቀ
መርገም የሞት ካባ ከላዬ ወደቀ
የማይጠፋ ተስፋ ለኔ ተጠበቀ
ይህ ሁሉ ቀራንዮ ላይ ተጠናቀቀ።

ለምሽቴ መሸ ሃጥያቴ ወደመ
አበቃለት መርገም በቃ አከተመ
ክስ ቆመ ፍርድ ቆመ በቃ የለም ቆመ
ሞት ሞቷል ከንግዲህ በሞቱ ታተመ🔒
የሚያሙተኝ የለም ሞቴ ተፈፀመ። 📝

Alazer

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

📥Group :
@yegetamianmahiber
📥Channel :
@Ye_Getami
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
   🔺🀄️🀄️ሉን🔺
           Join us
         🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲ 
ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

የገጣሚያን ማኅበር

20 Nov, 16:24


ተዉኝማ(3X) ጌታ አይችልም #አትበሉኝ🔥

የገጣሚያን ማኅበር

19 Nov, 16:12


.........ፍቅር ነህ

ሳይታሰብ ድንገት ከመንደሬ ገብተህ
በሬን ስታንኳኳ ከደጃፌ መጥተህ
ሳይህ ተሸነፍኩኝ ልቤም ሸፈተ
በአይኔ እየዞረ ትዝታው የአንተ
ተከትሄህ መጣሁ ምንም ሳታወራ
ፈቀጄ ተሸነፍኩኝ ልሆን ካንተ ጋራ
ግና..ክብርህ ስሰማ ከውበትህ አልፎ
እድፈቴ ታወሰኝ ከህሊናዬ ገዝፎ
ምን ድፍረት አግኝቼ ከፍትህ ምቆመው
የኔ ምለው የለኝ ፅድቄ የመርገም ጨርቅ ነው
አንደበቴ ከንቱ ብዙ ዉሸት አለው
ልቤም ሸካራ ፍቅር ሞልቶ አይታየው
ኧረ እንደው ስሜስ ዘሬ ማይታወቅ
ከፊትህ ለመቆም ማሰቤስ የሚደንቅ
እያልኩ ሳነባ ፍቅሬን ባይኔ እየሳልኩ
ድንገት ደጄ መጣህ አዝኜ እያለቀስኩ
እውነተኛ ወዳጅ እንደሰው ሳትርቀኝ
በጉድለቴ ብዛት ሳታሳቅቀኝ
እቅፍ እቅፍቅፍ አድርገህ አነሳኸኝ
አንተ የኔነህ አትፍራ አልከኝ
አንቺ የኔ ነሽ አትፍሪ አልከኝ
አዳፋ አካሌን በደምህ አጠብክና
ነውሬን ሸፍነህ በስምህ ቀደስከኝና
እረሳሁ ትላንቴን ያንን የሀጢዕ ጊዜ
አፍቃሪዬ መጥተህ አወጣኸኝ ከትካዜ
በቃ...በቃ ተማረኩኝ እጅ ሰጥቻለሁ
ፍቅርህ አሸንፎኝ ቤትህ መጥቻለሁ
ያየኝ ይገረም ጉድ ይበል መንደሩ
አፍቃሪዬ ጌታ ከኔ ጋ በመኖሩ
እቅፉ ይደላል አያስመኝም ሌላ
በደሙ ገዝቶኛል አልሄድም ወደኋላ

በ ጌታሁን አናሞ

   Like 👍 React ❤️ Share ↩️

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

19 Nov, 15:30


I'm Back saints 🥰🙌
I missed U all🥰🙌

የገጣሚያን ማኅበር

17 Nov, 05:28


👉 "ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?”
መዝሙር 139፥7

@worlds_light
@worlds_light

የገጣሚያን ማኅበር

16 Nov, 18:59


እዚ ቤት ስለዚ ስም ብቻ ነው ሚወራውስለ ንጉሱ

የገጣሚያን ማኅበር

16 Nov, 17:02


ሕይወት ኢየሱስ ነው
ከጥንት የሰማነው በነብያት ተፅፎ
ቃል የነበረው ወልድ በማሪያም አርፎ
በይሁዳ ቤቴልሄም በዳዊት ከተማ
መስፍን መወለዱን ሄሮድስ ሲሰማ

መኳንንት አዋቂዎች ሁሉንም ጠራና
ኮከብ ቆጣሪዎችንም ደግሞ አስመጣና
ጠየቀ በፅኑ የታሪክ ሊቃውንትን
ማመን ስላቃተው ሰብዓሰገሎችን

እኔን የገረመኝ የታሪክ አዋቂዎች
ከዋክብትን ቆጥረው ጊዜ ጠቋሚዎች
ለንጉሳቸው ጊዜ ቀን ቦታ ነግረው
ምነው ሳይደንቃቸው ተኙ ተመልሰው

ሰብአሰገል መተው ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
በነብዩ አፍ ያለውን እግዚአብሔር
በኮከብ ተመርተው ቤተልሄም ሲደርሱ
የቤቴልሆም አዋቂዎች ሚስጥሩን ረሱ

እውነት ነው አያውቁም ኢየሱስ ሚስጥር ነው
የዘላለም ህይወት መድሀኒት በእርሱ ነው
አይመስልም ነገሩ የመጣበት መንገድ
ፍቀሩ ወረት የለው ሁሉን በአንድ ሚወድ
ይህ እውነት ገብቶኛል እመሰክራለሁ
በስሙ ላመኑት ህይወት ኢየሱስ ነው
ብዙዎች ተከተሉት እንጀራ ፍለጋ
ለስጋቸው ረሀብ ሊሞሉ ማድጋ

ሸክፈው ከመና የሄዱት ስንቃቸው
ከሰፈር ሲደርሱ አለቀ ከእጃቸው
ከሰማይ የመጣህ የህይወት እንጀራ
እየፈካህ ምትሄድ የንጋት ጮራ
የማትደርቅ ምንጭ ነህ ባለ ብዙ ዝና
ነብሴን ላረስርሳት ከአንተ ልጠጣና

ስጋህም መብል ነው ደምህ የህይወት ዉሃ
የዋርካ ጥላ ነህ በሀሩር በረሃ
እጅህን ሳይሆን ፊትህን ሁልጊዜ እሻለሁ
ማራናታ ኢየሱስ ላይህ ናፍቃለሁ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ተፃፈ በጌታሁን አናሞ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

16 Nov, 16:34


ነገ ከቀኑ 8:00 ሰዓት

ኮልፌ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን አይቀርም። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። በጣም ደስ የሚል ጊዜ ይኖረናል።🥰

የገጣሚያን ማኅበር

16 Nov, 14:41


Online ስራ ለመስራት በዚህ ሊንክ ግቡና ጀምሩ👇👇👍👍

https://t.me/major/start?startapp=773589088

የገጣሚያን ማኅበር

16 Nov, 13:51


.....ናፍቆቴ ነህ

ሁሉንም አየሁኝ በታናሽ ማንነቴ
ሚስጥሬን ገልጬ መላ እኔነቴን
ዉሎ ማደር መኖር መሰንበት ከሁሉ
ቆየት ይልና ይሰለቻል ሁሉ
ደግሞ ቀያይሬ ርዕስ ላወራ
ልቤን የሚያረካ ሚቆይ ከኔ ጋራ
ይዤ ያገኘሁት የማያልቅ መሳዩ
ሰንበትበት ስልበት ይረግፋል አማላዩ
የኋሊት ተጉዤ መንገዴን ሳጠና
ስሰቅል ሳወርድ ስቆጥር እንደገና
ሁሉም አለፉብኝ እንዲያ የወደድኳቸው
እጅጉን ቀለሉ ተረሳ ታሪካቸው
ግን አንድ ብርቱ አለ ብልቤ የታተመ
ካነበብኳቸው ሁሉ በውስጤ የከተመ
ዝናውም ልዩነው ከባለታሪኮቹ
ሀይሉም ድንቅ ነው ከነገስታቶቹ
እድሜውም ረጅም የጥንት ጀመሪ
ፍጼሜ የሌለው ለዘላለም ኗሪ
ንጉሰ ነገስት ነው በሰው መልክ የመጣ
ራሱን አዋርዶ ለሀጥያን ተቀጣ
ፍቅርን ኖሮ አሳዬ በቃል ብቻ ሳይሆን
አለማትን ገዛ ሞትና መውጊያውን
እናንትዬ.🤔ብታዩኮ ደግሞ የምስኪን ወዳጅ ነው
ለመበለት ዳኛ ፍርዱም ትክክል ነው
ፊት አይቶ አያደላ ሀብታም ድሀ ብሎ
ሰማይ ምድር ገዛ በስልጣኑ ቃል ይዞ
ኡፍፍፍፍፍአፈቀርኩት በቃ ይሄን ባለ ግርማ
ነብስም አይቀርልኝ ስለሱ ስሰማ
እስኪመለስልኝ እስኪመጣ ዳግም
አምሬ ተውቤ ልጠብቅ ሳልደክም
ረሀቤ ነውና የነብሴ ጥማቷ
ናፍቆቴ ነህ ስትል የልቤ እርካታዋ
ሙሽራዬ ነው እርሱ ኢየሱስ የናዝሬቱ
ከባለ ታሪኮቹ ታሪኩ ነው ብርቱ
መጥቶ እስኪወስደኝ ወይ ሄጄ እስካየው
ኢየሱስ ንጉሴ ናፍቆቴ ነህ እለዋለሁ

በ ጌታሁን አናሞ
ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳችዋለሁ💙


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

16 Nov, 04:02


“ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።”
— ዘዳግም 4፥29

@worlds_light
 @worlds_light
join & share 💫💫

የገጣሚያን ማኅበር

16 Nov, 03:23


መቅረት ከቶ አይታሰብም!!


ነገ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ኮልፌ አጠና ተራ ቃለ ሕይወት ቤተከርስቲያን እንገናኝ። የእህታችንን ደስታ አብረን እንካፈላለን። ❤️

የገጣሚያን ማኅበር

15 Nov, 19:37


ወይ ልይ ወይ ንካኝ...



ናፍቆትህ በረዶ.....ትዝታክ ትኩሳት
ፊትህ እልፍ ፀሐይ እግር እቶን እሳት
ክንድህ እንደ ሰማይ መዳፍህ መስገጃ
(እንዴት ብዬ አቅፌ እንደምረካ እንጃ?)

የነካኸው ስንኩል....ቆሞ እየከነፈ
የነካኸው ዲዳ...........እየለፈለፈ
የነካኸው እውር.......እያየ ሲራመድ
የረገጥከው ወሃ......እየሆነ መንገድ
ያበላኸው ህዝብ ....ለታምርህ ሲቀኝ
እኔ ግን ፊትህ ነው....ሁሌ ሚናፍቀኝ።


ፊቴን በዓይኑ ያየ ይሞታል ስላልከኝ
እንባ አልቆኝ ከምሞት ሰርክ እየናፈከኝ
በአንበሳነትክ ጣት ሳሎን እንደ ግልገል
እንደ ያዕቆብ ንካኝ በእንቅልፌ ስታገል።

አንተን ችላ ብሎክ ፀጋ እንደ ተለየው
ዲን በሚያንሰው ቅጣት ሰው ሲኖር እያየሁ
ዘመኔን እንደ ሎጥ አልኑር እየሰጋሁ
ወይ ዓይቼክ ልሙት ወይም ጭኔን ንካው?

➫Ⓓየሱመልስ
Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

15 Nov, 10:56


እዚ ቤት ስለዚ ስም ብቻ ነው ሚወራውስለ ንጉሱ

የገጣሚያን ማኅበር

15 Nov, 10:55


@worlds_light
 @worlds_light
join & share 💫💫

የገጣሚያን ማኅበር

15 Nov, 04:46


አይኔ ሲጠብቅ፡ ያ'ንተን እጅ
አራስ ቤት ፡እንደጣሉት ልጅ
'ርቦት እንደሚያለቅሰው
ለመጥራት ቃል እንዳነሰው
ሲቃ አፍኖት ጉሮሮውን
እንደሚጮኽ አሁን አሁን
ማባበያ እንደሰለቸው
የውሸት ቃል እንደታከተው
በናፍቆት እየደከመ
እየተጠማ ወተቱን
እያመመው ውሃ አጥንቱን
እንደሚስቅ ሲያይ እናቱን።

ናፍቋል ሊያይክ ፡ ብሌን አይኔ
ናፍቋል ሊዪዝክ፡ እንጭጭ ክርኔ
መቆም አምሮት ተደግፎክ
ቀልቤም ሄዷል ተከትሎክ
.....ከሄድክበት ልትመለስ
ስትናፍቀኝ ........እየኝ ሳለቅስ
እያት እጄን አምሯት እቅፍ
አምሯት መክነፍ ....እይ እግሬን ስትወላከፍ
እየው ዓይኔን ሲቁለጨለጭ ፊትህ አጓግቶት፤
እየው ልቤን ...ልቤን ትቶት
እያት ነፍሴን ተንጠልጥላ
ገበያ የሄደች እናቱን  ፤ እንደሚጠብቃት ጨቅላ።

ናፍቀኸኛል...

➫Ⓓየሱመልስ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

14 Nov, 16:28


እዚ ቤት ስለዚ ስም ብቻ ነው ሚወራውስለ ንጉሱ

የገጣሚያን ማኅበር

13 Nov, 13:15


https://t.me/+TfsXHRGblWBkYWQ0



Joinnnn join🚨🚨

የገጣሚያን ማኅበር

12 Nov, 20:51


ያለ ኢየሱስ አይወራም ነውር ነው🫢 ስለ ኢየሱስ ደሞ መንፈስቅዱስ ያስታውቃችኋል ተራቡት🥰



my beloved HOLYSPIRIT we LOVE YOU🥰🥹😍




https://t.me/+TfsXHRGblWBkYWQ0

Joinnn join join🚨🚨🚨🚨🔥

የገጣሚያን ማኅበር

12 Nov, 16:08


         @worlds_light
          @worlds_light
join & share 💫💫

የገጣሚያን ማኅበር

11 Nov, 18:37


"................  ታገሡ፥ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።

      ታገሡ ቅዱሳን🥰
      ከዝህ ሁሉ መከራ
      ማረፍ ይሆንልናል

    የናፈቅነውን ጌታችንን
     በዓይናችን ልናይ ነው
🥰

😊ሶለን
(የያዕቆብ መልእክት 5:8)
Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

11 Nov, 12:45


✍️ለምን እኔ ልኑር

ባልተገመተበት  ባላሰበው  ወጥመድ
ሶምሶን  ቢሄድ  በደሊላ  መንገድ

አይኔን  ያሳወረ  ፍፃሜ  እንዳይሆን
ሰውነቴን  በልቶ  ሞቴን  የሚያፈጥን

የልብን የሚገልጥ መስሎ ወዳጅ ሰሚ
ያንተን ሳይሆን የክፉን ፍቃድ አስፈፃሚ

የእኔ  የዋህ  መሆን  ትህትና  ቢቀር
ያንተ  ስለሚበልጥ  ያየህልኝ  ክብር

የመከርከኝ  ምክር  የነገርከኝ  ያኔ
ለምን እኔ  ልኑር  አንተ  ስትኖር  በእኔ

ለምን  እኔ  ልኑር  አንተ  ስትኖር  በእኔ ??

        #Reyni_Tamiru
Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

11 Nov, 04:46


💕መፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ አይደለም ለሚያምንበት የሂወቱ መመሪያ ነው።
ስለዚህ ሴቶች ስንፀልይ እራሰችንን እንሸፍን እግዚአብሔርን እንጂ ዘመኑን አንከተል ።

1ኛ ቆሮንቶስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና።

… 
¹³ በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን?


@worlds_light

የገጣሚያን ማኅበር

10 Nov, 11:00


ቃሉን ለማስታወስ የሚረዱን ዘዴዎች👇👇👇


1) የጥቅሶቹን አውዳዊ ፍቺ
መረዳት

2) በቃሉ (በክፍሉ)ውስጥ
ራሳችንን በማስገባት ማሰላሰል

3) ልናሰላስለው የምንፈልገውን
ክፍል ወደ ትንንሽ ዐረፍተ ነገሮች
መቀየር።

4) ክፍሉን በመጻፍ ለማሰላሰል
መሞከር።

5) በአእምሮአችን ታትሞ እስኪ
ቀመጥ ድረስ መደጋገም።

6) መዝሙር መዘመር

@worlds_light

የገጣሚያን ማኅበር

10 Nov, 04:11


" ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:4)

በምንም ነገር እለፉ በምንም የደስታችሁን ጉዳይ ከሁኔታዎች ጋር አታያይዙ ለመደሰት በቂ ም/ት አላችሁ እርሱም ጌታ ነው!ነፍሳችሁ ስለዳነች በዚህ ሃሴት አድርጉ🕆

መልካም እሁድ ወዳጆቼ👋

@worlds_light

የገጣሚያን ማኅበር

09 Nov, 19:09




በእግዚአብሔር አምኖ የተደገፈ
ኃይሉ ይበረታል እንጂ አይወድቅም በሕይወቴ አይቻለሁ ሕያው ምስክር ነኝ። ከተደገፋችሁ አይቀር በእግዚአብሔር ተደገፉ።😊🥰

ሰናይ ምሽት❤️🥰

የገጣሚያን ማኅበር

09 Nov, 06:15


😱 Wow ቤተሰብ🥰🥰
ብዙ አልሰራንበትም እንጂ ከዝህ ባላይ እንሄድ ነበረ። እግዚአብሔር ይመስገን እናመሰግናለን በዩቲዩብ በጥቂት ጊዜ ወስጥ ብዙ ተከታይ አፍርተናል።ስለ አብሮነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን። በቅርቡ በቲክቶክ እንመጣለን። አሁንም አብሮነታችሁ አይለየን ተባረኩ። ዩቲዩብ ቻኔላችን ሰብስክራይብ አድርጉ።

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

08 Nov, 18:51


እኛስ ጴጤዎች? ተንቀናላ😐🤔

Me:- “እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥
— ፊልጵስዩስ 3፥20 🤓🤝

የገጣሚያን ማኅበር

07 Nov, 18:20


“ዳዊትም እየበረታ ሄደ፤ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።”
  — 2ኛ ሳሙኤል 5፥10

          @worlds_light
          @worlds_light
join & share 💫💫

የገጣሚያን ማኅበር

07 Nov, 10:46


ተባረኩበት የሀና ተክለ
ቁጥር 4 መዝሙር ነው
😍

የገጣሚያን ማኅበር

06 Nov, 18:11


መንፈሳዊ ፊልም የሚመቻችሁ ከሆነ አሁኑኑ JOIN ይበሉ ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇
https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk
https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk
wave ለመግባት👉 @wunuye_bot

የገጣሚያን ማኅበር

06 Nov, 17:06


ችላ_ዝም _አትበለው
መኖር እንኳን አለ:የለም እንዳይባል:ጥያቄም ሳይበዛ
በስፍራው ሲፈልግ:የተሰጠ ቦታ:ሰፍቶ እንዳይበዛ
አስተውዬ ሳየው:ከልብ ስመለከት
ለሰው መልሱ ሰው ነው:ከልቡ አክብሮ :ስፍራን የሰጠበት
በእምነት ጠብቆ:ልብ ላይ አድምቆ
መልካምን ፍሬ ህይወት:ከልቡ ሰንቆ
መልካም እንዳሰበው:ከፊት ቢዘልቅለት
እንዳይሆን ሆነና:ያሰበው የሰጠው:ስፍራ ራቀበት
ከቤቱ ቢፈልግ:በጩኸት ቢጣራ ለድምፀቱ ምላሽ:ሚሰጠውን ሲያጣ
ልቡ እየራደ:የተጣራለትን:ያሰው እስኪመጣ
በቃ ተወው ይቅር:ዝም በል የሚል ወገን
ከጉያው ተነስቶ:ቀን ሌሊት ሲናገር
በዝቶ ንዝንዙ:ድምፁን ተቀብሎ
መኖሩን ቀጥሏል:ሁሉን ነገር ጥሎ
ብቻ ይህ እንዳለ:ለሰሚ ይህ በለው
ባለህበት ስፍራ:የሚጠብቅህን:ያን ሰው ተቀበለው
ችላ ዝም አትበለው:ከስፍረው ያይሀል
ትመጣለህ ብሎ:ከደጃፋ ቆሞ:ልቡ እያሰበ ይከታተልሀል
አንድ ነው ሀሳቡ:ግልፅ ቃለ እውነታ  
ከልብ የያዙትን:ከልቡ ሲፈቱት:የወደቀ ለታ
ደግመው እንዲያነሱት:ጊዜውም አይመጣ
ብዙ ዋጋ መክፈል:የእውነት ህይወት ላይ:
ያስቀይራል እጣ
              
                                👉ክብር-ሰፈር
                                       ታሜ🔥      
                                 27/2/2017

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

06 Nov, 11:20


............ናፍቆቴ ነህ

ሁሉንም አየሁኝ በታናሽ ማንነቴ
ሚስጥሬን ገልጬ መላ እኔነቴን
ዉሎ ማደር መኖር መሰንበት ከሁሉ
ቆየት ይልና ይሰለቻል ሁሉ
ደግሞ ቀያይሬ ርዕስ ላወራ
ልቤን የሚያረካ ሚቆይ ከኔ ጋራ
ይዤ ያገኘሁት የማያልቅ መሳዩ
ሰንበትበት ስልበት ይረግፋል አማላዩ
የኋሊት ተጉዤ መንገዴን ሳጠና
ስሰቅል ሳወርድ ስቆጥር እንደገና
ሁሉም አለፉብኝ እንዲያ የወደድኳቸው
እጅጉን ቀለሉ ተረሳ ታሪካቸው
ግን አንድ ብርቱ አለ ብልቤ የታተመ
ካነበብኳቸው ሁሉ በውስጤ የከተመ
ዝናውም ልዩነው ከባለታሪኮቹ
ሀይሉም ድንቅ ነው ከነገስታቶቹ
እድሜውም ረጅም የጥንት ጀመሪ
ፍጼሜ የሌለው ለዘላለም ኗሪ
ንጉሰ ነገስት ነው በሰው መልክ የመጣ
ራሱን አዋርዶ ለሀጥያን ተቀጣ
ፍቅርን ኖሮ አሳዬ በቃል ብቻ ሳይሆን
አለማትን ገዛ ሞትና መውጊያውን
እናንትዬ.🤔ብታዩኮ ደግሞ የምስኪን ወዳጅ ነው
ለመበለት ዳኛ ፍርዱም ትክክል ነው
ፊት አይቶ አያደላ ሀብታም ድሀ ብሎ
ሰማይ ምድር ገዛ በስልጣኑ ቃል ይዞ
ኡፍፍፍፍፍአፈቀርኩት በቃ ይሄን ባለ ግርማ
ነብስም አይቀርልኝ ስለሱ ስሰማ
እስኪመለስልኝ እስኪመጣ ዳግም
አምሬ ተውቤ ልጠብቅ ሳልደክም
ረሀቤ ነውና የነብሴ ጥማቷ
ናፍቆቴ ነህ ስትል የልቤ እርካታዋ
ሙሽራዬ ነው እርሱ ኢየሱስ የናዝሬቱ
ከባለ ታሪኮቹ ታሪኩ ነው ብርቱ
መጥቶ እስኪወስደኝ ወይ ሄጄ እስካየው
ኢየሱስ ንጉሴ ናፍቆቴ ነህ እለዋለሁ

በ ጌታሁን አናሞ


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

06 Nov, 07:18


👉 ከእግዚአብሔር እርዳታ ለማግኘት ረጅም መንገድ መሮጥ የለብንም። ችግሮች ሲገጥሙን እርሱ ከእኛ ጋር ነው።

👉 ከእስትንፋሳችን ይልቅ ለእኛ ቅርብ ነው። አብሮነቱ ለአንዳንድ ችግሮች ብቻ ሳይሆን እስከ ህይወት ዘመን ድረስ ነው።

         @worlds_light
          @worlds_light
join & share 💫💫

የገጣሚያን ማኅበር

05 Nov, 08:29


መሥዋዕት!

ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን! መሥዋዕት ቁጥር 4 አልበም በዚህ ሳምንት ይለቀቃል!እስከዚያው ከአልበሙ ውስጥ"በማለዳ"በተሰኘው አዲስ ዝማሬ ተባረኩ!

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

https://youtu.be/binGZ6i8-yI?si=kcGoXx-QIYBNh9Hz

የገጣሚያን ማኅበር

05 Nov, 04:18


አድስ አበባዎቼ አላቹ ወይ?😍🙌
ድንቅ ፕሮግራም እየተዘጋጀ ነው
በሙሉ ማስታወቂያ ማታ እንመለሳለን።

የገጣሚያን ማኅበር

04 Nov, 16:55


........እጠብቅሀለሁ
መች ተማምነህ በእኔ ችሎታ
ሁሉን ስታሳምር የፍጥረቱ ጌታ
በራስህ ስላለህ ብቸኛ ችሎት
በሰው አትመካ ባለው ጉልበት
ይሄንን አውቄ ራሴን ሰጥቻለሁ
መጣለሁ ያልከኝ ቦታ እጠብቅሀለሁ
ቃልህን አትበላ ሀሩሩ ጠንቶብህ
ርዕሰ አትቀይርም መንገዱ ርቆብህ
እመጣለሁ ስትል ስትሄድ አሸንፈህ
መሆንን አልረሳሁም ከሞት ተነስተህ
ታዲያ ምን ያግድህ ይከለክል ብዬ
ለምን እፈራለሁ ስጋት አስከትዬ
በወጀቡ መሀል መንገድ ታበጅ የለህ ??
በደረቅ በረሀ ዉሃም ታፈልቃለህ
መካኒቱም ሆነች ወልዳ ሰባት መንታ
የትውልድ እናት አድርገሀል ጌታ
በደረቁ ምድር ኖኅ ከሰራ መርከብ
ታምኖ ከታዘዘ በዉሃ መድር አንድትከብ
ከሙት ስጋ መሀል ሳራም ወልዳለች
የሌለን ለማኖር አያቅትህ አንዳች
በዚህ ሁሉ አየሁ ሁሉን ቻይነትህን
ሁኔታው ያወራል ኤልሻዳይ መሆንህን
እኔም አምኛለሁ ትመጣልኛለህ
እጠብቅሀለሁ በቃልህ ታማኝ ነህ

በ ጌታሁን አናሞ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

04 Nov, 14:57


💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
በመዝሙሮቹ የተባረካቹበት እና የምትወዱትን ዘማሪ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

የገጣሚያን ማኅበር

04 Nov, 06:40


ምን ቢያደርግልህ/ሽ/ችሁ ትወዳላችሁ?

በመንበርከክያ ቦታችሁ ጠይቁት።
በርግጥም ሁሉ ቀርቶ እናየው ዘንድ እንማፀነዋልን። እርሱን ማየት የጥያቄ ሁሉ መልስ ስለሆነ🥹 እንደ እምነታችሁ ይሁን🖐️
የብዙ ማረኝ ጩኸት ፊቱን በማየት ይሰማላችሁ🖐️

ሉቃ 18: 40 በቀረበም ጊዜ፡— ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? ብሎ ጠየቀው።
41 እርሱም፡— ጌታ ሆይ፥ አይ ዘንድ ነው፡ አለው

@ቃሌ እወድዳቹሀለው🥰

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

03 Nov, 10:55


እዴት ናችሁ ቤተሰብ🥰🥰
ቸርች የሄዳችሁ
ምን ተማራችሁ😊🥰

Comment ላይ አስቀምጡ

የገጣሚያን ማኅበር

03 Nov, 06:35


“እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።”
  — ሮሜ 8፥1

መልካም እሁድ 🥰

የገጣሚያን ማኅበር

02 Nov, 18:44


(ሰሞንኛ)

እንጃልኝ ሰሞኑን
ያጋጨኛል ለጉድ ማዕበል እየለተመ
ይለበልበኛል መከራ ተዳቅሎ እየተፋፋመ
ውሎና አዳሬ በትካዜ  ሆኗል
ደምግባቴ የለም ከጎዳና መክኗል
ሆኛለሁ ለጠኔ ከአሳማ ሰፋሪ
እፋለመዋለሁ ላንዲት' ፍርፋሪ።
እንጃልኝ ሰሞኑን
እንደ አመድ አፋሽ አይወዛ ሆኛለሁ
በገረጣ ገፄ ሐሳብ እቀኛለሁ'
የለውም የለውም
ነፍሴ ከኔ ርቆ
በትካዜ መርከብ ከትዝታ ዝቆ
ሄደ ተሳፈረ ከሩቅ ሃገር በሮ
ትዝ አለው መሰለኝ፣ የአባቱ ቤት ኑሮ።
እየባሰ ሄድ አሳር አከሰለኝ
እንደ ባሪያም ብዬ ልመለስ መሰለኝ።
(እንደ ልጅህም ባይሆን)

(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

02 Nov, 16:44


ኢየሱስ ይመጣል👑

የገጣሚያን ማኅበር

02 Nov, 15:19


.........ለኔ ግን ጌታ ነህ

ሰዎች ባይገባቸው ሚስጥሩ ተገልጦ
ከአይምሮአቸው ተአምርህ በልጦ
አሰቡህ ለክተው ልክ እንደ ሰው
እንደ አንድ አዋቂ ብለው አወድሰው
ደግሞ ሌሎች መጡ አይተው ጭላንጭል
ተስፋን ስትዘራ ህይወትን ስታድል
መሲህ ነው አሉ ቃላቸውን ቀይረው
ይመጣል የተባለው እሱ ነው ብለው
ዳሩ ግን አልፀኑም ሌሎች ተነሱና
በቃላት ሲሞግቱህ ሀሳብ ቀየሩና
ሀጥያተኛ አሉህ ሰንበትን አያከብር
የዮሴፍ ልጅኮ ነው ያለ እታች ሰፈር
አናውቀውም እንዴ እህት ወንድሞቹ
የአናጢው ልጅ ነው እያሉ ሰዎቹ
ሙታን ስታስነሳ አንካሳው ሲዘል
ከሙኩራብ ገብተህ ቃልን ስታካፍል
መምህር ነው አሉ ቃሉ ይገርማል
የደረቀን ነብስ ተስፋ ያለመልማል
ኋላ ኋላማ ሊገድሉህ ወደዱ
ንገስ ባሉበት አፍ አንተን አሳደዱ
ከሄሮዲስ ጲላጦስ እየገፈታተሩ
ከመስቀል ሊያኖሩ እጅ እግርህን አሰሩ
አወጡህ ጎልጎታ በእንጨት ጠፍረው
ሰቀሉህ በመሀል ከወንበዴ ጋ አብረው
ሲሳለቁ ውለው ቀኑ ሲጨላልም
አንደኛው ተነሳ ሊሳደብህ ዳግም
አንተ ...ጌታ ነኝ አላልክም ያኔ
እስቲ ዉረድና ልውረድ ደግሞ እኔ

🤔🤔🤔አወይይይ ትዕግስትህ🤔
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
የኔ ጌታ ኢየሱስ የቀራኒዮ በግ
ለሰቀሉህ እንኳን ምህረትን ምታረግ
ያሻቸውን ይበሉ አንተ ግን ታላቅ ነህ
ማንም ምንም ቢልህ ለኔ ግን ጌታ ነህ
ያን ለታ ስትመጣ ስልጣንህን ጥለህ
መች አቅማማህ እኔ ልታይ ወርደህ
ቁስሎችህ ታወሱኝ ስለኔ የደማው
ጎንህም ተወጋ እያልክ  ተጠማው
ተራራውስ እንዴት ቻለ??አንተን ተሸክሞ
እንጨቱም ታዘዘ ላይጣመም ቆሞ
ሚስማሩ ሲመታ ስታጣጥር ሲቃ
እንዴት ብትወደኝ ነው እስከዛች ደቂቃ
ይበሉ የሰው ልጅ እያሉም ይጣሩ
ለኔ ግን ንጉሴ የገዛኝ በጣሩ
አይመንህ ሲፈልግ ፍጥረት አንድ ላይ
ለኔ ግን አዳኜ አንተ ነህ ኤልሻዳይ
ከሰጠኝማ ነብህን ህይወቴን ካዳንካት
ከጨለማ አለም ሞተህ ከታደካት
የኔ ምልው እስካኖር ውሰደው ራሴን
ዘመኔን ልሰዋ ልቀደስ መቅደስህን

በ ጌታሁን አናሞ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

01 Nov, 06:29


.........የት ጋ ነው ሰማይህ

ፍለጋዬ በዝቶ መገኛ አድራሻ
ከዳር እስከ ዳር ያለም መጨረሻ
ናፍቆቴ አይሎ ቃላትም ላይተኩ
መገኛህን ስሻ ስንት ዘመን ኖርኩ
ወይ አትከሰት ድንገት ሆነህ ዱብ ዕዳ
ጠውልጋ ለዛለች ነብስ ለተጎዳ
ካሊያም አትሰማ ከወንዙ ፏፏቴ
አንተን አንተን ስልህ ናፍቀኸኝ በሞቴ
አይኔ እንባ አዝሉ ሌተቀን ያነባል
ልቤ እየፈጠነ ስላንተ ያስባል
ቆይ...ቆይ እሺ የት ጋ ነው ሰማይህ
ሀዘኔ በርትቷል ፊትህን እስካይህ
ከልጅነት ወራት አድጌ በተስፋ
በእጅ ማይጨበጥ ጉም ሚሆን የጠፋ
ከዛሬ ነገ ስል ትንቢቴ ዘግይቶ
ባዶ ሩጫ ሆነ የማይያዝ ከቶ
የት ነህ.....የት ነህ ቆይ እስቲ ልጠይቅህ
ካልመጣህ ልምጣ ወይ ወዳለህበት
የዉስጠቴ ሲቃ ወጥቶ ከገሀዱ
አብዝቶ ይጣራል በጉጉት መንገዱ
አትመጣም ወይ ስለምን ዘገየህ
በቶሎ እመጣለሁ ብለህ ተናግረህ
የሙጥኝ እላለሁ አልነሳም ከዚህ
እወራረዳለሁ እስኪመጣ መልስህ
እኔም እጮሀለሁ አንተም አትመልስ
በፍጹም አልሄድም ጥያቄዬ ሳይመለስ

✍️✍️✍️በጌታሁን አናሞ✍️✍️✍️ Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

31 Oct, 05:48


የልቤ አምላክ😍😍😍😍

ዘማሪት አስቴር አበበ
@maranata_mez
@maranata_mez
join and share

የገጣሚያን ማኅበር

30 Oct, 18:45


From Wolaita Sodo😀😀
ዛሬ በብዙ ሚዲያ ላይ አነጋጋሪ የሆነ ቡና ቤት።

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

29 Oct, 18:44


ወንጌል🔥

የገጣሚያን ማኅበር

29 Oct, 18:33


ጸጋ የበዛላችሁ ለወንድማችን ወጉንም መነባነቡንም ግጥሙንም አድርሱለት ተባረኩ ሁላችሁም ተሳተፉ እስቲ የጌታ ጸጋ ይብዛላችሁ።🥰🥰 ስትጨርሱ በውስጥ አድርሱልኝ

@S_o_L_e_N_y

የገጣሚያን ማኅበር

29 Oct, 05:14


የራስህን...
እንደ ትኩስ እያበረድኩ
እንደ ህፃን  እያባበልኩ
እንደ አልማዝ ተጠንቅቄ
እንደ ሚስጥር ደባብቄ

ሰጠሁ ምለው የ'ኔ የለም
......................ከእጅህ ለእጅህ ስረዳሁ
ያለኝ ብዬ የምሰጥ ከራስህ ጋን እየቀዳሁ።
ስጠኝ ያልከኝ ችሮትህን
.....................ስጠኝ ያልከኝ ያንተኑ ቃል
ታሪክህን ቅረፅበት መባ ብዬ ልቤን ልጣል።
ስጠኝ ያለከኝ ከሰጠኸኝ
...................ስጠኝ ያልከኝ ያንተኑ ድምፅ
ምን ልዘምር ለውለታህ ላ'ገኘኸኝ ሳልታነፅ።


ይኸው እንካኝ...ሰውነቴን.....አንተን ሙላው እኔነቴን።

ይኸው እንካኝ ...ያ'ካሌን ጫፍ
..................አንተን ላውራ በራሴ አፍ።

መቅረዝ ስትል በ'ኔ ብራ
..................ገንዘብ ስትል በ'ኔ ስራ።

ይኸው እንካኝ ፍጥረትህን
...............እኔን ልስጥህ የራስህን።


በመሞትህ እየኖርኩት......በመሞቴ ባልፈልግህ
ስጠኝ ስትል እየሰሰትኩ የራስህን እንዳልነፍግህ።

ይኸው እንካኝ.....የራስህን !



➫Ⓓየሱመልስ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

28 Oct, 19:14


(የታሰረ ነፃነት)

ከእግዚሐር መልካም እስር፣ ሰውነቱን ስቦ
በሐጢያት ሰንሰለት፣ እጆቹን ተብትቦ
ነፃ ነኝ ይለኛል
ታስሮ በነፃነት እየተገፈተረ
ከሞት መርከብ ቀዝፎ እየተሳፈረ
ነፃ ነኝ ይለኛል ሆኖ ከወህኒ ስር
ተቀርንቶ ነፍሱ በዘላለም እስር
ነፃ ነኝ ይለኛል
ከበጉ ዙፋን ፊት ፍርድ እየጠበቀው
ከአንገቱ ድረስ በደል እያነቀው
ለመኖሩ ሳይኖር ለመሞቱ ሞቶ
በሐጥያቱ ትብታብ ፍጥኝ ተቀርንቶ
ነፃ ነኝ ይለኛል
;
ነፃ መሆን ማለት...
ከማይታይ ስፍራ ተጉዞ በኪዳን
በእግዚሐር ቃል አስሮ ነፍስን ሄዶ ማዳን
ነፃ መሆን ማለት...
ታልፎ ተሰጥቶ ለሞት ፍርድ ቅጣት
ስጋን ገሎ ለሞት ነፍስን ነፃ ማውጣት
ነፃ መሆን ማለት...
ስጋን ፍጥኝ አስሮ እየከፉ ለራስ
መኖር ለህይወት ቃል እያደሉ ለነፍስ
ነፃ መሆን ማለት...
ለህይወት ቃል ኪዳን
እየሞቱ መኖር እየታመሙ መዳን።

(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

28 Oct, 19:11


No Reaction
No Post
😒😐😐

የገጣሚያን ማኅበር

28 Oct, 18:35


ሙሽሪት እንደፃፈችው


የመምጣትህን ዜና ጆሮዬ ሲጠብቅ
በናፍቆት ወደላይ አይኔ ሲያንጋጥጥ
ምነው አረፍፈድክ?
.
.
ምን እክል ገጥሞክ ነው ተ መንገድ የቀረክ
እኔስ በሰአቱ ከቀጠርከኝ ቦታ
ተሰነዳድቼ ሳላረፍድ በአንድ አፍታ
ፈጥኜ ብደርስም 😔
ከቀጠሮው ቦታ ቀጣሪው የለህም
ሰአት እና ቀናት  ወራቶች አለፉ
አመታትም ቆየው የለህ በደጃፉ

ማትመጣ ከሆነ, , በቃ እኔም ልቅር
ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ልኑር
ማትመጣ ከሆነ , , ለምን ጠብቃለው
እንደ ወደጆቼ እንደ ጓደኞቼ
ፈታ ያልኩ ኖራለው
ያልመጣህ እንደሆን , , ነብሴን ማንሰፍሰፉ
ተስፍን የመስጠትህ ምን ይሁንስ ትርፉ😥
.
.
እንደውም አልጠብቅህም😡
አንተም ከወዲያ ኑር
እኔም በዚህ ልኑር
ኪዳናችን ይፍረስ ይፍረስ
ፍቅራችን ይደፍርስ
ብዬ እንዳልደመድም
ሙሽሪት ያላንተ መኖር አትለምድም😔


ከማጉረምረም ሌላ ከመጠበቅ ውጪ
ለነብሴም እያልኳት አርፈሽ ተቀመጪ
በግድ እየጎሰምኩ ደካማ ስጋዬን
በቃልህ እየገደልኩ የውስጥ መሻቴን
እጠብቅሀው
እጠብቅሀለው
በምጥ እንዳለች ሴት
እንደተቿኮለች ልታይ የልጇን ፊት
ነጭ እንደለበሰች እንደ ውብ ሙሽራ
እዳቁነጠነጣት እስኪመጣ ባሏ
አጠብቅሀለው
እንደተኳኳለች
ሌሎችን ሳትመስል በጌጥ እንዳማረች
እጠብቅሀለው በቶሎ እስክትመጣ
ደግሞ ብትዘገይስ እኔ ምን ላመጣ
ከመጠበቅ ውጪ አንተን ከመታገስ
ምን አማራጭ አለኝ??🤷‍♀️
በፍቅርህ ሰንሰለት ጠፍረህ ካሰርከኝ
ማህተብ አኑረህ ከልቤ ጓዳ ላይ
እንዳይስበኝ ከንቱው ከስርህ ዳልለይ
ዞሬ አማትሬ ሌላውን እንዳልቃኝ
እስርስር አረከኝ
ታድያ ምን ተሻለ
በቃ እንዲሁ ይቅር ልቤ እንደዋለለ?🤦‍♀️
አመታትንም ይፍጅ ወራትም ይቆጠር
ቁጭ ብዬ ላሻቅብ ከቀጠሮህ ወንበር
.
.
.
.
.
ስለዚህ ውድዬ መጥተህ እስክትወስደኝ
እጠብቅሀለው ምን አማራጭ አለኝ!!


በሩት✍️
9/2/17
₰₰

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

28 Oct, 11:41


ሞኞች ናቸው እየተባልን😄
...... በሰማይ ቤት ሰራን
🤓

የገጣሚያን ማኅበር

27 Oct, 05:57


በዚያ ሀዘን የለም መከራና ለቅሶ
መገፋት መጨነቅ ያበቃል ጨርሶ
አዎን እንሄዳለን ወደ ኢየሩሳሌም
በደስታ በሀሰት ልንኖር ዘላለም።

መንግስተ ሰማይ
እንደምን ናፍቀናል
መድኃኒታችንን በዓይናችን ልናይ
ፊት ለፊት ልናይ🥹🥰
.
.
.
ጽኑ ነው ተስፋችን ስንጠብቅህ ልናይ እንደገና
ትመጣልናለህ አለኝታችን በክብር በደመና
አሜን ማራናታ ቶሎ ናልን አትዘገይ የእኛ ጌታ
ልጆችህ ናፍቀንሃል ልንዳስስህ እንጆችህን እንደገና።

ኢየሱስ ሆይ ናልን
ሀገራችን ውሰደን


ሰናይ ዕለተ እሁድ
React🥰❤️
Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

27 Oct, 03:31


ርዕስ :-እንደ ሳሙኤል

የኔ ከምለዉ ለኔ በምለዉ ከኔ የምለዉ
እንዳይሆን አርገ ሳሙኤልን ስጠኝ
አንተዉ ዘግተኸዉ አንተንዉ ክፈተዉ
ለአንተዉ ክብር እንዲሆንል
በፊት የሚያድግ በብላቴናዉ የሚያገለግል    
እንደ ሳሙኤል ምገስ የሚያገኝ
ባክህ አደራ ትዉልድን ስጠኝ


             ፀሀፊ:-የአብስራ :ፍቅሬ


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

26 Oct, 18:58


በክርሰቶስ ሠላችሁ ይብዛ🥰🙌
ምሽቱም የተባረከና የተዋበ ይሁንላችሁ።ለዛሬ ምሽት ተብሎ የተመደቡ የሰይጣን ጭፍሮች ሁሉ በናዝረቱ በኢየሱስ ስም ወደ ስዖል ይውረዱ! በሌሊት ተነስታችሁ ጸልዩ ቅዱሳን🤚

መልካም ምሽት

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

26 Oct, 06:13


እፈልጋለዉ  እንጅ  አልፈልግም!

ባልፈለኩ ... ልቀምሰዉ
ባልተጣላዉ 🙄 ካምላኬ ከሰዉ
ዘመኔን  ባልኖርኩ  እንዳነከሰዉ።

  መፈለግ አይደል
የራሴ  መሻት 
ስጋዬን   ጎድቶ
ነሴን ....   ያሳሳት!

አልፈልግም !...ምን በወጣኝ
የሚያናድድ   የሚያስቆጣኝ
አልሆን  ሲለኝ  አልሳካ
የዉስጥ  እኔ  እያዉካካ
 
     እየሰማዉ  አልቆዝምም
      ለታዬልኝ  አልጠምም
      ለመሻቱ  ስሜቱነዉ  ሰዉ እወነቱ።

       ለኔ  .....ጌታ
ሚያስባትን  ያዉቃል 
      ለምን  ?
ጉልበቴ ቀድሞ ይሮጣል
      ለመድከምዝሎ 
          ለምነዉ ?  ጭንቀቱ
         ነጭ ላይሆን ፀጉሬ
         ጨምሮ ላይታይ ስጋዬ ቁመቱ
         ምረቱ 🙏አይደለ አዲስ...
ሁሌ በየለቱ

          እያልኩም  እያወኩ እፈልጋለሁኝ
            አንድ .... አንድ... አንዳድ ነገር
              በፀሎት  ስጣጋ  ላወራዉ  ልናገር
                አሊያም  ልፈዝበት  ትዝ ትዝሲለኝ
                አልፈል ግም እንጅ እፈልጋለሁኝ።
     

          አወ 🙌አወ 🙌 ግን  አልፈልግም
             ካላመጣሁት  ከቃሉ ግድም
     
                 ያምላኬንትቸ  የኔን አልወድም።

ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

25 Oct, 19:27


ክርስትና ከእረፍት ነው የሚጀምረው!

💕 አንድ ሰው ሰርግ ደግሶ ሰዎችን የሚጠራው ተቀምጠው እንዲታደሙ እንጂ ሰርገኛውን በስራ እንዲያግዙ አይደለም።

“የሰርጉንም ቤት ተቀማጮች ሞሉት።”
— ማቴዎስ 22፥10

💕 እንዲሁም ክርስትናን ስንቀበል የእግዚአብሔር ጥሪ ሲቀርብልን የእግዚአብሔርን ህይወት በእረፍት በመቀመጥ ልንኖረው እንጂ በስራ እንድንኖረው አይደለም።
💕 እግዚአብሔር አለምን ሁሉ ፈጥሮ ሲጨርስ በአምስተኛው ቀን አዳምን ፈጠረ በመጨረሻውም ቀን አረፈ አዳም ግን በመጀመሪያው ቀን እረፍት ሆነለት።
💕 ክርስቶስ የሰውን ለጅ ሀጥያት ሁሉ ወስዶ ከተቀጣ በኃላ ተፈፀመ አለ ያኔ ክርስትና ተጀመረ በስራችን ሳይሆን በፀጋው መዳን ቻልን ክርስቶስ ሰርቶ ከጨረሰ በኃላ በአባቱ ቀኝ ከተቀመጠ በኃላ የኛ ሂወት ተጀመረ። ስለዚህ ክርስትና ከእረፍት ነው የሚጀምረው ከስራ አይደለም።

  @worlds_light
          @worlds_light
join & share 💫💫

የገጣሚያን ማኅበር

25 Oct, 15:08


የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል።”
  — ምሳሌ 16፥9

እንዲህ ልባርካቹ🙌❤️🔥

እግዚአብሔር መንገዳቹን ያቅናላቹ🙌

እሱ በለመለመው ስፍራ ያሳድራቹ🙌

በእረፍት ውሃ ወንዝ ይምራቹ🙌

አሜን ላለ ይሁንለት🔥🫵



          @worlds_light
          @worlds_light
join & share 💫💫

የገጣሚያን ማኅበር

24 Oct, 13:41


ሠላም ቅዱሳን እንዴት አላችሁ 🥰
Graphics ሞያ ያላችሁ ምናልባት አብራችሁን ለማገልገል ፈቃደኛ ከሆናችሁ በውስጥ መስመር አናግሩን። ለዩቱዪብ ቻኔል አንዳንድ ነገሮችን ለመስራት አስበናል።

DM @S_o_L_e_N_y

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

24 Oct, 09:55


“ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር #ሁሉ አይጐድሉም።”
  — መዝሙር 34፥10
                  Say Amen🙏

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

24 Oct, 04:15


=======ከንቱ ፍለጋ=======

የት ትገኝ  ...  የት ትሁን ሠላም
ልፈልጋት፣
ህዝቤ እኮ ተንከራተተ ሠላም
በሌለበት።

ገንዘቡን ይዞ ወጣ.. .. .. የለም እርካታ፣
ገንዘብ ቁስን"ጂ መች ይሰጣል እፎይታ።


                     ተጻፈ በሶለን
          መስከረም 12/2015 e.c

@Ye_Getamian_mahiber
@Ye_Getamian_mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
      🔺🀄️🀄️ሉን🔺
           Join us
         🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲ 
ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

የገጣሚያን ማኅበር

23 Oct, 18:11


እግዚአብሔር የማያውቀው ህመም ፣ ስቃይ፣ ስብራት ፣ዝለት የለም።He knows how we feel, 🥺 Nothing is hidden from him....ምንም እንኳን ያልተመለሱልን እልፍ ጥያቄዎች ቢኖሩንም... እግዚአብሔር ግን አዋቂ ነው።በርሱ እንደመታወቀና እንደመታየት ያለ ነገር ምን አለ?.. እግዚአብሔር አዋቂ ነዉ ሁሉን እንደወደደው ያርገው 🙌!

Via:- unknown


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

22 Oct, 07:34


ርዕስ: ፀጋህ ብቻ

መች ጠፋ አለ የኔም ድካሜ
ፀጋህ በዝቶ እንጂ መቆሜ
የሚቆጠር ኩነኔ እንጂ በኔ ኑሮ
መች ሚቆጠር ፆድቅ ኖሮ
የኔን ሞት በሞት ሽሮ
ግና ባላዉቀዉም እንዲያ ባልወደዉም
አንዱ መጣ እኔን ሊገዛኝ በከበረ ደም
የሚታይልኝ ሊቀ ካህኔ ጠበቃ ሆነኝ
በመስቀል ስራዉ ፃዲቅ አረገኝ
ይኽዉ አለዉኝ እስከዛሬዉ ቀን
በፀጋው ብዛት አቅፎ ደግፎኝ
ምንም የለኝም መተማመኛ
ካላንተስ ፀጋ አወይ ባዶ ነኝ





                      ፀሀፊ :የአብስራ:ፍቅሬ❤️

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

21 Oct, 13:35


(አንተን ከኔ ማራቅ)

እኔን ካንተ ማራቅ
አውለብልቦ ሙዳ ስጋ
አንበሳን ማስከተል ከዚህ እስከ እዚያ ጋ
አንተን ከኔ ማራቅ
ከአንበሳው ታግሎ በሳምሶን ትክሻ
ያንን ሙዳ ስጋ
ተፍጨርጭሮ መንጠቅ  ከጥርሱ ንክሻ።
እንደዚህ ነው እግዚሐር
እኔን ካንተ ማራቅ ውስን አያለፋም
አንተን ከኔ ማራቅ፣ ኑሮ ነው አይገፋም።

(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

(ልቀቀኝ!..አለቅም!)

መስመር አለ ከግሬ' ላይ፣ በደል ሰፈር ሀጢያት ስቀኝ
ካለሁበት ድረስ መጥተህ፣ በህይወት ቃል የጠፈርከኝ
ሰንበር አለ ከእጄም ላይ፣ ስፍጨረጨር የሰነኩት
አለቅህም ያልከኝ ለታ'፣ እንድትለቀኝ የታገልኩት።
                      ;
እኔን መከተል ነው፣ ያንተ የለት' ፍዳ
ካንተ ለማምለጥ ነው፣ የኔ ደሞ እዳ
            ግና በዚህ ሁሉ
አልልህም ለምን ፤ እንዴት አትለቀኝም
ጥያቄ ነው እንጂ መልስስ አያልቀኝም
          ያኔ...ድሮ....ድሮ
          ልቤ ካንተ አድሮ
           የደከምኩ ለታ
እንዳትለቀኝ ብዬ የፀለይኩት ፀሎት
መልስ ይሆናልና መጥቶ ከፀባኦት።



(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

19 Oct, 05:02


ያድርገኝ🙏🙏🙏

እየከዳኝ እንጅ አቅሜ ጉልበቴ
አንተን መምሰል ነበር ለኔማ መሻቴ
ታዲያ ምን ያረጋል  አንሸ ተገኘዉ
ምኞት  አጎደለኝ  ሰዉነቴን ቃኘዉ፡፡
   
   ግን ....ግን....ምንም ማንም ብሆን
  በደሌ ቢሰፈር ባልማርም  ባልድን
  ቆሜ  ብመላለስ  እያለሁኝ  በድን
አልተዋትም  ከፀሎቴ  ያድርገኝን

    አወ  !አልተዋትም
     እየሱሴ !  አንተን የታመነ
    ተቀብሮም አይሞትም😒

ምረት 🙏ምረት 🙏እላለሁኝ እንጅ
  እራሴዉ  ወድቄ  ከደጅ
የምን መላክተኛ ደሞም አማላጅ

  እየሱስ 🙏እዲስ ኪዳላይነዉ
ጌታዬ 🙏አሁን እኔ ያለዉ።

ዳዊት ያንተ ባሪያ ያኔ ሲበድልህ
ያድርገኝ ነዉ እንጅ መቸሌላ አለህ።

   እኔም......!

ሰዉ እንኳን ፈርዶና ተዉኩሽ ማርኩሽ ቢለኝ
ንጉስ  ላያስበዉ ጥፋቴን ቢምረኝ

ትራራልኝ  እንደዉ
ስታይ እንዳልወደዉ
በራሴም በሌላ  ስዳኝስ አልገኝ
ጌታዬ በፊትህ የተጣልኩ ያድርገኝ።

አሜንንንንን 🙏🙏🙏

ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

18 Oct, 17:47


Join the channel 👆👆👆

የገጣሚያን ማኅበር

18 Oct, 17:47


ትንሽዬ ሹክ ልበላችሁ...😊

ዛሬ tik tok ላይ ያየሁት ነገር የዕለቱን ሀሳቤን ገዝቶት ነው የዋለው☹️:: scroll ሳደርግ "ሲምር ይምራል ጌታ ሳያቅማማ ላፍታ ላያስበው መልሶ እንባን ካይን አብሶ ይቅር ይላል ፈውሶ..."እያለች የምትዘምር አንዲት እህት አየሁኝ:: ልቧ ሐሴት እያደረገ ንስሐ እንደመግባት ባለ መልኩ ትዘምራለች:: ጉዞ የፈጠነ ወደ comment...🏃‍➡️🏃‍➡️😁
         - ለማያቅሽ...😒
         - ደፋር...🤨
          -አቤት አይን አውጣነት🙄
         - እንኳንም ምህረት በሰው እጅ አልሆነም🙏
የመጨረሻው comment አስደነገጠኝ:: ምናልባትም ይህች እህት ሕዝብ ያወቀላትን ሀጢአት ሰርታ ሊሆን ይችላል::  ግን የሰው ንስሃ መግባት ለምንድነው ደስ የማይለን?🥺 አንዳንዶቻችን ጌታ በደለኞችን ሲቀጣቸው እንጂ ሲምራቸው ከማየት እንላለን😏:: "ታላቂቱ ነነዌ በሦስት ቀን ውስጥ ትገለበጣለች" ብሎ ንስሐ እንዲገቡ የሰበካቸው ዮናስ... ሰዎቹ ማቅ ለብሰው ንስሐ እንደገቡና እግዚአብሔርም እንደማራቸው ሲያይ ተቆጣ:: "ለምን አልገለበጥካቸውም!😫" የሚል ሙግት ከፈጣሪ ጋር ያዘ:: ጭራሽ በእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ታጋሽነት ምህረተ ብዙነት ይናደድ ጀመር:: ዮናስ ላልለፋባት በአንድ ሌሊት በቅላ በአንድ ሌሊት ለደረቀችው ቅል ካዘነ... እግዚአብሔር እንዴት በሐምሳሉ ለፈጠራቸው ለእጁ ስራዎች አያዝንም🤷 ሳናስብ ወደ ጌታ የሚመጡ ሰዎች በር ዘጊ እንዳንሆን እሰጋለሁ🥺 እንኳንም ምህረት በሰው እጅ አልሆነም😇😇 ከነተሰወረ ክፋታችን ችሎ በምህረቱ ለሚያኖረን...ኤዝጎ🙌
                  ቋጨሁ!😊
                                        

ላትሪያ
https://t.me/amlko000
https://t.me/amlko000

የገጣሚያን ማኅበር

18 Oct, 04:12


Join the channel 👆👆👆

የገጣሚያን ማኅበር

18 Oct, 04:05


"አልጠግብ ባይ፥ ሲተፋ ያድራል" አሉ🤷‍♂። "ሕዝቅያስ" ይባላል የመጽሐፍ ቅዱሱ ወዳጄ ነው😄። ንጉሥ ነው by the way😎.  እናም "ንጉሡ ሕዝቅያስ" ተብሎ ሲጠራ ሞገስ አለው መሰለኝ😁። በእግዚአብሔር ፊት በእውነትና በፍጹም ልብ የሄደ፥ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበትንም ያደረገ ሰው ነበር። ነገር ግን አንዴ እስከሞት ድረስ በጠና ታመመ፤ ይባስ እንደሚሞት፥ በሕይወትም እንደማይኖር ተነገረው።

ይኸው እያነባ፥ እያለቃቀሰ 😢
የ"አትግደለኝ ባክህ🙆‍♂"፥ ስሞታ አደረሰ...
በእንባ ዱብዳ፥ በለቅሶ ሲዘራ
"አትግደለኝ ባክህ"፥ ሙግት ከአምላከ ጋራ...
እንዲያ ደም ሲያነባ፥ እንዲያ ሲያለቃቅስ
የእንባው ዘለላ፥ ጉንጮቹን እስኪያርስ
   ግና...
ምህረትን ሲቀበል፥ "ጆሮ ዳባ ልበስ!" ልብ አደነደነ
ለባቢሎን ምርኮ፥ ለመንግሥቱ መፍረስ፥ ምክንያት ራሱ ሆነ።
እርፍ🫢

በተሰጠን እድሜ ፈቃዱን አድርገን ማለፍ ይሁንልን።
ሰናይ ምሽት😍

ላትሪያ
Join & share👇👇👇
https://t.me/amlko000
https://t.me/amlko000

የገጣሚያን ማኅበር

17 Oct, 18:37


Why poor Reaction 🫤🥹

የገጣሚያን ማኅበር

17 Oct, 18:02


የሚረዳ  ...ሚረዳኝ....

     እኔ  እራሱ  እኔን  ሲዉጥ
     ሳለቅስ  ሳይ ብዙ  ሳምጥ
    ስደገፈዉ  ጎኔ   ሲለምጥ
     አለኝያልኩት  እንደ  ጤዛ
     ሸንበቆነዉ  ሰዉም ዋዛ።

    እንደሆነ  ቀድሞ  አዉቆ
    የሚረዳኝ  ከኔጠልቆ
    አንዳች   የለም   ምንም
     ማንም!

    የሚረዳኝ  የሚገባዉ
    የዉስጤ  ድጥ
    አንተዉ ጋርነዉ
    ሩጨ  ማመልጥ።


ጌታዬ ሆይ...
ይሄነን ሳይ....

ያልተረዳኝ
ልርዳሽ  ቢልስ
ቢያለቅስልኝ
እንባን ቢያፈስ

የ ይምሰልነዉ ከላይ ከላይ
ለሱምለሰዉ ሲል እንዲታይ

ካንተበላይ  ማን? ሊረዳኝ
ሊረዳኝስ  ባለሜ ዉስጥ
አብሮኝ ሚያለቅስ  አብሮኝ ሚያምጥ
ያንተ ፍቅር  እንዲህ  ታይቷል
  ጣርህራሱ  መስቀል ወጥቷል።

    አንተብቻ ....

ምትረዳ  ...የምትረዳኝ

ስለዚህም  ከኔ  አትራቅ🙏
ከፈቃድህ  እንድ ጣበቅ
ያንተን በኔ ትቸ እንዳለቅ

ሆዴን ብሶት ባር ባር ሲለኝ
የሚረዳ የሚረዳ ስለሌለኝ!


ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

16 Oct, 17:59


ሰላም ሰላም ዛሬም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ተሳተፉ አትፍሩ👏👏

1ኛ ቆሮንቶስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ የፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ
#በቤተ_ክርስቲያን #የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁናል ታስቀምጣላችሁን?
⁵ አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ።

ፓውሎስ ይሄንን ሲል ምን ማለቱ ነው በቤተ ክርስቲያን የሚናቅ ሰው አለ?🤔

የገጣሚያን ማኅበር

16 Oct, 15:37


የሕይወት ማስታውሻ

የሰው ልጅ ከሞተ በኋላ በ3ኛ ቀን ጥፍሩ መነቃቀል ይጀምራል በ4ኛ ቀን ጸጉሩ  ይራገፍና ጭንቅላቱ ባዶ ይቀራል በ5ኛ ቀን አእምሮው እንደ ቅቤ መቅለጥ ይጀምራል በ6ኛ ቀን ቆዳው ጠቁሮ መላላጥ ይጀምራል በ7ኛ ቀን የውስጥ አካሉ ሁሉ ይበሰብስና እጅግ በጣም መሽተት ይጀምራል! በ60ኛ ቀን ሥጋ ሁሉ ሸሽቶ ብዙ አጥንቶች ብቻቸውን ይቀራሉ!!

ይህንን መራራ እዉነት እያወቅን:-ከኩራት ከስግብግብነት ከክፋት ከጥላቻ ከራስ ወዳድነት ከተንኮል ... ብንርቅ   አይሻልምን ? ምንም ማንም ብትሆን መጨረሻህ መበስበስ ነው።

በነገሮች ሁሉ ትሁት እንሁን! ዝቅ ማለትን ከክርስቶስ ብትማር ዛሬ ላይ የምትኖረው ወዳቂ  ሕይወት አትኖርም ክርስቶስ ለጊዜው ዝቅ ብሎ ለዘላለም ከብራል። በሰዎች ሕይወት  በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር እንትጋ! ጠንካራ ጎበዝ ነኝ ብለህ አትኩራራ የሁሉም መጨረሻው መበስበስ ነው።በመኖርህ ሰይጣን እንጅ ፈጽሞ ሰው አይከፋ።

ይህቺ የምናያት ህይወት ከንቱ ናት። ይህቺ ዓለም ጊዜያዊ ድንኳን ናት። በዚህች ዓለም ሰዎች እርስ በርስ የሚተላለቁት ለ2 ነገሮች ብቻ ነዉ ፦ ለስልጣንና ለሀብት። ሰዎች ለስልጣንና ለሀብት የንፁሐን ደም ያፈሳሉ። ሰዎች ለስልጣንና ለሀብት ከፈጣሪ ጋር ይጣላሉ። ሰዎች ለሴልጣንና ለሀብት ኃጥአት ፤ ወኝጀል ፤ ነዉር ይሰራሉ። ታሪክ እንዳይወቅስህ ተጠንቀቅ ከሁለቱ አንዱን ባገኘክ ቁጥር በርትተህ ጌታን ፍራ።

ነገር ግን ስልጣንና ሀብት ወደ ዘላለማዊ ሕይወት አያስገቡም። ከዚህ ዓለም ስንለይ ወደ ዘላለም ህይወት ወይም ወደ ዘላለም ሞት መሄድ ምርጫችን ነው! ደግሞም ይህ እውነታ አይካድም። የት እንሄዳለን? መልሱን ለእናንተ እንተዉላችሁ! ክርስቲና ሞተ እንዳትኖር፤ ኖረህ ሙት።

         🧎‍♀በቀኝ እደሩ🤲
        ሶለን ጥቅምት 3/2017


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

15 Oct, 17:58


ጓደኞቻችሁን ወደ ዋናው መወያያ ጉሩፕ ይጋብዙ ወይም Add ያድርጉ
https://t.me/yegetamianmahiber

የገጣሚያን ማኅበር

15 Oct, 16:53


የትኛዉ ? ልምዴነዉ።

       መታቀፍ    በጀታ
እንዲ ሚያስለቅሰኝ
ባይኔ  መንታ መንታ።

ጉልበቴን  የሚያርድ
ልቤን   የሚረታ።

ሰዉ አጣሁኝ  ብዬ
ስነፋረቅ  እራሴን አዬው
አለማወቅ  ከመንገዴ
እንደዘገየዉ

ሲገባኝ....!🙄


ፀሎቴ 🙏 ይሄነዉ
ጌታ  የልቤን  አይን
እንዲያበራዉ

ያየሁትን  ሳይሆ
ያየልኝን  ላይነዉ።


ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

15 Oct, 15:51


የት ደርሰሀል🎼
    እመጣለሁ ብለህ ተስፋን
        ሰጥተኸናል
    ጌታ ሆይ ቶሎ ና ናፍቆት ብሶብናል
    አባቴ ጋ ሄጄ መኖሪያን ላዘጋጅ
  ቤታአልባ እንዳትሆኑ ቤታችሁን ላበጃጅ
  ብለህ ከሄድክ እኮ ሁለት ሺ አለፈ
   ዘመን እንደዋዛ በጀልባ ቀዘፈ
  መቼም እስካሁንስ መንገድ ጀምረሀል
  ጌታ ሆይ ንገረን ልናይህ ጓጉተናል
   ከሰማይ ሰማያት ነውና ምትመጣው
  አሁን የደረስከው የትኛው ሰማይ ነው
   ከሄድክ በኋላ ምድርን ብታያት
  ውጥንቅጧ ወጥቷል ብትመጣም
          አታውቃት
  ሰይጣን ተመችቶት ሲኦል አደረጋት
  እኛም ግራ ገባን በቤትህ እየኖርን
  አንዱ ይመጣና ከጌታ ነኝ ብሎን
  ጳውሎስ ነው ትክክል ሌላው ሁሉ ስተት
  ብሎ ይለንና ያስጠፋናል ከእውነት
  ደግሞ እንደገና ሌላው ይነሳና
  እንዲህ ነው ይለናል የኛ ክርስትና
   አንዴ ከዳናችሁ በቃ ድናችኋል
ሁል ጊዜ ንሰሀ ምን ይጠቅማችኋል
  ዳግም ሀጢያትን ብትሰሩም ባትሰሩም
  ከዘላለም ህይወት በፍፁም አትቀሩም
  እያለ ይልና ጠፍተን እንድንቀር
         ያደፋፍረናል
  ቃልህን አጣሞ ወንጌል ይሰብከናል
  ነብዩም ሳትለው ተብያለው ብሎ
ያሰናክለናል እውነትን አስጥሎ
  የዝማሬው ነገር ይቅር አይወራ
ግጥምና ዜማው ከሙዚቃው ጋራ
ትወደዋለህ ወይ ብለን ሳንጠይቅህ
ለኛ ስሜት ስንል እየዘመርንልህ
ለክብርህ ሚመጥን መስዋእት
           ከለከልንህ
        ጌታ የት ደርሰሀል?
እንዲህ ምንጠይቅህ እጅጉን አብዝተን
እዚህ ደርሻለሁ ብለህ ያልከን እንደው
ድንገት ብንደነግጥ ብንፈራ ብለን ነው
እኔ የንትና ነኝ እሱ ደግሞ የገሌ
ማለት አብዝተናል ሆነናል አለሌ
እሱ የወደቀለት እኛም እንደምንወድቅ
አሳዳጊ ሳይኖር ዛፍም እንደሚደርቅ
ተካይም አጠጪም በከንቱ
             እንደሚደክም
ጳውሎስ ቢነግረንም እኛ አልሰማነውም
ከቃልህ ተጣልተን ፀሎትም አቁመን
እውነተኛ አምልኮ ማቅረብም አቅቶን
ሰውና ሰይጣንም ድካማችን ገብቶት
ለከንቱ ቁሳቁስ ያስሮጠው ጀመረ
       ትውልዱን አስቶት
ብንሞትም ለጌታ ማለት ተስኖናል
በመጠንም መኖር እምቢየው ብለናል
ያኛውንም ለኔ ይሄኛውም ለኔ አልጠግም
        ብለናል
  እዚህ ደርሻለሁ ብለህ ያልከን እንደሁ
          ያስደነግጠናል
   እባክህ ንገረን ጌታ የት ደርሰሀል
  ትዝ ይለን እንደው ነው ሙሽራ እንዳለን
  ሚዜዎቼ ናችሁ እንዳተኙ ያለን
  ነቅታችሁ ጠብቁኝ መብራት
          አብርታችሁ
ሌባ እንደሚመጣ ነው ምመጣባችሁ
  ብሎ ያለን አምላክ ትዝ ይለን እንደሆን
  እገሌና እገሌን መከተልም ትተን
ነብይና ፓስተር መምሰልን አቁመን
  በፀሎት በርትተን በእምነትም ፀንተን
አንተንም ለመምሰል ራስን በማስለመድ
ዝግጁ እንድንሆን ነው ለእውነተኛ
            አካሄድ
  የት ደርሰሀል ምንል አጥብቀን
            ምንጠይቅ
ስትመጣ እዳታፍር  ከእኛም አንዳትርቅ
           ጌታ የት ደርሰሀል
እዚህ ደርሻለሁ ብለህ ያልከን እንደሁ
             ያስደነግጠናል
ይቀሰቅሰናል ይሆንና ደውል
             
          
                     ተፃፈ👩
                        በእጅጋየሁ አለሙ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

14 Oct, 18:42


ሰላም እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ለመመለስ አትፍሩ ዝም አትበሉ ተሳተፉ😊 ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ ሁሌም የምታደርጉት ነገር ነው።

ለምንድነው መንፈስ ቅዱስ ና የምንለው የትስ ሄዶ ነው🤔?

የገጣሚያን ማኅበር

14 Oct, 18:16


እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እግዚአብሔርም ሰማኝ።
— መዝሙረ ዳዊት 55:16


          @worlds_light
          @worlds_light
join & share 💫💫💫

የገጣሚያን ማኅበር

13 Oct, 18:58


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

13 Oct, 17:52


ከጭጋጋማው ደመና በላይ ጸሐይ አለ

ብዙ ጊዜ አስቸጋሪ መንገድን ለብቻችን አልፈን ይሆናል ተስፋ ቆርጠን ከሰወ መካከል ወጣ ብለን አልቅሰንም ይሆናል። ይደግፈናል ብለን ያመንነው ነገር ተሰብሮ ወግቶን ይሆናል። የማይነጋ ጨለማ ከፊታችን የተጋረጠ ልመስል ይችላል። የመከራ ብዛት ናራችን ሀላ ሊያዞር ይችላል።አስተውሉ ዮሰፍን ተመልከቱ እስከ ግብጽ ለባርነት ተሽጦ ነበረ በኃላም ገዥ ሆኖ ተሾመ። ዳዊትን ተመልከቱ ብዙ ስደትና መከራ ከሳኦል ደርሷል በኃላም ንጉስ ሆነ።ኢዮብን ተመልከቱ ከእጁ የወጣ ሁሉ በሁለት እጥፍ ተመለሰ።... እናም በዛሬ ሁኔታችሁ የነግያችሁን ተስፋ አትቁረጡ። መቼም ብሆን ከጭጋጋማው ደመና በላይ ጸሐይ አለ።❤️😊

በጌታ ክብር እደሩ
ሶለን ጥቅምት 1/2017

Link for our YouTube channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

13 Oct, 05:33


እስቲ ሁላችሁም በዝህ ርዕስ ግጥም ጽፉልኝ እስከ ሀሙስ አድርሱ ተባረኩ። ጽፋችሁ ስትጨርሱ @S_o_L_e_N_y 👈 ላኩልኝ። ለደቀ መዛሙርት ምርቃ ፕሮግራም ተፈልጎ ነው።

የገጣሚያን ማኅበር

12 Oct, 18:06


አንድ ቀን ውዱ ሙሽራችን በደመና ይመጣል እኛም ከዓለም መከራ ለዘላለም እናርፋለን። ደስታችን ሙሉ ይሆናል። በጆሮ የሰማናውን የሰማይ ቤታችንን በዓይናችን እናያለን። ለዝህም ዘውትር ማራናታ እንላለን። ታገሱ ሁሉም ያልፋል በመጨረሻም አሸናፊዎች እኛ እንሆናለን❤️🙏

Link for our YouTube channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

የገጣሚያን ማኅበር

12 Oct, 16:07


“For I know the plans I have for you,” declares the Lord, “plans to prosper you and not to harm you, plans to give you hope and a future.”
Jeremiah 29 : 11
Amen 🙏🏼🙏🏼

Link for our YouTube channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA