Ethiopian Kale Heywet Church Head Office @ethiopiankaleheywetchurch Channel on Telegram

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

@ethiopiankaleheywetchurch

This is the offical Telegram Page of the Ethiopian Kale Heywet Church#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@heywettv
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/@ethiopianka

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office (Amharic)

የኢትዮጵያ ካሌ ሐውተ ቤተ ክርስቲያን በመንካዶን አስተዳደር ቤተመንግሥት ቦታ የተገኘ በቴሌግራም ፕሮፓጭስን በሚገኘው መረጃ ይግባኝ። በዚህ መረጃ ከታመነ ዝርዝር አልተመረጡም፤ ይህ ቦታ ከኢትዮጵያ ካሌ ሐውት ሀገር ማን ነው? ምን ነን? የምንሰራቸውን መረጃ ይከታተልናል። የቴሌግራም እርዳታዎችን አማርኛ ወደ አማርኛ እንታይ ማድረግ ከመፍጠር እገዛና በማስተዳድ። የፌስቡክ ንግግር ቡድን ለእነዚህ መረጃ እንጠቀሙ። ድምፅም ከትኞቹ እስከዚያ ጠቃሚ ትላልቅና ንግግርዎቹን ያሳተፉና እንቅስቃሴዎቹን ማስገልገል እንችላለን። በመወዳወል በፍጥነት እንዲመሠረት ከእናቶ እስከ ቤተሰቦ መጣች።

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

30 Jan, 13:23

https://youtu.be/3tgYvLcXiIQ

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

23 Jan, 15:43

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ከጥር 7 እሰከ 11/ 2017 ዓ/ም አመታዊ የተሃድሶ ፤ የፆምና ጸሎት ኮንፍራንስ በደቡበ ሸዋ ቀጠና አካሄደች ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የብሄራዊ ቦርድ አባላት የዋናው ጽፈት ቤት መምሪያ ክፍል ሃላፊዎች ፤ የጸሎት ቡድኖች ፤ የየቀጠናው አመራሮች ፤ የዘርፍ አገልጋዮች ፤ ልዩ ህብረቶች የተወከሉ ወገኖች ፤ ከውጪ ሀገር የአለም አቀፍ የጸሎት ኮሌጅ አገልጋዮች ፤ የኢ/ቃ/ ህ/ ቤ/ክ የቀድሞ መሪዎች ፤ የእምነት አባቶችና እናቶች ተገኝተዋል። ይህ ለ15ኛ አመት የተካሄደ የ14ኛ ዙር መረሃ ግብር ነው ተብሏል ፡፡
በመረሃ ግበሩ ላይ የጸሎት ርዕስ የነበረው የ97 አመት የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዞ አስመልክቶ ጌታን ማመስገን ፤ 15 ዓመታት ሙሉ የተሃደሶ ጾምና ጸሎት አገልግሎቱ ስለዘለቀ ፤ ጌታ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወትን ቤተ ከርስቲያን ስላሰፋና ስላሳደገ ተመስግኗል ፡፡
እንዲሁም ሥር ነቀል ተሃደሶ እንዲመጣ ፤ እርቅና ይቅርታ እንዲሰፍን የተጸለየ ሲሆን የምልጃ ጸሎትና ንስሃ የመግባት ጊዜም ተካሄዷል ፡፡
ሌላኛው የጸሎት ርዕስ የሀገር ሰላም ፤ የሃገር ልማት አድነት እንዲመጣ ፤ ማህበራዊ ቀውስ እንዲወገድ ፤ ግጭቶች እንዲቆሙ ፤ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዲወገድ ፤ የአለም ሙቀት መጨመርን ለመቀነስ እና በተለያዩ የጸሎት ርዕሶች ላይ ጸሎት ተደርጓል።

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

22 Jan, 08:01

የሐዘን መግለጫ
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በዕጩ ዶክተር ይስሐቅ እንድሪያስ ህልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገለጸች፡፡
ዕጩ ዶክተር ይስሐቅ እንድሪያስ ወዳገለገሉት ጌታ በክብር መሰብሰባቸው የሚያኮራ ቢሆንም ድንገተኛ ህልፈታቸው ግን ወገኖችን ሁሉ እንዳሳዘነና ጥልቅ ሐዘንም እንደተሰማቸው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት ዶክተር ጣሰው ገብሬ፣ ምክትልነ ፕሬዚዳት ዶክተር ስምኦን ሔሊሶና ዋና ጸሐፊው ዶክተር ስምዖን መላቱ ገልጸዋል፡፡
ዕጩ ዶክተር ይስሐቅ እንድርያስ በወላይታ ቀጣና ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በምክትል ዋና ጸሐፊነት፣ መንፈሳዊ ዘርፍ ኃላፊነትና በወላይታ ኢቫንጀሊካል ሴሚናሪም ደግሞ አካዳሚክ ዲን ሆነው የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በትጋት በመወጣታቸው የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ ሆነው ሲታሰቡ እንሚኖሩ ያስታወቀው መግለጫው፣ ከፑላሳ ክፍለ ማህበር እስከ አገር አቀፍ ድረስ ያገለገሉ ዕጩ ዶክተሩ በሕንድ አገር ሕክም ሲከታተሉ ቆይተው በሃይማኖታቸው እንደጸኑ ወዳደለገሉት ጌታ በክብር መሄዳቸውም የሚያኮራ እንጂ ልብ የሚሰብር እንዳልሆነ አስታውቋል፡፡
ወንድማችን ይስሓቅ በእምነት የበረታና ትጉህ አገልጋይ ነበረ ያለው መግለጫው ለቤተሰቡ አባላት፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለወላይታ ቃለ ሕይወት እና ለመላው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

21 Jan, 09:03

በኢት/ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት 50ኛ አመት የምስረታ በዓል በደቡብ ምስራቅ ሸዋ ቀጠና በኤርጊራና የሀድሮ ከተማና ዙሪያ አጥቢያ ቤ/ክ ህብረት በደማቅ ተከበረ ።
በኢት/ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት ክፍል 50ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ መዋቅሮች እየተከበረ ይገኛል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢት/ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላቱ በእንግድነት የተገኙ ሲሆን በደቡብ ምስራቅ ሸዋ ቀጠና ሰብሳቢ ተገኝ ላሚሶ ፤ የቀጠናው ም/ክ ሰብሳቢና ኤልጌሉና የሀደሮ ከተማና ዙሪያ አጥቢያ ቤ/ክ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ጸጋዬ ዶሌ ተገኝተዋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ ዶ/ር ስምዖን ሙላቱ የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈሉ ሲሆን የህብርት ወጣቶት መዘምራን በዝማሬ አገልግልዋል ።
በህብረቱ ወጣቶች አስተባባሪነት ለረዥም ቀናት ጾም ጸሎት የተደረገ ሲሆን የሀደሮ ከተማና አካባቢን የማጽዳት ስነ-ስርዓት ተደርጓል ።
የኢት/ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላቱና በቀጠናው በወንጌል አገልግሎት ብዙ ዋጋ ለከፈሉ አባቶቸና እናቶች ከህብረቱ የወጣቶች አገልግሎት ከፍል ስጦታ የተበረከተ ሲሆን የቡራኬና የጸሎት ጊዜም ተደርጓል ።

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

28 Dec, 14:37

https://youtube.com/live/IVDfXLOwj1s?feature=share

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

27 Dec, 08:44

https://youtube.com/live/ZygUUCgXCBU?feature=share

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

18 Dec, 06:42

የመታሰቢያ  ፕሮግራም
ነገ ዕሮብ ታሕሳሰ 9/2017 ዓ.ም ለዮሐንሰ ደምሴ ማዴ  በኢንተርናሸናል ኢቫንጀሊካል ቤ/ክ ( lEC ) ከቀኑ 8:30 ጀምሮ የመታሰቢያ  ፕሮግራም ሰለተዘጋጀ በዚያ በመገኘት የሽኝት ፕሮግራም  ይካሄዳል ። እያፅናናችሁንን ላላችሁና በተለያያ መንገድ አብራችሁን የሆናችሁንን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ።

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

12 Dec, 09:34

https://youtu.be/yKuE_3U28b4

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

04 Dec, 08:35

https://youtu.be/akVnC4_KIC4

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

28 Nov, 11:50

https://youtu.be/WUd16_0n_K4

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

22 Nov, 09:14

https://youtu.be/Dp2765V_9hk

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

20 Nov, 13:48

በወቅታዊ የይዞታ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ቃ/ሕ /ቤ/ክ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስመዖን ሙላቱ መግለጫ ሰጡ ‍
ከ36 አመት በላይ የኢትዮጵያ ቃ/ሕ /ቤ/ክ ህጋዊ ይዞታ ሆኖ የቆየው ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የቢሾፍቱ አስተዳደር ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ 20 ሺ ካሬ መሬት ቆርጦ በመወሰድ ለግለሰቦች መስጠቱ ይታወሳል ። ይህም ድርጊት በብዙ የወንጌል አማኞች ዘንድ ቁጣና ጥያቄ አስከትሎ ቆይቷል ። ‍
ይህ ሁኔታ ያሳዘናቸው የወንጌል አማኞች የተላያዩ ማህበራዊ ሚድያዎችን በመጠቀም ድርጊቱን በማውገዝ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። ‍
ነገር ግን እስካውን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት አካላትና፣ የኦሮሚያ ክልልና የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ምላሽ አለመስጠታቸው ነግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታታል። ‍
ይህ በእንዲ እንዳለ ሰሞኑን የተወሰደው መሬት ተመልሷል የሚሉ ሃሰተኛ መረጃዎች በስፋት በማህበራዊ ሚዲያዎች በመሰራጨታቸው በርካታ ወገኖች መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።‍
ጉዳዩ እልባት አለማግኙቱንና በወንጌል አማኙ ዘንድ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ቃ/ሕ /ቤ/ክ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስመዖን ሙላቱ ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም መግለጫ ሰተዋል ።

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

18 Nov, 09:18

https://youtu.be/nat8NZmE16s

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

07 Nov, 09:24

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አጋር የሆነው DML  ኢንተርናሽናል ከ17 የአለማችን አገራት የተወጣጡ የአገልግሎቱ አገር አቀፍ አስተባባሪዎች አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤአቸውን በቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል አካሄዱ።
DML  የስራ ሰዎችን ደቀ መዝሙር የማድረግ አገልግሎት   55 አስተባባሪዎች ከተለያዩ የአለማችን አገራት ለሪፖርትና ልምድ ልውውጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ በኩሪፍቱ ማዕከል ጉባኤአቸውን አሄደዋል።
እንግዶቹ ከጉባኤው በፊት በጎተራ፣በለቡና በጀሞና አካባቢዋ በኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ አጥቢያዎች የእሁድ አምልኮ ስፍራዎች በመገኘት ተካፍለዋል ።
በኩሪፍቱ ማዕከል በተካሔደው የመክፈቻ መርሃ ግበር ላይ  የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላቱ እንግዶችን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በፕሮጀክተር የተደገፈ ታሪካዊና ጠቃሚ መረጃዎችን አቅርበዋል።
የዲኤም ኤል አገልግሎት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቀስ በቀስ  ከቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅሮች፣ መምሪያዎችና ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ፍሬአማ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ለታዳሚዎቹ አንስተዋል።
  የኢት/ቃ/ሕ/ቤ/ክ የሙያተኞች አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት መጋቢ ዮሴፍ በቀለ በበኩላቸው   አገልግሎቱ ከተጀመረ ሰባት አመታትን እንዳስቆጠረና ስለ አጀማመሩ ከተናገሩ በኋላ በሰባቱ አመታት የመጡ ውጤቶችን በጥቂቱ አንስተዋል።
እንዚህም  ለግል የጽሞና ጊዜ መስጠት፣ የቤት ውስጥ ቤተ ክርስቲያንን ማጠንከር፣ ስራን በጽድቅና በእግዚአብሔር መንገድ መስራት፣ በአስራት፣ በስጦታዎችና በወንጌል አላላክ ፣ በኢኮኖሚ ማደግ ፣ ታማኝ ግብር ከፋይ በመሆን ለአገር ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከትና የመሳሰሉት ፍሬዎች መታየታቸውን ገልጸዋል

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

05 Nov, 15:27

https://youtu.be/ySnYBR1UtrM

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

04 Nov, 07:59

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል የቦርድ አባላት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከልን ጉብኝት አደረጉ

ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል የቦርድ አባላት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የተሰሩ የልማት ስራዎቸን ተዟዙረው ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ፀሃፊ በዶ/ር ስምዖን ሙላቱ እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የማዕከላት ኃላፊና የኩሪፍቱ ማዕከል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ግርማ መሪነት ጉብኝቱ የተካሄደ ሲሆን በማዕከል የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ሰራዎች በሰፊ ቅኝት ተደርጓል። በተለይም የእንግዳ ማረፊያዎች ፣የእርሻ ውጤቶች የቦርድ አባላቱ ጉብኝት ካደረጉባቸው መካከል ተጠቃሽ ናቸው ።

ይህ በእንዲ እንዳለ በቢሾፍቱ አስተዳደር አላግባብ የተወሰደው የማዕኩሉ መሬት በተመለከተ የቦርድ አባላቱ ፍትህ እስኪሰጥ ጉዳዩን እንደሚከታተሉ እና ድምፃቸውን ማሰማታቸውን እንደሚገፉበት በመግለጽ ጉዳዩ እስካውን እልባት አለማግኙቱን በማንሳት ሁሉ የወንጌል አማኞች በጸሎትና ድምጻቸውን ማሰማት መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

31 Oct, 14:13

❗️❗️ሁላችሁም HEYWET TV የሚለውን የዩትዩብ ቻናላችንን subscribe እና share በማድረግ የጌታን ወንጌል አብረውን ይስሩ❗️❗️ከላይ pin የተደረገውን QR code ስካን በማድረግ ሁሉንም የማህበራዊ ገጾቻችንን ማግኘት ይችላሉ፡፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

31 Oct, 12:07

https://youtu.be/T76KxbnlQfE

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

29 Oct, 14:38

በኢት/ቃ/ሕ/ቤ/ክ አዲስ አበባ እና አካባቢው ቀጠና የሴቶች አገልግሎት ክፍል ከቢሊ ግርሐም ኢቫንጀልስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር የወንጌል ስርጭት ስልጠና ሰጠ ።
መርሃ ግብሩን በጸሎት ያስጀመሩት የአዲስ አበባ እና አካባቢው ቀጠና የሴቶች አገልግሎት ክፍል ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ብሩክ ቴራጎ እና የቀጠናው ዋና አስተባባሪ ወ/ሮ የሮማንወርቅ እንድሪያስ ናቸው ።
የስልጠናው አላማ ሴቶች በአዲስ አበባ እና አካባቢው ቀጠና ዙሪያው በሚገኙ ስፍራዎች ላይ የታላቁ ተልዕኮ {ወንጌል} አውቀውና ተረድተው ለሌሎች መመስከር እንዲችሉ ለማስታጠቅ ነው።
ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና ከ167 በአዲስ አበባ እና አካባቢው ቀጠና የተውጣጡ ሴቶች ተሳትፈዋል።
መርሃ ግብሩ የተከናውነው በኢት/ቃ/ሕ/ቤ/ክ ዋናው ፅ/ቤት ሲሆን ከግሬት ኮሚሽን የተውጣጡ አሰልጣኞች ስልጠና ሰተው ለስርጭቱ አጋዥ የሆኑ ቁሳቁሶችንም ለተሳታፊዎች አበርክተዋል

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

28 Oct, 13:21

https://youtu.be/NMG40stVJkM

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

25 Oct, 14:53

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የልጆች አገልግሎት ክፍል በአዲስ አበባና አካባቢው ለሚገኙ የህብረት አጥቢያ የልጆች አገልግሎት መሪዎችና አገልጋዮች ስልጠና ሰጠ
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የአገር አቀፍ የልጆች አገልግሎት ክፍል አስተባባሪ የሆኑት መጋቢ ማርቆስ አበበ እንደተናገሩት ሥልጠናው የተሰጠው በአዲስ አባባና አካባቢው በህብረቶችና አጥቢያዎች ላይ ለሚገኙ የልጆች አገልግሎት ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አገልጋዮች መሆኑን ተናግረዋል ።
ሁለተናዊ የልጆች አገልግሎት ራሱን የቻለ አገልግሎት ተደርጎ በጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ከተደራጀ ከ15 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የተናገሩት መጋቢው ፣ በእነዚህ ዓመታት በአዲስ አበባና አካባቢው ህብረቶች ላይ መደራጀት የጀመረው ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሆኑን ተናግረዋል።

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

21 Oct, 12:26

https://youtu.be/RrF_u_H4p-E

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

17 Oct, 14:25

https://youtu.be/4b5oDQgI9Z0?si=ouhyVlcIDOtfUWHw

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

16 Oct, 12:51

https://www.youtube.com/watch?v=72q1c1u17xY&t=4s

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

16 Oct, 11:25

https://youtu.be/_0k47qof6JA

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

16 Oct, 09:36

ይህንን QR code ስካን በማድረግ ሁሉንም የማህበራዊ ገጾቻችንን ማግኘት ይችላሉ

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

16 Oct, 09:31

https://youtu.be/Xr5m3LLcAyg

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

22 Aug, 08:46

በኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሙያተኞች አገልግሎት ክፍል ለጋስነት በተሰኘ ርዕስ የሁለት ቀን ስልጠና ተካሔደ።
ስልጠናው የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሙያተኞች አገልግሎት ክፍል ከላይፍ ኢን አባንዳንትጋር ባደረገው አጋርነት የተዘጋጀ ሲሆን ከአዲስ አበባ ቀጣና ከአራቱም ህብረቶች የተወጣጡ 35 መጋቢዎች በስልጠናው ተካፍለዋል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ወንድም ረታ ጳውሎስ በአምልኮ ዝማሬ ያስመለከ ሲሆን የአዲስ አበባ ቀጣና ዋና ጸሐፊ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ይህ ስልጠና አይን ከፋችና በለጋስነት የሚታጨዱ ድሎችን ለማጣጣም አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

አሰልጣኞች ፓስተር ሮበርት ከኬኒያ ላይፍ ኢን አባንደንስ የስልጠና ፕሮግራም አስተባባሪና የሙያተኞች አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት ፓስተር ዮሴፍ በቀለ ሲሆን የለጋስነት ማዕከልና ለምንና እንዴት እንለግስ በሚሉ መሪ ሀሳቦችን አቅርበዋል።
ስልጠናው በዋናነት
ለጋስነት ወንጌል መሆኑን
ለጋስነት ደቀመዝሙርነት መሆኑን
ለጋስነት ጥገኝነትንና ድህነትን ማርከሻ መድሀኒት መሆኑንና
ለጋስነት ሀብትን ለሚፈለግ ዓላማ የምናሰባስብበት በር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ላይ ያተኮረ ነበር።
በመጨረሻም መጋቢዎቹ ስለስልጠናው ጠቃሚነት የተለያዩ አስታየቶችን ከሰጡ በኋላ ስልጠናው የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል።
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@heywettv
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/@ethiopiankalehiwotchurch
ይከታተሉን፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

22 Aug, 06:17

በሀዋሳ እና አካባቢዋ ላላቹ የሕብረት መዘምራን በሙሉ የተላለፈ የሕብረት መዘምራን ስልጠና እና የአምልኮ ምሽት ከሪትም ሀገር አቀፍ መዘምራን ሕብረት ጋር
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@heywettv
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/@ethiopiankalehiwotchurch
ይከታተሉን፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

16 Aug, 17:06

ዜና እረፍት
ጋሽ ወልደ አምላክ ዲኬ በዘሬው እለት ወዳገለገሉት ጌታ ተሰብስበዋል
የኢትዮጲያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በጋሽ ወልደ አምላክ እረፍት የተስማንን ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዱ ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን
ለሁሉም ስው እንዲደርስ ሼር በማድረግ አብረውን ይሁኑ
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@heywettv
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/@ethiopiankalehiwotchurch
ይከታተሉን፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

14 Aug, 13:43

በዘማሪ አገኘው ይደግ አዲስ አልበም ላይ የተስጠ ሂስ ክፍል አንድ | singer Agegnew Yideg | Heywet TV | Pastor Merhawi Neguse
https://youtu.be/BmQj-jRCmh0
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@heywettv
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/@ethiopiankalehiwotchurch
ይከታተሉን፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

30 Jul, 06:44

የመራሐቸው መፅሀፍ ትረካ ክፍል አንድ በደረጀ አበበ
የመራሐቸው መፅሀፍ የቀድሞ የመሰረተ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የአሁኗ ጌጃ ቃለ ሕይወት አባቶች ቀደምት ታሪክ በጣም ብዙ ካልታዩ ምስሎች ጋር በትረካ የቀረበ ሲሆን የጽሁፍ ዝግጅቱን እንዲሁም ትረካውን ተወዳጁ ወንድም ደረጀ እንዲ አቅርቦልናል
ለሁሉም ስው እንዲደርስ ሼር በማድረግ አብረውን ይሁኑ
https://youtu.be/S10qTtivNfI

ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@heywettv
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/@ethiopiankalehiwotchurch
ይከታተሉን፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

26 Jul, 09:22

መንግስት ዋ ሊባል ይገባዋል?
https://youtu.be/gmCdwywqlsQ

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

26 Jul, 07:37

ከኢትዮጲያ ወንጌላውያን ዘማሪዎች እና ሙዚቀኞች ማህበር ስለ ኩሪፍቱ ማዕከል የተስጠ መግለጫ
https://youtu.be/x6JFu3rjb8M

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

26 Jul, 06:28

የኢትዮጲያ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ማስጠንቀቂያ ስጠ የካውንስሉን ሙሉ መግለጫ ይመልከቱ
https://youtu.be/gmCdwywqlsQ
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@heywettv
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/@ethiopiankalehiwotchurch
ይከታተሉን፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

25 Jul, 11:29

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ብሔራዊ ቦርድ የአቋም መግለጫ

https://youtu.be/1jKKxg5fPm8

ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@heywettv
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/@ethiopiankalehiwotchurch
ይከታተሉን፡

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

25 Jul, 09:26

የቃለ ሕይወት ኩሪፍቱ ወቅታዊ ጉዳይ‼️
ሐምሌ 18/2016
መጋቢ ጌትነት ለማ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በጎፋ ዞን፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬቶ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት በደረሰው አደጋ ካውንስሉ የተሰማውን ሃዘን በመግለፅ፤ በአደጋው ለተጎዱ ወገኖቻችን ማቋቋሚያ የሚሆን ድጋፍ እያሰባሰበ እንዳለ መጋቢው በመግለፅ፤
በዋናነት ዛሬ መግለጫ ሊሰጡ ወደ ተዘጋጁበት የቃለ ሕይወት ኩሪፍቱ ጉዳይ በማምራት፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላለፉት 90 ዓመታት በላይ በተለያዩ ማኅበራዊ እና የልማት ስራዎች ላይ የተሰማራች መሆኗን በመግለፅ እንዲ ያሉ ተቋማትን በልማት ስም መክሰስ የሃይማኖት ተቋማትን የልማት እንቅስቃሴ ከመናቅ እና ወንጌላውያን አማኞችን የማይወክል መሆኑን አንስተዋል።
በመግለጫቸው እስከ አሁን የተጀመረ ምንም ዓይነት ንግግር አለመኖሩን በመገንዘብ፤ ከከተማ መስተዳደሩም ሆነ፣ ከክልሉ መንግስትም እንዲሁም ከፌደራል መንግስት የተሰጠ ምንም ዓይነት ምላሽ አለመኖሩን በመገንዘብ ወንጌላውያን አማኞች ሰላማዊ በሆነ መልኩ ጥያቄያቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዩን ዕግድ በፍርድ ቤት አሰጥታ በፍርድ ቤት እየተከታተለች ቢሆንም ጉዳዩ የክልሉን እና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን የሚፈልግ በመሆኑ ማንኛውም የወንጌላውያን አማኝ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጎን በመቆም ድምፅ በማሰማት የተጀመረውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
ህዝብን በማደናገር እና የወንጌላውያን አማኞችን ለመከፋፈል እና የተጀመሩ ሰላማዊ ጥያቄዎችን ለመቀልበስ ተገቢ ያልሆነ መልዕክት እያስተላለፉ በሚገኙ የሚዲያ ተቋማትን በተመለከተ ህጋዊ የሆነ አካሄድ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት መሰል ስራ ላይ የተሰማሩ የሚዲያ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አንስተዋል።

Ethiopian Kale Heywet Church Head Office

25 Jul, 07:33

https://youtu.be/1UwzVUk8sv4?si=vKCyCHQU3V3qMQxI