ህዳር 12-2017ዓ.ም። ዕለተ-ሐሙስ
[አጉልዞ ጥያቄ]
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ አመታዊ የቅዱስ ሚካኤል የንግስ በዓል እንኳን አደረሳችሁ እያልን፣ አመታዊ የንግስ በዓሉን ሚስኪኖችን በማብላት፣ በማጠጣት እና የታረዙትን በማልበስ እንድሁም ተፈናቅለው በየአብያተ ቤተክርስቲያን እና መስጊድ እንድሁም በሌሎች የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖቻችንን በመጠየቅ እንድታሳልፉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
በክርስትና እመነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው ይህ አመታዊ የቅዱስ ሚካኤል የንግስ በዓል በየአቢያተ ቤተክርስቲያኖችም በሁሉም አከባቢዎች የሚከበር ሲሆን፣ በወለጋ ከሚገኙት ደግሞ የአንገር ጉትን የሚካኤል ቤተክርስቲያን ከአራቱም አቅጣጫ በተሰባሰቡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በደማቅ ይከበራል።
በዚህ አመታዊ የንግስ ዕለተ-በዓል ሁሉም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በቤታቸው በሚዘጋጅ ድግስ እንግዶችን በማስተናገድ በደመቀ ሁኔታ ያከብራሉ። በዛሬው ዕለት የጎረምሳዎችና የኮረዳዎች ጨዋታ፣ የተነፋፈቁ የሚገናኙበትና የተነፋፈቁ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር በአንድነት ተሰባስበው የሚጫወቱበት አስደሳች የተከበረ በዓል ከመሆኑም በላይ፣ በዕለቱ ከሁሉም ቤት ሁሉም የሚስተናገድበት ጥሪ የማይጠብቅበት ዕለት ነው።
ስለሆነም በአመታዊ የንግስ በዓል ሐይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ ፍጹም ሠላማዊ በሆነው የቅዱስ ሚካኤል የንግስ በዓል፥ በፊት በነበረው ጨዋዊ ሚስኪኖችን የማስታወስና የመጠየቅ የማብላትና የመንከባከብ ልምምዳቸውን ዛሬም እንደትናንቱ በመተግበር እንድታከብሩ እያሳሰብን፤ ለአመታዊ የቅዱስ ሚካኤል የንግስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።
ሠላም ለሐገራችንና ለህዝቦቿ ይሁን‼
🙏🙏🙏 ሠላም ለፍጥረቱ ሁሉ ይሁን🙏🙏🙏
መልካም በዓል!!