@Seleslamenwk @seleslamenwk Channel on Telegram

@Seleslamenwk

@seleslamenwk


.com

@Seleslamenwk (English)

Welcome to @Seleslamenwk, your one-stop destination for all things related to health and wellness! This Telegram channel is dedicated to providing you with valuable information, tips, and resources to help you live a healthier and happier life. Whether you're looking for healthy recipes, workout routines, mindfulness practices, or expert advice on various health topics, you'll find it all here at @Seleslamenwk. Our team of experienced professionals is committed to sharing the latest trends and research in the health and wellness industry to empower you to make informed decisions about your well-being. Join our community today and start your journey towards a healthier lifestyle with @Seleslamenwk!

@Seleslamenwk

20 Nov, 18:00


እስኪ ጥቆማ እናድርግ!

የወንድማችንን ቃል የቴሌግራምና ዩቱዩብ ቻናል በመቀላቀል አባል ይሁኑ። ወንድማችን ቃል በክርስትናው ነገረ መለኮት ዙሪያ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለ እውቀት ተደርገው ከተሰጡን ስጦታዎች መካከል አንዱ ነው። ስለሱ ብዙ የምንላችሁ ነገር ወደ ፊት ይኖረናል።

ለአሁኑ ግን የወንድማችንን ቃሌን ኦፊሻል ቴሌግራም ቻናልና ዩቱዩብ አካውንት ተቀላቀሉ(አባል) ኹኑ ወገኖች፦

ቴሌግራም፦ https://t.me/hokhmahchristianstudies

ዩቱዩብ፦ https://youtube.com/@hokhmah-y7y?si=6on3drQJvMhf-W3W


ሼር አድርጉት ተባረኩ።
@Yeshua_Apologetics_Ministry

@Seleslamenwk

12 Nov, 08:54


ሰላም!

ጥሩ የቪዲዮ ኤዲተር ካላችሁ በውስጥ
አናግሩኝ እስኪ፦

👉 @Y_Apolog

@Seleslamenwk

07 Nov, 17:07


አራት ዓይነት አፈጣጠር? በሚል ርዕስ የተጻፈውን ይህንን አዲስ ጽሑፍ ያንብቡ። የኢየሱስን ከድንግል መወለድ እንደ አራተኛ የሰው አፈጣጠር መንገድ ለሚቆጥሩት ሙስሊሞች የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ ነው https://ewnetlehulu.net/four-creation/

@Seleslamenwk

03 Nov, 11:02


"ወደ አባቴ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ..." ዮሐንስ ወንጌል 20፥17

የኢየሱስ ክርስቶስ ልጅነት የማይመረመር በዚህ ጊዜ ተገኘ በዚህ ጊዜ ያልፋል የማይባል ነው ልጅነቱም የባሕርይ እንደመሆኑ ቅዱሳን ከተቀበሉት ልጅነት ይለያል እኛስ በጸጋ በኵል የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል እርሱ ግን ለአብ የባሕርይ ልጁ ነውና አብን አባቴ አለው። ወበእንተ ህላዌ መለኮትሰ ይቤ አቡየ( የባሕርይ ልጅ ነውና አባቴ አለው)።

ባሕርየ መለኮቱን ሳይለቅ ወደ እኛ አንድነት ወይም ባሕርይ መጥቷልና ወይም የእኛን ባሕርይ ነሥቷልና አምላኪየ አምላኬ ሊል ተገባው «ወደለወ ይእዜ ከመ ይብል አምላኪየ በእንተ ምጽአቱ ኀቤነ እምኀበ እግዚአብሔር አቡሁ»
ግን ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር ሳይለይ ወደ እኛ አንድነት ስለመጣ ዛሬ አምላኪየ ሊል ተገባው።

ስለዚህ እንዲህ እንበል፦እግዚአብሔር አብ አምላኩ ውእቱ ለወልድ ውእቱ በእንተ ትስብእቱ ወአቡሁ በእንተ መለኮቱ ቀዳማዊ። «ሰው ስለሆነ እግዚአብሔር አብ ለወልድ አምላኩ ነው ስለቀዳማዊ ባሕርዩ ደግሞ አባቱ ነው»

ለእኛስ..? እርሱ በሰጠን ጸጋ በኵል ልጆች ተብለናል «በእንተ ጸጋ ዘጸገወ ለአርዳኢሁ ይቤ አቡክሙ» ለደቀ መዛሙርቱ ስለ ሰጣቸው ልጅነት አባታችሁ አለ።

ስለዚህ የኢየሱስ ልጅነት ቀዳማዊ ልጅነት የባሕርይ በባሕርየ መለኮት በመተካከል ጅማሬ የሌለው በመሆኑ ከቅዱሳን የጸጋ ልጅነት ልጅነት ፍጹም የተለያየ ነው።

መልካም ዕለተ ሰንበት 🙏

ማጣቀሻ
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ  ኤጵፋንዮስ ገጽ 177 ምዕራፍ 54 ከቍጥር 8-10

@Seleslamenwk

28 Oct, 14:11


ለፈሪው ኡስታዝ አድርሱ

@Seleslamenwk

27 Oct, 13:50


የድረ-ገጻችን አምደኛ የሆነው ወንድም ሚናስ ሌላ አዲስ ጽሑፍ ይዞልን መጥቷል። ይህንን ግሩም ጽሑፍ ለማንበብ አስፈንጣሪውን ይከተሉ https://ewnetlehulu.net/carmen-christi/

@Seleslamenwk

19 Oct, 11:17


ወንድማችን ሙሐመድ እውነት ለሁሉ ሌላ ታሪክ ውስጥ ነው ወገኖች እዩት..😁

ሊንኩ፦ https://vm.tiktok.com/ZMhPTLG9k/

አካውንቱን ፎሎ በሉት ኮፒሊንክ አድርጉለት..!
እስልምና ላይ ፊተኛ ከማረጋቸው ሰዎች መካከል ነው።

@Seleslamenwk

11 Oct, 15:17


ምሳሌ 8፥22 እና የኒቂያ ጉባኤ

በዩቱዩብ፦ https://youtu.be/BNROfoMjfZg?si=JhcJZWRdZy1Fh04j

በአሚነ ሥላሴ ያጽናን።

@Yeshua_Apologetics_Ministry

@Seleslamenwk

09 Oct, 14:38


https://youtu.be/zn_hcOSDNOo?si=ixAs23mlW7iWGup-

@Seleslamenwk

07 Oct, 13:37


ሙስሊሞች መልሱልን


ማን ነው ትክክል


መሐመድ ወይስ ዑመር?

ጥቁሩን ድንጋይ መዞርና መሳም መተሻሸት የሚጠቅም ከሆነ ዑመር ለምን አይጠቅምም አለ? ቡኻሪ 1597


ጥቁሩን ድንጋይ መዞርና መሳም መተሻሸት የማይጠቅም ከሆነ መሐመድ ለምን ሰባት ጊዜ ዞረ? ቡኻሪ 1603

@Seleslamenwk

06 Oct, 15:38


🗣ውድ የአፓሎሚክስ ቤተሰቦች
እንዲሁም 🎓ተመራቂ ተማሪዎች

ዛሬ ማታ 2:00 ላይ በ Tiktok Live እንገናኝ😍
ተጋባዥ አገልጋዮች
😇Sahih Iman
😇Mohammed Ewnetlehulu
😇Daniel Ewnetlehulu
😇Pastor wondosen (Amanuel Church)


🛑Live ለመከታተል በአፓሎሚክስ 👇

🛑Tiktok Account = https://www.tiktok.com/@apolomics?_t=8qJJI1IwiH7&_r=1


🛑Telegram =@apolomics


join our channel
@apolomics
@apolomics

@Seleslamenwk

05 Oct, 17:58


🚩 የእግዚአብሔር ቃል

👉 የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነው
" የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና ( ዕብ 4:12)

👉 የእግዚአብሔር ቃል የሚሰራ ነው
" የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም (ዕብ 4:12)

👉 የእግዚአብሔር ቃል የመንፈስ ሰይፍ ነው
" የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥
(ወደ ዕብራውያን 4:12)

👉 የእግዚአብሔር ቃል የሚመረምር ነው
" የእግዚአብሔር ቃል ... ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል (ዕብ 4:12)

👉 የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ወይም መብራት ነው
" ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥ (ምሳ 6:23)

👉 የእግዚአብሔር ቃል መስታወት ነው
" ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤"
(የያዕቆብ መልእክት 1:23)

👉 የእግዚአብሔር ቃል ዝናብ በረዶ ውሃ ነው

(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕ. 55)
10፤ ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥ 11፤ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።

@Seleslamenwk

03 Oct, 11:55


.           ከምልህ በላይ
ሰላም ደስታ - Live Worship

እንደ ሰው ቢቀርበኝ ራሱ ዝቅ አድርጎ ወደ እኔ ቢመጣ
ከላይ ከሰማያት ከከበረ ስፍራ ወርዶ እንደመጣ
ይህንን አምናለሁ እኔ እቀበላለሁ
መንደሬ ቢገኝም እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው
እኔን ሊያድነኝ በደዌ ቢደቅም
ሰው ብቻ ነው ብዬ እኔ አልታለልም

@Seleslamenwk

01 Oct, 18:59


የአፖሎሚክስ ኦንላይን ትምህርት ቤት ልዩ የክረምት ሰልጣኞ የምርቃት መርሀ ግብር

በአፖሎሚክስ ኦንላይን ትምህርት ቤት በክረምት መርሀግብር በ “Apologetics” (አቅብተ እምነት ) እና በ “Polemics” (መሞገት ) ሲሰለጥኑ የቆዩ ተማሪዎች መስከረም 26/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በሰርተፊኬት መርሀግብር የምናስመርቅ መሆኑን ስናሳውቅ በደስታ ነው።

በ “Apolomics Online School” የተማሩ ተማሪዎች :-

ክርስትናን የሚያውቁ እና የሚከላከሉ
ከክርስትና ውጪ ያሉትን በራሳቸው አስተምሮ በእውቀት የሚያፈርሱ
ለወንጌል አገልግሎት የታጠቁ ናቸው።

🎓በሀይማኖት ንፅፅር | Comparative Religion የወሰዷቸው ኮርሶች
✝️ስነ ሥላሴ Trinity
✝️ነገረ ክርስቶስ Christology + Soteriology
✝️ስነ መጵሐፍ ቅዱስ Bibliology
💪እስልምናን ማጥናት Islamic study
🤗ስነ አምንዮ Logic
😍የወንጌል ስርጭት Evangelism


በእለቱ :-
👉እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት
👉ተማሪዎች ውጤት እና ሰርተፍኬታችሁን የምታገኙበት
👉የተጋበዙ አገልጋዮች የሚገኙበት
👉እንዲሁም ስለ የወደፊት ፕሮጀክቶቻችንን ለተማሪዎች የምናሳውቅበት መርሀግብር ይኖረናል።

እሁድ መስከረም 26/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ አይቀርም

የአገልግሎቱ ተደራሽነት ይሰፋ ዘንድ
#Share
#Share
#Share

አድርጉ!!

Join our channel
🎓🎓🎓🎓 @apolomics

@Seleslamenwk

01 Oct, 18:40


መልስ ለሙስሊም https://vt.tiktok.com/ZS2BHsxbh/

@Seleslamenwk

19 Sep, 10:36


Here we go👇

https://youtu.be/64oZafzxJVA?si=qhjQpfPzsN8SA2Dw

መጽሐፍ ቅዱስ አይጋጭም....!


🚩 የቪዲዮ አላማ በሙሉ ሙስሊሞች የእርሱን ንግግር በመውሰድ እያስተጋቡ ስለሆነ ምሑራዊ ዳሰሳ ክፍል አንድ በዕዝራ እና ነህምያ ላይ አቅርበናል፤ እኛም እንዲህ ስንል ምልከታችንን በዚህ ቪዲዮ አስቀምጠናል(አንዳንድ አቃቤያን ሲስቱ ደሞ ትንሽ ሃይ ማለት ያሻል)😊

@Seleslamenwk

14 Sep, 16:55


የማይቀር ውይይት

የአምላክ ግልጠት ሥላሴ ወይስ ተውሒድ?

ዛሬ ማታ 3:00 ሰዓት

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@danit4all?_t=8pigX8muBcc&_r=1

@Seleslamenwk

12 Sep, 08:57


በሙስሊሞች ላይ ስል መከራከሪያዎችን በማቅረብ ፣ በእስልምና ላይ ያጠነጠኑ ጽሁፎችንና መጽሐፍትን በማዘጋጀት የምናውቀው ሳሙኤል ግሪን በሚከተለው መጽሐፍ እንዴት ወንጌልን ልናደርስ እንደምንችል መደላድል ይፈጥራል። ተባረኩበት!

📔ርዕስ፦ የምስራቹን ለሙስሊሞች ለማዳረስ ከየት እንጀምር?
👤ደራሲ፦ ሳሙኤል ግሪን
🗣ተርጓሚዎች፦ የእውነት ለሁሉ ቡድን
📑የገጽ ብዛት፦ 246 💾መጠን፦ 10.2MB
___
በተያያዘ ርዕስ፦
*የወንጌል ስርጭት ቁልፍ ዕቅድ በሮበርት ኮልማን
*እንድረስላቸው በገርሃርድ ኔልሰን እና ዎልተር ኤሪክ
___

@Seleslamenwk

10 Sep, 18:35


"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል"
(መዝሙረ ዳዊት 65:11)

🚩 እንኳን ለ2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ! ጌታ ኢየሱስ በልባችን የሚነግስበት አመት ይሁንልን!

@Seleslamenwk

09 Sep, 15:56


@Yeshua_Apologetics_Ministry

➟የሹዋ ዐቅበተ እምነት አገልግሎት አላማ

ከክርስትና እምነት አንጻር ደርዛቸውን የጠበቁ ስነ መለኮታዊ ፍልስፍና፤ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ጽሑፎችን ማቅረብ

በክርስትና ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሀሳቦችንና የኑፋቄ ትምህርቶችን መመከት

የሌላውን እምነተ መርህ ከሎጂክና ከታሪካዊ ዳራዎች አንጻር መመርመር።

-----
ቻናሉን በመቀላቀል ከአገልግሎቱ ተካፋይ ይሁኑ።🙏

@Seleslamenwk

30 Aug, 17:22


መልስ ለሙስሊም https://vt.tiktok.com/ZS2BHsxbh/

@Seleslamenwk

29 Aug, 06:55


👉 ለአላዋቂ ሙስሊም የተሰጠ መልስ

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 20)
1፤ ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች። 2፤ እየሮጠችም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር መጥታ። ጌታን ከመቃብር ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት #አናውቅም #አለቻቸው።

3:42

#መላእክትም #ያሉትን (አስታውስ)፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጻሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡»

#መላእክት #ያሉትን (አስታውስ)፡- «መርየም ሆይ! አላህ ከርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ (ልጅ) ያበስርሻል፡፡»

3:45

ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡

«እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፡፡ ጌታህን ፈሪ #እንደ #ሆንክ (አትቅረበኝ)» አለች፡፡

«እኔ ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ» አላት፡፡

19:17-19

@Seleslamenwk

26 Aug, 17:51


🚩 የማን አምላክ ነው ጾታ ያለው?

ሰሞኑን ሙስሊሞች "ክርስቶስ አምላክ ከሆነ እንዴት ጾታ ሊኖረው ይችላል?" የሚለውን የአቡ ሐይደርን አስቂኝ ጥያቄ ሲቀባበሉት ነበር። የጥያቀው አመክንዮ እጅግ ደካማ ሲሆን ከመሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮዎች መካከል አንዱ የሆነውን የስጋዌን (incarnation) ትምህርት ችላ ያለ ነው።

ክርስቶስ በመለኮት ጾታ አለው ብለን አናምንም። ስጋን ከመንሳቱ በፊት ወይንም ደግሞ በስጋ ከመምጣቱ በፊት ሲኖርበት በነበረው ባህርይው መለኮት ነበር። መለኮት መንፈስ ነው (ዮሐ 4:24) በቦታ (ኤር 23:24) በጊዜ (ራዕ 22:13) እና በቁስ (ኢሳ 31:3) አይገደብም፥ አይወሰንም። ስለዚህ ጾታ የለውም። ክርስቶስም በስጋ ከመምጣቱ በፊት መለኮት ስለነበር (ዮሐ 1:1-3 ኤር 23:5-6) ጾታ አልነበረውም።

ጾታ የኖረው፥ ቀድሞ የእርሱ ያልነበረውን የሰውን ባህርይ የራሱ ሲያደርግ ነው (ፊሊ 2:6-7) ይህን ባህርይ የራሱ ሲያደርገው፥ ከኀጢአት በቀር ጠቅላላ ባህሪያቱ (attributes) የእርሱ ሆኑ። ከሰውነት ባህሪያት ደግሞ አንዱ ጾታ ነውና ክርስቶስ ሲሰገው፥ ጾታ ኖረው። ከስጋዌው በኋላ ክርስቶስ የመለኮትም የስጋም ባህሪያት ያሉት ሲሆን፥ ጾታ ሊኖረው የቻለበትም ምክንያት ይህ ነው። በስጋ መገለጡ። እንጂ በስጋ የመጣው አምላክ ስላልሆነ አይደለም

♦️ አስተውሉ! በክርስትና አስተምህሮ መሰረት መለኮት ጾታ የለውም። እኛ ክርስቲያኖች መለኮት ጾታ አለው ብለን አናምንም። ክርስቶስ ጾታ ሊኖረው የቻለው፥ ሌላ ሁለተኛ ባህርይን የራሱ ስላደረገ እንጂ በአምላክነቱ ጾታ የለውም። ጾታ የመለኮት ባህርይ አይደለም።

✍️ እነርሱ ያነሱትን ጥያቄ በዚህ መልኩ ከመለስን ዘንድ፥ ወደ ተነሳንበት ርዕስ እንግባ። የማን አምላክ ነው ጾታ ያለው?

እጅግ በሚያስገርምና በሚያስደቅ መልኩ፥ ጾታ ያለው የሙስሊሞች አምላክ አላህ መሆኑን እንረዳለን! ለዚህ ማስረጃ የሆነውን የቁርአን አንቀፅ እንመልከት፦

"መጫወቻን (#ሚስትና #ልጅን) ልንይዝ #በሻን ኖሮ ከእኛ ዘንድ #በያዝነው ነበር፡፡ (ግን) ሠሪዎች አይደለንም" ሱራ 21:17

✏️ በዚህ ስፍራ የሙስሊሞች አምላክ አላህ ቢሻ ኖሮ ሚስትና ልጆችን ይይዝ እንደነበር ሲናገር እንመለከታለን። ብፈልግ ሚስትና ልጅን እይዛለሁ ማለት፥ ብፈልግ ሚስት አግብቼ ከዚያች ሚስት ልጅ መውለድ እችላለሁ ማለት ነው። ነገር ግን "ሰሪዎች አይደለንም" በማለት ይህን ነገር የማድረግ ፍላጎት እንደሌለው ይናገራል

ይህ ማለት የሙስሊሞች አምላክ አላህ ወንድ ነው ማለት ነው። ጾታ አለው። ሚስት አግብቶ ልጅ ያልወለደበት ምክንያት፥ ረቂቅ መለኮት ስለሆነ ሳይሆን ስላልፈለገ ነው። ጉዳዩ የፍላጎት እንጂ የባህርይ አይደለም። አላህ እንደ ወንድ ሚስት አግብቶ ልጅ የሚያስወልድ ባህርይ አለው። ነገር ግን ስላልፈለገ አያገባም። ልክ አንድ ሰው ከፈለገ ሚስት እንደማያገባው ልጅም እንደማይወልደው ማለት ነው። ታዲያ አግብቶ መውለድ የሚችል ወንድን እያመለኩ ለምንድነው ይህን አይነት ጥያቄ የሚያነሱት? ጾታ ያለው አምላክ እያመለኩ "እንዴት አምላክ ጾታ ሊኖረው ይችላል?" ብሎ ሌላውን በሀሰት መወንጀል ይቻላል እንዴ?

♦️ ነገሩን በይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ፥ ጾታ አለው ብለው ማመናቸው በመለኮት መሆኑ ነው። ሙስሊሞች እንደ ክርስቲያኖች መለኮት በስጋ ተገለጠ ብለው አያምኑም። ስለዚህ አላህ ጾታ አለው ሲሉ በስጋ አይደለም፥ ስጋ የለምና። ስለዚህ በትክክል አምላክ ጾታ አለው ብለው የሚያምኑት እነርሱ ናቸው ማለት ነው።

ይህ ደግሞ እስልምናን paganism ያደርገዋል። ምክንያቱም በመለኮት ጾታ አለው ብለው የሚያምኑት ፓጋኖች ናቸውና። ጣኦታዊ የነበሩት የጥንት ግሪካዊያን፥ ሮማዊያን፥ ከነዓናዊያን፥ ግብፃዊያን፥ ፋርሳዊያን፥ ባቢሎናዊያን፥ አሦራዊያን እና የሙስሊሞች ነብይ ሕዝቦች የነበሩት ጣኦታዊ አረባዊያን በሙሉ አማልክቶቻቸው በመለኮት ጾታ እንደነበራቸው ያምኑ ነበር። መለኮት ጾታ አለው በማለታቸው ወንድና ሴት አማልክት እንደነበሩ፥ እነዚህም አማልክት እንደሚጋቡና እንደሚወልዱ ያምኑ ነበር። እስልምናም አላህ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ ነው በማለቱ፥ ሳይወድ በግድ ከፓጋኖቹ ምድብ ይመደባል።

▶️ የቁርአን ተንታኞች (ሙፈሲሮች) ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምን አሉ?

ሙፈሲሮቹም ከቁርአኑ ጋር በመስማማት፥ አላህ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ መሆኑን ይመሰክራሉ። ከዚያ በተጨማሪም፥ ቢፈልግ እነ ማንን እንደሚያገባም ይናገራሉ፦

"Had We desired to find some diversion, that which provided diversion, in the way of a partner or a child, we would have found it with ourselves, from among #the_beautiful_eyed_houris or #angels were we to do {so}. But We did not do so, thus We never desired it"

✍️ Tafsir Al Jalalayn:- https://quranx.com/Tafsir/Jalal/21.17

የቁርአን ተንታኞች ሁለቱ ጃላላዎች እንዳስቀመጡት፥ አላህ ብንሻ ሚስትና ልጅ ብንይዝ ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ አብራርተውታል። እርሱም፥ ከፈለገ ከመላእክትና ከሁሪዎች (በእስላማዊ ጀና ያሉ እንግዳ እንስት ፍጥረታት ናቸው) ሚስት አግብቶ መውለድ ይችላል ማለት ነው ብለዋል። ስለዚህ አላህ በሰማይ ከሁሪዎችና ከመላእክት ጋር ሊጋባ የሚችል ወንድ ነው ማለት ነው

"Then Allah revealed the following, when they said that the angels are Allah's daughters: (if we had wished to find a pastime) if we wished to #have #daughter; and it is said that it means: if we wished to #have a #wife; and it is also said that this means: if we wished to #have #children, (we could have found it in our presence) from us from among #the_maidens of paradise (if we ever did) and we will never do this"

✏️ Tafsir ibn abbas:- https://quranx.com/Tafsir/Abbas/21.17

የሙስሞች ነብይ የአጎት ልጅ የነበረውና፥ "ኻብራል ኡማ/የኡማው የብዕር ቀለም" ተብሎ የሚጠራው ኢብን አባስ እንደተረጎመው፥ አላህ ሚስትና ልጅ ብፈልግ ኖሮ እይዝ ነበር ሲል፥ ከፈለኩ በሰማይ ያሉ ሁሪዎችን ማግባት እችላለሁ ማለቱ ነው ብሏል። ይህ ማለት አላህ አንዲትን እንስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ ነው ማለት ነው። ከሁሪዎቹ ጋር ተገናኝቶ ልጅ የሚያስወልድ ባህርይ አለው። ስለዚህ ጾታ ያለው የሙስሊሞች አምላክ ነው ማለት ነው።

🔊 ታዲያ እንዴት ክርስቲያኖች ጾታ ያለው አምላክ አላቸው ይላሉ? ራሳቸው በመለኮት ጾታ ያለው አምላክ እያመለኩ???

@Seleslamenwk

25 Aug, 11:36


የምትጠብቁት የክፍል አንድ ትምህርተ ሥላሴ ትምህርት ተለቋል።

ከዕብራይስጥ ቅዱሳት መጽሐፍት እና ሊቃውንት አንጻር ድንቅ ዳሰሳ

https://youtu.be/GAxXQrEqWfU?si=zt1oBtDGIP79MWDx

ሼር ይደረግ።

@Seleslamenwk

20 Aug, 17:20


🚩 እርሱ ግን ተኝቶ ነበር

(የማቴዎስ ወንጌል 8 )
23፤ ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።
24፤ እነሆም፥ #ማዕበሉ #ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር #ታላቅ #መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን 👉ተኝቶ👈 ነበር። 25፤ ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉ 👉አስነሡት👈 ። 26፤ እርሱም። እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ #ነፋሱን እና #ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
------------------------------------------------------------
👉 ደቀ መዛሙርቱ ተጨንቀዋል። ለሞት አንድ እርምጃ ነው የቀራቸው። ማዕበሉ ታንኳይቱን ደፍኖ ከባህሩ ስር ከቷታል። አሁን ሊያድናቸው የሚያስችል ልምድ ሆነብቃት የላቸውም። ነገር ግን በታንኳይቱ ውስጥ #አንድ #የተኛ ነገር ግን #የማዕበሉ #ታንኳይቱን እንደዛ ማናወጥና ከባህሩ ስር መድፈቅ #ቅንጣት #ያህል #እንቅልፉን #የማይቀሰቅሰው #ፍጥረት #የሚታዘዙለት #በስጋ #የተገለጠ #አምላክ አለ።

አስተውሉ ሰው የፈለገ ቢተኛ እኮ አይደለም የባህር መናወጥ ይቅር እና የስልክ ጥሪ ይቀሰቅሰዋል። ይህ እጅግ የሚገርም ነው በስጋ #የተገለጠው #አምላክ በዚህ ሁሉ መሀል #ተኝቶ ነበር ቀሰቀሱት #ንፋሱንም ፣ #ማዕበሉንም ገሰፀ ታላቅም ፀጥታ ሆነ።

በሕይወታችን ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ልንቆጣጠራቸው የማንችላቸው ብዙ ችግሮች ይገጥሙናል። ነገር ግን በእነዚህ ችግሮች እንዳንናወጥ እና ችግሮቹ ደፍቀው እንዳይጎዱን በጌታችን ላይ #መተማመን እና #መደገፍ አለብን። ችግሮቹ ችግርነታቸው ለእኛ እንጂ ለእርሱ አይደሉምና። ከማይክ በላይ ከፍ ብለው የሚጮሁ ችግሮቻችንን ገስፆ ፀጥታ እና ሰላም ይሰጠናል።

ሻሎም።
https://t.me/seleslamenwk

1,657

subscribers

711

photos

259

videos