Missionaries of Christ @missionaries_of_christ Channel on Telegram

Missionaries of Christ

@missionaries_of_christ


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊወስደን በቶሎ ይመጣል
════════
👉 ክርስቶስ ተኮር ትምህርቶች የቻናሉ መገለጫዎች ናቸው ፣ መዝሙሮች ፣ ግጥሞች ጌታ ቢፈቅድ ደግሞ ሚስዮናውያንን ማበረታታት ፣ መላክ ፣ መደገፍ እንፈልጋለን ጌታ ይርዳን ።

የዚህ ቻናል የመጨረሻው እና ዋንኛው ግብ ወንጌልን ላልሰሙት ማሰማት ነው!

ለአስታያየት @Ela_Christian

MISSIONARIES OF CHRIST

Missionaries of Christ (Amharic)

ምሳሌው 'Missionaries of Christ' እና 'missionaries_of_christ' ማህበረሰብን በማስቻሉ ሥራችንን የችግር ምልክት ለማሰማት ያለበትን የባለቤት ቪኦኤም መስመር ልጆቻችንን በዚህ ቦታ መደገፍ እና መቀየር አስፈላጊ እንዲሆን ይግዛችን። ምሳሌችን ተጨማሪ ማህበረሰብ ነን ፣ ምክንያት እንደመረጡ፣ ምቹ ስለሚቀርብ ፣ እንድሀረለን ያዝናል ። አማርኛችንን ለመረጃብን ሰሚዎች 'Missionaries of Christ' እና 'missionaries_of_christ' ተመልክተው እናመሰልኑ። አሁን ለአስታያየት @Ela_Christian እና ቢሊዮናውያን እንባንኖናችን መቼች እንዳለው በብቻ ለማዝንያን እንችላለን።

Missionaries of Christ

23 Jan, 19:30


.        የመዝሙር ጥያቄ
    💿ይህ መዝሙር የማነው?💿
                       👇
🎶የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው🎶
🎶ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው🎶
🎶ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም🎶
🎶በጣም ተዋደናል አንለያይም...🎶

ይህን ጥያቄ በትክክል ከመለሳቹ ጠቃሚ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ።

Missionaries of Christ

21 Jan, 18:09


የልቦና አይኖቻችንን እግዚአብሔር ያብራልን

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

18 Jan, 13:27


🎤ከወንድ ዘማሪዎች ውስጥ ማንን ታደንቃላቹ ?

በመዝሙሮቹ የተባረካቹ እና የምትወዱትን ዘማሪ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

Missionaries of Christ

08 Jan, 03:49


" እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥
ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።" (ኤፌ. 5:2)


በክርስቶስ ኢየሱስ የተሰጠን ፍቅር ከሰዎች የመውደድ አቅም በላይ መሆኑ እሙን ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚያብራራው ክርስቶስ ገና ኃጢአተኞች ሳለን፣ ገና ደካሞች ሳለን፣ ገና ጠላቶች ሳለን ስለእያንዳንዳችን ሞቷል።


የመውደዱን ልክ በመስቀሉ ሞትና ጣር አሳይቶናል። ታዲያ ኢየሱስ ያንን ፍቅሩን ነው በመንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ያፈሰሰው። የማያቋርጥ ጅረት ሆኖ፣ ከእኛ አልፎ ወደውጪው ዓለም እንዲፈስ! ክርስቶስ ጠላቶቹ ሳለን እንደወደደንና ስለእኛ ነፍሱን እንደሰጠ እኛም በዚህ ፍቅር ልንኖር እንደሚገባ ትዕዛዙን ሰጥቶናል።


በሃሳብ ደረጃ ቀላል ቢመስለንም መፈጸሙ ግን ሲያቅተን ይታያል። ቃሉ ነፍሳችንን እስከመስጠት ጠላቶቻችንን እንድንወድ አስተምሮናል። ለጠላቱ የሚሞት ክርስቲያን ግን በጭንቅ ቢገኝ ነው።
" እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።" 
(1 ዮሐ3:16)


ዳሩ ግን ለጥያቄያችን ቃሉ መልስ አለው። ወደ ክርስቶስ ፍቅር ማደግ ስንጀምር ያን ጊዜ ፍቅሩ በህይወታችን ፍሬን ያፈራል። ስለዚህም ሐዋርያው ይመክራል።
" ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"
(ኤፌ. 4:15)


ራስ ወደሆነው ፍቅሩን ይዘን ልናድግ፣ በህይወታችን ልንጠብቀው እንድንችል የጸጋው መንፈስ ይርዳን። እንደተወደዱ፣ ክርስቶስ መስዋዕት እንደሆነላቸው በፍቅሩ እንመላለስ።

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

06 Jan, 20:16


«ለቤትህ ቅርብ የሆነን ቤተክርስቲያን አትፈልግ፤ ይልቁንም ለመፅሐፍ ቅዱስ ቅርብ የሆነውን ቤተክርስቲያን ፈልግ።»

ፖል ዋሸር

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

06 Jan, 20:15


እጅግ በጣም የምወደውን የፖል ዋሸርን ንግግር ከስር እለቅላችዋለሁ 👇

Missionaries of Christ

06 Jan, 20:11


ኢየሱስ

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

06 Jan, 20:08


ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

ወንጌላዊ አማኝ የሆናችሁ ክርስትያን ወንድም እህቶቼ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን እንላለን ።

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

04 Jan, 19:24


.        የመዝሙር ጥያቄ
    💿ይህ መዝሙር የማነው?💿
                       👇
🎶ተራራው ግዙፍ ቢመስል🎶
🎶ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም🎶
🎶በፊትህ ከባድ የሚሆን🎶
🎶ማትችለው አንድ እንኳን የለም🎶
🎶እግዚያብሔር አንተ ሀያል ነህ 🎶
🎶ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው🎶
🎶ስታዘው ማይታዘዝ 🎶
🎶እረ ከቶ የቱ ነው🎶


ይህን ጥያቄ በትክክል ከመለሳቹ ጠቃሚ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ።

Missionaries of Christ

03 Jan, 14:39


🔴⚪️🔴⚪️🔴⚪️🔴⚪️🔴⚪️
በዓል እየቀረበ ነው ለዛውም ገና🎉

በዓሉን ድምቅ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን አዘጋጅተናል🪅
የፈለጋቹትን መርጣቹ ተቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Missionaries of Christ

02 Jan, 18:19


🎅የኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት🎅 መንፈሳዊ ፊልም ከፈለጋችሁ አሁኑኑ JOIN ይበሉ ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇
https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk
https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk
wave ለመግባት👉 @wunuye_bot

Missionaries of Christ

31 Dec, 11:45


ኢየሱስ

Missionaries of Christ

10 Dec, 08:30


“ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።”
— ገላትያ 2፥20

ክርስትና ክፉ ምኞታችንን ገድለን፣ ራሳችንን ትተንና መስቀላችንን ተሸክመን ክርስቶስን በመምሰል የምንኖረው ህይወት እንጂ የደካማ ስጋችንን ምኞት ልናሟላ የተጠራንበት ምልልስ አይደለም።

ክርስቲያን ለጌታው ታዛዥ እንደሆነ ታማኝ ባሪያ፣አባቱን እንደሚወድና እንደሚያከብር በጎ ልጅ፣መምህሩን ለመምሰል ራሱን በየእለቱ እንደሚያስለምድ መልካም ደቀመዝሙር ሊኖር ይገባዋል። ጌታችን አባታችን እንዲሁም መምህራችን የሆነው እግዚአብሄር እንዲከብር። እንግዲህ ትናንታችንን ሳንረግጥ እምነታችን ባለው ፍሬ ልቀን እንሂድ።

Missionaries of Christ

03 Dec, 11:45


“አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።”
  — ምሳሌ 4፥23


@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

27 Nov, 18:34


መንፈሳዊ ፊልም የሚመቻችሁ ከሆነ አሁኑኑ JOIN ይበሉ ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇
https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk
https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk
wave ለመግባት👉 @wunuye_bot

Missionaries of Christ

16 Nov, 11:59


#ባልታዛር_እና_ድብቁ_ገመናው

ሰላም ለእናንተ  ይሁን ሰሞኑን በ ሚዲያ የተዘዋወረው    ኢኳቶሪያል  ጊኒ የሚኖረው ባልታዛር እና ከጀርባው ያለው ሴራ በተመለከተ የጻፍኳት እቺ  አጭር ጹሁፍ አንባቢ  በቅድስና እግዚአብሔር  በመፍራት  እዲመራ እና የጨለማው አለም ምን ያክል ምድራችን  በዝሙት ለማጥለቅለቅ እንደተዘጋጀ  ለማስረዳት ያኸል ነው

ይህን ጹሁፍ ክርስቲያን  ላልሆኑም ሰዎች እንላክ🙏🙏

https://t.me/Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

12 Nov, 12:21



በቅርቡ ከተለቀቁ የመዝሙር አልበሞች ውስጥ የትኛው የመዝሙር አልበም እናድርሳቹ

የምትፈልጉትን መርጣቹ የሚመጣላቹሁን መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

Missionaries of Christ

05 Nov, 12:42


🎤ከሴት ዘማሪዎች ውስጥ ማንን ታደንቃላቹ ?

በመዝሙሮቿ የተባረካቹ እና የምትወዷት ዘማሪት ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

Missionaries of Christ

04 Nov, 14:58


💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
በመዝሙሮቹ የተባረካቹበት እና የምትወዱትን ዘማሪ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

Missionaries of Christ

03 Nov, 05:07


ለፅድቅ እንዳንገዛ ጉልበታችንን አቅም ባሳጣ÷ልናድግ ወደሚገባን ወደ ክርስቶስ ሙላት እንዳንጠጋ አቅማችንን በወሰደ ነገር ላይ
የመንፈስ ቅዱስ ሀይልን ይምጣልን😭
🎵🎵🎵🎵
ና በድካሜ.....
ና በጉድለቴ....
ና በዝለቴ....

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

02 Nov, 19:33


ሁላችሁም ተባረኩ 🙌 መልካም ምሽት 🌆

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

02 Nov, 19:20


👉መንፈስን አታጥፉ ❗️

ከ አገልጋይ ጆን ጋር የነበረን የእግዚአብሔር ቃል ጊዜ 👂

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

02 Nov, 18:44


ከ ዘማሪ ሜርሲ  ጋር የነበረን የአምልኮ ጊዜ 👂

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

02 Nov, 18:31


ከ ዘማሪ ገሎ ጋር የነበረን የአምልኮ ጊዜ👂

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

02 Nov, 18:00


Live stream started

Missionaries of Christ

02 Nov, 17:36


ፕሮግራማችን ምሽት 3:00 ላይ ይጀምራል ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ይቀራሉ

Missionaries of Christ

02 Nov, 05:22


የአምልኮ ምሽት

👉 ቀን ፦ ዛሬ

ከምሽት 3:00 ጀምሮ ፕሮግራማችን ይጀምራል ማንም እንዳይቀር እንላለን ሁላችሁም ተሳተፉ ድንቅ ምሽት አብረን እናሳልፍ ❤️

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

01 Nov, 06:22


የካታኮምቡ ሰማዕት በትረካ መስማት ለምትፈልጉ!

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

28 Oct, 17:34


እዚህ ቻናል ላይ ባይብል study የመጀመር ሀሳብ አለን ምን ትላላችሁ ?

Missionaries of Christ

28 Oct, 17:33


❤️

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

21 Oct, 19:20


💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
በመዝሙሮቹ የተባረካቹበት እና የምትወዱትን ዘማሪ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

Missionaries of Christ

20 Oct, 18:23


🎤አዳዲስ መዝሙሮች እና አልበሞች እየተለቀቁ ስለሆነ የምትፈልጉት ዘማሪ ስም በመንካት መሉ አልበም እና አዳዲስ ዝማሬዎችን ያገኙበታል 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Missionaries of Christ

20 Oct, 16:00



በቅርቡ ከተለቀቁ የመዝሙር አልበሞች ውስጥ የትኛው የመዝሙር አልበም እናድርሳቹ

የምትፈልጉትን መርጣቹ የሚመጣላቹሁን መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ

Missionaries of Christ

05 Oct, 15:43


እንደጠፋን ይገባናል በሰፊው እንመለሳለን..


ዛሬ ምሽት ከ 3:30 ሰአት በኃላ አብረን የምንማማረው ነገር ይኖራል ቅዱሳን

Missionaries of Christ

25 Sep, 19:42


(ዘሪው )

“ሌላውም ዘር በመልካም መሬት ላይ ወደቀ፤ በበቀለም ጊዜ መቶ ዕጥፍም አፈራ።”
ይህን ብሎ ሲያበቃም ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ” አለ።
ሉቃስ 8:8


በመልካም መሬት ላይ የወደቀውም ቃሉን ቅንና በጎ በሆነ ልብ ሰምተው የሚጠብቁ፣ ታግሠውም በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።
ሉቃስ 8:15

አንድ ታማኝ ገበሬ ዘሩን ዘርቶ ፍሬውን ለባለቤቱ ቢሰጠው ገበሬው ባለ ቤቱ የሚያሳየው የልቡ ደስታ እና የፊቱ ፈገግታ
ከክፍያ ይበልጥ ያስደስተዋል

እኛ የአመን ሰዎች አንድ አደራ አለብን
እርሱም የወንጌል አደራ ነው

ጳውሎስ ሲናገር
እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለ ዐደራዎች ሊቈጥረን ይገባል። ባለ ዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው።
1 ቆሮንቶስ 4:1-2


ዘራችንን ዘርተን ፍሬ እንድናፈራ ወንጌል በአገኘነው አጋጣሚ እንናገር እንመስክር🙏 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ተብለን ኤለ ለጨለመባቸው ሁሉ የክርስቶስን ብርሃን እናብራ

እድሜያችን እንደ ማቱሳላ ቢረዝም እግዚአብሔር በሕይወታችን ካልከበረ እንዲሁ ድነን ዘመናችን በከንቱ አልቆ ወደ መጣንበት አፈር ስንመለስ ከዚህ የበለጠ የሚያፅፅት ነገር የለም 😔😥

ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሆነልንን ያሁሉ መከራ ያሁሉ ስቃይ ለእኛ ሁኖልን
ያስችላል ወይ ዝም ማለት 😥??


እግዚአብሔር ይርዳን 🙏


@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

19 Sep, 03:22


" ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል" (ሚል 4:2)

" እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።"(ራእ 22:16)

የመጀመሪያው ጥቅስ በብሉይ ኪዳን መጨረሻ ላይ ሲገኝ ሁለተኛው ደግሞ በአዲስ ኪዳን መጨረሻ ላይ ይገኛል። ጌታ ኢየሱስ የጽድቅ ፀሐይ ብቻ ሳይሆን የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነው።

እስራኤላውያን እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ምድርን ይወርሱ ዘንድ የመረጣቸው ሕዝቦች ናቸው። እነርሱ ጌታ ኢየሱስ በክንፎቹ ፈውስን ተሸክሞ፤ በኃይልና በክብር ልክ እንደ ደማቅ ፀሐይ ሆኖ እንደሚገለጥላቸው ያምናሉ። ያኔ ታዲያ እርሱ በክብር ሲገለጥ የብረሃኑ ውበትና ድምቀት በምድር የሚኖሩት በሙሉ በደስታ ይሞላቸዋል።

ቤተ ክርስቲያን ያንን ደግሞ ዛሬ በምድር ላይ ኢየሱስ ለአማኞች የሚያበራ የንጋት ኮከብ ሆኖ እንደሚገለጥ ታስተምራለች።

የንጋት ኮከብ ገና ጨለማ ሳለ ፀሐይ በክብር ከመውጣቱ በፊት መንጋቱን ለማበሰር አስቀድሞ የሚወጣ ኮከብ ነው። ዓለም በሙሉ ተኝቶ ሳለ በድንገት ጌታ ኢየሱስ ከሰማይ እርሱን አምነው በመጠባበቅ ላሉት ይገለጣል።

በእርሱ የሞቱትንና እርሱን አምነው እየኖሩ ያሉትን ለዘላለም ከእርሱ ጋር ይሆኑ ዘንድ ይዞአቸው ይሄዳል። የንጋቱ ኮከብ የእርሱ ለሆኑት ብቻ አብርቶ ዓለም ገና በጨለማና በእንቅልፍ ሳለች የሚያምኑትን በክብር ይዞአቸው ወደ አብ ቤት ይሄዳል። (ዮሐ 14:3)


ኦ!!! ይህ እንዴት ያለ የተባረከ ተስፋ ነው!!! ዛሬ በምንም አይነት ውጣውረድ ወስጥ ብንሆን በዚህ ተስፋ እንጽናና። ጌታ ይወስደን ዘንድ ይመጣል።

እኛ እኮ ተስፋ የሌለን ከሞት በኃላ በቀኝ እንቁም በግራ ያላረጋገጥን ሰዎች አይደለንም፥ በሰማይ በእግዚአብሔር ቀኝ ከኢየሱስ ጋር የተቀመጥን ነን። ስሙ ብሩክ ይሁን። ኢየሱስ የዳዊት ሥር ብቻ ሳይሆን የዳዊትም ዘር ነው። እርሱ እንደ እኛ ፍጹም ሰው ነውና ዛሬ እያለፍንበት ያለውን ውጣውረድ ይረዳል፤ ሕመማችንን ያቀዋል፤ የልባችን መሰበር ይገባዋል። እርሱ ለሀዘኑ ዳርቻ፤ ለለቅሶው ወሰን፤ ለሰቆቃው ገደብ ያበጅለት ዘንድ ይመጣል።

እርሱ የነገረን ተስፋ ቢኖር " ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ" የሚል። (ዮሐ 14:18)


🙏🙏🙏አሜን ጌታ ሆይ ቶሎ ና።🙏🙏🙏

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

17 Sep, 13:00


በሥራው ፅደቅን 🙌

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

17 Sep, 06:57


መጽሐፈ መክብብ 05

2 እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።

Missionaries of Christ

16 Sep, 16:00


ጌታ ሆይ እባክህ🙏🙏 #ትዕቢተኛ ሳይሆን #ትሑት አድርገኝ
**
©“እ
ግዚአብሔር #ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ #ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ያዕቆብ 4:6
*
©ሰውን #ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ #ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርን ይጐናጸፋል።ምሳሌ 29:23
*
©ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ #ይታበያል፤
#ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች። ምሳሌ 18:12
*
©#ትዕቢት ስትመጣ ውርደትም ትከተላለች፤ #በትሑት ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች። ምሳሌ 11:2
*
©#ትዕቢት ጥፋትን፣#የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች። ምሳሌ 16:18

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

15 Sep, 14:59


ሙሽሪት ቤተክርስቲያን ሙሽራዋ ክርስቶስን ሁሌም ትናፍቀዋለች


በዘላለም ኪዳን የተዛመዳትን ከነገድና ከቋንቋ በደሙ የዋጃትን ርስትና ባለጠግነት በመንግስቱ ያዘጋጀላትን ታማኝ ወዳጅ ሙሽራዋን ያለመታከት ታወድሰዋለች።

ክርስቶስ በእርግጥም ውዳችን ነው እስከ መስቀል ድረስ የወደደን እስከ መቃብርም ያፈቀረን ዕዳና መርገማችንን በመስቀል ላይ ጠርቆ በመንገድ ያስቀረልን ከባርነት ቀንበር ፍጹም ነጻ ያወጣን አባ አባት ብለን የምንጠራበትን የልጅነት ክብር ያደለን በሕይወት መዝገብ ላይም ስማችንን ያኖረልን እውነተኛ አባትና አምላካችን እርሱ አማኑኤል ብቻ ነው።

ተወዳጆች ሆይ! ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ከውዳችን ሊለየን ደግሞም ስሙን ከአንደበታችን ሊነጥቀን በግልጽና በስውር በውስጥና በውጭ በአንድም በሌላም መንገድ ይዋጋናልና በእምነት ጸንተን እንቃወመው።

ከስም በላይ የሆነው የውዳችን ስም የጠላትን ምሽግ የምናፈራርስበት፣ ሉሲፈርን ወደ ጥልቁ አስረን የምንወረውርበት፣ ከመከራ ሸለቆ የምንሻገርበት፣ ወጀብና ማዕበሉን የምንገስጽበት፣ እረፍትና መጽናናትን የምናገኝበት፣ ፈውሳችን ነው።

ስሙን ጠርተን ስንዘምርና ስናመልክ ጠላት ይርዳል ምርኮም ይነጠቃል በእኛ ላይ ያጠመደው የተንኮል ወጥመድ እሳት እንዳየው የሸማኔ ፈትል ይበተናል ሐሳቡ ይመክናል ዓላማው ይጨነግፋል የውርደትን ካባ ተከናንቦም እንደ ትቢያ ከቅጥራችን ይበተናል።

ሳንፈራና ሳናፍር ውዳችንን እንዲህ እንበለው «ውዴ ክርስቶስ ሆይ አንተ የአጥቢያ ኮከብ፣ የጽድቅ ጸሐይ፣ የሕይወት መፍሰሻ የነፍሴ እርካታ፣ በልቤ ላይ የሾምኩህ ንጉሥ የሕይወቴ አክሊል ፣ድምቀትና ክብሬ የአንገቴ ድሪ ደግሞም ዝርግፍ ጌጤ፣ የነፍሴ እረኛ በልቤ ዙፋን ላይ ለዘላለም ንገሥ»።

ይህን ስም ሰምቶ ቅናት ይወገድ አለማመን ይራቅ ጥፋት ጸጥ ይበል የክፋት ሰራዊት ሁሉ በስሙ ብርታት ከምድራችን ይነቀል።

«ሞገሳችን ክብራችን የመድሐኒታችን ቀንድ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው»

ኢየሱስ የሚለው ስም ዘመንን ለሁለት የከፈለ ኃያል ስም ነው፤ ኢየሱስ የሚለው ስም  የምድሪቱን እንቆቅልሽ የፈታ ቡሩክ ስም ነው፤ ኢየሱስ የሚለው ስም ምሬታችንን ያጣፈጠ መዓዛችንን የለወጠ ቅዱስ ስም ነው፤ ኢየሱስ የሚለው ስም በሰውና በእግዚአብሐር መካከል የነበርውን የጸብ ግርግዳ ያፈራረሰ አስታራቂ ስም ነው፤ ኢየሱስ የሚለው ስም ሕዝብና አሕዛብን የሰማያዊ ርስት ወራሽ ያደረገ አዳኝ ስም ነው፤ ኢየሱስ የሚለው ስም የእግዚአብሔርን ቁጣና ፍርድ ያቆመ የመማጸኛ ስም ነው፤ ኢየሱስ የሚለው ስም ተራሮችን የሚያንቀጠቅጥ ኮረብቶችን የሚያቀልጥ ዓለቱን የሚሰነጣጥቅ ገናና ስም ነው፤ ኢየሱስ የሚለው ስም መቃብርን የሚገለብጥ ሞትን የሚገድል ሲኦልን የሚያስጨንቅ አሳሪውን የሚያስር መለኮታዊ ስም ነው፤ ኢየሱስ የሚለው ስም ከሰማይ በታች ያለ ፍጥረት በእምነት የሚጠራው የመጽደቂያ ስም ነው።

🙏ይህንን ስም ስናከብረው እንከብራለን ስንባርከው እንባረካለን ከፍ ከፍ ስናደርገው ከፍ እንላለን ስሙን ተሸክመን አንወድቅም እንጥላለን እንጂ አንሰበርም እንጠገናለን እንጂ እንታገላለን ደግሞም ጠላት በብርቱ ይዋጋናል የማታ ማታ ግን በድል ሰገነት ላይ እንጓደዳለን በስሙ ስልጣን የአውሬውን ራስ እየረገጥን ቀስቱን እያጣመምን በሳቅና በእልልታ ወደ ርስታችን እንገባለን።
🙏🙏«ኦ ኢየሱስ ሆይ ድል አድርገህ ድል አድራጊ ስምህን ስላወረስከን ዙፋንህ ለዘላለም የተባረከ ይሁን»

የክርስቶስ ሙሽራ ቤተክርስቲያን ሆይ ክብርሽ ታላቅ ነው ዕድልሽም ፍጹም ነውና ደስ ይበልሽ በዚህም ሐሴትን አድርጊ።

በክርስቶስ ያላችሁ ወገኖቼ በበጉ ደም የታተምን ሁላችን የክርስቶስ ሙሽሮች ነን ውዳችንን በክብር ከፍ እናድርገው የድል ዝማሬም ለበጉ እንሰዋለት መጽሐፍ እንዲህ ይላል «የበጉ ሰርግ ስለደረሰ ሚስቱም ራሷን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ» ራእ 19፥7 ክብርና ምስጋና ውዳሴና አምልኮ ለታረደው በግ ይሁን።


🙏🙏🙏🙏🙏አሜን🙏🙏🙏🙏🙏

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

15 Sep, 06:29


#ወደ_ቸርች_እንሂድ

@missionaries_of_Christ
@missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

14 Sep, 17:58


ተባረኩ ድንቅ ጊዜ ነበረን ❤️

Missionaries of Christ

14 Sep, 16:26


ሞገደኛ ሆኖ ከአምላክ ጋር መጣላት
ማገዶ መሆን ነው ለምፋጀው እሳት
#አይጠቅምም #በኃላ #እያወቁ #ማጥፋት
#እያወቁ #ማጥፋት
***
የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ #ሆን ብለን #በኀጢአት #ጸንተን #ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤  የሚቀረው ግን #የሚያስፈራ #ፍርድና #የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ #ብርቱ #እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።
ዕብራውያን 10:26-27

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

13 Sep, 17:02


መዝሙረ ዳዊት 32

1 መተላለፉ የቀረችለት ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው።

2 እግዚአብሔር በደልን የማይቈጥርበት በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ምስጉን ነው።

3 ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ ዝም ባልሁ ጊዜ አጥንቶቼ ተበላሹ፤

4 በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥ እርጥበቴም ለበጋ ትኵሳት ተለወጠ።

5 ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ።

6 ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይለምናል፤ ብዙ የጥፋት ውኃም ወደ እርሱ አይቀርብም።

7 አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጣርም ትጠብቀኛለህ፤ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።

8 አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።

9 ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።

10 በኃጢአተኛ ብዙ መቅሠፍት አለበት፤ በእግዚአብሔር የሚታመነውን ግን ምሕረት ይከብበዋል።

11 ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፤ ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ እልል በሉ።

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

13 Sep, 14:29


(ቅዱሳን ተዘጋጅታችሀል ወይ 😳?)



በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ። እኔ ወደምሄድበትም ስፍራ የሚያደርሰውን መንገድ ታውቃላችሁ።
ዮሐንስ 14:2-4


ጌታ የሰጠንን ተስፋ ሊሆን ጊዜው ቀርቧል

የናፈቀንው ጌታችን ሊመጣ ነው
እኛ አሁን ላይ ምን እየሰራን ነው?

 @Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

12 Sep, 13:50


ምህረቱ ለዘላለም ነውና..(መዝሙር 136)

የብርሃናት አባት የጊዜያት ሁሉ ባለቤት ታላላቅ ብርሃናትን ለጊዜያትና ለዘመናት ያበጃቸው በምህረቱ እና በቸርነቱ ብዛት መሻገርን አድርጎልናል እስመ ለዓለም ምህረቱ ብለን እንናገራለን..

መንገዳችንና ትንፋሻችንን ሁሉ በእጁ የያዘ አምላክ ዐዲሱን ዘመን እንደ ምህረቱ ብዛት ስላሳየን ምስጋና ይገባዋል።

እንኳን ለ2017 ዓም ዐዲስ ዐመት በሰላም አደረሰን ቤተሰብ ❤️

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

11 Sep, 08:25


እንኳን አደረሳቹ አደረሰን ቤተሰብ በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሁም ደግሞ የመተሳሰብ ይሁንልን

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

10 Sep, 10:57


በ2017
ስሉስ አምላክን በሁለንተናችሁ የምታከብሩ የክብር ሸክላ ያድርጋችሁ።
ክርስቶስ ኢየሱስን በበለጠ በማወቅ በርሱና በጸጋው የምትደሰቱ ያድርጋችሁ።
የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሄር መንፈስ ሁሌ እየተጠማችሁ የምትኖሩ ያድርጋችሁ።
በቅድስና ህይወት የምታጌጡ ሰዎች ያድርጋችሁ።
መንፈሳዊ ንባባችሁ የለመለመ ይሁንላችሁ።
በቃሉ እውቀት የተሞላችሁ መዝገብ ያድርጋችሁ።
በአስተምህሮ ንጽና የማትታማውን ህብረት ይስጣችሁ።
ጸጋው በመንፈሳዊ ተጋድሎ የበረታችሁ ያድርጋችሁ።
በስራ ትጋታችሁ ምርታማ ፍሬ የምታፈሩ ክርስቲያኖች ያድርጋችሁ።
ከኪስ አውላቂ ነቢያትና አሳዊ ሃዋሪያት ያርቃችሁ።
ስነ አመክኖ ጠልና ስሜት ወለድ ከሆኑ የሃይማኖት ተከራካሪዎች ይጠብቃችሁ።
ተሻገርን፣ ጠረመስን የሚሉ አዝማሪያን ከመስማት የጆሮ ንጽናችሁን ይጠብቃችሁ።
ለእግዚአብሄር መንግስት አንዲት ጠጠር የምትወረውሩ ያድርጋችሁ።
የጥበብና የፍርሃት መንፈስ ያለባችሁ አስተዋይ ያድርጋችሁ።
ቅዱሱን በማወቅ በጥበብ ህይወት ይምራችሁ።
ወንድሞቻችሁን የምትወዱ ያድርጋችሁ።
ከርሱ የተቀበላችሁትን መስቀል የምትሸከሙበትን ትከሻችሁን ያስፋላችሁ።
በጽድቅ እንጂ በነውራችሁ የማትመኩ ያድርጋችሁ።
በሃጢአት ስትወድቁ ወደ ማፍቀሬ ንሰሃ ልባችሁን ያቅናችሁ።

እንደ ፍቃዱ የሆኑ የልባችሁን ምክር እግዚአብሔር ይፈጽምላችሁ

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

09 Sep, 18:35


“ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን።”

—ቆላስይስ 1፥12—

Missionaries of Christ

09 Sep, 08:52


As a reminder:-

ከክፉ ሰው ከክፉ በክፉ አትመልስ። ሁሉንም ሰው በፊት የሚታይ የተሻለውን እንድታደርጉ ንቃ።" ሮሜ 12:17

የአምላክ ቃል በጣም ለትዕግሥትና ፍቅር ይመክረናል። በፍቅር ሕይወት ስንኖር፣ የፍቅር ኃይል ከብዙ አዳሜቻችን ይሸፍናል። ፍቅር ያልታገዙህ ፍቅር ለሚያሳዩህ ሰው አዲስ ተስፋ ይሰጣል።

የአምላክ ቃል በክርስቶስ የምናምኑ እኛ በኃጢአት፣ ክፉ፣ እና በዚህ ዓለም መከራ ውስጥ ያሉትን በጨለማ የሚያብረቁ ብርሃን እንደሆንን ይናገራል። ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩን ብርሃን እንድናበራ ወደ ዓለም ላከን። እኛን ወደ ክፉዎቹ መካከል እንድንልክና ምሥራቹን እንድንሰብክ ልኮናል። እኛ የምንኖረው መንገድ እና የምናደርጋቸው ነገሮች በቃላችንና በሰበካችን ከክርስቶስ ይበልጥ ጮክ ያሉታል።

አሁን፣ የአምላክ ቃል "ከክፉ ሰው ከክፉ በክፉ አትመልስ። ሁሉንም ሰው በፊት የሚታይ የተሻለውን እንድታደርጉ ንቃ" ሲል፣ ይህ የምናደርጋቸው ድርጊቶችና የምንኖረው መንገድ ለክፉ ያልሆኑት የክርስቶስን ፍቅርና የእርሱን ምሕረት ለማስተማር ታላቅ ኃይል ስላላቸው ነው።

May the Lord help us to love and to be kind amenn 🙏🙏

have a nice dayyyyyyyy

@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ

Missionaries of Christ

09 Sep, 07:44


ዛሬ የመጨረሻው የ2016 ሰኞ ነው።❤️
ስለዚህ ከ2016 በሕይወታችን ውስጥ ምን አስተማረን??


@Missionaries_of_Christ
@Missionaries_of_Christ