ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ @mukamil12 Channel on Telegram

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

@mukamil12


https://t.me/mukamil

የዪቲዩብ ቻናሌን ሰብስክራይብ ያድርጉ👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@Mukamil123

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ (Amharic)

ሐምሌም በአማርኛ የምትኖረውን ልጅ ድምፅን የምታውልቅ ሰው ጠቅላላ እና ከሌላ አስተያየት መካሄድ እፈልጉ። ናትና መታየት እስካሁን እናመሰናከንህ። ይህ ቢልጋ መሼል ይኖረልን። ናታና ሌሎችን ጽሁፋችሁን እጅግ ቻናል መብቸት ስሙ ስሜት ልንይታተን እናትን ማለትና ልቅሶ በቀልን መኖር ነፃነት የሚያድርገውን የዪቲዩብ ቻናልን ስለመለዋወጥና ስለመጠቀም ጠቅላላ እነሱን አስተያየት እንዳትሰብስል አዋልፉ። በከእር ካልተወስድ ነው። እባኮበርናለን!

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

07 Dec, 16:08


ጥያቄ እውነት ወይስ ሀሰት?

#የእስልምናን ጥሩ ገፅታ #ለማሳወቅ ንፅፅር ትምህርት #ጉልህ ቢና አለው

ጥያቄ ትክክለኛው መልስ ሰታገኙ የሚያመጣላችሁን add አድርጉለት

     🌟✍️በወድም ሙስጠፋ🌟

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

02 Dec, 16:24


ስለ እሥልምና እምነት ምን ማወቅ ይፈልጋሉ? ይጠይቁ🎁

ሙስሊሞች ሆናቹ ክሪስቲያን ወገኖች

ስለ ኢስላም እምነት ምን ማወቅ ይፈልጋሉ?

      መልሳቹ ጥያቄ አለኝ መጠየቅ እፈልጋለሁ የምትሉ አላቹ??

     #ምርጫው ስነኩት #የሚመጣላቹ ቻናል #ተቀላቀሉ ጠይቁ👍

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

02 Dec, 12:55


እንግዲህ ወደ ቲክቶክ ብቅ ብለናል😊
እዛው መንደር ያላችሁ ፎሎ በሉት🙂 https://www.tiktok.com/@mukamil85?_t=8rsf6Uge1hg&_r=1

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

01 Dec, 16:05


يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ

(📗ሱረቱ አል-ሁጁራት - 13)
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡

عن جابر -رضي الله عنه- عن النبي -صلى الله عليه وسلم قال﴿يا أيها الناسُ ! إنّ ربَّكم واحدٌ، و إنّ أباكم واحدٌ، ألا لا فضلَ لعربيٍّ على عجميٍّ، و لا لعجميٍّ على عربيٍّ، و لا لأحمرَ على أسودَ، و لا لأسودَ على أحمرَ إلا بالتقوى﴾

ጃቢር {ረ.ዐ} እንደተረከው የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብሏል! "እናንተ" ሰዎች ሆይ! "ጌታችሁ አንድ" ነው። አባታችሁም አንድ ነው። አዋጅ! "አረቡ" ከአጀሚዩ (አረብ ካልሆነው) አጀሚዩም ከአረቡ "ቀዩ "ከጥቁሩ" "ጥቁሩም "ከቀዩ "ብልጫ" የለውም! በተቅዋ (አላህን በመፍራት) ቢሆን እንጂ።”
[📚ሲልሲለቱል አስ-ሷሂህ 2700]

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

01 Dec, 14:44


ለኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክነት ባሕርይ አለውን?
ክፍል 1😊

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

01 Dec, 10:50


የንፅፅር ትምህርት እና በእስልምና ላይ ለሚነሱ ትችቶች መልስ የሚሰጥባቸው ቻናሎች ለማግኘት
👇👇👇👇👇
የስልክ በመኝካት ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇

╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃   👈ስልኩ
┃███████┃    👈ነክታቹ
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃    👈ተቀላቀሉ
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯
➶➶➶➶➶➶➶➶
እነዚ ውድ ቻናሉች ለማግኘት👆👆ከላይ ያለው የስልክ ምልኩቱ በመንካት ያግኑዋቸው ትጠቀሙበታላቹ ኢሻአላህ

የንፅፅር ቻናል ያላቹ wave ለመቀላቀል


በዚ አናግሩኝ➥
@mustef123
✍️ወድም ሙስጠፋ

የቻናሎች
#ባሌቤት ለማግኘት #ከፈለጋቹ ጥያቄ ካላቹ
በዚ ግቡና ጠይቁ 👇👇👇
@Contrastc_hannelswave

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

29 Nov, 13:20


https://youtube.com/shorts/REYw_yX0Llo?si=RvAK7L3XamMx6R84

አዲስ ቪዲዮ ናት ተመልከቷት እስቲ😊

ደግሞ ሰብስክራይብ አድርጉ እንጂ ቋጣሪ አትሁኑ አያስከፍልም (:😁)

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

29 Nov, 08:14


!

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

26 Nov, 18:21


ከዚህ ቀደም "ክርስቶስ ማነው?" በሚል አርዕስት በኡስታዝ አህመዲን ጀበል ተዘጋጅቶ የቀረበው መፅሐፍ በወንድም ጀማል ከድር በኦሮሚኛ ቋንቋ ተተርጉሞ አንባብያኑን እየጠበቀ ነው። (በነገራችን ላይ እስከምገዛው ጓጉቻለሁ!)

መፅሐፉን ማግኘት የምትፈልጉ፦
አየር ጤና፣አንዋር መስጂድ መጽሐፍ መደብር

ለተጨማሪ መረጃ፦
ወንድም አብዱ: +251920781016
ወንድም ጀማል: +251913463746

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

26 Nov, 08:39


ቁጭ ብሎ መሽናት

በ TIKTOK መንደር የሆነ ምስል ሼር ተደርጎልኝ ምላሽ ስጥበት ተባልኩ ምንድነው ብየ ስከፍተው በጣም ነው ያሳቀኝ ምስሉ የሙስሊሞች ነብይ መሓመድ ቁጭ ብሎ ይሸና ነበር ብሎ ይጀምራል።
ከዚያ ሙስሊሞች የሱን ሱና መከተል ስላለባቸው ቁጭ ብለው መሽናት አለባቸው ብሎ ይሞግታል😅

እኔን የገረመኝ በዚህ ልክ የክርስትናው አለም መውረዱ ነው።
አንድ ቀን እንኳ ፍሬ ያለው ጥያቄ መጠየቅ ያቅታቸው?

እኛ ሁሌ ነገረ መለኮት፣ ነገረ ድህነት አንስተን እንሟገታለን እነርሱ ሁሌ ጭን ስር መደበቅ በመሰረቱ ክርስቲያን የተባለ ሰው መች ጽዳት አለውና? ዓፍረት ማጽዳት እንኳ የሙስሊም ነው የሚሉ ጀግኖች ናቸው🤤
ከነዚህ ሰዎች ፊየል ትሻላለች። ለምን እንደኾነ አላብራራው።
የሚያሳዝነው ግን የራስን ንጽህና መጠበቅ እንደ ነውር ታይቶ እራስን መጣል እና ዓፍረትን አለማጽዳት እንደ ጀብድ መታየቱ ነው።

ለነገሩ እነሱ የሚያመልኩት ወንድ እንኳ እጃችሁን ሳትታጠቡ ብሎ አይደል የሚያስተምረው😅 ታድያ እጅን መታጠብ እንደ ነውር ያየ ሃይማኖት ሃፍረትን መጽዳት እንደ ጽድቅ ቢያይ ነበር የሚያጅበኝ።

https://t.me/ashraf_com1

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

23 Nov, 07:55


ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ?

https://youtube.com/shorts/12Bv5TI5sFE?si=gV57PYuSljvxGyPV

🎙ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

22 Nov, 18:05


አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ የእርሱን ማንነት በተመለከተ፡ በአራት መንገዶች ገልጾልናል፡፡

:-1ኛ_ "እኔ"
አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ በመጀመሪያ መደብ ነጠላ ስያሜ   ‹‹First person singular term›› "እኔ" እያለ ራሱን ያስተዋውቃል።

አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለይ በአምልኮ አንቀጾች ላይ እኔ አሏህ ነኝ ከእኔም በስተቀር ሌላ አምላክ የለም እኔን አምልኩ እኔን ተገዙ በእኔ ተመኩ እያለ ራሱን በእኔነት ይገልጻል።

ለምሳሌ

إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡
{📗20:14}

إِنَّ هَٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ
ይህች (ሕግጋት) አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ፡፡
{📗21:92}

:-2ኛ_ አንተ
አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ በሁለተኛ መደብ ነጠላ ስያሜ Second person singular term›› ራሱን አንተ ብሎ ይገልጻል።

አምላካችን አሏህ በብዙ የቁርኣን ጥቅሶች ላይ   እኛ እንድንማጸነውና እንድንለምነው እርሱን ‹‹አንተ›› እያልን እንድንጠራው፡ እራሱን ‹‹በአንተነት›› ይገልጻል።

ለምሳሌ
إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
{📗1:5}

رَبَّنَا إِنَّكَ مَن تُدْخِلِ النَّارَ فَقَدْ أَخْزَيْتَهُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ
«ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታገባውን ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሉዋቸውም፡፡»
{📗3:19}

:-3ኛ_ እርሱ
  አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ በሦስተኛ መደብ ነጠላ ስያሜ፡- ‹‹Third person singular term›› ራሱን እርሱ ብሎ "በእርሱነት" ይገልጻል

እኛ ሙስሊሞች ስለ አምላካችን አላህ ስናስተምር እና ስንሰብክ የእርሱን ስሞችና ባሕርያት ለሰዎች ስናስተዋውቅ ‹‹እርሱ›› ጌታችን አላህ ማለት እንዲህ ነው! እያልን እንድናስተምር  በቁርኣኑ ላይ እራሱን "በእርሱነት" ይገልጻል፡፡

ለምሳሌ
قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
በል «እርሱ" አላህ አንድ ነው፡፡
{📗112:1}

وَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَٰنُ الرَّحِيمُ
አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ "ከእርሱ" በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡
{📗2:163}

:-4ኛ_ እኛ
አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ በመጀመሪያ መደብ ብዜት ስያሜ ‹ First person Plural term›› ራሱ "እኛ" ብሎ "በእኛነት" ይገልጻል

ለምሳሌ
إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ
እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
{📗15:9}

أَلَمْ يَرَوْا أَنَّا جَعَلْنَا اللَّيْلَ لِيَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

"እኛ" ሌሊትን በእርሱ ውስጥ እንዲያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን ለሚያምኑ ሕዝቦች በዚህ ውስጥ ተዓምራቶች አሉበት፡፡
{📗27:86}

إِنَّا أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ
"እኛ" በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ፡፡
{📗108:1}

አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ እኔ ብሎ ራሱን እንዳስተዋወቀው ሁሉ አንተ ብሎም እርሱ ብሎም እኛ ብሎም ራሱን ገልጿል።

ስለዚህ አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ እኔ ብሎ ራሱን በእኔነት እንደገለፀው ሁሉ አንተ እርሱ እኛ ብሎ ሲናገርም ስለ ራሱ እየተናገረ ነው።

:- አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ እኔ ብሎ ስለ ራሱ ተናግሮ ሌላ ቦታ ላይ አንተ ብሎ ሲናገር አላህ ስለ ሌላ አካል  እየተናገረ ሳይሆን ራሱን በአንተነት እየገለጹ ነው።

:-እንዲሁም አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ ስለ ራሱ እኔ ብሎ ተናግሮ ሌላ ቦታ ላይ ስለ ራሱ እርሱ ብሎ ሲናገር ሌላ አካል ስለ አሏህ እየተናገረ ሳይሆን ራሱን በእርሱነት እየገለፀ ነው።

:-እንዲሁም አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ እኔ ብሎ ስለ ራሱ ተናግሮ ሌላ ቦታ ላይ እኛ ብሎ ሲናገር ከሌሎች አካላት ጋር ሆኖ ሳይሆን ራሱን በግነት በክብር በልቅና በልዕልና እየገለፀ ነው።


ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

22 Nov, 16:12


(😀:)

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

22 Nov, 16:01


አሁን 666 እኔ ነኝ ወይስ መልስ የሰጣሁዋት ልጅ ናት? ወይስ ተመልካቾቹ ናችሁ? አንዱ 666 ነህ እያለኝ ነው(Lol😁)

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

20 Nov, 13:06


ልዩ ስጦታችን የልባችን መርጊያ
ቁርዓን እኮ ነዉ ከሸይጧን መራቂያ
ቢቀራ አይጠገብ ቢሰማ አይሰለች
ማናለ እንደሱ ስንደክም አበርች
::

https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

20 Nov, 07:01


በጧቱ ፈገግ በሉ(Lol😂)

ክርስቲያን ወገኖቻችን የውሸት ለሁሉን አርቲክል እንደሚሸመድዱት ባይብልን ቢሸመድዱ የት በደረሱ?😂

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

20 Nov, 06:59


እህ😂 አርቲክሉን እንደሸመደድሽው ባይብሉን ብትሸመድጂው የት በደረስሽ😁

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

14 Nov, 02:31


ተውሒድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለትን ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?» በላቸው"፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ኢሥላም የትምህርቱ ጭብጥ እና የመልእክት አንኳር ተውሒድ ነው፥ አህሉል ኪታብን ስናገኛቸው ቅድሚያ ወደ ተውሒድ እሳቤ እንጠራቸዋለን። ይህ የተውሒድ እሳቤ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه  ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 24 ሐዲስ 1
“ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንዳስተላለፈው ነቢዩ”ﷺ”  ሙዓዝን"ረ.ዐ." ወደ የመን በላኩ ጊዜ እንዲህ አሉ፦ "ከአሏህ በቀር አምላክ እንደሌለ እና እኔም የአሏህ መልእክተኛ መሆኔን እንዲመሰክሩ ጥራቸው"።   عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم بَعَثَ مُعَاذًا ـ رضى الله عنه ـ إِلَى الْيَمَنِ فَقَالَ ‏ "‏ ادْعُهُمْ إِلَى شَهَادَةِ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، وَأَنِّي رَسُولُ اللّٰه
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97 ሐዲስ 2
“ኢብኑ ዐባሥ እንዳስተላለፈው ነቢዩ”ﷺ”  ሙዓዝን ወደ የመን በላኩ ጊዜ እንዲህ አሉ፦ ”ከመጽሐፍ ሰዎች የሆኑ ሕዝቦች ታገኛለህ፡፡ በቅድሚያ የላቀውን አሏህን "አንድ ነው" እንዲሉ ትጠራቸዋለህ” ።  يَقُولُ سَمِعْتُ ابْنَ عَبَّاسٍ، يَقُولُ لَمَّا بَعَثَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم مُعَاذًا نَحْوَ الْيَمَنِ قَالَ لَهُ ‏ "‏ إِنَّكَ تَقْدَمُ عَلَى قَوْمٍ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ فَلْيَكُنْ أَوَّلَ مَا تَدْعُوهُمْ إِلَى أَنْ يُوَحِّدُوا اللَّهَ تَعَالَى

እዚህ ሐዲስ ላይ “ዩወሐዱ” يُوَحِّدُوا  የሚለው የግስ መደብ ይሰመርበት! “ዋሒድ” وَٰحِد  የሚለው ቃል "ዋሐደ" وَٰحَدَ  ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንድ"one" ማለት ነው፥ "ተውሒድ" تَوْحِيد  ማለት ደግሞ "አንድ-ነት"one-ness" ወይም "አሐዳዊነት"Monotheism" ማለት ነው፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለትን ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?» በላቸው"፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

"አንድ" ለሚለው ቃል የገባው ቃል “ዋሒድ” وَٰحِد  መሆኑ አንባቢ ልብ አድርግ! ስለዚህ "ተውሒድ" የሚለው ቃል "ዋሒድ" በሚለው ቃል "ኢሥቲንባጥ" اِسْتِنْبَاطْ ሲደረግ ቁርኣን ላይም አለ ማለት ነው። "አሏህ አንድ ነው" ብሎ የሚያምን “ሙዋሒድ” مُوَٰحِد  ማለትም "አሐዳዊ"Monotheist" ይባላል፥ "ተውሒድ" تَوْحِيد የሚለውን ቃል ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ተጠቅመውታል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 25
ጃቢር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንዳንድ "የተውሒድ ባለቤቶች" የሆኑ ሰዎች ፍም እስኪሆኑ ድረስ በእሳት ይቀጣሉ፥ ከዚያም የአሏህ ምሕረት ይደርሳቸውና ከእሳቱ ይወጣሉ"።  عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يُعَذَّبُ نَاسٌ مِنْ أَهْلِ التَّوْحِيدِ فِي النَّارِ حَتَّى يَكُونُوا فِيهَا حُمَمًا ثُمَّ تُدْرِكُهُمُ الرَّحْمَةُ فَيُخْرَجُونَ

የተውሒድ ባለቤቶች እስካላሻረኩ ድረስ አህሉል ጀናህ ናቸው፥ ቅሉ ግን ከሺር ውጪ ያሉትን ወንጀሎች ንስሓ እስካልገቡ ድረስ ለሥራቸው ተመጣጣኝ ቅጣት ተቀብለው ወደ ጀነት ይገባሉ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 113
አቡ ዘር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጂብሪል ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ ሲል አበሰረኝ፦ "ማንም ምንም ነገር በአሏህ ላይ ያላሻረከ ወደ ጀነናህ ይገባል። እኔም፦ "ቢሰርቅም እና ቢያመነዝርም? ብዬ ጠየኩት። እርሱም፦ "ቢሰርቅም እና ቢያመነዝርም" አለኝ"*። عَنِ الْمَعْرُورِ، قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ أَتَانِي جِبْرِيلُ فَبَشَّرَنِي أَنَّهُ مَنْ مَاتَ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‌‏.‏ قُلْتُ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى قَالَ ‏"‏ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 33
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንዳንድ የተውሒድ ባለቤቶች የሆኑ ሰዎች ከእሳት ይወጣሉ፥ ወደ ጀነት ይገባሉ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏"‏ سَيَخْرُجُ قَوْمٌ مِنَ النَّارِ مِنْ أَهْلِ التَّوْحِيدِ وَيَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏

"ተውሒድ" የሚለው ቃል ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ የለም" የሚሉ ሚሽነሪዎች ምንተ ሐፍረታቸው ሲገለጥ ተመልከቱ! "ሥላሴ" የሚለው ቃል ግን ባይብል ላይ እንደሌለ የክርስትና ምሁራን ይስማማሉ። እኛም ጥያቄአችን "ሥላሴ" የሚለው ቃል ባይብል ላይ አለ ወይ? ሳይሆን "ሥላሴ" የሚለው ቃል የወከለው አሳብ አለ ወይ? የሚል ነው፥ አሳቡ፦ "አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው" እና "አንዱ አምላክ ሦስት አካላት አሉት" የሚል ሲሆን ይህ እሳቤ ባይብል ላይ የለም። "ሥላሴ" የሚለው ቃል "ሠለሠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሦስት-ነት" ማለት ነው፥ የስም መደቡ "ሥሉስ" ማለትም "ሦስት" ነው። "አምላክ በአካል ሦስት ነው" የሚለው ይቅርና "ሦስት" የሚለው ቃል አምላክ አካባቢ ዝር ብሎ አያውቅም፥ ሥላሴ ሰው በማመኑ የሚድነበት በመካዱ የሚጠፋበት ትምህርት ቢሆን ኖሮ ከነቢያት ወይም ከሐዋርያት መካከል፦ "አምላክ አንድ ነው" ባሉበት አፋቸው ሳት ብሏቸው እንኳን "አምላክ ሦስት ነው" ብለው ያስተምሩ ነበር።
እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! «ሦስት ነው» አትበሉም! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉም! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

10 Nov, 15:04


ምንም ሳትሰላቹ በቀላሉ በአመት ለ-6 ጊዜያት ቁርአንን ማኽተም ትፈልጋላችሁ?

እንግዲያስ በየቀኑ አንድ "Hezb" ማለትም ግማሽ ጁዝዕ አንብቡ! ያ ማለት በሁለት ቀን አንድ ጁዝዕ ማለት ነው! ያ ማለት በ_60 ቀን ማለትም በሁለት ወር ሙሉውን ሠላሳ ጁዝዕ ቁርአን አኸተማችሁ ማለት ነው። ያ ማለት በ-12 ወራት ማለትም በአንድ አመት ሙሉውን ቁርአን ለ-6 ጊዜ አኸተማችሁ!🔥

ሞክሩት ሞክሩት ሞክሩት በርግጠኝነት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ኢንሻ አላህ።

📲https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

10 Nov, 12:58


የንፅፅር ትምህርት እና በእስልምና ላይ ለሚነሱ ትችቶች መልስ የሚሰጥባቸው ቻናሎች ለማግኘት
ይቀላቀላሉ ለመ🀄️🀄️👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿
👉🏿👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👉🏽👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👈🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👉🏽👉🏼👇🏻👇🏻👇🏻👈🏼👈🏽👈🏾👈🏿
👉🏿 👉🏾 ቻናሎቹ ለማግ ይንኩት👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👉🏽👉🏼👆🏻👆🏻👆🏻👈🏼👈🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👉🏽👆🏼👆🏼👆🏼👆🏼👆🏼👈🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👆🏽👆🏽👆🏽👆🏽👆🏽👆🏽👆🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👈🏿
👉🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿☝️


የንፅፅር ቻናል ያላቹ wave ለመቀላቀል

በዚ አናግሩኝ➥
@mustef123
✍️በወድም ሙስጠፋ

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

09 Nov, 07:41


"እሰልምልሻለሁ" ብሎ አግብቶ ካስወለዳት ቦኋላ ወይም ክርስትናን ተቀበይ አለበለዚያ ልጄን ትተሽ ጥርግ ማለት ትችያለሽ ይላታል።

እርሷም የዓይን ማረፊያ ልጇን እና የሞቀ ትዳሯን ትታ መሄድ ይከብዳትና ፍጡር እያመለከች ፍጡር ማምለኳ ስህተት እንደሆነም እያወቀች ወደ እሳት ትጓዛለች💔

ወደዚህ ጣጣ ውስጥ ከመግባቷ በፊት መጀመሪያ ከካሐዲ ወንድ መራቅ ነበረባት!

ይህ ጉዳይ በብዙ እኅቶቻችን ላይ እየሆነ ያለ ጉዳይ ነው።

وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

[ አል-በቀራህ - 120 ]
አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

08 Nov, 19:39


እውነት ነው ሰለምቴው ወንድማችን ኻሊድ Bio ላይ ያገኘሁት😊

"አንተ ያድነኛል "የምትለውን" የሚገድል አምላክ አለኝ።


لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا إِنْ أَرَادَ أَن يُهْلِكَ الْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ۗ وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

(ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 17)
እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማነው በላቸው፡፡ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

07 Nov, 18:13


Live stream finished (1 hour)

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

07 Nov, 17:02


Live stream started

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

07 Nov, 09:26


ክርስትያኖች ውይይት ላይ ማስረጃ ሲጠየቁ እንትና የሚባለው ሸይኽ ነው ሲናገር የሰማሁት አንድ ኡስታዝ ነው ሲናገር የሰማሁት ቄስ እንትና ነው ሲናገር የሰማሁት ከቱሩክ ፊልም ላይ ነው ያየሁት የሚሉት ለካስ የቄስ አባ ሸሃውዚን ቫይረስ ተላልፎባቸው ነው (Lol😁)

ከአህያ ጋር የዋለች
ግደር ___ለመደች አሉ😁

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

07 Nov, 09:16


ቄስ አባ ሸሃውዚን ተጠየቁ ለጥያቄው መልስ አጡ😃
📲https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

04 Nov, 10:07


የንፅፅር ትምህርት እና በእስልምና ላይ ለሚነሱ ትችቶች መልስ የሚሰጡ ቻናሎች ለማግኘት
👇👇👇👇👇
አበባውን #ንኩትና ቻናሎቹ ያግኙ
◍◍◍◍◍🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌿🌷
        🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌿🌷
      🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌿
   🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌿🌷
   🌺🌹ቻናሉቹ🌹🌹🌹🌹🌹🌿🌷
   🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌿🌷
    🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🌿 🌷አበባው ተጫኑት
         🌺🌹🌹🌿🌹🌹🌿🌷🌼
_🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌿🌷🌼💐
__🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌿🌷🌼💐
___🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌿🌷🌼💐

☝️☝️አበባውን ይጫኑት ቻናሉቹ ያግኙ ትጠቀሙበታላቹ

#የንፅፅር ቻናል #ያላቹ wave #ለመቀላቀል

በዚ
#አናግሩኝ@mustef123
✍️በወድም ሙስጠፋ

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

04 Nov, 03:45


የማለዳ ስንቅ የአላህ ቃል ትሰማ ነፍሳችን ትረጋጋለይ  ከቁረአንጋርእንኑር

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

01 Nov, 05:28


ሱረቱ አል ካህፍ

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

31 Oct, 11:25


□ ወንድም አህመድ (ትንሹ) ይህችን ቆንጅዬ አርቲክል አንብቡ ብሎናል። ወደ መጨረሻ አከባቢ ደግሞ ለቆንጂዬዋ ዱዓ አድርጓል መሰለኝ 😁

● እናም ወደ ቤቱ ጎራ ብትሉ ምርጥ ምርጥ መጣጥፎችን ታገኛላችሁ😊
https://t.me/AhmedResponse/260

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

31 Oct, 01:37


⛔️«ኒቃቧን ለብሳ ትማራለች»⛔️

👉'ላንች ነው'' ጀግናዬ ኒቃቢስቶ''

ለኒቃቢስቶች እና ዋጋ ለከፈሉልሽ ሁሉ ይሁንልኝ..!!

🔴«ኒቃቧን ለብሳ ትማራለች»🔴

👉ኦርቶ አማራ×ኦርቶ ጉራጌ×የኢስላም ጠላቴ=..........

ሸር በማድረግ አድርሱልኝ አደራ ሰጠኋችሁ

👉በዚህ ልክ እንደምሳሳልሽና እንደማከብርሽ ጠላቶች እንዳውቁ እፈልጋለሁና አድርሱልኝ!!

👉በወንድምሽ ኑረዲን አል አረቢ

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

30 Oct, 13:41


ከ_2 ደቂቃ እስከ 10 ደቂቃ የሚሆኑ አጫጭር ቪዲዮ "ከጥቅስ" ጋር የማቀናበር ልምድ ያላችሁ ካላችሁ በውስጥ አናግሩኝ ጀዛኩሙሏሁ ኸይር

@Mukamil_Hussan

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

25 Oct, 05:09


ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ pinned an audio file

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

25 Oct, 04:53


ሱረቱ አል-ከህፍ 1-10

በኡስታዝ ሳዳት ሀፊዞሁሏህ

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

24 Oct, 14:43


የማታ ግብዣ
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

24 Oct, 06:28


እናንተ በሕይወት እንኑር እንጂ ብዙ እንሰማለን😁

قالَ يا محمَّدُ ما الإحسانُ قالَ أن تعبدَ اللَّهَ كأنَّكَ تراهُ فإنَّكَ إن لا تراهُ فإنَّهُ يراكَ


ሐዲሱ ጂብሪል በሚባለው ሐዲስ ላይ ጂብሪል ነቢዩን ስለ ኢሥላም እና ስለ ኢማን ከጠየቃቸው ቦኋላ አስቀጥሎ ስለ ኢሕሳን የጠየቃቸው ኢሕሳን የሚለውን ስለ ዒሳ ነው የጠየቃቸው ስለዚህ ዒሳ መመለክ እንዳለበት ያሳያል የሚሉ ክርስቲያን ተከራካሪዎችም መጥተዋል ወቸው ጉድ ነው አሉ!😁

ኢሕሳንን እና ዒሳን በምን እንዳገናኟቸው አላህ ይወቅ😂

ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ያሳፍራል የምር ሼም ነው ወገኖቼ ሆሆ😁

ኢሕሳን ማለት መልካም ሥራ ስራን ማሳመር ማለት እንጂ ኢሕሳን ማለት ዒሳ ማለት አይደለም።😁

۞ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

(ሱረቱ አል-ነሕል፥ - 90)
አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡

እዚህ አንቀጽ ላይ በማሳመር ለሚለው የገባው የአረብኛ ቃል وَالْإِحْسَانِ "ኢሕሳን" መሆኑ ልብ በል።

🎙ሙከሚል
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

24 Oct, 06:03


የኦሪት መጻሕፍት መበረዝ!

🎙ሙከሚል

VS

🎙 ሱራፌል

📲https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

21 Oct, 08:04


የነብዩ "ﷺ" ልጅ ኢብራሒም በሞተበት ቀን የጸሀይ ግርዶሽ ተከስቶ ነበር። ሰዎቹ ክስተቱን ከሳቸው ልጅ መሞት ጋር በማገናኘት የሀዘን ምልክት አድርገው ወስደውት ነበር። ኃላ ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ሲሰሙ ግን መሳሳታቸው ገልጸው ገሰጿቸው። ጸሀይና ጨረቃ የአሏህ ﷻ ተአምራት/ምልክቶች መሆናቸውን የጸሀይ ግርዶሽም በአንድ ሰው ሞትም ሆነ ህይወት ምክንያት የሚፈጠር እንዳልሆነ አብራርተው ስህተታቸውን አረሙ።

አንድ ሀሰተኛ ነብይ ቢሆን መሠል ወርቃማ እድልን ፈጽሞ አያሳልፍም ነበር። ክስተቱን ተመርኩዞ አይደለም በተቃራኒው ሊናገር ይቅርና ሀሳቡን በማጠናከር "ተመልከቱ በልጄ መሞት ሰማይ እንዴት እንዳዘነ" በሚል ለዚህ ሀሳብ መጀመሪያውኑ የቀረቡ ሰዎችን በተሻለ ለማሳመን እድሉን ይጠቀምበት ነበር። ግን ለእውነተኛ ነብይ ከእውነት በላይ ማስረጃም ጉዳይም የለውምና ይህንን የሚያደርጉበት ምክንያት ስልነበራቸው ፈጽሞ አላደረጉትም፣ ማድረግም አይጠበቅባቸውም ነበር..!

የሕያ ኢብኑ ኑሕ
https://t.me/Yahyanuhe

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

21 Oct, 05:58


#አትቆጣ!

ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ:

﴿أنَّ رَجُلًا قالَ للنَّبيِّ ﷺ: أوْصِنِي، قالَ: لا تَغْضَبْ. فَرَدَّدَ مِرارًا، قالَ: لا تَغْضَبْ.﴾

አንድ ሰው ለረሱል (ﷺ) መጥቶ ምከሩኝ አላቸው ‘አትቆጣ አሉት!’ ደጋግሞ ሲጠይቃቸው ‘አትቆጣ አሉት!’

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 6116

በሌላ ሐዲሳቸው ﷺ፦

﴿ليسَ الشَّدِيدُ بالصُّرَعَةِ، إنَّما الشَّدِيدُ الذي يَمْلِكُ نَفْسَهُ عِنْدَ الغَضَبِ.﴾

“ጀግና ማለት ታግሎ የሚጥል ሳይሆን በንዴት ግዜ እራሱን የሚቆጣጠር ነው።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል 6114

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

20 Oct, 06:55


ጥያቄና መልስ

📲ሞት በማን ምክንያት ወደ አለም ገባ?

ውይይት

📲ለፈጣሪ ሕይወት ይሰጠዋልን?

📲ለኢየሱስ ሕይወት የሰጠው ማን ነው?

📲ኢየሱስ በማን ሃይል ነው በሕይወት የሚኖረው?

📲ሰው ከእንስሳት ይበልጣል ወይስ አይበልጥም?

🎙ወንድም ሙከሚል

🎙 ከሁለት ወገኖቻችን ጋር

https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

19 Oct, 19:12


አማኝ ጂን?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው።

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
(📗ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

አምላካችን አሏህ ሰዎችን እና አጋንንትን እርሱን እንዲያመልኩት ነው የፈጠራቸው።

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
(📗ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

አላህ ሰዎችንም ሆነ አጋንንትን እርሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩት ሲፈጥራቸው ግን ነጻ ምርጫ የሌላቸው አድርጎ ሳይሆን አላህ ለሰዎችም ለአጋንንትም የማመንና ያለማመን ነጻ ምርጫ ሰጥቷቸዋል።

وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ ۚ
(📗ሱረቱ አል ከህፍ፥ - 29)
«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡

قَالَ اهْبِطَا مِنْهَا جَمِيعًا ۖ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ ۖ فَإِمَّا يَأْتِيَنَّكُم مِّنِّي هُدًى فَمَنِ اتَّبَعَ هُدَايَ فَلَا يَضِلُّ وَلَا يَشْقَىٰ
(📗ሱረቱ ጣሀ - 123)
አላቸው «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ሁላችሁም ከእርሷ ውረዱ ከእኔም የኾነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪየን የተከተለ አይሳሳትም አይቸገርምም፡፡

:-ከሰዎችም ሆነ ከጂኒዎች ነጻ ምርጫውን ተጠቅሞ "ያመነ" ሙሥሊም ይባላል ገነትም ይገባል።

وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا
(📗አል-ጂን - 14)
«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አልሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»

وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ
(📗ሱረቱ አል ረሕማን - 46)
በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡

:-ነጻ ምርጫውን ተጠቅሞ "የካደ ደግሞ" ከሐዲ ሲባል ወደ ገሃነም ይገባል።

وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا
(📗አል-ጂን - 14)
«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች(ከሐዲዎች) አልሉ፡፡ የሰለሙማ  እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»

وَأَمَّا الْقَاسِطُونَ فَكَانُوا لِجَهَنَّمَ حَطَبًا
(📗አል-ጂን - 15)
በዳዮቹማ(ከሐዲዎች) ለገሀነም ማገዶ ኾኑ፡፡

قَالَ اخْرُجْ مِنْهَا مَذْءُومًا مَّدْحُورًا ۖ لَّمَن تَبِعَكَ مِنْهُمْ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكُمْ أَجْمَعِينَ
(📗ሱረቱ አል-አዕራፍ - 18)
«የተጠላህ ብራሪ ስትኾን ከእርሷ ውጣ፡፡ ከእነርሱ የተከተለህ ከእናንተ ከመላችሁም ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው፡፡

:-አሏህ እርሱን እንዲገዙት ብሎ የፈጠራቸውና በተሰጣቸው ነጻ ምርጫቸው አማኝ የሆኑ አማኝ ጂኒዎች የእምነት ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ናቸው።

إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
(📗ሱረቱ አል-ሁጁራት - 10)
ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡

:-አሏህ እርሱን እንዲገዙት ብሎ የፈጠራቸውና በተሰጣቸው ነጻ ምርጫ ክህደትን መርጠው  የካዱ አመጸኛ ከሐዲ ሰይጣናት ጠላቶቻችን ናቸው።

إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَاتَّخِذُوهُ عَدُوًّا ۚ إِنَّمَا يَدْعُو حِزْبَهُ لِيَكُونُوا مِنْ أَصْحَابِ السَّعِيرِ
[ 📗ሱረቱ አል-ፈጢር - 6 ]
ሰይጣን ለናንተ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ጠላት አድርጋችሁ ያዙት፡፡ ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲኾኑ ብቻ ነው፡፡

:-እሩቅ ሳንሄድ በባይብል አጋንንት ፈጣሪ አንድ እንደሆነ ያምናሉ በመፍራትም ይንቀጠቀጡማል።

“እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።”
  {📗 ያዕቆብ 2፥19}

:-አጋንንት በእግዚአብሔርም "ካመኑና" እርሱን በመፍራት ከተንቀጠቀጡ አማኝ ናቸው ማለት ነው።

:-ከላይ ያለውን በያዕቆብ መልዕክት 2:19 ላይ ያለውን "አጋንንትም" እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ "ያምናሉ" የሚለውን ቃል ሚሽነሪዎች አይ ያምናሉ ሲባል ይገዛሉ ይታዘዛሉ ማለት አይደለም ብለው ለመቅጠፍ ይሞክራሉ እውነታው ግን "አመነ' ወይም "አማኝ" የሚለውን ቃል ከመዝገበ ቃላት መመልከት ይቻላል።

"አማኝ" ወይም "አመነ" የሚለውን ቃል የአማርኛ መዝገበ ቃላት እንደዚህ በሚል ያስቀምጠዋል

:-"አመነ" ማለት ያለ "ጥርጥር ተቀበለ" ተስማማ  "አረጋገጠ" ታዘዘ "ገበረ "ተገዛ

:-"አማኝ" ማለት "የአንድ "ሐይማኖት" ተከታይ የሚከተለውን "ሐይማኖት "አጥብቆ "የያዘ" ማለት ነው።

(📗የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል ኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ
የካቲት 1993) ገጽ 305)

:-አጋንንት አማኞች መሆናቸውን ካየን ዘንዳ አማኞች ደግሞ ወንድማሞች ናቸው!

“እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።”
  (📗ማቴዎስ 23፥8)
እንዲሁም በማርቆስ ወንጌል 3:33-35 እና በዕብራውያን 2:13 ወዘተ አማኞች ወንድማሞች ተብሏል።

ስለዚህ ሙሥሊሞች ከጂኒዎች መካከል አማኞች አሉ እነርሱ የእምነት ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ናቸው  ብለው ሲናገሩ እንዴት የጂኒ አማኝ ይኖራል እንዴትስ የእምነት ወንድሞቻችን ናቸው ትላላችሁ ብላችሁ ሊትደነቁና ልትገረሙ  አይገባም።

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

18 Oct, 07:03


ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።”
— መዝሙር 137፥9

ይህን መጽሐፍ ይዘው ነው እንግዲህ እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነው እያሉ የሚደሰኩሩት?

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

18 Oct, 03:39


🌸بســـــــم اللــــه الرحمــــن الرحيــــــم»🌷

🌹የጅመኣ ስጦታየ🌹

🌹ሱረቱል ካህፍ🌹

በወንድማችን  ቶውፊቅ አልሀበሽ

https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

17 Oct, 09:29


በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሌለበት አምላክ አሏህ።

اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ 

"አላህ ከእርሱ በቀር" ሌላ "አምላክ የለም፡፡ "ሕያው" ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም "እንቅልፍም አትይዘውም፡፡"
(📗አል-በቀራህ - 255)

 عن أبي موسى قال قام فينا رسول الله صلى الله عليه وسلم فقال إن الله لا ينام ولا ينبغي له أن ينام 
አቢ ሙሳ (ረ.ዐ) እንደተረከው
የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብሏል
"አሏህ"አይተኛም "መተኛትም" ለእርሱ"ተገቢው አይደለም።
[📗ሶሒህ ሙሥሊም  179 c]

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

17 Oct, 08:54


ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ ስለዚህ ተገዙት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡
[ 📗ሱረቱ አል-አንዓም፣ - 102 ]

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

17 Oct, 08:41


🔵 አደም እና ሙሳ ተከራከሩ!

ብዙ ጊዜ ክርስትያን ወገኖቻችን በኢሥላም የውርስ ኃጢአት አለ ብለው ለሚያቀርቡትም ማምታቻ የማያዳግም ምላሽ ነው!

🎙ኡሥታዝ አቡ ሀይደር

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

13 Oct, 07:31


عقبة بن عامر رضي الله عنه قال: قال رسول الله ﷺ: “لَا تَكْرَهُوا الْبَنَاتِ، فَإِنَّهُنَّ الْغَالِيَاتُ

ዑቅባህ ኢብኑ ዓምር (ረ.ዐ) እንደተረከው!
የአሏህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብሏል ሴቶችን አትጥሉ እነርሱ "ውድ" ናቸውና።

(📗السلسلة الصحية 3206)

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

12 Oct, 07:55


በባይብል ውስጥ ብዙ ነገሮች "እርኩስ" ተብሎዋል ከእነዚህ እርኩስ ከተባሉት ውስጥ አንዷ "ሴት" ልጅ" ናት።

“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት፤ እንደ ሕመምዋ መርገም ወራት ትረክሳለች።”
  — ዘሌዋውያን 12፥2



ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

11 Oct, 12:04


ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ pinned «እስቲ ሳኡዲ ውስጥ መዲና ላይ ስራ ፈልጉ ለብዙ ጊዜ ስራ አጥታ የተቀመጠች ልጅ አለች! እንዲሁም ጂዳም ላይ ካለ አሳውቁኝ ዱባይም ላይ ስራ ካገኛችሁ የወንድም ሆነ የሴት ስራ ካለ አሳውቁኝ! ካገኛችሁ በዚህ አድራሻ አሳውቁኝ @Mukamil_Hussan»

5,520

subscribers

210

photos

87

videos