Eliyah Mahmoud @e_m_ahmoud Channel on Telegram

Eliyah Mahmoud

@e_m_ahmoud


Eliyah Mahmoud (English)

Are you passionate about self-improvement and personal growth? Look no further than the Eliyah Mahmoud Telegram channel! Led by the inspirational Eliyah Mahmoud, this channel is dedicated to helping individuals reach their full potential and live their best lives. Eliyah Mahmoud is a renowned motivational speaker and life coach who has helped countless people transform their lives through his powerful guidance and wisdom. Whether you're looking to boost your confidence, overcome challenges, or achieve your goals, Eliyah Mahmoud provides the tools and motivation you need to succeed. Join the e_m_ahmoud Telegram channel today and start your journey towards a happier and more fulfilling life!

Eliyah Mahmoud

19 Jan, 02:36


https://youtu.be/rWNgcp7F9FQ?feature=shared

Eliyah Mahmoud

16 Jan, 10:56


በርካታ በዙሪያቸው ያሉ ሐገራት እንኳ ትተዋቸው የምዕራቡ ነጻ ሕሊና የገዛው ማሕበረሰብ በአደባባይ ስለ ነርሱ ድምጹን ከፍ ሲያደርግ ቆይቶ እነሆ ከዓመት በላይ የቆየው የፍልስጤም የነጻነት ትግል በሰላም ስምምነት ሊቋጭ የተቃረበ ይመስላል።

ብቻቸውን ኹሉንም ነገር ኾነው፥ኹሉንም ዓይነት መከራ አይተው፣በርሃብና ቸነፈር ሕጻናት ሳይቀር አልቀው አኹንም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረና እንዳልኾነባቸው ኹሉ ሰንደቃቸውን ከፍ አድርገው በፍርሃት ለራደውና ተድላ ለገደለው የዐረብ ሕዝብ ምሳሌ የኾኑ ሕዝቦች ናቸው።

አላህ ሰላሙን ያዝልቅላቸው!!!
https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

16 Jan, 10:33


إلى شرف الأمّة .. إلى غزّة
https://youtube.com/watch?v=1z4t8MzkyGY&feature=shared

Eliyah Mahmoud

15 Jan, 19:22


١٥ يناير ٢٠٢٥
https://youtube.com/watch?v=l7-boSsKgIE&feature=shared
በነብዩ ላይ የዋሸው ሰው መጨረሻ

Eliyah Mahmoud

14 Jan, 10:42


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብረሃማዊ ሃይማኖቶች በሚል ሶስቱን ማለትም ኢስላም፣ክርስትናና አይሁድን አጣምረው ኹሉም አንድ አምላክን ይሰብካሉ ስለኾነም አንድ ናቸዉ የሚል ሰበካና ጥምቀት እያየን ነው።

ይህ ሰበካ በየትኛውም ስሌት በአልቦ መረጃ የሚንቀሳቀስ ተራ ወሬ መኾኑ ግልጽ ቢኾንም ከጀርባው ግን ሰዎችን ሃይማኖት የለሽ የማድረግ ዕቅድ እንዳለው ቅቡል ነው።

ዛሬ ላይ ትልልቅ ኡማውን ሊጠቅሙ የሚችሉ ሐሳቦች ፈጽሞ ቦታ አጥተው መሰል የኩፍር አካሄዶች ግን ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው እየተቀጣጠሉ ይገኛሉ።

አንድ ከዐረቦች ጋር ግንኙነት ያለው በትምህርት ደረጃው የዶክትሬት ዲግሪ ያለው ወዳጄ እንዳጫወተኝ በኢብራሂሚያ ዙሪያ የትኛውም ዓይነት ደጋፊ ምክረ-ሐሳብ (ፕሮፖዛል) ካለ በቀላሉ ከዐረቦቹ በጀት ማግኘት እንደሚቻል፣ ከዛ ውጪ ግን ለተለመዱ ዓይነት ዳዕዋዎች የሚበጀት ቀርቶ የሚፈልጋቸውም እንደሌለ አስረግጦ አረዳኝ።

ወዳጄ ዛሬ ላይ ከመቼውም ጊዜ በባሰ መልኩ ኹላችንም በምልዓት ወደ ኢስላማዊ ዕውቀት የምናመጣበት ቤተሰቦቻችንንም ከዛ አኳያ የምንመክርበት ወቅት ነው።

ስንቱ ሚዲያ ላይ በዳዕዋው የምናውቀው በዚህ ኢብራሂሚያ የኩፍር ጥሪ ተሰናክሎ ዛሬ የኢብራሂሚያ ሃዋሪያና ዳዒ ኾኗል!?

اللهم يا مقلب القلوب ثبت قلوبنا على دينك
https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

14 Jan, 04:43


ما لا تعرفه عن مشروع البيت الإبراهيمي (الديانة الإبراهيمية) و الغاية منه...
https://youtube.com/watch?v=be43XViSaQw&feature=shared

Eliyah Mahmoud

11 Jan, 15:21


ወራሪዋ የአይሁድ መንግስት በፍልሥጤም ላይ የጀመረችውን የግፍ ጭፍጨፋ መቀጠል አለባት።


አሻንጉሊት የኾነውን የባይደን መንግሥት መስማት አይገባትም...ወዘተ እያለ በሚገደሉ ፍልስጤማውያን ላይ የውስኪውን ዋንጫ ሲያነሳ የነበረው ጄምስ ውድስ እነሆ ውድ ቤቱ ሎስ አንጀለስ ላይ በተነሳው ሰደድ እሳት ዶጋ አመድ ኾነ።

በዚህ ሰቅጣጭ ክረምት በቅዝቃዜና ርሓብ እያለቁ ባሉ የፍልስጤም ሕጻናት እምባ ላይ የሳቀው ጄምስ በአደባባይ ባንክ ውስጥ ባለኝ ስባሪ ሳንቲም ደግሜ ቤቴን እገነባው ይኾናል ብሎ አንብቷል።


هل الجزاء الاحسان إلا الاحسان


በሙስሊሙ ደም ላይ የተሳለቀ ኹሉ ያለምንም ርሕራሔ በተሳለቀው ልክ፣ባሴረው ልክ አላህ የጥፋቱን መዓት ያውርድበት።

اللهم آمين

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

11 Jan, 15:10


https://vm.tiktok.com/ZMk5DFVkY/

Eliyah Mahmoud

07 Jan, 07:00


40 Year Evangelist Challenges Muslim On The Crucifixion Of Jesus! Muhamm...
https://youtube.com/watch?v=RIPUEGsRKSs&feature=shared

Eliyah Mahmoud

06 Jan, 11:16


ከስነ-ልቦና ሰዎች ምክር


ከሰዎች ከአንተ በርካታ እንክብካቤን የሚፈልጉ አሉ፡፡ ኾኖም በተንከባከብካቸው ልክ አንተ ኹሌም ለነርሱ የሚገባውን እንዳላደረክ ስለሚያስቡ ለአንተ ቦታ ሊኖራቸው ይቅርና ይልቁንም አንተ ግዴታኽን እንደተወጣኽ አደርገው ያስቡታል፡፡

እንዚህን ሰዎች ስትሸሻቸው ስለሚፈልጉኽ ሳይኾን እነሱ ከሰዎች ያገኙት የነበረውን አጓጉል ክብርና ቦታ ያጡ ስለሚመስላቸው ብቻ ኪሳራቸው ስለሚያስፈራቸው ይፈልጉኻል፡፡

እነዚህ ሰዎች ከሚገለጡባቸው ምልክቶች አንዱ ትንሽንም ቢኾን መስዋዕትነት ወይም ውለታ መዋል በፍጹም አይፈልጉም፡፡

ቀረብኹት የሚሉት ሰው እጅግ አሳሳቢ ነገር እንኳን ቢያጋጥመው፣ምንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ አይደሉም፡፡

ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? ካሉ አቅም በፈቀደ ልክ ከነዚህ ሰዎች መሸሽ - ይህ ለውስጥ ሰላም ሲባል መወሰድ ያለበት እርምጃ ነው፡፡

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

02 Jan, 09:35


ዕውቅና በሰለፎች ዘንድ ፈተና ነበር ዛሬ ግን የስኬት መገለጫ ኾነ።

በፈተናና በስኬት መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ። ይህ ልዩነት በሰለፍችና በዛሬው ትውልድ መካከል ያለውን ተጨባጩን የመረዳት አቅም ፍንትው አድረጎ የሚያሳይ ነው።

Eliyah Mahmoud

02 Jan, 09:31


‏صورة من Eliyah

Eliyah Mahmoud

30 Dec, 14:17


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

#ኢስላም ማለት #ምን ማለት #ነው

መልሱን በመንካት ውሰዱ 🎁

➢ኢስላም ሰላም ማለት ነው

➢ኢስላም ማለት ለአድ አምላክ መገዛት ማለት ነው


➢ኢስላም ማለት የአድ አምላክ እጅ መስጠት
መገዛት ማለት ነው


➢ኢስላም ማለት በቃ ፍቺ የለውም


⭕️ ትክክለኛው  መልስ ስትነኩ  ብቻ  የሚመጣውን
𝕒𝕕𝕕   በመጫን ጠቃሚ  ቻናሎች ታገኛላችሁ


ስለ እሥልምና እምነት ምን ማወቅ ይፈልጋሉ? ይጠይቁ🎁
ጥያቄ
#ካላቹ በዚ ግቡና #ጠይቁ👇👇👇
https://t.me/Contrastc_hannelswave

Eliyah Mahmoud

29 Dec, 07:12


ቀለበት በየትኛው ጣት ላይ ይጠለቃል?!
.....

نَهَانِي رَسولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عليه وَسَلَّمَ
أَنْ أَتَخَتَّمَ في إصْبَعِي هذِه، أَوْ هذِه، قالَ: فأوْمَأَ إلى الوُسْطَى وَالَّتي تَلِيهَا.

المزيد..
الراوي : علي بن أبي طالب | المحدث : مسلم | المصدر : صحيح مسلم
الصفحة أو الرقم :2095

ዓሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በሚያወራው በዚህ ሐዲስ መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጠቋሚና መሐከለኛው ጣቶች ላይ ቀለበት እንዳላጠልቅ ከለከሉኝ በማለት ተናግሯል።

ምክንያቱን ዐወቅነውም ዐላወቅነውም መልክተኝው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የከለከሉንን መከልከል ግዴታ ነው።

መረጃው ከደረሰን በኋላ ግን እምቢኝ ማለት በአላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ላይ ማመጽ ስለኾነ ወጣቶች ይታሰብበት።

ሴት ልጅ በኹሉም ጣቷ ላይ ቀለበት ማጥለቅ እንደምትችል ይሰመርበት።

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

29 Dec, 07:01


🔰 እዚህ ቻናል ላይ የተለቀቁ ኦድዮዎች በጥቂቱ። በቀላሉ ለማግኘት 👇 ፅሁፉን ተጭነው መልሱን ያድምጡ። ኦድዮዎቹ አጫጭር ናቸው ፤ ባረከላሁ ፊኩም🔰

➸ ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል አንድ
➸  ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል ሁለት
➸  ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል ሶስት
➸ አላህ በነብዩ ዒሳ አንደበት ለምን አሕመድ የሚለውን ስም ተጠቀመ?ክፍል አንድ
➸ አላህ በነብዩ ዒሳ አንደበት ለምን አሕመድ የሚለውን ስም ተጠቀመ? ክፍል ሁለት
➸ ከወገብና ከርግብግቢቶች መካከል ይወጣል ሲል
➸ ጂኖች ነብይ ነበራቸውን?
➸ ከብጤው አንዲት ምዕራፍ አያመጡም
➸ ከብጤው አንድ አያመጡም ክፍል ሁለት
➸ ግምታዊ አገላለፅ በቁርአን
➸ የአላህ ፍላጎት በሰዎች ፍላጎት ላይ.
➸ ከአላህ ውጭ ሌሎች አማልክት ቢኖሩስ?
➸ኢስላም ዘረኝነትን ያስተምራልን?
➸ የነቢይነት ማህተም ወይስ እጢ
➸ ሐዲሱል ቁድስና ሐዲስ አነበዊ ክፍል አንድ
➸ ሐዲሱል ቁድስና ሐዲስ አነበዊ ክፍል ሁለት
➸ ወሕይ ማለት ምን ማለት ነው?
➸ ኣላህ ወደ መላኢካ ወሕይ እንዴት ነው የሚያደርገው?
➸ እውን አላህ ይረሳልን?
➸ ሰው ሰራሽ ዝናብ
➸ ከአንድ በላይ ማግባት
➸ የዘይነብና የመልእክተኛው ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋብቻ
➸ ነቢያትና ዝሙት በመፅሐፍ ቅዱስ
➸ ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡
➸ በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤
➸ የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከአራት በላይ ማግባትና ከአራት በላይ እንዳታገቡ የሚለው ቁርኣናዊ ሕግ
➸ አጋንንት የሩቅ ምስጢር ያውቃሉን?
➸ በጃሂሊያ አጠራር የታገዘውን የአባትህን…ብላችኹ አነውሩት
➸ ሩህ ፍጡር ነው ወይስ ፈጣ
➸ ወደ ዝንጀሮ፣ከርከሮ ስለተለወጡ ሰዎች
➸ ወደ ግመል አይመለከቱምን እንዴት እንደተፈጠረች
➸ ግመል ከሰይጣን ተፈጥራለች?
➸ ኢስላማዊ የጥቢ ህግጋት
➸ ኣላህ ለምን እኛን መፈተን አስፈለገው?

ይቀጥላል ኢንሻአላህ.......

Eliyah Mahmoud

28 Dec, 14:13


ምክንያት መስጠት
...

አንዳንዶቻችን ዱንያ ላይ ስንኖር ለራሳችን ኹሉንም ዓይነት ምክንያት ሰጥተን ሰዎች ያንን ምክንያት ያልነውን እንዲቀበሉን ስናስገድድ ይታያል።

ለሰዎች ደግሞ በአንጻሩ ምንም ምክንያት ሳንሰጥ መስጠትም ሳንፈልግ በእጃችን የምንቆጣጠራቸው ሮቦቶች እንደኾኑ ኹሉ በምንፈልጋቸው ሜዳ ላይ መገኘት አለባቸው የሚል አጓጉል ትምክኽትም አለን።

ወዳጄ በዚህች ዱንያ ላይ እኮ ኹሉም ማንም የማይሸከምለት የራሱ ጣጣ አለው።

ለመኾኑ እንዴት እንዴት ባስብ ነው የኾነን ሰው በየ አውጫጭኙና እህል በሚወቃበት አውድማ ኹሉ ካላገኘኹኽ የምለው?

ዕውነት ዕውነት እሎታለኹ ወዳጄ የገዛ ልጄም ቢኾን በዚህ ልክ ላሽከርክርኽ ብለው በጄ አይልም!!!

እኛ በፈለግነው ሜዳ የምንጋልበው ሌት ከቀን የገራነው ፈረሳችን ብቻ ነው። እሱም ቢኾን የኾነ ቀን መቆሙ አይቀርም።

ምን መሰሎት ወዳጄ? በዚህች ምድር ላይ እኔ የፈለግኹት ኹሉ ይኹንልኝ የማለት አባዜ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩትም አንዱና አደገኛው ምክንያት ግን ራስን እጅግ አግንኖ ማየት ነው።

የሰው ልጅ ከናለበት አሸር ባሸር ስብዕና ጋር በዚህ ልክ የተለጠጠ ራሰ-ቁልልነት በሂደት ሰዉ ኹሉ ዐይንኽን ለዐፈር ብሎ እንዲሸሸ ዐይነተኛ ምክንያት ነውና እነ አያ ነውጤ ይታሰብበት!

ሰዎች ከመሰል አጓጉል መልካም ስራን ከሚያበላሹ ባሕሪያት ለመላቀቅ ኢስላም ተዝኪየቱ አኑፉስ በሚል የሚያስተምረንን እጅግ ጥልቅ የስነ ልቦናና የነፍስ ሕክምናን መለማመድ የግድ ይላቸዋል።

ነገ አላህ ፊት አሸናፊ ኾነው የጀነት ባለቤት የሚኾኑ በተዝኪያ ትምህርት ቤት ውስጥ የተመላለሱና ልቦቻቸውን በሚችሉት ልክ መወልወል የቻሉ ብቻ ናቸው።

يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ

ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡


إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

27 Dec, 14:23


https://youtu.be/rJEtrzx2Xhk?feature=shared

Eliyah Mahmoud

26 Dec, 18:07


https://vm.tiktok.com/ZMkk81rpR/
ስላሴ በኢስላም (12)

Eliyah Mahmoud

25 Dec, 13:47


ቁርአን የልብ ወዳጅ
....

ከሰዎች ጋር ያለኽ ቀረቤታ ምንም ቢኾን የኾነ ቀን ያስቀይሙኻል።

ወዳጄ ኹሉም ሰዎች ሊያስደስቱህ አይችሉም።

እንዲያውም አንዳንዶች እንደ ቀጤማ ብትጎዘጎዝላቸው ዓላማቸው አንተን መውቀስ ብቻ ይኾናል።

ነብዩ ሉጥ (ዐለይሂ አሰላም) ያን ያህል የኾነላቸው ሕዝቦቹ በስተመጨረሻ እነዚህ መጥራራት የሚፈልጉ ስዎች ናቸውና አስወጧቸው በሚል ተገፍቷል ፦

قالوا أخرجوهم من قريتكم إنهم أناس يتطهرون

ከሰዎች ደግሞ በአንተ ስኬት ብቻ የሚጠሉኽና በምቀኛ ልቦቻቸው ውስጥ የሚያገኙት አንተን ብቻ የኾኑ አሉ።

ለነዚህ ደግሞ ከምቀኞች ተንኮል ጎህን በሚቀደው አላህ (ጀለት ከላሙሁ) ተጠበቅ፦

قل أعوذ برب الفلق....ومن شر حاسد إذا حسد

ከሰዎች በአንተ ተስፋ መቁረጥ የነርሱ ተስፋ የሚለመልም የሚመስላቸው አሉ።

ምናልባትም ከአንድ ሜዳ ተገናኝታችኹ ከኾነ፣ጨዋታውን ጥለኽ ብትወጣና እነርሱ ብቻ ከሜዳው እንዳሉ ቢነገርላቸዉም ይወዳሉ።

ለነዚህ ሰዎች ደግሞ ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ኸዲርን ፍለጋ ጉዞ በወጣበት የተናገረውና የሰነቀው ብርታት ኃይል ይኹንህ፦

وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِفَتَاهُ لَا أَبْرَحُ حَتَّىٰ أَبْلُغَ مَجْمَعَ الْبَحْرَيْنِ أَوْ أَمْضِيَ حُقُبًا

ሙሳም ለወጣቱ «የሁለቱን ባሕሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምኼድ ድረስ (ከመጓዝ) አልወገድም»

ሕይወት ምነኛ ብትከፋ በቀጣይ ምዕራፏ የተሻለች ናትና የመጨረሻው ፊሽካ እንደተነፋ አታስብ፦


وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ

ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡

ወደ የት እንደምትኼድ ጨርሶ ከጠፋኽ ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ከኋላው ፊርዓውን ከነ ጦሩ ከፊት ለፊቱ ደግሞ ባሕሩ ሲያፋጥጠው ያለውን አስታውስ፦


قَالَ كَلَّا ۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ

(ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» አለ፡፡

ሕመም እያሰቃየኽ ከኾነ አዩብን (ዐለይሂ አሰላም) ከነበረበት ሕመም ያወጣውን አላህ በተስፋ ምሉዕነት ለምን፦


۞ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡


فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَكَشَفْنَا مَا بِهِ مِن ضُرٍّ ۖ وَآتَيْنَاهُ أَهْلَهُ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنْ عِندِنَا وَذِكْرَىٰ لِلْعَابِدِينَ

ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን፡፡ ቤተሰቦቹንም ከእነሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው፡፡"

ወዳጄ አላህ ለኛ የሚያስፈለገንን ኹሉ በቁርአን እንደጠቆመን ልብ ይሏል።

ታዲያ ቁርአንን የልባችን ወዳጅ ማድረጉና ሌት ከመዓልት ማንበቡና ማስተንተኑ እንደምን ከበደን??

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

23 Dec, 16:21


ስላሴ በኢስላም (11)
https://youtube.com/watch?v=eHsZHrzMwEQ&feature=shared

Eliyah Mahmoud

21 Dec, 19:59


يسوع يحيي الموتى .. هل هو إله أم نبي؟ مناقشة موضوعية #مدارس_السبت 109 #م...
https://youtube.com/watch?v=88a_n3ECSGg&feature=shared

Eliyah Mahmoud

17 Dec, 11:46


https://vm.tiktok.com/ZMk2gvUjR/
ስላሴ በኢስላም (10)

Eliyah Mahmoud

16 Dec, 18:57


ከአንድ ሰው ጋር እያወጋኹ ግለሰቡ "እነ እገሌ ሼኽ ስለምነው ደርስ ስለሰጡ ደም-ወዝ ከመስጂዳችን የሚከፈላቸው?" አለኝ።

ሼኹ ሌላ መተዳደሪያ የሚኾን በቂ የግል ስራ
አላቸው እንዴ? ብዬ ጠየቅኹት።

"አይ እንቶኔ እንደነገረኝ ሌላ ስራ እንኳ የላቸውም ምናልባት የሚያከራዩት ትንሽዬ ቤት ነገር አላቸው መሰል" አለኝ።

ታዲያ እንዴት እንዲኖሩ አስበኽ ኖሯል ደም-ወዝ አያስፈልጋቸውም ያለከው?! ብዬ ረገጥ አድርጌ ጠየቅኹት።

ቀጠልኩናም መሰል ደም-ወዝ የሚወስዱ የማውቃቸውን ኹሉ ግለሰቦች ዘረዘርኹለት።

ወደ ኋላ ኼድኩናም ከነቡኻሪ ታላላቅ ሼኾች ውስጥ አቡ ኑዓይምን ከነ አባባሉ ጠቀስኹለት፦

تلومونني على الأجرة وعندي ثلاثة عشر نفسًا في البيت، ما عندهم خبز.

"ቁራጭ ዳቦ የማያገኙ አስራ ሶስት የቤተሰብ አባላት ይዤ ለምን ክፍያ ትጠይቃለህ ብላችኹ ትወቅሱኛላችኹ"

አቡ ኑዓይም ለእያንዳንዱ ሐዲስ ያስከፍል እንደነበር ጨምሬ ነገርኹት።

ሰውዬው ነገሩን ከኢኽላስ ጋር አዋዝቶ ማቅረብ ሞክሮ ነበር፤ግን ነገሩ ኢኽላስን የሚያጠፋው በተገላቢጦሽ በችግር መቆየታቸውና በየቀኑ እዚህ ለምን እቀመጣለሁ ወጥቼ ለምን የኾነ ነገር አልሞክርም ማለታቸው እንደኾነ ሲረዳ ይልቁንም አዘነ።

እናም ወዳጄ በየስርቻው ስንቱ የሚላስ አጥቶ ወይ በኢኽላስ ደርሱን አልያዘ ወይ ከነአካቴው የዱንያ ሰው አልኾነና ገበናውን አልሰተረ...ብቻ በየሰርኩ መሐል ላይ የሚዋልል ብዙ አለ።

ሙስሊሙ ባለሐብት ምናልባት ዘመዶቹን ወይም ስቸገር ይደርሱልኝ ይኾናል ያላቸውን ሰዎች ያበደር ወይም ያግዝ ይኾናል።

የኾነ ነገር አድርጎ የአንድን ሰው ሕይወት ከመቀየር ይልቅ ግቢ ውስጥ ባዶ ቦታ ፈልጎ ቡና መጠጫ ክፍል ቢሰራ ወይም የአጥር ቀለም ቢቀይር ይሻለዋል።

ስንቱ የማይኖርበትን ገንብቶ ገንብቶ ዘግቶ እያደረ እንደኾነ ዓይናችን አይቷል። ውስጣችንም ታዝቧል።

አኹን ላይ በሙስሊሙ የሚገነቡ ቤቶችን ላየ በትክክል ይሕ ትውልድ በሰለፎች የነበረውን የዙህድ ታሪክ እንደ አንድ ማዳ ሊማር እንደሚገባው ይረዳል።

ይህ በስስት ታጭቆ አጓጉል ፉክክር ውስጥ የገባው አካል ሞትን ረስቶ በግንብ መረዛዘሙ ሌላ መዓት እንዳያስከትልብን ያሰጋል።

በግሌ በዚህ ዱንያን ፍቅርርርር ባደረገ ትውልድ ኑስራና የበላይነት ይመጣል ብሎ ማሰብ ጅልነት ይመስለኛል።

"لو كان لابن آدم واديان من مال، لابتغى ثالثًا، ولا يملأ جوف ابن آدم إلا التراب، ويتوب الله على من تاب."
(رواه البخاري ومسلم)

" የሰው ልጅ ኹለት ሸለቆ ወርቅ ቢኖረው ሶስተኛ ይመኛል፤የሰው ልጅን ሆድ የሚሞላው ዐፈር ብቻ ነው፤ ንስሓ የገባውን ኹሉ አላህ ይቀበላል"

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

15 Dec, 14:16


ነብይ ለመኾን (፭)
...

አንድ ነብይ ነብይ ለመኾኑ ትንቢቶቹ ዕውን መኾን አለባቸዉ።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ከተናገሯቸው በርካታ ትንቢቶች ማሳያ የሚኾነን አንድ ብቻ እናንሳ።

አጠበራኒይ በዘገበውና አልባኒ በሲልሲለት አሰሒሓ ሐዲስ ቁጥር 481 ላይ መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንዲህ ይላሉ:-
لا تقومُ الساعةُ حتى يتَسافَدوا في الطريقِ تَسافُدَ الحَميرِ، قلتُ : إن ذلك لكائنٌ ؟ قال : نعم لَيكونَنَّ

"ሰዎች መንገድ ላይ እንደ አህያ ልቅ ኾነው ዝሙት እስካልሰሩ ድረስ የትንሳኤ ቀን አይከሰትም" ብለው ሲናገሩ እያዳመጣቸው የነበረው ሰሓቢይ ዐብደላህ ኢብን ዐምር ቢን ዐስ እንዴት ሊኾን ይችላል በሚል ግራሞት "ይሕ ነገር ይከሰታል ወይ" በማለት ጠየቀ መልዕክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) አጽንዖት ሰጥተው "አዎ በትክክል ይከሰታል" በማለት መልሰውለታል።

ይህ ትንቢት ዛሬ በትክክል ለመፈጸሙ ማንም ጥያቄ አያነሳም። በቅርቡ እንኳ ሜክሲኮ የአደባባይ ዝሙትን ሕጋዊ አድርጋለች።

ከሜክሲኮ አስቀድሞ ኔዘርላንድ፣ጀርመን፣ እንግሊዝና ዴንማርክ ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር የአደባባይ ወሲብን ከፈቀዱ ሐገራት ይመደባሉ።


ሌላው አላህ በቃሉ ሩሞች ከሽንፈት በኋላ ከሶስት እስከ ዘጠኝ ባሉ ዓመታት ውስጥ ፋርሶችን እንደሚያሸንፉ በመልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) አወረደ።

ይህ የተለመደ ዓይነት ትንቢት አይደለም። ምክንያቱም በተገደበው ዘመን ውሰጥ ሩሞች ካላሸነፉ የነብዩ ነብይነት በዜሮ የሚባዛ ይኾናል።

ታዲያ ቁርኣን ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ሩሞች አሸነፉ። ሙስሊሞች በእሳት አምላኪዎቹ መሸነፍ ተደሰቱ።


الم

አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡


غُلِبَتِ الرُّومُ
"ሩም ተሸነፈች፡፡

فِي أَدْنَى الْأَرْضِ وَهُم مِّن بَعْدِ غَلَبِهِمْ سَيَغْلِبُونَ

በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ፡፡

فِي بِضْعِ سِنِينَ ۗ لِلَّهِ الْأَمْرُ مِن قَبْلُ وَمِن بَعْدُ ۚ وَيَوْمَئِذٍ يَفْرَحُ الْمُؤْمِنُونَ

በጥቂት ዓመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)፡፡ ትዕዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ፡፡"

ይህ ትንቢት በሌሎች መጽሐፍ ሰፍሮ ቢኾን ምናልባት የተለየ ተደርጎ በተነገረለት ነበር።

የዛሬዎቹ ነብይ ነኝ ባዮች አስቀድመው መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ የተናገሯቸው የአየር ትንበያ መሰል ውሸቶች እንኳ ተፈጻሚ አልኾኑም።

አንድ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው የዛ ሰፈር ነብዩ ነኝ ባይ ኮሮና በዚህ ቀን ከምድር ይጠፋል ብሎ ተናግሮ ሳይሳካለት ይልቁንም በሽታው ብሶ በርካቶች ሲረግፍ "እግዚአብሔር አይሳሳትም እኔ የኝ የተሳሳትኩት" ብሎ ውሸታምነቱን አደባባይ አስጥቶታል።
...
ይቀጥላል

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

13 Dec, 06:49


https://vm.tiktok.com/ZMkFNH4qB/
ስላሴ በኢስላም (9)

Eliyah Mahmoud

11 Dec, 07:12


🔰 እዚህ ቻናል ላይ የተለቀቁ ኦድዮዎች በጥቂቱ። በቀላሉ ለማግኘት 👇 ፅሁፉን ተጭነው መልሱን ያድምጡ። ኦድዮዎቹ አጫጭር ናቸው ባረከላሁ ፊኩም🔰

➸ ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል አንድ
➸  ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል ሁለት
➸  ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል ሶስት
➸ አላህ በነብዩ ዒሳ አንደበት ለምን አሕመድ የሚለውን ስም ተጠቀመ?ክፍል አንድ
➸ አላህ በነብዩ ዒሳ አንደበት ለምን አሕመድ የሚለውን ስም ተጠቀመ? ክፍል ሁለት
➸ ከወገብና ከርግብግቢቶች መካከል ይወጣል ሲል
➸ ጂኖች ነብይ ነበራቸውን?
➸ ከብጤው አንዲት ምዕራፍ አያመጡም
➸ ከብጤው አንድ አያመጡም ክፍል ሁለት
➸ ግምታዊ አገላለፅ በቁርአን
➸ የአላህ ፍላጎት በሰዎች ፍላጎት ላይ.
➸ ከአላህ ውጭ ሌሎች አማልክት ቢኖሩስ?
➸ኢስላም ዘረኝነትን ያስተምራልን?
➸ የነቢይነት ማህተም ወይስ እጢ
➸ ሐዲሱል ቁድስና ሐዲስ አነበዊ ክፍል አንድ
➸ ሐዲሱል ቁድስና ሐዲስ አነበዊ ክፍል ሁለት
➸ ወሕይ ማለት ምን ማለት ነው?
➸ ኣላህ ወደ መላኢካ ወሕይ እንዴት ነው የሚያደርገው?
➸ እውን አላህ ይረሳልን?
➸ ሰው ሰራሽ ዝናብ
➸ ከአንድ በላይ ማግባት
➸ የዘይነብና የመልእክተኛው ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋብቻ
➸ ነቢያትና ዝሙት በመፅሐፍ ቅዱስ
➸ ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡
➸ በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤
➸ የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከአራት በላይ ማግባትና ከአራት በላይ እንዳታገቡ የሚለው ቁርኣናዊ ሕግ
➸ አጋንንት የሩቅ ምስጢር ያውቃሉን?
➸ በጃሂሊያ አጠራር የታገዘውን የአባትህን…ብላችኹ አነውሩት
➸ ሩህ ፍጡር ነው ወይስ ፈጣ
➸ ወደ ዝንጀሮ፣ከርከሮ ስለተለወጡ ሰዎች
➸ ወደ ግመል አይመለከቱምን እንዴት እንደተፈጠረች
➸ ግመል ከሰይጣን ተፈጥራለች?
➸ ኢስላማዊ የጥቢ ህግጋት
➸ ኣላህ ለምን እኛን መፈተን አስፈለገው?

ይቀጥላል ኢንሻአላህ.......

Eliyah Mahmoud

11 Dec, 06:07


ሙጃሂዲን ዲመሽቅ በሚገኘው በመስጂ አልአመዊይ ውሰጥ ዒሻእ ሶላትን በዚህ መልክ ሰግደዋል።

በሻር ሐገር ውስጥ ያከማቸውን ንብረት ኹሉ ጥሎ ጠፍቷል።

90% የሚኾነው ሕዝብ ከድህነት ጠለል በታች በሚኖርባት ሐገር ውስጥ ከምድር ስር ብቻ ደብቆ ያቆያቸው እጅግ ዘመናዊ መኪናዎች ከ40 በላይ እንደኾኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ያሳያሉ።

በሻር በርሱና በቤተሰቡ ስም የሰበሰበው ገንዘብ ሶሪያን እንደ ሐገር ለዓመታት ማኖር የሚችል እንዶኾነም እየተነገረ ነው።

የበሻር ቤተሰቦች ሐገር ውስጥ የዘረፉት ንብረት በፊርዓውን ልኬት እዛው ቀረ።

ከላህ በቁርአን ውስጥ ታሪክ ሲተርክልን በተራዛሚ በታሪኩ ውስጥ ያሉ ክስተቶች መሰሎቻቸው ላይ እንደሚደገሙ እየጠቆመን ነው።

فاقصص القصص لعلهم يتفكرون

በዳዮች ኹሉ ይዘገያል እንጂ የፊርዓውን ዕጣ ፈንታ ይደርሳቸዋል።


كَمْ تَرَكُوا مِن جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ

ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡

وَزُرُوعٍ وَمَقَامٍ كَرِيمٍ

ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡


وَنَعْمَةٍ كَانُوا فِيهَا فَاكِهِينَ

በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡


كَذَٰلِكَ ۖ وَأَوْرَثْنَاهَا قَوْمًا آخَرِينَ

(ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

11 Dec, 05:57


صلاة العشاء | الجامع الأموي - دمشق | - محسن غصن
https://youtube.com/watch?v=ONYnB40QgP0&feature=shared

Eliyah Mahmoud

09 Dec, 10:41


ሶሪያ-“በዚያ ቀንም ሙእሚኖች ይደሰታሉ”
….

እነሆ የኑሰይሪያው አምባገነን መሪ ተገለበጠ፡፡ ከ ሶስት አንድ ዓመታት ትግል በኋላም በደልን ሲዋጉ የነበሩ ሙስሊሞች አሸንፉ በግፍ የታሰሩ ቤተሰቦቻቸውንም አሰፍትተዋል፡፡

አባቱን ተከትሎ ዙፋን ላይ የተሰቀለው በሻር ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት በኹሉም ዓይነት በደል ሲንጣት ቆይቶ በስተመጨረሻ ጨርቁን ጥሎ ኮብልሏል፡፡

ሶሪያ ማለት የበርካታ ልሒቃን ምድር ናት፡፡ ለአብነት ያሕል ኢማሙ አነወዊ፣ ኢብኑ ተይሚያ፣ኢብኑል ቀዩም፣ የስነ-ምድር (ጂኦግራፊ) ሊቅ የነበረው አልመቅዲሲ ፣የኪነትና ፍልስፍና ጠቢብ የነበረው አቡል ዓለእ አልመዕሪ፣የሕክምና ሊቅ የነበረውና የደም ዝውውርን ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ኢብኑ ነፊስ…ወዘተ ይገኙበታል፡፡

በሶሪያ ምድር በአጠቃላይ የሱኒ ሙስሊም ቁጥር ሲበልጥ ከአስር በመቶ በታች የኾኑ የኑሰይሪያ እምነት ተከታዮች ይገኙበታል፡፡

ለመኾኑ ኑሰይሪያዎች እናማን ናቸው?
…..

በ አስራ ኹለት ኢማሞች የሚያምኑት ኢስና ዐሰሪያ ሺዓዎች ወደ ታች ቁልቁል ኢማሞቻቸውን ሲዘረዝሩ በአስራ አንደኛ ደረጃ ሐሰኑል ዐስከሪይን ይጠቅሳሉ፡፡

በሶስተኛው የሂጅራ ክፍለ ዘመን አቆጣጠር ላይ ከሐሰኑል ዐስከሪይ ጋ ግንኙነት አለኝ የሚል አንድ ሙሐመድ ቢን ኑሰይር የሚባል ግለሰብ ብቅ አለ፡፡

ይህ ግለሰብ ሐሰኑል አስከሪይ የአላህ መገለጫ ሲኾን እኔ ደግሞ ወደርሱ መዳረሻ በር (باب) ነኝ አለ፡፡ ቀስ በቀስ በራሱ ስም የሚጠራ “ኑሰይሪያ” የሚባል ከበቀለበት ከራሱ ከሺዓ ጋር እንኳ የማይስማማ አዲስ ሃይማኖት ፈጣጥሮ መስበክ ያዘ፡፡

አኹን ላይ የዚህ እምነት ተካቶዮች ብዛት ከ 1.5 እስከ 1.6 ሚሊዮን እንደሚጠጋ ይነገራል፡፡ አብዛኞቹ ሶሪያዊያን ሲኾኑ ጥቂቶች በሊባኖስ፣ እጅግ ጥቂቶቹ ደግሞ በቱርክ ድንበር አካባቢ የሚኖሩ ቱርኮች ናቸዉ፡፡

ኑሰይሪያዎች ምን ያምናሉ?
…..

፩) ሺዓዎች የሚዘረዝሯቸው ኢማሞች መለኮታዊ ማንነት አላቸው፤ወይም ደግሞ የአላህ መገለጫዎች ናቸው፤ወይም ራሳቸው አላህ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡

፪) ልክ እንደ ሂንዱና ቡድሃ ሃይማኖቶች ሰው ሲሞት “ሩሑ” ወደ ሰማይ ተመልሳ ትንሳኤን አትጠብቅም፤ይልቁንም ሟች መልካም ሰዉ ከነበረ የተሻለ መልካም ሰው ኾኖ ዳግም ወደ ምድር ይመጣል፡፡ አሊያም እጅግ መልካም ሰው ከነበረ ሩሑ ከአላህ ጋር ይዋሃዳል፡፡

፫) ጀነት ጀሃነም አለ ብለው አያምኑም፡፡

፬)የትኛውም በቁርኣንም ኾነ በሐዲስ የተገለጡ የዒባዳ ዓይነቶች ሚስጢራዊ ትርጉም አላቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ስለኾነም ለምሳሌ ሐጅ ማድረግ ወይም ሶሏት መስገድ በኢማሞች ማመን ማለት እንጂ በሌላ ተግባር የሚገለጽ አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡

፭) ልክ እንደ ብዙሃኑ ክርሲያኖች በራሳቸው የተቀነባበረ ስላሴያዊ እምነት አላቸው፡፡ አላህ እንደነሱ እምነት በሶስት መልኩ ተገልጧል፡፡

المعنى(1
الأسم (2
الباب (3

“አልማዕና” የሚሉት ዓሊይ (ረዲየላሁ ዓንሁ ሲኾን)፣”አልኢስም” ደግሞ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ናቸው፡፡ “አልባብ” የተባለው ደግሞ ሰልማኑል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዓንሁ ሲኾን) ነው፡፡

፮) ሒንዱዎች ብራሕማ (በነሱ የአምላክ ስም ነው) ዘጠኝ ጊዜ በአቫታር ተገልጧል ብለው ያምናሉ። የመጨረሻው አቫታርም ክሪሽና ነበር።

በተመሳሳይ መልኩ ኑሰይሪያዎች ደግሞ አላህ ራሱን ምድር ላይ ሰባት ጊዜ ገልጧል፡፡ የመጨረሻ መገለጫው ዓሊይ (ረዲየላሁ ዓንሁ ሲኾን) ነበር ብለው ያምናሉ፡፡

አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ዐሊይ ነው በቀጥታ ላለመለት لا هي هو ولا هو غيره የሚል ፌልስፍናም አላቸው።

፯) አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ራሱን በሶስት መልኩ እንደገለጸ ኹሉ ኢብሊስም ራሱን በሶስት መልኩ ገልጦ ነበር ብለው ያምኗሉ፡፡ ለምሳ በሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ዘመን ኢብሊስ በፊርዓውን፣ ቃሩንና ሃሩን መልክ ተገልጦ ነበር፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመንም በዋናነት በዑመር ከዚያም በአቡበክርና ቀጥሎም በዑስማን ( ረዲየላሁ ዐንሁም ጀሚዓን) መልክ ተገልጦ ነበር ብለው ያምናሉ፡፡

፰) ለዚህ ሃይማኖት ተከታዮች ዓሊይ (ረዲየላሁ አንሁ) ከነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚበልጥ ደረጃ አለው፡፡

በግልጽ እንደምንረዳው የዚህ እምነት አራማጆች በኢስላም ጥላ ስር የሚካተቱ ሙስሊሞች አይደሉም፡፡ ራሳቸው ሺዓዎችም ቢኾኑ ድንበር አላፊዎች (غلات شيعة) በማለት የሚገልጧቸውና የሺዓ አካልም የማያደርጓቸው እንደኾነ ይሰመርበት፡፡

የቀድሞ ሺዓ ልሂቃን በኩፍር ይፈረጇቸው እንደነበር መጽሐፎቻቸው ይናገራሉ።

በኋላ የመጡት ግን ከጀርባቸው ያለው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን ስለሚፈልጉት ይመስላል አቀራራቢ ፈትዋ በመስጠት የሺዓ አካል ሲያደርጓቸው ይታያል።

እስከ አሳለፍነው ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የዚህ ሃይማኖት መጠሪያ "ኑሰይሪያ" የሚል ነበር፡፡ በ1920 ዎቹ አካባቢ الكتلة الوطنية የሚባል የፖለቲካ ጭፍራ ሲመሰረት እነዚህን ኑሰይሪያዎችን ወደ ራሱ ለመሳብና በነርሱ ለመጠቀም “ዐሊዊይን” የሚል የዓሊይ ወገን መኾናቸውን የሚጠቁም ስም ሰጧቸው፡፡

በኋላ ላይም ፈርንሳይ የራሳቸወን ሐገር አቋቁማ የዐሊዊዪን ሐገር دولة العلوين በማለት እስከመጥራት ደርሳላች፡፡ ይህ መንግስትም ከ1920 እስከ 1936 ድረስ ቆይቷል፡፡

በኋላ በ1971 ላይ ሓፊዝ አልአሰድ (የቀድሞ የሶሪያ መሪ)- የሶሪያ የጦር ጀት አብራሪ እንደነበር ይረዷል- በነበረው መንግስት ላይ መፈንቅል መንግስት በማድረግ እ.ኤ. አ. ሕይወቱ እስካለፈበት እስከ 2000 ዓ.ል. ድረስ ይህንኑ የኑሰይሪያ ሐገረ-መንግስት ሲመራ ቆይቷል፡፡

የአባቱን ሞት ተከትሎ ልጅ በሻር አልአሰድ የሶሪያ መሪ ኾኖ በምክር ቤቱ ሲመረጥ ገና የ34 ዓመት ወጣት ነበር፡፡ በያኔው የሶሪያ ሕግ አንድ ሰው መሪ ኾኖ የሚሾመው 40 ዓመት ሲሞላው ብቻ ነበር፡፡ ኾኖም ግን ሓፊዝ አልአሰድ እንደሞተ በዐሊውይን የበላይነት የሚመራው ምክር ቤት ወዲያው ሕጉን አሻሽሎ ወደ 34 ዝቅ አደረገው፡፡

በለስ የቀናው በሻርም ስልጣኑን ገና በወጣትነቱ ተረክቦ የዚያን ሐገር ሕዝብ ቁም ስቅሉን ሲያሳየው ከርሟል፡፡ እነሆ ዛሬ ያ ስልጣን አከተመ፡፡ ሙስሊሞችም የሰላም ዐየር መተንፈስ ጀምረዋል፡፡ በዚሁ የሚቀጥልና የተሰደዱትም ወደ ሐገራቸው የሚመለሱ ይኹን፡፡ አሚን!!

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

07 Dec, 16:08


ጥያቄ እውነት ወይስ ሀሰት?

#የእስልምናን ጥሩ ገፅታ #ለማሳወቅ ንፅፅር ትምህርት #ጉልህ ቢና አለው

ጥያቄ ትክክለኛው መልስ ሰታገኙ የሚያመጣላችሁን add አድርጉለት

     🌟✍️በወድም ሙስጠፋ🌟

Eliyah Mahmoud

04 Dec, 15:22


ድንገት ጸጉሬን ተላጭቼ ነበርና አቡ ዩስራን አየር ላይ ሳገኘው እሱም ተላጭቶ ነበር።

የሕያ ኹለታችንንም እያየ እንደ ሒዳያ ተላጭታችኹ ነው እንዴ? በማለት በመላጣችን ከተረማመደ በኋላ "ሐሳባችን ኹኹኹሉ እንደዚህ ሙለጭ ብሎ ይጥፋ" ብሎ የሽማግሌ ዱዓ አደረገልን።

መላጣን አሽትቶ የሚመጣ "ጅን" አለ መሰለኝ (ሃሃሃሃ) ዱዓውን ተከትሎ ድንገት እነዚህ "ቡሄ በሉ" ስንኞች ተገለጡልኝ፦
...
አሚን ይኹን
አኹን አኹን!!!
ሳይዘገይ ድንገት
ኹሉም ባለበት
"ጭሱ" ሳይጠፋ
ኪሳችን ይስፋ
ይታጨቅ በብር
ይታፈን በክብር
አዕምሮ ሳይደክም
ጉልበት ሳይለግም
ይምጣ ይደፋ
ማንም ሳይለፋ
ይዋል እንዳሻው
ኻሊቁ እንዳለው
ስስት የሌለው
ዓይን ማይከጅለው
ወጥቶ ሚበዛ
ጀነት ሚገዛ
አሚን ይኹን
አኹን አኹን!!!
....

እናንተም አሚን በሉ (አኹን ከምሬ ነው)
https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

30 Nov, 15:34


https://vm.tiktok.com/ZMhEexUFU/
ስላሴ በኢስላም (8)

Eliyah Mahmoud

29 Nov, 06:24


ሲሳይ
...

አላህ በየትኛውም መንገድ ከሰዎች እጅ እንዳይኾን ያደረገው ሲሳይን ወም ሪዝቅን ነው።

የሰው ልጅ ምንም ያህል ራሱን ከሰዎች ፊት ቢያዋድቅ ሪዝቁን ሊሰጡት ወይም ከነርሱ ዘንድ ያለውን ሊያካፍሉት አይችሉም።

ما يفتح الله للناس من رحمة فلا ممسك لها وما يمسك فلا مرسل له من بعده وهو العزيز الحكيم

የሰው ልጅ ታላቅ ተደርጎ በመልካም አቋም ላይ ተሰራ እንጂ በሰው ፊት ሊዋደቅ በፍጹም አልተፈጠረም።

لقد خلقنا الانسان في احسن تقويم

ወዳጄ የሰው ልጅ የገዛ ወንድምህ ቢኾን ከአፍህ በሚወጣው ሊገምትህ ምናልባትም እጁን ዘርግቶልኽ ከነበር ከዛ አኳያ አሳንሶ ሊያይኽ መብት እንዳለው እንደሚያምን ልብ ይበሉ!!


አንሷሮች (ረዲየላሁ ዐንሁም) ለሙሃጂሮች በሰጡት ኹሉ ከልባቸው ውስጥ ስስት አልነበረባቸውም። ወደዷቸው እንጂ ቀነሱብን ብለውም አልጠሏቸውም።

وَالَّذِينَ تَبَوَّءُوا الدَّارَ وَالْإِيمَانَ مِن قَبْلِهِمْ يُحِبُّونَ مَنْ هَاجَرَ إِلَيْهِمْ وَلَا يَجِدُونَ فِي صُدُورِهِمْ حَاجَةً مِّمَّا أُوتُوا وَيُؤْثِرُونَ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ ۚ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

ይህ ሰጥቶ መደሰትና በሐሴት መስከር ብሎም ወንድም አድርጎ መያዝ ዛሬ ላይ ተገልብጦ ሰጥቶ በመናቅና በመጸየፍ ተለውጧል።

ዛሬ ትንሽም ብትኾን አለን የሚሉ አካላት አላህ ያዘነለት ካልኾነ በቀር በቃሩን መንፈስ የሚመላለሱ ናቸው።

አለን የሚሉት ኹሉ በነርሱ ብርታት እንደመጣ አድርገው ያስባሉ። ነገር ዓለማቸውም ይህን ያሳብቃል።

قَالَ إِنَّمَا أُوتِيتُهُ عَلَىٰ عِلْمٍ عِندِي

ቃሩን ከነንብረቱ በመሬት የተዋጠው ሐብታም ስለነበረ ሳይኾን የአላህን ሐቅ ስለረሳ ማንነቱንም ስለዘነጋ ብቻ ነው።

وَقَالَ الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ وَيْلَكُمْ ثَوَابُ اللَّهِ خَيْرٌ لِّمَنْ آمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا وَلَا يُلَقَّاهَا إِلَّا الصَّابِرُونَ .فَخَسَفْنَا بِهِ وَبِدَارِهِ الْأَرْضَ فَمَا كَانَ لَهُ مِن فِئَةٍ يَنصُرُونَهُ مِن دُونِ اللَّهِ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُنتَصِرِينَ
.....
اللهم إنا نسألك بفضلك ورحمتك فإنه لا يملكها إلا أنت

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

28 Nov, 19:21


የላይኛው ቲክታክ ለማትጠቀሙ ሰዎች ይኹን።

Eliyah Mahmoud

28 Nov, 19:21


https://vm.tiktok.com/ZMhwPyxBx/
ስላሴ በኢስላም (7)

Eliyah Mahmoud

28 Nov, 18:45


ነብይ ለመኾን (፬)
.....

በክፍል ፫ ጽሑፋችን ነብያት ኹሉ ይዘውት የሚመጡት ተዓምር (ሙዕጂዛ) በሌሎች ነብይ ባልኾኑ አካላት በየትኛውም ኹኔታ መፈጸም እንደማይችልና ከተፈጸመ ግን ያንን ነብይ ሐሰተኛ እንደሚያደርገው አይተናል።

በኢስላም አንድ ነብይ አይደለም ትላልቅ ወንጀል ሊሰራ ይቅርና ነብይነቱ ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ትንሽ ኃጢዓት ሊሰራ አይገባውም። አይሰራምም።

የክርስቲያኑ መጽሐፍ ታላላቅ ነብያትን ተራ አማኝ እንኳ የማይሰራውን ክፉ
ኃጢዓት ዝሙትን ጨምሮ ሲያሰራቸው እናነባለን።

እግዚአብሄር ሙሴን የፈርዖን አምላክ ሲያደርገው አሮንን ደግሞ ነብይ ይኾንለት ዘንድ መርጦታል።

“እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እይ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል”
ዘጸአት 7፥1

ታዲያ ነብይ አሮን በበትረ ሙሴ ተዓምራትን ሲሰራ ቆይቶ በምን ሒሳብ ነው ራሱ ጣዖት ሰርቶ ኢስራኤላውያን እንዲያመልኩ ያደረገው?!!!

ዘጸአት 32
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ሕዝቡም ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው፦ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና ተነሥተህ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን አሉት።
² አሮንም፦ በሚስቶቻችሁ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁም ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ አላቸው።
³ ሕዝቡም ሁሉ በጆሮቻቸው ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብረው ወደ አሮን አመጡለት።
⁴ ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፦ እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው።

በቁርአን እንደተነገረን ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ተውራትን ለመቀበል ሲሄድ ሳሚሪዩ ከወርቅና ጌጣጌጥ ጣዖት ቀረጸላቸው። ሀሩንም (ዐለይሂ አሰላም) ይህንን ተቃውሞ የኢስራኤል ልጆችን መክሯል።


فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ فَقَالُوا هَٰذَا إِلَٰهُكُمْ وَإِلَٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِيَ

ለእነሱም አካል የኾነ ጥጃን ለእርሱ መጓጎር ያለውን አወጣላቸው፡፡ (ተከታዮቹ) «ይህ አምላካችሁ የሙሳም አምላክ ነው ግን ረሳው» አሉም፡፡
ጠሃ/20

ቁርኣን "ሙሃይሚን" ተጠባባቂ ኾኖ ወርዷል። ስለኾነም ሌሎች መጽሐፍት ያምቦራጨቁትን ያጠራል።

وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ
المائدة /48

መሰል በርካታ የነብያት ክብር በባይብል መነካቱና ነብያቱን ተራ አማኝ የማይሰራውን ሰርተዋል ሲል ለሌሎች ክርስቲያን ነን ለሚሉ በኃጢአት መጨማለቅ አመክንዮአዊ በር ከፍቷል።

ለዚህ ማሳያ እንዲኾን የፕሮቴስታንት "ነብያት" እና የካቶሊክ ቀሳውስት የተዘፈቁበተን ወንጀልና ኃጢአት ማየት በቂ ነው።
.....
ይቀጥላል
https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

24 Nov, 11:38


ነብይ ለመኾን (፫)
....

ነብይ ለመኾን በሚል የጀመርነው ይህ ሶስተኛ ወጋችን ነው።

ከነብይነት መገለጫዎች ውሰጥ ተዓምራት ማሳያዎች ናቸው። ይህ ማለት ግን ኹሉም ነብያት በተመሳሳይ ተዓምራት ይነሳሉ ማለት አይደለም።

የሙሳ (ዐለይሂ አሰላምን) ተዓምር የትኛውም ነብይ አልደገመውም። አለመድገሙ ግን ከሙሳ (ዐለይሂ አሰላምን) የሚያንስ አያደርገውም።

በተመሳሳይ መልኩ የትኛውም ነብይ ይዞት የሚነሳው ተዓምር በየትኛውም ነብይ ባልኾነ አካል ሊተገበር ወይም በልምምድ ሊሞከር አይችልም።

ቁርአን እንደሚነግረን የሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ተዓመርን ድግምተኞቹ ሊሞክሩ ይቅርና ይባሱኑ እነርሱ ለማስመሰል የሞከሩትን ኹሉ ዶጋ አመድ ያደረገ ነበር።

በክርስቲያኑ መጽሐፍ የምናነበው ግን ድግምተኞቹ ራሳቸው አሮን የሰራውን መሰል ተዓምር ሰርተዋል፦

“የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ ”/ ዘጸአት 7፥22

ይህንን ታሪክ ከፍ ብለን ካነበብነው አሮን የአባይን ውኀ በብትሩ መቶ ደም እንዳደረገ ኹሉ አስማተኞቹም ይህንኑ አድርገዋል።

ቀጥሎ ባለው ምዕራፍም ደግሞ እንደ አሮን ኹሉ ጠንቋዮች ወንዙን በጓጉንቸር ሞልተውታል፦

ዘጸአት 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ አሮንን፦ በትርህን ይዘህ በወንዞቹና በመስኖቹ በውኃ ማከማቻዎቹም ላይ እጅህን ዘርጋ፥ በግብፅም አገር ላይ ጓጕንቸሮችን አውጣ በለው።
⁶ አሮንም በግብፅ ውኆች ላይ እጁን ዘረጋ ጓጕንቸሮቹም ወጡ፥ የግብፅንም አገር ሸፈኑ።
⁷ ጠንቋዮችም በአስማታቸው እንዲህ አደረጉ፥ በግብፅም አገር ላይ ጓጕንቸሮችን አወጡ።

እዚህ ጋር የኛ ጥያቄ የሚኾነው እንግዲህ እነዚህ ጠንቋዮች በአስማት የነብያትን ተዓምራት የሚያደርጉ ከኾነ፣ የነብያት ተዓምራት እንዴት ብሎ ነው ሙዕጂዛ የሚኾነው?!

"ሙዕጂዛ" ማለት ለሌላው በየትኛውም መንገድ የማይቻል በሰይጣንም ቢታገዝ ሊያደርገው የማይችለው ነገር ነው።

ቁርአን የፊርዓውን አስማተኞች የጣሉት በትርና ገመድ ለሙሳ እባብ መስሎ እንዲታየው ኾነ እንጂ በትክክል እባብ እንዳልኾነ ይነገረናል፦

فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ طه/66

"ዪኸየሉ ኢለይሂ" መመሰል እንጂ መኾንን እንዳማይጠቁም ልብ ይሏል!!!

ላይ ከዘረዘርነው ሐቲት አኳያ ለነብያት የሚሰጠው እንደ ቁርአን አስተምህሮ በትክክል ተዓምር "ሙዕጂዛ" ሲኾን ባይብል ግን በሌሎችም አካላት ሊተገበር የሚችል እንደኾነ ይነግረናል።

የትኛውም ተዓምር ሌሎች በየትኛውም ዓይነት ልምምድ ከተገበሩት ያኔ ተዓምርነቱ ያከትማል። ያ ነብይም ውሸተኛ መኾኑ ይታወጃል።

...

ይቀጥላል

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

21 Nov, 17:32


https://vm.tiktok.com/ZMh7NvtDN/

ልጆችዬ ዝሃራ ነኝ ክርስቲያን ወገኖች አካውንቴን ሰላዘጉት ከፍቻለሁ አድስ ፎሎው አድርጉ ዱዩት አድርጉ እና ፎሎው አስደርጉኝ

Eliyah Mahmoud

21 Nov, 04:46


ነብይ ለመኾን (፪)
...

ባስቀደምነው መንደርደርያ ጽሑፍ አንድ ነብይ ከመሬት ተነስቶ ነብይ ነኝ ማለት በፍጹም አይችልም።

ነብይነት በአላህ መመረጥ ብቻ ነው። አላህ እነማን ለዚህ ታላቅ ስራ በቂ ናቸዉ የሚለውን ስለሚያውቅ እርሱ ያዘጋጃል። ይመርጣልም።

ከበርካታ የነብይነት ምልክቶች ውስጥ የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ፦

፩ኛ) ተዓምራት (معجزة)

አንድ ነብይ በሕዝቦች መካከል ሲነሳ አብሮት የሚሰራ ሙዕጂዛ ይሰጠዋል። ሙዕጂዛ "የማይቻል" ወይም "የሚሳን" እንደ ማለት ነው።

ነብያት ከአላህ ለመላካቸው ማሳያ ይኾን ዘንድ እንዳሉበት ተጨባጭ የሚሰጣቸው ለሌሎች የማይቻል ተዓምራት ይሰጣቸዋል።

በሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ዘመን ሰዎች በድግምትና በአስማት እጅጉን ይመላለሱ ስለነበር ሙሳም (ዐለይሂ አሰላም) ከፍ ባለ ተዓምር ያውም ድግምተኞቹን ኹሉ እጅ እንዲሰጡ በሚያስገድድ መልኩ መጣ።

በመልክተኛው ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመን የነበሩ ዓረቦች በቋንቋቸው በዐረብኛ እጅግ የተካኑና እንዲያው ድንገት በሚከሰቱ ጉዳዮች ላይ እንኳ ከመካከላቸው አንዱ ብድግ ብሎ ስንኞችን የሚያንፎለፉልበት ፣ የግጥም ውድድሮች ይደረጉበት የነበረበትና አሸናፊዎች "ሎሬት" የሚኾኑበት የቋንቋ ልሕቀት ላይ ነበሩ።

ታዲያ ቁርአን መውረድ ሲጀምር ዓረቦች አስቀድመው በማያውቁት የስነ-ጽሑፍ ዘርፍ መምጣቱ የቋንቋ ልሒቃኑን አስገርሟል።

ቁርአን ግጥም ያልኾነና ዐረቦች "ቡሑር" - በአማርኛ ሰርጎ መገን፣ የወል ቤት፣ ቡሄ በሉ እንደሚባሉት - ብለው ከመደቧቸው የግጥም ዓይነቶች ውስጥም የማይካተት ከስድ ንባብም ያልኾነ አዲስ ስነ-ቃል ነው።

ማንበብና መጻፍ ከማይችል የስነ-ቃል ብሎም የግጥም ክሕሎት ከሌለውና ከልጅነቱ አንስቶ መሰል መክሊት ከሌለው ግለሰብ በዚሕ ልክ ጥልቅ ቋንቋዊ አብዬት ይዞ የመጣ መጽሐፍ ተዓምር ካልኾነ ምን ሊኾን ኖሯል?!

ይሕንን መስፈርት ብቻ ከፊት ለፊት አድርገን ስናወራ፣ ዛሬ ነብይ የሚባሉ አካላት የትኛውን ተዓምር ይዘው መጡ? ብለን እጠይቅ።

የትኛውም የዛ ሰፈር ነጋዴ ይዞት የመጣው አንድም ተዓምር አይደለም ቁም ነገር እንኳ የለም።

ግለሰቦቹ በየአውድማው እናነቃቃችኹ ከሚሉ ሰዎች የዘለለ ምንም የተለየ ስራ አልሰሩም።

ልዩነታቸው እነዚህ የሚያነቃቁት በትንቢት ስምና "ተደርጎልኻል፣ኾኖልኻል" በሚሉ ቀቢጸ ተስፋዎች ሲኾን፣ እነዚያኞቹ ደግሞ ዝም ብለኽ ተመኝ ይኾንልኻል፤ አንተ ድንቅ ሰው ነኽ! አንተ ለኾነ ዓላማ መጥተኻል፣ ገና ብዙ የምታሳካው አሉ...እያሉ አየር ማዘገናቸው ብቻ ነው።

እነዚህን ሰዎች የሚያመሳስላቸው ኹለቱም ለሚያዳምጣቸው ሰው የሕልም እንጀራ ሲያጎርሱት ለራሳቸው ግን ዕውነተኛ ወፍራም እንጓቻ መጋገራቸው ነው።
....

ይቀጥላል
https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

19 Nov, 18:22


أقول وقد ناحت بقربي حمامة
أيا جارتا لو تشعرين بحالي
معاذ الهوى ما ذقت طارقة النوى
ولا خطرت منك الهموم ببال
أيا جارتا ما أنصف الدهر بيننا
تعالي أقاسمك الهموم تعالي

ይህንን ግጥም አቡ ፊራስ አልሐምዳኒ የተባለ ፈረሰኛ ጀግና በጠላቱ እጅ ምርኮኛ ኾኖ ከወደቀ በኋላ እንደተናገረው ይነገራል።

ግለሰቡ ከታሰረበት ቦታ ከፍ ብሎ ልብን በሚሰብር ድምጽ አንዲት እርግብ ስታንጎራጉር ይሰማታል።

የርሱን ድንገት ከቤቱ ወጥቶ ምርኮኛ መኾንና ምናልባትም በዛ ሊቀር መኾኑን አስቦ፣ይሕች ወፍ በሐገሯ ሰማይ ስር ኾና በዚህ ልክ በሐዘን ስትዘምር ሲያይ፣ ከራሱ ኹኔታ ጋር እያወዳደረ፦

"ከጎኔ ኾና ስታንጎራጉር ወፊቷ ድንገት
ጎረቤቴ ሆይ ቢሰማሽማ ኹኔታዬ ያለኹበት
ትዕቢትን ጣል አርገሽ ብለሽ ድብቅ ስትር
በቅጽበት መለያየትንም ባልቀመስሽ ነበር
ሐዘንም ባልነካሽ ባላልሽ ክስት ምርር
ጎረቤቴ ሆይ ጊዜ ሲፈርድ እኮ ይደንቃል!
ነይማ ጠጋ በይ ጭንቀቴን ለአንቺ ላካፍል "

በማለት ያለበትን ጭንቀት ነገራት ይባላል።

ይሕ ክስተት በሐበሽኛ "እናቱ የሞተችበትም እናቱ ገበያ የኼደችበት ሕጻን እኩል ያለቅሳሉ" እንደ ማለት ነው።

اللهم لا سهل إلا ما جعلته سهلا وأنت تجعل الحزن إذا شئت سهلا
https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

17 Nov, 11:53


تجسيم للكعبة وعليها صور مغنيات!! فى موسم الرياض استفزاز شديد..السعوديين ...
https://youtube.com/watch?v=lx_0C5ckcvI&feature=shared

Eliyah Mahmoud

17 Nov, 07:12


በዚህ ተንቀሳቃሽ እንደሚደመጠው በሪያድ የታየውን ትርዒት አስመልክቶ የስዑዲ ሼኽ አንብቷል።

የካዕባን ምስል በአስመሳስሎሽ (አኒሜሽን) መድረክ ላይ አዘጋጅተው የተራቆቱ እንስቶች ፋሽን ሾው ሲያደርጉ ይታያል።

ይሕ ምን ማለት እንደኾነ ለማንም ግልጽ ነው። በዚህ ልክ ሙስሊም ነን በሚሉ አካላት ኢስላም ሲረክስ ማየት ብናኝ ኢማን ላለው እጅግ የሚሰቀጥጥ ነው።

ወዳጄ በግሌ በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ መጻፍ ፈልጌ ሳይኾን ጉዳይ እንደ ሙስሊም ኹላችንንም የሚመለከት ስለኾነ ብቻ ነው።

ካዕባ ለኹሉም ሙስሊም ቂብላ ነው። በዚህ ልክ በማንም ቅጥረኛ ሲፌዝበት ማየት አግባብ ነው ብዬ አላምንም።

ተው ይሉ የነበሩ ዱዓት ታስረዋል። ዛሬ ላይ እነዛ የታሰሩትን ደግፎ ለምን ታሰሩ? ያለ ስም ይሰጠዋል።

ቢን ሰልማንን ያልደገፈ ኹሉ በኾነ ስልቻ ውስጥ ተጨምሮ ይወቀጣል።

ወዳጄ ኢስላም ግለሰቦች ሳይኾኑ ኢስላም ኪታብና ሱና ነው። የትኛውም አካል በኪታብና ሱና ይለካል። ካለፈ ያልፋል ከወደቀም እንዲኹ!!!

እነዚህ ኹለት ዋቢዎቻችን ላይ ቆመን የቢን ሰልማን መንግሰትን እንመዝነው ወይም የሚመዝኑ ዑለሞችን እናዳምጥ።

እየኾነ ያለው ነገር የኢስላምን ቅዱስ ምድር በምዕራባዊው ሰይጣናዊ ርዕዮተ መበከል ብቻ ነው።

እንደው ስለ ዕውነት እናውራና ከሰለፎች አንዱ ቢኖር ይሕንን መረንነት ያደንቀው ነበርን ወይስ እስከ ሕልፈቱ ድረስ ያወግዘው ነበር?!

اللهم دمِّر المعتدين، أعداءك وأعداء الدين


https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

17 Nov, 06:48


راقـ ـصات حول مجسم الكعبة وشيخ سعودي يبكي على انتهاك حرمات الله في موسم ...
https://youtube.com/watch?v=YjA1kGMy1V8&feature=shared

Eliyah Mahmoud

16 Nov, 11:07


የምስራች ከቁርአን ቀጥሎ ትልቁን ኪታብ ሶሂሁ አልቡኻሪን መቅራት ለምትፈልጉ ሁሉ

ለመመዝገብ


አኅት ዘሃራ ሙስጠፍን፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት ዝሃራ ኢማምን ፦ @Zehar678
ያናግሩ

Eliyah Mahmoud

15 Nov, 04:34


https://vm.tiktok.com/ZMhsGTBLR/
ስላሴ በኢስላም (5)

Eliyah Mahmoud

14 Nov, 07:48


አወወ ይህንን ቻናል እናስተዋውቅልኽ ያላችኹኝ ሰዎች በመጀመሪያ አላህ ምንዳችኹን ይክፈል እላለሁ።

ቀጥዬ ቻናሉ ለዛ በቂ ነው ካላችኹ አስተዋውቁት ግን የኔ ግፊት አይኹን።

የተከታዬ ቁጥር ጨመረም ቀነሰም ማለት የፈለግኹትን የምልበት ቤቴ ስለኾነ ከመጻፍ አልቦዝንም።

ላለፉት ስምንት ዓመታት የዚህ ቤት እድርተኛ ከአንድ ሺህ ከምናምን ዘሎ አያውቅም።

ግን ማስታወቂያም ኾነ እዚህ እናድርሰው የሚል ቻሌንጅ ከትቤ አላውቅም። አለከትብምም።

የሻ ሰው ሐሳቤ ተስማማውም አልተስማማውም አብሮኝ ይዝለቅ። የኮሰኮሰው ደግሞ ሊሰናበተኝ መብቱ ነው።

ለማንኛውም ወዳጄ የማስተዋወቅና የማዳረሱን ምርጫ ለእርሶ ትቻለኹ።

🙏አመሰግናለሁ 🙏

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

13 Nov, 12:21


ነብይ ለመኾን
….

ነብይነት በአላህ የሚሰጥ የምርጫ ጉዳይ ያልኾነ በረከት ነው፡፡ በአንጻሩ እዝች ሐገር ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮ የቆለመመው ኹሉ እየተነሳ ነብይ ነኝ ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

በአዲስ ሃይማኖት ስም ብቅ ብሎም ነብይ ነኝ ያለና እምብዛም ያልተሳካለት ሰው እንዳለ ድፍን ሐበሻ ያውቃል፡፡

ግለሰቡ ዛሬ ላይ ጭራሽ በሚዲያ ገብቶ ሲዘላብደው የቆየው “ሕልምና” የከፊል ደመናማ “ትንቢት” እንዳላዋጠው ይልቁነም ንብረቱን ኹሉ በዛ ምክንያት እንዳጣ እያወራ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ ሜዳ ላይ ለየት ባለ ማሊያ የተሰለፉ የዛ ሰፈር ወጠምሻዎች ደግሞ ከአፍሪቃ ወንድሞቻቸው ቀድተው ሕዝቤን በአጓጉል ተስፋ እየሞሉ ሲዘርፉ ተው የሚል ሕግ አለመኖሩ እጅግ ያስተዛዝባል፡፡

ይዘገያል እንጂ አንድ ቀን በአደባባይ የሕግ እራት መኾናቸው በፍጹም አይቀርም፡፡ ለዚህ ትልቁ ማሳያችን አርኣያዎቻቸው ጆሹዋና ቡሽሪ ናቸው፡፡

ጆሹዋ ባዕድ /ሰይጣን አምላኪ የነበረና በራሱ ተከታዮች በስተመጨረሻ የተጋለጠ በበጎች መሐል የሚመላለስ ተኩላ ነበር፡፡ ቡሽሪ ደግሞ ጭራሽ በአየር ላይ እሄዳለኹ ይል የነበረ- መሄዱ ምን ትርጉም እንዳለው ግልጽ ባይኾንም- ከሰማይ እሳት አዛለኹም ብሎ በተራ ግለሰቦች እንዴት ነገራትን እንዲቀጣጠሉ ያደርግ እንደነበር የተጋለጠ ፍልጥ ጅል ነበር፡፡

ቡሽሪ ከደቡብ አፍሪቃ ለቆ አኹን ላይ ማላዊ እንደሚገኝና በዘረፈው ገንዘብ ትላላቅ ቢዝነሶችን እንደጀመረ ይነገራል፡፡

ነብይነት ወይም ነቡዋ (النبوة) የሚለው ቃል ነብእ (النبأ) ከሚለው ስረወ-ቃል የተፈለቀቀ ነው፡፡ ትርጉሙም ዜና ማለት ሲኾን በተጨማሪም ከፍ ማለት ወይም መላቅ የሚልም ትርጉም አለው፡፡

ነብይም ኾነ ረሱል ኹለቱም ከአላህ የተወረደላቸውን መልዕኮታዊ ራዕይ የሚያስተምሩ ሲኾኑ ብዙዎቹ የኢስላም ልሒቃን እንደሚስማሙበት ልዩነታቸው ነብይ የቀደመውን ስርዓተ-መለኮት (ሸሪዓ) የሚያሰተምር ሲኾን ረሱል ደግሞ በአዲስ ስርዓተ-መለኮት የሚነሳ ነው፡፡

ለመኾኑ አንድ ግለሰብ ነብይ ለመኾኑ ማስረጃዎቹ ምንድን ናቸው? እንደ አላህ ፈቃድ ቀጣይ የምንመለከተው ርዕስ ይኹን!
https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

11 Nov, 11:00


ሶስት ነገራትህን ሸሸግ አድርግ
....

ኢብኑል ጀውዚ ስስት ነጋራትኽን ሸሸግ አድርግ ይላል።

፩ኛ) ንብረትኽን

ይህን ያህል ገንዘብ አለኝ፤ይህን ያህል እነገሌ ዘንድ ደግሞ በብድር የተወሰደ አለኝ ወዘተ...ማለት ታይታን ወይም ምቀኝነት ስለሚያስከትል የንብረትኽን መጠን አታውራ ይላል።

፪ኛ) ዕቅድኽን

ዕቅድ በሰውዬውና በአላህ መካከል መሸሸግ ያለበት ነገር ነው።

ምናልባት እዚህ ጋር የጋራ ዕቅድ፣ ወይም የመስራ-ቤት ራዕይ እንዳልኾነ ይሰመርበት።

ኢብኑል ጀውዚ ሊነግረን የፈለገው ኹሉም መድረስ የሚፈልግበት የሕይወት ግብና መዳረሻ ነጥብ አለው፤ ያንን ነጥብ ለራሱና ለአላህ ይተወው የሚል ነው።

አንድ ሰው የሕይወት ግቦቹን የባቄላ ወፍጮ አድርጎ በየደረሰበት መበተኑ በአላፊ አግዳሚው አፍ እንዲገባ ከማድረግ በዘለለ የሚያተርፈው ሒስድን ወይም ተጠግቼ ልብላ የሚሉ ስግብግብ አፎችን ብቻ ነው።

፫ኛ) የሕይወት መርሆዎችኽን
....

ከኢስላማዊ ርዕዮት በዘለለ አንድ ሰው ከራሱ ተሞክሮ የሚከተላቸው የሕይወት ፍልስፍናዎች / አካሄዶች ሊኖሩት ይችላል።

ፍልስፍናው ለራሱ ሰርቶለት ለሌላው ግን ላይሰራ ስለሚችል ርዕዮቱን ቢደብቅ ይሻላል።

ማንም ሰው በግል ሕይወቱ ምከረኝ ካላለኽ በስተቀር ልምከረው ብለኽ አትጣደፍ።

ስለ ራስኽም ቢኾን ብዙ ከማውራት ተቆጠብ።

አንዳንዶች ሰዎች ስለነርሱ መስማት እጅጉን የሚጓጉ፣ ከልብ የሚያስደስታቸው የልጅነታቸው የእናታቸው የእሹሩሩ እንጉርጉሮ ይመስላቸዋል?

ወዳጄ ጉዳዩ ወዲህ ነው! ስለ አንተ ኹሉንም ነገር መስማት የምትወደው ብቸኛዋ ሰው እናትኽ ብቻ ናት።

ትላንት ከነምናምናችን ስማ ያጎረሰችንና ጀርባዋን እንዳይኾን ያደረግናት በሕይወት እስካለች ድረስ ስለ እኛ ምኑንም ሳትጠየፍ ኹሉንም ማወቅና መስማት ትወዳለች።

ከእናትህ ውጪ ያለ የትኛውም ሰው ራሱን የሚያዳምጥበት እንኳ በቂ ጊዜ ሳይኖረው ያንተን የጨረባ "ዘፈን" ሰለምን እንዲያዳምጥ ትፈርድበታለኽ?!

ወዳጄ ተቸገርኽ ከኾነ መቸገርኽ ለራስኽ ነው ! የኾነ ነገር መስራት ፈለግኽ እንደኾነ ለራስኽ ነው! ...በጥቅሉ አፍህን ከፍተኽ ላውራኽ የምትለው ኹሉ የኋላ ኋላ ቢታዘብኽ እንጂ ዘንጋዳ ዘግኖ አይሰጥኽም። ለአንተ ከሚሰጥኽ ይልቅ ቢበትነው እጅግ ይወዳል።

ወዳጄ ይህችን "ኹሉም ለራሱ ነው!!" የምትለውን የዱንያም የአኺራም መርሆን ልብ ይበሉ።

ዱንያ ላይ ኹሉም ለራሱ ብቻ ነው!!!! አኺራ ላይም ኹሉም ስለ ነፍሱ ብቻ ተሟጋች ነው።

لكل امرئ منهم يومئذ شأن يغنيه

ኢብኑል ጀውዚን (ዐለይሂ ረሕመቱላህ) ይህችን ውድ ነገር ስለነገረን አመሰገንን፦

اكتم عن الناس ذهبك وذهابك ومذهبك
....
ማብራሪያዎቹ የግሌ ናቸው
https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

09 Nov, 10:32


ኺንፊሻር
....

በዐረቦች ተረተ አንድ ኹሉን ዓዋቂ መሐል ጠሊቅ ነኝ የሚል ሰው ነበር አሉ።

ይህ ሰው ስለተጠየቀው ነገር ኹሉ ዐውቃለኹ እያለ ከጥንት ስነ-ግጥምም ከስነ-ቃልም ጭምር ምሳሌ እያደረገ ይመልስ ነበር።

አንድ ቀን የአካባቢው ሰዎች እርስ በርስ " ይህ ሰው እንዴት ይህንን ኹሉ ነገር ሊያውቅ ቻለ? ትላንት ከኛ ዘንድ ሲመላለስ የነበረና በዕድሜም ታናሻችን የኾነ የምናውቀው አይደለምን?" ተባባሉ።

ቀጠሉናም " ዕውነተኛ መኾኑን ለማወቅ አንድ የኾነ ቃል እንፍጠርና ይህ ምንድን ነው ብለን እንጠይቀው፤ ዐውቃለኹ ብሎ ከመለሰ ውሸታም መኾኑን እናውቃለን። እናጋልጠዋለንም።" ተባባሉ። ተስማሙም።

ከዚያም ሰውየው የሚያስተምርበት ቀን ላይ ሄደው ከፊቱ ተኮለኮሉ። ለጥቀውም "ኺንፊሻር" ምንድነው ብለው አዲስ የፈጠሩትን ቃል ጠየቁት።

ሰውየው አሰብ አደረገና " ኺንፊሻር ማለት የእጽዋት ዓይነት ነው። ቅጠሉ የዚህ ዓይነት ነው። ግንዱ ደግሞ ...ወዘተ" እያለ አናቶሚውን ዘረዘረው።

አስከተለናም ከጃሂሊያ ግጥሞች ማሰረጃ ለማድረግ የራሱን ስንኝ ፈጠረ፦

لقد عَقَدَت محبتُكم فؤادي

كما عقد الحليبَ الخنفشار

"ኺንፊሻር ወተትን እንደሚያረጋ
የናንተም ፍቅር ልቤን አረጋጋ"

ካለ በኋላ ከሐዲስም ጭምር ማስረጃ ለማምጣት ሲያኮበኩብ " በሌላው ላይ የዋሸኸው ይበቃል፤ በመልክተኛው ላይ ስትዋሽ መስማት አንፈልግም" ብለው ጮኸው ተነሱ። ሰውየውም ውሸታም መኾኑ ታወቀ።

ከዚያ ቅጽበት በኋላ ሰውዬው ከልቡ ውሸታም እንደኾነና በዙሪያውም ያሉ ከዕውቀት የተጣሉ የሰሙትን በጥሬው አምነው የሚቀበሉ መኾናቸው ይፋ ኾነ።

ወዳጄ ይህንን ምሳሌ ከዛሬዎቹ ኹሉን እናውቃለኖች ጋር አገናኙት።

ለኛ ትምህርት ይኾነን ዘንድ ደግሞ፦

"وَلا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْؤُولًا"

https://t.me/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

08 Nov, 10:46


መልካም ጥርጣሬ
.....

ልጅቷ በኹለት እጆቿ ቱፋሕ ይዛለች። እናት ከኹለቱ ቱፋሖች አንዱን ትሰጣት ዘንድ ጠየቀቻት።

ልጅቱም አሰብ አድርጋ በቀኝ እጇ የያዘችውን ቱፋሕ ግምጥ አድርጋ ማለመጥ ጀመረች።

እናት በግራ እጇ የያዘችውን ትሰጠኛለች ብላ ስትጠብቅ፣ልጂቱ ቀጥላ በግራ እጇ የያዘችውን ደግሞ ገምጣ ማላመጥ ጀመረች።

ይህን ያየች እናት በልጇ ተግባር ተናዳ፣ "ለእኔ ለእናትሽ አንዱን መስጠት እንዴት ከበደሽ? አንቺ ከመች ጀምሮ ነው በዚህ ልክ ስስታም የኾንሽው?..." ብላ ኃይለ- ቃል ጨማምራላት እየተመናጨቀች ጥላት ከክፍሉ ወጣች።

ብዙም ሳይቆይ ልጅቱ " እናቴ ይህንን እንኪ" እያለች ከኋላ ትከተላት ጀመር።

እናቲቱ የበለጠ ንድድ ብላ "የበላሽለትን ነው እንዴ የምትሰጭኝ? ትንሽ አይከብድሽም?..." ብላ አጉረጠረጠችባት።

ልጂቱም " የትኛው እንደሚጣፍጥ ስላላወቅኹ ነው እንደጠየቅሽኝ ልሰጥሽ ያልፈለኩት፤ ይኽኛው የበለጠ ስለሚጣፍጥ ይህንን ውሰጂ" ስትላት፣ እናት በራሷ እፍር ብላ በልጇ አስተሳሰብ ተደንቃ ተቀበለቻት።

እናም ወዳጄ አንድ ሰው በተመኩሮውም ኾነ በዕውቀቱ የትም ይድረስ በመልካም ጥርጣሬ ካላጌጠ ሲከፍቱት ተልባ መኾኑ አይቀርምና ይታሰብበት።

ፈረንጆቹ "Don't judge a book by its cover _ የመጽሐፉን ሽፋን ዓይተህ ስለመጻፉ አትፍረድ" ይላሉ።

መረሳት የሌለበት አላህ በቃሉ እጅግ በጣም ተጠንቀቁ ያለን ክፉ ጥርጣሬን ነው፦

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِنَ الظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ الظَّنِّ إِثْمٌ وَلَا تَجَسَّسُوا وَلَا يَغْتَبْ بَعْضُكُمْ بَعْضًا...

https://t.me/boost/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

07 Nov, 15:05


https://vm.tiktok.com/ZMhVoMkoe/
ስላሴ በኢስላም (4)

Eliyah Mahmoud

04 Nov, 16:36


لماذا كان ابن تيمية يُكرر سورة الفاتحة بعد الفجر حتى الشروق!؟.. تأملات
https://youtube.com/watch?v=AL9G9O0vim4&feature=shared

Eliyah Mahmoud

28 Oct, 10:55


https://vm.tiktok.com/ZMh9VtHt4/
ስላሴ በኢስላም (3)

Eliyah Mahmoud

27 Oct, 05:24


ماذا بعد المحنة؟ - أحمد سبيع
https://youtube.com/watch?v=ul1Lfx6jiA8&feature=shared

Eliyah Mahmoud

25 Oct, 12:18


https://vm.tiktok.com/ZMhuwL7bU/
ስላሴ በኢስላም (2)

Eliyah Mahmoud

22 Oct, 04:34


https://vm.tiktok.com/ZMhaKDdoQ/
ስላሴ በኢስላም (1)

Eliyah Mahmoud

19 Oct, 10:28


በሀድያ ዞን ሆሳዕናን ጨምሮ በርካታ የሚሽነሪ ት/ቤቶች አሉ። በዞኑ ያለው የሙስሊም ት/ቤት ግን አንድ ብቻ ነው። እሱም በሻሸጎ ወረዳ ቦኖሻ ከተማ የሚገኘው ኑር ት/ቤት ነው። በዚህ ት/ቤት በሚሽነሪ ት/ቤቶች ሊማሩ የነበሩ በርካታ ሙስሊም ልጆች ይማሩበታል።

ይህ ት/ቤት ግን በርካታ ወጭዎች ገጥመውት እየተንገዳገደ ይገኛል። ሁሉኑም ወጭዎች መሸፈን እንኳን ቢከብድ አሁን ላይ አንገብጋቢ ማነቆ የሆነባቸውን የመምህራን ደሞዝ ተባብረን እንድንሸፍንላቸው ለመማጸን ወደ እናንተ መጣሁ። የአንድ አመት የመምህራን ደሞዝ 600ሺ ብር ነው። ይህ በእርግጥ በአንድ ሰው ሊሸፈን ይገባው የነበረ ቢሆንም በአቅማችን ልክ ሁላችንም አኽለል ኸይር በመሆን እንድንሸፍነው እጠይቃችኃለው።

ከዚህ በታች የተቋሙን አካውንት አስቀምጣለሁ፣ ከ100 ብር ጀምሮ የአቅማችሁን በመነያት የኸይር ስራው ተጋሪ ይሁኑ፣ ከቻሉ ያስገቡበትን ደረሰኝ ኮሜንት ላይ በማስቀመጥ ለሌላውም መነሳሳት ይፍጠሩ፦

1000432023037
Bonosha Noor school

Eliyah Mahmoud

18 Oct, 04:51


استـ ـشهـاد يحيى الـسـ ـنـوار يفجر مفاجآت غير متوقعة! الشيخ يوجه رسالة ن...
https://youtube.com/watch?v=H-_rdTaGXGc&feature=shared

Eliyah Mahmoud

13 Oct, 09:32


https://vm.tiktok.com/ZMhU3XkDq/

Eliyah Mahmoud

11 Oct, 16:27


الرد على تاريخية صلب المسيح من خلال كتب المؤرخين
https://youtube.com/watch?v=PtkjnW6XsAA&feature=shared

Eliyah Mahmoud

07 Oct, 18:24


Atheist Challenges Muslim On The Need For The Existence of God! Muhammed...
https://youtube.com/watch?v=TCyh6BeSg50&feature=shared

Eliyah Mahmoud

03 Oct, 15:56


ጸጋችን ብዙ ነበር ግን…
……
እጅዎ የጋገረችልዎ የዳጉሳ እንጎቻ ሌሎች ከሚጋግሩልዎ የማር እንጀራ በባህር አሸዋ ቁጥር ልክ ይበልጣል፡፡ ምንም ትቆምጥጥ የእጅዎ ትሩፋት የኾነችው ኩርማን እንጎቻ ከደጋ ማር በላይ ጣፋጭ ናት፡፡

ኑሮዎን በራሶ ልክ ሰፍተው ለራሶዎ እንዲሰፋዎ ማድረግ ይቻላል፡፡ ብዙዎች ኑሮአቸው የጠበባቸው በራሳቸው ልክ መስፋት ስላልቻሉና ሌሎችን አስገብተው በሌሎች ቁመትና ወርድ ልክ ስለሰፉት ነው፡፡

ወዳጄ አኹንም ልብ ይበሉ! እግር ምንም ያህል ቀጭን ይኹን ጨቀጨቁን ማሻገር ከቻለ፣ ሰዎች ዘንድ ካለ ጢያራ በላይ ነው፡፡ አንገትም ምንም ያሕል ይቅጠን ራስን መሸከም ከቻለ ስለምን እንደነ እንቶኔ አንገተ -ደንዳና አልኾንኩም ማለት ጸጋን ማማረር ነው፡፡

ሰው ጤነኛ ኾኖ ሳይጨነቅ ውሎ እያደረ፣ቀናቸው ሌታቸውም ጭንቀትና ስጋት በኾኑ “ባለጸጎች” መቅናቱ አላህ ለርሱ የዋለለትን ዓለማወቁን ወይም እጅግ ዝንጉ መኾኑን ያሳያል፡፡

ቃሩን በጌጥ ተሸልሞ ከሕዝቦች ፊት ሲታይ “ምን አለ እንደ ቃሩን ለኛም በኾነልን” ብለው የተመኙ ቃሩን ከነንብረቱ ምድር ስትውጠው ምኞታቸው ከንቱ እንደነበር ሳይረዱ አይቀርም፡፡

ወዳጄ ሐብት ማለት መብቃቃት ብቻ ነው፡፡ የራስ ዳሽን ያህል ቁልል ወርቅ ካላብቃቃ ከድሃ ሆድ አድራ የምታሞቀው ጭብጥ ቆሎ ብትሻል እንጂ አታንስም፡፡ ስንቶች የቆለሉት ወርቅ ተንዶ መጨረሻቸው ከፍቷል!? ስንቶችስ ምንም ሳይኖራቸው ረዥም ዘመን በጤንነትና በሐሴት ተመላልሰዋል!?

ባለበርካታ ሕንጻ ባለቤቶች ብዙ ክፍል ባለው ሕንጻቸው ውስጥ በርካታ ክፍሎቻቸውን ዘግተው እነርሱ ግን በአንዲት ነጠላ ክፍል ተከርችመው ያድራሉ፡፡ ያ ኹሉ ማንም ላይኖርበት የተገነባ ሕንጻ የስንቱን ምስኪን በር በዘጋ ነበር?! ስንትስ መስጂድ በየገጠሩ ማስገንባት በቻለ ነበር?

ይህ ዓይኑ ቀድሞ መጥገብ እንዳለበት የሚያምንና በአንድ ገበታ አስር ሳሕን በየዓይነቱ ካልቀረበ ያልበላ የሚመስለው መብላትን ስራ አድርጎ የተያያዘ ሕዝብ ካለው ላይ መስጠትን ደም ከመለገስ በላይ አግዝፎ እያየ በርካታ መሄጃ ያጡ ሙስሊም ወጣቶች ከነዲግሪያቸው በየ ጫቱ ቤቱ ቢውሉ ምን ይገርማል?

ትንሽ አለኝ ያለውም፣ በአካፋ እያዛቀ ያለውም፣ ለመዛቅ እየተንደረደረ ያለወም ኹሉም በምልዓት መዳረሻውን ዱንያና ፌሽታ ብቻ አድርጎ እያለ ኡማው ድልና የበላይትን ያገኛል ብሎ ማሰብ፣ ክው ካላ ጓል አፈር ላይ ጤፍ ማጨድን ከመመኘት ይከብዳል!!

ጥቂቶች ብቻ የሰበሰቡት ብዙኋኑ ግን ተኮርምቶ የሚያድርበት ተጨባጭ ላይ ኹነን እጅግ ቅንጡና መትረፍረፍ የበዛበት ኅይወት “አርኣያ” ከሚባሉና መድረኮች ያለነሱ የእህል አውድማ ናቸው የሚባልላቸው ሰዎች ዘንድ ስታይ በዚህ ልክ በዱንያ ባለመፈተንህ አላህን ካላመሰገንኽ ኢማንኽን ተጠራጠር፡፡

“ተዝኪየቱ አኑፉስ” እያሉ የሚሰብኩን አንደበቶች የዱንያ እሽቅድቅድም ውስጥ ገብተው ትላንት ውኃን እንደ ምግብ በሚበሉበት ወቅት (ድሃ በነበሩበት ወቅት) የነበሯቸውን የልብ ወዳጆች ኹሉ አዘቅዝቀው ሲመለከቱ ስታይ አኹንም በዚህ ልክ ባለመፈተንኽ ጌታኽን ካላመሰገንኽን ኢማንኽን ተጠራጠረው፡፡

ወዳጄ አላውቅ አልንና ነው እንጂ እኛ ዘንድ ያለው ጸጋ ኹሉ ከሌላው እጅጉን ይገዝፋል!!!
وإن تعدوا تعمة الله لا تحصوها
https://t.me/boost/E_M_ahmoud

Eliyah Mahmoud

02 Oct, 18:35


ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የቀረበ የትምህርት እድል

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በተለያዩ አካባቢዎች ከሚሰጣቸው የንጽጽራዊ ሀይማኖት ስልጠናዎች በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ እና በሸገር ሲቲ የሚገኙ የተለያዩ መርከዞችና ኢስላማዊ የትምህርት ተቋማትን አወዳድሮ ከፊል የትምህርት እድል ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።

የንጽጽር ትምህርት ስልጠናው ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ለአንድ አመት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ማዕከሉ ባዘጋጀው ስርአተ ትምህርት/Curriculum/ መሠረት በዘርፉ ልምድ ባላቸው ኡስታዞች አማካኝነት ይሰጣል።

በዚህ የትምህርት እድል ለመስጠት የታቀደው የመርከዞችና የትምህርት ተቋማት ብዛት 6 ሲሆን በዚህ ዘርፍ ተማሪዎቻቸውን ማብቃት ለሚፈልጉ ተቋማት ባስቀመጥነው መስፈርት መሠረት አወዳድረን እድሉን እንሰጣለን።

በዚህም መሠረት በተቋማችሁ ውስጥ የኃላፊነት ወይንም የውሳኔ ሰጭነት ሚና ያላችሁ ወንድምና እህቶች ብቻ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ፎርም በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፦

https://bit.ly/4dvInRv

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

Eliyah Mahmoud

01 Oct, 16:17


الحاجز بين الإنسان والمعصية عند ابن تيمية
https://youtube.com/watch?v=Ly-DpaXhjGg&feature=shared

Eliyah Mahmoud

26 Sep, 06:22


ኢማም ኸሊፋ በፍርደ ገምድል ተገደለ (رحمه الله)
https://youtube.com/watch?v=1KH7XYe26qA&feature=shared

Eliyah Mahmoud

26 Sep, 05:24


https://vm.tiktok.com/ZMhjgKqm1/

3,039

subscribers

260

photos

172

videos