እንባ እንደው አይገድም
ፍቅርንና ናፍቆት መለየት ያቃተው
ለማፍቀር አይሄድም
ድም
ድም
ድም
ድም
ማሰብ ማሰላሰል
አስታወስኳት መሰል
ነጋሪት ቢጎሰም መለከት ቢነፋ
ከ'ሷ ዘንድ አድርሶ
ከ'ኔው ዘንድ ሚመልስ አንድ ዜማ ጠፋ
ሁሉም ወሳጅ ሆነ አድርሶ የሚያስቀር
ታድያ
የናፍቆት ነው እንጂ እንዲህ ሆነ ማፍቀር?
እንጃ
እንጃ
እንጃ
ከራስ ጋር ፍጥጫ
በምሰማው ዜማ እሷን ሚያስታውሰኝ
አንድ ነገር አላት
ቆይ እሷ ምንድን ናት
ብናፍቅ ሳልከጅል
እባላለው ወይ ጅል?
ብተክዝ ብፈዝም በሃሳብ ነበልባል
ናፈቃት ነው አፈቀራት ምባል?
አይ.....አይ አይ
ናፈኳትም አልናፈኳትም
ብቻ አላፈቀርኳትም።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan