"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel @andemnet Channel on Telegram

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

@andemnet


ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ አስተምሮ ያላቸውን መርሃግብሮች የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

ከነዚህም መካከል

➯ዝክረ ቅዱሳን (የየቀኑን ስንክሳር)፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ መዝሙር፣ የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ PDF፣
ወቅታዊ የኦርቶዶክሳዊ መረጃዎች እና ወ.ዘ.ተ

@AndEmnet Channel
@AndEmnetZeeOrtodoxTewahdo Group

@JONHABESHA Contact 🙏

፩ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel (Amharic)

የ፩ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel በማያያዝ አስተምሮ ያላቸውን መርሃግብሮች የሚቀርቡበት ቻናል ነው። ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መርሃግብሮች አሉት። ከነዚህም መካከል የየቀኑን ስንክሳር፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ መዝሙር፣ የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ PDF እና ወቅታዊ የኦርቶዶክሳዊ መረጃዎች እና ወ.ዘ.ተ አሉት። እናሊሁን የመለዩን ቻናል እና ቢንከስ አባልነታቸውን መዝሙርን ያስገቡ።

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

22 Nov, 20:11


አባ ዳንኤል ገዳማዊ

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

22 Nov, 20:11


ቅዱስ መርትያኖስ ዘጠራክያ

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

22 Nov, 17:38


አምስቱ አዕማደ ሚስጥራት ማን ማን ናቸው?

ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?

የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ሰባቱ አፅዋማት እነማን ናቸው?

አስሩ ቃላቶች እነማን ናቸው?

6ቱ ቃላተ ወንጌልስ ምን ምን ይለናል?


በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉን 👇👇

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

21 Nov, 18:03


ቅዱስ አባት ዘካርያስ

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

21 Nov, 18:03


.......➯በረቡዕ ዕለትም በዘጠኝ ሰዓት ደክሞት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ከበላዩ ካለችበት ግድግዳ ላይ ራሱን አስጠግቶ አንቀላፋ። በእንቅልፉም ውስጥ ሳለ የሥዕሊቱ እጅ ሥጋውን ሲዳሥሥ አየ በዚያንም ጊዜ ነቅቶ ሥጋው ከለምጹ ነጽቶ አገኘው ታላቅ ደስታም አደረገ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም አመሰገነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም አመሰገናት ረድኡም ሲመጣ ና ልጄ ሆይ ሥጋዬን እይ እመቤቴ ማርያም ከደዌ አንጽታኛለችና አለው በዚያችም ቤተክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እስከ ቀዳሚት ሰንበት ድረስ ኖረ።

➯ከዚህም በኋላ ተነሥቶ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዘካርያስ ሔደ በዕለተ እሑድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያለ በእርሱ ላይ የሆነውን አስረዳው እንዲህም አለው ይህ ሁሉ የተደረገልኝ በከበረች ጸሎትህ ነው። የከበረ አባ ዘካርያስም እንዲህ ብሎ መለሰለት እግዚአብሔር ንጹሕና ቅን የሆነ ልቡናህን ተመልክቶ ልመናህንና ዕንባህንም ተቀብሎ ከደዌህ አነጻህ አሁንም ከተቀበልከው ጸጋ እንባረክ ዘንድ ቀድሰህ ሥጋውንና ደሙን ልታቀብለን ይገባሃል። ያን ጊዜም መሥዋዕትን ሠርቶ ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው በቤተ ክርስቲያን ያሉትም ሁሉ ከእርሱ ቡራኬ ተቀበሉ ስለዚች ምልክትም አደነቁ ድንቆች ተአምራትን የሚያደርግ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

➯ሁለተኛም አንድ ዲያቆን ወደ አባ ዘካርያስ መጥቶ ሰገደለት በፊቱም አለቀሰ እግሮቹንም እየሳመ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ራራልኝ እኔ ተሳስቼ በኃጢአት ወድቄአለሁና ወዲያውኑ ሥጋዬ ሁሉ ለምጽ ሆነ። አባ ዘካርያስም ልጄ ሆይ በእግዚአብሔር ፊት በድካም ላይ መጽናት ይቻልሃልን አለው አዎን አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ።

➯በዚያንም ጊዜ በእርሱ ዘንድ በጨለማ ቤት ዘጋበትና እንዲህ ብሎ አዘዘው ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ በመቆም በቀንም በሌሊትም ስለ ኃጢአቱ እየተጸጸተ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት እንዲማልድ አባ ዘካርያስም ከሦስት ቀኖች በኋላ ጥቂት እንጀራ በሚዛን መዝኖ ጥቂት ውኃም ሰጠው ሦስት ሱባዔዎችም እንዲህ አድርጎ ሥጋውን ጐበኘ ለምጹንም አገኘው በወር መጨረሻም ጐበኘው ለምጹን በሥጋው ላይ አገኘ።

➯ልጄ ሆይ በርታ አትፍራ አለው አርባ ቀኖችም ከተፈጸሙ በኋላ ጐበኘው ሥጋው ከለምጹ ነጽቶ አገኘው ዘይትንም ቀባው ልጄ ሆይ እነሆ ድነሃል ነፍስህን ጠብቅ ከእንግዲህም ዳግመኛ ወደ ኃጢአት ሥራ እንዳትመለስ ተጠበቅ አሁንም በሰላም ወደ ቤትህ ግባ አለው እርሱም የተመሰገነ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ገባ።

➯እግዚአብሔርም በዚህ አባት እጆች ድንቆች ተአምራትን አደረገ በሹመቱም ወንበር ሃያ ስምንት ዓመት ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ ይኸውም ከንጹሐን ሰማዕታት ዘመን በሰባት መቶ ስልሳ ነው።


➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


ህዳር 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አእላፍ (99ኙ) ነገደ መላእክት
2.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
3."13ቱ" ግኁሳን አበው (ሽፍቶች የነበሩ)
4.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእንጽና
5.አባ ዘካርያስ ሊቀ ዻዻሳት

ወርኀዊ በዓላት

1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
4.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ


➯ - ስለ መላእክትም፦ "መላእክቱን መናፍስት፡ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ" ይላል . . .ነገር ግን ከመላእክት፦ "ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ" ከቶ ለማን ተብሏል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ፡ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን? (ዕብ. 1፡7-14)


@AndEmnet #ስንክሳር ህዳር ፲፫/13 ቀን

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

21 Nov, 18:03


ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእንጽና

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

21 Nov, 18:03


አእላፍ መላእክት (፺፱/99ኙ ነገደ መላእክት)

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

20 Nov, 19:10


#ቅዱስ_ሚካኤል_ወዳጅ_ነህ_ለሁሉ

#ዘማሪት፦ ምርትነሽ

@AndEmnet መልካም በዓል አሜን በሉ

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

20 Nov, 19:10


#ሚካኤል_ወረደ

#ዘማሪ፦ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

@AndEmnet

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

20 Nov, 19:10


#ኦ_ቅዱስ_ሚካኤል

#ዘማሪ ፦ ሊቀ-መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

@AndEmnet መልካም በዓል

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

20 Nov, 19:10


#ሚካኤል_ስዩመ

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

20 Nov, 19:10


#ቅዱስ_ሚካኤል

"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

20 Nov, 19:10


#ሚካኤል_ይለይብኛል

#ዘማሪ ፦ ዲ/ን አቤል መክብብ

18,852

subscribers

3,267

photos

29

videos