ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ @mkaddisababacentermedia Channel on Telegram

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

@mkaddisababacentermedia

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ (Amharic)

እንኳን ደህና መጣህ! በምትሳካሽ ቀረባ ስብስብ በመሆን ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ በትክክለኛ ድምፅ የተለያዩ እና የተሰማሩ የአስተዳደር ኮርፖሬሽን የሚዘረብኩበት ቦታ። የሚወጡ የቁሳቁሶ ስብስብ እና ልክ ታሪክ። እና ያይዘናል። mkaddisababacentermedia ከእነዚህ መነሻ ለሚሠሩ እና የሚገኙ ተመሳሳይ ጋቦንጎንት። ለመተንግት እና መሠረት ኃላፊዎች እና አገሪቱ ለመዝጋት በማላክና በማክበር የቁሳቁሶ ስብስብ ሚስዎችን ለማስተላለፍ የቱንዶን ምሁርና ቆሞንዳ ሚስዮች በተመሳሳይ እና ድምጽ ሥራዎች ይፈልጋሉ።

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

01 Jan, 09:25

የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎች አዲስ አበባ ማእከል እያስገነባ ያለውን የትውልድ ማእከል ግንባታ ፕሮጀክት ጉብኝት አደረጉ።

ባለሙያዎቹ በአጠቃላይ ዝርዝር ዓላማውን እንዲረዱ የተደረገ ሲሆን በተሰማሩበት የሚዲያ ዘርፍ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውን ከፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
በቴሌግራም

https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia/815
በፌስቡክ https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacentermk?mibextid=ZbWKwL ይከታተሉ

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

29 Dec, 12:19

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የአቅም ማጎልበቻ መርሐ ግብር እያከናወነ ይገኛል።

በማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል አባላት እና ማስተባበሪያ አገልግሎት ዋና ክፍል የማስተባበሪያዎች ቀን በሚል ርዕስ በተቋማዊ ለውጥ ትግበራ እንደ አዲስ በተደራጁት ማስተባበሪያዎችና ግንኙነት ማእከላት ለሚያገለግሉ የሥራ አስፈጻሚ አባላት የአቅም ማጎልበቻ መርሐ ግብር ከትላንት ምሽት ጀምሮ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የማእከሉ አባላት እና ማስተባበሪያ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ሐና ሽታዬ ገልጸዋል።

ወ/ሪት ሐና አክለውም ማስተባበሪያዎች የተቋማዊ ለውጡን እሳቤ ተገንዝበው እንዲያገለግሉ ለማድረግ እነዚህን የመሳሰሉ የአቅም ማጎልበቻ ሥራዎችን በተከታታይነት መተግበር ይገባል ብለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
በቴሌግራም

https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia/815
በፌስቡክ https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacentermk?mibextid=ZbWKwL ይከታተሉ።

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

23 Dec, 05:03

ለአዲስ አበባ ማእከል የትውልድ ማእከል ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ ልዩ መርሐ ግብር ተካሔደ።

(ዜና ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል) ታኅሣሥ14 ፣ 2017 ዓ.ም፤
------------------------------------------------

በግራንድ ኤልያና ሆቴል በተካሄደው በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና ጥሪ የተደረላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ምዕመናን በጉባኤው ላይ ተሳትፈው አስተዋጽዖአቸውን አበርክተዋል። ብፁዕነታቸው ስለ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ሲናገሩ የሚገነባው ባለ ዐሥራ ሁለት ወለል ሕንፃ መሆኑን አውስተው ይህ እየተገነባ ያለው ሕንፃ ለልጆቻችን ከመሆኑ ባሻገር ለትውልድ የምናስተላልፈው ቅርስ በመሆኑ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ሲሉ ተናግረው ፤ ማኅበረ ቅዱሳን እየሠራ ያለውን መንፈሳዊ ሥራ አድንቀው ብፁዕነታቸው ለሕንፃው መጠናቀቅ በሔዱበት ሁሉ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።

ይህ እየተገነባ ያለው ሕንፃ የሕፃናት እና የወጣቶች የስብዕና ፣ የክህሎትና ሙያዊ ፤ ሁለንተናዊ የሥነ ልቦና ግንባታ የሚሠጥበት ሕንፃ ነው ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ማእከል ሰብሳቢ ዲያቆን ኃ/ማርያም መድኅን ናቸው።
የማእኩሉ ሰብሳቢ አክለውም ይህ ሕንፃ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ከጎናችን አትለዩን ሲሉ ተሳታፊውን ተማጽነዋል።

መሪጌታ ባሕረ ጥበብ ሙጬ"ሉላዊነት ተጽዕኖ በኦርቶዶክስ ላይ" በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡት ሲሆን በጽሑፋቸው ዓለም አሁን የደረሰችበትን አሳሳቢ አጣብቂኝ አንስተው ሁላችንም እምነታችንን ለትውልድ ለማስተላለፍና ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ ብቁ ዜጋ ለማፍራት በንቃት መሥራት እንደሚገባ በዳሰሳ ጥናታቸው አረጋግጠው ለተሳታፊዎች አካፍለዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

02 Dec, 07:23

በዚሁ የአባላት ልዩ መርሐ ግብር ላይ በመ/ር ብርሃኑ አድማስ " እግዚአብሔርን ማየት" በሚል ትምህርተ ወንጌል፣ በቀ/ዶ/ር ይቻለዋል ጎሽሜ የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ፈተናዎችና ጉዞን በተመለከተ ልምድ የማካፈል እና  በቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ ብርሃኑ እና በዘማሪት ብዙዓየሁ ተክሉ የመዝሙር  መርሐ ግብራት ተከናውነዋል፡፡

በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አማካኝነት “እርፍ ይዞ ወደ ኋላ የለም፣ ማኅበራችሁን ጠብቁ ፣በገባችሁት ቃል መሠረት ቤተ ክርስቲያናችሁን አገልግሉ፡፡” በሚል አባታዊ ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

👉Telegram
https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia
👉Facebook
https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacentermk?mibextid=ZbWKwL

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

02 Dec, 07:21

“ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ” በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡

በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ወደ ቀደመ ነገር እንመለስ በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር በደብረ ሰላም ቦሌ መድኃኔዓለም እና መጥምቀ መለኮት ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ዕለት አከናውኗል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ የማኅበሩ የሥራ አመራር አባላት እና ከ2000 በላይ የአዲስ አበባ ማእከል አባላት ታድመዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ኃ/ማርያም መድኅን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ  “ አዲስ አበባ ማእከል በተቋማዊ ለውጡ ትግበራ መሠረት የጀመረውን አዲሱን መዋቅራዊ አደረጃጀት ውጤታማ ለማድረግ ቀዳሚው ተግባር የአባላትን አገልግሎት ማጠናከር ነው” ብለዋል፡፡  ቀጥለውም “ አባላት ቃል ኪዳናቸውን አድሰው የአገልግሎት ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወደ ማኅበሩ ሲቀላቀሉ የገቡትን ቃል ሊፈጽሙ ይገባል “ ሲሉ የአጽንዖት መልዕክታቸውን አስተላለፍዋል፡፡

የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ በዕለቱ ለተገኙ ታዳሚዎች ስለ ጉባኤው ዓላማ እና የአባላት ድርሻን በተመለከተ “የአባላት የአገልግሎት በር” በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን አባላት በተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ተሳትፏቸው የጎላ እንዲሆን የሚሳተፉባቸው የአገልግሎት አማራጭ በሮች ክፍት ሁነው እንደሚጠብቋቸውና ገብተው እንዲያገለግሉ አማራጭ የአገልግሎት በሮችን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

01 Dec, 12:11

በአሁኑ ሰዓት በመ/ር ብርሃኑ አድማስ ትምህርተ ወንጌል እየተሰጠ ይገኛል።

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

01 Dec, 10:50

ወደቀደመው ነገር እንመለስ ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር በጸሎተ ወንጌል ተጀምሯል።

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

30 Nov, 14:28

ወደቀደመ ነገር እንመለስ መርሐ ግብር ዝግጅት ተጠናቋል።

( የአባላት ልዩ መርሐ ግብር ዓቢይ ኮሚቴ )

ወደቀደመ ነገር እንመለስ በሚል መሪ ቃል በነገው ዕለት ለሚካሄደው የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር ዝግጅት ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን በመርሐግብሩ ዝግጅት ኮሚቴ ተገለጸ።

የዝግጅት ኮሚቴው አስተባባሪ የሆኑት ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ እንደገለጹት ይህ በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል አባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር ለረዥም ጊዜ ታስቦበት ልዩ ልዩ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ እና አስፈላጊ ክንውኖች ተጠናቀው አንድም የማእከሉ አባላት ሳይቀሩ የሚታደሙበት ሲሆን በዕለቱ የሚቀርቡት:-
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች
👉 ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች  ከልዩ ልዩ የትምህርተ ወንጌል እና መዝሙሮች ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ብለዋል።

ዲ/ን ሲሳይ አክለውም እኛ ተዘጋጅተናል። አባላትም በቀጠሯችን ይገኛሉ በማለት ሐሳባቸውን ሰጥተዋል።

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

30 Nov, 06:53

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማጽኛ  መርሐ ግብር

በዕለቱም፦

👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።

እርስዎም በማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!

ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

29 Nov, 09:50

29 Nov, 07:29

+++ማስታወቂያ+++

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

28 Nov, 07:16

27 Nov, 13:00

24 Nov, 14:34

23 Nov, 11:14

22 Nov, 08:16

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማጽኛ  መርሐ ግብር

በዕለቱም፦

👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።

እርስዎም በማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!

ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

👉Telegram
https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia
👉Facebook
https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacentermk?mibextid=ZbWKwL

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

20 Nov, 19:06

5ኪሎ ማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ 4ኛ ወለል ፦ 0935213944

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

16 Nov, 14:39

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማደሻ  መርሐ ግብር

በዕለቱም፦

👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 አባላት የአገልግሎት ቃል ኪዳናቸውን ያድሳሉ
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።

እርስዎም በማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!

ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

14 Nov, 15:34

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማደሻ  መርሐ ግብር

በዕለቱም፦

👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 አባላት የአገልግሎት ቃል ኪዳናቸውን ያድሳሉ
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።

እርስዎም ከማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!

ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

01 Nov, 10:58

ማስታወቂያ

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

01 Nov, 07:52

ማኅበረ ቅዱሳን ከቡስካ ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምና አቡነ ሙሴ ጸሊም እና ኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜና ማርቆስና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንድነት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመ።

ማኅበሩበ ቡስካ ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ወአቡነ ሙሴ ጸሊም እና ኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜና ማርቆስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንድነት ገዳም የተዘጋጀውን የቡስካ የማር ምርት ለማከፋፈል የስምምነት ሰነድ የተፈራረመ ሲሆን በዕለቱ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሓፊ መ/ር ዋሲይሁን በላይና የገዳሙ ተወካይ ተገኝተዋል፡፡

ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር መሠረት የሆኑት ገዳማት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆኑን ያነሱት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ይህ ስምምነት ገዳማውያን የትጋት ምሳሌ የመሆናቸው ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳንም ገዳማትን ለማጠናከር ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሠራ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው አሁንም ለሁሉም የሚጠቅም ስምምነት መፈራረሙን አድንቀዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ አክለውም ሌሎች ገዳማት ይህንን ተሞክሮ ወስደው ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን የሚጠቅም ሥራ መሥራት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ገዳማት ከማር ምርት ባለፈ በሌሎች ዘርፎችም አብሮ ተጋግዞ የመሥራት ልምድ መዳበር አለበት ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

👉Telegram
https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia
👉Facebook
https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacentermk?mibextid=ZbWKwL

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

01 Nov, 07:11

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ስለምጣኔ ሀብት እድገት፣ በሀገራችን እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆኑ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን፤ ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 21ቀን 2017ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

22 Oct, 10:26

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ጉባኤው፦
1.ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
3.ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
4.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ (ዘስያትል)
5.ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ
6.ብፁዕ አቡነ ኤጲፍንዮስ
7.ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕን በአጀንዳ አርቃቂነት ሰይሟል።

የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

22 Oct, 08:12

ይህም በመሆኑ ሁሉም ፍጡራን አራዊትም ሆኑ እንስሳት ይብዛም ይነስ ጠባቂና መሪ እንዳላቸው እናስተውላለን፤ በተለይም የፍጥረታት ቁንጮ የሆኑ መላእክትና ሰዎች መሪና ሹም እንዳሏቸው የማንክደው ሓቅ ነው፡፡ ቅዱስ መጽሓፍም ይህንን ደጋግሞ ያስረዳል፤ የእነዚህ ሁሉ ላዕላዊ ጠባቂና መሪ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በፍጡራን ላይ ፍጡራንን ጠባቂዎች አድርጎ ሲሾም ፍጡራንን የክብሩ ተሳታፊ ለማድረግ እንጂ የእሱ ጥበቃ አንሶ ወይም ድጋፍ ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ፍጹምና ላዕላዊ የሆነ ጥበቃው ሁሉንም ያካለለ ነውና ከእሱ ቊጥጥርና ጥበቃ ውጭ አንድም ነገር እንደሌለ የምንስተው አይደለም ፡፡
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
በአምሳለ እግዚአብሔር በተፈጠረውና በክብር መልዕልተ ፍጡራን በሆነው ሰው ላይ በዚህ ዓለም የተሾሙ ሁለት አካላት አሉ፤ እነሱም የመንፈስና የዓለም መሪዎች ናቸው፡፡ በተለይም የመንፈስ መሪዎችና ጠባቂዎች የተባሉት በመንፈስ ቅዱስ ተሹመን በዚህ ክርስቶሳዊ ጉባኤ የተሰበሰብነው እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ነን፡፡
ይህ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መሪና ጠባቂ ነው፤ ከዚያም ባሻገር እንደ ቃሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ቃሉን በመስበክ ፍጥረተ ሰብእን በሙሉ የመጥራት ተልእኮ ለእኛ የተሰጠ የቤት ስራ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የተሰጠን ኃላፊነት እጅግ በጣም ታላቅ እንደመሆኑ የሚጠበቅብን ውጤትም በዚያው ልክ ትልቅ ነው፤ ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይፈለግበታል ያለው የጌታችን አስተምህሮም ይህንን ያስታውሰናል፡፡
ሁላችን እንደምንገነዘበው አሁን የምንገኝበት ዘመን የጸላኤ ሠናያት መንፈስ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ከምንም ጊዜ በበለጠ ጦሩን ሰብቆ የተነሣበት ጊዜ ነው፤ አሁን ያለው ዓለም በሀገራችንም ሆነ በሌላው ክፍለ ዓለም ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ከባድ ፈተና ደቅኖብናል፡፡ ክፉው መንፈስ የሰውን አእምሮ በማዛባት ምእመናንን በቅዱስ መጽሐፍና በሕገ ተፈጥሮ ከተመደበላቸው የጋብቻ ሕግ በማስወጣት እንስሳት እንኳ የማይፈጽሙት ነውረ ኃጢአት እንዲፈጽሙ በመገፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ በአማንያን ልጆቻችን ላይም በረቀቀ ስልት ግድያ፣ እገታ፣ አፈና፣ የመብት ተጽዕኖ እና አድልዎ በማድረግ እንደዚሁም በአስመሳይ ስብከትና አምልኮ ጣዖትን በማለማመድ ሕዝቡ ሳይገባውና ሳይጠነቀቅ ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዲወጣ እያደረገ ነው፡፡
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ክፉው መንፈስ በተራቀቀና በተራዘመ ስልት ሊውጠን በተነሣ ልክ እኛም ከእሱ እጥፍ በሆነ መለኮታዊ ኃይል ልንመክተው ካልቻልን በፈጣሪም ሆነ በትውልድ እንደዚሁም በታሪክ ፊት በኃላፊነት መጠየቃችን አይቀርም፡፡ መከላከል የምንችለውም ችግሩን በውል ከመረዳት አንሥቶ ሕዝቡን በደምብ በማስተማርና በመጠበቅ እንደዚሁም ለመሪነታችን ዕንቅፋት ከሚሆኑን ዓለማዊ ነገሮች ራሳችንን በማራቅ ነው፡፡ ሕዝቡም በዚህ ዙሪያ ሊያደምጠንና ሊከተለን የሚችለው መስለን ሳይሆን ሆነን ስንገኝለት ነው፡፡ ሕዝቡ ሊከተለን የሚችለው እሱን በብቃት ለመጠበቅ ዓቅሙም ተነሣሽነቱም ቁርጠኝነቱም እንዳለን ሲመለከት፣ እንደዚሁም ከዕለት ተዕለት ተግባራችንና አኗኗራችን የሚያየው ተጨባጭ እውነታ ኅሊናውን ሲረታ እንደሆነ አንርሳ፡፡
የምናስተምረው ሌላ የምንሰራው ሌላ ከሆነ ግን ከሕዝቡ አእምሮ መውጣታችን እንደማይቀር መገንዘብ አለብን፤ በመሆኑም በሰብእናችን፣ በአስተዳደራችን፣ በአመራራችንና በጥበቃችን ሁሉ እንደቃሉና እንደቃሉ ብቻ ለመፈጸም መትጋትና በቁርጥ መነሣት ጊዜው አሁን ነው እንላለን፡፡ ይህ ሲሆን በምእመናንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት አስተማማኝና እንከን የለሽ ይሆናል፤ ይህ ከሆነ እውነትም የመሪነት፣ የእረኝነትና የመልካም ተምሳሌነት ኃላፊነታችንን በትክክል ተወጥተናል ማለት እንችላለን፡፡
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡ ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክልል መምራት ይጠበቅበታል፡፡ ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡
እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡ ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡ በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡ ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ

ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡ በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡
በመጨረሻም
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን የጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑ እናበስራለን፡፡
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን::

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

22 Oct, 08:10

በጥቅምት 2017 ዓም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
•ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጐጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
ዓመቱን ጠብቆ ስለ አጠቃላይ ተልእኮአችን ለመወያየት በዚህ ጉባኤ የሰበሰበን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን፤
“ወይእዜኒ ግብኡ ኀበ ኖላዊሃ ወዓቃቢሃ ለነፍስክሙ፤ አሁንም ወደ እረኛችሁና ወደ ነፍሳችሁ ጠባቂ ተመለሱ” (1 ጴጥ 2÷!5)
ሁሉን የሚችል አምላካችን እግዚአብሔር በፍቅሩና በፍቅሩ መነሻነት ብቻ ፍጥረታትን በሙሉ እንደፈጠረ ቅዱስ መጽሐፍ ያስተምረናል፤ ከፈጠረም በኋላ የክብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ወዶ ክብሩን አድሎአቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለፍጡራኑ ካደላቸው ነገሮች አንዱ በየዓይነታቸው ጠባቂና መሪ እያደረገ በፍጡራን ላይ ፍጡራንን መሾሙ ነው፤ ይህ ስጦታ በሰማይም ሆነ በምድር ላሉ ፍጥረታት የተሰጠ የሱታፌ መለኮት ስጦታ ነው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

21 Oct, 16:26

የቅዱስ ሲኖዶስ የ2017 ዓ.ም የጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ተካሄደ፡፡

የመክፈቻ ጸሎቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት የሥራ ኀላፊዎችና አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ካህናት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት በቅዱስነታቸው የመክፈቻ ንግግር የሚጀምር ይሆናል፡፡

👉Telegram
https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia
👉Facebook
https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacentermk?mibextid=ZbWKwL

1,288

subscribers

593

photos

27

videos