ማስታወቂያ
--
የሰው ኃይል ስልጠናና ልማት ቢሮ የውስጥ አሰልጣኞችን ለመመልመል በወጣው ማስታወቂያ መሰረት በስራ ክፍሉ የኢሜይል አድራሻ አማካይነት አመልካቾችን ስንቀበል መቆየታችን ይታወሳል፡፡
ይሁንና በርከት ያሉ አመልካቾች ማስታወቂያውን አላገኘንም የሚሉ ቅሬታዎችን ስላቀረቡልንና በ GO ዘርፍ የአዳማ 1 የን/ኃ/ማ/ጣቢያ እና በ TSO ዘርፍ የ Converter station የስልጠና ፍላጎቶች አለመካተታቸው ስለተገለጸልን ምዝገባው እነርሱን ያማከለ እንዲሆን ለማድረግ የምዝገባ ቀነ ገደቡን ለአንድ ሳምንት ያራዘምን ሲሆን የመጨረሻው ቀን ጥቅምት 24/2017 መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
--
ማሳሰቢያ፡-
· ለምዝገባ የስራ ክፍሉ ከላከው ቅጽ ውጪ አይጠቀሙ፤
· በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ኢሜይል አይላኩ፤ ማስተካከያዎች ሲኖሩዎት በቀደመው ኢሜይል ላይ reply በማለት ማስተካከያውን ይላኩልን፤
· በግል ኢሜይል የሚላኩ ማመልከቻዎች ኮሚቴው ጋ ስለማይደርሱ እባክዎን በስራ ክፍሉ ኢሜይል አድራሻ ብቻ (
[email protected]) ይላኩ፤
--
ከውስጥ አሰልጣኝ ምልመላ ጋር በተያያዘ ለተነሱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች (FAQ) ምላሽ ስለመስጠት፡-
1. አስቀድሞ በተቋሙ ውስጥ በማሰልጠን ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞችን/ የስራ ኃላፊዎችን ማስታወቂያው ይመለከታልን?
· በትክክል! የራስ አቅም ስልጠና ዓላማ በተቋሙ ውስጥ በእውቀት ሽግግር ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች/ የስራ ኃላፊዎች በአሰልጣኞች ስልጠና /TOT – Andragogy/ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስልጠና የወሰዱ ብቻ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፤ በዚህም መሰረት በስልጠና ተግባር ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች በየሦስት ዓመቱ የሚታደስ የሰርተፊኬሽን ስልጠና ወስደው ሰርተፊኬት መያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
2. አስቀድሞ ተመሳሳይ ፕሮግራም በሌለበት ሁኔታ የማሰልጠን ልምድ ከመስፈርቶች ውስጥ ለምን ተካተተ?
· ይህ አሰራር ጅምር እንደመሆኑና ቀደም ሲል በተቋሙ ውስጥ በቂ አሰልጣኞች ሰርተፊኬት እንዲኖራቸው ስላልተደረገ መስፈርቱ የዚህ ዙር የማወዳደሪያ ነጥብ አይሆንም፤ ሆኖም ተቋሙ በሁሉም የስራ ዘርፎች በቂ አሰልጣኞችን ፈጥሬያለሁ ብሎ ሲያምን ከዚህ በኋላ በሚኖሩ የኦፕሬሽን ዘርፍ ውድድሮች ላይ ማወዳደሪያው በ 100% ተግባራዊ ይደረጋል፤
3. በሌሎች ዘርፎች ላይ ማስታወቂያ መች ይወጣል?
· ቀደም ሲል እንደገለጽነው በሁሉም የስራ ዘርፎች ማስታወቂያዎች ይወጣሉ፤ በቅርቡ በ SAP Phase I ርዕሰ ጉዳዮች (HCM, FICO, PS, Material mgt… ወዘተ) ላይ አሰልጣኞችን እንመለምላለን፤ በቀጣይም በ HR, Safety, QMS, Legal, Finance, Cyber security, ICT, Gender… በመሳሰሉት ዘርፎች ላይ አሰልጣኞችን እንለያለን፤ በሦስተኛ ደረጃ የፕሮጀክትና የዲዛይን ይዘት ባላቸው የ Engineering, GC, TSC, Planning እና መሰል ዘርፎች ላይ አሰልጣኞችን እንለያለን፡፡
4. ከከፍተኛ በታች የስራ አፈፃጸም ምዘና ውጤት ያለው የሚለው ሃሳብ ቢብራራ፤
· “ከከፍተኛ በታች የስራ አፈፃጸም ምዘና ውጤት ያለውና በሕ/ስምምነቱ መሰረት በዲሲፕሊን ቅጣት የጊዜ ገደብ ውስጥ የሌለ መሆን አለበት” የሚለው አገላለጽ መጠነኛ ስህተት ያለው ስለሆነ “ከፍተኛ እና ከከፍተኛ በላይ የስራ አፈፃጸም ምዘና ውጤት ያለውና በሕ/ስምምነቱ መሰረት በዲሲፕሊን ቅጣት የጊዜ ገደብ ውስጥ የሌለ መሆን አለበት” በሚል ይታረም፡፡
· ከፍተኛ የስራ አፈፃጸም ውጤት ማለት ከ 90 እስከ 94.99 ድረስ ያለ ነጥብ ነው፤
5. የስራ ልምድ ውጤት እንዴት ነው የሚሰላው?
· የስራ ልምድ የሚሰላው እስከ 14 ዓመት ላለው የስራ ልምድ ለእያንዳንዱ ዓመት አንድ ነጥብ በመስጠት ሲሆን፣ 15 ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ባለሙያዎች/ የሥራ ኃላፊዎች ሙሉ 15 ነጥብ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
____
የሰው ኃይል ስልጠናና ልማት ቢሮ
We strive to create a learning Organization!