ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

@merkorawse


ንሴብሖ ለእግዚአብሔር

“ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል።”
— ምሳሌ 9፥9
“ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።”
— ሕዝቅኤል 7፥26





https://www.tiktok.com/@yaredaweyan

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

23 Oct, 07:36


🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

22 Oct, 07:14


ከታዘብኩት ነው

ቅዳሜ ዕለት ያደርኩበት ደብር የነበረው የሊቃውንት ብዛት አጃኢብ የሚያስብልና እጅግ አስደሳችም ነበር።

ከሁለት መቶ በላይ ሊቃውንትና ታዳጊዎች በተሳተፉበት የማህሌተ ፅጌ መርሀ ግብር ላይ ግን የማህሌተ ፅጌን መፅሀፍ ጥራዝ የያዙ ሊቃውንት ከሰባት አይበልጡም ነበር 💔

ካቻምና ይሻል ነበር .....

አምና ያሰጋ ነበር....

ዘንድሮ ግን ባሰ....

አንድ ካህን መፅሐፉን ያዝ አድርጎ ሲታይ ልክነቱ እንዳለ ሆኖ በራሱ ግርማ ሞገሱ ይማርካል።

በዚህ ጉዳይ ላይ #ሲኖዶሱ ሊያስብበት ይገባል።

ሁሉም የየራሱ አገልግሎት አለው ስማርት ስልክ የፀሎት መፀሐፍን በፍፁም ሊተካ አይችልም‼️

ቴክኖሎጂ መልካም ሆኖ ሳለ ቦታ ግን ብንመርጥለት ተገቢ ይመስለኛል።

@Abigail K Fasika

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

16 Oct, 14:48


የጥቅምት ወር አመታዊ በዓላት

ጥቅምት 4 - አብርሃ ወአፅብሃ - በመሪ ሃያት ፋኑኤል - በየካ ተራራ ዋሻ ተክለሃይማኖት - በዘነበ ወርቅ አቡነ አረጋዊ

ጥቅምት 5 - አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ

ጥቅምት 7 - ቅድስት ሥላሴ - በቦሌ አራብሳ ዋሻ ሥላሴ

ጥቅምት 13 - አቡነ ዘርዓ ብሩክ - በአስኮ ቃሉ ተራራ አቡነ ሃብተማርያም

ጥቅምት 14 - አቡነ አረጋዊ

ጥቅምት 17 - ቅዱስ እስጢፋኖስ

ጥቅምት 19 - አቡነ ሐራድንግል - በሃያት ጣፎ ዋሻ ሚካኤል

ጥቅምት 22 - ቅዱስ ዑራኤል - ኮተቤ

ጥቅምት 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም

ጥቅምት 28 - ቅዱስ አማኑኤል

ጥቅምት 30 - ቅዱስ ማርቆስ - 6 ኪሎ

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

14 Oct, 17:31


እንኳን ለአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ በአል አደረሳችሁ
የፃዲቁ በረከት ምልጃና ፀሎት ከሁላችሁም ጋር ይሁን ❤️❤️❤️

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

14 Oct, 17:31


🌺₅ ....ጥቅምት 5 [፭]

✞ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ✞
➝ ዕረፍት እና ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት🌺

1) ጀሞ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ

ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጀሞ

፪) አስኮ መካነ ሕይወት ቅዱስ አማኑኤል እና አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ/ክ/ከ አስኮ አዲስ ሰፈር

፫) ድልበር መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ጉለሌ ድልበር

፬) የሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም

ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ/ክ/ከ ልኳንዳ ፈጥኖ ደራሸ ካምፕ

፭) ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሐይማኖት

ልዩ ስም፦ ልደታ /ክ/ከ መርካቶ

፮) አየር ጤና ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ/ክ/ከ አየር ጤና

፯) ብርሀናተ ዓለም ጴጥሮስወጳውሎስ  እና ቅዱስ ገብርኤል

ልዩ ስም፦ አዲስ ከተማ ክ/ከ ዊንጌት ት/ቤት

፰) ቤተል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል  ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ኮ/ቅ/ክ/ከ ቤተል

፱) መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል

ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ/ክ/ከ ፋኑኤል ሰፈር

፲) ቦሌ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ

ልዩ ስም፦ ቦሌ ክ/ከ ቦሌ እግዚአብሔር አብ

፲፩) ኮተቤ ማኅደረ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል  ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ የካ ክ/ከ ሉቄ

፲፪) መሪ አያት ምስራቀ ፀሐይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ልዩ ስም፦ ቦሌ ክ/ከ መሪ

፲፫) ቱሉ አቦ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ፤ቅዱስ ዑራኤል እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ቱሉ አቦ

፲፬) የረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ቦሌ ክ/ከ ጎሮ

፲፭) ሲኤምሲ ደብረ ጽባህ ቅዱስ ሚካኤል  ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ የካ ክ/ከ ሲኤምሲ

፲፮) ደብረ ጽጌ ቅዱስ ኡራኤል

ልዩ ስም፦ ቦሌ ክ/ከ ካዛንቺስ

፲፯) ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ የካ ፈረንሳይ ለጋስዮን

፲፰) ጎፋ መብራት ኃይል ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጎፋ መብራት ኃይል

፲፱) ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል

ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 1 ለቡ(ፉሪ)

፳) መካኒሳ ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ አቦ

፳፩) ምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም

ልዩ ስም፦ አቃቂ ክ/ከ ሳሪስ

፳፪) ኮዬ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ኮዬ

፳፫) ቀርሳ ፈለገ ብርሀን ቅድስት ልደታ ለማርያምና አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ቀርሳ

፳፬) ደብረ ሠላም ቅዱስ በአለወልድ ቤ/ክ

፳፭) ቃሊቲ መካነ ስብሀት ቅድስት ሥላሴ እና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ ክ ከተማ
ወረዳ 8 አረጋውያን ክብካቤ ጀርባ

፳፮) የላምበረት ደብረ ፀሐይ አቡነ አረጋዊ ወገብረ መንፈስ ቅዱስ ወ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ

ልዩ ቦታ፦ የካ ክ/ከ ላምበረት

፳፯) አንቀፀ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ ሐብተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን

ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ ክፍለ ከተማ ወይራ የጋራ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ጀርባ

፳፰) የቦሌ አራብሳ ዋሻ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፣ ቅድስት ልደታ ለማርያም ፣ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ፣ ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን

ልዩ ስም፦ አራብሳ ኮንዶሚኒየም አከባቢ

፳፱) የካ አባዶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን

ልዩ ስም፦ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም

፴) ደብረ ሠላም ቅዱስ በአለወልድ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ገላን ከተማ መምህራን ሰፈር አለፍ ብሎ

በዓለ ንግሱ ይከበራል።
[ልዑል እግዚአብሔር ]
በፍቅር፣ በሠላም፣ በጤና ያገናኘን
🙏አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ይጠብቁን 🙏
    ₃..አሜን | Amen..₃ 🤲🙏
  ❤️🌼❤️🌼❤️🌼❤️🌼

🌺✞ የንግሥ በዓላት ✞🌺

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

13 Oct, 08:16


🌺₄ .... ጥቅምት 4 [፬]

✞ አብርሃ ወአፅብሃ ✞

፩) ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ ወ ገብረ ክርስቶስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ኮ/ቅ/ክ/ከ ወረዳ 1 ዘነበ ወርቅ

፪) ዋሻ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖትና አብርሃ ወአፅብሃ ውቅር ቤተክርስቲያን

ልዩ ስም፦ የካ ክ/ከ አንቆርጫ ዋሻ ሚካኤል

፫) መሪ ደብረ ታቦር ቅዱስ ፋኑኤል ፣ አብርሃ ወአጽብሐ ወቅድስት በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን

ልዩ ስም፦ አያት መሪ (ከመሪ ባቡር መውረጃ ፊት ለፊት ባጃጅ ተራ አለ። ከዛ እስከ ቤተክርስቲያኑ የሚያደርስ ባጅጅ ያገኛሉ ።)

በዓለ ንግሱ ይከበራል።
[ልዑል እግዚአብሔር ]
በፍቅር፣ በሠላም፣ በጤና ያገናኘን
🙏አብርሃ ወአፅብሃ ይጠብቁን 🙏
    ₃..አሜን | Amen..₃ 🤲🙏
  ❤️🌼❤️🌼❤️🌼❤️🌼

🌺✞ የንግሥ በዓላት ✞🌺

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

08 Oct, 17:13


🌹 ብክዩ ኀዙናን ሃልየክሙ ስደታ ለማርያም 🌹

ትርጉሙም

🌹 አልቅሱ ሁላችሁም የማርያም ስደቷ አስባችሁ 🌹
      ሰቆቃው ድንግል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለእናታችን  ወድንግል ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት አው ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የመታሰቢያ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን

👉 መስከረም ፳፱(29) በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዘተጽፈ ወንጌል ወአርሴማ ቅድስት ወካልኣት አንስት 👉

🙏 ዘነግህ ምስባክ 🙏

ይትፌሥሓ አድባረ ጽዮን
ወይትሐሠያ አዋልደ ይሁዳ
በእንተ ፍትሕከ እግዚኦ

🙏 ትርጉም 🙏

አቤቱ ስለፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው
የአይሁድም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ

        መዝ ፵፯-፲፩
               47   11

🙏 ወንጌል 🙏

ማቴ ም ፳፭ ቁ ፩-፲፬
           25     1   14

የቅዳሴ ምንባባት

ገላትያ ም ፬ ቁ ፩-፲፪
፩ ዮሐ ም ፩ ቁ ፩-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፫ ቁ ፩-፲፪

❖  ምስባክ ❖

እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ
ወአነ ዮም ወለድኩከ
ሰአል እምኔየ እሁበከ አህዛብ ለርስትከ

✥ ትርጉም ✥

እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ
እኔ ዛሬ ወለድሁህ
ለምነኝ አህዛብ ለርስትህ

            መዝ ፪-፯
                   2   7

❖ ወንጌል ❖

ሉቃ ም ፳፩ ቁ ፳፩-ፍ.ም
           21     21  ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ ❖

ዘእግዚእነ(ነአኩተከ)

"አቤቱ አምላኬ በኪሩቤል የምትኖር በልዑላንም የምታርፍ ለአንተ እገዛለሁ፤ትሑታንን ታውቃለህ በብርሃን አለህና "
       ቅዳሴ እግዚእነ
            ም ፩ ቁ ፷፮
                1     66

ፆሙን ፆመ ፀጋ ፆመ ትሩፍት ታድርግልን በዓሉን በዓለ ፀጋ በዓለ ምህረት ያድርግልን ቸሩ መድኃኔዓለም በምህረቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅን ከስደቷ በረከት ይክፈልንበየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ከእናታችን ቅድስት አርሴማ ድንግል በረከቷ ይደርብን በቅዱሳን ፀሎት ይማረን ዘመኑ ዘመን ፍሬ ያድርግልን ማኅሌት ጽጌ ሰቆቃው ድንግል የተቀበለ አምላክ የኛንም ፆም ፀሎት ምሥጋና ይቀበልልን ለአባ ጽጌድንግል ለአባ ገብረማርያም ዘደብረ ሐንታ ለአባ ገብረኢየሱስ ዘደብረ መጓዬና ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለአባ አርክሥሉስ ለቅዱስ ያሬድ ማኀሌታዊ ለአባ መባአፅዮን ለአባ ስብሐት ለቅዱስ ቴዎድጦስ ዘእንቋራ ለቅዱስ ደቅስዮስ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት ለቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢ ለቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ለቅዱስ ጊጋር መስፍነ ሶርያዊ ለአፄ ናዖድ ለአፄ ዳዊት ለአፄ ዘርዓያዕቆብ ለአፄ ሚኒሊክ ለአፄ ልብነድንግል ለማር ገላውዴዎስ ለቅዱስ አብርሃ ወአጽብሃ ለቅዱሳን አንስት የተለመነች እመ አምላክ ድንግል ማርያም በቸርነት ትለመነን ቅድስት ቤተክርስቲያን በረከት ይጠብቅል በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ለቅዱስ ሥጋው ለክቡር ደሙ ያብቃን ነፍሳት ሙታን ይማርልን ሕያዋን ይጠብቅልን የእመቤታችን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሙን በአንደበታችን ታሳድርብን 

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

03 Oct, 17:36


ሁለቱ መነኮሳት
ሁለት መነኮሳት ከገዳሙ ወጥተው ወደ ከተማ ከአበምኔቱ ተልከው ወደ ከተማ ወጡ ፤፤
በከተማው ውስጥ ሳይመለሡ አንዱ መለኩሴ በሀጢያት ወደቀ ከዚያ በበነጋታው ስራቸውን ጨርሰው ወደ ገዳሙ እንመለስ ሲል አንኛው መነኩሴ ለሌላኛው መነኩሴ ነገረው
መነኩሴውም ወንድሜ እኔ በሀጢያት ወድቂያለሁ ወደዚያ ወደ ንፁሆች ደናግላን ካሉበት ገዳም ልመለስ አይገባኝም አኔ ከነሀጢያቴ እዚሁ ከተማ ውስጥ ነው የምቀረው ወደ ገዳሙ አንተ ተመለስ አለው
ጓደኛውም በውስጡ አዝኖ ጓደኛው ከእግዚአብሔር እርቆ አዳይቀር በማሰብ አኔም እኮ በሀጢያት ወድቂያለሁ አተ ብቻ አይደለህም አለው
ነገር ግን ሁለታችንም ወደ ገዳሙ ተመልሰን ንስሀ ገብተን ወደ ቀድሞው ቅድስናችን እንመለሳለን ብሎ ነገረው
በሀጢያት የወደቀው መነኩሴም አይ እኔ ብቻ የወደኩ መስሎኝ ነው እጅ ሁለታችንም ከሆንማ እንሂድ ተባብለው ወደ ገዳሙ ተመለሱ
ከዚያ ንስሀ ገብተው ለ7 ቀን ሱባኤ ገቡ ከዚያም በ7ኛው ቀን ያንን በሀጢያት ወድቂያለሁ ወደ ገዳሙ አልመለስም ላለው መለኩሴ እግዚአብሔርን በራእዩ ተገልጦለት
ስላንተ ሱባኤ ሳይሆን ስለ ወድምህ ላንተ ብሎ በሀጢያት ሳይወድቅ ሀጢያት ሰርቻለሁ ብሎ ንስሀ ስለአንተ ብሎ ሳይበድል ንስሀ ስለገባው ወንድምህ ብዬ ይቅር ብዬሀለው አለው
በጣም ግሩም ነው ሀጢያት ሳይሰራ ጓደኛው በከተማው በሀጢያት ወድቆ እንዳይቀር ለጓደኛው በማሰብ ሀጢያት ሳይሰራ ሰርቻለሁ ብሎ ያን ጓደኛውን ታደገው
የሚገርም ነው አሁን እኮ እንኳን ስለጓደኛችን ንስሀ ልገባ ቀርቶ እራሳችን ለሰራነው ሀጢያት ንስሀ ገብተናል ወይ
አሁን የምናየው ነገርስ የምሰማው ግጭቱ  እርስ በርስ ጦርነት ረሃብ መፈናቀል አየተቀጣን ያለነው ሀጢያታችን በጣም በዝቶ ማመንና ንስሀ መግባት አቅቶን አይደለም
ስለሀጢያታችን አየተቀጣን ነው
አስቲ በዓለም ላይ ያለውን ነገር እዩ እውነት የሚናገሩት እንደ ወጀለኛ ተቆጥረው
ሀሰት ለሚናገሩት ሰውች ትልቅ ቦታ ተሰጥቷቸው ነው የምናየው በጣም ያሳዝናል ይህን ዘመን አሳልፎን እኛም ንስሀ እድገባ ከሀጢያታችን እድንመለስ እግዚአብሔር ይርዳን አሜን

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2



    ♡ ㅤ  ⎙ㅤ     ⌲         ✉️   
   ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
                       ꧁  ይ🀄🀄ሉ ꧂

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

28 Sep, 06:36


ዝናብ ያላደበዘዘው አስደናቂው ስነስርዓት ምን አይነት ድንቅ እምነት አለን
ተዋሆዶ ተዋህዶ ምን ልበል ቃል አጣሁለት
መስቀል አደባባይ አቤት ውበት