Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል) @abumeryemneja Channel on Telegram

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

@abumeryemneja


ተውሒድና ሱና የአንድነት ምንጭ ሲሆኑ፣
ሺርክና ቢድዓ ደግሞ የልዩነት ምንጭ ናቸው።
ስለዚህ ተውሒድና ሱና አጥብቀህ ያዝ።
ሺርክና ቢድዓ ደግሞ በእጅጉ ራቅ።
አላህ ቁርኣንና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች መንገድ
አረዳድ ተረድተው ከሚጓዙ ምርጥ ባሮቹ
ያድርገን።

ቻናሉን ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።
ለስተያየትና ጥቆማ እንዲሁም እርምት
👉 @NejaLobete 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል) (Amharic)

ሠላም እና እንበለይ! አቡ መርየም ቻናል (Abu Meryem Channel) ከሆነ፣ ባቡቲሊን አየር (አርቲስት) የአንድነት ምንጭ ስለሆኑ ይህን ልዩነት መሰረታዊ መልእክት ለመጠቀም ይጠቀሙ። ቻናሉን ለሌሎች ሼር በማድረግ እና በስልክ ላይ ይጫኑ። እናመሰግናለን ከሚጓዙ ምርጥ ባሮች ጋር እንዲሁም ከበደሉ ይሁኑ። ለስተያየትና ጥቆማ እንዲሁም እርምት እባክዎን ይቀላቀሉ። እናመሰግናለን! 👉 @NejaLobete 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

21 Nov, 19:37


ጫት መቃም፣ ሲጋራ ማጨስና ሌሎችንም ጎጂ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም ኢስላም ከልክሏል።

የአሏህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው ነጭ ሽንኩርት የበላ መስጅዳችን አይምጣ ቤት ይቀመጥ ብለዋል።

ታዲያ ጫት የምቂሙና ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎችስ ምን ልባሉ ነው?

አስቡት መንገድ ላይ እንኳን አንድ ጫት ቃሚ ወይም ሲጋራ አጫሽ የሆነ ሰው አጠገባችሁ ሲያልፍ ሽታው ምን ያክል ያስቸግራል? አዛ ያደርጋል? በተለይ የሲጋራ ሽታ! ስለዚህ በዚህች ቅፀበት መንገድ ላይ እስከምትላለፉ ሽታው እንዲህ አስቸጋሪ ከሆነ፣ መስጅድ ውስጥ ሰላት አጠገብ ለአጠገብ ቆመህ እየሰገድክ አጠገብህ ያለው ሰው ጫት ቃሚ ወይም ሲጋራ አጫሽ ከሆነ ሰላት እስከሚያልቅ ምን ያህል ሽታው እንደሚረብሽና እንደሚያስቸግር አስበው።!

ስለዚህ ጫት የምትቂሙ ሲጋራ የምታጨሱ ሰዎች ሆይ መስጅድ ሰላት ለመስገድ ገብታችሁ በእነዚህ እርኩስ ነገሮች ሽታ ስንት ሰው አዛ እንደሚታደርጉና ቀልብ እንደሚትሰብሩ አስቡት።! ስለዚህ እነዚህን እርኩስ ነገሮችን መጠቀም አቁሙ! አላህ ያግዛችሁ።!

እንደው ሌላው ቢቀር ወደ መስጅድ ስትገቡ የአፍ መሸፈኛ ማክስ ተጠቀሙ።! አላህ እነዚህንና መሰል እርኩስ ነገሮች ከምድር ገፅታ ያጥፋልን።

🖌 ወንድማችሁ:- አቡ መርየም

የቴሌግራም ቻናል=

👉 http://t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

21 Nov, 12:03


ማንኛውም ነገር ጥሩም ሆነ መጥፎ በተደጋገመ ቁጥር ያለ ምንም ጥርጥር አዕምሮ ላይ የመቀረፅ ወይም ከፍተኛ ተፅህኖ የማሳደር አቅም አለው።

🖌 ወንድማችሁ:- አቡ መርየም

የቴሌግራም ቻናል=
👉  http://t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

21 Nov, 09:21


https://t.me/ustazahmedyusuf
👆  👆   👆  👆  👆  👆 👆 👆  👆

ይህ አለም ባንክ መስዓብ መስጅድ ከዙህር ሰላት በኋላ በሸይኽ አሕመድ ዩሱፍ የሚቀርብ የቁርኣን ተፍሲር ትምህርት ብቻ የሚለቀቅበት ቻናል ሲሆን ተፍሲሩ የሚሰጠው ከሰኞ እስከ ሐሙስ ነው። ቻናሉን ይቀላቀሉ።ሌሎችንም ይጋብዙ።! ባረከሏሁ ፊኩም!!

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

21 Nov, 04:40


አንድን ሰው ስትወደውም ስትጠላውም ምክንያት ይኑርህ። ውዴታህም ጥላቻህም ድንበር ያለፈ አይሁን። በልክ ይሁን።

ምክንያቱም አንድን ሰው ስትወደው ውዴታህ ድንበር ያለፈ ከሆነ ያ ሰው የፈለገ ነገር ቢሰራ ያ ነገር ሁሌም ላንተ ትክክል ይመስለሃል። ግልፅ የሆነ ጥፋት ብያጠፋ እንኳን ለዛ ነገር ሌላ ምክንያት ትፈልግለታለህ።

በተቃራኒው አንድን ሰው ስትጠላው ወይም ለዛ ሰው ያለህ ጥላቻ ድንበር ያለፈ ከሆነ ደግሞ ያ ሰው የፈለገ ትክክል የሆነ ነገር ቢሰራ እንኳን ላንተ ምንም አይመስልህም። ያንን ነገር ውድቅ የሚታደርግበትን መንገድ ትፈልግለታለህ። ነገሩ ትክክል መሆኑን ውስጥህ ከማወቁም ጋር ግን ያንን ነገር ለማስተባበል ብዙ ጥረት ታደርጋለህ። ይህ ምቀኝነትም ነው።

አንድን ሰው ስትወደውም ስትጠላውም ምክንያት ካለህ፣ ውዴታህም ሆነ ጥላቻህ በልክና ድንበር ያላለፈ ከሆነ ግን ያ ሰው መልካም ሲሰራም በሰራው ስራ ልክ
ትወደዋለህ። ስህተትም ሲሰራ በስህተቱ ልክ በጥፋቱ መጠን ትጠለዋለህ።

ስትወደውም ሆነ ስትጠላው ምክንያት ይኖረሃል። በልክ ትሆናለህ። ውዴታህም ሆነ ጥላቻህ ድንበር ያለፈ አይሆንም።


🖌ወንድማችሁ:- አቡ መርየም

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።
👉 t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

17 Nov, 10:59


ልጅህን አረብ ሀገር ያላከው ወላጅ ሆይ!
ሚስትህን አረብ ሀገር ያላከው ባል ሆይ!
እህትህን አረብ ሀገር ያላከው ወንድም ሆይ!
👇
እህቶች ከአምስት አመትና ከዛ በላይ ላባቸውን ጠብ አድርገው ለፍተው ብዙ መከራዎችን ተቋቁመው ችለው አሳልፈው ያገኙትን ገንዘብ በአልባሌና በሱስ ነገሮች ላይ የሚታባክኑ አባቶች፣ባሎች፣ወንድሞች፣እህቶች ሆይ አላህን ፍሩ! ጭራሽ ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎ ከአረብ ሀገር ከተመለሰችም በኋላ ምንም አይነት ውለታ እንዳልዋለችላችሁ  አድርጋችሁ የምታመናጭቁ፣የምትሳደቡ፣በአጠቃላይ ልብ የሚሰብር ቃላትን የምትጠቀሙ ሁሉ አላህን ፍሩ!!

  🖌 ወንድማችሁ አቡ መርየም

          የቴሌግራም ቻናል:-
  👉
t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

17 Nov, 10:56


👉 ጥብቅ ማሳሰቢያ!

በንፅፅር ዳዕዋ ለተሰማራችሁ ወንድሞች፣ዳዒዎች፣ኡስታዞች በሙሉ
እንደሚታወቀው በአሁን ሰዓት ፕሮቴስታንቶች/ጴንጤዎች የኢስላም መገለጫ የሆኑ ነገሮችን ተጠቅመው ከመስበክ አልፈው ቁርኣንና ሐዲስንም ከሚያሲዘው መልዕክት አጣመው እየተረጎሙ፣ቆርጠው እየቀጠሉ ሙስሊሞችን ከትክክለኛ መንገድ አውጥተው ጨለማ ወደ ሆነው ክህደት ለማስገባት ብዙ በመጣር ላይ ናቸውና ለሚያነሷቸው ማምታቻዎች በሙሉ በቁርኣንና ሐዲስ መሰረት ምላሽ ልትሰጧቸው ይገባል።

ምክንያቱም በአሁን ሰዓት አብዛኛው ማህበረሰብ ከህፃን እስከ አዋቂ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ላይ ስለሆነ እነዚህ የሚያነሷቸው ማምታቻዎች ሁሉምጋ በቀላሉ የመድረስ እድል ይኖራቸዋልና ምን አልባት አንዳንዶች ብዥታ ልወድቅባቸው ስለሚችል ይህ ጉዳይ በደንብ ይታሰብበት ባይ ነኝ።

🖌ወንድማችሁ:- አቡ መርየም

ይህ መልዕክት ሁሉም ጋ እንዲደርስ አደራችሁን ሼር እናድርገው!

የቴሌግራም ቻናል:-
👉
t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

16 Nov, 18:35


👉በአሁን ሰዓት ላሉብን ችግሮቻችን መፍትሔ ያላገኘነው !!!

ስለ መልካም ነገር ሲወራ ምንም ባልሰራንበት እንዲሁ ራሳችንን እዛ ቦታ ላይ እናስቀምጣለን።

በተቃራኒው ደግሞ ስለ መጥፎ ነገር ሲወራ ቆም ብለን በራሳችን ላይ ያሉብን ችግሮቻችንን ለማስተካከል ከመሞከር ይልቅ ያንን መጥፎ ነገር በሆኑ ሰዎች ላይ ለማድረግ ጣታችንን እንቀስራለን። በአዕምሯችን የሆኑ ሰዎችን ማሳብ እንጀምራለን።

እስቲ ሁላችንም ራሳችንን እንፈትሽ ይህ ችግር የለብንም?!


ወንድማችሁ አቡ መርየም

👉 http://t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

16 Nov, 18:07


አንዳንድ ሰው መልካም ስራህን ምንም እንዳልሰራሀው አድርጎ ለመደበቅ ይሞክራል።

በተቃራኒው ደግሞ መጥፎ ስራ ሲሆን አይደለም ተሳስተህ ሰርተህ ሳትሰራ እንኳን ሰርተሃል ብሎ ይቀጥፍብሃል። ተሳስተህ እንኳን የሆነ ጥፋት ላይ ብትወድቅ ያንን ስህተትህን ግን ለሁሉም ያሰራጨዋል።

በአጭሩ ምን  ለማለት ፈልጌ ነው ሰው ከመልካም ጎንህ የበለጠ መጥፎ ጎንህን ብቻ ይከታተላል። ሁሉም ማለት ግን አይደለም።

🖌ወንድማችሁ አቡ መርየም


👉
t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

12 Nov, 09:24


የኡስታዞችን ደዕዋ፣ትምህርቶቻቸውን፣የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻቸውን ማለትም የቴሌግራም ቻናሎችን፣የዋቲሳፕ ግሩፖችን፣የፌስቡክ አካውንቶችን፣የዩትዩብ አካውንቶችንና ሌሎችንም የኡስታዞች ትምህርቶች የሚተላለፉባቸውን የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን ህዝቡ ዘንድ እንዲደርሱ በማስተዋወቅ፣ኣድ በማድረግ፣ሼር በማድረግ እና ለመስጂዶች ግንባታና ማስፋፍያ፣ለመድረሳ፣ ለታመሙ ሰዎች ለህክምናና ለመሳሰሉት የእርዳታ ጥሪ በሚደረግ ጊዜ ቀድመው የሚሰለፉት እህቶቻችን ናቸው ።በተለይ በተለይ ዐረብ ሀገር ያሉ እህቶቻችን በጣም በጣም ትልቅ አስተዋፅኦና አሻራ አላቸው። ትልቅ ባለ ውለታዎቻችን ናቸው። ሀገር ውስጥ ያሉትንም ውጭ ሀገር ያሉትንም አላህ ይጠብቃቸው። አላህ የዱኒያም የአኼራም ሓጃቸውን ገር ያድርግላቸው። ያሳቡትን ሁሉ ያሳካላቸው። ውጭ ሀገር ያሉትንም በሰላም ወደ ሀገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ይመልሳቸው። አላህ ይጨምርላችሁ። በዚህ ቀጥሉ!

🖌ወንድማችሁ አቡ መርየም

👉
t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

11 Nov, 18:33


አጭር ቀሚስ መልበስ 50 ሺህ ብር ያስቀጣል!

የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ የሚያሰራ ምግብ ቤት እና ሆቴል የ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ ረቂቅ ደንብ አፅድቋል::

ጎሽ! ትምህርት ቤቶቻችንና ትምህርት ሚኒስቴርም ከባህልና ቱሪዝም ቢሮው ጥቂት ቢማር ጥሩ ነው!

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

11 Nov, 17:59


ትልቅ ወንጀል ነው ተጠንቀቁ



🥀 ከአብደላህ እብን አምር ብን አልዓስ
ተይዞ ረሱል ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም
እንዲህ ብሏሉ👇

" የወንጀሎች ታላቅ ብሎ ማለት ሰውዬው ወላጆቹን መሳደቡ ነው ። አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ሰው ወላጆቹን ይሳደባልን? ኣዎ እሱ የሌላ ሰው አባትን ይሳደብና አባቱን ያሰድባል። የሌላ ሰው እናት ይሰድብና እናቱን ያሰድባል።"


📚ቡኻሪ 5973 ሙስሊም 90
ዘግበውታል


🗻 ነቃ እንበል በተለይ በአሁኑ ጊዜ ይህ
ወንጀል ወጣቱ ዘንድ በብዛት
ተንሰራፍቶ ይታያል ። እንደ ቀልድ
እናትህ እንዲህ ትሁን አባትህ እንዲህ
ይሁን ይባባላሉ። ስለዚህ ከሐዲሱ
እንደምንረዳው የሰውን ወላጅ
በሰደብነ ቁጥር የራሳችን ወላጅ
እየሰደብነ መሆኑንና ትልቅ ወንጀል
እየተዳፈርን መሆኑን አንዘንጋ።

🥀ይህን መልዕክት እኛ ጋር እንዳይቀር
ለተለያዩ ወዳጆቻችን በማስተላለፍ
የአጅሩ ተካፋይ እንሁን።


🥀 የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ ኢስላማዊ
እውቀቶችን ለማግኘት ከስር ያለውን
ሊንክ በመንካት ቻናሉን ጆይን ብለው
ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇https://t.me/+ZZzCjxcbaso3YzM0

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

06 Nov, 11:32


ሰው በሰው እንዲህ ተጨካከነ!

ምንድነው በየ ቀኑ እዚህ ቦታ እንትና የተባለች ልጅ በአሰቃቂ በጩቤ ተወግታ ተገደለች ሲባል መስማት ከጀመርን ሰነባብቷል።! በተለይ እንዲህ አይነት ግፍ ሴቶች ላይ ሲሆን ደግሞ በጣም ያሳዝናል!!

ግን እዚህ ሀገር መንግስት የለም እንዴ?!

ምን አለበት ሰውን በአሰቃቂ ጨፍጭፎ የገደለን እስር ቤት አስገብቶ ከመቀለብ ለሌላውም ትምህርት እንዲሆን እንደገደለ ቢገደል?! መቼም ትምህርት ይሆነዋል።ይማርበታል።ለሌላውም ትምህርት ይሆናል በሚል ነው እስር የሚወሰንበት። ግን እስከዛሬ አየነው ምንም ትምህርት የሆነ ነገር የለም። እንደሁም መገዳደሉ ብሷል። ታዲያ ምንድነው መፍትሔው? መፍትሔው የገደለ ይገደል። የሚለው ህግ ተግባራዊ ማድረግ ብቻና ብቻ ነው። ያኔ ሙሉ በሙሉ ማቆም ባይቻልም በጣም መቀነስ ግን ይቻላልና መንግስት ሆይ! በየ ቀኑ እንደ ዛፍ ቅጠል የሚረግፈው ህዝብ ያሳዝንህ!


ወንድም አቡ መርየም

http://t.me/AbuMeryemNeja

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

06 Nov, 07:05


👉ሸሪዓዊ አለባበስ!!

ሸሪዓው ወንዶች ልብሳቸውን ሱሪያቸውን፣ጀለብያቸውን፣ሽርጣቸውን ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ ታዘዋል።

ሴቶች ደግሞ መላ ሰውነታቸውን በሒጃብ እንዲሸፍኑ፣ ስስ ያልሆነ የሰውነታቸውን ቅርፅ የማያሳይ፣ የሆነና ከቁርጭምጭሚት በታች አንድ ስንዝር ለቀቅ አድርገው እንዲለብሱ ታዘዋል።

የሚገርመው በአሁን ሰዓት አንዳንዶች ዘንድ ነገሩ በተቃራኒ ሆኗል።

ወንዶች ልብሳቸውን አሳጥረው ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው እንዲለብሱ ታዘው ሳለ እንደ ሴቶች ካለበስን መሬት እየጎተትን መሬት ካልጠረግን አሉ።

ሴቶች ደግሞ በተቃራኒው ከቁርጭምጭሚት ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ የታዘዙት እነሱ ይመስል ከቁርጭምጭሚት ከፍ አድርገው ያውም ስስ የሆነ ያውም በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ የሰውነታቸውን ቅርፅ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ካለበስን አሉ።

በጣም የሚገርመው ከወንዶችም ከሴቶች ወደ ሰላት ሲገቡ ወንዱም ሱሪውን ወደ ላይ ያጥፈዋል።ሴቷም የለበሰችውን ቀሚሷን ወደ ታች ዝቅ ለማድረግ ትሞክራለች።

ስለዚህ ሸሪዓው ያዘዘውን አለባበስ ምን አይነት አለባበስ እንደሆነ ያውቃሉ ማለት ነው። ሸሪዓው ወንዶችን ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ የታዘዙት በሰላት ብቻ አይደለም። በየትኛውም ሁኔታ ነው። ሴቷም እንዲሁ በሰላት ብቻ አይደለም መላ ሰውነቷን እንድትሸፍን የታዘዘችው። ይህን ያልኩት ከላይ እንዳልኳችሁ ወንዱም ልክ ወደ ሰላት ሊገባ ሲል ሱሪውን ወደ ላይ ለማጠፍ ሲሞክር ታየዋለህ። ሴቷም ልብሷን ወደ ታች ዝቅ ለማድረግ ትሞክራለች።


ወንድሜ ሆይ! ሱሪህን፣ጀለብያህን፣ሽርጥህን ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገህ አሳጥረህ ልበስ። አርኣያዎችህ እነ አቡበክር፣እነ ዑመር፣እነ ዑስማን፣እነ ዐሊይና የመሳሰሉት ናቸው። ዑመር በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሊዘይሩት ከመጡ ሰዎች መካከል አንድ ወጣት ሱሪውን ሲጎትት ተመለከተው አስጠርቶ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ምንድነው ያለው አንተ ልጅ ሆይ ልብስህን ከፍ አድርገህ ልበስ። ይህ ለልብስህ ንፅህና የተሻለ ነው። ጌታህንም ለመፍራት የቀረበ ነው ብሎ ነው የመከረው። ዑመር በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ይህን ማለቱ ጉዳዩ በጣም ከባድ መሆኑን ነው የሚያሳየው።

እህቴ ሆይ! አንቺም አርኣያዎችሽ እነ ዓኢሻ፣እነ ኸዲጃ፣እነ ሱመያ፣እነ ሐፍሳና የመሳሰሉት ናቸው። እነሱን ተከተይ።
በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ያቺ አዙሮ የምጥል በሽታ የነበረባትን ሴት ተመልከቺ። በሽታው በጣም ያሰቃያት ነበርና በሽታው አዙሮ ሲጥላት ሰውነቷ ይገላለጣል።ይህቺ ሴት ለነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምንድነው ያለችው እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝ። በምወድቅበት ሰዓት ሰውነቴ ይገለጣል። ምን ላድርግ ብላ ስትጠይቃቸው የአላህ መልዕክተኛ ምንድነው ያሏት ከፈለግሽ አላህ ይህን በሽታ እንዲያነሳልሽ ዱዓ አደርግልሻለሁ። ከፈለግሽ ሰብር አድርጊ ጀነት አለልሽ አሏት። የሷ ምላሽ ምን ነበር ሰብር አደርጋለሁ። በሽታው በሚጥለኝ ሰዓት ሰውነቴ እንዳይገላለጥ ዱዓ አድርጉልኝ ነበር። ታዲያ አንቺና ይህቺ በበሽታ ምክንያት ራሷን ስታ በምትወድቅበት ሰውነቷ ለሚገላለጠው የሚትጨነቅ ሴት የትና የት ናችሁ?


🖌ወንድማችሁ አቡ መርየም

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።
👉 t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

05 Nov, 19:06


የ CMC አህባሾችና የተብሊጎች መርከዝ
ሙሓደራው በድምፅ ማስረጃ የተደገፈ ነው፡፡
1) የላኢላሃ ኢለላህን ትርጉም ማዛባት፣
2) ኢስላም ላይ መዋሸት፣
3) ውሸታም ሰዎችን ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
4) በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሙስሊም እራሱን፣ ቤተሰቡን እና መላው ሙስሊም ማህበረሰብን ከ CMC መርከዝ ያርቅ፡፡
ማስረጃውን በጥሞና እናዳምጥ፣ ከዛም በነዚህ ሰዎች ለሚታለሉ ሰዎች እናሰራጨው፡፡
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

05 Nov, 04:12


ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ያለ ክፍተት!

ጴንጤዎች ሙስሊሞችን በተለያዩ መንገዶች ከኢስልምና አስወጥተው ወደ ክህደት ለማስገባት የማይሰሩት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ይሰብካሉ። ከእነዚህም መካከል በዘይት፣በዱቄት፣የቤት ኪራይ በመክፈልና በመሳሰሉት ምንም ሳይሰለቹ ይጣራሉ።ይህን ሰበካቸውን እሺ ብሎ የተቀበለውን አካል ሌላም እርዳታ ያደርጉለታል።ምክንያቱም ወደ ኢስላም እንዳይመለስ በሚል ብዙ ነገሮችን ይሰጣሉ። እነሱ ለዚህ ለክህደት መንገዳቸው ሳይደክሙ ሳይሰለቹ ጧትና ማታ የትም ቦታ ይታገላሉ። ሰሞኑን ደግሞ ወደ ስልጤ ማህበረሰብ ሰበካቸው ምንም ለውጥ ሳያመጣ ሲቀር ነው መሰለኝ መፅሓፍ ቅዱሳቸውን ከአመርኛ ወደ ስልጥኛ በመተርጎሙ የስልጤን ህዝብ መስበክ ጀምረዋል። ኢንሻ አላህ አይሳካላችሁም!


ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ያለው ክፍተት ምንድነው እነሱ አስቡት በየ ቦታው በስራ ቦታ፣በአደባባይ፣በመንግስት ተቋማት ሳይቀር ይስብካሉ። ሙስሊሙ ጋ ስትመጣ ደግሞ ኢስላም ሐቅና ትክክለኛ ሃይማኖት መሆኑን በራሳቸው ጥናት አድረገው ወደ ኢስላም የመጡትንም ሆነ በንፅፅር ዳዕዋ በሚንቀሳቀሱ ኡስታዞችም አማካኝነት አላህ ሂዳያ ሰጥቷቸው ወደ ኢስላም የሚገቡትን በመንከባከብ አብሽሩ በማለት የሚያስፈልጋቸውን ነገር በማሟላት ትንሽ ክፍተት እየታየብን ነው። ምክንያቱም እነዚህን ወደ ኢስላም የመጡትን ሰዎች በደንብ ተንከባክበንና አብሽሩ ብለን ችግራቸውንም ተካፍለን ለችግራቸው መፍትሄ የማንሰጥ ከሆነ እነዚህ ሰዎች ወደ ኢስላም በመግባታቸው ብቻ በቤተሰቦቻቸውና በጓደኞቻቸው ከፍተኛ ጫናዎች ይበዛሉ። ወደ ቀድሞው የክህደት እምነት እንዲመለሱ የማያደርጉት ነገር የለምና። እስከ ግድያ ሁሉ ሊደርስባቸው ይችላል። ስለዚህ እንዲህ አይነት ሰዎችን ካላገዝናቸውና ለችግራቸው መፍትሄ የማንፈልግላቸው ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም እነዛ ቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው የሆነ ነገር ላይ ተቸግረው በሚመለከቱበት ጊዜ ምን ይሏቸዋል መጀመሪያ የነበራቹበትን እምነታችሁን ትታችሁ ባትሄዱ ይህ ችግር አይደርስባችሁም ነበር አሁንም ኑ ተመለሱ ብለው ዳግም ወደ ክህደት ልያስገቧቸው ይችላሉና ይህ ጉዳይ በንብ ይታሰብበት ባይ ነኝ።


✒️ከወንድማችሁ አቡ መርየም

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ። ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!

👉
t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

03 Nov, 10:23


ለፈገግታ!!

👉ራሳችንንም እንፈትሽበት!

አንድ ሰውዬ ነበር አራት ሱቅ ያለዉ ከዛ በጀመዓ ሰላት እየሰገደ ኢማሙ ተሳስተዉ 3 ረከዓ ብቻ ሰግደው አሰላመቱ።እና ሰውየው ጮክ ብሎ ሱብሓሏህ! ብሎ እንደተሳሳቱ ነገራቸው። ከዛ ሰላት ተሰግዶ ካበቃ በኋላ ኢማሙ ሰውየውን በጣም ጎበዝ ነህ አላህን እየፈራህ ሀሳብህን ስብስብ አርገህ ነው የምትሰግደዉ ማሻአላህ!

እንዴትስ እንደተሳሳትኩ አወቅክ ብለዉ በመገረም ሲጠይቁት


ሰውየው እንዲህ አላቸው '' እኔ አራት ሱቅ አለኝ። በእያንዳንዱ ረከዓ አንዳንድ ሱቆቼን ሂሳብ እያረኩ እጨርሳለሁ እና አንድ ሱቅ ሂሳብ ሳላደርግ ስላሰላመቱ ነው ያወቅኩት'' ብሏቸዉ እርፍ!

         
منقول
ይህ ጉዳይ አብዛኞቻችን የተፈተንበት ነገር ነው። አላህ ያዘነለት ሲቀር! አላህ በሰላት ቀልባችንን ይሰብስበው።
ኣሚን።


t.me/AbuMeryemNeja

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

03 Nov, 09:51


https://t.me/ustazahmedyusuf
👆 👆 👆 👆 👆 👆 👆 👆 👆

ይህ አለም ባንክ መስዓብ መስጅድ ከዙህር ሰላት በኋላ በሸይኽ አሕመድ ዩሱፍ የሚቀርብ የቁርኣን ተፍሲር ትምህርት ብቻ የሚለቀቅበት ቻናል ሲሆን ተፍሲሩ የሚሰጠው ከሰኞ እስከ ሐሙስ ነው። ቻናሉን ይቀላቀሉ።ሌሎችንም ይጋብዙ።! ባረከሏሁ ፊኩም!!

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

02 Nov, 20:01


👉 ትንሽ ጥቆማ ለመጅሊስ!!

እንደሚታወቀው ያለንበት ዘመን የፈተና አይነት የበዛበት ዘመን ነው። የኢስላም ጠላቶች በኢስላም ላይ በተለያዩ መንገዶች ጦርነት ከፍተዋል።

በመስጃዶች፣በትምህርት ቤቶች በሙስሊም ተማሪዎቻችን ላይ በኒቃብ፣ በጅልባብ እና በሰላት ትምህርትን ሽፋን አድርገው ኢስላምን ለማጥፋት ብዙ እየሰሩ ነው።

ስለዚህ መጅሊስ በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ ለሚደርሱ ትንኮሳዎች ተገቢና አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል።

በኒቃብ፣በጅልባብ እና በሰላት ጉዳይም ሌሎች ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖቻችን ተገላልጠው ሊማሩ መብታቸው እንደተጠበቀ ሙስሊም ሴት እህቶቻችን በኒቃብ፣በጅልባብ እንድማሩ መብታቸው
ሊጠበቅ ይገባል ማለት አለበት።

ሰሞኑን ካሚል ሸምሱ ስለ ኒቃብና ስለ ሲሕር አስመልክቶ የተናገረው ንግግር ጊዜና ቦታ ያልጠበቀ ንግግር ስለሆነ ስለዚህም ጉዳይ መጅሊስ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል። ትምህርት ቤቶች ትምህርትን ሽፋን በማድረግ ሙስሊም እህትቻችን በኒቃብ በጅልባብ እንዳይማሩ
እየተደረገ ባለበት ወቅት ሰሞኑን ካሚል ሸምሱ የተናገረው ንግግር ጊዜና ቦታ እንዲሁም ተጨባጩን ያላገናዘበ ነውና ካሚል ሸምሱ እርምት እንዲሰጥበት ማድረግ አለበት።

ሌላው በየቦታው ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ይከሰታሉ። ለምሳሌ ቅርብ ጊዜ በደቡብ ክልል በስልጢ ዞን በቅበት ከተማ የተከሰተውን ማንሳት ይቻላል። እንደዚህና መሰል ግጭቶች ሲከሰቱ ቶሎ ብሎ ወደ ቦታው በመሄድ ያለውን ነገር በተገቢ መልኩ ተከታትሎ መረጃውን ለህዝበ-ሙስሊሙ ማሳወቅ ይጠበቅበታል። በቅበት ከተማ በተከሰተው ጉዳይ ራሳቸው ሙስሊሙን ረብሸው ረበሹን ቤተ- ክርስቲያናችን ተቃጠለብን፣የተገደለው ሙስሊሙ ሆኖ ሳለ ተገደልን ብለው መረጃ ሳያጣሩ ያለውንም የሌለውን ጨማምረው ፈጥነው መግለጫ ሲሰጡ አይተናል። እውነት ለመናገር መጅሊሱ ግን ትንሽ ዘግይቷል።
ይህ መሆን የለበትም። ያለፈው አልፏል። ከአሁን በኋላ ላለው ግን መጅሊስ ነገራቶችን በደንብ እየተከታተለና ለሚከሰቱ ጉዳዮች መሄድ ባለበት መንገድ እየሄደ የደረሰበትንም መፍትሄ ለህዝበ-ሙስሊሙ ማሳወቅ ይኖርበታል ለማለት ያክል ነው።

በድጋሚ የተለጠፈ

    ወንድማችሁ፦ አቡ መርየም

    👉  
t.me/AbuMeryemNeja 👈

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

01 Nov, 06:08


ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
➠➻➠➻➠➻➠➻➠➧
↩️‏ #سنن_يوم_الجمعة

➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد
      
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ


👉 t.me/AbuMeryemNeja

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

01 Nov, 04:19


አንተ " በቃ አለቀልኝ! መጨረሻዬ ነው! " ብለህ ልታስብ ትችላለህ።
አላህ ግን ባላሰብከው መንገድ ሁሉንም ነገር ያስተካክልልሀል።

ታገስ…!

https://t.me/ibnunekir

3,035

subscribers

219

photos

42

videos