የእግዚአብሔር ክብር @gnjuf Channel on Telegram

የእግዚአብሔር ክብር

@gnjuf


The Glory of GOD

የእግዚአብሔር ክብር (Amharic)

ለአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ለሚከተሉት በቅኝ ሀላፊነት እና ሰላም ለየተለያዩ ሰዎች፣ 'የእግዚአብሔር ክብር' አማርኛ እና እንስሶችን አካባቢ መጠቀም እንዴት ነው። ይህ ታሪክ ከቤተ ክርስቲያን ህዝብ ጋር አዲስ አበባውን ከጠንካራ ድምፅ ውስጥ የምንደሰት ሀሳቦችና እናድርግቤት ልዩ ታሪክ እንዳለው አስተያየትና ሰማያዊ እርምጃ ነበር። በዚህ እንግዳ ታሪክ፣ አዲስ አበባውን አመሰግናለን እና በእግዚአብሔር እንመለከታለን!

የእግዚአብሔር ክብር

05 Nov, 18:45


🚨ሞት ሞት ከሸተተን በሁዋላ !

🚨ኢዮብ 2:8-9
8 ኢዮብም ገላውን ለማከክ ገል ወሰደ፤ በዐመድም ላይ ተቀመጠ።
9 ሚስቱም፣ “አሁንም ታማኝነትህን አልተውህምን? ይልቁን እግዚአብሔርን ርገምና ሙት!” አለችው።


🚨“እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፤ አሥራ አራት ሺህም በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩት።”
  — ኢዮብ 42፥12

አሜን ለሚል ይሁንለት

የእግዚአብሔር ክብር

03 Nov, 05:11


አንዳንድ ችግሮችን ሮጠህ አታመልጥም ከእግዚአብሔር ጋር ተቀምጠህ እንጂ! የእግዚአብሔር አብሮነት ደግሞ ያለው በእርሱ ፈቃድ ውስጥ ብቻ ነው!

የእርሱ ተኛ ከቆመ ይበልጣል! የእርሱ ተቀመጥ ከሮጠ ይቀድማል! ወዳጆች የእርሱ አብሮነት የችግሮች ሁሉ መፍትሄ እና በረከት ነው! ለገጠማችሁ ችግር መፍትሄ ለማግኘት ብቻ አትድከሙ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ውስጥ አብሮነቱን ፈልጉ!

ችግሮቻችሁን አልፋችሁ #ስትስቁ አያለው! አሜን!

የእግዚአብሔር ክብር

27 Oct, 19:37


በማእበል ዉስጥ ሰላም ከተሰማቹ
አትጠራጠሩ አሸናፊነቱ የናንተዉ ነዉ።😊
🥰

የእግዚአብሔር ክብር

16 Oct, 19:37


ዘዳግም 33
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።
²⁷ መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።
²⁸ እስራኤልም ተማምኖ፥ የያዕቆብም ምንጭ ብቻውን፥ እህልና የወይን ጠጅ ባለባት ምድር ይኖራል፤ ሰማያቱም ጠልን ያንጠባጥባሉ።
²⁹ እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።

የእግዚአብሔር ክብር

13 Oct, 06:56


ባዶ በቀረንበት ሰፈር ላይ ምንጭ ይፈልቃል
“ምስጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የፈጠርሁት ሕዝብ፥ የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን በበረሀም ወንዞችን ሰጥቻለሁና የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል።”
  — ኢሳይያስ 43÷20-21

የእግዚአብሔር ክብር

05 Oct, 15:58


🔴እግዚአብሔር  ህልም  የሚፈጽምበት መንገድ አለው
🔴ዘፍጥረት 41:14
14 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትእዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጕሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ።

የእግዚአብሔር ክብር

27 Sep, 20:14


እኛ እንጨርስ!!!!!!!!!!!!!!!
በሕይወታችን የእግዚአብሔር እጅ ሲሰራ ማየት ከፈለግን እኛ እንጨርስ በሕይወታችን ብዙ ማክረን ያልተሳካ ነገር አለ በቃ እኛ እንጨርስ እኛ ስንጨርስ አምላክ መስራት ይጀምራል
የኛን የእውቀት የኛን የፀሎት የኛን የገንዘብ የኛ የምንለውን ወይም  የተደገፍንበትን ነገር እንጨርስ የዛኔ የእግዚአብሔር እጅ በሕይወታችን ይሰራል
“እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።”
  — ዘዳግም 32፥12
ኢሳይያስ 10:23
23 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ያለቀ የተቈረጠ ነገርን በምድር ሁሉ መካከል ይፈጽማል።

እኛ ስንጨርስ እግዚአብሔር ለስራ ይመቸዋል
ነገሮች እንዲፈጥኑ የእኛን አቅም እንጨርስ
እንዲህ ልባርካችሁ እግዚአብሔር በናንተ የትኛውም ነገር መስራት ይጀምር

የእግዚአብሔር ክብር

23 Sep, 18:51


አስቴር 8፥16
      #እንድታሳካ
       #እንደተከናወነ
       #እንዲበረታን
       #እንደፈለጉት_እንዳልሆነ
#እንዲሆንልህ_በሰሙ_ገዜ_በጠላቶችህ_መንደር_መፍራት_ይወደቀባችዋል
¹⁶ ለአይሁድም ብርሃንና ደስታ ተድላና ክብርም ሆነ።
¹⁷ የንጉሡም ትእዛዝና አዋጅ በደረሰበት አገርና ከተማ ሁሉ ለአይሁድ ደስታና ተድላ፥ የግብዣም ቀን መልካምም ቀን ሆነ። አይሁድንም መፍራት ስለ ወደቀባቸው ከምድር አሕዛብ ብዙ ሰዎች አይሁድ ሆኑ።
            #አሜን_በለው_ለተቀበሉት_ሁሉ_የሆነላቸው
      #በእየሱስ ስም

የእግዚአብሔር ክብር

10 Sep, 18:27


በዚህ አመት የመለካት ጣልቃ ገብነት ይሆናል

በአገልግሎት
በስራ
በትዳር
በሀገር ጉዳይ
በየትኛውም ነገር ላይ የመለካት ጣልቃ ገብነት ይሆናል

ዳንኤል 3:24-25
24 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ናቡከደነፆር በአድናቆት ከተቀመጠበት ዘልሎ በመነሣት አማካሪዎቹን “አስረን በእሳት ውስጥ የጣልናቸው ሰዎች ሦስት አልነበሩምን?” ሲል ጠየቀ።
እነርሱም፣ “ንጉሥ ሆይ፤ እውነት ነው” አሉ።
25 እርሱም፣ “እነሆ፤ ያልታሰሩና ያልተጐዱ አራት ሰዎች በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ አያለሁ፤ አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል” አላቸው።


መልካም አዲስ አመት

የእግዚአብሔር ክብር

02 Sep, 20:11


#ጠላትህ_መከበርን_ያውቃል
“ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ፦ እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፥ ከሕዝቤ መካከል ውጡ ሂዱም፥ እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አገልግሉ”
— ዘጸአት 12፥31

የእግዚአብሔር ክብር

13 Aug, 20:57


አመሰግናለሁ

  2016 እያለቀ ነው በዚህ አመት በተለያየ ሁኔታ በአገልግሎት አብራችሁኝ ለነበራችሁ ስደክም ያበረታችሁኝ  ከጎኔ የቆማችሁ  ፊታችሁ ያልጠቆረብኝ  መልካምነትን ያሳያችሁኝ በሙሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ  ።ደግሞ በዘህ አመት ይሁዳ  የሆናችሁ በሙሉ  እኔን ወደ እግዚአብሔር አስጠጋችሁኝ አመሰግናለሁ  ነገር ግን  የይሁዳ መጥፊያ ከባድ ነው መንገዳችሁን አስተካክሉ
መልካም ያደረጋችሁሉኝ እንዲሁም ክፉ የዳረጋችሁብኝ ሁሉ አመሰግናለሁ !!!

የእግዚአብሔር ክብር

27 Jul, 19:46


ታሳ  ታ አዬ ናቶ

እግዚአብሔር አምላክ መጽናናትን  ይስጣችሁ
ራእይ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፦

የእግዚአብሔር ክብር

23 Jul, 19:24


🛑ከምስክርነት እና ከፀሎት መልስ ጋ እንገናኛለን🔥
    1ኛ ሳሙኤል 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ እርስዋም አለች፦ ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ጌታ ሆይ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ በዚህ በአንተ ዘንድ ቆማ የነበረች ሴት እኔ ነኝ።
²⁷ ስለዚህ ሕፃን ጸለይሁ፤
²⁸ እግዚአብሔርም የለመንሁትን ልመናዬን ሰጥቶኛል፤ እኔም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።

የእግዚአብሔር ክብር

10 Jul, 20:02


ግን ለምን  እግዚአብሔር 
አሁን ያለሁበት ሕይወት ማለፊያ አድርገው
አዲስ ቀን አዲስ ማለዳ አዲስ ሕይወት አዲስ ጋዳና ስጠኝ

የእግዚአብሔር ክብር

30 Jun, 21:10


ጠላት የዋጠውን በዚህ ሳምንት እግዚአብሔር ያስተፋላችሁ።

“በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም፥ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።”
— ኤርምያስ 51፥44