መንፈሳዊ ትረካ ብቻ @menefesawitereka Channel on Telegram

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

@menefesawitereka


እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነምህረት ስላለኝ ነው ምክንያት..........
መልቀቅ የምትፈልጉት ነገር ካለ @Ermiyas3 ላይ ወይም ደግሞ @Enate_mariyam3 ላይ አናግሩኝ #Ermiyas

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ (Amharic)

ምልሽ ኪዳነምህረት የሚባሉትን አስተመስተኞችን እናቴ ሆይ መልቀቅ የምትፈልጉት ነገር። አዲስ ነገርን አስተመስተኞችን ለመስራት እናቴ ሆይ ያልተገኙትን ዝርዝሮችን ለመስቀል እናቴ ሆይ የምትለዋን በመሆኑ በየቀኑ እናቴ ሆይ ይጠናቀነናል። በተጨማሪም @Ermiyas3 እና @Enate_mariyam3 ቢሆኑ የዚህ ይመልከቱ። #Ermiyas

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

12 Mar, 19:00


ይሄ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ለኦርቶዶክሳውያን የግድ ያስፈልጋል እባክዎ ከታች በመረጡት ይቀላቀሉ

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

31 Dec, 17:30


selam endet ameshachu wed yemenefesawi tereka abalatoch bemulu chanalachen endeketel fekadegna nachu demetsachu awon kehone be @Ermiyas3 lay yes belachu lakulen enamesegenalen

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

23 Apr, 14:49


#ሚስት_አጣሁ🤔

꧁ ❝ ውድ አንባቢያን 2 ደቂቃ እንዋሶትና  ይህንን አስተማሪ ታሪክ ላካፍላችሁ ።

አንድ ወጣት ሚስት ማግባት ፈለገ። በዙሪያውም ብዙ ቆነጃጂት ሞልተዋል።ወጣቱ ግን ለአይኑ እምትሞላ ፣ ለትዳሩ የምትበጅ ፣ ሙሉ የሆነች ቆንጆ ና ውብ ሴት የሚላት የትኛዋ እንደሆነች መምረጥ ተቸገረ። ሴት በሞላበት ሀገር ሚስት ፍለጋ ቢናውዝም ይችን ላግባ ብሎ መምረጥ እና መወሰን ተሳነው። ብቻ ቢፈልግም ቢያስፈልግም ሚስት አጣ።
...
ከዕለታት አንድ ቀን ምን ይሻላል ብሎ ሰው ሲያማክር እራቅ ወዳለ ሀገር አንድ ጠቢብ ሰው ስላሉ እሳቸው ጋር ቢሄድ አንዳች መፍትሄ እንደሚያገኝ ነገሩትና እርሱም ወደዛ አሉ ወደተባሉ ጠቢብ ሽማግሌ ዘንድ ይሄዳል። ጠቢቡ ዘንድም ደርሶ የበቆሎ ማሳ ቁጭ ብለው ሲጠብቁ አገኛቸው።
...
ሚስት ያጣው ወጣትም ከማሳው ዳር ካለው የእርሻው ዲብ ላይ ጺማቸውን አንጀርግገው በግርማ ሞገስ ቁጭ ብለው የበቆሎ ማሳ ወደሚጠብቁት ጥበበኛ ሽማግሌ ጠጋ አለና እንደምን ዋሉ አባቴ አላቸው።እርሳቸውም እግዚያብሔር ይመስገን እንደምን ዋልክ ልጀ አሉት።
...
ጥበበኛ ነወት ተብየ መምጣቴ ነው አላቸው። እርሳቸውም በእርጋታ ትኩር ብለው እያዩት " ምን እንድረዳህ ፈልገህ ነው የመጣኸው? " ብለው ጠየቁት። እርሱም "ሚስት አጣሁ !..."ብሎ የመጣበትን ጉዳይ አንድ በአንድ አስረዳቸው።
...
እርሳቸውም " አይይ ልጄ !! በል ና ተከተለኝ " ብለው ከበቆሎው ማሳ ዳር ቆሙና " የመጣህበትን እንድነግርህ ከዚህ ከምታየው የበቆሎ ማሳ ከዚህ ከቆምንበት ጀምርና እስከ ዳር ድረስ ውስጥ ለውስጥ ገብተህ ከዚህ ሁሉ የበቆሎ እሸት በመጠኑ ከፍ ያለ እና አሪፍ እምትለውን አንድ ብቻ የበቆሎ እሸት ዘንጥለህ አምጣልኝ ። ነገር ግን ማሳሰቢ ልስጥህ ።
...
1ኛ ከዚህ ከቆምክበ ከፊትህ ካለው እሸት ወደ ውስጥ ብገባም ከዚህ የበለጠ እሸት አላገኝም ብለህ ካመንክ እዚሁ ዘንጥለህ ልትሰጠኝ ትችላለህ።

2ኛው ማሳሰቢያ ከዚህ ጀምረህ እስከ ማሳው ዳር ድረስ ወደፊት እየተራመድክ መምረጥ ትችላለህ ነገር ግን ልብ በል አንዴ ያለፍከውን እሸት እንደገና ወደ ቡሀላ ተመልሰህ መቁረጥ አትችልም ወደፊት ብቻ።

3ኛው ማሳሰቢያ አጥቻለሁ ብለህ ባዶ እጅህን መምጣት አትችልም።

4ኛው እና የመጨረሻው ደግሞ ከዚህ ሰፊ የበቆሎ ማሳ አንድ የበቆሎ እሸት ብቻ ነው ቆርጠህ እምታመጣልኝ።
መጀመር ትችላለህ " አሉትና ተመልሰው ቁጭ አሉ ወጣቱም ወደ በቆሎው ገባና የተሻለ የሚለውን በቆሎ መፈለግ ጀመረ።
...
ሁሉም እሸት አማረው አይን አዋጅ ሆነበት ትንሽ ገባ እንዳለ በጣም የሚያማልል እሸት አየና ሊቆርጥ አሰበና " ወደፊት ከዚህ ከሚታየኝ የበለጠ ትልልቅ እና እሚያማምር ቢኖርስ ? ብሄድ ይሻላል"። ብሎ ፍለጋውን ቀጠለ። ነገር ግን ወደ ፊት በሄደ ቁጥር እንደ ቅድሙ የሚያምር ሳይሆን ጥራቱ እየቀነሰ ሄደ።
....
አሁንም ወደ ፊት ጥሩ እሸት አገኛለሁ እያለ መዳከር ያዘ። ነገር ግን ጭራሽ ከቅድሙ የባሰ በመጠኑ ያነሰ፣ ገና ለጋ የሆነ እና ትል የበላው እየሆነ መጣ። ወጣቱም ወደ ኋላ መመለስ አትችልም ስለተባለ ምናለ ቅድም ዳር ላይ ቆርጨ በነበር እያለ እየተፀፀተ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ ወደፊት ልክ ቅድም ስገባ እንዳየሁት እሚያማምር እሸት አገኝ ይሆናል እያለ በተስፋ ወደ ፊት ፍለጋውን ቀጠለ። እሚያሳዝነው የተባለውን እሸት ሳይቆርጥ በገባበት ተቃራኒ የእርሻው ዳርቻ ሊወጣ ሲዳረስ እንዳለ ግማሹን ወፍ የጠረጠረው እየሆነ መጣ።"
...
እስኪ እንደ ቅድሙ ዳር ላይ ጥሩ በቀሎ ባገኝ ብሎ የእርሻው ጫፍ ላይ ብቅ አለ ነገር ግን እሚገርመው ጭራሹንም ወፍ እልም አድርጎ የጨረሰውና ቆረቆንዳ ብቻ ሁኖ አገኘው።ወደ ቡሃላ እንዳይመለስ ወደ ኋላ መመለስ አትችልም ተብሏል። ባዶ እጁን እንዳይመለስ ምንም ቢሆን ባዶ እጅህን እንዳትመለስ ተብሏል።
...
ስለዚህ አማራጭ ስላጣ ወፍ የበላውን የበቆሎ ቆረቆንዳ አንዱን ዘንጥሎ ወደ ጠቢቡ ተመለሰ እና ከፊታቸው ቆመ።

እርሳቸም "እስኪ ያመጣኸውን አሳየኝ "አሉት። እርሱም አንድም በላዩ ላይ ጥሬ የሌለውን ቆረቆንዳ ሰጣቸውና በሀፍረት ፀጥ ብሎ ቆመ።"ይህንን ነው የተሻለ ያገኘኸው?" ብለው ቢጠይቁት እርሱም በሀፍረት አባቴ ያው የተሻለ አገኛለሁ ብየ ስፈልግ ሳላስበው ወፍ ከበላው ደረስኩ " አለ እየተንተፋተፈ።
...
ቁጭ በል እስኪ አሉና "አየህ የኔ ልጅ ሚስት እያማረጡ አንዷን ከአንዷ እያመረጡ መኖርም ልክ እንደዚህ ነው።
👉 አብዝቶ መምረጥ መጨረሻ ከምራጭ ይጥላልና ሚስት ከእግዚያብሔር ስለሆነች በአንተ ምርጫ አይሆንም። ከፊትህ ያለችውን ሚስት አድርግ "አሉት❞

ምንጭ "ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች"

ምን ተማራችሁ?

@menefesawitereka

https://t.me//menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

21 Apr, 17:42


#ከክፉ_ዘመናት_መሸሸግያችን_ነሽ
#መጠለያችንም_ቤተክርስቲያን_ነሽ
#የምንገባብሽ_በኃዘን_በደስታ
#ከቶ_ማንረሳው_አለብን_ውለታ
መዝሙሩን ተጋበዙልኝ

◉◉◉

🔊 ኦርቶዶክስ ተዋሕዷዊ ዝማሬ መሥራት ፈልጋችኹ ነገር ግን ግጥም ጽፋችኹ ዜማ ከቸገራችኹ፣ ዜማ ቀሏችኹ ግጥም ከቸገራችኹ አናግሩን፤ ከዘፈን ሳናገናኝ ያሬዳዊውን ዜማ እንሰጣችኋለን። በሊቃውንት አባቶች አስመርምረን እንሠራላችኋለን!

@Proud24
@Tselot21
@Abeselom27
@HibueEyesus

📞
+251969943778
+251704020186
+251919334222

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

16 Apr, 22:22


°° #ፈኑ_እዴከ °°

ኦ! አምላኪየ ጸራሕኩ ኅቤከ
እሞተ ከንቱ አድኅነኒ እብለከ
...
ዮም በዛቲ ዕለት አነ እብል ትንሣኤከ
በለኒ ነዓ ነዓ(ንዒ ንዒ) ፈኑ እዴከ
+++ ... +++
+++ ... +++

🌿 #ሰናይ_በዐለ_ትንሣኤ_ይኩን_ለኵልነ_ሕዝበ_ክርስቲያን!

🛑 Dn Mekuriya Murashe|

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

06 Mar, 18:15


#በዚህ_በጾም_ወቅት_ልናደምጠው_የሚገባ_መዝሙር

#ይደመጥ! #ይደመጥ!
#Share እንዳይረሳ!

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

03 Mar, 06:16


🌿 #ንነጽር_፵፰
የሰውን ልጅ ምኞት ካ'ለመገደቡ የተነሣ በ'የቀኑ ምኞቱ እያደገ ይመጣል።
ሊመኝ የሚችለውም የሌለው ነገር እንጂ መቼስ ያለው/የተሰጠው ነገር ስጠኝ ብሎ አይመኝ!
...
አስተውሉ! ያ የምንመኘው ነገር አኹን ባለንበት ሁኔታ ላይ ለእኛ ትርፍ ሊሆን ይችላል'ኮ! ምክንያቱም ከእኛ በላይ ስለ እኛ የሚያስብ አምላክ ያለን ስለሆነ ለእኛ የሚሆነውን ሰጥቶናል። ባይሰጠንም እንኳ ጊዜው አልደረሰም ማለት ነው።

ሰላም ለምድራችን🙏
@menefesawitereka
@menefesawitereka
ፍቅር
ለሕዝባችን🙏
t.me//menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

26 Feb, 07:01


🌿 #ንነጽር_፵፯
ቀኑ 19/06/2015 ዓ/ም ዕለቱም እሑድ ነው። በመኪና ረጅም ጉዞ በመጓዝ ላይ ነበርኩ። መኪና ውስጥ እንደገባሁ የታየኝ ብዙ ሰው እና አንድ ክፍት ወንበር ነበር። እኔም ወደ ወንበሩ ጠጋ አልኩና '
#ሰው_አለው?' ብዬ ጠየቅኩ። ❝አይ የለውም መቀመጥ ትችላለህ❞ ተብሎ ሲመለስልኝ የገባሁት ለመቀመጥ ነውና ተቀመጥኩ።
...
ልክ እንደተቀመጥኩ ከአጠገቤ የነበሩት ኹለት ሴቶች መዝሙር ከፍተው ከስልካቸው ጋር አብረው እየዘመሩ ሰማኹ። መቼስ መዝሙር ሲሰማ የማይወድ የለ! እኔም በመዝሙሩ ተመስጬ በውስጤ መዘመር ጀመርኩ።
...
ትንሽ እንደቆየኹ መዘመር አቆምኩኝ እነርሱን ማድመጥ ቀጠልኩ። ድምጻቸው ያረሰርስ ነበር። ኹለቱም የድምጽ መንትዮች ይመስላሉ ተመሳሳይ ድምጽ አላቸው። ያው ሰው አይደለን? ደካሞችም አይደለን? ድካም ይዟቸው ነው መሰል ዝም አሉ። ስልኩ ግን አልተዘጋም።
...
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን የማይታሰብ ነገር ተፈጠረ። መዝሙሩን ዘግተው ዘፈን ከፍተዋል። እጅግ አዘንኩና ከውስጤ ጠይቃቸው... ጠይቃቸው...! የሚል ስሜት ሲያስቸግረኝ ጠየቅኳቸው።
...
#ከትንሽ_ደቂቃ_በፊት_መዝሙር_ከፍታችኹ_ነበር_አኹን_ዘፈን_የመከፈቱ_ትርጕም_ምንድር_ነው? ብዬ ጠየቅኩ።
እነርሱም አሉኝ ❝መዝሙር እሚያምረው/እሚከፈተው ጠዋት ጠዋት ሲሆን ነው።❞ አሉኝ።
        ቀጠልኩና ጠየቅኩ...
...
#አኹን_ይህን_ዘፈን_በምታደምጡበት_ሰዓት_እንደበፊቱ_መዝሙሩን_ከፍታችኹ_ብታደምጡ_ችግሩ_ምን_ላይ_ነው?  እንዲህ አሉኝ...
❝አይ ችግር እንኳ የለውም፤ትንሽ ነቃ ነቃ ለማለት እንጂ።❞
         ጥያቄዬን ቀጠልኩ...
...
#አኹን_ዘፈን_የከፈታችኹት « #ነቃ_ነቃ_ለማለት» #ከሆነ_ቅድም_መዝሙሩን_የከፈታችኹት_ለምን_ነበር?
   ❝እንዳይደብረን❞

! እንግዲህ ልብ በሉ ዘፈኑን የከፈቱት «ነቃ ነቃ ለማለት» ነበር። መዝሙሩን ደግሞ «ድብርትን ለማላቀቅ»
...
ነቃ ነቃ በማለትና ድብርትን በማላቀቅ መሃል ያለውን ልዩነት አስተውሉልኝማ!
...
ምንም እንኳ መዝሙር የመክፈት ዋነኛ ዓላማ እነርሱ እንዳሉት ባይሆንም፤ ግን ከድብርት አያላቅቅም እንዴ እእእ?
...
እኛ ሰዎች ስንባል እንዲህ ነን ምክንያት ለማያስፈልገው ነገር የማይሆን ምክንያት የምንደረድር፣
ለስሜታችን ተገዝተን ሌላውን የምናሰናክል፣
ደጉንም ክፉውንም የእኛ የሚመስለን በኹሉ የምንዳክር። ኧረ ይቅር ይበለን!


ሰላም ለምድራችን🙏

@menefesawitereka
ፍቅር ለሕዝባችን🙏

...
#እወ_እግዚኦ_አምላክነ_አኃዜ_ኵሉ_ዘይነግሥ_ለኵሉ_ዓለም_አቡሁ_ለእግዚእነ_ወመድኃኒነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ#ንስእለከ_ወናስተበቍዐከ_በእንተ_ሰላም_ንጉሠ_ሰላም_ሰላመ_ሀበነ_እስመ_ኵሉ_ወሀብከነ_አጥርየነ_እግዚአብሔር_ወዕሥየነ_እስመ_ዘእንበሌከ_ባዕድ_አልቦ_ዘነአምር_ስመከ_ቅዱሰ_ንሰሚ_ወንጼውዕ_እንተ_ዘእምሰማያት_ሰላመከ_ፈኑ_ውስተ_አልባቢነ_ለኵልነ
     
🙏ተሣሃለነ🙏

t.me//menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

24 Feb, 20:51


🔔 #ጾም
ለተወሰነ ጊዜ እህል ከመብላትና ውሃ ከመጠጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት ከጥሉላት፣ ከሥጋ፣ ከቅቤ፣ ከወተት፣ ከእንቁላል በአጠቃላይ ከእንስሳት ውጤት መከልከል ነው።
...
ይህ ብቻ
#ጾምን ፍጹም ስለማያደርግ ሕዋሳት ሁሉ በ'የራሳቸው ክፉ ከመሥራት መታቀብ አለባቸው።
...
ይኸውም ዓይን ክፉ ከማየት፣ ጆሮ ክፉ ከመስማት፣ አንደበት ክፉ ከመናገር፣ እጅ ክፉ ከመሥራት፣ እግር ወደ ክፉ ቦታ ከመሄድ ይከልከሉ።
...
በተጨማሪም አዕምሮን ጎድተው ሰውን አስክረው የማይገባ ከሚያሠሩና ከሚያሳስቡ የአልኮል መጠጦች መጠበቅ እንዳለብን ማወቅ ይገባናል።
...
እንግዲህ ከላይ የተገለጸውን
#የጾምን ሕግ ስንፈጽም #ከጸሎት ተነጥሎ አይታይም። #ጾምና #ጸሎት በአንድነት ርኵሳን መናፍስትን ድል የምንነሳባቸው መሳርያዎች ናቸው።
...
#ጾማችንንና #ጸሎታችንን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው የተራበን የተቸገረን በሙሉ በአቅማችን ልንረዳ ይገባል።

◍ዘጸ ፴፬÷፳፰, መሳ ፳÷፳፮, ፩ኛ ሳሙ ፯÷፮, ፩ኛ ሳሙ ፴፩÷፲፫, ፪ኛ ሳሙ ፩÷፲፪, ፪ኛ ሳሙ ፲፪÷፲፮, ዕዝ ፰÷፳፩, ነህ ፩÷፬, ነህ ፱÷፩, አስቴ ፬÷፲፮, ማቴ ፲፯÷፳, ማር ፪÷፲፰, ሉቃ ፪÷፴፯, ሉቃ ፰÷፲፪, ሐዋ ፲፫÷፫, ሐዋ ፲፬÷፳፫, ፪ኛ ቆሮ ፲፩÷፳፯...

    
#መልካም_የጾም_ጊዜ
ትምህርተ ተዋሕዶ

ሰላም ለምድራችን🙏
@menefesawitereka ይቀላቀሉን
ፍቅር ለሕዝባችን🙏
...
#እወ_እግዚኦ_አምላክነ_አኃዜ_ኵሉ_ዘይነግሥ_ለኵሉ_ዓለም_አቡሁ_ለእግዚእነ_ወመድኃኒነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ#ንስእለከ_ወናስተበቍዐከ_በእንተ_ሰላም_ንጉሠ_ሰላም_ሰላመ_ሀበነ_እስመ_ኵሉ_ወሀብከነ_አጥርየነ_እግዚአብሔር_ወዕሥየነ_እስመ_ዘእንበሌከ_ባዕድ_አልቦ_ዘነአምር_ስመከ_ቅዱሰ_ንሰሚ_ወንጼውዕ_እንተ_ዘእምሰማያት_ሰላመከ_ፈኑ_ውስተ_አልባቢነ_ለኵልነ።❞
      🙏ተሣሃለነ🙏


t.me//menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

12 Jan, 20:21


🌈🌈ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ፪
🌺መቀላቀል ለምትፈልጉ 👇👇👇
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka
🌷🌹💐🌻🌼🌺🌺🌺🌺🌺💐🌸
Admin👉 @Ermiyas3

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

10 Jan, 00:15


🌈ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ፩

🌺መቀላቀል ለምትፈልጉ 👇👇👇
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka
🌷🌹💐🌻🌼🌺🌺🌺🌺🌺💐🌸
Admin👉 @Ermiyas3

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

06 Jan, 13:54


የገና በአል ቆይታ
#ከዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ ጋር
⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺
👉 ሰው እናቱን መርጦ አልተወለደም የጌታችን ...

👉 የሰብአ ሰገል አፅማቸው የት ይገኛል ???

👉 ወርቅ ፣ እጣን ና ከርቤ ምሳሌነቱ ??

👉 ለምን በግርግም ተወለደ ???

👉 ላሊበላና ኢየሩሳሌምን ምን ያመሳስላቸዋል ???

ሌሎችም ብዙ ጥያቄዎችን ይመልስላችኋል ...

#መልካም የልደት በአል

ለመቀላቀል 👇👇👇

🌺 @widase_betel 🌺
🌺 @widase_betel 🌺
🌺 @widase_betel 🌺

@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

06 Jan, 13:54


#ከጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ያገኘነው ምንድን ነው?

#ዳግም ልደት
በአዳም በደል ምክንያት አጥተነው የነበረው ልጅነታችንን ክርስቶስ በልደቱ ዳግመኛ እንደመለሰልን ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 1፥12 በማለት ገልጾታል።

#ሰላም
በጌታችን ልደት ለዓለም ሁሉ የሚሆን ዘላለማዊ ሰላም ተገኝቷል። ይህም “ክብር እግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ” እያሉ ቅዱሳን መላእክት በመዘመራቸው ተረጋግጧል። ሉቃ 2፥14። ስለዚህ በክርስቶስ ያገኘነው እውነተኛ ሰላም በእኛ ጸንቶ እንዲኖር ዘወትር በጾምና በጸሎት እየተጋን ስለሰላም የምንማፀን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ሰላም የክርስትና መታወቂያ አርማ ነውና።

#ብርሃን
“በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።” ኢሳ 9፥2። ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ያህል በዲያብሎስ ቁራኝነት ተይዞ የነበረው አዳም ወደሚደነቀው ብርሃን የተሸጋገረው በክርስቶስ ልደት ነው። እኛም በልደቱ ያገኘነውን የጽድቅ ብርሃን ጠብቀን ለመኖር (ብርሃነ ወንጌልን) ፈጽመን ከኃጢአት ርቀን በጽድቅ ሥራ ተወስነን ብርሃን ሆነን ልንኖር ይገባል።

#ነጻነት
“በነጻነት እንኖር ዘንድ ክርስቶስ ነጻ አወጣን። ከእንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገና በባርነት ቀንበር አትያዙ”። ገላ 5፥1። የሰው ልጅ እግዚአብሔርን በነጻነት እያመሰገነ ይኖር ዘንድ ተፈጥሯልና። ኃጢአት በመሥራት የዲያብሎስ ባርያ ሳንሆን በተሰጠን ነጻነት በመጠቀም የጽድቅ አገልጋዮች ሆነን ልንመላለስ ይገባል።

#ይቅርታ
በአዳም በደል ምክንያት ከአብራኩ የተከፈሉ በሙሉ በደለኛ ሆነው የነበሩበትን ዘመን ለውጦ አዳምንና የልጅ ልጆቹን በደል ደምስሶ ፍቅርን ይመሰርት ዘንድ ጌታ ተወለደ። በምድርና በሰማይ ላሉት ፍቅርን መሠረተ። እርሱ የሰው ልጆችን በደል ሳይቆጥር ሁሉን ይቅር እንዳለ ክርስቲያንም የበደሉትን ሁሉ ይቅር ይል ዘንድ የፈጣሪው ትዕዛዝ ነውና ዘወትር ሊፈጽማት የምትገባ ከእግዚአብሔር ጸጋ የምታስደምር የልደቱን ብርሃን ለማየት እንደበቁ በዚህም ደስ እንደተሰኙ እንደ ቅዱሳን መላእክት ለእውነተኛ ምስጋና የምታደርስ የጽድቅ መሠረት የበረከት በር ናት። ማቴ 18፥21-23፣ ማቴ 5፥23-25። መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ የሚለው አምላካዊ ቃል ይቅርታ የክርስትና ሕይወት መመሪያ መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልንፈጽማት ይገባል።

#ፍቅር
ፍቅር ሰሃቦ ለወልድ ኃያል እም መንበሩ ወአብጽሖ እስከለሞት /ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ አወረደው እስከ ሞትም አደረሰው።/ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጅን በደል ሳይቆጥር በዙፋኑ ሆኖ ምሬሃለሁ ማለት ሲችል ፍቅሩን ይገለጽ ዘንድ በከብቶች በረት ተወለደ። እውነተኛ ፍቅሩ ለክርስትናችን መሠረት ለጽድቃችን ፋና እንደሆነ መጻሕፍት ያረጋግጣሉ።

እንግዲህ በልደቱ ያገኘነውን ሰላም፣ ነጻነት፣ ይቅርታ፣ ብርሃንና ፍቅር ዋጋ የተከፈለበት ጸጋ የወረስንበት በመሆኑ ዘወትር በድንቅ ፍቅሩ የሚታደገን አምላካችን እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ እስከ መጨረሻው ድረስ ጸንተን እንድንኖር ክብራችንንና ጸጋችንን አስተውለን ከኃጢአት ርቀን በንሰሐ ታጥበን እራሳችንን ለክርስቶስ የተወደደ መስዋዕት አድርገን እንድናቀርብ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት አይለየን አሜን፫።
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka

t.me//menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

02 Jan, 04:30


ታህሣ ፳፬ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያት
እንኳን አደረሳችሁ!!!
👏👏 ተክለሃይማኖት ባህታዊ👏👏
ተክለሃይማኖት ባህታዊ
ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
በአደባባዩ ተተክለሀል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሀል
አዝ ............................
ቃልኪዳን አለህ የገነነ
ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውኃ አጠጥተን
ዋጋችን በዝቷል አባታችን
አዝ ............................
እኛም ሆነናል ልጆችህ
ማርኮ አስቀርቶን ምግባርህ
በምልጃህ ጸሎት ትሩፋት
ቤታችን መላ በረከት
አዝ ............................
ምህረት ይዘንማል ከሰማይ
በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ
ብዙ ተጋድለህ አትርፈሀል
ያገለገልከው አክብሮሀል
አዝ .........................
ተሰባበሩ ጣኦታቱ
አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ከአፍህ ወጥቶ
የአምላክ አድርጓል ሁሉን ገዝቶ

🌺መቀላቀል ለምትፈልጉ 👇👇👇
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka
🌷🌹💐🌻🌼🌺🌺🌺🌺🌺💐🌸
Admin👉 @Ermiyas3

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

30 Dec, 06:18


ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ላንቺ ይገባል አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ። ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ! ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኝልን ነሽ፤ ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምሕረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ቅድስት ሆይ ለምኝልን
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

30 Dec, 06:18


ሰላም ሰላም ለኪ
ማርያም ሰላም ለኪ/፪/እልልልልልልልልልልልልልልልል👏🕊👏🕊👏🕊👏🕊👏💐👏💐👏💐👏💐👏
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

30 Dec, 06:09


ገብርኤል ማለት ወልደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ይህንም ንጉሠ ፋርስ ከሠለስቱ ደቂቅ ጋራ አራተኛ ሆኖ በእሳት ውስጥ ሲመላለስ አይቶ አራተኛው የአማልክትን መልክ ይመስላል ብሎ የገለጸበት ስም ነው፡፡ በግዕዙ ‹‹ ወገጹ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብኤር ይመስል›› እንዲል (ዳን ፫፡፳፭)፡፡ ንጉሡ አራተኛው የአማልክትን መልክ ይመስላል እንጂ ቅዱስ ገብረኤል መሆኑን አልገለጸም፡፡ ይህንን የገለጸው ቅዱስ ያሬድ ነው፤ "ዝኬ ውእቱ ገብርኤል ዘባጢሁ ለእሳት -የሚነደውን እሳት ያጠፋው ገብርኤል ነው" ድጓ ገጽ ፻፸፡፡

በተጨማሪም ቅዱስ ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር ወዲበ ርእሱኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል፤ ገብርኤል ማለት ወልደ እግዚአብሔር ማለት ነው፤ ጥሬ ትርጉሙ ወልደ እግዚአብሔር ይባላል አለ እንጂ በቁሙ መላእኩ የእግዚአብሐር ልጅ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ በተጨማሪም ቅዱስ ገብርኤል "መጋቤ ሐዲስ፣ አብሣሪው መላእክ" ይባላል፡፡ የተባለብትም ምክንያት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም "ትፀንሲ  ወትወልዲ ወልደ"  ብሎ በስሙ ትርጓሜ ምሥጢረ ሥጋዌን በመናገሩ መጻሕፍት "ወልደ እግዚአብሔር" ሲሉ ይጠሩታል፡፡ መተርጉማን ሊቃውንትም "ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ፣እግዚእ ወገብር" ብለው ተናግረዋል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ "በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" እንዲል (ሉቃስ ፩፡፲፱)፡፡ በተራዳኢነቱና በአማላጅነቱ በምእመናን ዘንድ ፈጣን ነው፡፡ ያዘኑትን ለማፅናናት የምስራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን የሚላክና ፈጥኖ የሚደርስ መላእክ ነው፡፡

በጣዖት ፍቅር እጅግ ያለመጠን ልቡ ተቃጥሎ የነበረው የባቢሎን መሪ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል አሰርቶ መኳንንቱን ሰብስቦ ሕዝቡ በሙሉ ለጣዖቱ እንዲሰግድ አዋጅ አወጀ፡፡ ያ የመከራ ጊዜ ነበር፡፡ አስመሳዮች ለጣዖት ሰገዱ፡፡ እውነተኛ አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ንጉስ ሆይ "አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣዖት አንሰግድም" አሉት ሦስቱ ወጣቶች፡፡ ንጉሱም አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ እሳቱም ሰባት እጥፍ ነደደ፡፡ ወዲያውኑ የንጉሱ አገልጋዮች አናንያ፣ አዛርያን እና ሚሳኤልን ወደ እቶነ እሳቱ ወረወሯቸው፡፡ ከእሳቱ ኃይል የተነሣ የንጉሡ አገልጋዮቹም በእሳቱ እየተጠለፉ ነደዱ፡፡ ንጉሱም በዚህ ወቅት   ‹‹እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ እሳቱ ምንም አላቃጠላቸውም አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል፡፡›› አለ፡፡

ንጉስ ናብከደነፆር በግልፅ ተመልክቶ እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ከዚህ በላይ እንደተገለፀው ሊቀመላእክት ቅዱስ ገብርኤል ስለ ሃይማኖታቸው መከራ የተቀበሉትን ወጣቶች የነደደውን እሳት አብርዶ በሃይማኖታቸው እንደአፀናቸው በግልጽ በነብዩ ዳንኤል ተገልጿል፡፡

የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት እኮ ጥንት የነበረ ብቻ ሳይሆን እስከ አለንበት ዘመን ደርሶ የመልአኩን አማላጅነት በዓይን የተመለከትነው ተጨባጭ ድርጊት ነው፡፡ የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰ መከራ ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ ድነው እውነተኛ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ጸጋ ተረድተን መልአኩን ልናከብረውና ልናመሰግነው ይገባል፡፡ አምላከ ቅዱሳን በረከቱን ያሳድርብን
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka
t.me//menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

30 Dec, 06:09


በመልአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን🙏
ገብርኤል ሆይ ከሰው ወገን ከቶ ጠዋትና ማታ እንደኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም። ከመላእክትም ወገን እንዳንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም። ገብርኤል ሆይ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ። ይህን ያቀረብኩልህን ጸሎት እንደትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የማረጋጋት ቃለህን አሰማኝ።🙏
መልክአ ገብርኤል
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

27 Dec, 12:03


🌈አምስቱ አእማደ ምሥጢራት መግቢያ ፩
💥መንፈሳዊ ትረካ
🌺አድምጡ👂👂 መልካም ቆይታ🌺
መቀላቀል ለምትፈልጉ 👇👇👇
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka
🌷🌹💐🌻🌼🌺🌺🌺🌺🌺💐🌸
Admin👉 @Ermiyas3

2,082

subscribers

52

photos

12

videos