ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት @bibleztewahido Channel on Telegram

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

@bibleztewahido


"ልጄ ሆይ በክርስትናህ መጎልመስ ከፈለክ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር ራስህን አዛምድ"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷 t.me/bibleztewahido 🌷
🌷 t.me/bibleztewahido 🌷
  🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
https://t.me/+Q8cDirroZudEPWKP

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት (Amharic)

ከእንግሊዝ ስንት መከራብ ጋር የሆነው 'ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት' ተቀማጭ መጽሔት ለመጠቀም ተዘጋጅቷል። የትምህርት፣ የአካል ቅኝ እና መልዕክት መድሀኒት እንደሆነ ማንም ሰው አለመሆን አይችልም። 'ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት' በአባታችን ዮሐንስ አፈወርቅ በጣም መጠን ይፈልጋል። ማንም ትምህርትን ይከብራል እያሉ በጣም እንዲፈልጉ ይጠበቃል። ተጨማሪ አባታችን ዮሐንስ አፈወርቅ እንዴት ማለፍ እንችላለን። ፈልገን በእጅጉ እንመለከታለን። ትምህርትን ለማፈልፈል ለመጠቀም ጠበቁን 'ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት' በትክክለኛ ቋንቋ እንደሚገባ እንችላለን።

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

23 Nov, 19:50


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

23 Nov, 19:10


በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

18 Nov, 18:20


“ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም። እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤ የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”
— ማቴዎስ 8፥10-12

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

17 Nov, 20:58


“መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።”
— ራእይ 5፥8

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

17 Nov, 05:35


ራእይ 4:4-11
⁴ በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።
⁵ ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፥ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።
⁶ በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
⁷ ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
⁸ አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።
⁹ እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥
¹⁰-¹¹ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

17 Nov, 05:35


ሕዝቅኤል 1:4-9
እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስና ታላቅ ደመና የሚበርቅም እሳት መጣ፥ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ፥ በመካከልም በእሳቱ ውስጥ እንደሚብለጨለጭ የወርቅ ምስያ ነበረ።
ከመካከልም የአራት እንስሶች አምሳያ ወጣ። መልካቸውም እንደዚህ ነበረ፥ ሰውም ይመስሉ ነበር።
ለእያዳንዱም አራት አራት ፊት፥ ለእያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት።
እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ እግሮች ነበሩ፤ የእግራቸውም ኮቴ እንደ ጥጃ እግር ኮቴ ነበረ፤ እንደ ተወለወለ ናስም ይብለጨለጭ ነበር።
በክንፎቻቸውም በታች በእያራቱ ጐድናቸው እንደ ሰው እጅ ነበረ፤ ለአራቱም እንደዚህ ያሉ ፊትና ክንፍ ነበሩአቸው።
ክንፎቻቸው እርስ በእርሱ የተያያዘ ነበረ፤ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር፥ እያንዳንዱም ፊቱን አቅንቶ ይሄድ ነበር።

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

30 Oct, 16:46


ነገ ረቡዕ በጥናታዊ ጽሑፍ መድረክ ከቻሉ ይሳተፉ።

-ርዕስ- Mystical Theology: Insights from Spirituality -ምሥጢራዊ ነገረ መለኮት ከኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት እይታ አንጻር''

-ነገ ረቡዕ ጥቅምት 20 /02/2017 ዓ.ም

-ሰዓት 11:00

-አቅራቢ አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ(ፕ/ር)

-ቦታ 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

30 Oct, 16:14


“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ። ኢየሩሳሌምስ እርስ በርስዋ እንደ ተገጠገጠች ከተማ ተሠርታለች። የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ ዘንድ፥ ለእስራኤል ምስክር ሊሆኑ የእግዚአብሔር ነገዶች ወደዚያ ይወጣሉ። ዙፋኖች በዚያ ለፍርድ ተቀምጠዋልና፥ የዳዊት ቤት ዙፋኖች። ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ፤ አንተንም ለሚወድዱ ልማት ይሁን። በኃይልህ ሰላም፥ በጌጠኛ ቤትህም ልማት ይሁን። ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም፦ በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ። ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ።”
— መዝሙር 122፥1-9

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

29 Oct, 19:38


" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን"
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

26 Oct, 04:40


“እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።”
— ይሁዳ 1፥20-21

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

21 Oct, 18:30


የጌቴሴማኒ እናቶቻችንን ጥያቄ መመለስ የክብር ጉዳይ ነው
CBE 1000003777689
--
ገዳሙን የተሳላሚ ያህል አውቀዋለሁ፡፡ የሰው ፊት ማየት አይወዱም፡፡ አንድ ገዳም እንዴት መኖርና ማኖር እንዳለበት ብሔራዊ ማሳያ ናቸው፡፡ ይሠራሉ፡፡ ያስተምራሉ፡፡ ያሳድጋሉ፡፡ ይጦራሉ፡፡ በልመና አይታዩም፡፡ የሠሩትን ሲሸጡ ብቻ አይተናል፡፡ አሁንም ፊታችን የቆሙት የነበረውን ለማስቀጠል እንጅ ልመናን የማይቋረጥ ዘላቂ ተግባር አድርገው አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ … ያልታሰበ ቀን የሰው ፊት ያቆማል፡፡ እናቶቻችን ሰው ፊት መቆም አልለመዱም፡፡ ጊዜ ጥሏቸው እንጅ ኩሩዎች ሠርቶ አዳሪዎች ነበሩ፣ ናቸው፡፡ በነበሩበት የመንፈስ ልዕልና እንዲቀጥሉ ማስቻል የክብር ጉዳይ ነው፡፡ የሽግግር ጊዜያቸውን አሳጥረን በነበሩበት የትሩፋት ተግባር ማስቀጠል ግዴታችን ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

16 Oct, 16:55


"እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።"

የዮሐንስ ራእይ 22:12-14

7,720

subscribers

1,166

photos

2

videos