መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች @recordingyt Channel on Telegram

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

@recordingyt


ኣርቶዶክሳዊ ትረካና ፅሁፎች

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች (Amharic)

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች ከrecordingyt መጋቢት እና ሣራቺን በላይ ይመልከቱ። ይህ ትረካና ፅሁፎች በእንዚህ አካባቢዎች በዓለም ላይ የሚገኝበት የስልክ እና ቢሮ ትረካን ነው። ወደኛው ትረካና ፅሁፎ ለማንበብ ይህንን ቻናል በማድር ይግባኝ። ስለሆነ የቻናል አሰጣጥጦች የrecordingyt በጣም ስለሚከተሉ ቻናሎችን በያሉ የሚሰራ ወዘን።

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

13 Jan, 16:15


ጌታ ኩሩ መንፈስ ላላት ነፍስ እራሱን አይገልጥም። ኩሩ መንፈስ ያለው ምንም ያህል ብዙ መጻሕፍትን ቢያነብም እንኳን እግዚአብሔርን ሊያውቀው አይችልም። በትእቢቱ ምክንያት ለመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ቦታ አይሰጥምና፤ ትሁት መንፈስ ያለው ሰው ብቻ ግን እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ ይደርሳል።

(St. Silouan the Athonite, Writings, III.11) "

እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።"
(ያዕ 4:6)

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

12 Jan, 15:15


https://youtu.be/_dtzoiMsdMk

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

12 Jan, 12:34


ዛሬ ይለቀቃል፡፡
የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ማብራሪያ
ምዕራፍ አምስት ክፍል 1 (ከቁጥር 1-12) https://www.youtube.com/@MerhaTewahedo

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

11 Jan, 13:44


ማንም እግዚአብሔርን ቢፈራ ከሌላ ከማንኛውም አይነት ፍርሃት ነፃ ነው። የዚህን አለም ፍርሃት ከራሱ በማራቅ ለእነሱ እንግዳ ይሆናል እናም ማንኛውም አይነት መንቀጥቀጥ(ድንጋጤ) ወደ እርሱ አይቀርብም።

(St. Ephraim the Syrian, On the Fear of God and the Last Judgement)

“ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘድን እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው።”
— ምሳሌ 14፥27

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

10 Jan, 12:58


ስለኃጢአቱ ይቅርታን የሚሻ ትህትናን ይወዳል። በሌላ ሰው ላይ የሚፈርድ ግን የራሱን ክፉ ምግባር ይበልጥ የጸና እንዲሆን ያደርጋል።

(St. Mark the Ascetic, Homilies ,1. 126)

" እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።"
(ማቴ7:1-2)

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

09 Jan, 08:15


https://youtu.be/SppkRSMiz_c?si=umwxVRYl-05IEgor
እንኳን ለቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጥፋኖስ በዓለ እረፍት በሰላም አደረሰን የበረከት በዓል ይሁንልን.

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

08 Jan, 09:24


በፈተና ወድቀህ እንደሆነ ፤ የኃጢአተኝነት(የጥፍተኝነት) ስሜት ከመጸለይ እንቅፋት እንዲሆንብህ አትፍቀድለት።
ንስሓ እስክገባ ብለህ መጸለይን ካቆምክ፤ መቼም ቢሆን ንስሓ አትገባም። ጸሎት ወደ እውነተኛ ንስሐ መግቢያ በር ናትና።

St. Pope Kyrillos (Cyril) lV

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

05 Jan, 09:34


ቅዱሳን እንደኛ ሰዎች ነበሩ። ብዙዎቹም ከታላላቅ ኃጢአቶች የተመለሱ ናቸው፤ ነገር ግን በንስሓ አማካኝነት መንግስተ ሰማያትን ወረሱ።

እናም ወደዛ የገቡ ሁሉ የገቡት በንስሓ አማካኝነት ነው፤ ይኸውም መሃሪና ይቅር ባይ ጌታችን በመከራው አማካኝነት ለኛ የሰጠን ነው።

(St. Silouan the Athonite, Writings, XII.10)

" ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና። እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።"
(የሐዋርያት ሥራ 11:18)

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

04 Jan, 09:55


ስለ ክርስቶስ ስትል መራብና መጠማትን ውደድ። ስጋችንን በሚቻለን መጠን ማረጋጋት ስንችል፤ነፍሳችንን በበጎ ምግባር እንድታጌጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይደርጋል።

ስለ በጎ ሃሳባችን፣ ንግግራችን እና ስራችን ዋጋ የሚሰጥ አምላካችን፤ ስለሱ ብለን ለምንቀበላት ጥቂት መከራ እንኳን ዋጋችንን አያስቀርብንም።

(St. Gennadius of Constantinople, The Golden Chain, 41)

" እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።"
(ዕብ 6:10)

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

03 Jan, 09:25


ሁላችንንም ገና ከመውለዳችን በፊት ለሚያውቀን ለእግዚአብሔር የልብህን መሻት በጸሎትህ ውስጥ ንገረው። ሁሉም ነገር እንደኔ ፈቃድ ይሁን ብለህ አትጠይቅ፤ ምክንያቱም ሰው ለእርሱ የሚጠቅመውን ምን እንደሆነ ላያውቅ ይችላልና።

ስለዚህ ለእግዚአብሔር እንዲህ በለው እንደ ፈቃድህ ይሁን! እርሱ ሁሉን ለጥቅማችን ያደርገዋልና።

(St. Gennadius of constantinople, The golden chain, 47)

" ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤"
(1ኛ ተሰ 4:3)

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

02 Jan, 11:28


እንኳን ለፃድቁ አባታችን አባ ተክለሃይማኖት በዓለ ልደት አደረሰን. አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው ከቃል ኪዳናቸው ያሳትፈን.

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

02 Jan, 06:32


https://youtu.be/2KiSW1h4_6U?si=j1DTAeNCG4SjupZm

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

31 Dec, 15:54


ቅድስና የምትሰጠው ለሚታገሉ ነው።

ልባችንን ሳንመረምር አንዲትስ ሰዓት ልታልፍ አይገባም፤ የፍርድ ሰዓት መች እንድትመጣ እናውቅምና፤ ስለዚህም ስለ ህይወታችን በእግዚአብሔር ፊት መልስ ለመስጠት ዝግጁ መሆን አለብን።

ልባችንን መመርመር ስንለማመድ፤ መንፈሳዊ እድገት ሊገኝ የሚችለው በቅድስና ህይወት እግዚአብሔርን ደስ ለማስኘት ከሚኖር ጽኑ ፍላጎት መሆኑን በማወቅ ነው። በሥራችን ውስጥ በጎ የሆነ ነገር ብናገኝ፤ ክብሩን ለእግዚአብሔር እንስጥ።

መንፈሳዊ ተጋድሎዋችንን ቸል እንዳልንና በሞኛሞኝነት እንደተውነው ካወቅን፤ ወደ እግዚአብሔር በንስሓ ልንመለስ ያስፈልጋል። በእያንዳንዷ ጊዜና ሰዓት እራስችንን ለመመለስ መወሰንና፤ በእግዚአብሔር እርዳታም ከነፍሳችን ጠላት ጋር መዋጋት አለብን። ቅድስና የምትሰጠው(የምትገኘው) ለሚታገሉ ነውና።

( Abbot Tryphon)

" በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤"
(ሉቃ13:24)

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

30 Dec, 09:55


እንዲህ ሚባል ህግ አለን፤ ይቅር የምትል ከሆነ እግዚአብሔር ይቅር ብሎሃል ማለት ነው። ወንድምህን ይቅር የማትለው ከሆነ ግን፤ ኃጢአትህ ካንተ ጋር ይቆያል ማለት ነው።

(St. Silouan the Athonite, Writings, VII.9)

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 6÷14-15)
ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤
ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።
@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

29 Dec, 09:38


https://youtu.be/qOEyjQ_KW70

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

29 Dec, 05:46


የኛ ጌታ ድንበር የለውም። ለኛ ያለው ፍቅር በቃል ሊነገር የማይቻል እጹብ ድንቅ ነው። በተከፈተ ልብ ወደ እርሱ ልንቀርብና ሁል ጊዜ ከእርሱ ጋር ልንሆን ያስፈልጋል እርሱ ያለማቋረጥ ከእኛ ጋር ነውና።

(Elder Thaddeus of Vitovnica) " ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ፤ "
(ምሳ 23:26)
@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

27 Dec, 13:53


ሠለስቱ ደቂቅን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እንዳዳናቸው
https://youtu.be/wxFBF_RfirI?si=A_f1XEWp8rw4gRl7

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

27 Dec, 04:14


https://youtu.be/UaJrY4YhBRw?si=9YDUtX1d973Smvcf

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

26 Dec, 11:52


https://youtu.be/d6cCtsyqYIs

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

26 Dec, 04:09


እኔ ብዙ ኃጢአትን አድርጌአለሁ በእግዚአብሔር ፊት እራሴን ዝቅ አደርግ ዘንድ የምገባ አይደለሁም አትበል።

ተስፋ አትቁረጥ ተስፋ በመቁረጥም የኃጢአትህን ብዛት አትጨምር። ሁሉን ይቅር በሚል አምላክ እርዳታ ለውርደት አትሰጥም።

እንዲህ እንዳለ " ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤"(ዮሐ6:37) ። ስለዚህ እርሱ ንፁህ እንደሆነ እና ወደእርሱ የሚቀርቡትንም ሁሉ እንደሚያነፃ ያለመጠራጠር እመን

እውነተኛ ንስሃን ለመፈጸም ከፈለግህ በተግባር አሳይ። ያም ማለት በትእቢት ወድቀህ እንደሆነ ትህትናን ፣ በሰካራምነት ከወደቅህ ፈጽሞ ከመጠጥ በመራቅ ፣ በእርኩሰት ከወደቅህ የንጽህናን ህይወት አሳይ። እንዲህ እንደተባለ " ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤" (1ኛ ጴጥ3:11) (st Gennadius of constantinople, the golden chain,87-89)

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

01 Dec, 13:27


100K view

https://youtu.be/7lA5ItVk7FU?si=WTItpLXXecg9TCtZ

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

30 Nov, 03:58


ታቦተ ጽዮን ጣኦቱን እንደሰባበረችው
https://youtu.be/_i5S0lgdWV0?si=WXNfydS3-JwT4O2u

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

29 Nov, 04:31


የቅድስናን መንገድ ለማውቅ የቅዱሳንን ህይወት መጽሐፍት የሚያነብ ለሱ የቅድስናው መንገድ ይከፈትለታል.

ቅዱስ ቄርሎስ VI

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

26 Nov, 04:45


https://youtu.be/UaJrY4YhBRw?si=rleVYK4IF-JCT9Bc

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

22 Nov, 14:15


https://youtu.be/ujDglfetXb0

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

22 Nov, 10:44


ሁላችንም ኃጢአት መስራትን አናቋርጥም። እንሳሳታለን እናም እንወድቃለን። ብዙ ጊዜ በዲያቢሎስ ወጥመድ ውስጥ እንያዛለን።

ቅዱሳን አባቶቻችን ሁልጊዜ እንደሚነግሩን " በወደቅክበት ጊዜ ፈጥነህ መነሳትህና ወደ እግዚአብሔር ጉዞህን መቀጠልህ በጣም አስፈላጊ ነው።"

በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ብትወድቅ እንኳን ምንም ማለት አይደለም ወሳኙ ጉዳይ ተነስተህ ወደኋላ ሳትመለከት ወደ እግዚአብሔር መራመድህን ቀጥል።

የሆነው ነገር ሆኗል እናም ያለፈ ነገር ነው። አንተ ግን እርዳታን ከእግዚአብሔር እየጠየክ ጉዞህን ሳታቋርጥ ቀጥል።
Elder Thaddeus of Vitovnica
Our thoughts determine our lives
@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

21 Nov, 12:49


እንኳን አደረሰን የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ተራዳይነት ከሁላችን ጋር ይሁን.

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

20 Nov, 10:02


እግዚአብሔር እራሱ ወደ እርሱ እንድትመለስ ይፈልጋል። ያንተ ከእርሱ መለየት ያንተ ትክክለኛ ቦታ አይደለም እንዲሁም አንተ የተፈጠርክበት መለኮታዊ አላማ ይህ አይደለም። ወደ እርሱ እንደምትመለስ እርግጠኛ ሁን! በዚህ ፈተና በበዛበት ዓለም ምንም ሰላም አታገኝም። አንተ ልክ በጥፋት ውሃ ታሪክ ውስጥ እንዳለችው ርግብ ነህ ፤ እግሯን የምታሳርፍበት ቦታ ባጣች ጊዜ ደግማ ወደመርከቡ እንደተመለሰችው።( ዘፍ ፰፥፱ )

አቡነ ሺኖዳ lll

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

18 Nov, 05:59


አቤቱ እውነተኛ ዳኛ ሆይ ምንም እንኳን ትእቢተኛና ጉረኛ፣ ጨካኝ እና በንግግሬም እብሪተኛ ብሆንም፤ እንደ ፈሪሳዊው ቆጥረህ አትቃወመኝ።

አቤቱ መሃሪ የሆንከው ሆይ፤ ይልቁንም እንደቀራጩ ያለ ትህትናን አድለኝ ከእርሱም ጋር ቁጠረኝ።

ሉቃስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።
¹¹ ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤
¹² በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።
¹³ ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።
¹⁴ እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።


@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

16 Nov, 11:28


https://youtu.be/nmHht0BSmTg

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

16 Nov, 09:28


9.3 Mb

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

16 Nov, 07:12


"ሰው እራሱን በእውነት ለእግዛብሔር ትእዛዛት አሳልፎ ቢሰጥ, መንፈስ ቅዱስ እራሱንና አካሉን እንዴት ሊያነፃ እንደሚችል ያስተምረዋል"

ታላቁ ቅዱስ እንጦንስ

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

14 Nov, 19:00


"የእግዚአብሔር ኃይል በአንተ ላይ ድንቅን ሊያደርግ ይችላል ነገር ግን ያንተን የእምነት ኃይል ይጠብቃል።"
አቡነ ሺኖዳ III
@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

11 Nov, 12:12


ስኬታማ መሆን ከፈለክ ስለ ደካማነትህ አታስብ. ይልቁንም የእግዚአብሔርን ኃይል አስብ እንጂ.

አቡነ ሺኖዳ lll

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

10 Nov, 06:57


እግዚአብሔር በማታውቀው መንገድ የልቦናህን መሻት ይፈጽምልሃል። ስለዚህ በሰላም ሁን እና እግዚአብሔርን ጥራው።

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

08 Nov, 16:43


"ፍቅር ከምንም በላይ ውድ ነው፣ከምንም በላይ ውብ ነው፣ ሸክምን ያቀላል፣ ተንኰልንም በትዕግስት ይቀበላል። ፍቅር መራራውን ወደ ጣፋጭነት ይለውጣል፣ የሰውን ልጅ ከፍ ያደርጋል፣ ሰላምንም ይፈልጋል።"
- ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኪሪሎስ

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

08 Nov, 07:47


https://youtu.be/zWVa0dz0ju0?si=8jEgOXMNZp-AGsJl

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

08 Nov, 07:07


https://youtu.be/_O_S0XzMz_Q?si=4ay2Jr70sS9aR6px

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

06 Nov, 05:08


አብርሃም ያያት ቀን 👇👇👇
https://youtu.be/3fWmKmo_tyM?si=Iop-PtiXHLkRj_SI

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

06 Nov, 04:35


ውድ የመርሐ ተዋሕዶ ቤተሰቦች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተጨማሪ የምንማርባቸውን የቅዱሳን ታሪክ በዝክረ ቅዱሳን አምዳችን የተወሰኑ ቪድዮች አድርሰናል፤ ነገር ግን አብዛኞቻችሁ አላያችዋቸውምና ተመልከቱዋቸው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱስ ጳውሎስ የመጨረሻውን ክፍል አኒሜሽን ነው የሚቀረው ለማድረስ እንሞክራለን። ላይክ፣ ሼር ያድርጉ።
የመርሐ ተዋሕዶ ዝግጅት ክፍል
👇👇👇
https://youtube.com/playlist?list=PL-UZSkBjy_KEYCUT3oMskHLXEhx-j2WCy&si=fXtWvAY4qb9t66UR

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

04 Nov, 03:31


https://youtu.be/YGt-5IaHZHk?si=GeUAjGfFt6OHYPpi

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

03 Nov, 08:11


አንተ ትፆማለህ ሰይጣን ግን አይበላም. አንተ በብርቱ ትደክማለህ ሰይጣን ግን አይተኛም. ሰይጣንን ልትበልጠው የምትችለው ብቸኛ መንገድ ትህትና ሲኖርህ ነው, ሰይጣን ምንም አይነት ትህትና የለውምና.

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

02 Nov, 19:47


https://youtu.be/qaleE7YlYO4?si=_0nALJrhF4-D6Wb1

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

02 Nov, 16:35


https://youtu.be/in_1GOjUuUM?si=pXnsnapytUWCls3L

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

02 Nov, 12:16


https://youtu.be/TgnSuTwvPhE?si=Byq4-ITywak2X0AB

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

02 Nov, 06:44


አእምሮ እግዚአብሔርን ወደ ማስታወስ ስመጣ, ልብ በቀጥታ በፍቅር ይንቀሳቀሳል, አይንም ብዙ እንባን ያፈሳል. ይህ የፍቅር ልምድ ነው የሚወዱትን ሰው ባስታወሱ ጊዜ እንባን ማፍሰስ.

+ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ+

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

01 Nov, 01:03


ከክፉ ሰዎችና ከዲያብሎስ ከሚመጣ ምንፍቅና እና ስህተት, ፈጠራ እና ወጥመድ የምንድንበት በቸኛ ተስፋ ጸሎት, ንስሐ እና ትህትና ናቸው.

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

31 Oct, 09:52


ጻድቃን ሲባል በስንክሳር ላይ የተጻፉ ከመቶ አመታት በፊት የነበሩ በትረካ እና ገድል መልክ ብቻ እንጂ እውነት ዛሬ የሚፈጠሩ የማይመስሉን ስንቶቻችችን ነን?
ዛሬ ዕረፍቷ የሚታሰበው ጻድቋ ሴት ሔራኒ ግን እንደኛ በመኪና እየተጓዘች በአውሮፕላን እየተመላለሰች በዘመናዊ አለም ኑራ በተአምሯ ብዛት አለምን አስደንቃለች እናም ዛሬ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተነሱት ተአምር ሰሪ ጻድቃን አንዷ የሆነችው በተአምራቷ ብዛት የምታተወቀው የድሮ ካይሮ የአቡሰይፊን ወይም ቅዱስ መርቆሬዎስ የሴቶች ገዳም የበላይ ጠባቂ እና እመምኔት እማሆይ ጣማፍ ኡምና ኤሬን በ1999 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በክብር ያረፈችበት ቀን ነው።(ጥቅምት 21) በጣም በብዙ መጽሀፍ ከሚታተመው ተአምራዊ ህይወቷ በጥቂቱ እነሆ
+ + + + +
እመምኔት ታማቭ ሔራኒ(ሂራኒ)፦በግብፅ አገር ልዩ ስሙ ጊርጋ በተባለ ስፍራ በየካቲት 2 ቀን 1929ዓ.ም በዘመነ ሰማዕታት ከአባቷ ያሳኼላ እና እናቷ ጄኔየፍ ማታ አል-ፌዚ ተወለደች። የልደት ስሟ ፋውዚያ ይባላል፡፡ ይህች ቅድስት እንደ ሌላዉ ቅዱሳን በሰላም አልተወለደችም ማለትም እናቷ ከመጠን በላይ ነበር የታመመችዉ (እርሷን በምወትልድበት ጊዜ) በዚያ በጭንቅ ሰዓት አባቷ እና አያቷ ይፀልዮ ነበር አባቷ አምላክን ለወለደቸች ለክብርት እመቤታችን አያቷ ደግሞ ለሰማዕታት አለቃ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲያማልዷቸዉ አጥቀብዉ ይጸልዮ ነበር ከዚያም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ መጥታ ለእናትዋ ተገለጸችላት ቅዱስ ጊዮርጊስንም 'ጀርባዋን ዳስሰዉ' አለችዉ እርሱም እጅ ነስቶ ጀርባዋን ዳሰሰዉ በሰላምም ተገላገለች እመቤታችንም ህጻኗን ታቅፋ 'ይህች ልጅ የእኛ ናት' ብላ ህጻኗን ባርካ ወደ ሰማይ አረገች፡፡ከዚያም እያደገች በሄደች ቁጥር ለክርስቶስ ያላት ፍቅር እየጨመረ መጣ ሳታውቀውም ወደ ገዳም ለመሔድ ትናፍቅ ጀመረ እንደዚህ አይነት ፍላጎት የነበራት ገና የ8 ዓመት ልጅ በነበረችበት ጊዜ ነዉ፡፡የምትማረዉ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነበረ በዚያም ደናግላን (ሴት መነኮሳይያት) ነበሩ እንደ እድሜ ጓደኞቿ መጫዎትን ትታ እነርሱን ታይ ነበረ እንድ ቀን በትምህርት ቤታቸዉ በሚገኝ የደናግላኑ ጸሎት ቤት ሔደች ከዚያም አንዷ የካቶሊክ ደናግል ስትጸልይ አገኘቻት ጸሎቷን እስክትጨርስ ቁጭ ብላ
መጠበቅ ጀመረች ያቺ መነኩሲት ጸሎቷን ፈጽማ ወደ ተቀመጠቸዉ ቅድስት ሄዳ ልጄ ምን ሆንሽ አለቻት ቅድስቲቱም እኔ እንደ እናንተ መነኩሴ መሆን እችላሁ? ብላ ጠየቀቻት መነኩሲቷም አዎን ትችያለሽ አለቻት በመቀጠልም
በመጀመሪያ እኔ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ስለሆንኩ በራሴ ቤተክርስትያን ልቁረብና ከዚያም ልቀላቀላችሁ አለቻት መነኩሲቷም መነኩሴ መሆን ከፈለግሽ ትችያለሽ ግን መቁረብ የምትችይዉ በእኛ ቤተክርስትያን ነዉ
ምክንያቱም የእኛ እምነት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይለያልና አለቻት ቅድስቲቱም ታዲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማትን አላውቃቸውም አለቻት መነኩሲቷም እኔ እነገርሻለሁ ለምንኩስና የመሚያስፈልጉትን ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ
አስተምርሻሁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖትሽን እንድትለቂ አልፈልግም አለቻት፡፡መነኩሲቷም እንደነገረቻት በቤቷም ሆነ በቤክርስትያን ትጸልይ ነበረ በተለይም ጠዋት ጠዋት ደስ የሚል የቤተክርስትያን ዕጣን ይሸታት ነበረ ግን ይህ
የሚሆነዉ ከቅዳሴ በፊት ነበረ፡፡ ይህ ነገር ያሳሰባት እናቷ ወደቤተክርስትያን ሄዳ ለካህኑ ነገረችዉ እርሱምም ልጅሽ የተባረች ናት ያ የዕጣን ሽታ ሥውራን ባህታውያን በሚጸልዩት ሰዓት የሚሸት ነዉ አላት፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እናቷ
ታመመች ህመሙም የሚያነቃንቅ አልነበረም ይህንን የምታውቀዉ ቅድስቲቱ እናቷን አጽናንታ ወደ ቤተ-ክርስትያን ሄዳ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ስዕል ፊት ቆማ መጸለይ ጀመረች እመቤቴ ሆይ እባክሽ እናቴን ፈውሻት እኛ
ልጆችሽ ነን አምንሻሁ ብላ ጸለየች።አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ለእናቷ ተገለጻ እንዲህ አለቻት ለምን ታቅሻለሽ እናትየዋም ልጆቼ ህጻናት ናቸዉ እኔ ከሞትኩ እግዚአብሔር እንደሚፈልገዉ ላያድጉ ይችላሉ
እባክሽን ከጌታ ፊት አማልጂኝ ታላቅ እህታቸዉ እስክታድግና ኀላፊነትን እስክትረከብ ድረስ አለቻት አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን መልሳ ከእኔ ጋር ነይ አለቻት ከዚያም እናትየዋ ወዴት እኔ ለባለቤቴ ሳልናር አልወጣም አለቻት
አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን መልሳ አንቺ በባልሽ ቦታ ብትሆኚ ከጌታ እናት ጋር ለመሔድ ደስ ይልሽ ነበረ ብላ ወደ ሰማይ ይዛት ሄደች ከዚያም በመልካም መኝታ አስተኛቻት ከዚያም እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ጊዮርጊስ
እስኪ እያት መርምራት አለችዉ እርሱም እናቴ እመቤቴ ሆይ እንደምታውቂዉ የእርሷ ጉዳይ አብቅቷል ድናለች አላት ክብርት እመቤታችንም እኔ እንዳማልዳት ጠይቃኝ ነበረ እኔም ልመናዋን ተቀብዬ ለልጄ ለወዳጄ ነግሬዋለሁ አሁን ያለባትን ችግር ነቅለህ ጣልላት አለችዉ ቅዱስ ጊዮርጊስም እናቴ ያንቺ እጅ ይዳሳትና ከዚያ አወጣዋለሁ አላት እመቤታችንም ዳሰሰቻት ቅዱስ ጊዮርጊስም አውጥተቶ
ለእናትየዋ ይህንን ይዘሽ ወደ ቤትሽ ሒጂ አላት፡፡ቅድስት ኄራኒ ገዳም የመግባት ፍላጎቷ እየጨመረ መጣ ከዚያም ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆርዮስ ተገለጸላት ስለእርሱም ሰምታ አታውቅም ነበረ እርሱም ራሱን ካስተዋቃት በኋላ ወደ ገዳሙ ወሰዳት ከወሰዳትም በኋላ ገዳሙን ሁሉ ካስጎበኛት በኋላ ወደ ቤቷ በደቂቃ መለሳት ገዳሙ ርቀት ነበረዉ የወሰዳትም በሕልም ሳይሆን በውን በፈረሱ ነዉ፡፡ እመቤታችን ለእናትየዋ ተገልጻላት ያኔ ስትወልጂ የኛ ነች ብየሽ አልነበረ አሁንም ወደ ገዳም ውሰጃት አለቻት (ምክንያቱም አባቷ አትሄጂም ብሎ ስለከለከላት)፡፡ ገዳምም ገብታ የገዳም ኑሮ ጀመረች በዚያ ገዳም እማሆይ አፍሮዚና የምትባል ኢትዮጵያዊት ቅድስት መናኝ ነበረች እርሷም እንዳየቻት "ኢንቲ አልደብራ ረይሳ ደብራ አቡ ሰይፈን" አለቻት ትርጓሜውም አንቺ የደብረ አቡ ሰይፈን ገዳም እመምኔት(አለቃ) ትሆኛለሽ አለቻት (ግብፆች ቅዱስ መርቆሬዎስን አቡ ሰይፈን ብለዉ ይጠሩታል አቡ ሰይፈን ማለት የሁለት ሰይፎች አባት ማለት ነዉ፡፡) የበጎ ነገር ጠላት የሆነዉ ሰይጣን ቅድስቲቱን ይፈትናት ነበር እርሷም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታባርዉ ነበር እመቤታችንም በየጊዜዉ ትጎበኛት ነበር፡፡የተተነበየላት ነገር ደረሰ እመምኔት እንድትሆን በቅዱስ ቄርሎስ ስድስተኛ ተመረጠች እርሱም ፕትርክና ከመሾሙ በፊት አንድ ጊዜ አግኝቷት እመምኔት እንደምትሆን ነግሯት ነበር፡፡ ከዚያም ቅድስት ታማቭ ኢሪኒ እኔ እመምኔት መሆን አልፈልግም አለች በግድ ጎትተዉ ወደ ጳጳሱ ወስደዋት ተባርካ አስኬማ ለብሳ እመምኔት ሆነች እመምኔት ከሆነች በኋላ በግል ፀባዩዋ ላይ የታየ ለውጥ አልነበረም እንደድሮ ትህትናዋን ለብሳ እናቶችን ታገለግል ነበር።የቅዱስ ፓኩሚየስን ( ጳጉሚስ) የገዳማዊ ኑሮ ሥርዓት እንደገና በስራ ላይ እንዲውል ያደረገች ቅድስት ናት፡፡ካለችበት ቦታ ወደ ፈለገችው ቦታ ልክ እንደቀደሙት ቅዱሳን ወዲያውኑ ሰከንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትደርስ ነበር ገነት እና የተሰወሩ የቅዱሳን ያሉበትን ቦታ በየጊዜው ትጎበኝ ነበር ።ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ድንግል እናቱ እና ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሌሎች ብዙ ቅዱሳን ጋር መጥተው ያረጓጓት ነበር።የሰዎችን ችግር ማንም ሳይነግራት አውቃ እስከነ መፍትሄው ነግራ ታጽናናቸው ነበር።በሽተኞችን ትፈውስ ነበር ያዘነውን ታረጋጋ ነበር ገዳሙን ከነረበት ችግር አላቃ ወደ ትልቅ ገነትነት ለውጣዋለች ።እናም ብዙ ልጆችን

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

31 Oct, 09:52


(መነኮሳያት) አፍርታ እነርሱም እንደእርሷ የበቁ ለመሆን
ችለዋል፡፡መሞት አይቀርምና ገዳሙን በደንብ ካስተዳደረች በኋላ በክብር አርፋች፡፡ጸሎትና በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቋ ቅድስት ጻድቅ ታማቭ ኢሪኒ ጸሎት ይማረን።
✞✞✞
ነቢል ጂንዲ የተባለ በግብጽ ካይሮ የሚኖር የKLM COMPANY ፊልድ መካኒክ ነበር ።ይህ ሰው የጻድቋ እማሆይ የጣማፍ ኡምና ኤሬን (ሔራኒ) የዘወትር ጠያቂና መንፈሳዊ ልጅ ነበር።ይህ ሰው ቅድስት ሔራኒ አጊባ (AGIIBA) ወደ ተባለ ቦታ ስትሔድ እሷን ለመሸኘትና በረከቷን ለመቀበል የመጣ ሰው ነበር።ተጓዦቹ ሶስት መነኮሳት ሔራኒ ና ይህ ሰው ነበሩ።የሚጓዙትም በሁለት ጉዞ መጀመሪያ ወደ ማርሳ መጥሩህ ወደሚባል ትንሽዬ ኤርፖርት ከዛ ወደ አጊባ ነበር ።እናም አቶ ነቢል ያጋጠመውን ነገር እንዲህ ይመሰክራል።
"በጊዜው ኤር ሲናይ የተባለ ከግብጽ አየር መንገድ ጋር በትብብር የሚሰራ ድርጅት ነበር።ይህ ድርጅት የሀገር ውስጥ በራራ ብቻ የሚሰራ ሲሆን 3 foker-27 የተባሉ ፕሌኖች ነበሩት።በእለቱ እኛ ከነዚህ በአንዱ የተሳፈርን ሲሆን
ጉዞውም ከካይሮ-እስክንድርያ-ማርሳ መጥሩህ ነበር። ፕሌኖቹ ደካማ እና ትናንሽ ስለሆኑ ወደላይ ከፍ ብለው ብዙም አይሄዱም ነበር።ፕሌኑ ከተሳፈርን በሁዋላ ለመነሳት በሚያኮበኩብበት ጊዜ የሆነ ችግር እንዳለው ጠርጥሬ ነበር።ወደ ካፒቴኑ (አብራሪው) ሒጄ ስለጉዳዩ ብጠይቀውም "ተሳፋሪዎች ይረበሻሉ"በሚል ምክንያት ምንም መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም።ትንሽ እንደሔደ ግብጽ ዴልታ አከባቢ ሲደርስ አውሮፖላኑ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ካይሮ እየተመለሰ እንደሆነ አስተዋልኩ ነገሩንም ስረዳው አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነን አውሮፖላኑ እንደተነሳ ጎማዎቹ በሙሉ መሰብሰብ ነበረባቸው በርግጥ የኋላ ጎማዎች በትክክል
ቢገቡም የፊቶቹ ግን የሆነ ስታክ አርጎ የያዛቸው ነገር ነበር። ዞሮ ዞሮ ወደተነሳበት ኤርፖርት ቢመለስም ማረፍ አይችልም ምክንያቱም ጎማዎቹ በሆነ ነገር ስታክ ስላደረጉ መዘርጋት አይችሉም።ባጭሩ ጎማዎቹ ለመብረርም ለማረፍም
በማይቻልበት ሁኔታ ተይዘዋል ማለት ነው።ፕሌኑ ወደ ካይሮ ተመልሶ ዝም ብሎ ሰማዩን ይዞር ነበር ምክንያቱ ደግሞ ነዳጁን ለመጨረስ እና በሚያርፍ ጊዜ የሚፈጠረውን እሳት አደጋ ለመቀነስ ነው። እኔም እንደባለሙያ እንደማንተርፍ
ባውቅም ጻድቋ እማሆይ ጣማፍ ከኛ ጋር ስላለች ምንም አንሆንም ብዬ እራሴን አሳመንኩ። ሁኔታውን የተረዳው ተሳፋሪም በመንጫጫት እና ድንጋጤ እየጮኸ ያያት ነበር በርግጥ ሁሉም ክርስቲያን ባይሆን ተአምር ሰሪነትዋን በዝና
የማያውቅ ግን አልነበረም።እሷም ከተነሱ ይወድቃሉ በማለት በእጇ እንዲቀመጡ መንገር ጀመረች።እየጮኸችም ቁጭ በሉ አይዞአችሁ ምንም አትሆኑም እያለች ልታረጋጋቸው ትሞክር ነበር።በአውሮፖላኑም የድርሱልኝ መልእክት 7 የእሳት አደጋና 8 አምቡላንስ ምድር ላይ ሆነው የሚሆነው ይጠባበቁ ነበር። ጣማፍም ወደ እኔ ዞር አለችና "ስለተፈጠረው ነገር ያረጋገጥከው ነገር አለ?? "አለች እኔም
በድንጋጤ አዎ እናታችን ያረጋገጥኩት ነገር አለ እሱም " ድንግል ማርያም በዚህ በኩል ያለውን ክንፍ ትደግፍልናለች፣ አቡ ሰይፊን (መርቆሬዎስ) በፈረሱ የፊቱን በኩል ይደግፍልናል፣ ጻድቁ አቡነ ቄርሎስ ፓትርያርኩ በዛኛው በኩል ይይዙልናል " እያልኩ ስርበተበት እሷ ኮስተር ብላ ቅዱስ ሩፋኤልስ ? ስትለኝ ክንፉ ከአውሮፖላኑ በታች ዘርግቶ እንዳይወድቅ ያደርገዋል ከዛ አውሮፖላኑ በሰላም ያርፍና ሁላችንም እንወርዳለን ብዬ ምኞቴን ስጨርስ።አዎ እንደዚህ ነው የሚሆነው አለችኝ።የተነጋገርነው የእምነት ንግግር እንጅ እየተደረገ ነበር ለማለት አልነበረም። ጣማፍ ግን በመስኮት እያየች የጠራናቸው ቅዱሳን መጥተው የቱን የቱን ቦታ እንደደገፉ ስትነግረን መደነቅ ጀመርን ።በሚገርም ሁኔታ አውሮፖላኑ በትክክል መጓዝ ጀመረና ወደ መሬት ተጠጋ ይህ እንዴት እንደሆነ በጣም ገርሞኝ ነበር ወደ መሬት እየተጠጋ መጥቶ ማኮብከቢያ አስፋልትን ሊይዝ ሲል ነዳጅ አለቀ ይህም ካፒቴኑ አየር ላይ እያዞረ ስለጨረሰው ነበር እናም ፕሌኑ ሚዛኑን ስለሳተ በአፍንጫው ወደ መሬት ተቀረቀረ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ተሳፋሪው ሁሉ በትክክል እንደሚሔድ እንጅ ምን እንደተፈጠረ መረዳት እስከማይችል ድረስ ምንም አይሰማውም ነበር።አውሮፕላኑ መሬት ላይ ቢወድቅም ማንም ተሳፋሪ ምንም የአደጋ ስሜት አልተሰማውም ደግሞ
ከካፒቴኒ ጀምሮ አንድም ሰው ምንም አደጋ አልደረሰበትም ነበር።ካፒቴኑም በፍጥነት ወደ ወስጥ መጥቶ የጣማፍን እጅ እየሳመ እናቴ ያንቺ ጸሎት ነው ያዳነን ይላት ነበር።እሷም ከሰዎች ሁሉ ጋር በሰላም ከፕሌኑ ወጣች አውሮፕላኑም ከውጭ ስናየው አፍንጫው ሙሉ ወደ መሬት ውስጥ ገብቶ ነበር።በተፈጠረውም ሀገር ሁሉ ተደንቆ እንዲያውም በታዋቂው አል አሕራም ጋዜጣ ወጥቶ ነበር "ብሏል።
(ምንጭ የእግዚአብሔር ዙፋን The Throne of God)

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

31 Oct, 02:36


ጸሎት የደካሞች ኃይላቸው , የድሀዎች ሀብታቸው, ለችግርኞች መጠለያቸው, ላዘኑት ምጽናኛቸው እና ለኃጢአተኛው ደግሞ አማላጅ ነው.

+አቡነ ሺኖዳ lll+

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

30 Oct, 07:10


መንፈሳዊ ተጋድሎ ይህ ነው: በሕይወትህ የምገጥሙህን ነገሮች ሁሉ ወደ በጎ መቀየር. መከራ ቢገጥምህ እራስህን ለጸሎት ስጥ. ቀስ በቀስ ሁሉንም ድካሞችህን (በክርስቶስ) ማከም ትችላለህ.

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

30 Oct, 03:40


https://youtu.be/v7psAh7VURw?si=SLAEl_IENXVj1qzz

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

29 Oct, 07:59


የኃጢአቶችህ ድምር የእግዚአብሔርን የምህረት መጠን አይበልጥም. ቁስሎችህም ከታልቁ ሀኪም የመፈውስ ችሎታ በላይ አይደሉም.

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

28 Oct, 13:10


https://youtu.be/gKUGzlozQfY?si=4NQRZ9EbSHSuyJ6W

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

27 Oct, 16:39


https://youtu.be/gatzR9tMA-M

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

27 Oct, 08:40


https://youtu.be/SppkRSMiz_c?si=qpYZWpE83YfBEdX5

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

26 Oct, 16:13


https://youtu.be/7lA5ItVk7FU?si=H3GoSQT6TvKH5isg

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

25 Oct, 23:26


በክርስቶስ መፍትሄ የሌለው ምንም ከባድ ችግር የለም። በችግሮችህ ምክንያት ምንም አትፍራ ይልቁንም ወደ ክርስቶስ ተመለስ ለችግሮችህ ሁሉ መፍትሄ ይሰጥሃል።

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

24 Oct, 17:56


https://youtu.be/t9R8QBfY4O0?si=ni1m01z0RyfwVhSF

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

23 Oct, 10:12


https://youtu.be/Fh09-ZizsT0?si=xAeRVgeMz13L4PJu

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

23 Oct, 07:15


ቤተክርስቲያን መሸሸጊያ ነች። በውስጧ እስከሆንክ ድረስ ተኩላው አይደርስብህም፣ ከሷ ከወጣህ ግን አውሬዎቹ ይይዙሃል። ከቤተክርስቲያን እራስህን አታርቅ፣ እንደ ቤተክርስቲያን ሃያል የለም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት። ቤተክርስቲያን መዳኛህ ናት። ቤተክርስቲያን ከሰማያት ከፍ ትላለች። ቤተክርስቲያን ከድንጋይ በላይ ጠንካራ ነች። ቤተ ክርስቲያን ከምድር ትሰፋለች። ቤተክርስቲያን መቼም አታረጅም ነገር ግን ሁሌም እራሷን ትድሳለች።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

22 Oct, 11:37


ከኔ በላይ ደካማ የሆነ አላውቅም, እንደ ጌታዬ ጸጋ ያለ ደግሞ ጠንካራ የሆነ ነገር አላውቅም.

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

22 Oct, 09:49


በጥቅምት 12 በሚነበበው ድርሳን ሚካኤል ላይ የምናገኘው ዳዊት እንዴት ለንግሥና እንደተመረጠና ዳዊት ጎልያድን እንዴት እንዳሸነፈ የሚልጥ ነው። እኛም ይሄን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጋብዘነዎታል።
https://youtu.be/4tjQSIR1YfI?si=wAjhoYORKfkRrCeD

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

21 Oct, 07:22


https://youtu.be/IIbB1WKjpIc?si=NEM0z711PXzrcNNB

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

21 Oct, 05:54


ተጻፈ በዲ.ን ሔኖክ ኃይሌ

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

21 Oct, 05:26


ልክ የጳውሎስ እና ሲላስ የምሽት ጸሎት የእስርቤቱን መዝጊያ እንደከፈተ, እንዲሁ የክርስቲያኖች የምሽት ጸሎት የሰማይን መዝጊያ ይከፍታል

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

20 Oct, 07:15


https://youtu.be/FEiQgcW_K5g?si=2PzKEwd33a1Ps2aa

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

20 Oct, 06:51


ሰዎች ስታስፈልጋቸው ብቻ ሲያስታውሱህ አትበሳጭ. ይልቁንም እድለኝነት ይሰማህ አንተ በጨለመባቸው ሰዓት በአእምሮዋቸው የምትመጣ ሻማ ነህና.

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

19 Oct, 12:12


https://youtu.be/i-XFIY0BRLk?si=RejTHMnlYGWYQavh

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

19 Oct, 05:18


እውነተኛ ነፃነት ማለት ሰው ከኃጢአቱ ነፃ ሲሆን ነው.

+አቡነ ሺኖዳ lll +

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

18 Oct, 13:07


https://youtube.com/@merhatewahedo

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

18 Oct, 10:23


https://youtu.be/ge2348f7Ft4?si=xpFcIvtWI1AR-AYm

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

18 Oct, 05:10


ቅዱሳን ኃጢአት የሌለባቸው ሰዎች አይደሉም. ይልቁንም ከኃጢአት ጋር ሲጋደሉ የኖሩ ሰዎች ናቸው እንጂ.

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

17 Oct, 10:13


ወደ መንግስተ ሰማያት የሚወስደው መንገድ ምንም እንኳን ጠባብና ከባድ ቢሆንም, ግን ወደ ሕይወት የሚመራና ከገቡበት በኋላ ሰፊ እና ጣፋጭ የሚሆን ነው . ይህን የቀመሱትና ያጣጣሙት እነዚያ የዚህ ምስክር ናቸው.

+ቅዱስ አትናቴዎስ+

@recordingYT

መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች

17 Oct, 06:51


https://youtu.be/IrKphs58oho?si=Rw5f32KlOCaw-ss9

1,392

subscribers

420

photos

6

videos