የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

@tewahdo_haymanotie


✍️"አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች ❹፥➎)

✍️ጥንታዊቷንና እውነተኛዋን ሃይማኖት ለመማር ከ1️⃣ኛ ዓመት ጀምሮ ኮርሶች እየተሰጡበት ያለ የእግዚአብሔር ቤት ነው።

✍️የማንኛውም ሃይማኖት ተከታይ ገብቶ መማር ይችላል። 🌹ቅድሚያ ለነፍስዎ ይኑሩ!🌹

ኮርሶች👇
t.me/Tewahdo_Haymanotie/703

አገልጋዮችን ለማግኘት
@Dingl_Ruhruhitu_bot

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

11 Sep, 13:54


🌺🌼🌼🌼መልካም በዓል መልካም ዘመን መልካም ሥራ...🌸🌸🌸🌺

🌻01-01-2017 ዓ.ም🌻

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

17 Jul, 16:52


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
➥ቀሳውስት ከሹመት የሚሻሩበት ሥርዐት
በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ሊጠብቀው የታዘዘውን የማይጠብቅ፤ እንዳይሠራው የተከለከለውን የሚሠራ፤ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ሕዝቡን የማያስተምር የማይመራ ቄስ ቢኖር ከክህነቱ ይሻራል። (ፍት.መን.አን.6 ክፍል 51)
ሁለት ጊዜ የተሾመ፤ ሁለት ጊዜ ያገባ ወይም ሁለት ሚስት ያለው፤ ሕዝቡን የማያስተምር፤ የተቸገሩትን ካህናት የማይረዳ፤ ጉቦ ሰጥቶ የተሾመ፤ የኃጢአተኛውን ንስሐ የማይቀበል፤ በሐሰት የሚመሰክር፤ ሰውን የሚያጣላ፤ የሚኮራ፤ የክፋትን ሥራ የሚሠራ፤ የሚሠክር፤ ኮከብ የሚቆጥር፤ አራጣ/ወለድ የሚቀበል፤ በሐሰት የሚምል፤ የጠንቋዮችን ነገር እውነት ነው ብሎ የሚቀበል፤ ከሴሰኛ ሴት የደረሰ፤ ሥር የማሰ፤ ቅጠል የበጠሰ፤ ሰውን የሚመታ፤ ከመናፍቃን የተጠመቀ፤ የሰረቀ፤ የመናፍቃንን ቁርባን የተቀበለ፤ አብሮአቸው የጸለየ፤ አባለ ዘሩን የሰለበ፤ ሲሰስን፣ በሐሰት ሲምል የተገኘ፤ በገብያ መካከል የሚበላ፤ የአይሁድን ትራፊ የሚበላ፤ ከአይሁድ ምኩራብ፣ ከዐላውያን ቤተ ክርስቲያን የሚበላ፤ የአይሁድን ጾም የሚጾም፤ በዓላቸውን የሚያከብር የበዓላቸውን እጅ መንሻ የሚወስድ፤ ሃይማኖታቸውን ወደ ለወጡ ሰዎች ቤተክርስቲያን እጅ መንሻ የሚወስድ፤ ከተወገዘ ሰው ጋር የተነጋገረ፤ አብሮ የጸለየ፤ የኤጲስ ቆጶሱን ደብዳቤ ሳይዝ ሩቅ አገር የሄደ፤ በአገልግሎት ምክኒያት ሚስቱን የተለየና የፈታ፤እመነኩሳለሁ ተባሕትዎ እይዛለሁ ብሎ ሚስቱን የተወ ወይም ያሰናበተ ካህን ከሹመቱ ይሻራል። (ፍት.ነገ.አን.6 ክፍ 5 / 2 ቀሌ 3 / 3 ኛ ቀሌ 5)
ቄስም ሆነ ዲያቆን በሹመቱ በኃጢአት ከተሻረ በኋላ ደፍሮ ለአገልግሎት ቢገባ ከቤተ ክርስቲያን ተወግዞ ከምዕመናን ይለያል። እያወቁ በዚህ ደፍረቱ የተባበሩት ሁሉ ከምእመናን ይለያሉ። (ፍት.ነገ. 6 / ረስጠብ (2 ቀሌ) 19 / ጾክ 4)
ቄስ ወይም ዲያቆን በሀገሩ የተሾመውን ኤጲስ ቆጶስ ንቆ አቃልሎ ለብቻው ቤተ ክርስቲያን ከሠራ ኤጲስ ቆጶሱ እስከ ሦስት ጊዜ ጠርቶት ካልመጣ እሱና የመሳሰሉት ከሹመታቸው ይሻራሉ። (ፍት.መን.6 / ረስጠብ (ቀሌ)*22)
ቄስ ያለበትን ቤተክርስቲያን ትቶ የሚያገለግለው ሳይኖር ሕዝቡ እየማለደው ሳይሰናበት ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ከሔደ፤ እንዲመለስ ተነግሮት ካልተመለሰ ከሹመቱ ይሻራል። (ፍት.ነገ.6 / ረስጠብ (ቀሌ) 14 ኒቅያ 4፥4)
ቄስ በቁጣ ወይም በማናቸውም ምክኒያት ምዕመናንን ሥጋ ወደሙን ከከለከለ ከስልጣኑ ይሻራል። (ፍት.መን.አን.6 ክፍል 5 / ኒቅያ 27)
ቀሳውስትና ዲያቆናት በሥጋዊ ነገር ዋስ፣ ተያዥ፣ ምስክር አይሆኑም ይህን ያደረገ ከሹመቱ ይሻራል። (ፍት.መን.6 ክፍል 5 / ኒቅያ 28)
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> ፫ #ኤጲስ ቆጶስ
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ➊➋❼

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

14 Jul, 20:52


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
➥ትእዛዘ ቀሳውስት
ቄስ ምእመናንን መጠበቅና ሲታመሙ መጠየቅ፣ በትምህርት ማጽናት እንደሚገባው ታዝዟል፡፡ እውነተኛ : ፍርድ መፍረድ ይገባዋል (ፍት.መን. አን 6 ክፍል 4)
በመሠዊያው ቀኝ የሚቆሙ ቀሳውስት ካህናቱን ያስተባብራሉ፡፡ ሥጋ ወደሙ የሚቀበሉትን በየተራቸው እንዲቀበሉ ይቆጣጠራሉ። በግራ የሚቆሙ ቀሳውስት ሕዝቡን ያስተናብራሉ። (ፍት.መን.አን.6 ክፍል 4)
ቀሳውስት ሐዋርያት አሠሩት ሥርዓት ውጭ ትእዛዝ በማክበድ ሕዝቡን እንዳያስጨንቁ ታዝዟል፡፡ (ፍት.መን.6 ፤ በስ 51)
ቄስ ታሞ በሚመረመርበት፣ በሚታከምበት ጊዜ ከአልሆነ በስተቀር በማንም ጊዜ ፈጽሞ ዕርቃኑን ሊጥልና ሊጋለጥ አይገባውም። (ፍት.መን.አን 6 ፤ ክፍል 4 በስ 53)
ቀሳውስት ከኤጲስ ቆጶሱ ዘንድ በየዓመቱ ፫ ጊዜ እንዲሰበሰቡ ታዝዟል። (ፍት.መን. አን. 6 ክፍል 4 ኒቅያ 59::
ካህናት የራስ ጠጉራቸውን ማሳደግና ማጎፈር አይገባቸውም፡፡
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> ➥ቀሳውስት ከሹመታቸው የሚሻሩበት ሁኔታ
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ➊➋➏

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

12 Jul, 19:45


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
➥ሢመተ ቅስና
ኤጲስ ቆጶስ በአንብሮተ እድ ይሾመዋል ቀሳውስት ቆመው ይዳስሱታል ይጸልዩለታ፡፡ ቄስ፣ ዲያቆን፣ ንፍቅ ዲያቆንና ከዚያ በታች ያሉት የሚሾሙት በኤጲስ ቆጶስ ብቻ ነው፤ ኢጲስ ቆጶሱ እነዚህን ሲሾም የመዓርጋቸውንና የሥርዓተ ነህነታቸውን ደረጃ ጠብቆ በሕዝብ ፊት ጸሎተ ሢመቱን አድርሶ ይሾማቸዋል። (ፍት.መን.አን. 1 ክፍል 2 ፤ ረስጣ 2፥24)

ኤጲስ ቆጶስ ሳይፈቅድ ቄስና ዲያቆን አይሾምም፡፡ “ወኢይሠየም ቀሲስ አው ዲያቆን ዘእንበለ በምክረ ኤጲስ ቆጶስ መዓርጊሁ ዘውእቶሙ ታሕተ ሥልጣኑ ወይሢም ኤጲስ ቆጶስ ባሕቲቱ እስመ ሳልሣይ መዓርጊሁ (ፍት.መን.አን. 6 ክፍል 2 ፤ በስ ፲ ፤ ረስጣ 2) እንዲል፡፡

➥የቀሳውስት ተግባርና ሥልጣን
ቄስ መምህር ነው፡፡ መምህር እንደመሆኑ የቀናች ሃይማኖትን ያስተምራል፡፡ እስመ ቀሲስ በአምሳለ መምህር፡ ወይኩኑ ቀሳውስት በኀቤክሙ መምህራነ ለእዕምሮተ እግዚአብሔር (ፍት.መን.አን. 6 ፤ ድስቅ 7) እንዲል፡፡
ቄስ ሥራው ማስተማር፣ ማጥመቅ ቀድሶ ማቁረብ መባረክ ማሠርና መፍታት መናዘዝ ነው፡፡ (ፍት.መን.አን.6 ፤ ክፍል 3)
ቄስ በአንብሮተ እድ ሕዝቡን ይባርካል፡፡ “ወይባርክ ወኢይትባረክ እምዘ ውእቱ ይንእስ (ፍት.መን.አን. 6 ረስጣ 28)
ቄስ ሥልጣነ ክህነት አይሾምም አይሽርም፡፡ (ፍት.መን.6 ክፍል 3)
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> ➥ትእዛዛተ ቀሳውስት
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ➊➋➎

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

12 Jul, 04:52


🍃የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ታሪክ ባጭሩ🍃

አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡

🍃ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡

🍃በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ፡፡
አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም

🍃በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው <ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን> ብለው አመስግነዋል።

🍃በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡
🍃በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡
🍃መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡

ለፅንሰትከ ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በብሥራተ መልአክ ለተፀነስነከው መፀነስና በወርኃ ታኀሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ።
🍃ክቡሩ አባት ሆይ ስለ ዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደገበረ፤ እኔም ፍጹም ልባዊ የእጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ።
🍃ለተኃፅኖትከ፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለ አደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ።

የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከትታቸው አይለየን አሜን
ወስብሓት ለእግዚአብሔር🙏

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

11 Jul, 21:08


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
➥ለቅስና ሹመት የሚያበቁ ሁኔታዎች
ለቅስና የሚመረጥ ዲያቆን ነውርና ነቀፋ የሌለበት፣ አንዲት ድንግል ሴት ያገባ፣ ደጎች ልጆች ያሉት፣ ቂመኛ ያልሆነ፣ አብዝቶ የማይጠጣ፣ እጁን ለመማታት አንደበቱን ለመገዘት የማያፈጥን፣ ገንዘብ የማይወድ፣ እንግዳ የሚቀበል፣ በጎ ሥራን የሚያፈቅር፣ ከኃጢአት የነጻ፣ ደግና ቸር የሆነ፣ ሰውነቱን ከፍትወት የገታ፣ ወንጌል በማስተማር ምእመናንን የሚረዳ፣ እውነተኛ ትምህርት በማስተማር ሰውን ማጽናናት የሚቻለው፣ ክደው ሊያስክዱ የሚተናኮሉትን የሚከራከራቸው መሆን እንዳለበት ሥርዓት ተሠርቷል። (ፍት.መን.አን.7 ክፍል 1 ፤ ዘሌ 21፥7-16)

ሠላሳ ዓመት ያልሞላው እንዳይሾም ተከልክሏል፡፡ ኢይሠየም ቀሲስ ዘእንበለ በ፴ ዓመት (ፍት.መን.6 ቀጠግ 11)

ብሉያትን ሐዲሳትን ያልተማረ፡ ይልቁንም አራቱን ወንጌል ያላወቀ ቅስና እንዳይሾም ተከልክሏል። <ወኢይኩን አሐዱሂ ቀሲስ ዘኢየአምር ነገረ መጻሕፍት አምላካውያት ሠናያት (ፍት.መን አን 6 ፤ በስ 89)

ለቅስና መብቃቱ ያልተመሰከረለት ቅስና አይሾምም፡፡ <ወኢይኩን አሐዱሂ ቀሲስ ዘኢተንእደ በስምዐ ሐምስቱ ዕደው> (ፍት.መን.አን 6 ፤ በስ 47)

የካህናት አብነታቸው <ሊቀ ካህናት> የተባለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ እጅግ ሰላማውያን ከሰዎች የማይጋጩ ሊሆኑ ይገባል፡፡ <አይከራከርም አይጮኸምም፣ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም፡፡ ፍርድን ድል ለመንሳት እስኪያወጣ፤ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርን አያጠፋም፡፡> ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ የተነገረው ምንም እንኳን ለጌታችን ቢሆንም አሠረ ፍኖቱን የተከተሉ ካህናትም እንዲሁ ሰላማውያን መሆን እንዳለባቸው ያስተምረናል፡፡ (ኢሳ.42፥1-4 ፤ ማቴ 12፥18-21)

ካህን የሚለው የተጸውዖ ስም ሳይሆን የወል ስም በመሆኑ ቀሳውስትንና ኤጲስ ቆጶሳትን የሚወክል ሲሆን በምእመኑ ዘንድ ግን <ካህን> ማለት <ቄስ> እንደማለት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ቅስና ለክህነት እጅግ አስፈላጊው የክህነት ደረጃ ነው፡፡ ቄስ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ሆኖ ለማስታረቅ፣ ለማስተማር የተሾመ ነው፡፡ ሕዝቡንም የሃይማኖትን ትምህርት ገልጦ በማስተማር በሕገ እግዚአብሔር በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖሩ ይመራል፡፡ <ካህኑ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ ዕውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፡፡ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል፡፡ > ተብሎ በነቢዩ መነገሩም ይህንኑ ያረጋግጥልናል። (ሚል 2፥7)
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> ➥ሢመተ ቅስና
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ➊➋❹

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

09 Jul, 19:44


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
፪. #ቅስና
ቅስና ሙያው ሲሆን ባለመዓርጉ ቄስ ይባላል፡፡ በግእዙ ቀሲስ ይለዋል፡፡ ይህም ካሺሾ (Kashisho) ከሚለው የሶርያውያን ቃል ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ታላቅ (Elder) ማለት ነው፡፡ በእንግሊዝኛው ፕሪስት (Priest) ሲለው ግሪኮች ኤፕሬስቫቴሮስ (Epresvateros) ይሉታል፡፡ በሁሉም ትርጓሜው ታላቅ ሽማግሌ እንደ ማለት ሲሆን በግዕዙም አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ይህም የተባለበት ምክንያት ዕድሜው የሸመገለ በመሆኑ ሳይሆን የተሠጠው ሓላፊነትና ግብሩም የታላቅ፣ የሽማግሌ ከመሆኑ በተጨማሪ ሕዝቡን ለማገልገል የተሾመ በመሆኑ ነው፡፡

መሠረቱ የብሉይ ኪዳን ክህነት ሲሆን በሐዲስ ኪዳን በጌታችን ሐዋርያትን መሾም ፍጹም ሆኗል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያት በመልእክታቸው ደጋግመው ያነሡት፡፡ ሐዋ.10፡23 ፤ ቲቶ 1፥5 ፤ ያዕቆብ 1፥10)
ቅስና ከፍተኛ መዓርግ በመሆኑ ኤጲስ ቆጶሳት ብቻ ከሚሰጡት ሥልጣን (ሹመት) በስተቀር የተቀሩትን ምሥጢራት ሁሉ ለመፈጸም ሙሉ ሥልጣን አለው፡፡ ለቅስና መዓርግ የሚመረጠው ከበሰሉ ዲያቆናት መካከል ነው፡፡
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> ➥ለቅስና ሹመት የሚያበቁ ሁኔታዎች
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ➊➋❸

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

08 Jul, 18:11


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#የዲያቆናውያት_ሢመት_ሥርዓት (የሴቶች)
➥ለዲያቆናዊትነት ሢመት የሚያበቁ ሁኔታዎች
ሀ/ በልባቸው ከኃጢአት የነጹ
ለ/ ለበጎ ሥራ የነቁ
ሐ/ በሥራው ሁሉ የሚታመኑ
መ/ ነገር የማይሠሩ
ሠ/ 60 ዓመት የሞላቸው
ረ/ በአንድ ወንድ ጸንተው የኖሩ
ሰ/ ልጆቻቸውን በሥርዓት ያሳደጉ
ሸ/ እንግዳ የሚቀበሉ
ቀ/ የቅዱሳንን እግር የሚያጥቡ
በ/ በደዌ ችግር ለተጨነቁት የሚራሩ
ተ/ በበጎ ሥራ ሁሉ ጸንተው የኖሩ፤
በበጎ ሥራ ጸንተው ለመኖራቸው የተመሠከረላቸው ሴቶች ዲያቆናዊትነት ይሾማሉ። (ፍት.መን.አን 8 ክፍል 1 ፤ ድስቅ 17 ፤ 1ኛ ጢሞ 5፥9-10)

➥ሥርዓተ ሢመት ዲያቆናውያት
ዲያቆናውያት በአንብሮተ እድ አይሾሙም። የሚሾሙት በቃል ብቻ ነው። (ፍት.መን.አን 8 ክፍል 1 ፤ ድስቅ 17)

➥የዲያቆናውያት ሥራ
ዲያቆናውያት የሚሾሙት ከኤጲስ ቆጶሱ ወደ ሴቶች ለመላክ፤ የሚጠመቁትን ሴቶች ከአንገት በታች ቅብአ ቅዱሱን፣ ሜሮኑን እንዲቀቡ በጠቅላላ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ሴቶች ሊፈጽሙት የሚገባውን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲፈጽሙ ነው። (ፍት.መን.አን 8 ክፍል 1 ፤ ድስቅ 17 ረስታ 59)
ዲያቆናውያት ሴቶች አይባርኩም፤ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሠሩትን የክህነት ሥራ አይሠሩም፤ ሲቶች የሚገቡበትን በር ብቻ ይጠብቃሉ። (ፍት.መን. 8 ክፍል 8 ፤ ረስጣ 59)
ዲያቆናውያት በሕዝቡ ዘንድ ክብር አላቸው። <ወትኩን ዲያቆናዊት ክብርተ በኀቤክሙ> (ፍት.መን.አን 8)
ዲያቆናውያት እንደ ዲያቆናት <ተንሥኡ ጸልዩ> እያሉ ጸሎት አያዝዙም ፤ ዲያቆን ሳያዝዛቸው ምንም ነገር አይሠሩም። (ፍት.መን.አን 8 ክፍል 3 በደስ 6)
ስለማናቸውም ጉዳይ ለማነጋገር አንዲት ሴት ዲያቆናዊትን ሳትይዝ ብቻዋን ወደ ዲያቆን ወይም ወደ ኤጲስ ቆጶስ መሄድ አይገባትም፤ ክልክል ነው። (ፍት.መን.አን 8 ክፍል 3 በደስ 34)
ዲያቆናውያት ቅስና አይሾሙም፤ ቄስ አይባሉም በቤተክርስቲያንም የማኅበር ጸሎት ጀማሪ፣ ፈጻሚ አይሆኑም።
ዲያቆናውያት ቃላቸውን ከፍ አድርገው ጮኸው አይጸልዩም <ወኢይጸልያ በልዑል ቃል> (ፍት መን.አን. 8 ክፍል 3 ጾክ 11)
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> ቅስና
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ➊➋➋

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

08 Jul, 06:47


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
፮. ሊቀ ዲያቆን
የቃሉ ትርጉም <የዲያቆናት አለቃ> እንደ ማለት ነው። በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት አርክ ዲያኮን (Arch Deacom) ይባላል። አርክ (Arch) ማለት በግሪክ (ጽርዕ) ቋንቋ መሪ ማለት ነው:: በጥምር አርክ ዲያኮን (Arch Deacon) <የዲያቆን መሪ> ወይም አለቃ ማለት ነው::

በዚህ መዓርግ የተጠራ የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነው፡፡ (ሐዋ 6፥8)

በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ዕድሜው ከ28 ዓመት ያልበለጠውን ይሾሙታል፡፡ በእኛ ቤተ ክርስቲያን ግን የዕድሜ ገደብ አልተቀመጠለትም። ዋና ሥራቸው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን መንፈሳዊ አገልግሎት ማስተባበር፣ ዲያቆናትን ለአገልግሎት መመደብ፣ መቆጣጠርን የመሰለ ነው፡፡

በቤተክርስቲያናችን ግን ከሚያገለግሉት ዲያቆናት መካከል አንዱ ተመርጦ ይሰየማል፡፡ እንዲያውም አልፎ አልፎ ካህናት (ቀሳውስት) በሊቀ ዲቁና ሲያገለግሉ ይታያል፡፡
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> የዲያቆናውያት ሢመት ሥርዓት
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ➊➋➊

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

06 Jul, 19:16


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
ዲያቆን ከማዕረጉ የሚሻርበት ምክኒያት፦
፩. ጉቦ ሰጥቶ፣ ወይም በጉልበት አስገድዶና አስፈራርቶ ወይም ይህን በመሰለ ሌላ ተንኮል የተሾመ፣ ወይም ሁለት ጊዜ የተሾመ፡፡

፪. ሁለት ሴት ያገባ፣ ወይም በተሾመ ጊዜ ከሴት ርቄ ንጽሕ ጠብቄ እኖራለሁ ብሎ ተስሎ ከተሾመ በኋላ ስዕለቱን አፍርሶ፣ ሚስት ያገባ፣ ወይም ከዘማዊት ሴት የደረሰ፣ ወይም ተደብቆ ተክሊል ያደረሰ፣ ወይም እመነኩሳለሁ ብሎ ሚስቱን የፈታ፡፡

፫. ዘወትር የሚሰክር፣ በክፉ ሥራ ጸንቶ የሚኖር፣ በሐሰት የሚመሰክር፡፡

፬. አራጣ የሚቀበል ነጋዴ የሆነ

፭. ባልንጀራውን የሚያማ

፮. በሰው የሚታበይ፣ ኃይልን የሚያሳይ፣ ሰውን የሚመታ፣ ኤጲስ ቆጶስ ሳይፈቅድለት የመነኮሰ፣ ኤጲስ ቆጶሱን የናቀና ያቃለለ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ጠርቶት አልመጣም ብሎ የቀረ፣ ከደሟ ያልነጻችውን ሴት ወደ ቤተ ክርስቲያን ያስገባ፣ ሥጋውን ደሙን እንድትቀበል ያደረገ፣ ከተሻረ በኋላ የክህነት ሥራ የሚሠራ፣ ለብቻው ሌላ ቤተ ክርስቲያን የሠራ።

፯. ቤተ ክርስቲያን ትቶ ከሔደ በኋላ የተመለሰ፣ ከመናፍቃን የተጠመቀ፣ ቁርባናቸውን የተቀበለ፣ ከመናፍቃን ጋር የጸለየ፣ ቤተ ክርስቲያኑን ትቶ ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን የሔደ፣ ወታደር የሆነ ከዲቁናው መዓርግ ይሻራል። (ፍት.መ.አን 7 ፤ ክፍል 5/
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> ሊቀ ዲያቆን
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ➊➋⓪

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

05 Jul, 18:44


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
➥የዲያቆናት ሥራ፦
ዲያቆናት እንደ ኤጲስ ቆጶስ ያለ ነውር ያለ ነቀፋ መኖር አለባቸው። (ፍት.መን.አን 7 ክፍል 3 ፤ ስድቅ 37)
ዲያቆናት መልካም ሥራን በመዓልትም በሌሊትም ሁሉ የሚሠሩ መሆን ይገባቸዋል። (ፍት.መን.አን 7 ክፍል 4 ፤ ረስጣ 18)
የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደመሆናቸው ለኤጲስ ቆጶሱና ለቄሱ ይላላካሉ። (ፍት.መን.አን 7 ፤ በደ 5)
ሕሙማንን መጎብኘት የችግረኞችን ጉዳይ ወደ ቄሱ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ በማቅረብ፣ ለችግረኞች ምጽዋት የሚሰጡትን ምእመናንን ሁሉ በማስተባበርና በመላላክ እንዲያገለግል ታዟል። (ፍት.መን.አን 7 ክፍል 3)
በምሥራቅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆናት ወንጌል ያነብባሉ ፤ በእኛ ቤተክርስቲያን ግን አያነቡም። በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ግን ዲያቆን ወንጌል እንዳያነብ አይከልከልም። (ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀ 12)
በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ሕዝቡ ሥርዓት ይዘው እንዲቆሙና እንዲጸልዩ፣ እንዳያንቀላፉና እንዳይዘብቱ፣ እንዳይስቁና እንዳይሳለቁ ይቆጣጠራል። (ፍት.መን.አን 12 ፤ ድሰቅ 12)
በሥርዓተ ቅዱስ ቁርባን ጊዜ ከካህኑ ጎን ቆሞ ደሙን ያቀብላል። (ፍት.መን.አን 12 ፤ ድሰቅ 12)
ቆሞሱና ሊቀ ዲያቆናቱ ለኤጲስ ቆጶሱ እንደ ሁለት እጆችና እንደ ሁለት ክንፎች ሆነው ሹመት በሚሰጥበት ጊዜ በቀኙና በግራው ይቆማሉ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔድ አብረው ይሔዳሉ።
ወደ ሌላም ቦታ ለአገልግሎት ሲሔድ አይለዩትም። ሊቀ ዲያቆን በቀኙ ሌሎች በግራው ሆነው ያጅቡታል። (ፍት መን.አን. 7 እና 12)
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> ዲያቆን ከማዕረጉ የሚሻርበት ምክኒያት
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ❶❶❾

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

04 Jul, 20:49


"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
፭. #ዲያቆን
ሥርው ቃሉ ዲያኮንያ (Diakonia) የሚለው የግሪኮች ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ረዳት፣ አገልጋይ ማለት መሆኑን ቀደም ብለን ተመልክተናል። በቅብጥ ዲያቆን (Diacon) በሶርያውያን ዲያኮን (Deacon) ይባላል። ትርጓሜው ግን ለውጥ የለውም።

➥ለሹመት የሚያበቁ ምክኒያቶች፦
◆ከዚህ ሹመት በፊት የነበረውን የአገልግሎት ጊዜ በመልካም ሁኔታ ተፈትኖ ያለፈ። (1ኛ ጢሞ 3፥10)
◆ጭምት፣ ቃሉ የማይለወጥ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጅ የሆነ (ጢሞ 3፥10)
◆በንግግሩ፣ በአመለካከቱ፣ በፍቅር፣ በንጽሕና እና በመንፈሳዊ ሕይወቱ ለሌሎች ምሳሌ አርአያ የሆነ
◆ትሑት ሕሊና ያለው፣ ለገንዘብ የማይስገበገብ አገልግሎቱን ያለማንጎራጎር በትዕግስት የሚሸከምና የማያዳላ
◆መጽሐፍትን ለማንበብ የሚተጋና በመንፈሳዊ ሕይወቱ የሚያድግ
◆ቸርነቱ፣ ታማኝነቱ፣ ፍቅሩና ሰላማዊነቱ በሌሎች የተመሠከረለት
◆በምዕመናን "ለሹመት ብቁ ነው" ተብሎ የተመረጠ።
ከላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶች የተሟሉ ከሆኑ "ዲያቆን" ተብሎ እንዲሾም ይፈቀዳል። (ፍት ነገ 7፣ ረሥጣ 17፣ ፍት. መን. አን. 6 ክፍል 1)

➥ሢመተ ዲቁና፦
◆እስስካሁን ያየናቸው ሹመቶች በሙሉ የተሰጡት በቃል ብቻ ነበር እንጂ በአንብሮተ ዕድ አልነበረም። ዲቁና ግን ከበፊቶቹ ሁሉ ከፍ ያለው ማዕርግ በመሆኑ ሢመቱ በኤጲስ ቆጶሱ አንብሮተ እድ ይፈጸማል።
◆"ዲያቆን 25 ዓመት ሳይሞላው አይሾምም" ይላል። (አን. መን. አን 7 ክፍል 2፤ ቀጠግ 11) ይሁን እንጂ ብቁ ሁኖ ከተገኘ ከዚህ እድሜ በታችም ያለ ቢሆን ይሾማል። የዲያቆናቱ ቁጥር በቤተ ክርስቲያኑ ሰበካ ስፋትና ጥበት ይወሰናል። (አን. መን. አን 7፤ ቀጠግ 14፤ ኒቅያ 67)
◆የዲቁና ማዕረግ የሚሰጣቸው ከጋብቻ በፊት ነው። በኋላም በተክሊል አግብቶ የቅስና ማዕረግ ይቀበላል። ዲቁናውን እንደተቀበለ ለመመንኮስ ሲፈልግ ግን ገዳም ገብቶ ይመነኩስና የቅስና ማዕረግ ይቀበላል። (1ኛ ጢሞ 3፥2-4፣ 12፤ የሐዋርያት ቀኖና 4፤ የስድስተኛው ሲኖዶስ ቀኖና 13)
◆ከጋብቻ ውጭ ግን ለካህናት ከሴት ጋር መኖር ለውድቀት ነው። "ኤጲስ ቆጶስ፣ ካህን፣ ዲያቆን ከሴት ጋር አይኑር ዘመዱም ብትሆን" (ትእ 2) እንዳለ።
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

✍️@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን--> የዲያቆናት ሕይወትና ሥርዓት እና ከማዕረጉ የሚሻርበት ምክኒያት
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐

ገፅ ❶❶❽

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

04 Jul, 20:41


ሰላም እንዴት ናችሁ የተዋህዶ ፍሬዎች?

ለብዙ ጊዜ ሥለጠፋን በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን

በየቀኑ ኮርሱችን ለመልቀቅ እስኪመቸን ከመንጠብቅ በሚመቸን ቀን ብቻ እየለቀቅን ለመቀጠል ስለወሰን ከዛሬ ጀምሮ መልቅ እንጀምራለን።


ያቋረጥን ከዚህ👇👇👇 ላይ ነበር
t.me/Tewahdo_Haymanotie/768

በጸሎታችሁ አስቡን

መልካም ጥናት📖

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

28 Jun, 07:13


@Tewahdo_Haymanotie
@Tewahdo_Haymanotie
@Tewahdo_Haymanotie

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

28 Jun, 07:13


#ጌታችን_በሰኔ_20_ተገልጦ_ሐዋሪያቱን_ሰብስቦ_በስሟ_ቤተ_ክርስቲያን_ከሰራላት_በኋላ_በቀጣዩ_ቀን_በ21_ቅዳሴ_ቤቷን_ያከበረበት_ቀን_ነው

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችኹ 🙏🙏🙏

በዚኽች ቀን በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች::

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይኹንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" (አሕዛብን ኹሉ ሒዱና አስተምሩ) /ማቴ. ፳፰:፲፱/ ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::

የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. ፮:፶፮) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::

በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲኽ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲኼድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ::

በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚኽ ምክንያት መምህራን ሕዝቡን "ካመናችኹ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችኹ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደኾን የለን" ሲሉ መለሱላቸው::

ነገሩ ከደጋጎቹ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም?" አሉ:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይኾንም" አለ:: (ለዚኽ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን የማይታነጸው::)

ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ኼደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መኾኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ::

በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ኹሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ::

ኹሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው::

እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ ጌታችን ቆሞለት ሐዋርያትም እየተራዱት ግርምት የምትኾን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ፶፪ ዓ.ም. በዛሬዋ ቀን አንጿል:: 🙏🙏🙏

አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር - የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ - የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን 🤲🤲🤲 አሜን🙏

@Tewahdo_Haymanotie
@Tewahdo_Haymanotie
@Tewahdo_Haymanotie

የተዋህዶ ቤተሰቦች ኮርስ መስጫ

22 Jun, 17:04


12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና በእንተ እግዝእትነ ማርያም።

በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት የኃጥያት ማሠሪያ ይፍታችሁ ሁኑ ሲል ፲፪ [12] ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና ፲፪ [12] ደግሞ በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላል። ካህናትና ምዕመናን በሙሉ በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህንኑ ፲፪ [12] ጊዜ እንላለን።

እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት፦ አቤቱ ክርሰቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርሰቶስ ማረን ማለት ነው።

አስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሌሊቱ 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሠራነው ኃጥያት ለሃያአራቱ ፳፬ [24ቱ] ሰዓት ምሕረትን እናገኝ ዘንድ ነው።

ሌላው አሥራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት ፦

➥፩ኛ. በስመ ሥላሴ ነው። በእያንዳንዱ ፊደል
አ ብ ወ ል ድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

➥፪ኛ. የድኃነታችን ምክንያት በሆነችው በእመቤታችን ስም ፊደል
ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

አቆጣጠሩም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደታች ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት [በትንሿ] ጣት ወደላይ ነው።

➥ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች፦ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን።

➥መሐል ጣት ወደላይ፦ ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን

➥በቀለበት ጣት ወደታች ስንቆጥር፦ ለፍርድ መምጣቱን

በትንሿ ጣት ወደላይ ስንወጣ፦ ደግሞ ሁላችንን በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው።


በእንተ እግዝእትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ፦ ከትንሽ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደላይ ይፈፀማል። ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳየን ምስጢር ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
@Tewahdo_Haymanotie