የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ @gibigubae Channel on Telegram

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

@gibigubae


Contact= +251901629875
✍️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ
✍️ የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ መጽሐፍት
✍️ አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች
✍️ ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ
✍️ ወቅታዊ መረጃዎች
✍️ ስብከቶችን የሚያቀርብበት ገፅ ነው፡፡
በመርሐግብሩ ላይ አስተያየት ፥ ሐሳብ ፥ ጥያቄ ካለዎት ይጻፉልን @gibigubae_hasab_bot

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ (Amharic)

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ መጽሐፍትን መጠበቅ ያዙ ወይም ሐሳብን ለመማር ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ ትምህርቶችን ይጠቀሙ! በበመርሐግብሩ ላይ በሚያቀርብበት ገፅ በተለያዩ ስብከቶች እና መረጃዎች ይቀበሉ። ስለጎን እና ጥያቄዎች መልስን የግፍ መመዝገብ ይጠቀሙ። በትምህርቶችና የመጽሐፍት ወሬዎች የሚከተለው ይህ ግቢ ጉባኤ በ@gibigubae_hasab_bot ገብቻ ለመጠፋት ለእኛ የሚያደርግልን።

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

07 Dec, 16:59


ኅዳር 29

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ የምሩቃን መርሐ ግብር

ሁሉም የግቢ ጉባኤው ምሩቅ የሆነ ሁሉ የሚሳተፍበት ልዩ የአንድነት ጉባኤ ነው።

▫️በዕለቱ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ይካሔዳሉ።

በጉባኤው እንዲገኙ መንፈሳዊ ጥሪያችንን አቅርበንልዎታል!

🏷ቦታ፦ ቃሊቲ ካፍደም ሕንፃ ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ት/ቤት ውስጥ
🏷ሰዓት፦ ከቀኑ 7:30

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ከግቢ ጉባኤው ጋር በመተባበር።

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

07 Dec, 15:14


https://t.me/QuizBot?start=Ho9GCDGo

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

06 Dec, 18:46


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «»

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

05 Dec, 06:55


Channel photo updated

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

05 Dec, 03:01


እናስተዋውቃችሁ – Telegraph

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

04 Dec, 14:36


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «»

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

04 Dec, 14:36


Channel photo updated

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

04 Dec, 09:55




            3 ቀን ቀረው



ቲኬት ማግኘት የሚችሉባቸው ቦታዎች:-
         👉 ኮፒ ቤት
         👉 የክፍላት ተጠሪዎች ጋር
         👉 የሴክሽን ተወካዮች
        👉 ረቡዕ ጉባኤ ላይ
         👉 የኮርስ ቀን

የጉዞ ቲኬት በአካል ተገኝተው መቁረጥ ካልቻሉ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ።

ቴሌብር:- 0960148019
ንግድ ባንክ:- 1000289849711

የከፈሉበትን ማረጋገጫ በዚህ @Guzoo_ticket_bot ይላኩልን።
▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

03 Dec, 06:30


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ አራት በዚህች ቀን የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው ፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር ያጠኑበት ነው ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

02 Dec, 19:11


ኅዳር 29

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ የምሩቃን መርሐ ግብር

ሁሉም የግቢ ጉባኤው ምሩቅ የሆነ ሁሉ የሚሳተፍበት ልዩ የአንድነት ጉባኤ ነው።

▫️በዕለቱ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ይካሔዳሉ።

በጉባኤው እንዲገኙ መንፈሳዊ ጥሪያችንን አቅርበንልዎታል!

🏷ቦታ፦ ቃሊቲ ካፍደም ሕንፃ ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ት/ቤት ውስጥ
🏷ሰዓት፦ ከቀኑ 7:30

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ከግቢ ጉባኤው ጋር በመተባበር።

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

02 Dec, 09:40




5 ቀን ቀረው




የጉዞ ቲኬት በአካል ተገኝተው መቁረጥ ካልቻሉ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ።

ቴሌብር:- 0960148019
ንግድ ባንክ:- 1000289849711

የከፈሉበትን ማረጋገጫ በዚህ @Guzoo_ticket_bot ይላኩልን።
▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

01 Dec, 11:59


🔔🔔🔔🔔🔔 አዋጅ 🔔🔔🔔🔔🔔

እውነት እውነት እላቹሃለሁ ንስሓን ከማይሹ ጻድቃን ይልቅ ንስሐን በሚገባ አንድ ኃጥዕ ሰው በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል:: ሉቃ15:10

ውድ የልዑል_እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ!! እንኳን ለጾመ ነብያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ግቢ ጉባኤያችን ከኅዳር 16 - ታኅሣሥ 05 የንስሐ ሳምንት ማዘጋጀቱን ስንነግራችሁ በታላቅ ደስታ ነው ከእናንተ ሚጠበቀው ንስሐ አባታችሁ ጋር ሄዳችሁ ንስሐ መግባት ፤ ንስሐ አባት ያልተመደበላችሁ ደግሞ ከታች በተጠቀሰው ስልክ ደውላችሁ አሳውቁን በተጨማሪም ይህን መልእክት ለሁሉም እያዳረሳችሁ የሐዋርያነት ኃላፊነታችሁን ተወጡ!!!

የንስሓ ሳምንት:-
ከሕዳር 16 - ታኅሣሥ 05

የንስሐ አባት ከፈለጉ በእነዚህ ስልክ ደውለው አስተባባሪዎችን ማናገር ይችላሉ።

ስልክ:- 0955001943
       :- 0940442282



▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

30 Nov, 08:32



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ኅዳር ፳፩ ቀን የሚከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል ነው

  እንኳን አደረሳችሁ

+ ጽዮን ማርያም +"*+

=>"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::

+እግዚአብሔር ከዘመነ አበው ብኋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች::

+ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት  ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19)

ኅዳር 21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:-

.ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19)

.በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1)

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

30 Nov, 08:32


በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል::

"ሰላም ለኪ ማርያም እምነ::
ዘሰመይናኪ ጸወነ::
ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ::
ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ::
ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21)

.በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1)

.በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል::
👉ኅዳር ፳፩  በተለየ መልኩ የምናከብረው:-

በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ

ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ

በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት

.ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
5.ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ ምሳሌዋን ራዕይ ያየበት

ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት

.አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ

እግዚአብሔር አምላክ በእናቱ በእመቤታችን አማላጅነት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሠውረን፡፡ አሜን!🙏

▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

29 Nov, 18:01


🌿እናስተዋውቃችሁ🌿

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

29 Nov, 08:40




            8 ቀን ቀረው



▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

28 Nov, 19:59


ምስጢሬን ላካፍላችሁ – Telegraph

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

28 Nov, 11:07


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «»

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

28 Nov, 06:50




9 ቀን ቀረው



▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

26 Nov, 08:27


ውድ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ምሩቃን እንዴት ከረማችሁ? የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ የምሩቃን አባላት መረጃ በማደራጀት ላይ ስለሆንን ይሄን Google Form በኃላፊነት እንዲሞሉ እና ለሌሎች share እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።

https://docs.google.com/forms/d/1m1jnR9UlbEvFDg1JdysUA_TGn70rEzQ-YPmtXl-6sNI/edit

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

25 Nov, 08:01


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ከወዲሁ እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ እያለን። ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ሁሌም በጾም ወቅት ዳቦ የምናወጣ ሲሆን ይህም ለነዳያን መርጃ እንዲሁም የግቢ ጉባኤውን አገልግሎት ለመደገፍ ይውላል።

በመሆኑም ከዚህ በረከት ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ የሆናችሁ ኦርቶዶክሳዊ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሙሉ ካፌ መግቢያ በር ላይ የጾመኞች ምዝገባ ስለሚኖር ይህንን አውቃችሁ እንድትመጡ ስንል መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ልብ ይበሉ:- እስከ 6 ሰዓት ጾመኛ ከሆኑ ለቁርስ ካፌ መግባት ወይም ዳቦ ማውጣት አይችሉም፤ የ9 ሰዓት ጾመኛ ከሆኑም እንዲሁ።
ነገር ግን እስከ 9 ሰዓት ለሚጾሙ ብቻ ካፌው 9 ሰዓት ላይ ስለሚከፈት የመግቢያ ቲኬት መያዝ ግድ ይላል።


👉ለምዝገባ ስትመጡ ID በነፃ ኮፒ እያደረጋቹ እንድትመጡ።

ለተጨማሪ መረጃ: 0960148019 ይደውሉ። አሊያም ካፌ በር ላይ የሚመዘግቡትን ልጆች ማናገር ይቻላል።

▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

24 Nov, 18:30


🎲 Quiz 'ይመልሱ_ይሸለሙ'
🖊 12 questions · 1 min

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

24 Nov, 18:26


📣📣📣📣📣📣


ዝግጁ ናችሁ????


▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

24 Nov, 18:17


ሳምንታዊው የ'ይመልሱ ይሸለሙ' ውድድር ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።


ተዘጋጅታችሁ ጠብቁን

▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

24 Nov, 15:02


🔔🔔🔔🔔🔔 አዋጅ 🔔🔔🔔🔔🔔

እውነት እውነት እላቹሃለሁ ንስሓን ከማይሹ ጻድቃን ይልቅ ንስሐን በሚገባ አንድ ኃጥዕ ሰው በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል:: ሉቃ15:10

ውድ የልዑል_እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ!! እንኳን ለጾመ ነብያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ግቢ ጉባኤያችን ከኅዳር 16 - ታኅሣሥ 05 የንስሐ ሳምንት ማዘጋጀቱን ስንነግራችሁ በታላቅ ደስታ ነው ከእናንተ ሚጠበቀው ንስሐ አባታችሁ ጋር ሄዳችሁ ንስሐ መግባት ፤ ንስሐ አባት ያልተመደበላችሁ ደግሞ ከታች በተጠቀሰው ስልክ ደውላችሁ አሳውቁን በተጨማሪም ይህን መልእክት ለሁሉም እያዳረሳችሁ የሐዋርያነት ኃላፊነታችሁን ተወጡ!!!

የንስሓ ሳምንት:-
ከሕዳር 16 - ታኅሣሥ 05

የንስሐ አባት ከፈለጉ በእነዚህ ስልክ ደውለው አስተባባሪዎችን ማናገር ይችላሉ።

ስልክ:- 0955001943
       :- 0940442282



▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

24 Nov, 09:41


💥የበረሓው ሰው መርዩጥ የሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ለመሄድ መንገድ እንደሳቱ ቀድሞ ተረድቶ ነበርና "የማር ሚናስን ገዳም ነው የምትፈልጉት? በማለት ይጠይቃቸዋል። እነርሱም ችግራቸውን እንዴት እንዳወቀ በልባቸው እያደነቁ "አዎን" አሉት። የበረሓው ሰውም እየመራ ከገዳሙ አደረሳቸው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛም ወደ በር ወጥተው ተቀበሏቸው።

💥ከዚያም "ምነው ዘገያችሁ? መንገድ ሳታችሁ እንዴ?" ብለው እንደ ቀልድ ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን! በጣም ተቸግረን ሳለን ይህ የበረሓ ሰው ደርሶልን መንገዱን አሳየን" ብለው ወደ ሰውየው ለማመልከት ዘወር ሲሉ እርሱ በአካባቢው የለም። አቡነ ቄርሎስም "መንገድ እንደጠፋችሁ ስለተረዳሁ ሚናስን ልኬላችሁ ይዟችሁ የመጣው እርሱ ነው" አሏቸው።

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ያካፍለን!!

▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

21 Nov, 22:03


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ከወዲሁ እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ እያለን። ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ሁሌም በጾም ወቅት ዳቦ የምናወጣ ሲሆን ይህም ለነዳያን መርጃ እንዲሁም የግቢ ጉባኤውን አገልግሎት ለመደገፍ ይውላል። በመሆኑም ከዚህ በረከት ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ የሆናችሁ ኦርቶዶክሳዊ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሙሉ ዛሬ…»

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

21 Nov, 17:30


⚜️⚜️ታላቁ ገዳም ደብረ ዳሞ⚜️⚜️

ዙሪያው ፍፁም ተራራ የሆነው ይህ ገዳም ከአክሱም ፅዮን
ቤተክርስቲያን በ፸ ኪ.ሜ ርቀት ላይ በትግራይ ክፍለ ሀገር በአድዋ
አውራጃ ውስጥ ተገድሞ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ
አጅግ አስደናቂ ከሚባሉ ገዳማት አንዱ ሲሆን ወደገዳሙ አናት
ለመውጣት በግምት ከ፳፬ - ፴ ሜ ርዝመት ባለው ገመድ
መጠላጠል ግድ ነው፡፡

⚡️ከመሬት ወለል በላይ ከ፪ሺ ሜ በላይ ከፍታ ያለው ይህ ገዳም
የተመሰረተው ከዘጠኙ ቅዱሳን መካከል አንዱ በሆኑት በአቡነ
አረጋዊ/ ዘሚካኤል/ ሲሆን ለብሕትውና በመረጡት በዚህ ስፍራ
ወደተራራው ለመውጣት በገቡት ሱባኤ እግዚአብሔር አምላክ
ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሚረዝም ዘንዶ ልኮ ዘንዶው
እንዳይተናኮላቸው ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸው ወደ ተራራው
ጫፍ እንደወጡ ገድላቸው ይዘክራል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም የዚህ ዘንዶ
ምሳሌ የሆነው እረጅም እድሜ ያስቆጠረና እስካሁን ለመውጫና
መውረጃ የሚያገለግለው የጠፍር ገመድ ይገኛል፡፡

⚡️በአፄ ገብረመስቀል አማካይነት ከመሬት እስከተራራው ጫፍ
የሚደርስ ደረጃ ተሰርቶ የነበረ ቢሆንም ንጉሱ በእመቤታችን
ድንግል ማርያም ስም በ፮ኛው ክ/ዘ ላሰሩት ህንፃ ቤተክርስቲያን
ግንባታ የሚውሉትን ቁሳቁሶች ለማመላለስ አገልግሎት ላይ
ከዋለና ከቅዱስ ያሬድ ጋር ቤተክርስቲያኗን ከመረቁ በኋላ በአቡነ
አረጋዊ ትዕዛዝ እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት የገዳሙ
ስም “ዳሕምሞ” ብለው በግዕዙ ስላዘዙ /“አፍርሰው” የሚል
ትርጓሜ አለው/ ደረጃውን በማስፈረሳቸው ምክንያት ከጊዜ ብዛት
ዳሞ የሚለውን ቃል ወልዶ ገዳሙ “ደብረዳሞ” በሚል መጠሪያ
እንዲታወቅ ሆኗል፡፡

⚡️የተራራውን ግማሽ በገመድ ተወጥቶ ግማሹን ደግሞ በጠባብ
መሿለኪያዎች ውስጥ ታልፎ ከተራራው አናት ሲደረስ በእጅጉ
የተንጣለለ ሜዳ ላይ ብዙ የረቀቀ ጥበብ የሚታይበትን
ቤተክርስቲያን፣ ከ፻፶ በላይ የውኃ ምንጮች ፣ በሶስት የተከፈሉ
የገዳማውያን መንደሮችና የመቃብር ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡

⚡️በዚህ ገዳም እጅግ የሚደንቀው ነገር እዚህ ሰማይ ጠቀስ
ከሆነው ተራራ ምንጮች በብዛት መኖራቸውና ምንጮቹም
በእያንዳንዳቸው መነኮሳት ቤት ውስጥ መገኘታቸው ሲሆን የበለጠ
የሚያስደንቀው ደግሞ ከዝናም በስተቀር ማንኛውም ከገዳሙ
ውጪ ያለ ውሃ ከተቀላቀላቸው አካባቢውን የሚበክል መጥፎ
ጠረን መሆናቸው ነው፡፡
ሁላችንንም ከገዳሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
  ወለወላዲቱ ድንግል
             ወለመስቀሉ ክቡር
                   ✞ይቆየን✞
በትምህርት ክፍል ትምህርታዊ ጽሑፍ ዝግጅት ንዑስ ክፍል እናስተዋውቃችሁ የቴለግራም መርሐግብር ዝግጅት ክፍል የቀረበ።


▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

20 Nov, 18:26


የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል

▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

20 Nov, 12:54


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ከወዲሁ እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ እያለን። ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ሁሌም በጾም ወቅት ዳቦ የምናወጣ ሲሆን ይህም ለነዳያን መርጃ እንዲሁም የግቢ ጉባኤውን አገልግሎት ለመደገፍ ይውላል።

በመሆኑም ከዚህ በረከት ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ የሆናችሁ ኦርቶዶክሳዊ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሙሉ ዛሬ ከእራት ሰዓት ጀምሮ ካፌ መግቢያ በር ላይ የጾመኞች ምዝገባ ስለሚኖር ይህንን አውቃችሁ እንድትመጡ ስንል መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ልብ ይበሉ:- እስከ 6 ሰዓት ጾመኛ ከሆኑ ለቁርስ ካፌ መግባት ወይም ዳቦ ማውጣት አይችሉም፤ የ9 ሰዓት ጾመኛ ከሆኑም እንዲሁ።
ነገር ግን እስከ 9 ሰዓት ለሚጾሙ ብቻ ካፌው 9 ሰዓት ላይ ስለሚከፈት የመግቢያ ቲኬት መያዝ ግድ ይላል።


👉ለምዝገባ ስትመጡ ID በነፃ ኮፒ እያደረጋቹ መምጣት ትችላላችሁ።

ለተጨማሪ መረጃ: 0960148019 ይደውሉ። አሊያም ካፌ በር ላይ የሚመዘግቡትን ልጆች ማናገር ይቻላል።

▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

20 Nov, 10:51


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «»

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

20 Nov, 05:33


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ዐሥራ አንድ በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።

ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት።

ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት

💠 የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት
💠 ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ
💠 ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት

ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግልማርያምን ያገለገለቻት ናት።

ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ቅዱስ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት።

ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት

ሰሎሜ ፣ኤልሳቤጥ እና ቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

ይህችም ጻድቅ ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።

ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።🙏

(ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_11)
▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

18 Nov, 16:46


ሳምንታዊ የኪነ ጥበብ መርኃ ግብር – Telegraph

▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

18 Nov, 11:52


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «»

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

18 Nov, 08:45


<<<<<<ሰኞ ኅዳር ዘጠኝ>>>>>>>>

         †††      ስንክሳር     †††

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

          †   እንኳን አደረሳችሁ   †

    🕊የቅዱስ አባት ይስሐቅ እረፍት🕊

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ዘጠኝ በዚች ዕለት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አንደኛ የእስክንድርያ አገር ሊቃ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ይስሐቅ አረፈ ። ይህም ቅዱስ ቡርልስ ከሚባል አገር ነው ወላጆቹም እግዚአብሔርን የሚፈሩ እጅግም ባለጸጎች ናቸው ከረጅም ዘመንም በኋላ ይህን ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በታላቅ ደስታ ደስ ተሰኙበት ። ከዚህም በኋላ ያጠምቀው ዘንድ ወደ ኤጲስቆጶስ በአቀረቡት ጊዜ ኤጲስቆጶሱም ሲያጠምቀው በሕፃኑ ራስ ላይ የብርሃን መስቀልን አየ በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን እጅ ይዞ በራሱ ላይ አኖረ ። እንዲህም ብሎ ትንቢት ተናገረለት ይህ ሕፃን በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾማል አባቱንም እንዲህ አለው ይህን ልጅ ጠብቀው እርሱ ለእግዚአብሔር የተመረጠ መሣሪያ ይሆናልና ። ጥቂትም በአደገ ጊዜ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ጽሕፈትን አስተማሩት የቅዱሳንንም ዜና የሚያነብ ሆነ ወላጆቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በአበ ምኔቱ በአባ ዘካርያስም ዘንድ መንኩሶ በገድል ተጠመደ ። በአንዲትም ዕለት አንድ ጻድቅ ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አየው በእርሱም ላይ ይስሐቅ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾም ዘንድ አለው ብሎ ትንቢት ተናገረ ። በዚያም ወራት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ ጸሐፊ የሚሆነውና የሚረዳው ብልህ ሰው ፈለገ ስለ አባ ይስሐቅም ነገሩት እርሱም መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ይጽፍለትም ዘንድ ደብዳቤ ሰጠው እርሱ ግን አባ ይስሐቅ እያወቀ ጽሕፈቱን አበላሽ ሊቀ ጳጳሳቱ እንዲተወውና ወደ አስቄጥስ ገዳም እንዲመለስ ነበር የዚህን ዓለም ክብር ይጠላልና ። ሊቀ ጳጳሳቱም እንዲተወውና እንዲአሰናብተው አውቆ ማበላሸቱን በአወቀ ጊዜ በጥሩ ጽፈሃል ከዚህም እንድትሔድ እኔ አልተውህም አለው አባ ይስሐቅም እንደማይለቀው አውቆ የሚያውቀውን ሁሉ ጥበቡን ያማረ ጽሕፈቱንም ገለጠለት ሊቀ ጳጳሳቱም በእርሱ እጅግ ደስ አለው ። ከጥቂት ወራትም በኋላ አባ ይስሐቅ ወደ አስቄጥስ ገዳም ተመለሰ አባ ዮሐንስም የሚያርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ስለርሱ ሊቀ ጵጵስና የሚሾም ማን እንደሆነ ያስረዳው ዘንድ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ጌታም በራእይ ከአንተ በኋላ ለዚች ሹመት የሚጠቅም ረዳትህ ይስሐቅ ነው አለው ። ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ጠራቸውና ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ የሚሾም ረዳቱ ይስሐቅ እንደሆነ አስረዳቸው ከዚህም በኋላ አባ ዮሐንስ በአረፈ ጊዜ ይህን ቅዱስ አባት ይስሐቅን ይዘው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት በዘመኑም ቤተ ክርስቲያን ብርሃን ሆነች ብዙዎች አብያተ ክርስቲያንንም አደሳቸው ይልቁንም የወንጌላዊ ማርቆስን ቤተ ክርስቲያን አሳምሮ አደሳት የሊቀ ጵጵስናውንም ቤት አደሰ ።ይህንንም አባት ብዙ ችግርና መከራ ደርሶበታል በወንጌላዊ ማርቆስ መንበርም ሰባት ዓመት ተኩል ኑሮ አረፈ ። በዚህም ቅዱስ አባት በመጽሐፈ ገድሉ ከእሑድ ቀን በቀር ሊቀ ጳጳሳት እንዳይሾም የሚያዝ ጽሑፍ አለ ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †


https://t.me/gesem24


▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

17 Nov, 18:00


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ስር በሚገኘው በሙያና በጎ አድራጎት ክፍል የነጻ ሙያ ንዑስ ክፍል ለግቢ ጉባኤ ልጆች ያስፈልጋል ብሎ ያዘጋጀዉን የሁሉንም የAASTU ዲፓርትመቶችን ፋይል በtelegram folder መልክ አዘጋጅቶ አቅርቦላችኋል።
በዚህ telegram folder ውስጥ
👉🏿 ለሁሉም ዲፓርትመቶች የቴሌግራም ግሩፕ አለ 👉🏿ሁሉንም የኮርስ ፋይሎች በየባቹ እንዲሁም በየሴሚስተሩ ማግኘት ይቻላል 👉🏿የቴሌግራም ግሩፑ Reference book, pdf, ppt, worksheet, exam የመሳሰሉትን ይዟል
ከስር ያለዉን link በመንካት ዲፓርትመንታችሁ ግሩፕ ጋር በመግባት ተጠቃሚ ይሁኑ https://t.me/addlist/BrVQ9v5E8NcyNjY0
🦻ከእናንተ ጋር ያሉ ይጠቅማሉ የምትሏቸዉን ፋይሎች በየዲፓርትመንታችሁ share አድርጉ 🙏🙏🙏

▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

04 Nov, 11:11


<<<<<<ሰኞ ጥቅምት ፳፭>>>>>>>

         †††      ስንክሳር     †††

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

          †   እንኳን አደረሳችሁ   †

  🕊 ቅዱስ አባ ቡላ (አቢብ) እርፍት🕊

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ሃያ አምስት በዚች ቀን ታላቅና ክብር የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሐሪክ ነው እነርሱም ከሮሜ አገር ሉፊ ከሚባል አውራጃ ናቸው በዘመናቸውም ከሀዲው ንጉሥ መክስምያኖስ በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራ ስለ አመጣ ስደት ሁኖ ነበርና እነርሱም በስደት ብዙ ዘመን ኖሩ ። ልጅንም በአጡ ጊዜ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ በጾም በጸሎት ተወስነው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም ተገለጠላቸውና ፍሬ የመላበትን ዘለላ ሰጣቸው ። ይህም ቅዱስ በተፀነሰ ጊዜ በቤታቸው አጠገብ ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉም ላይ በሮማይስጥ ቋንቋ ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው የሚል ጽሑፍ ነበረበት ።

በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው እርሱም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው እናትና አባቱም ሳይነግሩት ቡላ ስለ ሰየመው አደነቁ ዕፁብ ዕፁብ አሉ ። ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ በጸለየ ጊዜ የቊርባን ኅብስትና ወይን የተመላ ጽዋ ከሰማይ ወረደ እርሱም ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ከሕፃኑ ጋር አቀበላቸው በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ የአንድ ዓመት ልጅ ሲሆን በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ አብ በግብር በአካል በሰም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ ወልድ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት በአብ ከወልድ ጋር አንድ የሆነ መንፈስ ቅዱስ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ ተናገረ ።

ከጥቂት ዘመንም በኋላ አባትና እናቱ ኅዳር ሰባት ቀን ሙተው ሕፃኑ ብቻውን ቀረ ። ሕፃኑም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለጣዖት መስገድን የሚያዝ ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ቡላም በሰማ ጊዜ ወደ መኰንኑ ሒዶ የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ መኰንኑም በአካል ታናሽነቱን አይቶ እጅግ አደነቀ በዚያንም ጊዜ በችንካር እንዲቸነክሩት ሥጋውንም እንዲሠነጣጥቁት ቆዳውንም ከዐጥንቱ እንዲገፉ እጆቹንና እግሮቹንም በመጋዝ እንዲቆርጡ ጀርባውንም እንዲገርፉ በሾተሎችና በጦሮች መካከል አድርገው ከመንኰርኵር ውስጥ እንዲጨምሩት ዳግመኛም በመንገድ ላይ እንዲጐትቱት አዘዘ የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው ።


ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ መኰንን ሒዶ እርሱንና የረከሱ ጣዖቶቹን ረገመ መኰንኑም ተቆጥቶ በሚያዝያ ወር ዐሥራ ስምንት ቀን ራሱን በሰይፍ ቆረጠው ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ከሙታን ለይቶ አስነሣው ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ የምንኲስና ልብስንና አስኬማን በመስቀልም ምልክት አለበሰው ። እንዲህም አለው ከቅዱሳን ጻድቃን አንድነት ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር አዝዞሃል ። ያን ጊዜም ቅዱስ አባ ቡላ ከደረቅ ተራራ ላይ ወጣ ያለ ማቋረጥም በውስጧ እየተጋደለ ኖረ ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራውንና ስቅለቱን በአሰበ ጊዜ ከረጅም ዕንጨት ላይ በመውጣት ራሱን ወደታች ሁል ጊዜ ይወረውር ነበር ።
በአንዲትም ቀን ከዛፍ ላይ በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን ሊገድለው ስለ በረታበት ሞተ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና መድኃኑታችን ከሞት አነሣውና እንዲህ አለው ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ይባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህና ። እርሱም የክርስቶስን ፍቅር እጅግ ጨመረ ፊቱንም እየጸፋ ሥጋውን በየጥቂቱ እየቆረጠ ጀርባውንም ሰባት መቶ ጊዜ እየገረፈ ኖረ ጌታችንም ይፈውሰው ነበር በየእሑድም ቀን ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም እንደተወለደ በሌሎች ቀኖችም እንደተያዘና ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበለ ሁኖ ይገለጽለት ነበር ። ስለዚህም ሳይበላ ሳይጠጣ አርባ ሁለት ዓመት ኖረ ዳግመኛም ናላው ፈስሶ እስቲአልቅ ዐሥራ ሁለት ወር በራሱ ተተክሎ ኖረ ።

በአንዲትም ቀን የጌታችንን መከራ በአሰበ ጊዜ ሰይፉን በአንጻሩ ተከለ ከዕንጨት ላይም ወጥቶ በላዩ ወድቆ ሞተ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም ከአእላፍ መላእክት ጋር መጥታ የእኔና የልጄ ወዳጅ ሰላምታ ይድረስህ አለችው ። ከበድኑም ቃል ወጥቶ የሰማይና የምድር ንግሥት እመቤቴ ሰላምታ ይገባሻል አላት እርሷም በከበሩ እጆቿ ዳሥሣ ከሞት አስነሣቸው ። ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ ተገለጠለት ወዳጄ አቢብ ሆይ በማያልቅ ተድላ ደስታ ደስ አሰኝህ ዘንድ ወደእኔ ና ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ ኃጢአቱን አስተሠርይለት ዘንደ በራሴ ማልኩልህ ወይም ለተራቆተ የሚያለብሰውን ለተራበም የሚያጠግበውን ለተጠማ የሚያጠጣውን የገድልህን መጽሐፍም የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውንና የሚሰማውን በጸሎትህም የሚታመኑትን ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እምራቸዋለሁ ይህንም ብሎ አፉን ሳመው በደረቱም ላይ አድርጎ ወደአየር አወጣው የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች ።


ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በቅዱስ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †




ምንጭ: የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢጉባዔ ቤተ መጻሕፍት



▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

04 Nov, 04:14


🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
“አቤቱ፥ በታላቁ ጉባኤ ውስጥ እገዛልሃለኹ፥ በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግንሃለኹ።”
        መዝሙር ፴፬፥፲፰

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹 የመዝሙር ዳሰሳ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

በዕለቱ መርሐ-ግብራችን የሚነሱ  ዓበይት ጉዳዮች:-

፩. መዝሙር ማለት ምን ማለት ነው?

፪. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ-ክርስቲያን የምትቀበላቸው መዝሙሮች ምን ምን ባህርያትን እና ስርዓቶችን ማሟላት አለባችው?

፫. እንዲኹም የተመረጡ መዝሙሮች በስፋት ይዳሰሳሉ።

ስለሆነም በዛሬው መርሐ-ግብራችን ኹላችንም ተቀሳቅሰን በመምጣት  ስለመዝሙሮቻችን ምንነት እንድናውቅ ግድ ነው። መቅረት ብቻ ሳይሆን ማርፈድም ያስቆጫል።

👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
👏👏👏👏👏👏መቼት👏👏👏👏👏👏👏
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

መቼ:- ዛሬ በዕለተ ሰኑይ ከምሽቱ 12:30 አስከ 2:00፤

የት:-  ፋ/ደ/ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የዓብነት መማሪያው አዳራሽ፣


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሰላመ እግዚአብሔር ከኹላችን ጋር ይሁን።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ፤ መዝሙር እና ሥነጥበባት ክፍል
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

03 Nov, 08:23


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «»

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

02 Nov, 17:00


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንኳን ለ5ተኛ ሳምንት ጾመ ፅጌ በሰላም አደረሳችሁ።

ዛሬ ለፅጌ ማኅሌት ቤተክርስቲያን ለመሄድ የምትፈልጉ ማታ ተሰባስበን ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅ/ሩፋኤል እና ቅ/አርሴማ ቤ/ክ በጋራ እንሄዳለን።

መገናኛ ቦታ:
ለሴቶች: Block 2 ዶርም ፊትለፊት
ለወንዶች: Block 8 ክብነሽ ካፌ
ፊትለፊት

ሰዓት: 3:00

ለበለጠ መረጃ:-
0968535740
ይደውሉ።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

01 Nov, 03:22


💛 የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.፻፲፩፥፮💛





▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

29 Oct, 13:31


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «»

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

29 Oct, 06:01


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ የአባላት እንክብካቤ እና አቅም ማጎልበቻ ክፍል
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

25 Oct, 09:11


ረቡዕ የእንኳን ደህና መጣችሁ ጉባኤ ላይ የተነሱ ፎቶ እና ቪዲዮዎችን https://t.me/GGgallery1 ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

23 Oct, 15:05


መርሐግብራችን ስለተጀመረ ያልመጣችሁ ቶሎ ኑ።

የግቢ ጉባኤ ቲሸርት የለበሱ ልጆች ከግቢው ጀምሮ መንገዱን ለማሳየት ቆመዋል

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

23 Oct, 11:30


ነጠላ የለበሱ ልጆች ከግቢው ጀምሮ እስከ ቤ/ክ ድረስ ቆመው መንገዱን ይጠቁሟችኋል።

በተጨማሪም በ video የተዘጋጀ አቅጣጫ በ @GGgallery1 ያገኛሉ።

ትርፍ ቀሚስ እና ነጠላ ያላችሁ  እህቶቻችን ማዋስ የምትፈልጉ በ @gibigubae_hasab_bot ያሳውቁን።

መቅረት አይደለም ፤ ማርፈድ ያስቆጫል።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

23 Oct, 06:00


🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀


🎉🎉 ልዩ የሆነችዋ ቀን እነሆ ዛሬ ናት🎉🎉

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

ውድ የ1ኛ ዓመት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እነሆ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ልንቀበላችሁ ጥቂት ሰዓታት ቀርተውናል።


ዛሬ ከ11:30 ጀምሮ እራታችንን በጊዜ በልተን ጉዞአችን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ይሁን።


⛪️ ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን
🗓 ረቡዕ፡ 13/02/2017 ዓ/ም
🕰 11:30
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

22 Oct, 07:00






               ፩ ቀን ቀረው






ትርፍ ቀሚስ እና ነጠላ ያላችሁ  እህቶቻችን ለነገ የአንደኛ ዓመት እንኳን ደህና መጣችሁ ጉባኤ ለእህቶች ማዋስ የምትፈልጉ በ @gibigubae_hasab_bot ያሳውቁን።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

21 Oct, 09:00






፪ ቀን ቀረው






▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 17:41


ከሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የስድስተኛ ዙር የበገና ተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ተጠናቋል።

የተመዘገባችሁ ስልጠናው ከአንድ ሳምንት በኋላ ይጀምራል።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

17 Oct, 19:25


በትላንትናው ዕለት የነበረን የዓመቱ የመጀመሪያው የአንድነት ጉባኤ ይሄን ይመስል ነበር።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

17 Oct, 12:02


https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSczFnlAgaVtWWopfjVBXyT-0t5HiFpkX7rk_7lnPH9aLKdNNg/viewform?usp=sf_link


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

16 Oct, 14:40


🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

የግቢ ጉባኤያችን የመጀመሪያው የአንድነት ልዩ ጉባኤ በጸሎት ጀምረናል።

እራታችንን በጊዜ በልተን ሁላችንም እንድንገኝ።


⛪️ ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

14 Oct, 16:29



"ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ"  -- መዝ 122፥1 --


ውድ የግቢ ጉባኤያችን አባላት እንኳን ለ 2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ ።

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐግብር

➩ውዳሴ ማርያም ጸሎት
➩ዝማሬ በሰ/ት/ቤት ታዳጊዎች
➪ትምህርት በተጋባዥ መምህር
➪ሥነ-ጽሑፍ
➪ዝማሬ በማኅበረ ቅዱሳን ዘማርያን

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

📆 ረቡዕ ፡ 06/02/2017 ዓ/ም
  11፡00

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

14 Oct, 04:44


+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አምላክ አሜን።  +++

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
ታላቅ የምሥራች ለበገና ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ በመዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል በ 2017 ዓ.ም ተማሪዎቹን የበገና ትምህርት ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ የእናንተን መምጣት ይጠባበቃል። ስለሆነም መማር ለምትፈልጉ በሙሉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው ዕለት፣ ሰዓትና ቦታ በአካል  በመገኘት  እንድትመዘገቡ ስንል እናሳስባለን።

➥የመመዝገቢያ ቀን ➪ከ ጥቅምት 4 እስከ ጥቅምት 8 
         ⌚️ ከ 10:30-12:30 (ሠርክ ሰዓት)

➥የመመዝገቢያ:- ቅዱስ ሩፋኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን (ግቢ ጉባኤው ቢሮ)               

➪የመመዝገቢያ :  50 ብር

👉 ወርኃዊ ክፍያ : 300 ብር

➪➪➪ ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ።


ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0906581712 ወይም በ 0909536757 ይደውሉ

📌 ትምህርቱ የሚያጠቃልለው ከ፪ኛ-፭ኛ ዓመት ተማሪዎችን ብቻ ይሆናል።
                   
                መዝሙርና ሥነ ጥበባት ጽ/ቤት
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

13 Oct, 05:01


ውድ የ2017 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የድንግል ማርያም የአስራት የአደራ ልጆች

እንኳን ወደ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ በደህና መጣችሁ!



✏️✏️✏️
ማንኛዉም ጥያቄ እና እርዳታ ከፈለጋችሁ @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን


https://t.me/gibigubae ይከታተሉን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

05 Oct, 18:53


👉👉👉👉 ዘመነ ጽጌ

ጽጌ ማለት ' ጸገየ ' ከግእዝ ቃል የመጣ ሲሆን አበባ ማለት ነው ፤ ዘመኑም ሳያልፍ መልካም ሥራ ለመሥራት ትንሣኤ ኅሊና የሚነሣበት ጊዜ ነው ። ጾመ ጽጌ በየዓመቱ  ከመስከረም ፳፮ - ህዳር ፮  ይህም የሚጾምበት ምክንያት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ይዛ መሰደዷን መራቧን መጠማቷን በማሰብ ነው ።

በዘመነ ጽጌ ቅዱስ ያሬድ ከደረሰው ድጓ በተጨማሪ በ፲፬ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣ አባ ጽጌ ድንግል በግጥም መልክ የተደረሰ በአምስት ስንኞች ያሉት " ማኅሌተ ጽጌ " በመባል ይታወቃል ።

እመቤታችንም ጣዕሟንና ፍቅሯን እንዲሁም ምስጋናዋ ሲናፍቁ የነበሩትን ቅዱስ ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስ ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን እንደገለጸችላቸው ለፍቅሯ ሲሳሳ ለነበረው ለአባ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌ እንዲደርስ አድርጋዋለች ። በዚህ ድርሰት ላይም አባ ጽጌ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጃን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚያስረዳበት ድርሰት ነው።

@gesem24