Apostolic Church of Bole Hermon Branch @acebolehermon Channel on Telegram

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

@acebolehermon


"፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤"
(ኦሪት ዘዳግም 6: 4)

Apostolic Church of Bole Hermon Branch (Amharic)

አስራኤል ሆይ፥ ስማ! አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው! በባህታዊ ቁምፊዎች እና እናቶችን በተወካዮችና ምክር ቤቶችን ከአገሬ ከአበራና ከሶማት ትቅደሳና አልነበረም ባለው ወጣት በባኩም ጥንቃቄዎች ላይ በተሰጡ በባሕሩና ሄርሞን ወራት በሶማት መዳረሻ ላይ በደርግ እነሆ። በአሰሊና በመሌዋይና በአምባሳል የተማሩ ተቃውሞ በፍጥረቶችህ ተመልከቱ። በሳተላሳና አሉላይ የግፍኖች ደምበኞች ላይም እንደፍፁም አፈራረቅ አለው። እስራኤል በበ቉ትም ቅድሚያ ክብደት ወዳ መንፈሳዊ ብልት መፍጠር እንችላለን። ምንም አልፊልም እና አልኝም፣ የነቃቂ እንቅስቃሴዎችን በፍርድህ እንከተለን። አስር ለአምላክ ከትክክለኛይት የተወገኑ፣ የተማረኘ ህዝብን እና የመፃፀር ልጅንም ለማድረስ እኛ ለማያውቁ እንጠየቅን።

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

06 Jan, 03:52


" እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።"
ሉቃ2፥9-14

የተወደዳችሁ ቅዱሳን ነገ ማክሰኞ:- እግዚአብሔር በስጋ መገለጡን (መወለዱን) በሰዎች ልማድ ቀን ቢቆጥሩለትም, እኛ ግን የቀኑ ቁጥር ሳይገደን:- የተገኘችውን ይህቺን ቀን ተጠቅመን ጌታችንን እናደንቅበታለን፤ ሥራህ ግሩም ብለን በመወለዱ የበራልንን ብርሃን እያሰብንና እያደነቅን እናመልከዋለን!!! እንሰግድለታለን !!! ሃሌሉያ!! ሁላችንም ለምስጋና እንገኝ!!!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Jan, 02:27


📌 ሙሉ ሰው ወደመሆን ማደግ
( ክፍል አንድ )

“ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።”
ኤፌ 4፥12-13

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

01 Jan, 02:45


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ነገ ረቡዕ ጾም ጸሎት እና ከጾም ጸሎቱ በኋላ  ያለን የማታው ፕሮግራም በተለመደው ሰዓት 1:30 ላይ እንጀምራለን ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

26 Dec, 04:27


📌 በጽድቅ ህይወት የሚገኝ በረከት
( ክፍል ሶስት)

“ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፤ ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዓይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፤ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።”
ዘፍ 20፥16

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

19 Dec, 05:06


📌 በክብር ህይወት የሚገኝ በረከት !
(ክፍል ሁለት)

" ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን፦ ያቤጽ ብላ ጠራችው። ያቤጽም፦ እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
1ዜና 4፥9-10

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

16 Dec, 01:14


📌 በክብር ህይወት የሚገኝ በረከት !
( ክፍል አንድ)

" ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን፦ ያቤጽ ብላ ጠራችው። ያቤጽም፦ እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
1ዜና 4፥9-10

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

11 Dec, 01:49


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ነገ ረቡዕ ጾም ጸሎት እና ከጾም ጸሎቱ በኋላ  ያለን የማታው ፕሮግራም በተለመደው ሰዓት 1:30 ላይ እንጀምራለን ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

04 Dec, 17:34


📌 በሰልፍም ስንብቻ የለም!!

" የሰው መከራ በእርሱ ላይ እጅግ ስለ ሆነ ለነገር ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለውና። የሚሆነውን አያውቅም፤ እንዴትስ እንደሚሆን የሚነግረው ማን ነው?መንፈስን ለማስቀረት በመንፈስ ላይሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞቱም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በሰልፍም ስንብቻ የለም፥ ........"
መክ 8፥5-8

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

04 Dec, 08:14


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ይብዛላችሁ!!

በአገልጋዮች ኮንፈረንስ ምክንያት መጋቢአችን ስለማይገኙ የማታውን ፕሮግራም በቤታችሁ ከቤተሰብ ጋር እንድታደርጉ ከቤታችሁ መሰዊያ እሳትን እንዳይጠፋ አደራ እንላለን።

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

30 Nov, 06:33


አዲስ የመዝሙር አልበም!

"አልወርድም" በዘማሪ አበበ ተስፋዬ

የቃሊቲ አጥቢያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ዘማሪ

እጃቢዎች:
ዲያቆን አማኑኤል ብርሀኑ፣
ዲያቆን አቤኔዘር ፈቃደ፣
ዘማሪ ሊያ ታደስ፣
ዘማሪ ሳራ ደምሰው፣
ዘማሪ ዘነበች መሂዲ፣
ዘማሪ በረከት አለምዘውድ፣
ዘማሪ ቤተል አዳነ፣
ዘማሪ ምህርት ታደሰ፣
ዘማሪ መቅደሰ ሰለሞን፣
ዘማሪ ትሁት ኤፍሬም፣
ዘማሪ አልእዛር ጨመረ፣
ዘማሪ እስራኤል ተሾመ፣
ዘማሪ ኤርሚያስ ደረጀ፣
ዘማሪ  ኢቮን መሀመደ፣
ዘማሪ  ጌዲዮን አዲስ

Music Arrangement: Samuel Atelababchew, Natnael Tsehay, Eyassu Tsegaw, and Yonathan Argaw
Recording: Natnael Tsehay and Eyassu Tsegaw
Mixing: Natnael Tsehay and Eyassu Tsegaw
Mastering: Eyassu Tsegaw

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

27 Nov, 18:16


📌 በረከታችን ከላይ ከብርሃናት አባት ነው!

“በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።”
ያዕ 1፥17

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

27 Nov, 09:16


የተወደዳችሁ ቅዱሳን :-

የረቡዕ ማታ ፕሮግራም ይኖረናል በቤታችሁ መሰዊያ በጸሎት እንገኝ! ተባረኩ

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

26 Nov, 06:04


Apostolic Church of Bole Hermon Branch pinned an audio file

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

26 Nov, 02:06


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ይብዛላችሁ !

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አመታዊ የአገልጋዮች ሴሚናር ከህዳር 24-26 ቀን 2017 ዓ.ም በዋራ ቤቴል የኮንፍራንስ ማዕከል ላይ ይካሄዳል። በጉባኤው የሰበካና የቅርንጫፍ ሰበካ ኃላፊዎች፣ የንዑስ ሰበካ ተጠሪዎች፣ የአጥቢያ መጋቢዎችና በተለያየ ደረጃ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እያገለገሉ ያሉ የወንጌል አገልጋዮችና ባለቤቶቻቸው ከሃገር ውስጥና ከውጭ ይገኛሉ ።

በዚህ ጉባኤ:-".....የነብያት ጉባኤ ያገኙሃል
.........የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።”
1ኛሳሙ 10፥6
በዚህ የህይወት ከፍታና ለውጥ በመታደስ አገልጋዮቻችን እንዲባረኩልንና ለበረከት እንዲሆኑልን ከነገ ህዳር 17 - 19 ,2017ዓ/ም ለሦስት ቀን ለዚህ ጉባኤ ጾም ጸሎት ይደረጋል። ቅዱሳን ሁላችሁ ጊዜ የምታገኙ በጸሎት ቤት ሌሎቻችን በያለንበት ሆነን አገልጋዮቻችንን እናስብ።

"የባሪያዎቹን ሰላም የሚወድድ እግዚአብሔር በሁሉ መንገድ ሰላምን ይስጥ!!

" አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ። ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።
በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።
ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን ቅድስናዬ ያብባል።
መዝ132፥15-18

“በእግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ወደ እናንተ መጥቼ ከእናንተ ጋር እንዳርፍ፥ በይሁዳ ካሉት ከማይታዘዙ እድን ዘንድ፥ ለኢየሩሳሌምም ያለኝ አገልግሎቴ ቅዱሳንን ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ ጸልዩ።”
ሮሜ 15፥31-32

ተባረኩ ! ለበረከትም ሁኑ!!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

26 Nov, 02:06


📌 የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን

“አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።”
መዝ19፥14

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

20 Nov, 01:11


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ነገ ረቡዕ ጾም ጸሎት እና ከጾም ጸሎቱ በኋላ ያለን የማታው ፕሮግራም በተለመደው ሰዓት 1:30 ላይ እንጀምራለን ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

14 Nov, 14:05


📌 በድንኳናችን ምን ይሰማል?

“የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው"

መዝ118፥15

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

13 Nov, 00:10


የየተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ዛሬ ረቡዕ በጸሎት ቤት ባለው ጾም ጸሎት እንድትገኙ እያሳሰብን ከጾም ጸሎቱ በኋላ ደግሞ ማታ ምሽት የቤተሰብ አምልኮ ከ1:30 - 2:30 ድረስ ለአንድ ሰዓት በሚኖረን የአምልኮና የትምህርት ጊዜ በቤታችሁ መሰዊያ በጸሎት እንድትጠብቁን ከአደራ ጋር እናሳስባለን! ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ !!

“በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።”
                  ዕብራ10፥25

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

07 Nov, 15:35


የተወደዳችሁ የቦሌ አርሞንኤም ወጣቶች ሰላም ይብዛላችሁ! ፊታችን እሁድ ህዳር 1, 2017ዓ.ም ከሰአት በኋላ ያላገቡ ወጣቶችን እና ያገቡትንም የሚያግዝ ልዩ የህብረትና የትምህርት ጊዜ ተዘጋጅቷል !!ሁላችሁም እንድትገኙ ተጋብዛችኋል ። ሌላ ቀጠሮ አንያዝ!!እንድንገኝ እንትጋ!!

ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ !! share it pls??

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

07 Nov, 06:25


📌 ለህሊና ንጽህና መትጋት

“ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”
ሐዋ 24፥16

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

05 Nov, 23:31


የየተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ዛሬ ረቡዕ በጸሎት ቤት ባለው ጾም ጸሎት እንድትገኙ እያሳሰብን ከጾም ጸሎቱ በኋላ ደግሞ ማታ ምሽት የቤተሰብ አምልኮ ከ1:30 - 2:30 ድረስ ለአንድ ሰዓት በሚኖረን የአምልኮና የትምህርት ጊዜ በቤታችሁ መሰዊያ በጸሎት እንድትጠብቁን ከአደራ ጋር እናሳስባለን! ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ !!

“በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።”
                  ዕብራ10፥25

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

31 Oct, 07:38


📌 ሳትማረክ አትቀበልም

" ስለዚህ፦ ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ ይላል።"
ኤፌ4፥8

የጸጋ ሙላት እና ወጤቱ የመጨረሻው ክፍል

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

30 Oct, 01:26


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ዛሬ ረቡዕ በጸሎት ቤት ባለው ጾም ጸሎት እንድትገኙ እያሳሰብን ከጾም ጸሎቱ በኋላ ደግሞ ማታ ምሽት  የቤተሰብ አምልኮ ከ1:30 ላይ :-
                            (ክፍል ሁለት)
                     የጸጋው ሙላትና ውጤቱን
የሚለውን የመጨረሻውን ክፍል እናስተላልፋለን እናንተም በቤታችሁ መሰዊያ በጸሎት ጠብቁን!!ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!!

“በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።”
ዕብራ10፥25

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

25 Oct, 04:17


ይቅርታ ማስተካከያውን ተመልከቱ🙏

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

24 Oct, 19:56


የተወደዳችሁ የቦሌ አርሞንኤም ወጣቶች ሰላም ይብዛላችሁ!እሁድ ከሰአት የቀጠርነው የወጣቶች ፕሮግራም ቀድሞ ከተያዘ ፕሮግራም ጋር ስለተደረበብን ከይቅርታ ጋር እሁድ ህዳር 1, ከሰአት በኋላ ያላገቡ ወጣቶችን እና ያገቡትንም የሚያግዝ ልዩ የህብረትና የትምህርት ጊዜ አዘጋጅተናል!!ሁላችንም እንድንገኝ እንትጋ!!

ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ !! share it pls??

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 17:41


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 17:31


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 17:22


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 17:11


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 17:00


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 16:52


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 16:51


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 16:51


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

23 Oct, 03:05


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ዛሬ ረቡዕ በጸሎት ቤት ባለው ጾም ጸሎት እንድትገኙ እያሳሰብን ከጾም ጸሎቱ በኋላ ደግሞ ማታ ምሽት  የቤተሰብ አምልኮ ከ1:30 ላይ :-
                            (ክፍል ሁለት)
                     የጸጋው ሙላትና ውጤቱን
የሚለውን ክፍል እናስተላልፋለን እናንተም በጸሎት በቤታችሁ መሰዊያ በጸሎት ጠብቁን!!ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

20 Oct, 18:08


“ሥርዓትህንም አሰላስላሁ።”
መዝ119፥48

📌 ሐዋርያ ጳውሎስ ቅዱሳንን
ጥቂት ብጠግባችሁ ያለው ለካ ሰው ስለሚርብ ነው !

📌 ያለ እንባ ፍሬያማነትን መጠበቅ ከንቱ ድካም ነው !

📌 የእግዚአብሔርን የኃይሉን ችሎት ስንረዳ በችሎታው ለማረፍ እምነት ይኖረናል !

📌 ጠላትን በብርቱ የሚያስፈራው መኖራችን ሳይሆን የምንኖርበት አላማ ነው !

📌 በህይወት ጉዞአችን በጠላት ከምንፈተንበት በላይ በራሳችን የምንፈተንበት ፈተና ይበልጣል!

📌 መውደቅ መነሳት ታሪካችን የሆነበት ምክንያት በትርና ምርኩዝ ከሆነው ቃል ስለራቅን ነው !

📌 ጠላት ሁልጊዜ እየሔድን አድራሻችንን በማጥፋት በአዙሪት ህይወት ዘመናችንን እንድንጨርስ ያደርገናል !

📌 ጠላት ከፍርስራሹ የሚያገኘው ጥቅም ስላለ ሰንባላጥን ያስነሳብሃል !

📌 የፍሬ ዛፍ ስትሆን የሚዋጋህ ብዙ ነው !ግን ታሸንፋለህ!

የቦሌ አርሞንኤም መጋቢ ካስተማሩት የተወሰደ

ይቀጥላል.....
@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

17 Oct, 22:24


"መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው"
ዘዳ33፥27

እስራኤል ወደከነአን በሚጓዝበት የምድረበዳ ጉዞ የእያንዳንዱ ሰው ኑሮ በእግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ ነበር። ለጤፍ፣ ለዘይት፣ለመብራት፣ ለቤት ኪራይ ..እያለ የሚያስቀምው ተቀማጭ ይሁን የባንክ ደብተር እንዲሁም ባለአደራ ፤ልበ ደርም የሚለው የተሻለ ዘመድ..ጎረቤት እንዳይ
ል የወጣበት ስፍራ የኑሮ ልዩነት የሌለበት ሁሉን እኩል ያደረገ ምድረበዳ ነበር። አቤት ወደማን ይኬዳል?
እስራኤል ወደደም ጠላም መኖሪያው አምላኩና አምላኩ ብቻ ነበር! ወደየትም አትሩጥ አንጋጥ የሚባለው አይነት!!
"የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ። አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥
ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ"
መዝ145፥15-16
እግዚአብሔርም በዚያ ጭው ባለ ምድረበዳ ብቻውን መኖሪያ መሆኑን አስመስክሯል !በምድረበዳ አረባ አመት ሲመራ
አንዳች አላሳጣውም!ስለሚበላው ስለሚጠጣው አይደለም፦ ጸሃይ እንዳያቃጥለው እንኳ ደመናን እንደ ጃንጥላ ዘርግቶ አቀማጥሎ መርቶታል!!!
እኛም በእጃችን ባለው አልበቃ ካለን የኑሮ ጉድለት አይናችንን አንስተን ሁሉን አትርፎ በሚሰጥ ጌታ ላይ ልባችንን አርገን መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ ነው ብለን እርፍ ብለን እንኑር!!

አሜን!!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

16 Oct, 17:18


ሰላም ቅዱሳን !! እህታችን ዘማሪት አስቴር እና ወንድም ልዑል እግዚአብሔር የሆድን ፍሬ ስለሰጣቸው በሰላም ስለወለደች እንኳን ደስ ያላችሁ በሏቸው!!

“ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።”
2ኛ ቆሮ 9፥15

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

16 Oct, 10:59


ጸጋህን አብዛልን

ዘማሪ ዮርዳኖስ መለሰ

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

16 Oct, 10:58


የተወደዳችሁ ቅዱሳን በአገልጋዮች ሴሚናር ምክንያት አገልጋዮች ስለማንገኝ የማታውን ፕሮግራም ሁለት ሶስት ሆናችሁ በየቤታችሁ እንድታደርጉ አደራ እንላለን።

“ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም።”
ዘሌ 6፥13
ተባረኩ!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

11 Oct, 10:20


📌 ብቃትን ሁሉ የሚሰጥ ጸጋ
( ክፍል ሁለት)
የጸጋ ሙላትና ውጤቱ
“....... እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።”
2ኛ ቆሮ 9፥8-9

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

09 Oct, 02:33


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ነገ ረቡዕ በጸሎት ቤት ያለው ጾም ጸሎት እንድትገኙ አደራ እያልን ከጾም ጸሎቱ በኋላ ደግሞ ማታ ምሽት የቤተሰብ አምልኮ ከ1:30 ላይ :-
           (ክፍል ሁለት)
  የጸጋው ሙላትና ውጤቱን
የሚለውን ክፍል እንቀጥላለን እናንተም በጸሎት በቤታችሁ መሰዊያ ጠብቁን!!ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Oct, 17:48


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Oct, 17:42


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Oct, 17:31


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Oct, 17:21


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Oct, 17:11


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Oct, 17:02


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Oct, 16:51


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

02 Oct, 16:40


@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

01 Oct, 17:23


የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን!!
እንደተለመደው ነገ ረቡዕ በጸሎት ቤት ባለው ጾም ጸሎት ላይ እንድትገኙ አደራ እያልን ከጾም ጸሎቱ በኋላ ደግሞ ማታ ምሽት የቤተሰብ አምልኮ ከ1:30 ላይ :-
           (ክፍል ሁለት)
  የጸጋው ሙላትና ውጤቱ
የሚለውን ክፍል እናስተላልፋለን እናንተም በቤታችሁ መሰዊያ በጸሎት ጠብቁን!!ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

01 Oct, 03:03


“በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ.....”
ኤፌ 5፥19

📌 የእንደገና አምላክ ነው!!
ድንቅ ቅኔ

እህት ኤልሳቤጥ ቢያድግልኝ
ቦሌ አርሞንኤም አጥቢያ

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

30 Sep, 06:00


📌 ሕይወታችሁን ለመለወጥ


➧ሕይወታችሁን ለመለወጥ ምርጫችሁን ለውጡ፡፡

➧ምርጫ ሳይለወጥ ሕይወት አይለወጥም፡፡

➧ሕይወታችሁን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ስትመርጡ ህይወታችሁ መለወጡ አይቀርም።

➧የምትውሉበትን አካባቢ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

➧የምታዩትን ማሕበራዊ ሚዲያ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

➧የማይሆኑ ጓደኞቻችሁን ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

➧የምታነቡትን መጽሐፍ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

➧በየቀኑ በመደጋገም የምታደርጓቸውን ልማዶች ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

➧በማይሆን ምርጫችን በምንከፍለው የማይሆን ዋጋ ብንማረር ምንይጠቅመናል?

በጊዜ ምርጫችን ይስተካከል !!!!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

28 Sep, 17:28


መንግሥተ ሰማያት ምን ትመስላለች?
ሉቃ 13፥18

📌 በእርሻ ውስጥ የተሰወረን መዝገብ ትመስላለች። ማቴ 13፥44

📌 መልካም እንቁ የምሻ ነጋዴን ትመስላለች። ማቴ 13፥45

📌 ወደ ባህር የተጣለች ከሁሉም አይነት የተሰበሰበች መረብን ትመስላለች። ማቴ 13፥46

📌 ባሮቹን ልቆጣጠር የወደደን ንጉስ ትመስላለች። ማቴ 18፥23

📌 ለወይኑ አትክልት ሰራተኞችን ልቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ትመስላለች። ማቴ 20፥1

📌 ሰው ወስዶ በአትክልቱ የጣላትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች። ሉቃ 13፥18

📌 ሴት ወስዳ ሁሉ እስክቦካ ድረስ በሦስት መሰፈርያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች። ሉቃ 13፥21

📌 መብራታቸውን ይዘው ሙሽራን ልቀበሉ የወጡ አስር ቆንጃጅቶችን ትመስላለች። ማቴ 25፥1

📌 ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉስን ትመስላለች። ማቴ 22፥2

📌 በእርሻ መካከል መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች። ማቴ 13፥24

አሰላስሉት!!

@ACEBoleHermon

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

26 Sep, 17:46


https://youtu.be/sRWD8rDgFXs?si=XktMZ5wgUG1Sv_xa

Apostolic Church of Bole Hermon Branch

26 Sep, 11:21


በየስፍራው ሁሉ ላላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች!

የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችሁ ይሁን

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በሃድይኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን አቲ አቴቴሜ ደበሰንቶዮ (አንተ ያው አንተ ነህ አትለወጥም) የተሰኘ የዝማሬ ስንዱቅ (Album) ሲያቀርብላችሁ በደስታ ነው።

ይህንን የዝማሬ አልበም በብዙ ድካም ያዘጋጀውን ዘማሪ አልባስጥሮስ ኤርሚያስ (ወንድሙ) እና በአልበሙ ዝግጅት በተለያየ መንገድ የተሳተፉትን ሁሉ
እግዚአብሔር እንዲባርካቸው እየፀለይን፥  አልበሙን በ Apostolic Songs መተግበሪያ ላይ የተለቀቀ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን።


በኢትዮጵያ ያላችሁ ተጠቃሚዎቻችን ዝማሬዎቹን ለማውረድ የምትጠቀሙበትን ኮድ በቴሌግራም ቦት t.me/ApostolicPayBot ላይ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ከኢትዮጵያ ውጪ ያላችሁ ደግሞ ክሬዲት ካርድ በመጠቀም አልበሙን ማግኘት እንደምትችሉ እንገልፃለን።

አልበሙን ለማግኘት የመተግበሪያውን የመዝሙር ቋንቋ ምርጫ የሃድይኛ አልበሞችን እንዲያካትት ማስተካከል እንዳለቦት አይርሱ። እንዴት ማስተካክል እንደሚችሉ ለማየት ይህንን ይጫኑ

የኦዲዮ ቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል

መስከረም 2017 ዓ.ም