ማኅቶተ ቶኔቶር ፩ @mahtotetonetor1 Channel on Telegram

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

@mahtotetonetor1


ማኅቶት ማለት መብራት ነው ቶኔቶር ደግሞ የኢትዮጵያ የጥንት ስሟነው እናም ማኅቶተ ቶኔቶር ማለት የኢትዮጵያ መብራት ማለት ነው መብራቷ ደግሞ መካከሏን ገነት ዳሯን እሳት እያለች የምትጠብቃት የምትጸልይላት እምነቷ ቅድስት ተዋህዶ ጥንት የሌላት ጥንታዊት ዘመን የሌላት ዘመናዊት ናት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምሮ ነው
አስተያየት ካለዎት
@mahtotetonetor2
@mahtotetonetor1

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩ (Amharic)

እንኳን አደራሽ! በትላንት ለተከሰተ አመት እና የአፍሪካ ሚሊዮንስ በአማርኛ ዳይምክ አካዋቂና እና አስተምሮ ታቡሱና በመሆኑ እንቅስቃሴን ለመስተጠጄ ነው ማኅቶተ ቶኔቶር ፩ በሚል ልዩ ተካንዥ የምንገኘው ማለት. ማኅቶተ ቶኔቶር ፩ ከከባቢያቲል ፣ ከወጣቶቹ እና ከኢትዮጵያዊያን ጋር የተደረገው የአሞት መረጃ ለእናቴኬኮ በሽቅት እየሠራች፣ በሽቅት ቆዝና ታከብሩና ከእናትና ልጅ ሁኔታ ጋር አደረገው. በምስል ተጠቃሚነቴን የምታደርገው በሰላምና በእንቅስቃሴ እና አስተምሮስ ኣሰተናከ ትም በህዝቤ በኦሮሞና መስማት በዳሯ ለዓለማዊ ትረካት በዓለም ላይለይ።

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

21 Nov, 07:16


ከላይ ስትሆን(ገንዘብ ሲኖርህ) ሁሉም ሰው ወዳጅህ ነው ልጠፍጠፍልህ ልነጠፍልህ ነወር ነወር ና ተቀመጥ ብሎ የሚነሳልህ ብዙ ነው የሰው ልክ ማለት እሱ አይደለም የወዳጅነትህ ልክ መሰረቱ ከታች ሆነህ  ነው  ።አዋርዶ ከፍ የሚያደርግህ ሌላ ውርደት ስላጣልህ ነው ።ዝቅ ከአልንበት ዝቅ ብሎ የሚያነሳ ምንኛ ክቡር ነው።

ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

21 Nov, 03:40


ቅዱስ ሚካኤል የሚከብርበት ፫  ምክንያቶች

፩) በዓለ ሲመቱ(የተሾመበት)፣

፪) በእነ ዱራታኦስ እና ቴዎብስታ ቤት የተገለጠበት እና ቤታቸውን የባረከበት ፣

፫) ህዝበ ፳ኤልን ከግብጽ እየመራ ወደ ፳ኤል ያስገባበት።


ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

20 Nov, 18:49


በድካም ውስጥ ብትሆንም ተስፋ አትቁረጥ፤ ተስፋ መቁረጥ ወደከፋ ደረጃ ከሚያስገባህ ባለህበት ብትቆይ ይሻልሃልና።

ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ
ሳልሳዊ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

20 Nov, 09:47


ይህ ፎቶ ሾብ አይደለም እውነት ነው !!
✍️..የሮማ ካቶሊክ ያልተገባ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን መፍቀዷ ብቻ አይደለም የሴት ካህናትና ጳጳሳትም እያለማመደች ነው። የሮማ ፓፕ ድፍረት ወደ ሌሎች አህጉር እየተስፋፋ ሴቶች ካህንና ጳጳስ መሆን አለብን ጥያቄ ተስፋፍቷል። ይህ ጉዳይ እኛን ይጠብቀን


Dn Ermias

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

19 Nov, 21:33


እመቤቴ ማርያም ጠጅ እያማረሽ
ማር አትይውም ወይ ሲቆርጥ ልጅሽ

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

19 Nov, 20:25


▶️፲፩. ወራት የባሰባት ሴት ማለት ምን ለማለት ነው? እንዲሁም መካኗ ሰባት ወልዳለች ይላልና ሐና የወለደቻቸው ስንት ናቸው?

✔️መልስ፦ ወራት የባሰባት ሴት ማለት መከራ የተደራረበባትና በዚህም ምክንያት ያዘነች ሴት ማለት ነው። ሐና ከሳሙኤል በኋላ ሦስት ወንዶች ልጆችንና ሁለት ሴቶች ልጆችን ወልዳለች። ሳሙኤል ምስፍናን ከክህነት አንድ አድርጎ ይኖር ስለነበር ስለሁለት ተቆጥሮ ነው መካኗ ሐና ሰባት ወልዳለች የተባለው። በሌላ አገላለጽ ሰባት በዕብራውያን ፍጹም ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ ፍጹም ደግ ልጅ ሳሙኤልን ወለድኩ ስትል ሐና መካኗ ሰባት ወልዳለች ብላ ስለራሷ ተናግራለች።


መጋቤ ብሉይ በትረ ማርያም አበባው


@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

19 Nov, 20:25


▶️፩. "ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ" ይላል። በዚህ አገባብ ቀንድ የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የሳሙኤል እናት የሐና እንደ በሬ እንደ ላም ቀንድ ነበራት ለማለት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ቀንድ እየተባለ የሚጠራ ሥልጣን ነው። ስለዚህ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለቷ ሥልጣኔ ከፍ ከፍ አለ ለማለት ነው።

▶️፪. "ስለዚህም የዔሊ ቤት ኃጢአት በመሥዋዕትና በቍርባን ለዘላለም እንዳይሠረይለት ለዔሊ ቤት ምያለሁ" ይላል (1ኛ ሳሙ.3፥14)። ይህ ነገር ከእግዚአብሔር መሓሪነትና ይቅር ባይነትጋ አብሮ ይሄዳል ወይ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር መሓሪነት አያጠያይቅም። በባሕርይው ቸር መሓሪ እግዚአብሔር ብቻ ነው። የዔሊ ወገኖች ከበደላቸው ቢመለሱ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል። ነገር ግን እንደማይመለሱ አውቆ አይሠረይላቸውም አለ።

▶️፫. "የእግዚአብሔርም ታቦት ተማረከች፥ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ" ይላል (1ኛ ሳሙ.4፥11)። በዚህ ዘመን ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በአክራሪ ኃይሎች ይቃጠላሉ፤ ታቦታትና ንዋየ ቅድሳት ይዘረፋሉ፤ አገልጋይ ካህናት ይገደላሉ። አንዳንድ ሰዎች እንዴት ታቦት ካህን ባልሆነ ያውም በማያምን ሰው እጅ ይያዛል? እውነት የምትሰግዱለት ታቦት የሆነ ኃይል ካለው ለምን አይቀሥፍም? ወይስ  ለምን ሌላ ተአምር ሠርቶ አያጠፋቸውም? ይላሉና ከዚህ ጥቅስ ተነሥተው ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ፈታሒ (ፈራጅ) ብቻ ሳይሆን መሓሪም ነው። አንድ ሰው አጥፍቶ ሳለ እንኳ ወዲያው አያጠፋውም በንስሓ ይመለስ ዘንድ በድሎም ዝም ይለዋል። የእርሱ ማደሪያ የሆነው ታቦት ብቻ ሳይሆን እርሱን ራሱን ኢየሱስ ክርስቶስን ይሁዳ ስሞ ሲሸጠው ሲሰቅሉት እንደሚታረድ በግ ዝም እንዳለ ተገልጿል። ይህ ሁሉ የእግዚአብሔርን መሓሪነት ሰው እንዲረዳ ነው። ታቦተ ጽዮን መማረኳ ስለሁለት ነገር ነው። አንደኛ እስራኤላውያን ስለበደሉ በእርሷ መማረክ አዝነው ንስሓ እንዲገቡ ነው። ሁለተኛ ተማርካ የአሕዛብን አማልክት እነዳጎንን እንድትሰባብርና አሕዛብ የሚያመልኳቸው አማልክት የእጅ ሥራዎች መሆናቸውን አሕዛብ እንዲረዱ ነው። ስለዚህ ታቦት የሚሰርቅ ሰው ያልተቀሠፈ እግዚአብሔር መሓሪ ስለሆነ የንስሓ እድሜ እየሰጠው እንጂ ወዲያው ማጥፋት አቅቶት እንዳልሆነ ሊረዳው ይገባል።

▶️፬. "የእግዚአብሔርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ አለው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በግብጽ በፈርዖን ቤት ባሪያ ሳለ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ" ይላል (1ኛ ሳሙ.2፥27)። የእግዚአብሔር ሰው የተባለው ነቢይ ነው ወይስ ማነው?

✔️መልስ፦ ስሙ ከዚህ ያልተጻፈ ነቢይ ነው። መተርጉማን በሰው አምሳል ስለታየ ነው እንጂ መልአክ ነው ብለዋል።

▶️፭. "እነሆ፥ ለቤትህ ሽማግሌ እንዳይገኝ፥ ክንድህን የአባትህንም ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል። በእስራኤል በረከት ሁሉ፥ በማደሪያዬ ጠላትህን ታያለህ በቤትህም ለዘላለም ሽማግሌ አይገኝም። ከመሠዊያዬ ያልተቈረጠ ልጅህ ቢገኝ ዓይንህን ያፈዝዘዋል፥ ነፍስህንም ያሳዝናል ከቤትህም የሚወለዱ ሰዎች ሁሉ በጎልማስነት ይሞታሉ" ይላል (1ኛ ሳሙ.2፥31-33)። ክንድ የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ክንድ የተባሉ ወገኖች ናቸው። ክንድህን ማለት ወገንህን ማለት ነው፣ የአባትህንም ቤት ክንድ ማለት ደግሞ የአባትህን ወገኖች ማለት ነው። ዘርህን ወገንህን የማጠፋበት ቀን ይመጣል ለማለት የተነገረ ቃል ነው።

▶️፮. "ዔሊም በስፍራው ተኝቶ ሳለ፥ የእግዚአብሔር መብራት ገና ሳይጠፋ፥ ሳሙኤልም የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ሳለ" ይላል
(1ኛ ሳሙ.3፥3)። ታቦት ባለበት መቅደስ ውስጥ መተኛት በዛን ዘመን ሥርዓት ነበር? አሁን በዚህ ዘመን ላለን ሰዎችስ በሕንፃ ቤተ ክርስቲያን (በቅኔ ማኅሌት፣ በቅድስት) ውስጥ መተኛት ይፈቀዳል ወይ? አንዳንድ ካህናት ታቦቱ ባለበት መቅደስ ወስጥ ሳይቀር ገብተው የሚተኙ (የሚያንቀላፉ) አሉና ከዚህ ጥቅሰ አንፃር ሥርዓቱን ቢነግሩኝ።

✔️መልስ፦ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ነበር መባሉ ከቅጽሩ ውስጥ ሆኖ በዙሪያው ተኝቶ ነበር ለማለት ነው እንጂ በደብተራ ኦሪት ውስጥ ተኝቶ እንደነበረ የሚገልጽ አይደለም። በሕንፃ ቤተክርስቲያን ውስጥ መተኛት ፈጽሞ አይገባም። በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 1 ላይ እንደተገለጸው ቤተክርስቲያን የጸሎት ቤት ናት እንጂ የመኝታ ቤት አይደለችም። በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉም ንቁሕ ሆኖ ቃለ እግዚአብሔርን በንቃት መከታተል፣ በንቃት መጸለይ ይገባዋል እንጂ መተኛት ፈጽሞ አልተፈቀደም። መቅደስ ውስጥ ገብተው የሚተኙ ካሉም ስሕተት ነው መታረም አለበት።

▶️፯. "የውስጥ አካላቸውን በእባጭ መታ"
ይላልና ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የውስጥ አካላቸውን በእባጭ መታ ማለት ብልታቸውን (መሽኛቸውን) በእባጭ መታ ማለት ነው።

▶️፰. "በዚያንም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነበር፤ ራእይም አይገለጥም ነበር" ይላል። ራእይ አይገለጥም ሲል ምን ማለቱ ነው እግዚአብሔር ስዎችን እንዴት ነበር የሚያናግራቸው?

✔️መልስ፦ በዚያን ዘመን እግዚአብሔር ማንንም እንዳላናገረ የሚገልጽ ቃል ነው። በራእይም በሌላም መንገድ ለሕዝቡ አልተገለጠም አልተናገረም ነበር። ስለዚህ በዚያን ወቅት ያናገረው ሰው አልነበረም ማለት ነው።

▶️፱. "ከተሸከሙትም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በታላቅ ድንጋጤ በከተማዪቱ ላይ ኾነች። ከታናሹም እስከ ታላቁ ድረስ የከተማዪቱን ሰዎች መታ ዕባጭም መጣባቸው" ይላል። ማን ነበር ታቦቱን የሚሸከመው?

✔️መልስ፦ ታቦቷን በሠረገላ ስለነበር የሚያደርጓት በሠረገላ አድርገው በላሞች ነበር የሚያስጎትቷት እንጂ በተለየ ታቦተ እግዚአብሔርን የሚሸከም አልነበረም። ወደእስራኤል ስትመጣ ግን ሌዋውያን ይሸከሟት ነበር።

▶️፲. "እግዚአብሔርም ማሕፀኗን ዘግቶ ነበርና ጣውንቷ ታስቈጣት ታበሳጫትም ነበር" ይላል። ጣውንቷ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጣውንት ማለት ጎባን ማለት ነው። ለምሳሌ አንዲት ሴት ያገባችውን ባል ሌላ ሴት ብታገባው አንዷ ለአንዷ ጎባን ናቸው ይባላል። የወንድም እንዲሁ ነው። አንዱ ያገባት የነበረችን ሴት ሌላ ሲያገባት ጎባን ሆኑ ይባላል።

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

19 Nov, 16:30


ዛሬ ታክሲ ውስጥ እያለሁ ከአጠገቤ ያለ ሰው ብዙ ያወራል እኔን ስላልመሰለኝ አሐቲ ድንግልን እያነበብኩ ነበርና ዝም አልኩት አንድ ቃል ግን እንዲህ አለኝ ከአንድ ታዋቂ ሰው የተዋስኩትን ሀሳብ ብሎ ነው የጀመረልኝ One best book is equal to hundred good friends but one good friend is equal to library አለኝ ያው የፈረጅኛ አፍ ብዙም አይደለሁም ግን ማንበብ ጥሩ ነው ለማለት የፈለገ መሰለኝና ልክ ነው አልኩት ።

ማንበብ ማንበብ ነገም ዛሬም ማንበብ መልካም ነው እላችኋለሁ።

ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

19 Nov, 07:36


የዋህነት ልበለው አለማወቅ ?
አንቺ ዓለም አንቺ ዓለም የማይልሽ የለም አለ ሰውዬው ጉድ እኮ ነው!
የካህናት ሩጫ ግን ይዘጋጅልን 😂እኔ አንደኛ የምወጣ ይመስለኛል!
ለወንጌል አልፋጠን ካልን ይህ የሚሻል አይመስላችሁም ?
ፖሊስም ከነ ሙሉ ትጥቁ እንደማይሮጥ ኹሉ ፥ ካህንም ከነ ቆቡ አይሮጥም፤
እውቅና ለማግኘት ሲባል ራስን ማጣትም አለ !
ኅሊናዎ ግን እንዴት እሺ አለዎት ??
አይ የዋህነት .!!!

ዲ/ን ኤርምያስ
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

19 Nov, 07:05


No friend no problem
No girlfriend no boyfriend no problem
No cash big problem አለ ትረምፕ አለኝ አንድ ጓደኛዬ እንዴ ትክክል አይደል እንዴ ታዲያ አልኩት እየውልህ የችግሮች ሁሉ ችግር No health ,ነው አለኝ እና ጓደኛዬ አሜሪካን ቢመራ ብዬ ለማሾፍ አስቤ እውነትም ገንዘብ ሆስፒታል ሊገነባ ይችላል ጤና ማለት ታሞ ሆስፒታል መግባት አይደለም ጤና ማለት ከጭንቀት ፣ከአካላዊ እክል ፣ከሁሉም ነገር ጤናማ መሆን ነው ፣ጤናማ ከሆንክ ሁሉም በጊዜው ይኖርሃል ።ጓደኛዬ አንተ ትክክል ነህ ።


ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

16 Nov, 01:31


'የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጎምጀትም ሁሉ ተጠበቁ '

በ40 ዓመቷ በጨጓራ ካንሰር ከመሞቷ በፊት በዓለም ታዋቂው ዲዛይነር እና ደራሲ “ክሪስዳ ሮድሪጌዝ” እንዲህ ስትል ፅፋለች።
1. ጋራዥ ውስጥ የአለማችን ውድ መኪና ነበረኝ፣ አሁን ግን በዊልቸር መንቀሳቀስ አለብኝ።
2. ቤቴ ሁሉንም አይነት ብራንድ ያላቸው ልብሶች፣ ጫማዎች እና ውድ እቃዎች ይሸጣል፣ አሁን ግን ሰውነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ ጨርቅ ተጠቅልሏል።
3. በባንክ ውስጥ ብዙ ገንዘብ አለኝ። አሁን ግን ከዚህ መጠን ምንም አልጠቀመኝም።
4. ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነበር አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በሁለት አልጋዎች ተኝቻለሁ።
5. ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል. አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ ከአንድ ላብራቶሪ ወደ ሌላ በመንቀሳቀስ ጊዜዬን አሳልፋለሁ
6. በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ፊርማ ሰጥቻለሁ ነገርግን በዚህ ጊዜ የሕክምና መዝገቦች የእኔ ፊርማ ናቸው።
7. ፀጉሬን ለመስራት ሰባት ፀጉር አስተካካዮች ነበሩኝ ፣ አሁን ግን - በራሴ ላይ አንድ ፀጉር የለኝም።
8 .በግል ጄት ላይ፣ የትኛውም ቦታ መብረር እችላለሁ፣ አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በር ለመራመድ ሁለት እርዳታዎች ያስፈልጉኛል።
9. ምንም እንኳን ብዙ ምግቦች ቢኖሩም, አሁን የእኔ አመጋገብ በቀን ሁለት ክኒን እና ምሽት ላይ ጥቂት የጨው ውሃ ጠብታዎች ናቸው::
10. ይህ ቤት፣ ይህ መኪና፣ ይህ አውሮፕላን፣ ይህ የቤት ዕቃ፣ ይህ ባንክ፣ ብዙ ዝናና ዝና፣ አንዳቸውም አይመጥኑኝምነበር። አሁን ግን ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም ሊደርሱልኝ እና ሊጠቅሙኝ አልቻሉም፡፡
“የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ ..🤔
ምንጭ :-ጋዜጠኛ ጌጡ እንደፃፈው
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

14 Nov, 18:15


#ኅዳር_6
#ደብረ_ቁስቋም

ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡

አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡

ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡

ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡

እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡

ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

13 Nov, 19:35


"ክፉ ዘመን ቢመጣና በቤተክርስቲያን መገልገል ባንችል ቀድሰን የምናቆርበዉ እናንተ ቤት ስለሆነ ክርስቲያኖች ሆይ የምትኖሩበትን ቤት በቅድስና ና በክብር ያዙት፤ ጠብቁት" (ሊቀ ሊቃዉንት ስምዐኮነ መልአክ)
@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

13 Nov, 15:33


ውጪ ለምትገኙ እና በOnline መማር ለምትፈልጉ

*የዘወትር ጸሎት
*ውዳሴ ማርያም
*አንቀጸ ብርሃን
*መልክአ ማርያም
*መልክአ ኢየሱስ
*ንባብ
*ዳዊት
*ውዳሴ ማርያም ዜማ
@mahtot2 ላይ ያናግሩን ይፃፉልን

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

13 Nov, 15:29


መታረም ያለባቸው ብሒሎች፦

➽ "እርጉዝ ሴት ቅዱስ ቍርባን መቀበል አትችልም" ማለቱ ልክ አይደለም። ከእርግዝናዋ ጋር ተያይዘው የሚመጡ እንደ ማቅለሽለሽ ፣ ቶሎ ቶሎ ምራቅ መትፋትና ፣ ፈሳሽ ነገር የማያስቸግራቸው ካላኾነ በቀር ።

➽ "ወጣቶች የፈቲው ጾር ስላለባቸው ትዳር ካልያዙ በቀር ቅዱስ ቍርባን መቀበል አይችሉም" ማለትም ስህተት ነው። የፈቲው ጾሩን የሚቋቋሙት በቅዱስ ቍርባን መስሎን።

➽ "ቀን በቀን መቍረብ አይቻልም" ማለትም አይቻልም። ግለሰቡ ቅዱስ ቍርባን እንዳይቀበል የሚያደርግ እንቅፋት ካልገጠመው በቀር ይችላል። ተገኝቶ።

➽ "ካህናት ከኾኑ ካልቀደሱ በቀር ቅዱስ ቍርባን መቀበል አይችሉም" ማለት ስሕተት ነው። ቀዳሽ ኾኖ ከገባ እሰየው። ካልኾነ ግን አይከለከልም።

➽ "ባልና ሚስት ቅዱስ ቍርባን መቀበል ያለባቸው በተመሳሳይ ቀን ብቻ ነው፤ ካልኾነ አይችሉም" ማለትም አይቻልም። አብረው ቢቀበሉ ጥሩ። ኹኔታዎች ካልተመቻቹ ግን {ለምሳሌ አንዱ አካል የሥራ ጫና ውስጥ ከወደቀ} አንዳቸው ሊቀበሉ ይችላሉ። ያልተቀበሉት ደግሞ ሌላ ጊዜ ይቀበላሉ።

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

10 Nov, 10:26


This is our reality

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

10 Nov, 01:59


እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቃችሁ በእውነት ክብር ያድልልን ሰው አስራቱን መባአውን ሲሰጥ የጎደለበት የሚመስለው አለ ይህ ግን ስህተት በጭራሽ መድኃኔዓለም አትርፎ ይሰጣል እንጂ አጉድሎ አያውቅም።
EGUA D/MIHRET MEDIHANIALEM
እጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን
🫴🫴አቢሲኒያ ባንክ 182395657

🫴🫴በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000273479744
  
በምንም ጉዳይ ለምትፈልጉት መረጃ ስልክ:-የእጅ ስልኮቻችን 

+15092943369 አሜሪካ ለምትገኙ

+251912494703  =ኢትዮጵያ ለምትገኙ
ይደውሉልን ወይም ቴሌግራም @sekokaw ላይ ይጻፉልን



ዲ/ን ኤርምያስ

@mahtotetonetor2

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

09 Nov, 21:21


ከአውሬ የተረፈ ፣ታንቆ የሞተ ፣ለጣኦት የተሰዋውን ፣መርዝ ያላቸውን ፣ከእነደሙ የሆነን ፣ በፍጹም እንዳንበላ ተከልክሏል ። አንድ ሰው ከሌላ ባህልና እምነት ቢመጣ ከተጠመቀ ከአመነ ሥጋወደሙን ከተቀበለ ለመዳን የሚያስፈልገው ዋናው ይህ ነው። ይህን ብላ ይህን አትብላ ተብሎ አይገደድም እንደባህሉ እየተመገበ ይኖራል እንጂ
ከዛ ውጪ በኦሪት የነበረ በክርስቶስ ተሽሯል ግዝረት በጥምቀት ፣መስዋዕት በክርስቶስ ተተክቷል ። ይሁን እንጂ ኦርቶዶክሳውያን ሚዲያዎች ስለምታቀርቡት ብትጠነቀቁ ግን መልካም ነው። ምክንያቱም እናንተ በምትጠይቁት ልክ ሳይሆን ሀሳቡ ተቆራርጦ ( ሙሉ ሀሳብ ያልሆነ) ያልጸኑት ጋር ይደርስና ህዝበ ክርስቲያንን ይበትናል።

ዲ/ን ኤርምያስ

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

09 Nov, 20:07


እኒህ ሊቀ ጳጳስ ሲናገሩ ብቻ ነው እንዴ ??እነ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ፣እነ መምህር ኃይለማርያም (ዘቦሩ ሜዳ ጉባኤ መምህር )ሲያስተምሩ ቃለሕይወት ያሰማልን ሲል የነበር https://www.facebook.com/share/v/17dGVK8Mp1/?mibextid=5SVze0

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

09 Nov, 12:54


የእኒህ ሊቀ ጳጳስ ስህተት ምንድነው በየሚዲያው እንዲህ መነጋገሪያ የሆኑበት ።ኧረ ኦርቶዶክሳዊያን እንረጋጋ በእግረኛው ሚዲያ ከተናገሩት ስህተት የሆነው የትኛው ነው??? የቱ ጋር ይህን ብሉ ይህን አትብሉ ብለው ተናገሩ??እኔ አልገባኝም ።እውነትን በሚደፍሩ አባቶች እውነት እየመጣች ነው ይህን ባሕል እና እምነት የቀላቀለ ሕዝብ ለማንቃት ብዙ ድካም ይጠይቃል ግን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መምህራን ድምጻችሁን አሰሙን።

@mahtotetonetor2

ዲ/ን ኤርምያስ

@sekokaw

1,398

subscribers

2,365

photos

30

videos