የዳቦ ማምረቻው ፋብሪካው ስራአስኪያጅ አቶ ምህረት ሙላቱ ለኢቲ ኒውስ እንደተናገሩት በከተማዋ የሚሰተዋለውን የዳቦ እጥረት ያስቀራል።
በስራው ጅማሮ ለ150 የደብረብርሃን እናቶችና ወጣቶች ቋሚና ግዚያዊ የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል ብለዋል።ፋብሪካው በቀን ከ100 እስከ 150ሺ ዳቦ በቀን የማምረት አቅም እንደሚኖረውም አስረድተዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደብረብርሃን ከተማ በርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎች እየተገነቡ ይገኛሉ።ሁሉም ወደ ስራ ሲገቡ ለከተማዋ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ተስፋ ተደርጓል።ለለውጥ የሚሰሩን ማበረታታት ይገባል።