ልሣነ አምሐራ ሚዲያ @lsaneamara2129 Channel on Telegram

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

@lsaneamara2129


በዚህ ቻናል ፈጣንና ወቅታዊ የአማራ ፋኖ እለታዊ ዘገባዎች እንድሁም ፈጣን ዜናዎች ይቀርባሉ።

ለማንኛውም ጥቆማ በ @lisaneamhara ያናግሩን‼️

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ (Amharic)

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ በዚህ ቻናል ፈጣንና ወቅታዊ የአማራ ፋኖ እለታዊ ዘገባዎች እንድሁም ፈጣን ዜናዎች ይቀርባሉ። ለማንኛውም ጥቆማ በ @lisaneamhara ያናግሩን‼️nይችላሉ ያለበት ቋንቋችንን እርዳታዊ አዝናኝ ያቀናብሩ። ስለሆነ፣ ከዚህ በበር ፈጣን ዜናዎችን ይቀርባሉ። በሚቀጥለው መለያ ላይ እንነካችኋለን ፡፡

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

20 Nov, 09:19


#ሰበር ዜና!

ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለ ጦር በ7ለ70 ብርጌድ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

የ7/70 ብርጌድ በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፣ የመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለ ጦር መሥራቾች አንዱ ብርጌድ የነበረ ሲሆን የአማራን ሕዝብ በጠላትነት የፈረጀውን የብልፅግናን አገዛዝ በመመከት እና በመደምሰስ ይታወቃል፡፡ ይህ በይፋት ቀጠና የሚንቀሳቀሰው የ7ለ70 ብርጌድ ሰፋፊ ሥራዎችን እየሠራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ጠላት ብልፅግና የተኩራራበትን የመከላከያ ሠራዊት፣ የሚኒሻ እና የአድማ ብተናን ድባቅ በመምታት ብትንትኑ እንዲወጣ ያደረገው የ7/70 ብርጌድ ለሸዋ የጀርባ አጥንት የሆነ የፋኖ አደረጃጀት እንደሆነ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡

7ለ70 ብርጊድ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለ ጦር መስራች የነበረው ብርጌድ በሸዋ ምድር እየተንቀሳቀሰ ጠላትን ሲመታ የቆየ የፋኖ አደረጃጀት እንደሆነ ወዳጆቻችን ቀርቶ ጠላቶቻችንም የሚመሰክሩት እውነታ ነው፡፡ ነገር ግን 7ለ70 ብርጌድ ሸዋ እንደ ሸዋ አንድ የፋኖ አደረጃጀት እንዲገነባ ከፍተኛ ፍላጎት የነበረው ቢሆንም አንድ የፋኖ አደረጃጀት ሳይመጣ መቅረቱ እጅጉን አሳዝኖናል፡፡ ይባስ ብሎ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የሚባለው አብዛኛውን የፋኖ አደረጃጀት ያላካተተ፣ የፋኖን ኃይል የሚከፋፍል ድርጅት መመስረቱን ስናውቅ ድርጅቱንም ሆነ የድርጅቱን ዓላማ ባለመቀበላችን 7ለ70 ብርጌድ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅቱን በብርጌድ ደረጃ የተቃወምን በመሆኑ ይህንን የአቋም መግለጫ ለመስጠት ተገደናል፡፡ ይህንን መግለጫለ መስጠት ያስገደዱን ዐበይት ምክንያቶች እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

1ኛ፦ የአማራን ሕዝብም ሆነ የአማራን ፋኖ አደረጃጀት የሚከፋፍል ድርጅት በመሆኑ በልዩነት ይህንን መግለጫ ለመስጠት ተገደናል፡፡

2ኛ፦ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝከፍተኛ አመራሮችን፣ የሠራዊት አባላትን እያሰረ፣ እያንገላታ እና ትጥቅ እያስፈታ ስለሆነ ከዚህ ድርጊቱ መቆጠብ ባለመቻሉ፣ ለምሳሌ በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምክትል ዘመቻ ሻለቃና ለ እንግዳሸት እና የአፄ ምኒሊክ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት በእስር እና እንግልት ላይ ስለሚገኙ፣

3ኛ፦ የ7ለ70 ብርጊድ ሠራዊት ጠላትን ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ ሲመታ ሕዝባዊ ድርጅቱ ግን በቀጠናችን እየገባ የራሱን ሠራዊት በስውር እያደራጀ ተገኝቷል። ለዚህም ተግባሩ ከአሁን በፊት ማስጠንቀቂያ የሰጠን ሲሆን ከዚህ በኋላ ከዚህ ከፋፋይ ድርጊቱ የማይታቀብ ከሆነ ጦራችንም ሆነ ማኅበረሰባችን የማንታገስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

4ኛ፦ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የትግል መስመር የአማራን ሕዝብ የህልውና ትግል እና የፖለቲካ ጥያቄዎችን የማይመልስ መሆኑን ስላረጋገጥን በልዩነት ከድርጅቱ ወጥተናል፡፡

5ኛ፦ እኛ 7ለ70 ብርጌድ ከየትኛውም የአማራ ፋኖ አደረጃጀት ወንድሞቻችን ጋር አብረን ለመታገል ቁርጠኛ የሆንን ሲሆን እርስበርስ ግን ከየትኛውም የአማራ ፋኖ አደረጃጀት ወንድሞቻችን ጋር በጥላቻ መነጋገርም ሆነ መዋጋት እንደማንፈልግ ለመላው የአማራ ሕዝብ ልናሳውቅ እንወዳለን፡፡

6ኛ፦ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት አሰራርም ሆነ አካሄድ "ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ" እንደሚባለው ብሂላዊ አነጋገር በሓሳብ የበላይነት፣ በንግግር ወይም በውይይት የማያምን ሲሆን እኔ የተናገርኩት፣ እኔ የሠራሁት ብቻ ትክክል ነው የሚለው አካሄድ የአማራን አሁናዊ የትግል ደረጃ የማይመጥን እና ዘመኑን ያልዋጀ በመሆኑ ይህን መገለጫ ለመስጠት ተገደናል።
7ኛ፦ ይህንን መግለጫ የሰጠነው ችግራችንን በውይይትም ሆነ በንግግር መፈታት ከማንችልበት ደረጃ ላይ በመድረሳችን ነው።

8ኛ፦ እኛ 7ለ70 ብርጌድ ይህንን መግለጫ የሰጠን ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ በድምፅም ሆነ በምስል ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ለመስጠት ዝግጁ ነን፡፡

ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ሕዝብ
ክብር በጀግንነት ለተሰው አርበኞቻችን
ከ 7ለ70 ብርጌድ

ኅዳር 10/2017 ዓ.ም

https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

20 Nov, 05:25


ሰበር ዜና -ደብረማርቆስ ከተማ ታሪክ ተሰራ
ዛሬ ሌሊት ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ፣ንስር ልዩ ኮማንዶ እና በረኸኘው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ደብረማርቆስ ከተማ ታሪክ ሲሰሩ አድረዋል።
10/03/2017ዓ.ም
የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር!!!!
@እንጅነር እስቲበል አለሙ


https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

19 Nov, 14:58


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ የአብይ አህመድን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ማሳቀቅ መፈናፈኛ ማሳጣትና ረፍት መንሳቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል::

በፋኖ ጌታሁን ሲሳይ የሚመራው አሳምነው ክፍለጦር  የሰሜን ወሎ ዞን መቀመጫ ወልድያ ከተማና አካባቢዉን ከበባ ዉስጥ አስገብቶ ትላልቅ ድሎችን እያስመዘገበ ያለ ሲሆን በዛሬው እለት ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ረፋድ አሳምነው 4ኛ ሻለቃ ሳንቃ ከተማ መግቢያ ላይ ያልታሰበ ደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ሁለት የመቶ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ በድል የታጀበዉን ተጋድሎ እያስቀጠሉ ይገኛሉ::

ተጋድሎው በደፈጣ ጥቃት የተጀመረ ቢሆንም ዉጊያው ወደ መደበኛ በማደጉ እስከ ሳንቃ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት ዙፋን ጠባቂው የጠላት ሃይል ላይ ከባድ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ሙትና ቁስለኛዉንም በባጃጅ ሲያመላልስ መዋሉን የአሳምነው ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ንጉስ አበራ ለጣቢያችን ገልጿል::

በቀጣይም የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአሳምነው ክፍለጦር ዋና አዛዥ ፋኖ ጌታሁን ሲሳይ ገልጿል።

https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

19 Nov, 12:58


መረጃ
በቀን 09-03-2017ዓም ከደቡብ ጎንደር ወረዳ አርብገበያ ላይበተደረገው የደፈጣ ትንቅንቅ የጠ*ላት ሀይል ከሳናተነስቶ ከበባ የፈፀመ ሲሆን የወገን ሀይል በደረሰው መረጃ መሠረት ከአጎራባች ወረዳወች ጋር በመናበብ ጥምረት በመፍጠር
✔️ ከደቡብ ጎንደር ከደራ የጣና ገላውዲወስ እንዲሁም
✔️ ከጢስ አበይ ሻለቃ ጋር መረጃወችን በአግባቡ በመለዋወጥ ወታደራዊ ታክቲኮችን በመጠቀም ቀድሞ ደፈጣ በመያዝ ከፊትየመጣውን ሀይል በጨበጣ ውጊያ የጠላትን ሀይልን ስላንበረከከው መቋቋም ስላልቻለ ከልጫ የቀረውን ሀይል ሙለበሙሉ በመኪና በመጫን በማስጠጋት ለመከላከል ቢሞክርም ትንታጎች የወገንሀይል በትንሽ ኪሳራ ከፍተኛ ድል የተጎናፀፈ ሲሆን በአይነ እማኞች የተረጋገጠ 3ፓትሮል አ*ስ*ክሬን ጭኖ የወጣ ሲሆን ዛሬ ጧት ረፋድ ድረስ ቁ*ስ*ለኞችን በማውጣት ላይነው
ጠላት ከደረሰበት ሽንፈት አኳያ ንፁሀንን በመጨ*ፍ*ጨፍ የተለመደውን አረመኔዊ ድርጊትየአማራን ስነልቦና ለመጉዳት 1አስክሬን አቃጥለዋል ።
በቀጣይም ትግላችን እንደአማራ ስለሆነ በየትኛውም አካባቢ ካሉ ፋኖወች ጋር በጥምረት የጋራ ጠላታችን በመ*ደ*ምሰስ የአማራን ህዝብ እረፍት ለመስጠት እየሰራን መሆኑን እገልፃለሁ።
የብልፅግና ሰ*ራ*ዊት በሌሊት እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ ሁሉም ፋኖወች ይኸን በመረዳት በንቃት መረጃወቻችን በማጠናከር ከፍተኛ ስራ ለመስራት መዘጋጀት አለብን እያልኩ
በመጨረሻም
እኛም የተለያዩ አሰራር እና አሰላለፎችን በማዘጋጀት የተለያዩ ወጣቶችን ወደብልፅግና እንዲቀላቀሉ በማድረግ በውስጥ ጠቃሚ ስራወችን እየሰራን ሲሆን በቀላሉ ነገሮችን ለማስተካከል እያገዙን ይገኛል ።

ሐብታሙ የሱፍ
የባህርዳር ብርጌድ ቃልአቀባይ

https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

19 Nov, 11:17


ሰበር የድል ዜና!!
ባህር ዳር ብርጌድ በላይ ዘለቀ ሻለቃ እና ጢስ አባይ ሻለቃ ከ ጣና ገላውዲዎስ ፋኖዎች ጋር ጥምረት በመፍጠር
አርብ ገበያ ላይ ጠላትን 2-ፓትሮል አስከሬን አሸክመው ልከውታል!!

@ Habtamu yusuf

https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

19 Nov, 10:34


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ተኛ አገው ምድር ክፍለጦር ፲ አለቃ ኤፍሬፍ አጥፉ ብርጌድ አስደናቂ ተጋድሎ በማድረግ አዲስ ቅዳም ከተማን ተቆጣጥሯል።

በዚህ አውደ ውጊያ ከ20 የማያንስ መከላከያ ተማርከዋል፣ ከሙትና ከመማረክ የተረፈው የብልጽግና ስልጣን ጠባቂ የሆነው ሚኒሻ እና መከላከያ ተብዬው ወደ ኮሶበር ፈርጥጧል።

https://t.me/Lsaneamara2129
https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

19 Nov, 07:31


🔥#የድል_ዜና ° ጎጃም‼️
=======
ትናንት የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ውስጥ የሚገኙት ሶስቱ ብርጌዶች ከፍተኛ ጀብዱ ፈፅመዋል።
፩, የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ ~~~በቀኝ አቦ
፪, ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ~~~በደንበጫና በዳባ
፫, በላይ ዘለቀ ብርጌድ~~~ በደንበጫና በዳባ

ታሪክ መስራት ልማዱ የሆነው የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ ውሏል። ለአስራ ሁለት ሰዓት ቀጥሎ የዋለው ውጊያ እጅን በአፍ የሚያስጭን ገድል ተፈፅሞበታል።

ጠላት ተወሽቆበት ከነበረው የደብረዘይት ቀበሌ ተነስቶ የንጉስ ተክለሐይማኖት ፋኖ ይገኝበታል ያለውን ቀኝ አቦን ለመያዝ በጥዋቱ ቢንቀሳቀስም እንደ ተርብ የሚናደፉት የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድና የየቦቅላ አባይ ብርጌድ ፋኖዎች የብርሐኑን አራዊት ሰራዊት ጦር ዶግ አመድ ሲያረጉት ከደብረ ማርቆስ በመነሳት ፔንፔ እና ዙ-23በመያዝ የተከበበውን ኃይሉን ለማሰለቀቅ ከአራት መቶ በላይ ኃይሉን ጭኖ በመግባት ቢያስለቅቀውም፤

ከየሰንበት፣ ከቁይ፣ ከደብረ ማርቆስ እንዲሁም ከፋኖ ቅጥቀጣ ያመለጠው ኃይል የቦቅላ ላይ ተሰብስቦ ተከማችቶ ነበር።

ይሁንምና ከቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድ እና ከሀዲስ አለማየሁ ፯ኛ ክፍለ ጦር  በየቦቅላ አባይ ብርጌድ፣ በተድላ ጓሎ ብርጌድ ተከቦ ጠላት መውጫ መግቢያ አጥቶ የተፈጠረበትን ቀን እስኪረግም ተወግሯል።

በደንበጫ ወረዳም በተካሄደ ውጊያ ደንበጫ ከተማ እና ዳባ ላይም ጠላት ቀምሷል።

በዳባ ላይ በተደረገ ውጊያ ከቢቡኝ ወረዳ የኮረብታ ፋኖ እንዲሁም ከቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር በላይ ዘለቀ ብርጌድ እና የደንበጫ ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ታሪክ ሰርተዋል። ቀኑን ሙሉ በቀጠለው ውጊያ ጠላት ሬሳውን እና ቁስለኛውን ማንሳት አልችል ብሎ ውሏል።
ደንበጫ ከተማንም በከፊል ፋኖ ተቆጣጥሯት ነበር።

ብርሐኑ ጁላ በባህርዳር ከተማ ተገኝቶ የተሸለመው ካባ አዲስ አበባ ሳይደርስ እንዲሁም ያቀደውን እቅድ ለነፍስ አባቱ አብይ ሳይነግረው ያሰማራው ጦር እግር በእግር እየተመታና እየተሸነፈ ነው።


ምንጭ:- ©የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ታደገ ይሁኔ (ሸርብ)

https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

19 Nov, 07:05


ጎንደር አዲስ ነገር

ፋኖ ባለፉት 24 ሰአታት በመተማ ግንባር አስደናቂ ጀብድ ፈፅሟል።

ሰሞኑን ለ7 ቀናት በመተማ ግምባር በተደረገው ፍልሚያ 6  መስመራዊ አዋጊወች ተሸኝተዋል።
ሁለቱ ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው ናቸው ተብሏል::


በደቡብ ጎንደር ቀጠናም በእስቴ፣ በአንዳቤት፣በአርብ ገበያ ፋኖ ድል ቀንቶታል።


በሌላ መረጃ:-

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎቤ ክ/ጦር ለአማራ ህዝብ ህልዉና መረጋገጥ ዋጋ እየከፈለ በሚገኘዉ በአቶ ክርስቲያን ታደለ ስም ብርጌድ' ሰይሞለታል።

ጎንደር አልተቻለም🙏

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Nov, 20:32


ጎንደር

ገንፎ ቁጭ ቀጠና ውስጥ ወይዘሮ ጥሩየ የምትባል የአየር ጤና ቀበሌ የብልፅግና ፅ/ት ቤት ሀላፊ የነበረች ሴት ተላላኪ ባንዳ በመሆኗ የተነሳ ተደጋጋሚ ብትመከርም አልሰማም ብላ ዛሬ በቀን 9/03/2017 በፋኖ ቁጥጥር ስር ውላለች::

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Nov, 20:30


ጎጃም

ከእንጅባራ እና ቲሊሊ የተነሳው የአገዛዙ ጥምር ጦር ከቲሊሊ ወደ ረቡዕ ገበያ ዳንጊያ ኪዳነ-ምህረት፣ እንዲሁም ከእንጅባራ ሻራታ ጊዎርጊስና ጃንጉታ በመግባት በሞርታርና መድፍ ሽፋን በማድረግ ባንጃ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ቀሌዎች ላይ አሰም ስላሴ፣ ኳንቻ አቦ  እና አከና ጂፊ ቀበሌዎች ላይ ንፁሀንን እረሽኗል።

ጃንጉታ ጊዮርጊስ ላይ ወፍጮ ያላቸውን ሰዎች ሌሊቱን ሲገርፍ አድሯል። እናትና አባቶችምንም የፋኖ ወላጅ ናችሁ በማለት እየገደለ እደበደበ ይገኛል። የስሜነህ ደስታ ብርጌድ አርበኞች በቆራጥነት ተፋልመውታል። ከዘንገና ብርጌድና ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌዶችም ድጋፍ ለማድረግ ተንቀሳቅሰው አስፈርጥጠውታል !

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Nov, 19:31


9 አውደ ውጊያ በአንድ ቀን የአማራ ፋኖ በጎጃም
=================================
ህዳር 9/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎጃም
     ረቡዕ ገበያ፣ምርክታ፣ደንበጫ ከተማ፣ዳባ፣ቀኝ አቦ፣እነጋትራ፣አጋምና፣የሺሚት፣የሰንበት ላይ ከባድ ውጊያ ሲያደርግ ውሏል።

√#ረቡዕ ገበያና #ምርከታ ላይ የ3ኛ( ጎጃም አገው ምድር)ክፍለ ጦር ለ2 ቀን ያክል ጠላትን ሲቀጠቅጠው ውሏል።
   የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር
       #ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ(እንጅባራና አካባቢው)
       #ዘንገና ብርጌድ (ቲሊሊና አካባቢው)
       #ጊዮን ብርጌድ (ሰከላና አካባቢው)
       #፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ (ፋግታ ለኮማና አካባቢው)
በጥምረት ባደረጉት አውደ ውጊያ ቁጥሩ ያልታወቀ የብርሃኑ ጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።
√ #ደንበጫ ከተማ ላይ የ6ኛ(የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክ/ጦር #ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ 2 ሻለቃ ጦር በማስገባት ጠላትን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ደንበጫ ከተማን ለረጅም ሰዓት መቆጣጠር ችሏል።

√#ዳባ ላይ የ6ኛ(የቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክፍለ ጦር
      #ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ
       #በላይ ዘለቀ ብርጌድ እንዲሁም
     #ከ2ኛ(ተፈራ ዳምጤ) ክፍለ ጦር #መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ
  በጥምረት ባደረጉት ውጊያ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።ከሞት የተረፈው የጠላት ኃይል እስከምሽት ድረስ ሙትና ቁለኛውን እያነሳ ይገኛል።

√#ቀኝ አቦ(ቢሮ) ከሚባል ቦታ ላይ የ6ኛ(ቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክፍለ ጦር #ንጉስ ተ/ሃይማኖት ብርጌድ ና ከ7ኛ(ሐዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #የየቦቅላ አባይ ብርጌድ በጥምረት የአብይን ገዳይ ቡድን ከደብረ ዘይት ተነስቶ ወደ የቦቅላ ለመግባት ሙከራ እያደረገ እያለ በከበባ ሲቀጠቀጥ ውሏል።በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።

በዛሬው እለት ከአምስት አቅጣጫ (ከደ/ማርቆስ፣ከሉማሜ፣ከአምበር፣ከደብረ ዘይት) ብዙ ቁጥር ያለው የአብይ ጭፍራ ወደ የቦቅላ ለመግባት ሙከራ ያደረገው የጠላት ኃይል በጀግኖቹ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ተቀጥቅጦ ያሰበውን ሳያሳካ ሙትና ቁስለኛውን ጭኖ ተመልሷል።

√#እነጋትራ ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #መብረቁ ብርጌድ 2ኛና 3ኛ ሻለቆች ጠላትን በደፈጣ በመያዝ እያባረሩ ሲረፈርፉት ውለዋል።

√#የሻሚትና #አጋምና ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #ደባይ ጮቄ ብርጌድ ወደ ቀኝ አቦ በመሄድ ላይ የነበረን ጠላት ከበባ ውስጥ በማስገባት ሲለበልበው ውሏል።

√#የሰንበት ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር
       #የቦቅላ አባይ ብርጌድና
       #መብረቁ ብርጌድ
በጥምረት የብርሃኑ ጁላን ጨፍጫፊ ቡድን እያባረሩ ሲደመስሱት ውለዋል።
ሲጠቃለል እጅግ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

   የአብይ ገዳይ ቡድን እንደተለመደው የንጹኃን ግድያ፣የንብረት ውድመት፣የአርሶሩን ሰብል በከባድ መሳሪያ ሲያቃጥል ውሏል።የየሰንበት 2ኛ ደረጃ ት/ቤትን ንብረት በሙሉ ጭኖ ወስዶታል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

ዮሃንስ አለማየሁ
የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ቃል አቀባይ



https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Nov, 18:04


የአማራ ሰሜን ኮሪያ የምንላት የየጁዋ እመቤት ወልዲያ ከተማ ውስጥ ከባድ ጦርነት ተቀስቅሷል:: ከሼሁ ስታዲየም ሜካናይዝዱ ሰራዊት የሚተኩሰው ከባድ መሳሪያ አልጋ ይወዘውዛል:: ጄኔራል መድፍ ነው መሰል ከእስከዛሬው ይለያል::

የመረጃ ምንጮች

እሳቱ ብዕረኛ


https://t.me/Lsaneamara2129
https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Nov, 16:20


👍👍👍
ጎንደር አንዳቤት

ጥላት ደቡባዊ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ አይቀጡ ቅጣትን ተቀጥቶ የተረፈ ሀይሉን ይዞ አንዳቤት ወረዳን ሙሉ ለሙሉ ለቆ ፈርጥጧል

https://t.me/Lsaneamara2129
https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Nov, 16:13


የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ በፋኖ ዘውዱ ዳርጌ የሚመራው ካላኮርማ ክፍለጦር ራያ ቆቦ አራዱም ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

ሰሞኑን ከራያ ቆቦ አራዱምና መንጀሎ እስከ ጎብየ በርካታ ተጋድሎዎችን እያደረገ ያለው ካላኮርማ ክፍለጦር ዛሬ ህዳር 9/2017 ዓ.ም ንጋት አራዱም ጎሊና ወንዝ ላይ ከቆቦ ከተማ ወደ ወልድያ መስመር ይጓዝ የነበረ የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ በፈፀመው ደፈጣ ጥቃት በርካታ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛዉን በስድስት ባጃጅ ሲያመላልስ የዋለ ሲሆን የተረፈው የጠላት ሰራዊትም ገሚሱ አጋጣሚዉን ተጠቅሞ የጠፋ ሲሆን የተረፈው ተበታትኖ ማሽላ ለማሽላ እግሬ አውጭኝ ብሎ እንደተለመደው ፈርጥጧል ሲል የካላኮርማ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ አታሎ ፈንታው ገልጿል::

የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊው  ገልጿል።


https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Nov, 16:09


Channel photo updated

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Nov, 15:39


የተከበራችሁ የልሳነ አማራ ተከታታዮች በጣም ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በአንዳንድ አጋጣሚዎች ምክንያት መረጃወችን በሚገባ ባለማድረሳችን።
አሁን ላይ ወዴ መደበኛ ስራችን ስለተመለስን በቀጣይ መረጃወችን ትንተናዎችን አልፎም ድሎችን የምናበስራችሁ መሆኑን ስገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ።

https://t.me/Lsaneamara2129
https://t.me/Lsaneamara2129

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

15 Nov, 16:48


መረጃ ደጀን

ህዳር 06/2017ዓም

  የአገዛዙ ተላላኪ ሠራዊት እና ሆድ አደሩ የደጀን ወርዳ ፖሊስና ሚሊሻ ከህዳር 3/2017ዓም እስከ ህዳር 6/2017 ዓም ደጀን ወረዳ ኩራር ቀበሌ ንፁሀን የደጀን ወርዳ ኖሪዎችን ማሰሩን በውስጥ የመርጃ ምንጭ አርጋግጠናል።በደጀን ወርዳ የገጠር ቀበሌዎችና ከደጀን ከተማ የታፍኑበት ቀበሌ እና ቀጥር በተመለከተ:-ገልገሌ ቀበሌ 3 ሰው ፣ከየትኖራ ቀበሌ 3 ሰው፣ ከዘመትን ቀበሌ 6 ሰው ከደጀን ከተማ 6 ሰው፣ከኩራር ቀበሌ 24 ሰው ድምር 42 ንፁሀን የደጀን ወርዳ ኖሪዎች የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ በሚል ምክንያት በደጀን ወረዳ የሚገኜው የአገዛዙ ሰራዊት እና ሚኒሻ ፖሊስ ንፁሃንን አስረው እያሰቃዮ ይገኛል።ከታሠሩት ንፁሀን የደጀን ወረዳ ኖሪዎች መካከል:-👇👇👇
1,አቶ አለማይ ውድነህ
2,አቶ ታሪክ አለማይ
3,ወ/ሮ መለሰች ጌታቸው
4,ህፃን በረከት ደምስ
5,አቶምሬ ሁነኛው
6,ወ/ሮ አረጋሽ ጫኔ
7,ወ/ሮ አለምነሽ ምሬ
8,ወ/ሮ ተግባር መስፋን
9,ወ/ሮ ሃይማኖት ወለላው
10,ህፃን ሀይማኖት አንተነህ
11,ህፃን አበበች አንተነህ
12,ህፃን ባንቺ አለም አንተነህ
13,አቶ አበባው መኩ
14,ወ/ሮ መአዛ ጥላሁን ከነ ልጇ
15,ወ/ሮ በእናት ጥላሁን ከነልጇ
16,አቶ ሞሱ ሙሉ
17,ወ/ሮ አዳነች
18,ወ/ሮ አድና በለጠ
19,አቶ ገብሩይርዳው
20,ወ/ሮ ዘቢደር
21,አቶ ሃብታም መኮነን
22,ወ/ሮ ትሁኔ ሹመቴ
23,አቶ አያሌዎ ተሰማ
24,ወ/ሮ አበቡ አፍራሽ
25,አቶ እንዳለው አያሌው
26,ወ/ሮ አንቺንአሉ አያሌው
27,አቶ አበጀ አያሌው
28,አቶ አስችለኝ አያሌው
29,አቶ አያሌው ካሳው
30,ወ/ሮ እቴነሽ አለሙ
31,አቶ አለኸኝ አያሌው
32,ወ/ሮ ቻይና ጌቴ
33,ወ/ሮ ሙሉ አለም ታደሰ
34,ወ/ሮ አበባ ልየው
35,አቶ አለሙ ሙንየ
36,አቶ ሙንየ አቦየ
37,ወ/ሮ ተብለጥ አስረስ
38,ህፃን ውድነሽ ሃብቴ
39,ህፃን መስከረም ሃብቴ
40,ወ/ሮ እታገኝ ይትባረክ
41,ወ/ሮ በላይነሽ ደረሰ
42,ወ/ሮ አለምነሽ ጌቶ
የተባሉ ግለሰቦች በአማራ ፋኖ በጎጃም በላይ ዘለቀ 8ኛ ክፍለ ጦር የመርጃ ደህንነት ክትትል የአገኜናቸው ሲሆኑ አነዚህ ንፁሃን በደጀን ወረዳ ኩራር ቀበሌ በአገዛዙ ታግተው እየተሰቃዮ ይገኛሉ።የተቀሩት የደጀን ወርዳ ንፁሃን ደግሞ ዘራፌው የብልፅግና ወንበር ጠባቂ ሀይል ፈርተው ከቀያቸውን ለቀው በበርሃ በርሃብ እና ውሃ ጥም አየተሰቃዩ ይገኛሉ።መርጃው ሸር ይደረግ

Yibeltal Getie Mitiku

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

15 Nov, 16:31


#የኮሎኔሉ_ጩኸት_በባህርዳር

ሻዕቢያ የኢትዮጵያን መከላከያ ለመገዳደር ሰላሳ ዓመት ፈጅቶበታል ( 30 ዓመት) ፤ወያኔ በድጋሜ የኢትዮጵያን መከላከያ ለመገዳደር  አስራ ሰባት ዓመት (17 ዓመት)  ፈጅቶበታል ፋኖ ግን ፋኖ ግን ለመገዳደር አይደለም ለማፈራረስ  አንድ አመት (1 ዓመት) አልፈጀብትም ስለዚህ ነጋዴው የማህበረሰብ ክፍል እባካችሁ ከጎናችን ቁሙ ።ኮሎኔል ጌታቸው ባህርዳር አቫንቲ ሆቴቴል ነጋዴውን የማህበረሰብ ክፍል ሰብስበው ከተናገረው😂😂😂-

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

14 Nov, 18:32


የአሳምነው ቀኝ እጅ ፋኖ መንበረ አለሙ በዛሬው  የችሎት ውሎ የተናገረው‼️

ፈፅመሀል የተባልሁትን ወንጀል አልፈፀምሁም።  ለዚህ የልብ ወለድ ክስ የዳረገኝን የpoletical motive በተመለከተ ግን አንድ ነገር ማንሳት እፈልጋለሁ። አለም በአንድ ድምፅ ያወገዘውን፣ በጥቁር መዝገብ የመዘገበውን፣ በናዚው ፊትአውራሪ ሂትለር አማካኝነት በይሁዳዊያን የተፈፀመውን የዘር ማፅዳት በሚያስንቅ ሁኔታ አማራወች ላይ ባለፉት 6 ዓመታት የዘር ማፅዳት ሲፈፀም አይተናል።

አማራ በመሆናቸው ከ15 በላይ የዩንቨርሰቪቲ ሴት ተማሪወች እንደወጡ ቀርተዋል፣ ህፃናት፣ አዛውንት፣ እመጫት ንፁሀን አማራወች በተኙበት ቤታቸው ከውጭ ተዘግቶባቸው በእሳት ተቃጥለዋል፣ ነፍሰ-ጡር እናቶች የአማራ ፅንስ እንዳይወልዱ በእንጨት ተቀደው ፅንሱም እነሱም ሲገደሉ ተመልክተናል፣ አማራ መሆን ቀርቶ፤ የአማራ እንስሳት መሆን እንኳን ወንጀል ሆኖ በሬወቹ እነ ጮሬ፣ ላሞቹ እነ አደይ፣ ፍየሎቹ እነ ጠዲት፣ ስንዲት በጋጥ እንደተዘጉ ተቃጥለዋል።

አማራወች ለስብሰባ እየተጠሩ ታርደዋል፣ በጅምላ የዘር ፍጅት ተፈፅሞባቸው፣ በጅምላ ተገለውም የሰውነት ክብረ-ፀጋው ተነፍጓቸው ከሞላው የአማራ መሬት ለአማራወች አስከሬን 3 ክንድ መሬት መቃብር ተነፍጎት በጅምላ በዶዘር ሲቀበሩ አይተናል ተመልክተናል። እኔ ይሄ ሁሉ  ግፍ የሚፈፀምበት፣ሳይበድል የተፈረደበት፣ መከረኛ ህዝብ አካል በመሆኔ እና እንደ አንድ የተማረ ሙህር አማራን የማፅዳቱን ወንጀል በመቃወሜና በመሞገቴ ብቻ ወንጀለኛ ነህ ተብየ በመንግስት አይነተኛ በትር በሆነው #አቃቢ_ህግ የልብ-ወለድ ክስ ተመስርቶብኛል። እኔ ላይ የተፈጠረው ነገር:-

''በገብረማሪያም ሰርግ፣ ወልደማሪያምን እንደማወደስ'' የሚቆጠር ነው!  አማራን በጅምላ የሚገሉት እና የሚያስገድሉት በህግ ሊጠየቁ ይገባል በማለቴ፣ ንፁሀን አማራወችን ገዳይ እና አስገዳይ ቁመው ሊጠየቁበት በሚገባው የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ-ቤት  እኔ ከተገዳዩ እና የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት ካለው አማራ በመወለዴ በሀሰት ተከስሻለሁ።

እኔ ግን እላለሁ:-

➧ፋሽስታዊ የሆነው ስርዓት በሚቃወመው የፖለቲካ አመለካከቴ፣

➧ አማራዊ በሆነው ማንነቴ እና ህያው በሆኑት አባቶቸ
#አጤ_ምኒሊክ እና #ጀኔራል_አሳመነው_ፅጌ ስም ምየ የምነግራችሁ በግልም ሆነ በቡድን ፈፅመሀል የተባልሁትን ወንጀል አልፈፀምሁም።

ወንጀሌ አማራ ሁኘ መወለዴ እና የአማራን ዘር ማፅዳት ተቃውሜ በመገኘቴ ብቻ ነው። ይሄን ደግሞ ቀጣይም እስከ መጨረሻዋ እስትንፋሴ የማደርገው ነው። ለታሪክ ይመዝገብልኝ አመሰግናለሁ።

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

13 Nov, 07:52


በዘር ይሁን - 13 ፕሮጀክት የተሰራ !

           በፋኖ ሳይንቲስቶች የተሰራ ፀረ ተሽከርካሪና የቡድን መሳሪያ ሲሆን በአንድ ጊዜ ስድስት ተተኳሾችን የሚሸከም ሲሆን እስከ ሀያ ኪ.ሜ ድረስ ውጤታማ መሆኑ ታውቋል። ይህ የቡድን መሳሪያ በወጣት ፋኖ ሳይንቲስቶች የተሰራ ሲሆን በሪሞት መተኮስም እንዲችል ሁኖ የተሰራ ድንቅ ፈጠራ ነው።

       " የታላላቅ ህልመኞች ልጆች ነን። ህልም ደግሞ በታላላቅ የመፅሀፍ ገፆች ብቻ ሳይሆን በDNAም ይተላለፋል። ይሄ ግኝት የአማራ ፋኖ በጎጃም ንብረት ብቻ ሳይሆን የመላው አማራ ሀብት ንብረት ነው።" ሲሉ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰብሳቢ ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ገልፀዋል።

ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የአባቱን የአፄ ቴወድሮስን ራዕይ ወራሽ ጀግና !

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

13 Nov, 05:20


የመረጃ ምንጭዎ፣


በአራቱም አማራ ግዛቶች (ወሎ፣ ሸዋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር) አካባቢና በሌላውም የአገር ውስጥ ስላለው የፋኖ ትግል እና የመከላከላያ እንቅስቃሴ እንዲሁም አጠቃላይ ሁኔታ መረጃ ለማግኘት የነገደ አምሐራ ሚዲያን ይወዳጁ

@Negedeamharas
@Negedeamharas
@Negedeamharas 👈 ይቀላቀሉ

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

24 Oct, 18:30


ሂሳቡን ስራው እያሉ የሚመፃደቁ የአገዛዙ አፈቀላጤዎች የዘመቻ 100 ተራሮችን ሪፖርት ሂሳብ ሰርተውት ይሆን? 

ከሻለቃ ዝናቡ ሪፖርት እንደተረዳሁት በ2 ሳምንት ውጊያ 1,305 ያህል ወታደሮች የአብይ አህመድን እብደት ለማስቀጠል ሲዋጉ ተደምስሠዋል።  በተመሳሳይ 699 ያህል ተማርከዋል፤ የቆሰሉት ደግሞ 418 ያህል ናቸው።  ይሄ ቁጥር የአብይ አህመድ እግረኛ ወታደር አቅም ለፋኖ ሃይሎች ስጋት አለመሆኑን ይነግረናል።

በዚህ ኦፕሬሽን የተገኘው የጦር መሳሪያ በብዛትም በዓይነትም ከዚህ ቀደም በ1 ኦፕሬሽን ከተገኘው ከፍተኛው ይመስለኛል። 120 ሚ/ሜ ሞርታርን ጨምሮ 882 በላይ ክላሽንኮቭ፣ ዲሽቃዎችና ከ23 በላይ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች 100 ሺህ ገደማ ከሚጠጋ ተተኳሽ ጋር መማረካቸውን ከሪፖርቱ ለመረዳት ይቻላል።

ሂሳቡን ስሩት እያሉ የድሃ ልጅ ወደ እሳት የሚከቱ ሰዎች ይህ መሰሉ ሽነፈት የ አበዳሪዎች ዶላር፤ ታሪካዊ ጠላትህን ግጠም እየተባለ የሚመለመለው የኦሮሞ ወጣት ሞት በቃኝ እስካላለ ድረስ  የሚያስደነግጣቸው አይመስልም። "የህልም ጉልበት" ወደሚል መፈክር የተሸጋገሩት ብዐዴኖችም ከባህር ዳር እስካልተነቀሉ ድረስ ሌላው እንደ አርማጌዶን ቢሆን የሚያሳስባቸው ጉዳይ አይደለም።

ጦርነቱን ለማሳጠርም ሆነ ህመሙ የማይሰማቸው ሰዎች እንዲሰማቸው የማድረጉ ጉዳይ በፋኖ እጅ ያለ ካርድ ነው።  በጣም እርግጠኛ ሆነን መናገር የምንችለው ነገር አብይ አህመድ ይህ ጦርነት እንዲቆም ፈጽሞ አይፈልግም። በብልጽግና አጠራር የኛ የሆነ የሚባል ህዝብ አለ። ያ ህዝብ  እስካልተነካ ድረስ ሌላው ህዝብ ቢጨፈጨፍ የበረሮና ትንኝ ተረት እየተተረተበት ሞቱ የቤተ መንግስቱ የምሽት ሳቅ ማድመቂያ ሆኖ ይቀጥላል። ምናልባት ጦርነቱ የብልጽግና ወደሚባሉት ዜጎች ደጅ ከደረሰ ሌላኛው የብልጽግና ገጽ ይገለጥ ይሆናል።

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

24 Oct, 15:01


ሰበር ዜና!

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በተኩስ እየተናጠ ነው።

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓም ኢትዮ 251 ሚዲያ።

ይህ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ሰዓት ባህርዳር ከተማ ላይ የሚገኘው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ጣቢያው በተኩስ እየተናጠ ነው።

የአማራ ፋኖ በጎጃም አንደኛ ክፍለ ጦር ባህርዳር ብርጌድ በላይ ሻለቃ በአሁኑ ሰዓት በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋናው ጣቢያ ለይ የቦንብ ጥቃት መፈፀሙን ለኢትዮ 251 ሚዲያ አሳውቋል።

በዚህ ተቋም ላይ በፋኖ ሀይሎች የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎም የአገዛዙ ሀይሎች በንፁሀን መንደሮችና በባህርዳር ከተማ ባሉ በርካታ ትምህርት ቤቶች ላይ ጭምር  በህፃናትና ንፁሀን ላይ የቦንብ ጥቃቶችን እየፈፀመ እንዳለ የኢትዮ 251 ሚዲያ የመረጃ ምንንጮች ገልጠዋል።

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

24 Oct, 05:23


"ልዩ ዘመቻ በቅርቡ እናውጃለን፤ ሕዝባችን ይዘጋጅ!" ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው!

ከአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የተሰጠ መግለጫ!

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

20 Oct, 08:48


«በአዲሱ ዘመቻ እና ድሎቹ እንገናኛለን!» -አርበኛ ዘመነ ካሴ

“ከግድያ ሙከራ መትረፍ  የኦሎምፒክ ውድድር ቢሆን ኖሮ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፍ ነበር።"-ይህን ያለው ከ600 ጊዜ  በላይ ከግድያ ሙክራዎች እንዳመለጠ የሚነገርለት የቀድሞው የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ነበር።

የግድያ ዜና በ 2025ቱ ( የፈረንጆች አቆጣጠር) የጃፓን ቶክዮ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አንዱ የውድድር አይነት ከሆነ በሰሞኑ የነ አብይ አህመድ የተስፋ መቁረጥ "የገደልነው ዘመቻ" ብቻ ወርቅ ባላገኝ የብር ሜዳሊያ አላጣም። የመለያ ቁጥሬም 21-12 ይሆናል።

•በሁሉም ረገድ፣ በሁሉም ሰበብ እና ምክንያት ልትጠልፉኝና ልታጠለሹኝ የሞከራችሁ እና በየቀኑ የምትሞክሩ ሰዎችና ቡድኖች መጨረሻችሁ ውርደት እና የእድሜ ልክ መሸማቀቅ እንደሚሆን ዛሬ ድረስ በጥቂቱ በምታውቁት፣ነገና ከነገ ወዲያ ደግሞ ሰፊውን ማንነቱን በምትረዱት በዘመነ አምላክ ስም እነግራችኋለሁ። አምላኬ ይቅር ይበለኝና ብዙዎች አይሆን ሞክረውኝ፣ ደጋግመው ሞካክረውኝ መጨረሻቸው የሌባ ጣት ጥፍራቸው ውስጥ መደበቅ ሆነ። (ድንግል ማርያምን ያሳዝኑኛል።)

የቀብሮ ጫጫታ የማያስደነብረኝ፣ጀርባዬ ላይ ሊወጣ የሚሞክረው ሁሉ ቢሳካለት እንኳን የማይከብደኝ "ዝሆን" ነኝ።በቃ እንደዚህ ነው የሰራኝ።

•ከንግስና ዙፋንና ዘውድ ጀምሮ በተለያዩ የህዝብ አስተዳደር እርከኖች እና ሃላፊነቶች እስከ ጦር ሜዳ ውሎዎች  በብዙ ፈተና መሃል እያለፈ ሃገር የገነባ ቤተሰባዊ ማንነትና የመከራ ዘመን በቅጡ የገነባኝ ሰው ነኝ።በአለሙ ውስጥ በማንኛውም ሁኔታ  እንደ ህፃን በደስታና በሃዘን በእምባ የምሟሟ ተራ ሰው፣ ምድራችን በድንገት ጨረቃ ብትሆን እንኳን የማይጨንቀኝ ልበ-ሙሉ "ጨካኝ" ፍጡር ነኝና በጅራፍ ጩኸት ልታስደነብሩኝ የምትሞክሩ የዋሆች አትድከሙ።

•እኔና ጓዶቼ ፣ከትውልድ አጋሮቻችን ጋር እንደምናሸንፍ የተፃፈው የእናቶቻችን ማህፀን ውስጥ እያለን ነው።ወኔና ድል አድራጊነትንም የተጋትነው  በእትብት ነው።ይህ ትውልድ አሸናፊ ትውልድ ነው።ልድገመው!ይህ ትውልድ  የአሸናፊነት  እጣፋንታውን ግንባሩ ላይ ተነቅሶ ወደዚህ ምድር የተላከ ትውልድ ነው። እየታገለ ነው ፥ድል አድርጎ የአማራን ህዝብ ህልውና በፀሃይ ፊት ያረጋግጣል።

ይህ ትግል ለትግሉ ብቻ የተሰጠ እና የሚሆን ራሱን የቻለ ልዩ ነፍስ ይፈልጋል። እንጨት እንጨት የሚል ሰዋዊና ፖለቲካዊ ስብእና ተይዞ ፥ነፍስን ቅናት፣ምቀኝነትና ተንኮል በሚባሉ የመንፈስ ቆሻሾች መርዞ ታጋይም አታጋይም መሆን አይቻልም። እና "ልፋ ያለው በህልሙ ዳውላ ይሸከማል" እንዲሉ በብዙ የተበከለች ነፍስ ተሸክማችሁ ለ ደካማ ተልእኮ አጉል የምትደክሙ ወገኖች ከድል ሃውልት ውጭ ከፊታችን መቆም የሚችል ነገር የለምና ነፋስን ለማሰር በመሞከር ጊዚያችሁን አታጥፉ። ይህ ትውልድ እያለ የአማራን ህዝብ ጉልበት መሬት አታስነኩትም። በኩራት ቆሞ ገጥሟችኋል፥ ያሸንፋችኋል።

እና በባንዶች ፊታውራሪ በተመስገን ጥሩነህ አገላለፅ "ዘመነን አስወግደነዋል፥ ከዚህ በኋላ ድምፁን አትሰሙትም" የሚለውን የሰሞኑን ብልፅግናዊ አዲስ መዝሙር ስቃችሁበት እለፉ።ሌት ተቀን እያቀድንላቸው ነው።ከጠፋሁም ያጠፋኝ የጠላት ስሥ ብልት ልየታ ቢዚ አድርጎኝ ነው።የዘመነ ትውልድ የአለማችን እድለኛና ገድለኛ ትውልድ ነው።መንጋው እንዲበተን እረኛውን ምታው የቆዬ ብሂል በኛ ትግል ውስጥ አይሰራም።ትግሉ ሚሊዮን እረኞች ከበውታል፥መንጋው ራሱ ረኛ ከሆነ አመታት አልፈዋል።

ዘመነ የእናንተን ሞት ቆሞ ለማዬት ለተአምር ተፈጠረ እንጅ በዘመነ መጥፋት ለአንድ ሴኮንድ እንኳን የሚንገራገጭ ትግል የለም። ይህ ትውልድ ከቀደምቶቹም ከነገዎቹም ትውስታና መንፈስ ቀድቶ የትሸከመውና ያጎለበተው ከእድሜውና ተሞክሮው በላይ ያበሰለው አንዳች ነገር አለው።ስለሆነም ያሸንፋል።
ይኸው ነው! በአዲሱ ዘመቻ እና ድሎቹ እንገናኛለን!!

አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ
አርበኛ ዘመነ ካሴ
ጥቅምት 10 ቀን-2017 ዓ.ም

#Amhara #Ethiopia

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

18 Oct, 19:30


አማራ በዚህ ጥልቀት ርህራሄህን በጭካኔ ቀይረህ ምርር ብለህ ለህልውናህ ታገል ..‼️‼️

ኦሮሙማ ውጊያ ሲያቅተው ንፁሀንን

የምንታገለው የግለሰብ እና የቡድን ፍላጎቶችን ሳይሆን ለህልወናችን ነው።

ይህ ድምፅ እድል አግኝተው ድምጻቸው ሳይለማ ታፍኖ በየቤታቸው በሀዘን ተኮራምተው እየማቀቁ ያሉትን እልፍ የአማራ እናቶችን ድምፅ ይወክላል።

እናት
" በእኩለ ሌሊት አጠፉኝ።በእኩለ ሌሊት አጠፉኝ።ልጄን ካሳደግኩ በኋላ ።ከእኔ ወሰዱት።በእኩለ ሌሊት ከእኔ ወሰዱት። በእኩለ ሌሊት ከእኔ ወሰዱት ።" 🥲

ጥያቄ ፡ የሟች ስም ማን ይባላል?
ወንድም ፡ መዝገቡ
ጥያቄ ፡ መዝገቡ ማነው?
ወንድም ፡ መዝገቡ ታደለ
ጥያቄ ፡- መዝገቡ ታደለ ላንተ ማን ነው?
ወንድም ፡ ወንድሜ
ጥያቄ ፡ ታላቅ ወንድምህ ነው?
ወንድም ፡ አይ ታናሽ ወንድም
ጥያቄ ፡ እሱ ታናሽ ወንድምህ ነው? ዕድሜው ስንት ነበር?
ወንድም፡ 7

እናት፡
"ከእኔ ወሰዱት፣ ልጄን ከእኔ ወሰዱት። ልጄ፣ ልጄን ከእኔ ወሰዱት። ከእኔ ወሰዱት። " 🥲

" ማነው ከጎኔ የሚሆነው? ልጄ ከጎኔ ሳልኖር እንዴት እተኛለሁ? " 🥲🥲

"ልጄን ወሰዱ፣ ልጄን ወሰዱት። እነዚያ ጭራቆች ልጄን ወሰዱት። " 🥲

ጥያቄ ፡ እንዴት ሞተ?
ወንድም፡- ድሮን አድማ

እናት፡
" ምን አደረጋቸው? ምን አደረገላቸው? ለምን እንዲኖር አልፈቀዱለትም? ለምን እንዲያድግ አልፈቀዱለትም? 🥲

መታሰብ ያለበት ነገር እንዴት ይበልጥ በህብረት መታገል አለብን የሚለው ደምቆ ይሰመርበት‼️‼️

*_*_*_*_*
"
#ወሎ#ጎጃም#ጐንደር#ሸዋ የአካባቢ መጠሪያዎች እንጂ አማራ ዝንታለም አንገቱ አንድ ነው

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

11 Sep, 06:21


በዱር በገደሉ ላሉ ሁሉ ፋኖዎች እንኳን አደረሳችሁ ..🌼🌼

ፋኖነት መንፈስ ነው የጀግና ልጅነት የሚወረስበት
ፋኖነት አቅም ነው የጀግና ጉልበት የሚታደስበት
ፋኖነት ጥበብ ነው ልብ የሚበራበት፤ ፋኖነት ጥበብ ነው ታዳሚ ያለበት
ፋኖነት ረቂቅ ነው ሁሉም የሆነበት
ፋኖነት ሀሳብ ነው
በልባችን ፅላት ነው የተሞሸረው
ቃርሚያ ውስጥ ያደጉ የነቀርሳ እባጮች
አፍ ሲከፍቱ ታዩ በዚህ ቆራጥ ዘማች
ፋኖነት አይወይብ፣ አይገረጣ ቶሎ
ሲዘከር ይኖራል  በድፍረት ተንጣሎ
ተምጦ ተወልዶ ተጠምቆ በብሶት 
የሀገር መቋሚያ ነው የሚመረኮዙት
ፋኖነት ሀሳብ ነው
በልባችን ፅላት ነው የተሞሸረው
ፋኖነት መንገድ ነው መቋጫ የሌለው
በትውልድ መካከል  የሀረግ ገመድ ነው
ሁላችን ፋኖ ነን፤ ማን ከማን ይለያል
ባርነትን ጠልተን ነፃነት ናፍቆናል
ፋኖነት ራዕይ ነው ነፃ ሚወጡበት
ፋኖነት ሀሳብ ነው ትጥቅ ማይፈታበት
ፋኖነት ታሪክ ነው እውነት የሚያድርበት 
ፋኖነት ኩራት ነው አማራነት የሚፈካበት፡
ፋኖነት ኩራት ነው ወገን ሚድንበት፡፡
ፋኖነት ኩራት ነው ሀገር ሚድንበት፡፡

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

11 Sep, 06:17


ታሪክ የማይዘነጋት ክህደት

በቀይ ቀለም ተቀልማ ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን ማስተማሪያ የምትሆን ታሪካዊ የክህደት ምሳሌ ናት ይህች አሁን በክርስቲያን ታደለ ላይ የተፈፀመች ክህደት::

እሱ ወንድሜ ባላቸውና እነሱ ግን አማራዊ ወንድማማችነትን ለምግብና መጠጥ ብለው ክደው ከጠላት ኦሮሙማ ጋር አብረው መረጃ ማቀበል "የሀሰት ምስክርነት" የፈፀሙ የታሪክ ተወቃሾች::

የኦነጉ አቃቢህግ በክርስቲያን ታደለ ላይ ባዘጋጃቸው ብዙ የፈጠራ ክሶች ላይ በሀሰት የመሰከሩ 5 የሀሰት ምስክሮችን ታሪክ ይቅር አይላቸውም::

የአብንን የስራ አስፈፃሚ አባላት ውይይቶች ድምፅ መቅጃ እየቀዱ ለኦሮሙማ ደህንነቶች ከማቅበል ጀምሮ የተቋሙን ቃለ ጉባዔ አሳልፎ እስከመስጠት የደረሰው ታሪካዊ ክህደት !!!

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

11 Sep, 05:21


የበዓል አከባበር የጥንቃቄ መልዕክት
***
የአዲስ ዓመት በዓል ስናከብር ካለንበት ወቅታዊ የትግል ሁኔታ አኳያ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊሆን እንደሚገባ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የጥንቃቄ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

በዓላት በመጡ ቁጥር የደም ግብር የለመደው የብልጽግና አገዛዝ የሚሸርባቸው ክፉ ሴራዎች በመኖራቸው፣ በዓሉ ሲከበር በመላው ሕዝባችን ዘንድ ጥበብ የተሞላበት የደህንነት ጥንቃቄ በመጠቀም የአገዛዙን ሴራዎች በማክሸፍ ሊሆን ይገባል፡፡

በተጨማሪም ለድሮን ጥቃት ተጋላጭ ሊያደርጉን ከሚችሉ መሰባሰቦችና የተጋላጭነት ሁኔታን የሚያሳድጉ ሁነቶችን ከመፍጠር ተቆጥበን፣ በተለመደው የመረዳዳት መንፈስ በዓሉ እንዲከበር ለሕዝባችን የጥንቃቄ መልዕክት እናስተላልፋለን።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ
ጎንደር፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ
ጷግሜ 5/2016 ዓ.ም.

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

10 Sep, 19:07


የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልእክት

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

10 Sep, 13:01


ሰበር የጀብድ ዜና ሸዋ | ሸዋሮቢት ከተማ ..‼️‼️

ሰበር መረጃ!! ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ሸዋሮቢት በሸዋሮቢት ከተማ የስረዓቱ አገልጋይ የባጃጅ አሽከርካሪ ወጣቶችን ሲያገላቱና የንግድ ሱቆችን ሲያፈርሱ የነበሩ ባንዳ የሚሊሻ አባላት እርምጃ ተወሰደባቸው በዛሬው እለት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ቃኝዎች ወደ ከተማው ገብተው ባንዳዎች ላይ እርምጃ የወሰዱ ሲሆን ግራ የገባው የፋሽሽት አብይ አህመድ ጎመን ሰራዊት በእውር ድንብር ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው ።

ድል ለአማራ ህዝብ !!
ድል ለአማራ ፋኖ !!

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

09 Sep, 17:51


ፋኖ ንጉስ አበራ የአማራ የክፉ ቀን ደራሽ!

ልጥጥ ያለ ህይወት ይኖር የነበረ፤ የአማራ ህዝብ በአገዛዙ የሞት አዋጅ ሲታወጅበት የቅንጦት ህይወቱን እርግፍ አድርጎ ትቶ ዱር ቤቴ ያለ የአማራ ደም መላሽ ነው።

የብርሃኑ ጁላን ሰራዊት በገፍ በመማረክ “10 አለቃ ብርሃኑ አይችልም፣ ፋኖ ምሬ ወዳጆ ይችላል” ስታስብለው የዋለችው ይች ሰው ናት!💪

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

09 Sep, 17:39


የዓመቱ ምርጥ ባንዳ DK

2016 ዓም ከተስተናገዱ ክስተቶች መካከል በእኔ እምነት በባንዳነት እና በወንጀለኛነት ይኼንን ግለሰብ የሚስተካከል የለም ።

* በአማራ ህዝብ ላይ የጥላቻ ንግግር ቀስቃሽ ማሽን !

* በአማራ ህዝብ ላይ የሃሰት መረጃዎች በመፈብረክ እና በማሰራጨቱ።

* በአማራ ህዝብ ላይ ጥቁሩ ናዚ ጥቃቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል በማቃጠር እና ህዝባችንን ትኩረት ያደረገ  አስነዋሪ ንግግሮችን በማህበራዊ ሚድያና በተለያዩ መድረኮች በማስተላለፉ ።

* ወልዳ አሳድጋ ኮትኩታ እከኩን ያራገፈችለትን እናት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጓዳ ጎድጓዳዋን ለጠላት አሳልፎ ሰጥቶ ለትልቅ ውርደት በመዳረጉ።

*በአለቅላቂነቱ

ስንቱን እዘረዝረዋለሁ ?

ለእኔ የ2016 ዓም ባንዳ እና ወንጀለኛ ግለሰብ ነው !!

እርግጠኛው ነገር ዐብይ አህመድ ቀድሞ ካልበላው የእኔ ትውልድ ለህዝብ ፍርድ ሲያቀርበው እዚሁ ሰፈር ተቀምጨ እመለከታለሁ።

በየአመቱ በአዲስ አመት መግቢያ FB እንዲያስታውሰኝ ለታሪክ እዚህ ይቀመጥ

ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

09 Sep, 11:40


አድማ ብተና 5ሻለቃ ሻንበል አዛዥና ከልዩሀይል ወደ ፖሊስ ተመድ ከፖሊስ ወድ አድማ ብተና በመግባት ሸዋሮቢት ከተማ ላይ ከአውሬው የአድማ ብተና አዛዥ ሻለቃ ፀሀዬ ጋር ሆኖ የሸዋሮቢት ወጣቶችን ሲደበድብና ሲያንገላታ የነበረው ዋና ሳጅን እንግዳው ንጉሴ በመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለጦር ከነነፍሱ ተይዞ መቷል !!