የሙሂ ማስታወሻዎች @sun_flowere Channel on Telegram

የሙሂ ማስታወሻዎች

@sun_flowere


የተለያዩ አጫጭር ማስታወሻዎችን እንዲሁም ለፕሮፋይል የሚሆኑ አስተማሪ ፁሁፎችን በዚህ ቻናል ያገኛሉ

Onther channel ↓
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


كنتم خير أمة أخرجت للناس تأمرون
بالمعروف و تنهون عن المنكر

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ

የሙሂ ማስታወሻዎች (Amharic)

የሙሂ ማስታወሻዎች በማድረግ ላይ አጫጭር አስተማሪ ማስታወሻዎችን የተለያዩ እና በማስታወሻ እንዴት ማለት ነው ድምፅ እንዲሆነ፣ ወደ ሌሎች ማስታወሻዎች ይቀርባል። የሙሂ ማስታወሻዎች በዚህ ቻናል መስራት ላይ የገና ለውጥና ለአባቶች ወዳጄ ተዋናይ እና ማልበስበስ ላኩ። የማስታወሻ ሌሎች ቻናሎች ወደሌሎች ትምህርት በመገኘት የሚፈልጉትን ይዘቱን እና ቀጥተኛውን ጨዋታዎችን እንሳል።

የሙሂ ማስታወሻዎች

29 Jan, 17:29


አብሽር ሲጋራህን ጥለህ መስጅድ ና!
ጫትህንም ተፍተህ ና።! ምንም አይነት ወንጀል ውስጥ በመግባትህና ሰዎች ማወቃቸው ግዴታ ከሆኑብህ ኢባዳዎች እንዳያዘናጋህ። ከሶላትህም በኋላም ሁሌም አላህ በላዓውን እንዲያነሳልህ ለምነው።



https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

28 Jan, 03:50


ፀፀት ማለት ተውበት ነው! አሉን ውዱ ነብይ(ስለዋቱ ረቢ ወሰላሙዓለይሂ)

ፀፀት ከሌለው ተውበታችን ትርጉም የለውም ማለት ነው። አንዳንዴ ደግመን ደጋግመን እንወነጅልና ልባችን ደንዝዞ መፀፀትንም ላናገኝ እንችላለን። ይሄ ከባድ አደጋ ነው።!
ስለዚህ ቶሎ እንመለስ ወንጀል ላይ አንዘውትር። ያረቢ ይቅር በለኝ እይታህን ረስቸ አይደለም ነፍሴ አታላችን ነው፣ አሁን ተመልሻለው፣ አልመለስበትም ያለፍውን ታረቀኝ እንበለው። አላህም በደስታ ነው መርሃባ አብሽሩ ባሮቸ የሚለን።!
ነገር ግን አልመለስም ብለን በወንጀላችን ከኮራን እንደራቅነው ይርቀንና ህይወት ጨልሞብን ዱንያ አኼራ ላይ ምንይዘው ምንጨብጠውን እንጣለን። ትልቁም ውርደት ይሄ ነው።!አላህ ይጠብቀን

እንመለስ ወደ አላህ ባረከላሁ ፊኩም


በዝሙት አንዘምን join& share
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

የሙሂ ማስታወሻዎች

27 Jan, 03:36


ውዷ እህቴ አማኙም ከሃዲውም እንዲህ ሚያሰፈስፍብሽኮ ንፁህነትሽን አውቆ ነው። ታዲያ አንችስ ንፁህን አትፈልጊም እንዴ ለመጣው ሁሉ መልስ ምትሰጭው?

ለሳቀው ሁሉ አትሳቂ ለሚጎትትሽ እምቢ በይ! ለራስሽ ህይወት ወሳኟ አንች ነሽ!



ወንድምሽ ሙሂ
join & shar👇👇👇
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

25 Jan, 15:53


አብሽሪ አላህጋ ያለሽን ሁኔታ አጠንክረሽ ትንሽ ሶብር አድርጊንጂ አላህ ጥሩ ባሮች ሞልቶታል በሃላል መንገድ ያመጣልሻል። የተመኩበትን አሳፍሯቸው አያውቅም ወላሂ!



https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

24 Jan, 15:51


ብዙዎቻችን እንዴት እንደምኖር እንጂ ለምን እንደምኖር አናውቅም! አላህ ያዘነለት ካልሆነ አኗኗራችን እንደ እንስሳ እየሆነ ነው።

እንበላለን እንጠጣለን እንተኛለን ኢባዳችንም ባህል ሁኖብናል ከመጥፎ ነገር እየከለከለን አይደለም።
አላህ ይዘንልን


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

22 Jan, 10:17


ዝሙት በደል ነው❗️

ማንን ነው ምንበድለው ካልን አላህን አይደለም ራሳችንን ነው።!


ከዚህ ቆሻሻ ከሆነው ዝሙት አላህ ይጠብቀን።! ትክክለኛ የአላህ ባሮች እንሁን። ጌታችን ባሮቸ ዝሙት አይሰሩም ብሎናል። ከተፈተንበትም ቶሎ ወደ ጌታችን እንመለስ። ከወንጀል የተመለሰ ልክ ወንጀል እንደሌለበት ነው። አላህ ባላችሁበት በረካ ያድርጋችሁ!


የሙሂ ማስታወሻዎች
join & share
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

21 Jan, 12:08


ዲን ባስተያየት አይደለም ወህይ ነው። ማናውቀውን እንጠይቅ እንጂ እንዲህ ቢሆን ብለን አናውራ።

የሙሂ ማስታወሻዎች

20 Jan, 16:07


ውዷ እህቴ ሃራም ተራ ነገር ነው እንደ ጀብድ እንዳታይው አይደለም በጅሽ ስልክ ኑሮ በእናት አባትሽ ስልክም ተጀናጅነሽ ዝሙት ላይ ልትወድቂ ትችያለሽ።


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

19 Jan, 10:56


እዚህ ቁንጅናሽ ላይ ሜካፕ ምትጨምሪበት ውበት ለመጨመር ከሆነ ከኒቃብ የበለጠ ያማረ መዋቢያ አታገኝም። ካላመንሽኝ ልበሽውና በመስታወት እይው ራስሽን!

ወታደር ጉልበት ባይኖረው እንኳ ዩኒፎርሙን ሲለብሰው ጀግንነት ይሰማዋል። አንችም ኒቃቡን ስትለብሽው ተሰምቶሽ ማያውቀው ደስተና ሰላም ይሰማሻል፣ ወደ አላህም የበለጠ እየተቃረብሽና ወንጀሎችንም ስትርቂያቸው ይታወቅሻል። ያም የሚሆነው ግን ለአላህ ብለሽ ከለበሽው ነው።
አላህ ይወፍቅሽ!


Share & join
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

18 Jan, 16:11


አላህ ሆይ ረመዳንን አድርሰን!

የሙሂ ማስታወሻዎች

17 Jan, 12:46


ለዲንህ ስትደክም ሲያዩህ ስራፈት፣ ሰነፍ፣ ቦዘኔ ይሉሃል ከአላህ እንድትርቅ...
አንዳንድ ሰዎች አላማቸው ዱንያ ብቻ ናት አምሮባቸው ተውበው መገኘትን እንጂ የተበላሽውን ነገር ማስተካከል አይፈልጉም። በነዚህ ሰዎች እይታ ወርደህ ነው ምትታየው። እና አብሽሩ ፈተና ነው እንዳትንሸራተቱ።



https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

15 Jan, 13:34


ቁንጅናሽጋ ሃጃ የለባቸውም ስጋሽን ነው ሚፈልጉት ጠንቀቅ በይ እህቴ ስሜቱን አምላኪው በዝቷል!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

13 Jan, 15:47


አብሽሪ ወላሂ ሪዝቅሽ እንዳያሳስብሽ ላንች ካለው የትም አይሄድም።! ሶብር አጠን ሪዝቃችንን ለማግኘት በሃራም መንገድ ሰበብ አደርሳለሁ ካልን ትርፉ ሪዝቃችንን ማጥበብ ነው።!

ሪዝቅ ማለት ጥሩ ፀጋዎች ሁሉ ናችው ኢማን፣ ትዳር፣ ልጅ፣ ጤና፣ ገንዘብ...


የሙሂ ማስታወሻዎች
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

12 Jan, 20:01


ወላሂ ልባችን ንፁህ ቢሆን ቁርአንን ባልጠገብነው ነበር!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

11 Jan, 13:57


የኢሳ ባሮች ሆይ! ጥያቄ አለን

የተረዳው ካለ መልሱን እንፈልጋለን

ጌታ ግፍ አቅቶት ሰዎች ከገደሉት

አለቀ አከተመ የታል አምላክነት?!

ፈጣሪዋን አጥታ አለም ስትዋትት!

ሰው ወደማን ነበር የሚያስበው ፀሎት?!

የሰማይ መላዕክት ምነኛ ለጎሙ?!

እጁ ተቸንክሮ ዋይታውን ሲሰሙ!

እንጨቱም ተዐምር ነው አቅሙ መቋቋሙ!

አምላክን ያክል ነገር ችሎ መሸከሙ

ኋላስ ራሱ ነቃ ከሞት አንሰራራ?!

ወይስ ጌታ አገኘ ህይወት የሚዘራ?!

ጉድ በሉ ለቀብር ጌታ አቅፎ ለያዘ!

የባሰም ሆድ አለ አምላክ ያረገዘ!

ዘጠኝ ወር ታሽጎ ሲኖር በጨለማ!

የወር አበባ እየተጋተ ደም እየተጠማ

ብልት ቀዶ ወጣ አቡሻ ህፃኑ

አፉን ለጡት ከፍቶ አቤት ማሳዘኑ!

ሲበላ ከዛ ሲጠጣ ከዛ ሲያስከትል

ከዛ የነዚህ አስገዳጅ አለ.... ይህ አምላክ ነውን?!

ጌታዬ ከፍ አለ (ጠራ) ከክርስቲያን ቅጥፈት
ሁሉም ይጠየቃል በቀባጠረበት!

الحمد لله على نعمة الإسلام

ሼር & ጆይን
https://t.me/+qYjPc2hSWSw5YWI0

የሙሂ ማስታወሻዎች

08 Jan, 19:58


ሞትኮ ረፍት አይደለም መሰለን እንጂ! ወላሂ ከዱንያ በላይ ጭንቀት ያለው ከሞትን በኋላ ባለው ህይወት ነው።!

ቤተሰቦቻችን ጀናዛችንን ይዘው በዙርያችን እያለቀሱ ወደ ቀብር ሲሸኙን እኛ እየተደሰትን እንድንሄድ ስንቅ እንያዝ።!ከስንቆች ሁሉ ስንቅ አላህን እንፍራ ነው! አላህን መፍራት ማለት የከለከለውን መከልከል ያዘዘውን መስራት ማለት ነው።



🎁 የሙሂ ማስታወሻዎች
👇👇join & shar
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

07 Jan, 10:14


አውሬም በላን፣ ውሃ ወሰደን፣ መሬት ላይም ወድቀን ቀረን ቀብር የሚጠብበት ሰው አይቀርለትም።! ቀብሩ የሚሰፋለት ደግሞ ተጣብቆ ቢቀበርም እንኳ ይሰፋለታል።! ሱብሃናላህ!
አላህ ይጠብቀን ከቀብር ጥበት!

ስንቅ እንያዝ! ከስንቆች ሁሉ ስንቅ አላህን መፍራት ነው።!


የሙሒ Shar & join
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

06 Jan, 15:30


ሙስሊም ነን? እንግዲያውስ

ከሆን ሙስሊምነት የሃያ ብር ኮፍያ ጣል ባደረገ ወይም የሃምሳ ብር ልብስ ፀጉሯ ላይ ጣል ስላደረገች ሳይሆን እውነተኛ ሙስሊም ኩፋሮች ካር አይመሳሰልም። ምን ልላችሁ መሰላችሁ የገና ባአል እኛ ሙስሊሞችን አይመለከትም። እንኳን አደረሳችሁ ማለት እንኳ የነሱን እምነት መደገፍ ነውና ምላሳችንን እንጠብቅ። እንዲሁም በንግድ ላይ የተሰማራችሁ እህት ወንድሞች እነሱን የሚገልፁና ለበአላቸው የሚጠቀሙበትን ማንኛውም እቃ መሽጥ አይቻልም። ክልክል ነው።! አላህን እንፍራ

አንዳንዶች ከመሸጥም በላይ ስራ ቦታቸውጋ የሚንጠለጠሉ ዲኮሮችን(እፍኞችን) ሲያደርጉ ይታያሉ ይሄ ወንጀል ነው። አላህን አለመፍራት ነው።

ነብያችን(አለይሂሰላቱ ወሰላም)ህዝቦችን የተመሳሰለ ከነሱ ነው ብለውናል። ስለዚህ እነሱጋ ከመመሳሰል እነሱንም ከማገዝ እንዲሁም እንኳን አደረሳችሁ ብሎ ከማብሰር ራሳችንን እንጠብቅ።

እንዲሁም ሰልማችሁ ቤተሰብጋ የምትኖሩ እህት ወንድሞች አላችሁ በአሉን የሚመለከቱ ስራዎችን ከመስራትና እነሱን ከማገዝ ተቆጠቡ እንዲሁም ለበአሉ ከተዘጋጀው ምግብ ስጋ እንኳ ባይሆን እንዳትጠቀሙ። ሽሮም ቢሆን ለራሳችሁ ለብቻ ሰርታችሁ ተጠቀሙ። ይሄን ስታደርጉ እነሱጋ መጣላት መቀያየም ሊኖር ይችላል አብሽሩ ሶብር አድርጉ የመጣነው ለፈተና ነው። እስልምናን ለሰጣችሁ ጌታ ይሄን ማድረግ ትንሽ ነገር ነው። ባረከላሁ ፊኩም

         لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ
«ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ፡፡ (ከቁርዓን)

   Share


   የሙሂ ማስታወሻዎች
    ጆይን & ሼር👇👇👇
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

05 Jan, 20:00


ውዷ እህቴ ራስሽን ሁኝ የቀለም ማስታወቂያ ምትሰሪ መስለሽ አትውጪ


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

04 Jan, 14:56


👆
ባሮቸ ዝሙት አይሰሩም እያለን ነው አላህ❗️


ዝሙት ቆሻሻ ነው ወላሂ!
ልክ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ቮልቴጅ እንዳለው መብራት እንራቀው።


አጫጭር ማስታወሻዎቸን
ምታገኙበት ቻናል👇👍
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

03 Jan, 18:29


እናታችን አኢሻ ረድየላሁ አንሃ ስለ ነብዩ(ስለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የለይል ሶላት ስትናገር የሶላቶቹ ውበታቸውና ስለረዝመታቸው አትጠይቀኝ ትላለች! ሱብሃናላህ
ለሷ ሶላት ያምራታል ውበት አለው ለኛስ ሶላት ውበት አለው? እናጣጥመዋለን ጣእም አለው?



https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

02 Jan, 14:55


አንዳንዴ አላህ ፊት ሚጠብቀንን ስናስብ ቃላት እናጣና ያ አላህ ብቻ እንላለን አይደል!?

ያ አላህ!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

01 Jan, 15:38


እስልምና ካንች ብዙ እየጠበቀ አንች ግን በወንድ ቃላት ተምበርክከሽ በጊዚያዊ ስሜት ራስሽን ጥለሻል! ያሳዝናል


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

30 Dec, 10:32


🎁 በሒጃብ ላይ ልዩ ማስታወሻ 

«እህቴ ሆይ! ምናልባትም አንቺ አሁን በሕይወት እያለሽ የተሟላውን ሒጃብ ለመልበስና በአግባቡ ለመሸፋፈን ላትፈልጊ ትችያለሽ፡፡ ያው በግልጽ እንደምናየው ፀጉርሽን ከፍተሸ፣ ሽቶ ተቀባብተሸ ከንፈርሽን ሊፒስቲክ አጥግበሽ፣ ጡትሽን እሹለሽ፣ ደረትሽ ከፍተሽ፣ ዓይኖችሽን ተኳኩለሽ፣ እጆችሽንና እግሮችሽን ገላልጠሸ፣ ስሜት ቀስቃሽ ጠባብና አጭር ጨርቆችን ለብሰሽ የትም እየታየሽ ነው፡፡ ከሩቁ ድብን ብላሽ የሰው ዓይን ውስጥም እየገባሽ ነው፡፡ ነገር ግን አስታውሺ!  አንድ ቀን ከራስ ፀጉርሽ እስከ እግር ጥፍርሽ ድረስ በተገቢው ሁኔታ ትለብሻለሁ፡፡ ግና የዛኔ ወደመቃብር ነው የምትወርጂው፡፡ ስለዚህ ያንን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሟላ ሒጃብን የምትለብሽበት ቀን አታድርጊው፡፡ እባክሽን አሁኑኑ ልበሺው ዞሮ ዞሮ ከቤት ኖሮ ኖሮ ከመሬት ሲባል አልሰማሽም? ገላ ፈራሽ ነው፤ ውበትም ጠፊ ነው፡፡ አዎ! ምንም ያህል ብታምሪ፣ የቱንም ያህል ድብን ብለሽ የወንዶች ዓይን ውስጥ ብትገቢ አንድ ቀን ሟች ነሽ፡፡ እናም ከወዲሁ የኣኼራ ሕይወትሽን ገንቢ። በዱንያ ሳለሽ ለቀበርሽ ስንቅ ያዥ፡፡!

ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! ልክ እንደ ሉል ሁኚ፡፡ እንደሚታወቀው ሎል ውድ እና ብርቅ ነው፡፡ ለዚህም የበቃው የተቀመጠበት ቦታ ነው፡፡ ሉል ለፈላጊዎች እሩቅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ውድ ሆኗል። አንቺም እንደዚያ መሆን አለብሽ፡፡ በሌላ በኩል እንደዘመኑ ቀበጥ ሒጃቢስቶች እዚያም እዚህ አትታይ፡፡ እንደ አበባም እትሁኚ፤ ተጠቅመውብሽ ይወረውሩሻልና፡፡ እናም እንቺ ትክከለኛ ሒጃቢስት ሴት ሁኚ፡ በዚያን ጊዜ ሒጃብሽ መከበሪያሸ ይሆናል፡፡ ምንዳሽም ጀንት ይሆናል።


🚨 ሼር Share


  የሙሒ ማስታወሻዎች 👍
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

29 Dec, 11:49


ያረቢ ለየት ያለ የተረጋጋና ድስ የሚል ጥፍጥ ያለ ህይወትን ስጠን ተመሳሳይ ህይወት እንዳታኖረን!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

27 Dec, 17:04


🔥ሽርክ ዙልም(በደል)ነው❗️

በሽርክ የሞተ ሰው ጀሃነም ነው ሃገሩ በዚህ አንጠራጠርም።! ምክንያቱም አላህ ነው ያረጋገጠልን። ሽርክ ሲባል ሌላን አምላክ መገዛት ወይም ቤተክርስቲያን ሂዶ መስገድ እንዲሁም እየሱስን አምላክ ነው ማለት ብቻ እንዳይመስለን። በዱአህ ሌላን አካል በማይችለው ነገር ከለመነው አሻርከናል ጀሃነምም እንዘወትራለን።! አስምሩበት ሃገራችን ላይ ያለውም ተጨባጭ ይሄ ነው።

ሚስኪኑ ህዝባችን በየ ቀብሩና ብየ ጠንቋይ ቤት ልጅ ስጡኝ፣ ጤና ስጡኝ፣ ሃብት ስጡኝ፣ ዝናብ አዝንቡልን እያለ ይንከራተታል። ዱዐ ኢባዳ ነው ከአላህ ውጭ አይሰጥም።! አላህ ይጠብቀንና ሌላን እየተጣራን ከሞትን ተስፋ የለንም።

ነብያችንም(ስለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)ዱአ ማለት እሱ ነው ኢባዳ ብለዋል። ኢባዳ ነው እንኳ አይደለም ያሉት እሱ ነው ኢባዳ ነው ያሉት ልዩነት አለው።

ቆም እንበል ህዝባችንን እንድረስለት!

ኢንሻ አላህ በቅርቡ በሰፊው የተውሂድ ትምህርቶችን እጀምርላችኋለሁ። ለየት ባለ መልኩና ሃገራችን ላይ ስላሉ የሽርክ ችግሮችም በግልፅ የምንመካከር ይሆናል። ኢንሻ አላህ ማንም ባልሄደበትም መንገድ ሽርክን እንዋጋለን በንግግርም ብሌሎችም መንገድ።!

لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡


አሁንም ቆም እንበል! ተውሂዳችንን ሳናጠራ ብንሰግድ፣ ባህሪያችን ያማረ ቢሆን፣ ላይል ሶላት ብንቆም አይጠቅመንም።!


  ወንድማችሁ ሙሂዲን

ሼር እናድርገው ቻናሉን እናሳድገው

    የቀደምቶች መንገድ
የቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቅለው ይከታተሉን
👇👇👇 🎁 🎁 🎁
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah

የሙሂ ማስታወሻዎች

26 Dec, 18:38


አዎ! አላህ ወንጀሎችን በሙሉ ይምራል ግን ሳንቶብትም ሊወስደን ይችላል እየሄዱ እንዳሉት። ነገ ነገ አንበል(ተውበት አና'ዘግይ)የቀብር ሰዎች ብዙ ለቅሶ ቆይ እቶብታለሁ እያሉ ሞት ስለቀደማቸው ነው።!


የሙሂ
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

24 Dec, 11:37


🎁 መሳጭና አስተማሪ አጭር ታሪክ

እወቂ አላህ ይዘንልሽና
 ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ
አንድ ጊዜ አበባና ሉል ተወያዩ። በውይይቱ ውስጥ ሰምጠው እያሉም በመሃል በአበባዋ ላይ የመጨናነቅ ምልክት ታየባት። ሉሏ ለአበባዋ «በጨዋታችን ውስጥ ምንም ለጭንቀት የሚዳርግ ነገር የለም፤ ታዲያ ለምንድነው የተከፋሽው»? ስትል ጠየቀቻት። አበባዋ ቁና ቁና እየተነፈሰች «የሰው ልጆች እኛን የሚያሳድጉን ለኛ ብለው አይደለም፤ ከኛ ፍካትን፣ መዓዛና ውብ ገጽታን፣ ደስታን ለማግኘት እንጂ። የኛን እጅጉን ዋጋ ያለውን ገጽታ፣ ድምቀትና መዓዛን ከተጠቀሙበት በኋላ እነርሱ እኛን በየመንገዱና በየቆሻሻ ገንዳዎቹ ውስጥ ይወረውሩናል» ስትል አምርራ ተናገረች።
 
 በማስከተልም አበባዋ ለሉሏ «እስኪ ስላንቺ የሕይወት ተሞክሮ ንገሪኝ አንቺ እንዴት ነው የምትኖሪው?» ምን ይሰማሻል? በባህር ሥር ተቀብረሽ መኖሩ እንዴት ነው? ስትል ጠየቀቻት። ሉልዋ ምላሽ ስትሰጥ «ምንም እንኳ እኔ ያንቺ ዓይነት አንዳችም ልዩ መልክና ጣፋጭ መዓዛ ባይኖረኝም፤ ግና የሰው ልጆች እኔ ውድ መሆኔን ያስባሉ። እኔን ለማግኘት ሲሉ የማይቻሉ ነገሮችን ይሠራሉ። እኔን ፍለጋ ረጅም ጉዞን ያደርጋሉ፣ እኔን ለማግኘት በባህር ውስጥ ጥልቅ ይሰምጣሉ። አንቺ ምናልባትም እኔ የበለጠ ከሥር በተገኘው ቁጥር ይበልጡኑ ውብና ደማቅ እንደምሆን ስታውቂ ልትደነቂ ትችያለሽ። ያ ነው እንግዲህ በነርሱ አስተሳሰብ ውስጥ የኔን ዋጋ ከፍ የሚያደርገው። እኔ የምኖረው በወፍራም ቅርፊት ውስጥ በጨለማ ባህሮች ውስጥ ተለይቼ ነው። ሆኖም ግን እኔ ደስተኛ ነኝ።  በሰላማዊ ቦታ ላይ በመሆኔም ኩራት ይሰማኛል። ከአድፋጮችና አታላይ እጆች የራኩ ነኝ። እናም አሁንም የሰው ልጆች እኔ የላቀ ዋጋ እንዳለኝ ያስባሉ» አለቻት።
 
 ውድ እህቶቼ ለመሆኑ አበባውና ሉሏ ምንን እንደሚያመለክቱ አስታውላችኋል? አበባዋ ያቺ ውበቷንና ድምቀቷን ለሌሎች የምታሳይ ሴት ናት። ሉልዋ ደግሞ ውበቷን የምትሸፍን ትክክለኛ ባለሒጃቧ ሴት ናት። አዎ! የተሟላ ሒጃብ የለበሰች ሴት ውድ ናት፣ ማንም እንደፈለገ አይዳፈራም፣ ማንም በቀላሉ ሊያገኛት አይችልም፣ እርሷን ማግኘትም ከፍተኛ ጥረትን ይጠይቃል፣ እርሷ ትክክለኛ ሙእሚን ናት። ከቤቷ የምትወጣውም ጋባዥ ፍለጋ ወይም ውበቷን ለማሳየት ሳይሆን ለመሠረታዊና ግዴታ ለሆኑ ነገሮች ብቻ ነው። ሒጃብ በእውነቱ ያስከብራል።! ስለዚህ አንችም እንደ አበባዋ ተጠቅመው የሚወረውሩሽ አይነት ሴት ሳትሆኚ በሂጃብሽ ውስጥ ተከብረሽ ልክ እንደ ሉላ ውድ ሁኚ።!
 
በመሆኑም እነዚያን ተገላልጠው፣ ሰውነታቸውን አጣብቀውና አጭርና ስስ ልብስ ለብሰው ለሚሄዱ እህቶቻችን ሰፊና ወፍራም ረጅም የሆነን ሙሉ ጅልባብ ለብሳችሁ እስከ አይናችሁ ከፍ እያደረጋችሁ ልበሱ እንላቸዋለን። እነዛ ጅልባብን የሚለብሱትን ደግሞ በላጭ የሆነውን ኒቃብ እንዲያደርጉ እንመክራቸዋለን። እነዚያን ኒቃብን ያደረጉትን ደግሞ ፅናትን እንለምንላቸዋለን። ሰዎችን የሚፈትን ልብስ የምትለብሱ እህቶቻችን ግን አላህን ከማመፅ ሰውንም ወደ ስሜት ፈተና ከመጣራት እንድትቆጠቡ እንመክራችኃለን።

በሒጃብሽ እንደ ሉሏ ውድ ሁኚ!!

🚨🚨🚨ሼር ሼር ሼር


የሙሂ ማስታወሻዎች👇👍
ይቀላቀሉን እንመካከር በመመካከር ህይወት ትቀላለች። 🎁🎁🎁
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

22 Dec, 18:02


ዚና
.
.
.
የልብ ድርቀት ጥግ ነው!!


የሙሂ ማስታወሻዎች
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

20 Dec, 18:50


ተውሒዳችንን እናጥራ! ውዶ አድርገን ውዶ የሚያፍርሱ ነገሮችን ስናድርግ ውዷችን ተበላሽቶ ስላታችንም ትርጉም እንደሚያሳጣው የኢባዳን አይነት በኢኽላስ ብናተራምስም ተውሂዳችን ካተስተካከለ ትርጉም የለውም። ይሄን ያክል የከበደ ጉዳይ እያለ እኛ ግን ተዘናግተናል። መቸ ይሆን የምንቃው!

ተውሂድ ተውሂድ!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

19 Dec, 20:19


በነብያችን ላይ ሰለዋት እናውርድ
እጃችን ስራ ቢይዝም ምላሳችን ግን ብዙ መዝከር ይችላል አይደል? ስለዚህ...


ስለ ሰለዋት ምን ግርም ይለኛል መስለችሁ..
አንድ ሰለዋት በነብያችን ላይ ስናውርድ አላህ በኛ ላይ አስር ስለዋት ያወርዳል ምን ያክል ቢያልቃቸው ነብያችንን ይሄ የሆነው?
አላሁ አክበር!

آللهہ‌‏مـ صـليـﮯ وسـلمـ على حبيـﮯبنآ مـحمـد

https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

19 Dec, 12:54


ፊትሽ ሲያዩት የጨዋ ፊት ነው
አለባበስሽ ግን ተቃራኒ ሆነብኝ ምንድን ነው ነገሩ?


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

18 Dec, 11:08


ራስሽጋ ተሳሰቢ! ስለሌላ ሰው አታውሪ መጥፎ ነገር ካየሽባት ያለችበት መንገድ ልክ እንዳልሆነ ለራሷ ቀስ አድርገሽ አስታውሻት ዱዓም አድርጊላት ከዛ ውጭ እሷኮ እንደዚህ ናት፣ እንደዚህ ስታደርግ አይቻታለሁ፣ መጥፎ ናት፣ አስመሳይ ናት እያልሽ የእህትሽን ስም አታጥፊ።! በተቃራኒው ከሷ የከበደ ወንጀል እየሰራሽ ሊሆን ይችላል! ስለሷ ለሌላ ሰው ስታውሪ።!
የታየውም የተሰማውም ሁሉ አይወራም ምላስሽን ይዢው! ውዱ ነብይሽም ምላሱን እና ብልቱን የጠበቀ ለጀነት ዋስ እሆነዋለሁ ብለዋል።!

ዝምምምም ያለ? ጨርሽው
.
.
.
ነፃ ወጣ!


የሙሂ ማስታወሻዎች
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

16 Dec, 03:17


በቃ ይመርብሽ እንጂ የፈለግሽውን አይነት ልብስ ብትለብሽ ችግር የለውም ነው?
አላህን ፈሪ እህቴ! ለነፍስሽ ጥሩ ጋደኛ ሁኚላት! ነፍስሽ እንደፈለገች ስትሆን ተይ ነፍሴ ቀብር አለብሽ፣ ጌታሽም ፊት መቆም አለ በያት።! ከመልካም ስራሽ ውጭ አብሮሽ እስከመጨረሻው የሚከተልሽ የለም፣ ይሄን ውብ ፀጉርሽን፣ ገላሽን ትላትሎች እንዳነበረ ያደርጉታል ወላሂ።! መቸ ካልሽኝ አላህ ዘንድ ብቻ ነው ያለው እውቀቱ።! ለምን እሱ ዘንድ ብቻ ሆነ ካልሽኝ ሁሌም ዝግጁ ሁነሽ ሞትን እንድትጠባበቂ ነው።! ከስካርሽ ንቂ! ዱንያ ላይ ባሉት ሰው ሰራሽ ብልጭልጮች አትታለይ ጀነት ላይ ያሉት ብልጭልጮች ይበልጣሉ።! ጀነት ላይ ጭራሽ ይኖራሉ ብለሽ እንኳ ማታስቢያቸው ፀጋዎች ናቸው ያሉት የተዘጋጁትም እዚህ ዱንያ ላይ ነፍስያቸውን ላልተከተሉ ባሮች ነው።!


🚨Share

ወንድምሽ ሙሂ👇🌻
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

13 Dec, 16:17


ዚናም ላይ ሁኖ
.
.
.
ተጣብቆ መቅረት አለ❗️



የሙሂ ማስታወሻዎች
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

11 Dec, 03:42


ዱንያ ለአኼራ ስንቅ የሚዘራባት ሃገር እንጂ የሚኖርባት ሃገር አይደለችም። ወደ አኼራ መሄጃ ድልድይ ናት! ድልድይ ላይ ቁሞ አቅል ያለው ሰው አይጫወትም!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

10 Dec, 03:31


ዚናም ላይ ሁኖ
.
.
.
መሞት አለ!ምን ዋስትና አለን?


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

08 Dec, 10:21


ቀጠሮውን እንዳትረሽው
.
.
.
 የቂያማውን!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

05 Dec, 20:05


ካፊሮች ናቸው ሴቷም ወንዱም ኒካህ ባያስሩም አብረው ለመተኛት ከተስማሙ ዝሙት የማይመስላቸው እና እኛም እንደነሱ እየሆን ነው !?? አላህን እንፍራ! ማንም ከእይታው የሚደበቅ የለም! አያየንም ብለን ካሰብን በሱ መካድ ነው።! እያየን እንደሆነ ካወቅንም እሱን መናቅ ነው።

እንመለስ ወደ አላህ ጌታችን አላህ ወንጀሎችን በጠቅላላ ማሃሪና አዛኝም ነው።! አናስረዝመው መራቁን! የተውበታችንን እድል እንጠቀመው እስከ ወንጀላችን ጌታችን ፊት እንዳርቀርብ።


ለፕሮፋይል ከላይ ያለውን ፎቶ ይጠቀሙ

የሙሂ ማስታወሻዎች
join & share 👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

04 Dec, 12:49


አይናችንን ሰበር እናድርግ! ካየን ማሰባችን አይቀርም፣ ካሰብን ወዳሰብነው እንሄዳለን፣ ከሄድን ደግሞ ድርጊቱ ላይ እንወድቃለን! ስለዚህ አስቀድመን አይናችንን እንቆጣጠር።

አይንን አለመቆጣጠርም የአይን ዝሙት ወንጀል እንዲፃፍብን ያደርጋል።

አይናችንን በመስበር ልባችንን እንጠብቅ!


የሙሂ ማስታወሻዎች
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

03 Dec, 10:22


የኔ ብርቅ

https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

01 Dec, 09:26


የራህማን ባሮች
.
.
.
ዝሙት አይሰሩም! አላህ ነው ያለው።


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

29 Nov, 07:09


አንዳንድ ሰዎች ተቸግረህ ሰውም አስቸግረህ ለችግራቸው ደርሰህላቸው እነሱ ግን ሳይቸግራቸው እንኳ አይቸገሩልህም። ደስ የሚለው ግን አላህ ጥሩ ሰሪዎችን አይተውም።!



የሙሂ ማስታወሻዎች👇👍
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

28 Nov, 10:15


💦 አርተፊሻል ቆንጆ

በኩል አሳምራ ለስና ቅንድቧን
ክሬም ተቀብታ ሁለት ጉንጮቿን
በጋለ ካዊያ ተተኩሳ ፀጉሯን

አጭር ቀሚስ ለብሳ ገልጣ ሰውነቷን፣
ስትል ሰበር ሰካ አድርጋ ታኳዋን፣
በምድር ላይ ሳለች ከሷ ወዲያ ሴት
በዚህ አለም ቆንጆ የለለ መስላት፣

በጉራ ተገፍታ በትእቢት ተወጥራ፣
ልታይ ልታይ ብላ ስትል ኮራ ኮራ፣
ወዲያው ወረደና የዝናብ መአት፣
ለመሮጥ አትችል ልብሷ ሲወጥራት፣

ተበላሸ ተኩሱ ፀጉሯም በሰበሰ፣
የጉንጮቿ ክሬም በአይኗ ኩል ራሰ፣

ዝናብ አጠበና ሜካፑን ወሰደው፣
ፅጌሬዳ መስላ ከቤቷ ስትወጣ፣
ዝናቡ አስመሰላት ጭራሽ የሰው ጦጣ፣

ያ''' ሁሉ ቅባቅብ ሂጃቧን ያስጣላት፣
ለካስ አርተፊሻል ሰው ሰራሽ ቆንጆ ናት



Shar & join

https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

27 Nov, 16:05


ለጎሮቤት ጎረበጥ አንሁን


@sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

25 Nov, 19:47


እንዲህ ያማሩና ጠንካራ ሁለት እግሮች ስጦን ለሶላት አለመቆም ውለታ ቢስነት አይሆንም?

በጣም ከሚገርመኝ ነገር አንዱ እንትና ሶላት አይሰግድም እንትናም ሶላት አትሰግድም ሲባል መስማት ነው! ቆይ ምን አይነት ህይወት ነው ያለ ሶላት? ግን እርግጠኛ ናችሁ ይቻላል መኖር ? ወይስ ሌላ መኖር አለ?

እንዴት ሰው በሶላቱ ይዘናጋል ሰአቱ ደርሶ ነፍሱን እንስኪያሳርፋት ይቸኩላል እንጂ


የሙ 📜
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

24 Nov, 11:57


ቤተሰቦችሽን ትወጃልቸዋለሽ? ውለታቸውን መክፈል ባትችይ እንኳ ማሳዘን አትፈልጊም አይደል? እንግዲያውስ ክብርሽን ጠብቂ ውርደት እንዳታመጭባቸው።!

ወላሂ ውርደት ነው በክብር አሳድገውሽ የሰርግሽ ቀን አንገታቸውን ካስደፋሻቸው።!
ስሚኝ ውድ እህቴ ባልሽን ወደድሽውም አልወደድሽውም ተገደሽ ብታገቢውም እንኳ የክብርሽ(የድንግልናሽ)ሃቅ የሱ ብቻ ነው በሃላል ለወሰደሽ።❗️

አገባሻለሁ ግን ከኒካህ በፊት ክብርሽን ስጭኝ ቢልሽም ሃቁ የሱ አይደለም ቢያገባሽም እንኳ።! አላህንም ፍሪ ከቤተሰቦችሽ በላይ አላህ ይቀናብሻል።


Share
የሙሂ ማስታወሻዎች & join
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

22 Nov, 09:15


አላህን ባወቅሽው ቁጥር እየፈራሽውና ትንሿ ወንጀል እንቅልፍ እያሳጣችሽ ትመጣለች ካላወቅሽው ግን ልብሽ ይደነድንና ወንጀሉም ወንጀል መሆኑን ትረሽዋለሽ።!

ስንቶች ከአፍር በታች በሆኑበትና አንች ያለሽበትን ጊዜ አንዴ አግንተውት ወደ አላህ መቃረብን ብቻ በሚያስቡበት ሁኔታ አንች ግን ልትዘናጊ አይገባም።

ውድ እህቴ ከስካርሽ ንቂ ያሉሽንም ፀጋዎች የአላህን ሃልያልነት ከፍ ለማድረግ ተጠቀሚባቸው! እሱንም ከማወቅ ጀምሪ።!


🎁 የሙሒ ማስታወሻዎች👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

20 Nov, 17:00


በሶላቱ ላይ ኹሹእ ወይም እርጋት ያለው ሰው ሲሰግድ ብዙም ሰውነቱ ሲንቀሳቀስ አታዩትም! የሚያሳዝነው ያልበላንን ምናከው፣ ጥፍራችንን የምንቆርጠው፣ ልብሳችንን ምናስተካክለው፣ የጠፋን ነገር ትዝ የሚለን ሶላት ላይ ነው።! ይሄም የሆነው ልባችን ላይ ኹሹእ ወይም አላህን መፍራት ስላጣን ነው። ኹሹዕም ስለሌለንና የሶላትን ጥፍጥና ስላጣን ነው ሶላት ስንሰግድ የምንሰላቸውና ሰግደንም ስንጨርስ እንደ መላቀቅ የሚሰማን።

አላህ ኹሹእን እንዲሰጠን ሁሌም ዱአ እናድርግ።


የሙሂ ማስታወሻዎች 👇 👍
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

19 Nov, 14:52


በሒጃብሽ ላይ ሶብር አድርጊ ክብሩንም፣ መስፈርቱንም ጠብቂ ስለተሸፈንሽ እንደፈለግሽ መሆን ትችያለሽ ማለት አይደለም። አላህን ፍሪ በድብቅም በግልፅም። አይደለም ምትሰሪውን ምታስቢውን ያውቃል። አለባበስሽም ስለተስተካከለ ባለበሱት ላይ ኩራት እንዳይሰማሽ ለአላህ የሚጨምርለት ነገር የለምና። ላለበሱ እህቶችሽም አዝነሽ ዱአ አድርጊላቸው ሊታዘንላቸውም ይገባልና ነገ አላህ ፊት ሚጠብቃቸውን ስለዘነጉ በመራቆታቸው።



የሙሂ ማስታወሻዎች 🔭
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

18 Nov, 11:59


الَّذِينَ صَبَرُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
(እነርሱ)እነዚያ የታገሱት በጌታቸውም ላይ የሚጠጉት ናቸው፡፡

ያረቢ ከነሱ አድርገን!


የሙሂ ማስታወሻዎች
2,222 members👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

17 Nov, 17:02


ጓደኞችሽ የእውነት ከልባቸው የሚወዱሽ ከሆነ መጥፎ ነገር ስታደርጊ እያዩ ዝም አይሉሽም ምክንያቱም ጊዚያዊ ለምታገኝው ደስታ ሳይሆን ነገ አላህ ፊት ስትጠይቂ የምትሆኝው ነው ሚያስጨንቃቸው። የሚያሳዝነው አንች ግን በተቃራኑው ከመጥፎ የሚከለክሉሽንና በመልካም ነገር የሚያዙሽን ጓደኞች ለምን ያጨናንቁኛል በማለት መራቅን እየመረጥሽ ነው። ከዛም ክርስቲያኖችን መውዳጀትን መረጥሽ። እናት አባትሽ እንኳ ቢሆኑ እንደፍለግሽ ስትሆኚ ዝም የሚሉሽ ከሆነ እንደማይወደሽ እወቂ እውነታው ይሄ ነው አንቺጋ በተቃራኒው ስለሚወዱሽ ቢመስልሽም። አንችም እንደዛውም መጥፎ ነገር ሲያደርጉ ክልክል ነው አላህን ፍሩ የማታያቸው ከሆነ ውዴታሽ ከልብሽ እንዳልሆነ ልታውቂው ይገባል። ምክንያቱም ከልብሽ ቢሆን ከዱንያው በላይ አኼራ በጀነት ላይ እነሱጋ መሆንን ትመኝ ነበር።

ጓደኛህን/ጓደኞችሽን ምረጭ ጊዚያዊ ደስታን አንምረጥ!

እናስታውስ እንዲህ የሚለውን የጌታችን ቃል፦

وَيَوْمَ يَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ يَدَيْهِ يَقُولُ يَٰلَيْتَنِى ٱتَّخَذْتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِيلًا يَٰوَيْلَتَىٰ لَيْتَنِى لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا لَّقَدْ أَضَلَّنِى عَنِ ٱلذِّكْرِ بَعْدَ إِذْ جَآءَنِى وَكَانَ ٱلشَّيْطَٰنُ لِلْإِنسَٰنِ خَذُولًا
በዳይም «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
«ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡ (የእምነት ቃልን)ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)፡፡
ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው፡፡


join & shar
የሙሂ ማስታወሻዎች
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

16 Nov, 10:36


እናትሽ እንዴት ነው ምትወድሽ? ውዴታዋ በተግባር ነው ስለሷ ቃላት የለሽም አይደል?
  አላህ ግን ወላሂ ከሷ በላይ ነው ሚወድሽ ሚያሳዝነው ግን ስለ አላህ ለማወቅ ጊዜ ስላጣሽ አልገባሽም ውዴታው።!! የብር ጥቅም ገባን የአላህ ጥቅም ግን አልገባንም! ያልፈራነውም ስላላወቅነው ነው።

አላህ ይመልሰን!💦


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

14 Nov, 15:53


ጣቷ ላይ የዚክር ማድረጊያ ቀለበት አድርጋለች ጥፍሯን ደግሞ ቅርፅ ሰርታለት አስድገዋለች ውድ እህቴ አብሮ ይሄዳል? ወይስ መዝከሪያው ጌጥ ነው?

የኛ ነገር የርመኛል ምላሳችን አስተغፊሩሏህ ይላል ልባችን፣ እጃችን ግን ወንጀሉ ላይ ነው። አላህ ይመልሰን


የሙሂ ማስታወሻዎች
👇👇👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

13 Nov, 17:45


ተቀባብታለች፣ ታኮ ጫማ ነው የለበሰችው፣ ወገቧን ያው ቅርፁ እንዲታይ በገመድ አስራዋለች ከታክሲ ነው አብረን የወረድነው ወርዳ ትንሽ እንደተራመደች አንዱ መጦ አንገቷን አቀፋት አታውቀውም ተናዳ ጮሆችበት..!
እኔም አለባበስሽ ነው እንድትደፈሪ ያደረገሽ ብያት ሄድኩ ዙራ አይችና ሄደች!

አላህ እንዲህ አላለሽም፦

 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና(በባለጌዎች)እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡( Al-Ahzab:59 )


ዲን የለቀቀች ነፍስ አክባሪ የላትም❗️


የሙሂ ማስታወሻዎች
👇👇👇 👍
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

12 Nov, 13:35


ሳትቀባቢ፣ ሳትገላለጭም በጣም ቆንጆ ነሽ! ምን ሁነሽ ነው ባለሽ ነገር መደሰት ያቃተሽ? አንቺ ያሉሽ ውድ ፀጋዎች የሌላቸው ብዙ እህቶችሽን አላየሽም? ታዲያ ምስጋናሽን በአመፅ ነው ምትገልጭው? ተመለሽ እህቴ አልሃምዱሊላህ! አስተغፊሩላህ በይ!

እይውስኪ እጅሽን ፊትሽንም እግርሽንም አፍር የሚበላው አይመስልማ ይበላዋል ወላሂ! ትሎችም ይሻሙታል እንዳልነበርሽም ትረሻለሽ! ዛሬሽን ተመልከችና ሁኔታሽን አስተካክይ!
ዋ! ጥፋቴ እያልሽ በቁጭት እጅሽን የምትነክሽበት ቀን ሳይመጣ።! እሳት አለ ፊት ለፊታችን አይደለም በወንጀል ላይ ሁነን መልካም እየሰራንም ያስፈራል ምክንያቱም ተቀብሎን ይሁን አይሁን አናውቅም የጠራ መስሎን የተመለሰብን ብዙ ስራ ሊኖር ይችላል። 💦

አልሃምዱሊላህ! አስተغፊሩላህ!


🎁 የሙሂ ማስታወሻዎች👇
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

11 Nov, 11:45


አንዳንድ እህቶች ለምን ነው እንደዚህ የለበሳችሀት ለምን ትገላለጣላችሁ ሲባሉ የሚገርማቸው አሉ እንዴት እንደዚህ አለኝ ብለው ለምን ይመስላችኋል በደምብ ዳውአው ስላልደረሳቸው ነው ጥቅሙና ጉዳቱንም ስላልተገነዘቡ ነው። እናም የተገላለጡና ተጠባብቀው የሚሄዱ እህቶችን ስናይ ቀስ አድርገን እናስታውሳቸው። የፈለገውን የሚመራው አላህ ነው። በግድና በስድብ የሚሆን ነገር የለም።! ዳውአችን አድርሻለሁ ብለን ለመላቅቀ ሳይሆን አዝነንላቸውና የሒጃብ ጥፍጥና እንዲያገኙ አስበን ይሁን። ምክንያቱም አንዴ የሒጃብን ጥፍጥና ካገኙት በሒጃባቸው የሚመጣውን ሊጋደሉት እንደሚደርሱ ጥርጥር የለውም።!!

ሒጃብ ውበት መከበሪያም ነው!
ለራሷ ክብር ያላት ሴት ተገላልጣ ተጠባብቃና ተጠባብቃ አትወጣም ሞቷን ትመርጣለች እንጂ!


Shar & join
የሙሂ ማስታወሻዎች 👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

09 Nov, 19:55


ሲፅፉልሽ ስላልመለሽ፣ ሲደውሉ ዝም ስላልሽ ፍቅር አይገባትም ኋላቀር ናት አሉሻ? አዎ ከሶሃቦች ጋር የቀረሁ ነኝ በያቸው! ማንም እንዲዝናናብሽ እንዳትፈቅጂለት! ለፉጡር ልብሽን እንዳትሰጭ! ልብሽን ከፈጠረው በላይ የሚንከባከበው አታገኝም ልታቆስይውና ከጌታሽ ልታርቂው ካልሆነ።!


🎁 የሙሂ ማስታወሻዎች
👇👇 Share & join
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

08 Nov, 09:17


ከንቱ ጩኸት ከንቱ እሪታ
ሌላ ማምልክ ትቶ ጌታ
በገዛ እጁ ክብሩን ንቆ
ከመሬት ላይ አፈር ዝቆ
ብጥብጥ አርጎ እየጋተ
ያ ሚስኪን ሰው ውስጡ የሞተ
ዛፍ ላይ ጨሌ እያሰረ እየፈታ
በፍርሀት ያለ ያጣ ደስታ
ለጠንቋዩ ለዛ ከንቱ
የሚገብር አለ ስንቱ?
ከቀብር ደጅ ከሙታኑ
የሚጠና ከካፊሩ
ስጠኝ ብሎ የሚለምን
በህይወቱ ላይ የሚጨክን
ከፈጣሪ የተጣላ
ኢባዳውን በጠቅላላ
ያደረገ ለጥንቆላ
ስንት ቂል አለ ከኛ መንደር
ሱጁድ ሚወርድ ለሙት ቀብር
ሚጠውፈው ሚለምነው
ድረስ ብሎ ሚጠይቀው
በየአመቱ ሚዘይረው
ክብር እያለው ክብሩን ያጣው
በሌላ አይደል በዚህ እኮ ነው
ተውሂድ ትቶ ሽርክ መጠጣቱ
ከንቱ ጩከት ባዶ ከንቱ
ጌታ እያለ ለመቃብር መደፋቱ


የቀደምቶች መንገድ የቴሌግራም ቻናል
ተቀላቅለው ሼር ያድርጉ👇👇
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah

የሙሂ ማስታወሻዎች

06 Nov, 18:51


ሙሂ ብዙ ጊዜ ያረቢ ሰው አድርገኝ እያልክ ዱአ ስታደርግ እሰማለሁ ላንተ ሰው መሆን ማለት ምን መሆን ነው? 

ልክ ነህ በርግጥ በሰዎች ዘንድ ሰው አድርገኝ ማለት ሃብትን ገንዘብን ይዘው መገኘትን ነው። እኔጋ ግን እንደዛ ሳይሆን የሶሃቦችን ህይወት መኖር ስችል ነው ሰው ነኝ ብየ የማስበው።! ሚዛኖቸ እነሱ ናቸው እንደታዘዙ ቀጥ ያሉ! ኑ ሲባለ የሄዱ ቁሙ ሲባሉ የቆሙ! ለአላህ ትእዛዝ የተሽቀዳደሙ የሰው ሁሉ ምርጦች! እነሱን ምን አይነት ቃል ይገልፃቸዋል!? አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው! የነሱን መሳይም ጀግና አላህ ይስጠን። እና እነሱን ሳልሆን መሞትን እፈራለሁ አላህን ሳላውቀው።!



የሙሂ ማስታወሻዎች
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

05 Nov, 15:51


በማንኛውም ኢባዳችን እነዚህን መስፈርት እንጠብቅ!
አላህን ወደነው፣ ፍርተነውና ከሱም ጥሩን ነገር ፈልገን ይሁን! እንዲሁም በኢኽላስና ነብዩን በመከተል መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ ከሆነ ጥቅም አናገኝበትም። ራሳችንን እንፈትሽ!


ሼር Share
የሙ👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

04 Nov, 16:09


ያረቢ እነሱ ከማያውቁትም ወንጀላችን ማረን!!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

04 Nov, 11:32


ህፃን ልጅ እናቱን ሲያጣ ከሚሰቃየውና ከሚበላሸው በላይ እኛ የሰው ልጆች ከአላህ ስንርቅ እንበላሻለን! ከአላህ ስንርቅ ከሸይጧን እጅ መውደቃችን የማይቀር ነው ሸይጧን ደግሞ ጠላታችን ነው እንደፈለገ ይጫወትብናል… ሸይጧን ለሰው ልጅ ግልፅ ጠላት ነው።!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

31 Oct, 20:06


መከፋትሽንና ማዘንሽን ሰው ፊት አታሳይ እየመረረሽም ቢሆን ዋጥ አድርጊውና ፈገግ በይ… አብሽሪ የአንችም የደስታ ቀን ይመጣል…! ጥርጥር የለውም ከመጨነቅ፣ ከሃዘን፣ ከችግር በኃላ ደስታ እፎይታ አለ።! ትልቁ ነገር ሶብር ነው!ፈተናውን በሶብር አላህጋር ሳትጣይ ካለፍሽው አብሽሪ ካንች በላይ እድለኛና ጀግና የለም።!!

ሶብረኞችን አብስራቸው!

የሙሂ ማስታወሻዎች👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

30 Oct, 19:23


🌍 ለኒቃቢስቷ ተማሪ እኔም ድምፅ ነኝ‼️

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ
ሙስሊም እህቴ ተገላልጣና ተጠባብቃ ተቀባብታ ስሜት ቀስቃሽ አለባበስ ለብሳ ወጣ ወንዶችን ወደ ዝሙት እየሳበች ሳያት ውስጤን እንደሚያንገበግበኝና እንደምቃወመው ተገላልጠሽ ካልወጣሽ የሚሉ የእስልምና ጭፍን ጥላቻ ያለባቸውንም ግለሰቦችም እቃወማለሁ‼️

እንደሚታወቀው በእነሱ አስተሳሰብ መገላለጥ እንደ ዘመናዊነት የሚታይ ተግባር ነው። አዕምሯቸው በመጠጥ የተሸፍነ ስለሆነ ሴትን ልጅ ገላጠዋት እንዲዝናኑባት ነው የሚፈልጉት።! እንጂ ሲጀመር ከእምነት ወጠን እንኳ ሴት ልጅ የፈለገችውን አይነት አለባበስ ለብሳ የመውጣት መብት አላት ብለው ሲከራከሩና መብት ሲሰጡ የነበሩ ሰዎች አይደሉ ታዲያ አሁንስ መሸፈነን ስትመርጥ ለምን ያመማቸው ይመስላችኋል!? ምክንያቱም አንደኛ ሴትን ልጅ እንደ መዝናኛና ቁሳዊ እቃ ስለሚያዮት ነው እንዲሁም እምነታዊ ልብስ ነው ብለው ስላሰቡ ጭፍን የሆነው ጥላቻቸው እንጂ ቢያንስ ኒቃቡን አስወልቀው በማስክ ለመግባት ፍቃደኛ ከሆኑ እንዴት ይሄን ተግባር የሚቃወሙ ይመስላችኃል!? ማስክ ማለት ጤናንም ለመጠበቅ የሚበረታታ ተግባር ነው ነገር ግን በኒቃቡ የተቀየረ ነው ብለው ስላሰቡ ይሄንንም መቃወም ፈለጉ ታዲያ ይሄ ጭፍን ጥላቻነት አይደለም ነው የምትሉኝ? ይሄ ለማንም ግልፅ ነው።!

ተሸፍነው ሲገቡ አሸባሪ መሆናቸውን በምን እናውቃለን ብለው ተልካሻ ምክንያት ሊያቀርቡ ይችላሉ ታዲያ ይሄ ነገር በኮሮና ጊዜ ለምን ትዝ አላላቸውም⁉️ እሽ እንደዛዝ ቢሆን አንድ ሴት ቀጥረው መታወቂያዋን እና እሷን እያስተያየች እንድትገባ ማድረግ አይችሉም? ወይስ የሚቀጥሩበት ብር የላቸው ይሆን? አይደለም ወዳጆቸ ይሄ ጭፈን ጭፍንፍን ያለ ጥላቻ ነው።! ይሄን ደግሞ አንቀበልም።! ኢትዩጲያ የነሱ ብቻ እንደሆነች የሚያስቡም አሉ ተሳስተዋል የኛም ናት ቆም ብለው ማሰብ ከቻሉ።

ገርሞ ገርሞ የሚገርምኮ ነው አንዲት ሴት ራሷን ቁጥብ በማድረጓና ወንዶችን አልፈትንም ትምህርታቸውን ይማሩበት ብላ ሰውነታን መሸፈኗ የቱ ላይ ነው ጥፋቷ? የግድ እንደነሱ ሴቶች እስከ ጉልበታቸው ዩንፎርማቸውን ለብሰው ወደ እንስሳዊ ስሜት መጣራት አለባቸው!? ይሄን ለማድረግ እምነታችን ብቻ ሳይሆን ሰዋዊነት ባህሪያችንም ይከለክለናል። የሚገርመው ደግሞ እነዚህ ተማሪዎች በትምህርታቸውም የሚታሙ ተማሪዎች አይደለም ጥሩ ውጤት ማምጣት የሚችሉ ናቸው። እመኑኝ አላማቸው ጭፈን የእምነት ጥላቻ እንጂ ሌላ አይደለም።!

🛑 በዚሁ አጋጣሚ የተቀዳደደ ጠባብና አጭር ዩኒፎርም እንዲሁም ኖርማል ዩኑፎርም የምትለብሱ ሙስሊም እህቶች ሙሉ ጅልባብ መልበስ ጀምሩና እስከ ግቢው ድረስ ማስክ እየተጠቀማችሁ ግቡ። ሲነካኩን እንደገና የምንጠነክር መሆኑን እናሳያቸው። ኢንሻ አላህ ጉዳዩም ይስተካከላል እንዲሁ በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም።❗️

ስለ ሒጃብ የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀቶችን አዲስ አበባ ላይ በየ ትምህርት ቤቱ በደምብ ብንበትነው የሚል ሃሳብ አለኝ ኮፒ ማድረጊያ ማገዝ የምትፈልጉ አናግሩኝ።

  🚨እኔም ድምፅ ነኝ የሚል ፁሁፉን በቻለው ያክል ሼር ያድርገው‼️

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ @jezakellah

በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ጆይን & ሼር 👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

የሙሂ ማስታወሻዎች

27 Oct, 20:29


ሃብታም ሞልቷል ችግሩ ግን ይሄን ሰጧል ብሎ ስሙን ከፍ አድርጎ የሚጠራለት ከሌለ የሚሰጥ እየጠፋ ነው።
አላህ ይዘንልን



https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

25 Oct, 10:34


ሶላት አሰጋገዳችን ያማረ ሊሆን የሚችለው አላህን ስንፈራ ነው! አላህን የሚፈራ ሰው ቤትም ውስጥ ይስገድ መስጅና አደባባይም ላይ ይስገድ ለብቻው ጨለማ ላይም ይስገድ ነብያችን ስገዱ ባሉት መልኩ ረጋ ብሎ ልቡን ሰብስቦ መስፈርቱን መሰረቱን አሟልቶ ይሰግዳል አላህን የማይፈራና ፈራቻው የሚጐለው ሰው ግን ቢሰግድም ላይ ላዩን ነው ነካ ነካ የሚያደርገው የሙናፊቅ ሶላት ነው የሚሰግደው ልክ ዶሮ እህል እንደሚያነሳው ሩኩንም ሱጁዱንም አጣድፎ የሚወጣው/የምትወጣው። በማንኛውም ሁኔታችን ላይ አላህን የፈራን እንሁን።

የሶላታችንን ነገር አደራ! የማንሰግድም እንስገድ የምንሰግድም ሩህ ያለው ሶላት እንስገድ። ለመላቀቅ ሳይሆን ከሶላቱ ጥቅም ለማግኘት ይሁን ምንሰግደው።

Share & join

የሙሂ ማስታወሻዎች 👇👍
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

24 Oct, 14:40


ዝሙት ስርቆት ነው!!

for profile
share & join
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

22 Oct, 12:40


ሌባው በዝቷል ልብሽን ጠብቂ!
አንዴ ካጣሽው ለማስመለስ ቀላል አይደለም የምታጫቸውም ብዙ ነገሮች አሉ። ከነዛም ውስጥ አንዱና ከባዱ አላህን ከማውሳት መራቅና የኢባዳሽን ጥፍጥና ማጣት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ በደል አለንዴ እህቴ? በርግጥ መጀመሪያ ጥፍጥናውን እግንተሽው ካልሆነ ስታጭውም ላይገባሽ ይችላል።


የሙሂ ማስ.. ጆይን & ሼር
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

19 Oct, 16:03


ምን ሁንሽ ነው የከፋሽ እህቴ? አይዞሽ ለፈተናኮ ነው የመጣነው ጠንከር በይንጂ ደካማነትን ከመረጥሽማ ህይወት ከዚህም በላይ እያከበደች ነው ምትሄደው። አብሽሪ ጌታሽ የሁሉም ነገር ሃብታም ነው ለኔም ስጠኝ በይው የመሬምን ፀጋ።!

ያረቢ የሚመጣውን ካለፈው የተሻለ አድርግልን!


ሙሂ ነኝ👇Share & join
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

18 Oct, 16:02


ተመሳስለዋል!

ስሚኝ አላህ የይዘንልሽና!

እህቴ የት ቡና ቤት ነው ምንትሰሪው? ማለቴ የት ሆቴል ላይ? ለምን ጠየቅከኝ ካልሽኝ አለባበስሽ እንደዛ አይነት ቦታ የምትሰሪ ስለመሰለኝ ነው። እስኪ እውነቱን እናውራና ለጥያቄየም መልስ ስጭኝ ሆቴልና ጭፈራ ቤት የሚሰሩ ሴቶች ወይም ሰውነታቸውን ሽጠው የሚተዳደሩ ሴቶች አለባበሳቸው ምን አይነት ነው? ሰዎችን ወደ ሃራም ለመሳብ ብለው ጠባብ ሁኖ የሰውነታቸውን ቅርፅ የሚያሳይ ልብስ አይደል የሚለብሱት?፣ ተቀባብተውና ተገላልጠው አይደል የሚወጠት? እንዲሁም አጭርና ስስ የሆነ አለባበስ አይደል የሚለብሱት!? ነዋ? አዎ በሉኛ ታዲያ ምንድን ነው ከነሱጋር ያተመሳሰለው አለባብስሽን!? ውዷ እህቴ አስበሽው አታውቂም? ወይስ ለራስሽ ክብር የለሽ ሁነሽና በጌታሽ ላይ ተስፋ ቆርጠሽ ነው።? እስኪ በደምብ አስቢበት። እኔ ይሄን የምጠይቅሽ ተጨንቄልሽና ጀሃነምን ፈርቸልሽ ነው እንጂ የፈለግሽውን አይነት ህይወት እንደፈለግሽ ሁነሽ የመምራት እንደ ሙስሊም ሴት መብት ባይኖርሽም ግን ምርጫ አለሽ ይጠቅመኛል ብለሽ ካሰብሽ። እኔም ላስታውሽ እንጂ ልሰድብሽ ፈልጌ አይደለም በዚህ ህይወትሽና ሁኔታሽም ጊዜያዉ ደስታን እንጂ ውስጥሽ መረጋግትና ደስታ እንደሌለው ላንች አልነግርሽም ግልፅ ነው። ስለዚህ ትክክለኛውን ደስታ ታገኚ ዘንድ ያለፈውን በተውበት ከጌታሽ ጋር ታርቀሽ የወደፊቱን አስተካክይ። አብሽሪ በዱንያም በአኼራም ኸይር ነገር ታገኛለሽ።!

ያንንም የቂያማ ቀን አስታውስሻለሁ ሰማይ እንደ ዘይት አተላ የምትሆንበትን! ጋራዎች በቀለማት እንደተነከረ ሱፍ የሚሆኑበትን! ህዝቦች የሚንበረከኩበትን በታላቁ ሃያል የሃይል አያያዝ።! በወንጀል ህመምተኛ ከሆንሽ እኔ ሃኪም እጠቁምሻለሁ አሳማሚ ቁስሎችን የሚያክም እሱም የአለማቱ ጌታ አላህ ነው። ተውበትሽን እውነተኛ አድርገሽ ወደ አላህ ተቃረቢ ልብሽ ይረጋጋል ህይወትሽን ይስተካከላል። ከዚህ ውጭ የደስታ መንገድ የለም።! ማስመሰልና ጊዚያዊን ደስታ ከመረጥሽ ግን ስሜትሽ ያለሽን ሁሉ መከተል በቂ ነው። ግን መጨረሻው ፀፀት ነው። እንመለስ ወደ አላህ ባረከላሁ ፊኩም!


🚨 Share ሼር
ወንድምሽ ሙሂ @jezakellah


በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል
ይቀላቀሉን እንመካከር
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

የሙሂ ማስታወሻዎች

17 Oct, 10:04


አላህን ከፈራነው
የወደድነውን ሁሉ ይሰጠናል።!

ነገር ግን እሱን አስከፍተን የወደድነውን ነገር ብናገኝው እንኳ በረካ አይኖረውም።! ውሳኜያችን በጥንቃቄ የተሞላ ይሁን አላህን መቸም መሸወድ አንችልም።
አይ ብለን አግበስብሰን እናልፋለን ብለን ካሰብን የሆነ ሰአት ይይዘናል! በልጃች ወይም በሃብታችን ወይም በጤናችን ወይም በቤተሰባችን።
አላያችሁም በሃብታቸው መጥፋት፣ በልጃቸው፣ በጤናቸው፣ በቤተሰባቸው ሲፈተኑ የወንጀላችን ውጤትኮ ነው።! ሰለዚህ ሁሌም አላህን የፈራን እንሁን! በተውበትም ከጌታችን ጋር እንታረቅ።



🎁Share
የሙሂ ማስታወሻዎች
ጆይን & ሼር👇👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

15 Oct, 19:19


ምን ያደርጋል
ቁንጅናሽን ጅህልና ሸፍኖታል!


የሙሂ ማስታወሻዎች ጆይን & ሼር 👇👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

13 Oct, 20:58


ወንድሜ ሆይ ብር ወንድም አይሆንም እናትም፣ አባትም፣ እህትም አይሆንም ለቤተሰቦችህና ለተቸገሩት ብር ለማውጣት አትሰስት።! ስጥ አሰጣጥህን አይቶ ይሰጥሃል። አከፋፋዩ ከላይ ነው።!
ሰርቸኮ ነው ያገኘሁት እያልክ አትኮፈስ ለማግኘትህ ሰብበ ማድረስህ ብቻ በቂ አይደለም አላህ ሲፍቅድ ነው የምታገኘው። በጅህ የያስከው ገንዘብ ፈተና መሆኑን አትርሳ። ከጌታህም እንዳያርቅህ ጥንቃቄ አድርግ። ከፈንህም ኪስ እንደሌለው አትርሳ። እንደሞትክ ሞባይልህን፣ ሃብትህን ይቀባበሉታል፣ አንተ ባካበትከው ሃብት እንኳ ለአባቴ፣ ለወንድሜ ሶደቃ የሚሆነው የውሃ ጉድጓድ ላስቆፍር ብሎ የሚያስብ አታገኝም።!

ከዱንያ ስካር ንቃ! ትሞታለህ ለማንም ዘላለም መኖርን አልተሰጠውም።!መሞቴ አይቀርም ስሞት ከኔጋር ምንድን ነው ወደቀብሬ አብሮኝ የሚሄደው እያልን ራሳችንን እንጠይቅ።


💐 ሼር & ጆይን
የሙሂ ማስታወሻዎች 👇👍
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

12 Oct, 10:22


ማሻ አላህ ፕሮፋይሎችሽ ደስ ይላሉ(ከሴት ፎቶ የፀዱ፣ ቁርአን፣ ሃዲስና አስተማሪ መልክት...ሃያዕ ያላት ሴት የሚገልፁ ናቸው።) ግን እውነታውስ እንደዛው ነው? ማለት አንችን ይገልፃሉ? ወይስ ፍላጐት ነው? ወይስ ራስን ማታለያና መደበቂያ ነው?
መልሱን ራስሽን ፈትሽበት ጌታሽ ጋር ቀርበሽ በግዳጅ ከመፍተሽሽ በፊት!


🍫 🫧Share
የሙሂ ማስታወሻዎች👇 👍
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

11 Oct, 15:33


በሄድክበት ሁሉ ትክከለኛ ሙስሊም ሁን!

https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

07 Oct, 21:46


የሞተ ዘመዱን በህልሙ አየውና እንዴት ነህ አለው!
ሰውየውም እጅግ በጣም ተፀፀትን እናውቃል(ሁሉም ነገር ግልፅ ሁኖልናል)ግን ችግሩ አንሰራም! እናንተም ታውቃላችሁ ግን አትሰሩም አለው!
ሱብሃናላህ! አንቃን!
ያረብ ዱንያ ዱንያ እንዳልን እንዳትወስደን!


የሙ 👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

06 Oct, 13:28


ቤትሽ ይብቃሽ!
ልታይ ልታይ አትበይ

https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

05 Oct, 14:59


ቀብር እየጠራሽ ነው!
አንቺ ግን አሁንም ተዘናግተሻል

https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

04 Oct, 08:28


🎁 ኢስላም ብቻ!

ሙስሊሞች ነን። አመታዊ በአሎቻችን ሁለት ናቸው።
ዒደል ፊጥር እና ዒደል አድሓ። ከዚህ ውጭ
👉 የሳዑዲም ይሁኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ በዓላት
👉 የብሄርም ይሁኑ የባህል አውዳመታት አይመለከቱንም።!
የአዲስ አመት መግቢያን፣ የዘመን መለወጫን ብናከብር ኖሮ ከክርስትናው እንቁጣጣሽ ይልቅ የኢስላማዊውን ሙሐረምን እናከብር ነበር።

አዎ! በኢስላም መስቀል፣ ጥምቀት፣ መውሊድን (ገና)፣ ኢሬቻ የሚባል በዓል የለም። በዘር ተጎትተን በልማድ ታስረን የምንጓዝበት ስርአት የለም።❗️

    ኢስላም ብቻ❗️👍

🩸ሼር ሼር ሼር
Join & share
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

የሙሂ ማስታወሻዎች

03 Oct, 17:03


ኹጥባ ላይ ሙባይል መንካት ጁሙዓን ያበላሻል።! የጁሙአን ኹጥባን ክብር እንወቅ። ስልካችንን ሳይለንት ከማድረግ ውጭ ኹጥባ እየተደረገ ስልክ አንነካካ። አላህን እንፍራ!


🎁 የሙhi ማስታወሻዎች 👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

02 Oct, 11:45


አላህ ሆይ ልቤ ውስጥ ለአማኞች ጥላቻ እንዲኖር አታድርግብኝ! ሁሉንም አማኞች እንድወድ እንዳከብር እንዳዝንላቸው አድርገኝ፣ ያጠፋም አማኝ ካለ እንድመክር ወፍቀኝ!!


የሙሂ ማስታወሻዎች 👇
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

28 Sep, 19:03


መሃተሙን ጠብቂው!
ሃቁ ያልሆነ ሰው እንዳይነካው።!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

25 Sep, 20:14


ለራሱማ እንስሳም ያውቃል ትንሽ ከእንስሳ ከፍ እንበል!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

21 Sep, 19:36


አሁንስ ገባሽ ለምን ሃራም ነው እንደተባለ!?


የሙሂ ማስታወሻዎች 👇
https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

18 Sep, 09:20


በውዴታ ስም!?
.
.
.
ቢስሚላህ
እስኪ እውነት እውነቷን እናውራ።

የአኺ አንድ ሰው ከጀርባችን ስማችንን እያጠፋ ንብረታችንን እያወደመ ክብራችን ላይ ድምበር እያለፈ መቶ እወዳሃለው ብሎ ቢያቅፍንና ቢስመን ውዴታውን ይገልፃል? ልክ እንደዚሁም ሱናቸውም መከተል አቅቶን በዲናችን ላይ አዲስ ነገርን እየፈጠርን ነብዩን እወዳለሁ ማለት ውስጣችን የሚቀበለው ነገር ነው።?

ወንድሜ ሆይ ፖንክ ተቆርጠን ፣ ሱሪያችንን አየጎተትን፣ ስቲክኒ ለብሰን፣ ከበሮ እየቀጠቀጥን መጨፈር ነውንዴ ውዴታ? ነበዩን መውደድ ማለት ልብ ቅርፅ ልብሳችን ላይ መፃፍ ነው? ፊዳከ አቢ ወኡሚ እያልን በየ ሚዲያውና በመኪናችን ላይ መለጠፍ ውዴታ ነው? ወላሂ ነብዩን ምንወድ ቢሆን ሱናቸውን ነበር ምንከተለው፣ ቢድአን ርቀን ተውሂድን አፍቃሪ፣ ሃቅን ላይ ቋሚ እንሆን ነበር!

አንቺስ ያ ኡኽቲ ሰውነተሽን አጣብቀሽ የመቀመጫሽንና የወገብሽን ቅርፅ በአደባባይ እያሳየሽ፣ ተቀባብተሽ፣ ፀጉርሽን እንደ ግመል ሻኛ ቆልለሽ ወተሽ ወንድሞችሽን እየፈተንሽ በመጨፈር ትክክለኛ የነብዩን ወዳጅነትሽን ይገልፃል ብለሽ ታስቢያለሽ ወይስ በሳቸው ላይ ማሾፍ? እውነት ነብዩ ይሄን ተግባርሽን ቢያዩ አታፍሪበትም? በሙሉ ልብ ይሄን ያደረኩት ስለምወድህ ነው ትያቸው ነበር።? በጭራሽ አታያቸውም ስለዚህ ማስመስሉን እንታወውና የእውነት ወዳጆች እንሁን።! እንደ እንቁ ሴት ሶሃብያቶች ይሁን አለባበስሽም፣ ሀይዕሽም፣ ስነ ምግባርሽም፣ እውቀትሽንም በመያዝ፣ በድብቅም በግልፅም አላህን የፍራን እንሁን። ያኔ ነብዩን እወዳለሁ ብለሽ መናገር አይጠበቅብሽም ተግባርሽና ሁኔታሽ ይናገራልና ነብዩን የምትወጂ መሆንሽን።

ስሚ እህቴ አላህ ይዘንልሽና! ከማስመሰል እርቀሽ ትክክለኛ የነብዩ ወዳጅ ብትሆኚ ኒቃብሽን ለብሰሽ ራስሽንም ወንድሞችሽንም ከፈተና አድነሽ፣ ከመጥፎ ጓደኞች ርቀሽ፣ ነብዩ የተላኩበትን ዲን ለማወቅ ዝቅ ብለሽ ኢልምሽን በመፈለግ ውስጥ ራስሽን የደበቅሽ ትሆኝ ነበር። መልሽልኝ እስኪ ከልብሽ ነው ውዴታሽ? አይደለም ራሳችንን ማታለል ካልፍለግን ለነብዩ ውዴታ ቢኖረን ኑሮ ነብዩን በተግባር ተከታዩች እንሆን ነበር፣ በተግባር ከሳቸው ፊት አንቀድምም ነበር(በግልፅ በደረሱን ትእዛዞች እንብቃቃ ነበር።)አዎ መውሊድ እያልን ያልሰሩትን በመስራት ነብዩ የገነቡትን ዲን ባላፈረስንና በሱናቸውም በተብቃቃን ነበር።!

እንመለስ ወደ አላህ ራሳችንን ማታለል ይበቃ!
   (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

  ያረቢ  ትክክለኛ የነብዩ ወዳጆች ያድርግን እንጂ በውዴታ ስም በሳቸው ላይ የምንሾፍ አታድርገን። 
 
ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ
   @jezakellah

በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል
     መገኛችን👇👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

የሙሂ ማስታወሻዎች

16 Sep, 20:15


ከመስገጃሽ ላይ ሶብር አድርጊ!


https://t.me/sun_flowere

የሙሂ ማስታወሻዎች

15 Sep, 14:27


አንዳንድ ስሜቶች በቃላት አይገለፁም… ስሜት ብቻ ናቸው።!


https://t.me/sun_flowere

2,631

subscribers

145

photos

2

videos