🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️ @khalidkebede Channel on Telegram

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

@khalidkebede


ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል።


ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ
በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ
ስልክ- 0935439820
ኢሜይል- [email protected]

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️ (Amharic)

ዘወልድ ምክረ-ሕግ አለመንገድ አንደኛዉም ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ማጋራት ያልቻናችሁ ሁኔታ ነው። ለሕግ ከታስፈለገ እና ከምክረ አገልግሎቷም በታች ያሳውቃሉ። ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ፣ በማንኛም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ እስልክ- 0935439820 ኢሜይል- [email protected]

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

19 Nov, 18:04


ሰ.መ.ቁ 248877 ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ . ም- የወራሽነት ማስረጃ የወሰደ ሰው በሕግ በታወቀ ጋብቻ ውስጥ ወይም እንደ ባልና ሚስት ግንኙነት ወይም ከሁለቱ በአንዱ በሕግ በሚታወቅ ግንኙነት ውስጥ እንዳልተወለደ ከተረጋገጠ የሟች ልጅ እንደሆነ በመግለጽ ከአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ነው ተብሎ የተሰጠ ማስረጃ ጸንቶ ሊቀጥል የሚችለው ሟች ልጄ ነው በማለት የተቀበሉት ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 131 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሠረት እና በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 143 እና ተከታዮቹ መሠረት አባትነት በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚታወቅባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን በመግለጽ በማስረጃ የተደገፈ ክርክር ሲቀርብ መሆኑን: ሰዎች የወራሽነት ማስረጃ የሚወስዱት መብት ለማቋቋም በማሰብ እንደመሆኑ ይህን ማስረጃ በመጠቀም በሚደረግ ተግባራት የሶስተኛ ወገኖች መብቶች ሊነካ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ከግምት በማስገባት ማስረጃውን የሚሰጠው ፍርድ ቤትም የወራሽነት ማስረጃ ሲሰጥ ጠያቂዎቹ ከሟች ጋር አለን የሚሉትን ግንኙነት በተገቢው ማስረጃ እንዲያረጋግጡ ማድረግ እንደሚኖርበት: በዚሕ አግባብ ተረጋግጦ የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ መሆኑን ማስረጃው የተሰጠው ሰው ባላስረዳበት ሁኔታ ማስረጃውን በመቃወም ክስ ያቀረበ ሰዉ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ የታገደ ነው የመካድ ክስ እንዲያቀርብም ሊፈቀድለት አይገባም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆኑን በመግለጽ አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

17 Nov, 09:41


የሂሳብ ሰራተኛ ሆነ የገንዘብ ጉደለት አለበት ተብሎ የተከሰሰ ሰው ጉድለት እንዳለበት አምኖ ክስ ከቀረበ በኋላ ገንዘቡን የከፈለ ቢሆንም በእምነት ማጉደል ወንጀል ተጠያቂ ከመሆኑ አይድንም፡፡
ገንዘቡን በሽያጭ ከሰበሰበች በኋላ በወቅቱ ለተበዳዩ ድርጅት ገቢ ሳታደርግ ከቆየች በኋላ የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ክስ እንደቀረበባት ባወቀች ጊዜ ያለ አግባብ ይዛ የቆየችውን የግል ተበዳይ ንብረቶች የሆኑ ካርዶች ሽያጭ ዋጋን መመለሷ የዐ/ህግን ክስና ማስረጃ የሚያጠናክር ከመሆኑ በቀር ወንጀሉን አልፈጸመችም የሚያሰኝ ባለመሆኑ፣ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሷ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስባ ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል የፈጸመችና የተከሰሰችበትን የህግ አንቀጽ መተላለፏን ተጠሪው ዐ/ህግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ያስረዳ ስለሆነ የሥር ፍርድ ቤት ይህንን ማስረጃ በአግባቡ ሳይመዝን እና ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀሉን ከፈጸመች በኋላ ገንዘቡን መመለሷ ብቻ ወንጀሉን የመፈጸም ሃሳብ እንደሌላት የማያረጋግጥ መሆኑንም ከግንዛቤ ሳያስገባ፣ ሂሳቡ የተመረመረው በተገቢው መንገድ ተጠሪዋ ሳትጠራ በመሆኑ ለሚለው ምክንያቱ በተገቢው መንገድ አልተጠራችም ስላለበት ምክንያት መነሻ ያደረገው ምንም በክርክሩ ሂደት የተገለጸና የተረጋገጠበት ሁኔታ ሳይኖር በኦዲተር ተጠሪዋ የፈጸመቸውን ጉድለት የሚያሳየውን የኦዲት ሪፖርት፣ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መነሻነት ከፌዴራል ዋና ኦዲተር የተላከውም ደብዳቤ በአንድ የውስጥ ኦዲተር የተሰራ የኦዲት ምርመራ ህጋዊነት የሌለው ነው በማለት የሚያረጋግጥ ባለመሆኑ የኦዲት ሪፖርቱን ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር የሥር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዳሜ የማስረጃ ምዘና ስህተት ያለበት በመሆኑ ተጠሪዋ ክሱን ልትከላከል ይገባል ብለናል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 242958 ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከሰጠው ውሳኔ የተወሰደ

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

16 Nov, 15:06


በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 161 የተቀመጠዉ ቅድመ ሁኔታ ተሟልቶ አንድ ክስ ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይ ትዕዛዝ ሲሰጥ ነገሩ እንዲሰማ በተቀጠረበት ቀን ተከሳሹ ሳይቀርብ ቢቀር በሌለበት የሚፈረድ መሆኑን የሚገልጽ የመጥሪያ ማስታወቂያ በጋዜጣ እንዲወጣ ፍርድ ቤቱ እንደሚያዝ ወይም ተከሳሹ የሚደርስ መስሎ ከታየዉ መጥሪያዉ የሚደርስበትን ሌላ መንገድ ፍርድ ቤቱ ሊያዝ እንደሚችል በቁጥር 162 ተመልክቷል፡፡ ይህን ሥርዓት ተከትሎና በዚሁ ሕግ ቁጥር 163(3) መሠረት እንደ ማንኛዉም ደንበኛ ክስ ታይቶ ፍርድ የተሰጠ እንደሆነ በሕጉ ቁጥር 197 እስከ 202 በተመለከቱት ምክንያቶች ፍርዱ ዉድቅ እንዲደረግ ተከሳሹ ማመልከቻ ማቅረብ እንደሚችል በቁጥር 164 ተመልክቷል፡፡ የሕጉ ቁጥር 199(ሀ እና ለ) ደግሞ በሌለበት ፍርድ የተሰጠበት ሰዉ ፍርዱ ዉድቅ ተደርጎ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ የሚያቀርበዉ ማመልከቻ የሚፈቀደዉ እንዲቀርብ መጥሪያ ያልደረሰዉ እንደ ሆነ ወይም ራሱ ወይም ጠበቃዉ ከአቅም በላይ በሆነ ኃይል ምክንያት መቅረብ አለመቻሉን ያስረዳ እንደሆነ ነዉ በማለት ደንግጓል፡፡
መጥሪያዉ ያልደረሰዉ እንደሆነ” የሚለዉ መስፈርት እንዴት ሊተረጎም ይገባል የሚለዉን ስንመለከት “መጥሪያዉ ያልደረሰዉ እንደሆነ” የሚለዉን መስፈረት በተመለከተ እንደሕጉ አጻጻፍ መጥሪያ የደረሰዉ መሆኑን የማስረዳት ግዴታ ያለበት ዐ/ሕግ እንጂ ተጠሪ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የሕጉ አጻጻፍ ፍ/ቤቱ መጥሪያ የደረሰዉ መሆኑን ግምት እንዲወስድ ዕድል አይሰጥም፡፡ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 162 የተመለከተዉ የጋዜጣ ጥሪ ጉዳዩን ተከሳሹ በሌለበት ለማየት ጥሪ የማድረጊያ ዘዴ እንጂ ፍርዱ ውድቅ ተደርጎ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ የቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ ለማድረግ የሚያስችል መስፈርት አይደለም፡፡ ተከሳሽ የሆነ ወገን “መጥሪያዉ ያልደረሰዉ እንደሆነ” የሚለዉን መጥሪያ ያልደረሰዉ መሆኑን በማስተባበል ማስረዳት የሚጠበቅበት፤ ግምት መዉሰድ ሳያስፈልግ ዐ/ሕግ ለተከሳሹ መጥሪያ የደረሰዉ መሆኑን በበቂ ማስረጃ ማረጋገጥ ሲችል ብቻ ነዉ፡፡
ከላይ ከተገለጸዉ በተጨማሪ “መጥሪያዉ ያልደረሰዉ እንደሆነ” የሚለዉን መስፈርት ተከሳሽን በሚጠቅም መልኩ በሰፊዉ መተርጎም እና የተከሳሽን የመከራከር መብት የማረጋገጥ ግዴታ ፍ/ቤቶች ግደታ አለባቸው፡፡
ሆኖም ግን ፍ/ቤት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ለማድረግ የሰጠው ምክንያት በምስክሮቻቸው አመልካች አዲስአበባ ከተማ የነበሩ ስለመሆኑ አሳማኝ በሆነ ሁኔታ አላስረዱም በማለት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 162 ተከሳሹ በሌለበት ነገሩ እንዲሰማ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ለመስጠት የሚችልበትን ቅድመ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ለአመልካች የጋዜጣ ጥሪ ማስተላለፉ መጥሪያ ይደርሳቸዋል የሚል ግምት ለመውሰድ እንጂ መጥሪያ እንደደረሳቸው ማረጋገጫ አድርጎ የሚወሰድ ባልሆነበት እንዲሁም ተጠሪ የሆነው ዓቃቤሕግ አመልካች ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ወይም የወንጅል ክስ የቀረበባቸው ስለመሆኑ እያወቁ የተደበቁ ስለመሆኑ ባላስረዳበት አመልካች ከተከሰሱበት ወንጀል ክብደት አንጻር በሌሉበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ጉዳዩ ባሉበት እንዲታይ ማድረግ ሲገባው የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ብይን የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 199(ሀ) ድንጋጌ ይዘትና በሕገመንግስቱ ለተከሰሱ ሰዎች የተጠበቁላቸውን መሠረታዊ መብቶች ያላገናዘበ በመሆኑ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ብይን በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4/ ሀ እና ሸ) እና ቁጥር 10(1/ሐ) ላይ ከተቀመጡት መመዘኛዎች አንጻር ሲታይ በዚህ ችሎት ሊታረም የሚችል መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ነው፡፡
ምንጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሰ/መ/ቁ. 242504 ሰኔ 28 በቀን 2016 ዓ.ም ከሰጠው ውሳኔ የተወሰደ /ያልታተመ/

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

10 Nov, 11:14


በሌላ ሰው ገንዘብ በራስ ስም ቤት ስለመግዛት
--------------------
ከሳሽ ተከሳሽ በኃይል የያዘብኝን ቤትና ቦታ ለቆ እንዲወጣ ይወሰንልኝ የሚል ክስ ሲያቀርብ ሊለቅልኝ ይገባል የሚልበት ምክንያት በተከሳሽ ስም ቢገዛም የከሳሽ ነዉ በሚል ከገለጸ ከሳሽ ከቤቱ ጋር በተያያዘ መብትና ጥቅም ያለዉ መሆኑን በግልጽ በሚያሳይ ሁኔታ የቀረበ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። ተከሳሽ ከሳሽ ምንም ዓይነት የባለሀብትነትም ሆነ የባለይዞታነት መብት ባይኖራቸዉ ያቀረበዉ ክስ ነዉ በሚል ያሚያቀርበዉ መቃወሚያ ከሳሽ በእርግጥ በቤቱ ላይ መብት ያለዉ መሆን ያለመሆኑ በክርክር ሂደት ተጣርቶ እልባት ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ ከሚባል በስተቀር ከሳሽ ክሱን ለማቅረብ መብትና ጥቅም የለዉም ወደሚል ድምዳሜ የሚያደርስ ባለመሆኑ ከመነሻዉም በመጀመሪያ መቃወሚያነት ሊቀርብ የሚገባዉ አይደለም።
ሰ/መ/ቁ 216702 ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓም የተወሰነ
source:- Minda Girma Law Office

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

09 Nov, 07:10


ምስክር ሆነ ማስረጃ የሚቀርበው ተከራካሪዎች
ያቀረቡትን ፍሬነገር መኖር አለመኖር ወይም
ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንጂ አዲስ ክርክር
ለማቅረብ/ለመቀበል አይደለም፡፡በግራቀኙ ተከራ
ካሪዎች ያልተነሳን ፍሬነገር መሠረት በማድረግ ፍርድቤቶች ጭብጥ በመያዝ መወሰን
መሠረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ግድፈ
ት የተፈጸመበት ነው።
የሰ/መ/ቁ 234525 ያልታተመ

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

07 Nov, 14:18


የሰበር መ/ቁ 241380/#DANIEL FIKADU LAW OFFICE/                                                                                       አመልካች፡- ሃሌ ሉያ አጠቃላይ ሆሰፒታል ኃ /የተ/የግ/ማህበር
ተጠሪ፡- 1ኛ- ህጻን ደጀን ፋሲል
2ኛ- ወ/ሮ ዮልያ ረዳ                                                                       
በህክምና ስህተት ምክንያት - ብር 1844000 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አራት ሺህ ብር) እንዲከፈል ተወስኗለ !!!      
የሰበር አቤቱታው ጭብጥ -2ተኛ ተከሳሽ የተናጠልና የጋራ ሃላፊነት ስላለበት ግማሹን ክፍያ እነዲከፍል ይደረገልኝ  !!!

                                                                                     የሰበር አመልካች በፍ/ብ/ህ/ቁ 2155 መሰረት ከስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ ጋር የአንድነት እና የነጠላ ሃላፊነት አለባቸዉ የተባሉ ናቸዉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪዎች ከሁለቱ አንደኛዉን መክፈል ይችላል ብለዉ ያመኑበትን ሰዉ ከሰዉ መጠየቅ እንደሚችሉ ከፍህቁ 2161 ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻል ነዉ ፡፡ ስለዚህ የሰበር አመልካች እኔ ብቻዬን እንደከፍል መወሰኑ ያላግባብ ነዉ በማለት ያነሱት ቅሬታ የህግ መሰረት የሌለዉ ነዉ፡፡ መብታቸዉ የተወሰነዉን ገንዘብ ከፍለዉ የስር አንደኛ ተከሳሽ እንዲተካቸዉ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2161(2) መሰረት መጠየቅ ብቻ ነዉ ፡፡

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

05 Nov, 19:26


በተከራካሪ ወገኖች መካከል የሽያጭ ውሌ የሌለና ረቂቅ ውል በመሆኑ የሚፈጽሙት የቤት ሽያጭ የለም ከተባለ ግራ ቀኙ ከውል በፊት ወደነበሩበት ቦታ የሚመለሱ እና ቤት ሽያጭ በሚል የተከፈለ ገንዘብ የሽያጭ ዋጋ ክፍያ/ ቅድሚያ ክፍያ እንጅ/ ቀብድ አለመሆኑ ከተረጋገጠ የተከፈለ ገንዘብ ያክል መመለስ እንጅ አጠፌታ እንዲከፍል የሚስገድድ አይደለም፡፡
- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 26 በመ/ቁ 211204 ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ላይ የተወሰደ፡፡

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

28 Oct, 05:23


የአ/ብ/ክ/መ ረቂቅ የገጠር መሬት አዋጅ

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

27 Oct, 14:46


#የሰበር መዝ/ቁ 240242
~ግንቦት 29/2016ዓ.ም~
`````````````````````
የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የ አደራ ውል የግድ በፅሁፍ ሊደረግ የማይገባ ስለመሆኑ እና አንዲህ አይነት ዉል (ይዞታ ላይ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የ አደራ ዉል) ንብረቱን ሌላ ሰው ለግዜው አንዲጠብቅ አንጂ የማስተላለፍ ዉጤት ያለው ባለመሆኑ ዉሉ የ ፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1723(1) በሚደግገው መሰረት በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት የግድ መደረግ የሌለበት ስለመሆኑ የፌደራል ጠ/ፍ/ቤ/ሰበር ሰሚ ችሎታ በመዝገብ ቁጥር - 240242 (ያልታተመ) ላይ በ ቀን - 29/09/2016 አ.ም አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቷል::

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

27 Oct, 09:34


አስቀድሞ የተደረገው ክርክር መነሻነት የተሰጠው ውሳኔ የተፈጸመ ከሆነ እና በዚህ ፍርድ እና ውሳኔ መብቴ ተነክቷል የሚል አካል ያለው መፍትሄ ምንድን ነው?
የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በአንድ ንብረት ላይ መብት አለኝ፣ በክርክሩ ሂደት አልተካተትኩም በሚል ምክንያት መብቴ ተነክቷል የሚል ወገን መብቱን ሊያስከብር የሚችልበትን ሥርአት በየደረጃው ዘርግቷል፡፡ ለዚህም ጉዳዩ በክርክር ሒደት ላይ ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41 መሠረት የጣልቃገብነት አቤቱታ በማቅረብ፤ ውሳኔው ከመፈጸሙ በፊት ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ በማቅረብ፤ ውሳኔው በአፈፃፀም ሂደት ላይ ሆኖ ንብረቱ ያለአግባብ ተይዞብኛል የሚል ወገን ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 418 መሰረት መብቱን ማስከበር የሚችልበት አግባብ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዚህ አግባብ መብቱን ማስከበር የማይችል እና በንብረቱ ላይ የተሻለ መብት አለኝ የሚል ተከራካሪ ወገን ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 421 ወይም እንደነገሩ ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 455 መሰረት ክስ መሥርቶ መብቱን ማረጋገጥ የሚችል መሆኑን በድንጋጌዎቹ ላይ በግልጽ ተመልክቷል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በዚህ ረገድ በሰ.መ.ቁ 50835 እና በሌሎችም መዛግብት በየትኛውም እርከን ላይ የሚገኙ ፍርድ ቤቶችን አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶአል፡፡
በያዝነው ጉዳይ አመልካች ክስ ያቀረቡበት አከራካሪ የሆነው ይዞታ አመልካች ተከራካሪ ባልሆኑበት መዝገብ ውሳኔ አግኝቶ አፈፃጸሙ ተጠናቅቆ ተጠሪ ይዞታውን በተረከቡበት ሁኔታ አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት ፍርዱን ሊቃወሙ የሚችሉበት አግባብም አይኖርም፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ የቀረበለት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች አስቀድሞ የተሰጠው ፍርድ መብታቸውን የሚነካው ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት መቃወሚያ ከሚያቀርቡ በቀር አዲስ ክስ ማቅረብ አይችሉም በማለት የሰጠው ወሳኔ የድንጋጌውን ይዘት እና ዓላማ ያላገናዘበ እና መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 210420 ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት /ያልታተመ/ ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ላይ የተወሰደ፡፡

1,438

subscribers

583

photos

183

videos