አለሕግAleHig ️ @alehig Channel on Telegram

አለሕግAleHig ️

@alehig


ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

አለሕግ (Amharic)

አለሕግ ማን ነው? እና ምን ነው? ይህ ታሪክ ፕሮማችህን ወከፋትና የአየር ግቡን መፍትሄዎች እንዲሰራበት በተዘጋጀ ቻናል ውይይትን በከፍተኛ እውቀት ማድረግና ከሆነ አንዳንድ ሰዎችን በአንዳንድ ምክር እንዴት ማድረግ ወደ ትክክለኛው ውይይት ለመጠቀም ይቻላል። ይህን ቻናል ከእኛ ፕሮማችህን ለመቀረፍ እና መረጃዎቹን ዙሪዎችን ለማቅረብ እባክዎ ለማግኘት ለማከናወን የተለየ እርምጃ ከተሰማበት አንዱ ሰዎች የሚያደርግን እና ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ መረጃዎቹን ማግኘት እንችላለን። እናም በመሆኑ የሚከተለው ቢሆንም አለሕግ ቻናል በነዚህ በመቆጣጠር ለነባር የታሰሩት ልዩ ተቆጣጤዎችን ውይይትን ለማድረግ የሚከታተሉበት ነው። እናንተ ያንን እናም ሌሎች የአለሕግ ቻናል እንዴት መረጋገጥ እንችላለን? የአለሕግ ቻናል በተለየ መክፈት ድምፅ፣ ለመመሪያዎ ማቆም፣ መከተል ለማስቆም የቻናል አለቃዎ እና ክፍል የሚደረግ የህግ ምክር እና መፍትሄዎች ላይ መለያየት ያለው ነው። አለሕግ በአስተማሩ ውስጥ የተመሠረተ ነው።

አለሕግAleHig ️

27 Jan, 07:51


የፌደራል የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016 https://www.alehig.com/proclamation-no-1333-2024-the-federal-public-procurement-and-property-administration-proclamation/

አለሕግAleHig ️

27 Jan, 07:47


የተፈቀዱ የግዥ ዘዴዎች
1. በማናቸውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ግዥ አፈፃፀም የሚከተሉት የግዥ ዘዴዎች ሥራ ላይ ይውላሉ፡-
ሀ) ግልፅ ጨረታ፣
ለ) በማጣሪያ የሚከናወን ጨረታ፣
ሐ) ውስን ጨረታ፣
መ) በቀጥታ የሚፈፀም ግዥ፡፡ የፌደራል የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016 https://www.alehig.com/proclamation-no-1333-2024-the-federal-public-procurement-and-property-administration-proclamation/

አለሕግAleHig ️

24 Jan, 20:49


ትራምፕ በአሜሪካ የሚወለዱ ህጻናት በቀጥታ ዜግነት እንዳያገኙ ያሳለፉት ውሳኔ በፌደራል ዳኛ ታገደ

22 ግዛቶች ህጻናትን "ሀገር አልባ" ያደርጋል ያሉት የፕሬዝዳንቱ የስራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ እንዲታገድ ክስ መስርተዋል።

https://bit.ly/3E9XGmO

አለሕግAleHig ️

24 Jan, 20:42


#Ethiopia

ግምሩክ ኮሚሽን አምራቾች ወደ አገር ዉስጥ እቃዎችን ሲያስገቡ በሚያቀርቡት ህጋዊ የግብይት ዋጋ ብቻ እንዲስተናገዱ ፈቅዷል።

ኮሚሽኑ በአምራቾች ወደ አገር ዉስጥ የሚገቡ ዕቃዎች የዋጋ አተማመን ስርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።

158/2011 የተደነገገውን በጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ዋጋ አተማመን መመሪያ እንዲከለስ ማድረጉን ነዉ የተገለጸው።

ይህ መመሪያ በአምራቾች ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ በሚወስንበት ወቅት የሚወስደው ጊዜ ከአምራቾች ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ ይገኛል።

ይሄን ተከትሎ በአምራቾች ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ አተማመን ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉን ተነግሯል።

መመሪያ ቁጥር 158/2011 እስኪሻሻል ድረስ በክሊራንስ ጊዜ የዋጋ ማጣራት ሃደቱ የሚወስደውን ጊዜ ለማስቀረት በሚል አምራቾች እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ በሚያቀርቡት ህጋዊ የግብይት ዋጋ እንዲስተናገዱ ኮሚሽኑ በላከው ሰርኩላር ፈቅዷል።

ይህ ሰርኩላር ፦
- አምራቾች
- ልዩ መብት የተሰጣቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ፕሮግራም ተጠቃሚ ድርጅቶች፥
- ለኢንቨስትመንት ሥራ ዕቃዎችን በቀረጥ ነፃ የሚያስገቡ ድርጅቶች፤
- የመንግስት ፕሮጀክትን ለመስራት በግል ድርጅቶች የሚገቡ ዕቃዎች፣
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የፌዴራልና የክልል መንግስታት ተቋማትን ይመለከታል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካቲፓል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

አለሕግAleHig ️

22 Jan, 15:59


በ6 ወራት የተመዘገበ ፍቺ ሲጨርም ጋብቻ ቀንሷል።

የአዲስ አበባ ሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ የተቋማቸውን የበጀት አመቱን የስድስት ወራት አፈጻጸም ትላንት ሪፖርት አድርገዋል።

በዚህም ወቅት እንደገለጹት ከተከሰተው 21,674 ጋብቻ ለመመዝገብ ታቅዶ 15,574 (72.65%) ምዝገባ ማደረግ እንደተቻለ ተጠቁሟል። ቁጥሩ ከ2016 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 7% የምዝገባ ቅናሽ አሳይቷል።

ከተከሰተው ፍቺ 4,873 ለመመዝገብ ታቅዶ 3,769 ፍቺ የተመዘገበ ሲሆን ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 33.99% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።

በተጨማሪ ፦

➡️ ከተከሰተው ሞት 15,716 ለመመዝገብ ታቅዶ 11,376 (72.38%) ምዝገባ በማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 29.83% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።

➡️ ከተወለዱ ህፃናት ውስጥ 37,750 ለመመዝገብ ታቅዶ 41,183 መመዝገብ መቻሉ ተጠቁሟል። ይህም በከተማው ምዝገባ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።  ከ2016ዓ.ም አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር 103% ብልጫ አሳይቷል።

በሌላ በኩል ፥ ባለፉት 6 ወራት 25,581 የክልል መሸኛዎች ትክክለኛነት እንዲጣራ ለክልሎች መላኩን የገለጸው ተቋሙ አገልግሎት ለማግኘት ሪፖርት ያደረጉ 9,504 አመልካቾችን መሸኛ መርምሮ የነዋሪነት ምዘገባ አድርገው አገልግሎት እንዲያገኙ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

ተጨማሪ
@addisvaitalpress

አለሕግAleHig ️

22 Jan, 15:48


በማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 17 ንዑስ አንቀፅ 4 መሰረት በአንድ ሰዓት የስርጭት ጊዜ ውስጥ የአንድን ምርት ወይም አገልግሎት ተመሳሳይ የንግድ ማስታወቂያ ከሁለት ጊዜ በላይ ማሰራጨት አይቻልም፡፡

*በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡

አለሕግAleHig ️

21 Jan, 19:37


መራቆት ነውር ባልሆነባት ሀገር ሂጃብን መከልከል ያሳፍራል!💬⚠️⚠️⚠️

መከልከል የነበረበት መጥፎ ድርጊት ስንት ነበር?🔽⁉️🚫▶️🔖

አለሕግAleHig ️

21 Jan, 11:38


15 ሺህ 574 የጋብቻ ምዝገባ💎
3 ሺህ 769 ፍቺ ምዝገባ💎💎
ተከናውኗል 💎

አለሕግAleHig ️

21 Jan, 05:49


ከማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ የመንደር ውል ህጋዊ የሚሆንባቸው 5/አምስት/ ሁኔታዎች 👉(Abraham Yohanes)

የማንይቀሳቀስ ንብረትን ለማስተላለፍ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል በ ፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ካልተደረገ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን ከተወሰኑ የሰበር ችሎት ውሳኔዎች በመነሳት የመንደር ውል ህጋዊ ተብለው የሚቆጠሩበት ሁኔታዎች አሉ። እነዚህ 5 ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

❶ኛ የሽያጭ ውል መኖሩ ከታመነ ወይም ካልተካደ

ገዢ ውል እንዲፈፀምለት ክስ አቅርቦ ከሳሽ መከላከያ መልሱ ላይ በመካከላቸው ውል መኖሩን ካመነ ወይም ካልካደና በሌሎች ነጥቦች ላይ መልስ ከሰጠ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት አልተደረገም ብሎ ውድቅ ሊያደርገው አይችልም።

❷ኛ በማህበር በመደራጀት የተሰራ ቤት በሽያጭ ማስተላለፍ (ሰ/መ/ቁጥር 36294 ቅፅ 8)

በማህበር በመደራጀት እየተሰራ ያለ ቤት ቤቱ ተጠናቆ ካርታ እስኪወጣለት ድረስ የማህበሩ አባል የሆነ ሰው ይህን ቤት ቢያስተላልፍ ቤት የመስራት መብቱን ወይም እጣውን እንዳስተላለፈ እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረትን እንዳስተላለፈ አይቆጠርም። የማህበሩ አባል በስሙ ካርታና የባለቤትነት ማስረጃ እስካልተሰጠው ድረስ ቤቱ ወይም እየተሰራ ያለው ቤት በማህበሩ አጠቃላይ ይዞታ ስር የሚገኝ በመሆኑ የማህበሩ አባል ለ 3ኛ ወገን ሊያስተላልፍ የሚችለው እጣውን ወይም ጥቅሙን እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት አይደለም። እንዲህ አይነት ውሎች የግድ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ሊረጋገጡ አይገባም።

❸ኛ ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (ሰ/መ/ቁጥር 32222 ቅፅ 7)

ብዙን ግዜ እንዲህ አይነት ውል ከ Real Estate ቤቶች ግንባታ ጋር የተያያ ነው። ምንም እንኳን ውላቸው ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ቢሉም ዉሉ በሚደረግበት ግዜ ቤቱ ያልነበረ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ከአንዱ ወደ ሌላው ተላልፏል ሊባል አይችልም። ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል የግንባታ ውል እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ሊባል የሚችል ባለመሆኑ ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መረጋገጥ አይኖርበትም።

❹ኛ አዋዋይ ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች ለተወሰነ ግዜ ሳይፈፀምበት የቆየ የመንደር ውል (የሰ/መ/ቁጥር 36740 ቅጽ 8)

ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ በሰጠው ውሳኔ መሠረት በግራ ቀኙ መሀከል የተደረገው የመንደር ውል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች የተሟሉት የተወሰነ ግዜ ከቆየ በኋላ ቢሆንም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰው አካል ፊት ያልተደረገ ነው በሚል ውድቅ ሊደረግ አይገባም የሚል ነው።

ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ እንዳለው ቤቱን የሚመለከቱ እዳና እገዳ ለማጣራትና ክፍያ ለመፈፀም የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በውል ላይ ማህተም ሣያሣርፍበትና የፕሮቶኮል ቁጥር ሰጥቶ ሣያረጋግጥበት የተወሰነ ጊዜ ያለፈ ቢሆንም እነዚህ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እስኪከናወኑ ድረስ በውል ላይ ማህተም ሣያርፍበት መቆየቱ ወይም የፕሮቶኮል ቁጥር ሣይሰጠው መዘግየቱ ውል እንዳልተደረገ የሚያስቆጥረው ነው ለማለት አያስችልም፡፡

❺ኛ የሊዝ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (የሰ/መ/ቁጥር 191095 & 225796)

በሊዝ የተገኘ ይዞታ ላይ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ወይም ተጀምሮ በግማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የሊዝ መብት ዘመኑ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቦተው የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ ይቻላል። ነገር ግን የሚተላለፈው በቦታው ላይ ግማሽ ግንባታ ከተከናወነ በኋላ ከሆነ በቦታው ላይ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ ከተሰራው ህንፃ ጭምር በመሆኑ የሊዝ መብት ማስተላለፍ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንደ ማስተላለፍ ይቆጠራል። ስለዚህ ሁለት ነገር መታየት ይኖርበታል። የመጀመሪያው አንድ ሰው መሬት በሊዝ ወስዶ ምንም አይነት ግንባታ ካልፈፀመበት ወይም ግንባታ ጀምሮ በግማሽ ከማጠናቀቁ በፊት የሊዝ መብቱን በመንደር ውል ማስተላለፍ ይችላል። ሁለተኛው የግንባታው ደረጃ ግማሽና ከዛ በላይ የደረሰ ከሆነ ግን የሚተላለፈው በቦታው ላይ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ የተገነባውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ጭምር በመሆኑ ውሉ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ መረጋገጥ ይኖርበታል።
https://t.me/Law_issue

አለሕግAleHig ️

19 Jan, 12:10


በጃፓን ሀገር አንድ ለየት ያለ ሕግ አለ እሱም ሜታቦ ሕግ በመባል ይታወቃል፡፡
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
ይህ ሕግ ወፍራም መሆንን የሚከለክል ሲሆን በዚህ ሕግ መሰረት አንድ ዕድሜው ከ40 እስከ 74 የሆነ ወንድ ጃፓናዊ የወገቡ መጠን ዙሪያ ከ90 ሴንቲ ሜትር መብለጥ እንደሌለበት የተደነገገ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ለሴቶች ደግሞ ከ 85 ሴንቲ ሜትር በላይ እንዳይሆን ያስገድዳል፡፡

በዚህ መሠረት አንድ ጃፓናዊ የወገብ መጠኑ በሕግ ከተቀመጠው በላይ ከፍ ካለ የውፍረት መቀነሻ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርግ ወይም እንድታደርግ በሕግ የሚገደዱ ሲሆን በየዓመቱም የጃፓናውያን የወገባቸውን ልክ ማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ሀገሪቱ ይህንን ሕግ ያረቀቀችው የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ ስትል እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

(Success Tax professional)
እርስዎ የሚያውቁት አስገራሚ ሕግ ካለ ቢያጋሩን!
Via Comedian Eshetu Melese

🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱
https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱Website: alehig.com

Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram: ✉️ @MikiasMelak

Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት

We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️

አለሕግAleHig ️

19 Jan, 09:09


በአደራ የቲክቶክ አካውንታችሁን እንድናስተዳድር፣ የምትፈልጉትን ቪዲዮ ብቻ በመልቀቅ በአደራ እንዲቆይ የምትፈልጉ ልታዋሩን ትችላላችሁ።
#Share

አለሕግAleHig ️

17 Jan, 07:02


አሽከርካሪዎች በቀን እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ እንደሚከፍሉ በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአዲስ አበባ ኮሪደሮች ላይ የሚጠየቀው የመኪና ማቆሚያ ዋጋ የሕብረተሰቡን አቅም  ያላገናዘበ እንደሆነ ጥናት ማመላከቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ጥናት በፒያሳ ፣ በቦሌ ፣ በአራት ኪሎ ያሉ አራት የኮሪደር መንገዶችን ላይ ባሉ የመኪና ማቆሚያዎች ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን  በቀን  አሽከሪከዎች ከ40 እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ ወጪ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።

እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ በቀን ለመኪና ማቆሚያ የማያወጡት ብር አቅማቸውን ያላገናዘበ እንደሆነ ተናግረዋል።

አንድ ወር የፈጀው ጥናት በእነዚህ ኮሪደር መንገዶች የእግረኛም ሆነ የመኪና ፍሰቱ ቀልጣፋ መሆኑን ከ400 የጥናቱ ተሳታፊዎች 65 በመቶ የሚሆኑት የገለጹ ቢሆንም የመንገድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና የመኪና መጨናነቅን ቀንሷል ብሎ ቢያመላክትም ከንግድ ሱቆችና ከመኖሪያ ቤቶች መፍረስ እግረኛንም ሆነ የመኪናን ቁጥር ከመቀነሳቸው ጋር ያያያዘው ነገር የለም ተብሏል፡፡

ጥናቱን ያጠኑት ሻካ አናላይቲክስ ከ አለም አቀፍ የቢዝነስ ልማት  ጋር በመተባበር ሲሆን የቢዝነስ ልማቱ  በኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ አሰፋ " ጥናቱ ያተኮረባቸው ኮሪደሮች  ከፒያሳ አራት ኪሎ ፣ ከአራት ኪሎ እንግሊዝ ኤንባሲ ፣  ከአራት ኪሎ ቦሌ ድልድይና   ከሜክሲኮ ሳርቤት እንደሆነና  አጠቃላይ ጥናቱ አንድ ወር ፈጅቷል" ማለታቸው ተገልጿል፡፡

አለሕግAleHig ️

15 Jan, 14:17


ከሕክምና ስህተት ተጠያቂነት ⚠️💎

አለሕግAleHig ️

15 Jan, 11:47


" 16.3 ቢሊዮን ብር ሰብስበናል ! " - ICS

" ባለፋት ስድስት ወራት 10 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደን ከ16.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስበናል። ከ721 ሺህ 623 በላይ ፓስፖርቶችን የማተም ስራም ተሰርቷል። ከታተመው 98 በመቶው ለተገልጋዮች ተሰጥቷል " - ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት (የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር) #EPA

@tikvahethiopia

አለሕግAleHig ️

09 Jan, 10:49


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንብረት ማስመለስ አዋጅ

በወንጀልና በሙስና የተፈራ ንብረት የማስመለስ  አዋጅ ጸደቀ
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው14ኛ መደበኛ ስብሰባው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

አዋጁ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈራን ንብረት ማስመለስ የሚያስችሉና የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በረቂቅ አዋጁ የተደረጉ ማስተካከያዎችና የተጨመሩ አንቀጾችን አስመልክተው ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በአዋጁ ላይ በአስረጅ፣ በህዝብና የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ግብዓት እንደሰበሰበ ገልጸዋል።

የንብረት ማስመለስ አዋጅ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን ለማስመለስ የነበረውን የሕግ ክፍተት የሚሞላ እንደሆነ አስረድተዋል።

አዋጁ ዜጎች በላባቸውና በወዛቸው ንብረት እንዲያፈሩ የሚያበረታታ፣ በወንጀል ንብረት የሚያፈሩትን ተጠያቂ የሚያደርግ፣ የአገርን ዕድገት የሚያሳልጥ እንደሆነ አስተያየት የሰጡ የምክር ቤት አባላት አንስተዋል።

ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ በመሆኑ በተፈጻሚነቱ ላይ ጥንቃቄ ማድረግና አስፈጻሚ አካላትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ እና የዜጎችን ንብረት የማፍራት መብት እንዳይጋፋ መታየት አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።     

የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በአዋጁ ሃብት የማፍራትና የማውረስ ሕገ-መንግስታዊ መብትን የሚቃረን ድንጋጌ አለመካተቱንም አብራርተዋል።

የጸረ-ሙስና ትግል እንዲጠናከር የሚያደርግ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘና የተመዘበረ የአገር ሃብትን ለማስመለስ የሚያስችልና ሕገ-ወጥነትን የሚያስቆም አዋጅ እንደሆነም ጨምረዋል።

ምክር ቤቱ በአዋጁ አስፈላጊነትና ወቅታዊነት ላይ ዝርዝር ውይይት በማድረግ በ ሶሰት ተቃውሞ እና በአራት  ድምጸ  ታቅቦ  በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

አለሕግAleHig ️

09 Jan, 05:38


ውሸት ለማናገር ቀላል ነች፣💎
እውነት ግን ለሚናገሩት ሆነ ለሚሰሙት ከባድ ነው
💎📸💎

አለሕግAleHig ️

07 Jan, 19:12


Losing a top performer will cost far more than retaining them.
Pay people what they're worth.

አለሕግAleHig ️

07 Jan, 12:28


ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፍትሕ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት በክልሉ ሥር በሚገኙ ወረዳዎች ዳኛ ወይም ዐቃቤ-ሕግ ሆኖ ለመሥራት ለሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ያወጣው ማስታወቂያ

ብዛት፡- 300
የመመዝገቢያ ጊዜ፡- ከታኅሳስ 30 እስከ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

አለሕግAleHig ️

05 Jan, 20:53


<<ሊገባን ይገባል አሁን እየተፋፈርን ስለሆነ ነው እንጂ ማንም ኑሮን እየተቋቋመው (Afford) እያደረገ አይደለም፡፡ከሁለትና ሦስት ዓመት በፊት 10 እና 15 ሺህ ደመወዝ የሚያገኙት ሠራተኞች ጥሩ ነበሩ፡፡አሁን ግን 30 ሺህ እና 40 ሺህ ብር ደመወዝ የሚያገኙት ጥሩ ደረጃ ላይ ናቸው አልልም፡፡ የቤት ኪራይ:የትምህርት ቤት ክፍያው:የኑሮ ውድነት ሰማይ ወጥቷል::>>

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ
ለሪፖርተር ጋዜጣ ከሰጠው ቃለምልልስ የተወሰደ

አለሕግAleHig ️

03 Jan, 19:28


⚠️⛔️ባልና ሚስት በጋብቻ መካከል በየትኛውም ንብረት ላይ እርስ በራስ የሚያደርጉት የስጦታ ውል ፍርድ ቤት ቀርቦ ካልፀደቀ በቀር  በህግ ፊት ተቀባይነት የለውም
🔽ፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ.መ.ቁ. 158292 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም‼️

አለሕግAleHig ️

03 Jan, 18:27


Proclamation no. 1321/2024 personal Data Protection proclamation

አዋጅ ቁ. 1321/2016 የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ

አለሕግAleHig ️

02 Jan, 08:05


ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ የሕግ እውቀት alehig.com

አለሕግAleHig ️

01 Jan, 16:32


#ፋይል: አጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ።
https://t.me/Law_issue

አለሕግAleHig ️

01 Jan, 05:10


Happy New Year 2025! We wish you and your loved ones a remarkable year filled with prosperity, happiness, and countless achievements. May this year be a time of growth, fulfillment, and abundant blessings. Here's to new beginnings and endless possibilities! #አለሕግ @AleHig

አለሕግAleHig ️

28 Dec, 10:23


የፍትህ ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት
   መግቢያ📤💬📥
የፍትህ ሥርዓቱን በማጎልበት ረገድ ሁሉም የመንግስት አካላት እና ህብረተሰቡ የሚጫወቱት ሚና የማይናቅ ቢሆንም በዋነኛነት ግን ፍርድ ቤት፣ ዐቃቤ ህግ እና ፖሊስ በዚህ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት በግልፅ እንደተደነገገው የዳኝነት ተግባር ለፍርድ ቤቶች የተሰጠ ስልጣን ሲሆን የአስፈፃሚ አካል የሆኑት የፍትህ ሚኒስቴር እና ፖሊስ ስልጣንና ተግባር የሚመነጨው ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገው ከወጡ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ከተደነገጉ አዋጆችና ተቋማቱን ለማቋቋም ከወጡ የማቋቋሚያ አዋጆች ነው፡፡ በዚህም እያንዳንዳቸው የየራሳቸው የሆነ ሥልጣንና ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ 
ሆኖም ብዙውን ጊዜ በተለይም ከወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከምርመራ እስከ ፍርድ ባለው ሂደት ውስጥ የሶስቱን ተቋማት ማለትም የፖሊስ፣ ፍትህ ሚኒስቴርና ፍርድ ቤቶችን ሚና ካለመለየት የተነሳ የወንጀል ተጎጂዎችም ሆኑ ሌሎች ባለጉዳዮች ጉዳያቸውን ለማን ማቅረብ እንዳለባቸው አለማወቅ እና ከምርመራ እስከ ፍርድ ባለው ሂደት የሶስቱንም ተቋማት ሚና ቀላቅሎ የመረዳት ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ ከዚህ በመነሳትም ይህ ፅሁፍ ፍትህ ሚኒስቴር በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ የተሰጡትን ዋና ዋና ስልጣንና ተግባራት በአጭሩ ይዳስሳል፡፡
  ⬇️⬇️⬇️🔈🔈🔈🔖
  የፍህ ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት የህግ ማዕቀፍ
በሌሎች ህግጋት ለሚኒስቴሩ የተሰጡ ሀላፊነቶች እንደተጠበቁ ሆነው የፍትህ ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት በዋናነት የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመደንገግ ከወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀፅ 40 እና በዚሁ አዋጅ የስም ለውጥ ተደርጎበት የፍትህ ሚኒስቴር ከሆነው የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 ይመነጫል፡፡ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 6(2) መሰረት ፍትህ ሚኒስቴር በህግ ጉዳዮች የፌዴራል መንግስት ዋና አማካሪና ተወካይ ሆኖ የመስራት ስልጣን ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ በወንጀልና ፍትሐብሔር ጉዳዮች፣ በሰብአዊ መብት፣ በህግ ማርቀቅና ማስረፅ እንዲሁም በተለያዩ ህግ ነክ ጉዳዮች ዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡፡ ዋና ዋናዎቹን እንደሚከተለው እንመለከታቸዋለን፡፡

  የወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ የፍትህ ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት
የወንጀል ህግ በዋነኛነት የሀገርንና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወጣ ሆኖ እንደ ወንጀል የሚቆጠሩ ድርጊቶችን የያዘ እና ድርጊቶቹ ተፈፅመው በተገኙ ጊዜም የሚያስከትሉትን ቅጣቶች የሚደነግግ ህግ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የፍትህ ሚኒስቴር የወንጀል ፍትህ ሥርዓቱ የሚፈልገውን ዓላማ እና ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ የተለያዩ ስልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡፡ ይህም
• በሌሎች ህጎች ለፖሊስ የተሰጠው ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በፌዴራል ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር የማድረግ፣ የተጀመረ የወንጀል ምርመራ ላይ የክትትል ሪፖርት እንዲቀርብ የማድረግ
• በምርመራ ሂደት ላይ ለመርማሪ ፖሊስ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የማድረግ
• የወንጀል ምርመራዎች በህግ መሰረት መከናወናቸውን የማረጋገጥ፣ አስፈላጊውን ትእዛዝ የመስጠት
• የተጠናቀቁ የምርመራ መዝገቦችን ከህግና ከማስረጃ አንፃር መርምሮ ያስከስሳል ወይም አያስከስስም ውሳኔ የመስጠት 
• የጥፋተኝነት ድርድር የመወሰን፣ ድርድር የማድረግ፣ አማራጭ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድ የመወሰን እና ተግባራዊነቱን የመከታተል
• የፌዴራል መንግስትን በመወከል የወንጀል ጉዳዮች ክስ የመመስረት፣ የመከራከር፣ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ክስ የማንሳት፣ የተነሳ ክስ እንዲቀጥል የማድረግ
• ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የሚሰጡዋቸው ውሳኔዎችና ትእዛዞች የመፈፀምና መከበራቸውን የመከታተል፣ ካልተፈፀሙ ወይም አፈፃፀማቸው ህግን ያልተከተለ ከሆነ ለፍርድ ቤት በማመልከት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ
• በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የወንጀል ቅጣቶች በአግባቡ እንዲፈፀሙ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን የማደራጀት ወይም መደራጀታቸውን የማረጋገጥ
• በፍርድ ቤት የተሰጡ የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የማቅረብ እና አፈፃፀሙን የመከታተል ሀፊነቶችን የሚያካትት መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 6(3) መመልከት ይቻላል፡፡
  የሰብአዊ መብትን በተመለከተ የፍትህ ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት
በአዋጁ አንቀፅ 6(8) መሰረት የሰብአዊ መብቶች ከማክበርና ከማስከበር አንፃር ፍትህ ሚኒስቴር
• በፖሊስ ጣቢያና በማረሚያ ቤት ቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎችን የመጎብኘት፣ አያያዛቸውና ቆየታቸው በህግ መሰረት መፈፀሙን የማረጋገጥ፣ ህገ ወጥ ተግባር እንዲታረም ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ወይም እንዲወሰድ የማድረግ
• ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውን ወይም የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች አፈፃፀም የመከታተል፣ ለሚነሱ ጉዳዮች እንደ አግባብነታቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ምላሽ የመስጠት፣ የስምምነቶቹን ብሔራዊ አፈፃፀም ሪፖርት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የማዘጋጀት
• ነፃ የህግ ድጋፍን አሰጣጥ ስትራቴጂዎችን የመቅረፅ፣ አፈፃፀሙን የመከታተል፣ በመስኩ የሚሰማሩ አካላትን የማስተባበር
• ብሔራዊ የሰብአዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብርን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማዘጋጀት፣ አፈፃፀሙን የመከታተል፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚመለከታቸውን አካላት የማስተባበር፣ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት የማቅረብ
• ነፃ የህግ ድጋፍ አሰጣጥ ስትራቴጂዎችን የመቅረፅ፣ አፈፃፀሙን የመከታተል እና በመስኩ የሚሰማሩ አካላትን የማስተባበር እንዲሁም
• የሰብአዊ መብት ትምህርት እና የንቃተ ህግ ለማዳበር በተለያዩ ዘዴዎች ትምህርት የመስጠት እና  በዘርፉ የተሰማሩ የሚመለከታቸው አካላትን የማስተባበር ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡

  የፍትሐብሔር ጉዳዮችን በተመለከተ የፍትህ ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት
በአዋጁ አንቀፅ 6(4) መሰረት በፍትሐብሔር ጉዳዮች ረገድ ፍትህ ሚኒስቴር
• በፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የህዝብ እና የፌዴራል መንግስት መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ የመከራከር፣ የማስከበር፣ እንዲከበሩ የማድረግ፣ የመከታል እና የመቆጣጠር
• ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶች የውል ዝግጅት እና ድርድር የማድረግ፣ የህዝብና የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ይጎዳል ብሎ ሲያምን በሌሎች ጉዳዮች የውል ዝግጅትና ድርድር የማድረግ ወይም የሚመለከታቸውን አካላት የማማከር
• የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤትን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ የመመስረት፣ በከሰሱበት ወይም በተከሰሱበት የፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ ክርክር የማድረግ፣ በክርክር አመራር ላይ ለመስሪያ ቤቶች አቅጣጫ የመስጠትና በህግ መሰረት ፍርድን የማስፈፀም

አለሕግAleHig ️

28 Dec, 10:23


• የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸው ያልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር  ጉዳዮች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ እንዲወሰን ውሳኔ የመስጠት፣ በውሳኔው መሰረት መፈፀሙን የማረጋገጥ
• በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ክስ ለመመስረት የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ወክሎ የመከራከር
• የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ ተበዳዮች እንዲካሱ፣ መልሰው እንዲቋቋሙ እንዲሁም ከጉዳቱ የተያያዙ የፍትሐብሔር ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እነሱን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ የማቅረብ ወይም የመደራደር
• የኢፌዲሪ መንግስት በአለም አቀፍ የዳኝነትና ከፊል ዳኝነት አካላት በሚከስበት ወይም በሚከሰስበት ጉዳይ መንግስትን በመወከል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ክርክር የማድረግ፣ ድርድር የማካሄድ እና ውሳኔውንም የማስፈፀም ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡

  የህግ ማርቀቅ እና ማጠቃለል ሥራን በተመለከተ የፍትህ ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት
ከህግ ማርቀቅ አንፃር ሚኒስቴር መ/ቤቱ
• በፌዴራል መንግስት የሚወጡ ህጎችን የህግ ረቂቅ ዝግጅት መሥራት፣ የመንግስት አካላት የሚያዘጋጁት ረቂቅ ህግ ከህገ መንግስቱና ከፌዴራል ህጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ለሚመለከታቸው ክፍሎችም አስተያየት ማቅረብ፣ በክልሎች ጥያቄ ሲቀርብለት የህግ ረቂቆችን በማዘጋጀት መርዳት
• የህግ ማሻሻያ ጥናቶችን እንዲሁም የኮዲፊኬሽንና የፌዴራል ህጎችን የማሰባሰብና ማጠቃለል ሥራ መሥራት፣ የክልል ህጎችን ማሰባሰብ እንደአስፈላጊነቱም እንዲጠቃለሉ ማድረግ
• ኢትዮጵያ የምትፈርመው ወይም የምትቀበለው ዓለም አቀፍ ስምምነት ህገ መንግስቱን እና የአገሪቱን ሌሎች ሕግጋት ያገናዘበና ከብሔራዊ ጥቅም አንፃር ተቀባይነት ያለው መሆኑን የማረጋገጥ ሀላፊነት እንዳለበት የአዋጁ አንቀፅ 6(5) ተደንግጓል፡፡
• በተጨማሪም በአዋጁ አንቀፅ 6(6) መሰረት ፍትህ ሚኒስቴር የፌዴራል መንግስቱ ህጎች ተግባራዊ መደረጋቸውን እና አተገባበራቸውም ወጥነት ያለው መሆኑን የማረጋገጥ እና የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ሥራቸውን በህግ መሰረት ማከናወናቸውን የማረጋገጥ ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡

  የህግ ጥናትና ስልጠናን በተመለከተ
በአዋጁ አንቀፅ 6(9) መሰረት ፍትህ ሚኒስቴር
• አሰራሩን ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ ጥናትና ምርምር የማድረግ
• የወንጀል ፍትህ መረጃዎችን ለማሰባሰብ፣ ለማደራጀት፣ ለመተንተን እና ለማሰራጨት የሚያስችል ሥርአት የመዘርጋትና የማስፈፀም
• ዐቃያነ ህግ ስለ ሥራቸው ያላቸውን አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት በተከታታይ እና በየደረጃው ለማሳደግ ስልጠና የመስጠት ወይም ስልጠና እና ትምህርት እንዲሰጣቸው የማድረግ ሀላፊነት ያለበት ከመሆኑም በተጨማሪ
• በአዋጁ አንቀፅ 6(7) መሰረት ለፌደራል መንግስት ባለስልጠናት፣ ሹመኞች፣ ተመራጮች፣ ሰራተኞች እና ለግሉ ዘርፍ ተሳታፊዎች እንደአስፈላጊነቱ የህግ ስልጠና የመስጠትና እንዲሰጥ የማድረግ ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡

  ሌሎች ሀላፊነቶች
ሌላው በአዋጁ አንቀፅ 6(11) መሰረት በፌደራል ፍርድ ቤት ደረጃ የጥብቅና አገልግሎት ለሚሰጡ ጠበቆች በህግ መሰረት ፈቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ማገድ፣ መሰረዝ፣ ጠበቆችንና የጥብቅና አገልግሎትን ማስተዳደርና መቆጣጠር እንዲሁም በአዋጁ አንቀፅ 6(12) መሰረት በሌሎች ህጎች ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠው ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ በወንጀልና በፍትሐብሔር ጉዳይ አለም አቀፍ ግንኙነቶችነና ትብብሮች ማድረግ በአዋጁ ለፍትህ ሚኒስቴር  የተሰጡት ተግባራት ናቸው፡፡

በተጨማሪም ከላይ ከተጠቀሱት ስልጣንና ተግባራት በተጨማሪ የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር በተለያየ ወቅቶች በወጡ ሌሎች ህጎች ለምሳሌ በንግድ ህግ፣ በተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ፣ በፌደራል ጥብቅና አገለግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ፣ በፌደራል አስተዳደር ሥነ ሥርአት አዋጅ እና መሰል ሌሎች ህጎች የተሰጡት ስልጣንና ኃላፊነቶች ያሉት መሆኑን ከህግጋቱ መረዳት ይቻላል፡፡

   ማጠቃለያ
ከላይ በዝርዝር እንደተገለፀው ፍትህ ሚኒስቴር በተለምዶ በብዙሀን ዘንድ ከሚታወቅበት የወንጀል ጉዳዮችን መከታተል በተጨማሪ የመንግስትን የፍትሐብሔር ጥቅሞች ከማስጠበቅ፣ ከሰብአዊ መብቶችን ከማክበርና ከማስከበር፣ ህጎችን ከማርቀቅ፣ የህጎችን በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲሰርፁ ከማድረግ እና ተፈጻሚነታቸውንም ከመከታተል አንቀፃር ዘርፈ ብዙ ሀላፊነቶች የተጣሉበት ተቋም ነው፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስለጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ 
ፍትህ ሚኒስቴር
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
Mikias Melak Birhanie
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
#Alternative_legal_enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና
https://t.me/AleHig
የሕግ እውቀት alehig.com
⭐️አለሕግ⭐️
🔠🔠🔠   🔠🔠🔠

አለሕግAleHig ️

27 Dec, 19:53


የፍትህ ሚኒስቴር ህጋዊነት የህግ ጆርናል የህትመት የፅሁፍ ጥሪ/ Ministry of Justice Higawinet Law Journal Call for Paper/
💬💬💬💬💬💬🎤🔝
ፍትህ ሚኒስቴር

አለሕግ🟠AleHig

06 Dec, 18:58


👆
ረቂቅ አዋጁ ፀደቀ

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

አለሕግ🟠AleHig

06 Dec, 17:52


👆
ረቂቅ አዋጁ ፀደቀ

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ዛሬ በምክር ቤት የፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የሪል ስቴት አልሚ ድርጅት ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ እንደማይችል አስቀምጧል።

በተጨማሪ በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር እንደማይችልም አስቀምጧል።

የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?

👉 የሪል ስቴት አልሚ የቦታና የተናጠል ይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን በተመለከተ ፦

1) በከተሞች ለሪል ስቴት ልማት የሚውል ቦታ በሚከተለው አግባብ የሚቀርብ ይሆናል፤

ሀ. በአዲስ አበባ ከ5 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፤
ለ. እንደከተሞች ተጨባጭ የቤት ፍላጎትና ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባለ ከተሞች ከ1 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፣
ሐ. ከነዚህ ባነሰ ስፋት ቤት ለሚፈልጉ ከተሞች ደግሞ 500 ቤት በላይ የሚገነባና የሚያስተላልፍ የሪል ስቴት አልሚ መሬት ቅድሚያ ተሰጥቶት በስፋት እንዲቀርብለት ይደረጋል።

2) የሪል ስቴት አልሚው የገነባውን ቤት በተናጠል ለቤት ፈላጊ በሽያጭ ለማስተላለፍ ግንባታው የተፈቀደለትን መስፈርት አሟልቶ 80 በመቶ ሲጠናቀቅ ለየቤቱ የተናጠል የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፤

👉 የሪል ስቴት አልሚ ግዴታዎች ምንድናቸው ?

የሪልስቴት አልሚ በውል ሰነዱ በህንጻ እዋጁ እና በሌሎች የህግ ማዕቀፎች የተመላከቱ ግዴታዎችን ማክበር እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪነት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል ፡-

1) ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡

2) በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር አይችልም፡፡

3) ቤቶቹን ለመገንባት የሚያስችለውን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከመረከቡ በፊት ደንበኞችን መመዝገብና ቅድመ ክፍያዎችን መሰብሰብ አይችልም፡፡

4) በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም።

5) የመኖሪያ ቤት ገዢ ደንበኞች ማኀበር እንዲያቋቋም ያበረታታል ፤ የህንጻ መግለጫ ያስረክባል።

6) ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ፣ የቤቱ የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት፣ አርክቴክቸራል፤ ሳኒተሪ ፣ ስትራክቸራል እና ኤሌክትሪካል ዲዛይን፤ የግንባታ ፍቃድና የሪል ስቴት ልማት ፍቃዱን ቅጂዎች ከውል ሰነዱ ጋር አያይዞ ለደንበኛው መስጠት አለበት።

7) ደንበኛው ለከፈለው ገንዘብ ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት አለበት።

👉 ዋስትና ስለመስጠት ፦

የአገር ውስጥ አልሚ ቤቱን ሳይገነባ ለቤት ፈላጊዎች በቅድሚያ በሚሽጥበት ወቅት የሚከተሉትን የዋስትና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡

1) የሪል ስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመስራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካለ አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት፡፡

2) ከቤት ገዥዎች የሚሰበስበውን ገንዘብ አግባብ ካለው አካለ ፈቃድ መሰረት በሚከፈተው የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ፣

3) የሪል ስቴት አልሚው በቅድሚያ መሽጥ የሚፈልገውን ቤት የመስሪያ ቦታ የይዞታ ማስረጃ ቤቱ ለተጠቃሚዎች ተገንብቶ እስከሚተላለፍ ድረስ በሚመለከተው አካል እንዳይሽጥ እንዳይለወጥ እንዲታገድ ማድረግ፤
📌 በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡
አዋጁ ከተች በ PDF ተቀምጧል።
#ቲክቫህ

አለሕግ🟠AleHig

05 Dec, 04:51


የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ጨምሮ ስምንት የመንግስት ልማት ድርጅቶች በኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር እንዲተዳደሩ ተወሰነ

ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ተጠሪ የነበሩ የልማት ድርጅቶች ከአሁን ጀምሮ በባለቤትነት የሚተዳደሩትና የሚመሩት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፣ ኢትዮ ፖስት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን እና ለኢትዯ ፋርማ ግሩፐ ተጠሪ የሆኑት ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ተቋምና ሺልድ ቫክስ በኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር እንዲሆኑ የተደረጉት መንግስታዊ ተቋማት ናቸዉ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር) እንደተናገሩት እነዚህ የልማት ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ኢንደስትሪላይዜሽን እና የዕድገት ምኞቶችን ለማሳካት ወሳኝ ናቸው ብለዋል፤ "እኛም ባለን ትኩረት፣ ሙያዊ አስተዳደር እና ንቁ ባለቤትነት እነዚህን ድርጅቶች ወደ አዲስ የስራ አፈጻጸም እና ፈጠራ እንደምናመጣ እርግጠኞች ነን" ሲሉም እርምጃውን አድንቀዉታል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 487/2022 የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን አሁን ላይ አዳዲሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ 25 በላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በባለቤትን እያስተዳደረ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
Source: capitalethiopia
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልገሎት
Alternative legal enlightenment and Service
https://linktr.ee/alehig
alehig.com

አለሕግ🟠AleHig

03 Dec, 15:14


http://alehig.com

አለሕግ🟠AleHig

03 Dec, 15:10


https://www.alehig.com/%e1%89%a0%e1%89%b4%e1%8a%ad%e1%8a%96%e1%88%8e%e1%8c%82-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8b%b0%e1%8c%88%e1%8d%88-online-registration-%e1%8a%a8%e1%88%95%e1%8c%8d-%e1%89%a2%e1%88%ae-%e1%8b%a8%e1%8c%bd%e1%88%91/

አለሕግ🟠AleHig

03 Dec, 10:56


https://www.alehig.com/understanding-the-legal-landscape-in-ethiopia-key-services-and-insights/

አለሕግ🟠AleHig

02 Dec, 04:36


No Fayda no service‼️
ከጥር 2017 አጋማሽ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የባንክ አገልግሎት ለማግኘት ግዴታ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያስፈልጋል‼️

-ከሰኔ ወር 2017 መጨረሻ ጀምሮ ደግሞ በሀገሪቱ ባሉ ሁሉም ትልልቅ ከተሞች ባሉ ባንኮች አካውንት ለመክፈት ፋይዳ ግዴታ ነው

-በመላው ሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ባንኮች ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፋይዳ መታወቂያን ግዴታ ያደርጋሉ

-በታሕሳስ 2019 ዓ.ም ነባር የባንክ ደንበኞችም ቢሆኑ ፋይዳ ካልያዙ አገልግሎት አያገኙም።
#ዋዜማ

አለሕግ🟠AleHig

01 Dec, 17:41


Subscribe AleHig Youtube channel 👇👇
https://youtube.com/@ale_hig?si=1Y_d-YnQu9ZaRu8D

አለሕግ🟠AleHig

28 Nov, 07:26


'ከረሜላ ልስጥሽ' በማለት አታሎ የ9 ዓመት ህጻን የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት እስራት ተቀጣ

በይርጋጨፌ ከተማ የ9 ዓመት ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

ግለሰቡ ድርጊቱን የፈጸመው በቀን 10/9/2016ዓ.ም በግምት ከጥዋቱ 4 ሰዓት በይ/ጨፌ ከተማ ካራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ነው።

የግል ተበዳይ 9 ዓመት ህጻን ተማሪ ስትሆን ሜክ አፕ ተጠርታ ተምራ እየመጣች ባለችበት ቅ/ኪዳነምህረት ት/ቤት ፊት ለፊት ባለው  የመጠጥ ማከፋፈያ ውስጥ ሆኖ እማ ነይ ከረሜላ ልስጥሽ በማለት ደስታ ከረሜላ የመሰለ ነገር እንደበላች እራሷን እንደሳተች የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

በመቀጠልም ወደ ውስጥ በማስገባት በፒላስቲክ ጅባ ላይ አስተኝቶ አሰገድዶ የደፈረ መሆኑንና ተከሳሽ ሆን ብሎ አስቦ በማድረጉ ተገልጿል።

ተከሳሹ፥ 1997 ዓ.ም በሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ዕግ አንቀፅ 627/1 የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀመው በሕፃናት ልጆች ላይ በሚፈፀም በግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

በዚህም ተከሳሹ 14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉን የይርጋጨፌ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

@TikvahethMagazine

አለሕግ🟠AleHig

26 Nov, 13:52


ውርስ በኢትዮጵያ ሕግ https://www.alehig.com/%e1%8b%8d%e1%88%ad%e1%88%b5-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%88%95%e1%8c%8d/

አለሕግ🟠AleHig

25 Nov, 19:50


Follow the አለሕግ/Alehig Legal Service channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va8we4WG3R3hJxkEqN1t

አለሕግ🟠AleHig

25 Nov, 13:43


ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተገልጋዮች ጥራቱን የጠበቀ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ (Online) Registration) ከሕግ ቢሮ የጽሑፍ አገልግሎት ያገኛሉ።
በየትኛውም ቦታና ስዓት ሁነው ሰነዶች ማረጋገጫ(ውልና ማስረጃ) የሚሄዱበት ጉዳይ ሲኖራችሁ ለተገልጋዮች ስለሚፈልጉት አገልግሎት እና ማሟላት ስላለባቸው ሰነዶች ነፃ የሕግ ምክር እና የሕግ ድጋፍ እንሰጣለን።
👉 #ውክልና_ለመስጠት
👉 #ብድር_ውል ለመፈፀም
👉 #የሺያጭ ውል
👉 #ቃለ_ጉባዔ ለማጽደቅ
👉 #ሼር መግዛት /መሸጥ........ወ.ዘ.ተ
ሌሎችንም አገልግሎት በአካል መገኘት ሳይጠበቅብዎት በአሉበት ቦታ ሁነው በተመጣጣኝ ክፍያ በሕግ ባለሙያ ተፅፎ በቴሌግራም፣ በዋትስአፕ ወይም በኢሜል ከሕግ ቢሮ ይላክላችኋል።
ከእናንተ የሚጠበቀው ፕሪንት አድርጎ ወደ አቅራቢያ ሰነዶች ማረጋገጫ በመሄድ ምንም ጊዜ ሳያባክኑ አገልግሎት ማግኘት ብቻ።
ይደውሉ:- 👉 0920666595
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልገሎት
Alternative legal enlightenment and Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

https://t.me/AleHig

alehig.com

አለሕግ🟠AleHig

24 Nov, 08:41


ከሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ | A Timely Statement Issued by Lawyers for Human Rights
#Ethiopia #LHR # Statement

ድርጅታችን "የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች" በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ዓ.ም. መሠረት በምዝገባ ቁጥር 4113 መስከረም 09 2012 ዓ.ም. ዳግም ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ ያለ ሀገር በቀል ሲቪል ማህበር ሲሆን:
ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከፖለቲካ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ በሀገራችን የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ዓላማው አድርጎ በርካታ ሥራዎችን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ከፌደራልና ክልል አስፈጻሚ አካላት እና ከሌሎች ሲቪል ማህበራት ጋር በመተባበር ሲያከናውን ቆይቷል።

ሆኖም ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ሕዳር 12/2017 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ድርጅቱ “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መስራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዳ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ..." በሚል ከማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ የታገደ መሆኑን ገልጾልናል።

ባለሥልጣኑ ማህበራችን ተሰማራበት በማለት በደብዳቤው ላይ የጠቀሰው አባባል ማህበራችንን የማይገልጽ እና የማይመለከት መሆኑን በአፅንኦት እየገለፅን የተጣለብን ዕግድ እንዲነሳ ለማድረግና ወደ መደበኛ ሥራችን ለመመለስ ሕጋዊ ሂደቶችን የምንከተል መሆኑን እናሳውቃለን።

Our organization, Lawyers for Human Rights, is a civil society entity duly re-registered under Proclamation No. 1113/2011 on September 20, 2019. Since its inception, we have maintained our independence and political neutrality, actively collaborating with the Ethiopian Human Rights Commission, federal and regional government bodies, and other civil society organizations to promote human rights in our country.

However, on November 21, 2024, the FDRE Authority for Civil Society Organizations issued a letter stating that our organization had been suspended from all activities for allegedly 'acting without political neutrality and beyond its purpose and engaging in actions harmful to the country’s interests and public welfare.’

We wish to clarify that the claims outlined in the letter do not accurately reflect our organization's activities. We are committed to following the legal process to challenge the suspension and resume our normal operations.

https://drive.google.com/file/d/1n28sWS4Lig2efcsXW7s6pH5k8Zn-NKYe/view?usp=sharing

አለሕግ🟠AleHig

22 Nov, 12:08


መንግሥት ካርድ የተሰኘዉን የሰብአዊ መብት ድርጅትን ጨምሮ ሌላ አንድ ተቋምን ከስራቸዉ አገደ‼️

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን ዋዜማ አረጋግጣለች። ከታገዱት ድርጅቶች መካከልም “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል” (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃሉ “CARD” እና “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” (AHRE) ይገኙበታል። 

ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል።  

ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል” የሚል ነው። ዋዜማ የደረሳት መረጃ የታገዱት ድርጅቶች ቁጥር ከሁለት እንደሚበልጥ ቢጠቁምም፣ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻልንም። 

ይህ እርምጃ መንግሥት በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በሚሠሩ ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ስለጉዳዩ በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። የእግድ እርምጃው በድርጅቶቹ መሪዎች አካባቢ የተጠበቀ እንዳልነበር ለመረዳት ችለናል።

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን መያዶችን የማገድ ስልጣን ቢኖረውም “የአሁኑ እርምጃ በሕጉ የተዘረዘረውን ቅደም ተከተልና ቅድመ ሁኔታ የሚጥስ ነው” ብለዋል ሌላ የሕግ ባለሞያ። ድርጅቶቹ እግዱን በሕግ የመቃወም መብት ይኖራቸዋል። ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ የዋዜማ ምንጮች እገዳው የተላለፈበት ሂደት ለእርሱም ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

አለሕግ🟠AleHig

22 Nov, 10:53


በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን
ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ DRAFT

አለሕግ🟠AleHig

21 Nov, 09:23


ወድቆ ካገኘችው የሞባይል ስልክ ላይ በሞባይል ባንኪንግ 85 ሺህ ብር የሠረቀችው ግለሰብ.......

ወድቆ ካገኘችው የእጅ ስልክ ላይ የሞባይል ባንኪንግ ምሥጢራዊ ቁጥር በመጠቀም ወደ እራሷ አካውንት ብር ያዘዋወረችው ግለሰብ በእሥራት ተቀጥታለች።

በምዕራብ አርሲ ዞን ተከሳሽ ዝናሽ ሃጎስ የተባለችው ግለሰብ ወድቆ ከተገኘ ስልክ ገንዘብ መሥረቋን የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ከድር ጅቦ ተናግረዋል።

ግለሰቧ የስልኩን ባለቤት የሞባይል ባንኪንግ የምሥጢር ቁጥር ከፍታ በፍተሻ ማግኘቷ የታወቀ ሲሆን የእጅ ስልካቸው የጠፋባቸው ግለሰብ ...የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጄ ቅርንጫፍ በመሄድ የባንክ አካውንታቸውን ሲያስፈትሹ 85 ሺህ ብር በሞባይል ባንኪንግ እንደተላለፈ አረጋግጠዋል።

ተከሳሿ ገንዘቡን ወደ ራሷ ከወሰደች በኋላ ለሌሎች ሁለት ሰዎች ማስተላለፏም ታውቋል።

በዚህም ገንዘቡ የተላለፈላቸው ሁለት ሰዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር እንዳልዋሉ ተነግሯል።

ተከሳሽ ዝናሽ ሃጎስ የተባለችው ግለሰብ የፈጸመችው ወንጀል ሙሉ በሙሉ በዓቃቤ ሕግ ማሥረጃ በመረጋገጡ ...የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ዝናሽ ሃጎስ በ4 ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር እንድትቀጣ ወስኖባታል።
(ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን)
እንደዚህ አይነት ክስተት ቢያጋጥሞ ምን ያደርጋሉ??
አማራጭ የሕግ እውቀት
https://linktr.ee/alehig
Alternative legal enlightenment/ALE
Telegram👉 @MikiasMelak
WhatsApp👉 #+251920666595

አለሕግ🟠AleHig

20 Nov, 14:12


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመንግሥት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡

በዚህም መሰረት የፌዴራል መንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 10/64/2010 ተሻሽሎ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡
አማራጭ የሕግ እውቀት
https://linktr.ee/alehig
Alternative legal enlightenment/ALE
Telegram👉 @MikiasMelak
WhatsApp👉 #+251920666595
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

https://t.me/AleHig

alehig.com

አለሕግ🟠AleHig

20 Nov, 13:36


ሙስና መኖሩን የሚያመላክቱ ዋና ዋና ማሳያዎች

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ. ህዳር 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስና በተለያዩ መንገዶች ሊገለፅ የሚችል፣ በባህሪው ተለዋዋጭና ውስብስብ ነው፡፡ ሆኖም ሙስና መኖሩን የሚያመላክቱ ዋና ዋና ማሳያዎች የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

1. የግልፀኝነት ጉድለት
👉 ግልፅ ያልሆነ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ሲኖሩ እና መረጃዎችን ለህዝብ ወይም ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ያለማድረግ ችግሮች ሲበራከቱ፣

2. የጥቅም ግጭት ሲፈጠር
👉 የግል ፍላጎት ከተቋም ፍላጎት ጋር የሚጋጭበት ሁኔታዎች ሲፈጠር፣

3. ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም
👉 ውሳኔ ሰጪ አካላት ከተቋማቸው ጥቅም አንጻር ውሳኔዎችን ከመወሰን ይልቅ ለግል ጥቅማቸውና ለሌሎች ግለሰቦችና ድርጅቶች በሚያመች መንገድ በመወሰን ስልጣናቸውን አለአግባብ ሲጠቀሙ፣

4. መመሪያዎችን ችላ ማለት
👉 ከመመሪያ ውጪ የሚሰሩ ስራዎች ሲበራከቱ፣

5. ከመጠን ያለፈ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ወይም ያልተለመደ ቅናሽ ሲያጋጥም
👉 ድንገተኛ የዋጋ ጭማሪ ወይም ከገበያ ዋጋ ጋር የማይጣጣሙ ግዥዎች መፈፀም፣

6. ሙስና ጠቋሚዎችን ችላ ማለት
👉 ሪፖርት የተደረጉ ስጋቶችን አለመፈተሽና ሙስና ጠቋሚዎችን ችላ ማለት፣

7. የተጠያቂነት ማነስ
👉 ደካማ የተጠያቂነት ስርዓት ሲኖርና ተመጣጣኝ የእርምት እርምጃ መውሰድ አለመቻል፣

8. የክትትል ማነስ
👉 ደካማ የውስጥና የውጪ ክትትልና ቁጥጥር ሲኖር ነው፡፡

በመሆኑም የሙስና ምልክቶችን ለይቶ በማወቅ ራሳችንን፣ የሥራ ክፍላችንን ብሎም ተቋማችንን በመጠበቅ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በማድረግ የሙስና መከላከል ሚናችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

አለሕግ🟠AleHig

20 Nov, 13:28


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ድምጽ ቅጂ ቅጽ 3- ክፍል 2
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

አለሕግ🟠AleHig

20 Nov, 09:42


#Ethiopia

ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ከነማሻሻያ አዋጁ ትላንትና ፀድቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ረቂቅ አዋጁንና ማሻሻያ ሪፖርቱን አስመልከተው የተለያዩ የድጋፍና የተቃውሞ ሐሳብና አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ 
የምክር ቤት አባልት ምን አሉ ?

- ማሻሻያው ከአሁን ቀደም ከሥራ ባህሪያቸው አንፃር ለየት ባለ የአደረጃጀትና የአሠራር መዋቅር ተደራጅተው የነበሩ የፍርድ ቤቶችን መሰል አዋጆችን መሻሩን የወቀሱ ነበሩ፡፡

- ማሻሻያ አዋጁ ልክ ለገቢዎችና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች እንደሰጠው ሁሉ፣ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባ እንደነበርም ተገልጿል።

- ሥራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በየትኞቹ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎች በእኩልነትና በፍትሐዊነት ሊወዳደሩ የሚችሉበት አስገዳጅ ሁኔታ በግልጽ በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ አለመቅረቡ ተነስቷል።

- የውስጥ ዝውውርን በተመለከተ አንድ የተቋም ኃላፊ ለውጤታማነት በሚል ሠራተኞችን ወደ የሚፈልግበት ቦታ አዛውሮ ማሠራት፣ ይህንን የማይቀበሉ ሠራተኞች ደግሞ መልቀቅ ይችላሉ መባሉም ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ የአሠራር ክፍተቶችን የሚፈጥር እንደሆነም ተመላክቷል።

የአብን የምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፦

" እንዲህ ዓይነት አዋጆች ሲዘጋጁ ሰፊ ዝግጅትና ውይይት ይፈልጋሉ። እንዲሁም የሠራተኞችን ሥጋት ማካተት ይገባል።

የረቂቅ አዋጁ መንደርደሪያ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ኢትዮጵያን የሚመስል የሠራተኞች ስብጥር እንዲኖር ነው በሚል መገለጹ ችግር አለበት።

' ሲቪል ሰርቪሱ በአንድ ብሔር የበላይነት ተይዟል ' በሚል የቀረበ ነው። ያን ለማለት ደግሞ በሚያስችል መንገድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

ሲቪል ሰርቪሱ ብቃትንና አቅምን መሠረት አድርጎ ሊገነባ ይገባል። ኮታን ወደ ማከፋፈል አይወስደንም ወይ ? ሥራን በኮታ ማደላደሉ ማቆሚያው የት ነው ?

አንድ ሠራተኛ አፈጻጸሙ ምንም ይሁን ምን ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እስከፈለገ ድረስ አንስቶ ሌላ ተቋም ላይ በተመሳሳይ ደረጃና ደመወዝ መመደብ ይችላል። ያን የማይፈልግ ከሆነ ሠራተኛው መልቀቅ ይችላል መባሉ የሠራተኞችን መብት የሚጋፋና ዕጣ ፋንታቸውን በአለቆቻቸው እንዲወሰን የሚያደርግ ነው።

እንዲሁም ከሥራ እንዲለቁ የሚገፋፋ ነው።

የሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ጉዳይ ከ39 ወደ 48 ሰዓታት እንዲያድግ መደረጉም አግባብነት የሌለው ነው " ብለዋል።


የኢዜማ አባል አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በረቂቅ አዋጁ ' ዘመናዊና ኢትዮጵያን የሚመስል ' መባሉ በዘወርዋራው የኮታ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።

' ዘመናዊ አገርና ዘመናዊ ቢሮክራሲ እንፈጥራለን ' እያልን የመንግሥት ሠራተኞችን ከችሎታና አቅም ይልቅ በብሔር ኮታ እንቅጠር ማለት እርስ በርሱ የሚቃረን ሐሳብ ነው።

ማይክሮሶፍትን መሰል ዓለም አቀፍ ተቋማት በአሜሪካውያን ሳይሆን በህንዳውያንና በቻይናውያን የሚመሩና የሚተዳደሩ ናቸው።

የመንግሥት ተቋማት የሃይማኖት የስብከት ቦታዎች እየሆኑ ነው። ይህ በጥብቅ ሕግ ጭምር ሊከለከል ይገባል።

አንድን ሠራተኛ መሥሪያ ቤቱ ወይም የበላይ ኃላፊው በፈለገው ቦታ መድቦ ማሠራት ይችላል የሚለው ሰው በሙያ (ፕሮፌሽን) እንዳያድግና የካበተ ልምድ እንዳይኖረው እንደሚያደርግ፣ ይህ ደግሞ በተቃራኒው ቢሮክራሲውን የበለጠ የሚጎዳ ነው።

የበላይ አመራሩ የመጨረሻ ወሳኝ መሆኑ ከሕግና ከሥርዓት የሚፃረርና ሰብዓዊ መብትንም የሚጋፋ ነው።

ይህ ከሆነ ባርነትን እንደገና በሕግ እያፀደቅን ነው ማለት ነው ? ውሳኔውን ፍርድ ቤት መስጠት አለበት " ብለዋል።


የምክር ቤት አባል አቶ ለማ ተሰማ ምን አሉ ?

" ረቂቅ አዋጁ ሠራተኞች በትምህርት መስክና ደረጃቸው እንዲሁም በልምዳቸው እንጂ፣ ከዚያ ውጪ የሚመደቡበትን አሠራር አይፈጥርም።

የሚነሱ ሥጋቶች ቀጥለው ሊወጡ በሚችሉ ደንቦች ሊመለሱ ይችላሉ።

በረቂቅ አዋጁ የተካተቱ አንዳንድ ጽንሰ ሐሳቦች በጥርጣሬ ሊታዩ አይገባም። ሲቪል ሰርቪሱ መለወጥ አለበት። ትናንት የነበረው አግላይ ነበር። ዕድልንም አይሰጥም ነበር።

ረቂቅ አዋጁ ሁሉንም ጠርጎ የሚያስወጣ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በብቃቱ ተወዳድሮ ሠራተኛ መሆን የሚችልበትን ዕድል የሚፈጥር ነው። "


ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የሰው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

🔴 ብዙዎቹ ጥያቄዎች በውይይት ወቅት ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው ነበር።

🔴 ፍርድ ቤቶች በልዩ ሁኔታ መታየት ነበረባቸው መባሉ በረቂቅ አዋጁ በሚቋቋመው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የሜሪትና የደመወዝ ቦርድ በኩል ራሱን ችሎ ምላሽ ሊያገኝ ይችላል።

🔴 በረቂቅ አዋጁ ውስጥ ኮታ የሚል ነገር የለም። ኮታ ተቀባይነት እንደሌለው በረቂቅ አዋጁ ውስጥ ተቀምጧል።

🔴 ረቂቅ አዋጁ የሥራ አመራር ኢንስቲቲዩትን እንደ አዲስ የብቃትና ሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት በሚል ስያሜ አቋቁሞ ሠራተኞችን በብቃታቸውን ለመመዘን ያስችላል።

🔴 ሠራተኞችን የማዘዋወሩ ኃላፊነት በማኔጅመንት እንጂ በበላይ ኃላፊዎች ብቻ አይወሰንም። የሠራተኛው ምክንያት የሚደመጥበትና መብቱ የሚጠበቅበት አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተካቷል።

ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት ይህ ረቂቅ አዋጅ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ሆኖ በ3 ተቃውሞ በአራት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡#ሪፖርተር

@tikvahethiopia

አለሕግ🟠AleHig

16 Nov, 11:31


#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

የመመሪያውን ሙሉ ክፍል ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡- https://t.me/AleHig/10068

አለሕግ🟠AleHig

11 Nov, 17:43


#AddisAbaba

የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን  ደንብ መውጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህ ቢሮ አሳውቋል።

ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ነው።

ደንቡ " በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ ነው " ብሏል።

ከደንቡ የአለባበስ ስርአት ውስጥ ለአብነት ፦

ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፤

የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤

ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል፡፡

ቢሮው " ደንብ ቁጥር 178/2017 በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም  በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ነው " ብሏል።

ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል ይደረጋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል ነው የተባለው።

መረጃው ከየአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia

አለሕግ🟠AleHig

11 Nov, 10:44


ኢትዮጵያ ለዲጂታል ማጭበርበር ከተጋለጡ ሃገራት መካከል መሆኗን ጥናት አሳይቷል።

Sumsub የተሰኘ መረጃ ጠቋሚ የ103 ሀገራትን ለዲጂታል ማጭበርበር ያላቸውን ተጋላጭነት የሚያሳይ የመጀመሪያውን አለም አቀፍ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ጥናቱ የዲጂታል ማጭበርበር ስጋትን የሚያሳይ በ103 አገሮች ላይ የተደረገ የመጀመሪያው ጥልቅ ጥናት ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ ሃገራት መካከል የተቀመጠች ሲሆን በሰንጠረዡ ላይም ከ 113 ሃገራት በ 99 ላይ ተቀምጣለች።

ከዲጂታል ማጭበርበር ደህንነታቸው የተጠበቁ 10 አገሮች መካከል ሲንጋፖር፣ ሉክሰምበርግ፣ ስዊዘርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን፣ አየርላንድ እና ሊቱዌኒያ ይጠቀሳሉ።

ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋላጭ የሆኑ ወይም ደህንነታቸው ውስን የሆኑ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ ፣ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ አርጀንቲና፣ ዩክሬን፣ ብራዚል፣ አልጄሪያ እና ሲሪላንካ ተጠቃሽ ናቸው ይላል ሪፖርቱ።

ጥናቱ ከቁጥሮች ይልቅ ለዲጂታል ማጭበርበር የሚያጋልጡ መንስኤዎችን በመለየት የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በማለም የተደረገ ነው።

እስካሁን ድረስ፣ ዲጂታል ማጭበርበር በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ስጋት ቢፈጥርም ስለ ማጭበርበር መጠን የሚያሳይ አጠቃላይ የሆነ ዓለም አቀፍ ትንታኔ አልነበረም።

ትንበያዎች እንደሚያሳዩት በአለም በኦንላይን የክፍያ ማጭበርበር ሳቢያ የሚደርሰው ኪሳራ ከ2023 እስከ 2028 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ362 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል ይላል።

የጥናቱ ዓላማ በዓለም ዙሪያ የኦንላይን ማጭበርበርን የሚያነሳሱትን ዋና ዋና ምክንያቶች እና ሁኔታዎች በጥልቀት በመመርመር ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ግንዛቤዎችን ለመስጠት፣ መንግስታት እና ተቆጣጣሪዎች ማጭበርበርን የሚገቱ የታለሙ እርምጃዎችን እንዲተገብሩ ለማስቻል ያለመ ነው ።

ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋልጠው ያቃሉ? እንዴት ?ያካፍሉን!

@tikvahethmagazine

አለሕግ🟠AleHig

11 Nov, 09:50


የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን  ደንብ ወጣ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ሲሆን
በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ ነው፡፡
ከደንቡ የአለባበስ ስርአት ውስጥ ለአብነት ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፤የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል፡፡
ደንብ ቁጥር 178/2017 በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም  በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡
ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል የሚደረግ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
 ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት
Alternative legal enlightenment/ALE
WhatsApp👉 #+251920666595
https://linktr.ee/alehig
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
https://t.me/AleHig
መሰረታዊ የሕግ እውቀት alehig.com

አለሕግ🟠AleHig

09 Nov, 19:17


አንድ ሰው በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ ሳይኖረው ቼክ ከፃፈ በወንጀል ሕግ ቁጥር 693 መሠረት በቼክ ማጭበርበር ወንጀል የሚቀጣ ሲሆን ድርጊቱ ሆን ተብሎ ወይም በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ የተፈጸመ ከሆነ ቅጣቱ ከአስር አመት የማይበልጥ እስራት ሲሆን ድርጊቱ በቸልተኝነት ከተፈጸመ ደግሞ ከአንድ አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት ነው፡፡
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት
Alternative legal enlightenment/ALE
WhatsApp👉 #+251920666595
https://linktr.ee/alehig
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
https://t.me/AleHig
መሰረታዊ የሕግ እውቀት alehig.com

አለሕግ🟠AleHig

09 Nov, 17:10


https://www.facebook.com/share/r/1B75wZEK3q/

አለሕግ🟠AleHig

09 Nov, 11:26


ተራዘመ‼️
ነዋሪ ያልገባባቸዉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዉላቸዉን ለማቋረጥ የወጣው ማስጠንቀቂያ ለ ተጨማሪ እንድ ወር መራዘሙ ተገለፀ‼️

በእጣ የተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል ።

በዚህም በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ የማይገቡበት ከሆነ ውል የሚቋረጥ መሆኑን የገለፀ ቢሆንም ዛሬ በሰጠዉ ማስጠንቀቂያ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ማራዘሙን ነዉ ያስታወቀው።
⬇️⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇⬇️⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇👇
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት
Alternative legal enlightenment/ALE https://t.me/AleHig
WhatsApp👉 #+251920666595
https://linktr.ee/alehig
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ መሰረታዊ የሕግ እውቀት alehig.com

አለሕግ🟠AleHig

09 Nov, 05:36


በአሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶች እና የጥፋቶቹ እርከን
ሐ/ ሶስተኛ ደረጃ የጥፋት ዝርዝር
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016

አለሕግ🟠AleHig

08 Nov, 17:36


ለስራ ፈላጊዎች
ክፍት የስራ መደብ ለህግ ተመራቂዎች
ሸር ላይክ በማድረግ ተባበሩ
https://t.me/Lawsocieties
@Lawsocieties
የሕግ ቤተሰብ

አለሕግ🟠AleHig

07 Nov, 18:59


ክፍት የስራ መደብ ለህግ ተመራቂዎች
ሸር ላይክ በማድረግ አድርሡ
https://t.me/Lawsocieties
@Lawsocieties
የሕግ ቤተሰብ

አለሕግ🟠AleHig

07 Nov, 17:44


ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያን በመወከል የመላው አፍሪካ አይኤችኤል ውድድር እየተሳተፈ የሚገኘው ቡድን ግማሽ ፍጻሜው አልፈዋል።

አለሕግ🟠AleHig

05 Nov, 12:08


ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት
Alternative legal enlightenment/ALE https://t.me/AleHig
WhatsApp👉 #+251920666595
https://linktr.ee/alehig
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ መሰረታዊ የሕግ እውቀት alehig.com

አለሕግ🟠AleHig

31 Oct, 03:17


በአዲስ አበባ ከተማ #ለአፓርትመንት_ቤቶች እና #ለጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።
በተሻሻለው  የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦
➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣
➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣
➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣
➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር  ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን #መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።

በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።
ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ያሳወቃል።
https://linktr.ee/alehig

አለሕግ🟠AleHig

30 Oct, 14:51


https://youtu.be/ojXnNlL4KnM?si=psMeUdEcOHeUDPiK

አለሕግ🟠AleHig

28 Oct, 09:56


የጥብቅና ፈቃድ እና የጠበቆች ሙያዊ ግዴታ

https://www.alehig.com/%e1%8b%a8%e1%8c%a5%e1%89%a5%e1%89%85%e1%8a%93-%e1%8d%88%e1%89%83%e1%8b%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8c%a0%e1%89%a0%e1%89%86%e1%89%bd-%e1%88%99%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%8c%8d%e1%8b%b4%e1%89%b3/

አለሕግ🟠AleHig

25 Oct, 19:29


የሕፃናት ወርሃዊ የቀለብ አወሳሰን የስሌት
የሕፃናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያ

አለሕግ🟠AleHig

24 Oct, 07:48


የፍቺ አፈፃፀምና ህጋዊ ውጤቶቹ በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ

https://www.alehig.com/%e1%8b%a8%e1%8d%8d%e1%89%ba-%e1%8a%a0%e1%8d%88%e1%8d%83%e1%8d%80%e1%88%9d%e1%8a%93-%e1%88%85%e1%8c%8b%e1%8b%8a-%e1%8b%8d%e1%8c%a4%e1%89%b6%e1%89%b9-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%88%bb%e1%88%bb%e1%88%88/

አለሕግ🟠AleHig

24 Oct, 04:26


AHRE is seeking a qualified trainer to deliver training on labor rights and basic human rights for employees in the Oromia region (Gelan Guda Sub City). Please find the details of the call in the PDF below.
https://t.me/AleHig

አለሕግ🟠AleHig

23 Oct, 19:36


ከሳሽ የሆነ ወገን ያቀረበው ክስ በፍ/ስ/ስ/ስ/ህ/ቁ-229&231 መሠረት ክሱ ውድቅ ከተደረገበት በደንቡ መሠረት ለዳኝነት የከፈለው የሚመለስለት ሆኖ(ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ-232(1)ለ እንዲሁም በራሱ ተነሳሽነት ክሱን ሲያቋረጥ ከላይ በተጠቀሰው መመሪያ አንቀፅ-11 መሠረት ገንዘቡ ይመለስለታል።
https://t.me/Lawsocieties

አለሕግ🟠AleHig

23 Oct, 14:00


Share የጥብቅና ፈቃድ መግቢያ ፈተና ከአለሕግ.pdf
https://t.me/AleHig

አለሕግ🟠AleHig

22 Oct, 19:57


ችሎት ከዕረፍት መልስ የሚጠብቅህ እንዲህ ከሆነ ምን መደረግ አለበት?

አለሕግ🟠AleHig

21 Oct, 18:13


ደመወዝ‼️

ከዚህ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ የደሞዝ ስኬል

የተሻሻለው የመንግስት ደሞዝ ጭማሪ ስኬል ይፋ ሆኗል።
የጥቅምት ወር የመግስት ሰራተኞች ደመወዝ በተጠቀሰው ስኬል መሰረት ይተገበራል።

አለሕግ🟠AleHig

19 Oct, 18:32


የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር 'በክልሉ እየተፈጸመ የሚገኘው የዳኞች እስር' እንዲቆም  ጠየቀ፤ 8 ዳኞች በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

በአማራ ክልል ውስጥ "ዳኞችን ያለአግባብ ማሰር እና ማዋከብ የተለመደ እና ካለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ ደግሞ ተባብሶ የቀጠለና ሞትንም እስከማስከተል የደረሰ ሆኗል" ሲል የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር አስታውቋል።

ማህበሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ ባለፈው አንድ አመት ብቻ በክልሉ ውስጥበሚገኙት ሁሉም ዞኖች ከ35 በላይ ዳኞች ያለአግባብ ታስረው የተፈቱ መሆኑን ማረጋገጡን ገልጿል። በአሁኑ ወቅትም 8 ዳኞች በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ዳኞቹ በዋናነት እየታሰሩ የሚገኙት ከስራቸው ጋር በተገናኘ ነው ያለው ማህበሩ በወንጀል የሚፈለጉ እንኳን ቢሆን በሕግ አግባብ ምርመራ አጣርቶ መያዝ ሲገባ ከሚያስችሉበት ችሎት ጭምር በአደባባይ በሚያገለግሉት ህዝብ ፊት እየተያዙ የሚታሰሩበት ሁኔታ እጅግ አደገኛና የተቋሙንም ነጻነት ጨርሶ እያጠፋ ይገኛል ሲል ከሷል።

አከሎም ይህ ሁኔታ ዳኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ እንቅፋት የሆነ እና ክብራቸውንም የሚነካ በመሆኑ ሁሉም ዳኛ ለሙያው ያለው ፍቅር እንዲቀንስና የስራ ሞራልን እየጎዳ ያለ ተግባር ነው ብሏል።

እስካሁን ባለው ሂደትም የማህበሩ አመራሮች በተለያየ እርከን ከሚገኙ የፍ/ቤት አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ችግሩ በንግግር እንዲፈታ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም ችግሩ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ተብሏል። በመሆኑም ማህበሩ የክልሉ መንግስት የሚመለከታችሁ አካላት በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ የሚገኙትን ዳኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንዲያደርግ ጠይቋል። በቀጣይም በዳኞች ላይ የሚፈጸም ያልተገባ እስር እንዲቆም እና ይህን ተግበር በሚፈፅሙ የፀጥታ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል::
@Ethiopialegalinfo

አለሕግ🟠AleHig

18 Oct, 18:16


Today, Bahir Dar University's moot court team, Yonas Muche, Roza Yimer, and Yeabsira Belete-coached by Mekashaw Chane-won the national round of the 2024 International Committee of the Red Cross (ICRC) Moot Court Competition in Addis Ababa. 

The team will now represent Ethiopia in the African regional rounds in Nairobi, Kenya, where they will compete against top students from across the continent.
https://t.me/Lawsocieties

አለሕግ🟠AleHig

17 Oct, 16:19


ሐሰተኛ የባንክ ቅርንጫፍ ቢሮ ከፍተው የሚያጭበረብሩት ሌቦች

አጭበርባሪዎቹ ለ10 ቀናት ህጋዊ ተቋም መስለው ቅርንጫፍ ከፍተው ሰዎችን ሲያታልሉ ነበር ተብሏል

ፖሊስ አጭበርባሪዎቹን እያደነ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን እስካሁን ተጠርጣሪዎቹ ስለመያዛቸው አልተገለጸም

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3NuYCni


Stay Connected with #AleHig!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://linktr.ee/alehig

Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

Website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice

አለሕግ🟠AleHig

16 Oct, 16:26


ስትወሰልት ያገኛት ሚስቱን ያጋለጠው ባል የስድስት ወራት እስር ተፈረደበት

ባልየው ሚስቱን እጅ ከፍንጅ ከያዘ በኋላ ከውሽማዋ ጋር በመደራደር ገንዘብ ተቀብሏል ተብሏል

በሚስቱ ክስ የተመሰረተበት ባልም የተላለፈበትን የስድስት ወራት እስር ይግባኝ ቢልም እስከ መጨረሻው ያለው ፍርድ ቤት ውኔውን አጽንቷል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/48h4mKT

አለሕግ🟠AleHig

16 Oct, 07:21


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 https://linktr.ee/alehig

አለሕግ🟠AleHig

15 Oct, 13:00


I am delighted to meet Her Excellency Mrs. #MeazaAshenafi, former President and Chief Justice of the Federal Supreme Court of Ethiopia, at the African Union. #MeazaAshenafi
#President, #FederalSupremeCourt #Ethiopia #SupportWomeninLaw
#SayYesToEqualPay #SayYesToEqualPromotion
#WomenInCharge
#ChampionWomenLeaders.
#womeninleadershipmatters
#herleadershipcounts
#HeforShe #EqualPay #EqualityCantWait #Inspireinclusion
#GenderEquality #WomenInLaw #IAWL9 #LegalEmpowerment #AU #GenderJustice #WomenLeadership #EqualityInLaw #ChampionWomenLeaders #HerLeadershipCounts
IAWL ~ Institute for African Women in Law

አለሕግ🟠AleHig

14 Oct, 14:08


#የፌዴራል #የማናቸውም #ፍርድ_ቤት #የጥብቅና #ፈቃድ መግቢያ #ፈተና መውሰድ የሚፈልግ ሰው ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ መመዝገብ የሚችል መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀፅ 6፣13፣16/2/ እና 21/3/ በተደነገገው መሰረት እንገልፃለን::
Stay Connected with AleHig!
https://linktr.ee/alehig
alehig.com
Follow us for real-time updates and empower yourself with knowledge to navigate the legal landscape in Ethiopia!
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE #የሕግአማካሪ
Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

official website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice

አለሕግ🟠AleHig

14 Oct, 11:31


ጠቃሚ የቴሌግራም ቻናሎች ናቸው::
      👇👇👇
👉የመረጡትን ይክፈቱ እና ይቀላቀሉ👈

አለሕግ🟠AleHig

14 Oct, 10:26


https://www.alehig.com/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%8a%95%e1%8b%b0%e1%89%85-%e1%8b%93%e1%88%8b%e1%88%9b-%e1%88%95%e1%8c%8d-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab/