® አላህ ለሁላችንም መጨረሻችንን ያሳምርልን ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺭﺯﻗﻨﻲ ﺣﺴﻦ ﺍﻟﺨﺎﺗﻤﺔ

@husnelkhatima


አላህ ለሁላችንም መጨረሻችንን ያሳምርልን ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺭﺯﻗﻨﻲ ﺣﺴﻦ ﺍﻟﺨﺎﺗﻤﺔ

ለበለጠ መረጃ ዪቲዪብ ቻናላችንን ሊንኩን ተጭነዉ ይቀላቀሉ
For more Subscribe our you tube channel
https://m.youtube.com/channel/UCZgEN0I_MtxY4zuqmMtsy-Q

® አላህ ለሁላችንም መጨረሻችንን ያሳምርልን ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺭﺯﻗﻨﻲ ﺣﺴﻦ ﺍﻟﺨﺎﺗﻤﺔ

12 Jun, 19:30


ይህ ወጣት እናቱ አፉ እስካላለችው ድረስ ጀነት ይቅርና የቀብር ሠላም አያገኝም አሉ፡፡
😭ገራሚ ታሪክ

አንዴ አንድ ሠው ወደ ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም)ዘንድ ይሔድና መሥጅዳቸው አጠገብ ይቆማል፡ነብዩም (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሠግደው ሢወጡ አዩት ከዛ አንተ ወጣት ምነው? ለምን ቆምክ ?ብለው ጠየቁት፡፡

እሱም የአላህ መልክተኛ የአላህ ሠላም ባንተ ላይ ይሁን አላቸው እሳቸውም ባንተም አሉት፡፡ከዛ ይህ ወጣት የቆመበትን ችግር ይነግራቸው ጀመር፡፡አላቸው እናቴ በጣም ትወደኝ ነበር በጣም ከመውደዷ የተነሣ የማገባት ሤት እሷ መረጠችልኝ ፤ሚሥት ባገባሁ በሁለተኛ አመት ከባለቤቴ አልተሥማሙም ይጣላሉ እኔ እናቴን እቆጣት ጀመር የመጀመሪያ ልጄና ሚሥቴ ይዜ ከእናቴ ራቅ ወዳለ ስፍራ ሔድኩ በእናቴ ተናደድኩ ላያት አሥጠላችኝ እሧ ላላይ ወሠንኩ ከተወሰነ ጊዜ በሗላ ልጄ ሞተ ባለቤቴ እናትህ ነች ልጄ የገደለችብኝ ትለኛለች እኔም እውነት ሖኖ ታየኝ እናቴ የባሠ ጠላሗት😭በመንገዴ እንዳላያት ነገርኳት አሥፈራራሗት ከጊዜ በሗላ ነገር ግን እናቴ በድንገት በጣም ታመመች ልጠይቃት ብመጣ እንዳላያት ተከለከልኩ እናቴ ጣረሞት ይዟት እንኳ ልጄ ትላለች እኔ ግን .

የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም)አለቀሱ 😢 እያለቀሱም ይሰሙታል ሚስቴ ጥላኝ ሔደች አላቸው፡፡ እሱም ያለቅስ ጀመር በል ዝምበል አሉት መላክተኛው ንግግሩ አቋርጠው

አሁን እናት አለች ወይስ ሞተቸ? አሉት እሱም ሞተች አላቸው ወየውልህ አሉት ላንተ የተቀጣጠለች እሳት አንዷ ፍም የዱንያ ውሐ ሑሉ አያጠፋውም አሉት እሱም ከዚህ ቅጣት መዳኛ መንገት ጠየቃቸው! እሳቸውም እናትህ ቀስቅሳትና አፉ ትበልህ አሉት
ያ አላህ ውድ ወንድሞችና እህቶቼ ሠው ከሞተ በሗላ ማነው ሚቀሰቅሰው? ???

ታድያ እናታች ሣትለየን ካሁኑኑ ለምን አፉታ አንጠይቃትም &?ለምን አናሥደሥታትም
የሥንቶቻችን እናት በኛ ታዝናለች ራሣች እንጠይቅ
አላህ ሕደያው ይስጠን፡፡

ይህ ወጣት እናቱ አፉ እስካላለችው ድረስ ጀነት ይቅርና የቀብር ሠላም አያገኝም አሉ፡፡

❤️እናታች አላህ እረጅም እድሜ ይስጣት
እኛም የናታችን ፍቅር ይስጠን

የሞቱትንም አላህ ይማራቸዉ 🤲

® አላህ ለሁላችንም መጨረሻችንን ያሳምርልን ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺭﺯﻗﻨﻲ ﺣﺴﻦ ﺍﻟﺨﺎﺗﻤﺔ

09 Apr, 15:51


የኢድ ሰላት አሰጋገድ #share
°
የኢድ ሶላት አሰጋገድ የማያውቁ ስላሉ እርሶ ፅሁፉን ሼር በማድረግ
ያድርሱ!!
የኢድ ሰላት “ሱና ሙአከደህ’ ከሆኑ ሰላቶች አንዱ ነው
ማለትም ነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያጠብቁት
የነበረ ሱና ነው።
የአሰጋገድ ስነስርኣት
1. ሰጋጁ በልቡ እንዲህ በማለት ኒያ ያደርጋል፡ ለአሏህ ብዬ የኢድ አል-
ፊጥር 2 ረከኣ ሱና ሰላትን ኢማም ሆኜ
(ኢማም ለሆነ) መእሙም ሆኜ (ተካታይ ሆኖ ለሚሰግድ) በማለት ሰላቱን
ያስራል።
2. የኢሕራም ተክቢራ (አሏሁ አክበር)ን ይላል።
3. ከዚያም ሰባት ተክቢራዎችን ያደርጋል በያንዳንዱ
ተክቢራ መካከል
ﺳﺒﺤﺎﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﻭﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ
“ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊሏህ ወላ ኢላሀ ኢልለሏህ ወሏሁ አክበር”
ይላል።
4. ከዚያም ፋቲሓን ይቀራል
5. ከዚያም ሱረቱ “ቃፍ” ወይም ሱረቱል አዕላን ያነባል።
6. ከዚያም ለሩኩዕ ይወርዳል።
7. ከዚያም ቀጥ ብሎ መቆም (ኢዕቲዳል)
8. ከዚያም ሁለት ሱጁድ ያደርጋል
9. ከዚያም ለ ሁለተኛ ረከዐ ይቆማል
10. ከዚያም አምስት ተክቢራ ያደርጋል በያንዳንዱ
ተክቢራ መካከል
ﺳﺒﺤﺎﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﻭﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ
“ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊሏህ ወላ ኢላሀ ኢልለሏህ ወሏሁ አክበር”
ይላል።
11. ከዚያም ፋቲሓን ይቀራል
12. ከዚያም ‘ሱረቱል ጋሺያ’ ወይም ‘ሱረቱል-ቀመር’ን
13. ከዚያም ለሩኩዕ ይወርዳል
14. ከዚያም ቀጥ ብሎ መቆም (ኢዕቲዳል)
15. ከዚያም ሁለት ሱጁድ ያደርጋል
16. ከዚያም ተሹድ ያደርጋል
17. ከዚያም በነቢዩ ሙሐመድ ሰለዋትን ያወርዳል
18. ከዚያም ያሰላምታል
((አደራ ሼር ማድረግ አንዘንጋ!!!))

® አላህ ለሁላችንም መጨረሻችንን ያሳምርልን ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺭﺯﻗﻨﻲ ﺣﺴﻦ ﺍﻟﺨﺎﺗﻤﺔ

06 Apr, 17:56


የዘካ ድንጋጌ

® አላህ ለሁላችንም መጨረሻችንን ያሳምርልን ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺭﺯﻗﻨﻲ ﺣﺴﻦ ﺍﻟﺨﺎﺗﻤﺔ

06 Jan, 23:43


(ሙስሊም ዘግበውታል)
_____
➊➑. ባል ሆይ ! ሚስትህ ለሚያስፈልጋት ነገር ወጭ የማውጣት ግዴታ አለብህ !
ልትሰስትባት አይገባም ! ሚስት ሆይ ! ባልሽ ላንቺም ሆነ ለልጆችሽ የሚያፈልጋችሁን
ወጫችሁን የማይሰጣችሁ ከሆነ ስስታም ከሆነ - አግባብ ባለው መልኩ ለሚያስፈልጋችሁ
ወጭ እሱ ሳያውቅ ከገንዘቡ ወስደሽ መጠቀም ትችያለሽ ፡
እናታችን አዒሻ እንዲህ አሉ
የአቡ ሱፍያን ሚስት "ሒንድ ቢንት ዑትባህ" ወደ ነብያችን ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች ፡
አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! አቡ ሱፍያን ስስታም ሰው ነው ለእኔና ለልጆቼ የሚበቃንን
ወጭ አይሰጠንም እናም እሱ ሳያውቅብኝ ለኔና ለልጆቼ የሚያስፈልገንን ወጭ ከገንዘቡ
እወስዳለሁ ፡ ይሄን በማድረጌ ወንጀል ይኖርብኝ ይሆን ?
ከዚያም የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለው መለሱላት "ለአንቺም ለልጆችሽም የሚበቃ
የሆነ፣ አግባብ ባለው መልኩ የሚያስፈልግሽን ገንዘብ ከርሱ ውሰጅ "።""
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
______
➊➒. ባል ሆይ ! የሚስትህን ስሜትና ፍላጓት ልትረዳላት ይገባል ከዚያም የምትፈልገውን
አድርግላት አሟላላት ፡
የአላህ መልዕክተኛ ለእናታችን አዒሻ እንዲህ አሏት:-
""አዒሻ ሆይ ! አንቺ በእኔ ደስተኛ ስትሆኒና እንዲሁም ስትቀየሚ አውቅብሻለው።""
(ሙስሊም ዘግበውታል)
______
➋0. ባል ሆይ ! ሚስትህ ሲከፋት አፅናናት፡፡ በቻልከው አቅም ተንከባከባት፡፡ ሚስትህ ማለት የነብዩ አደራ ናት፡፡
የአላህ መልዕክተኛ ሴቶችን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል "አደራ የሴቶችን ነገር" ።
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

አደራ ይሄን ፅሁፍ ለሌሎችም ሸር (Share) አድርጉት

® አላህ ለሁላችንም መጨረሻችንን ያሳምርልን ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺭﺯﻗﻨﻲ ﺣﺴﻦ ﺍﻟﺨﺎﺗﻤﺔ

06 Jan, 23:43


ባል ለሚስቱ ማድረግ ያለበት 20 ነገሮች ከነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት)፡-
አንብባቺሁ ስጨርሱ ለሌሎችም #ሸር አድርጉት
________
➊. ባል ሆይ ! ከአላህ ዘንድ በላጭ ሰው ሁነህ መገኘት ካሰኘህ "ለሚስትህ መልካም ሰው ሁንላት" ።
የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ
"ከእናንተ መሀል በላጭ ሰው ብሎ ማለት ለሚስቱ መልካም የሆነ ሰው ነው ።""
(ቲርሚዚ ዘግባውታል)
_____
➋. ባል ሆይ ! ምግብ ስትበላ ከሚስትህ ጋር አብረሀት ብላ "እየበላችሁ ሳላችሁም በእጅህ
አጉርሳት" ይህ ፍቅራችሁንም ይጨምራል ይሄን በማድረግህም ከአላህ ዘንድ ከፍ ከፍ ያለን
ምንዳ ያስገኝሀል ፡
የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ
""አንተ ስጦታን አትሰጥም አላህ በዚያች በሰጠሀት ስጦታ ምንዳን የከፈለህ ቢሆን እንጂ ፡
ሚስትህን ለማጉረስ ወደ አፏ በምታነሳት ጉርሻ ሳይቀር አላህ ምንዳህን ይከፍልሃል ።"
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
______
➌. ባል ሆይ ! ሚስትህ ውሀ በጠጣችበት ቦታ ላይ በመጠጣት ለርሱዋ ያለህን ፍቅር
ግለፅላት ፡ በተለይ በሀይድ ጊዜ ላይ ስትሆን የምትፀየፋት እንዳይመስላት ከሌላው ጊዜ
በተለየ መልኩ ለርሱዋ ያለህን ፍቅርህን በተለያዩ ነገሮች ግለፅላት ፡
ታላቋ እናታችን አዒሻ እንዲህ አሉ
""ሀይድ ላይ ሳለሁ ውሀ እጠጣና የተረፈኝን ለነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እሰጣቸዋለሁ ፡
ከዚያም አፋቸውን "እኔ በአፊ በጠጣሁበት ቦታ ላይ አድርገው ይጠጡ ነበር" ።"
(ሙስሊም ዘግበውታል)
_____
➍. ባል ሆይ ! ቤት ውስጥ ቁርአን በምትቀራ ጊዜ ሚስህን አቅፈሀት ምናምን ቅራ ልክ እንደነብይህ ፡
እናታችን አዒሻ እንዲህ አሉ
"ሀይድ ላይ እያለሁ የአላህ መልዕክተኛ ታፋዬ ላይ ተደግፈው ቁርአን ይቀሩ ነበር ።"
(ቡኻሪና ሙስሊም)
______
➎. ባል ሆይ ! ለሚስህ ፍቅርህን ግለፅላት ፡ አብረሀትም ሆንክ አልሆንክም። ከሌሎች ጋ
በምትሆን ጊዜ አደራህን ጥሩነቷን ደግነቷን ብቻ አውራ
የአላህ መልዕክተኛ ስለ ሚስታቸው "ኸዲጃ" እንዲህ አሉ፦
""እኔ የኸዲጃን ፍቅር ተለግሻለሁ ።""
(ሙስሊም ዘግበውታል)
_____
➏. ባል ሆይ ! ሚስት ቤት ውስጥ በምትሰራቸው ስራወች ልታግዛት ይገባል ሁሉን ነገር
የግድ እሷ እስክትሰራልህ መጠበቅ የለብህም ራስህን ኻድም አንዳንዴ !
እናታችን አዒሻ እንዲህ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ የአላህ መልዕክተኛ ቤት ውስጥ
በሚሆኑ ጊዜ ምን ምን ይሰሩ ነበር ?
እናታችን አዒሻ እንዲህ ብለው መለሱ ፡- ""የአላህ መልዕክተኛ ቤት ውስጥ ልክ እንደሌላው
ሰው ነበሩ የተቀደደ ልብሳቸውን ራሳቸው ይሰፋሉ፣ ፍየሎችን ለቤሰሰብ ወተት ያልባሉ፣
እንዲሁም ራሳቸውን በራሳቸው ይኻድማሉ ያገለግላሉ።""
(አህመድ ዘግበውታል)
____
➐. ባል ሆይ ! ሚስትህን አቆላምጠህ ጥራት ፡ እንዲሁም ኩንያ ካላት በኩንያዋ ጥራት ፡
የአላህ መልዕክተኛ እናታችን አዒሻን "አዒሽ" ብለው ይጠሯት ነበር ።
(ቡኻሪና ሙስሊም)
ሌላ ቦታ ላይ እናታችን አዒሻ እንዲህ አሉ
አንድ ቀን ረሱልን እንዲህ አልኳቸው "አንቱ የአላህን መልዕክተኛ ሆይ ! ሁሉም ሚስቶችህ
የየራሳቸው የሆነ ኩንያ አላቸው እኔ ስቀር" ከዚያም (ኡሙ አብደላህ) አሉኝ።
(አህመድ ዘግበውታል)
____
➑. ባል ሆይ ! ሚስትህ ሰው ነችና አንዳንድ ጉድለቶች ይኖሯታል ታዲያ አንተም የሆነ ጎደሎ
ጎን ካየህባት ሌላኛውን መልካም ጎኗን ተመልከትላት ፡
የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ
""አማኝ ባል አማኝ ሚስቱን እንዳይጠላት ፡ የሆነ ባህሪዋን ቢጠላባትንኳን ሌላኛውን
መልካም ባህሪዋን ይውደድላት ።"
(ሙስሊም ዘግበውታል)
_____
➓. ባል ሆይ ! ሚስትህ ሲከፋት እቅፍ አድርገህ አፅናናት ካለቀሰችም እያባበልክ በእጆችህ
እንባዋን አብስላት ፡ ለቅሶዋን እስክታቋርጥ ድረስ አረጋጋት ፡
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ አሉ
"አንድ ቀን የአላህ መልዕክተኛ ሚስት "ሶፊያ" አለቀሰች ፡ ከዚያም የአላህ መልዕክተኛ
በእጃቸው የሶፊያን እምባ አበሱላት ከዚያም ቡሀላ አባበሏትና ማልቀሷን አስተዋት ።""
(ነሳዒ ዘግበውታል)
___
➊➊. ባል ሆይ ! ሚስትህ የሰራችውን ምግብ ልታጥላላባት አይገባም ! ከተመቸህ ብላ
ካልተመቸህ ተወው !!
አቡ ሁረይራ እንዲህ አሉ
"የአላህ መልዕክተኛ አንድም ቀን ምግብን አጥላልተው አያውቁም "ከወደዱቴ ይበሉታል
ካልወደዱት ደግሞ ይተውታል።"
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
______
➊➋. ባል ሆይ ! የሚስትህን ቤተሰብና ጓደኞቿን ልታከብርላት ይገባል !
እናታችን አዒሻ እንዲህ አሉ
የአላህ መልዕክተኛ ፍየል ካረዱ "ከስጋው ለኸዲጃ ጓደኞች ይሰጧቸው ነበር" ።
(ቲርሚዚ ዘግበውታል)
____
➊➌. ባል ሆይ ! ለተወሰነ ጊዜ ራቅ ወዳለ ቦታ ጉዞ ማድረግ ስትፈልግ ሚስትህንም አብረህ
ይዘሀት ሂድ ካንተ ጋ ፈታ ብትን ትበል ፡
የአላህ መልዕክተኛ ወደሆነ ቦታ ሰፈር (ጉዞ) ማድረግ በሚፈልጉ ጊዜ ፡ በሚስቶቻቸው
መሀል እጣ ይጥላሉ ከዚያም እጣ የወጣላትን ከርሳቸው ጋር አብረው ይዘዋት ይሄዳሉ።
(ቡኻሪና ሙስሊም)
______
➊➍. ባል ሆይ ! ከቤትህ ከመውጣትህ በፊት ቅድሚያ ሚስትህን ግጥም አድርገህ ሳማት ፡
እናታችን አዒሻ እንዲህ አሉ
""የአላህ መልዕክተኛ ሚስቶቻቸውን ስመው ከዚያም ሶላቴ ለመስገድ ይሄዱ ነበር ።""
(አቡ ዳውድ ዘግበውታል)
እንዲሁም በሌላ ሀዲስ ላይ እናታችን አዒሻ እንዲህ አሉ
""አንድ ቀን የአላህ መልዕክተኛ ሊስሙኝ ፈለጉና ፆመኛ ነኝ አልኳቸው ፡ ከዚያ "እኔም ፆመኛ
ነኝ አሉና ሳም አደረጉኝ" ።""
(ነሳዒ ዘግበውታል)
___
➊➎. ባል ሆይ ! አደራ የሚስትህን ሚስጥር ጠብቅላት ፡ አንቺም እንደዛው !
የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ
""የትንሳኤዋ እለት አላህ ዘንድ ከሰው ሁሉ መጥፎ ሰው ብሎ ማለት የሚስቱን ሚስጥር ለሌሎች የሚበትን ሰው ነው ።""
(ሙስሊም ዘግበውታል)
_____
➊➏. ባል ሆይ ! ይሄን ሀዲስ ልብ ብለህ ተመልከተውና ለሚስትህ ተግባራዊ አድርግላት ፡
አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ዘንድ መጣና "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ
ሆይ ! ሚስት በባል ላይ ያላት ሀቅ ምንድነው ? ብሎ ጠየቃቸው ፡ ከዚያም ረሱል እንዲህ
ብለው መለሱለት - "አንተ በምትበላ ጊዜ ልታበላት፣ በምትለብስ ጊዜ ልታለብሳት፣ ፊቱዋን
ላትመታት፣ እርሱዋንም ሆነ የምትሰራውን ስራዋን ላታጣጥልባት፣ ካኮረፍክም ቤት ውስጥ
እንጂ ውጭ ላይ ላታኮርፋት።"" አሉት፡፡
(አህመድ ዘግበውታል)
____
➊➐. ባል ሆይ ! ሚስትህን የመመገብና የማልበስ እንዲሁም አስፈላጊ ለሆኑ ወጮች
የማውጣት ሀቅ (ግዴታ) አለብህ ፡
የአላህ መልዕክተኛ ሀጀተል ወዳዕ/የመሰናበቻ ሀጃቸው ላይ እንዲህ ብለዋል ፡
""አደራችሁን በሴቶች ላይ አላህን ፍሩት ! ወጫቸውና ልብሳቸውም በእናንተ ላይ ያለ ሀቅ ነው:: አግባብ ባለው መልኩ ።""