በአሜሪካ የሚገኙ ስደተኞች ዶናልድ ትራምፕ እየወሰዱ ያለውን ርምጃ በመፍራት ከቤት መውጣት አለመቻላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል:: የትራምፕ አስተዳደር ወደስልጣን በመጣ ማግስት ከወሰዳቸው ርምጃዎች አንዱ የሕገ ወጥ ስደተኞች ጉዳይ ሲሆን፤ በዚህ ውሳኔም በርካቶች ወደሀገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ::
የአይስ አባላት ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከትምህርት ቤት፣ ከሥራ ቦታ፣ ከእምነት ተቋማት፣ ከሆስፒታል እና ከመሰል ሊሸሸጉበት ይችላሉ ብሎ ካመነበት ስፍራ እያሳደደ ይገኛል:: በዚህ ስጋት የተነሳ ሥራ መሄድ እንዳቆሙና እና ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ እንዳልቻሉ ቃላቸውን ለቢቢሲ ከሰጡት ስደተኞች ማወቅ ተችሏል::