ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ @sufiyahlesuna Channel on Telegram

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

@sufiyahlesuna


╔════◈◉◈════╗
                     أهل السنة والجماعة
            ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⚪️አህለሱና ወልጀመዓህ ስንል የሰለፎችንና የኸለፎችን የግንዛቤ ዘይቤ የሚከተሉ ማለት ነው።

🔴ይህ መንገድ ሌሎች የኢስላም አስተሳሰብ ተከታዮችን አያከፍርም

🔎አመላካች የሰሪን ምንዳ ያገኛልና ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩልን

╚════◈◉◈════╝

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ (Amharic)

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ የተወሰነ የማህፀን ቁምነገር እና መፅሔፍ ለሌሎች ቅናት ይዘቁት። አህለሱና ወልጀመዐህ በእርስዎ በከፍተኛ ሲያልፍ ሰለፊ ቀልዶችንና ኸለፍችን በመንፈስ አዘጋኝቻለሁ። ይህ መንገድ ወልጀመዐህ የኢስላም አስተሳሰብ ተከታዮችን ለመመለስ የቀረበ ማለት ነው። አመላካች የሰሪን ምንዳ በላይ የሆነውም ያገኛልና በስልኩ ሼር በማድረግ እንዲቆይ በዚህ መንገድ የድህረ ሴትን ሼር ለመጠቀም ያግኙ።

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

03 Dec, 18:16


لا تصدق كل ما تسمع
‏فهناك ثلاثة تفسيرات لكل قصة :
‏تفسيرك ، وتفسير غيرك ، ‏والحقيقة.

የሰማኸውን ሁሉ አትመን
ለእያንዳንዱ ታሪክ ሦስት ማብራሪያዎች አሉ ፡-
የአንተ ትርጓሜ፣ የሌላ ሰው ትርጓሜ እና እውነታ ናቸው።😌





https://t.me/sufiyahlesuna

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

03 Dec, 12:10


ቴክኖሎጂና ወሀቢያ
—————————-
/ አእምሯቸው ውስጥ የተሳለው ሙስሊሞች በባእድ አምልኮ የመፈረጅ ማሳያ /


የገመድ አልባ ማሽኑ ሪያድ ውስጥ ተገጥሞ ጥቅም ላይ ሲውል ሰዎች ይህንን ጣቢያ ማቋቋም የክፉ እና የጥሩ ድንበር ነው ብለው እርስ በርሳቸው ወሬ ያሰራጩ ነበር ። የእስልምና ሊቃውንቱ ያ ሰይጣኖችንና ለርሱ መስዋእትነት የሚቀርቡ እርዶች ይመለከቱ ዘንድ የሚያምኗቸውን ሰዎች ይልኩ ነበር ፤ ነገር ግን ምንም አላገኙም።

የጣቢያው ሰራተኛ እንደነገረኝ አንዳንድ ወጣት ሸይኾች በየጊዜው ይጎበኟቸውና ስለ ሰይጣኖች የጉብኝት ጊዜ ይጠይቁት ነበር። ታላቁ ሰይጣን መካ ነው ወይስ ሪያድ? ዜናውን ለመዘገብ የሚረዳው ስንት ልጆች አሉት? ብለው ይጠይቁት ነበር

ሰይጣኖች ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው ሲነግራቸው እውነታውን እንዲነግራቸው አንዳንዶቹ በገንዘብ ጭምር ሊያታልሉት ይሞክሩ እንደነበር ይናገራል ። ሰራተኛው ግን ዜናውን ተቀብሎ ከፊት ለፊታቸው እየላከ ጉዳዩ የኢንደስትሪ ብቻ እንደሆነ ይነግራቸው ነበር።

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

03 Dec, 07:38


አንድ ትልቅ ሀንበሊይ ዐሊም ራሳቸውን እንዲህ በማለት ይገልፃሉ :-

አሽዐሪይ ፤ ሀንበሊይ ፤ ዛሂሪይ —— ራፊዲይ ( ሺአ )
أشعري حنبلي ظاهري ......... رافضي ، هذه إحدى العبر

የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ኮክቴል ይልሀል ይህ ነው

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

02 Dec, 18:32


ይህን የሚያዩ ፈረንጆች ሙስሊሞችን እንዴት ሊስሉ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም : መጀመሪያ ቪዳዮውን ስመለከተው ሲቀልድ ነበር የመሰለኝ ግን የምር መድኸሊ ውስጣዝ ነው

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

02 Dec, 14:44


የዘመናችን ተጨባጭ ሁኔታ

https://t.me/sufiyahlesuna

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

02 Dec, 10:43


♦️አንድ ወቅት በወኪዕ ቢን አልጀራህ መጅሊስ ላይ አንድ ሰው ተነሳና አቡ ሀኒፋ ተሳስተዋል አለ

ወኪዕም፦ ‹አቡሀኒፋ እኮ ከርሳቸው ጋር፦
🌹በቂያስ(በተዛምዶ) ክሎታቸው የተካኑት እንደ አቢ ዩሱፍ እና ዘፈር እያሉ፣
🌹ሐዲስን በመሸምደድ እንደ የህያ ቢን አቢ ዛኢዳህ ፣ ሐፍስ ቢን ጚያስ ፣ ሂባን ፣ ሚንድል እያሉ ፣
🌹በአረበኛ ቋንቋ ጥልቅ እውቀታቸው እንደቃሲም ቢን መዒን እያሉ
🌹በምነናቸውና በጥንቁቅነታቸው የሚታወቁት- ዳውድ አል-ጧኢይ እና ፉደይል ቢን ዒያድ☆ እያሉ እንዴት ሊሳሳቱ ይቻለቸዋል?

እነዚህ አቀማማጮቹ የሆኑለት ሰው ሊሳሳት አይቻለውም፥ ምክንያቱም ቢሳሳቱ እንኳ ወደሀቁ ይመልሷቸዋልና።አሉት👐

تاريخ بغداد 365/16

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

02 Dec, 08:23


እኔ ለራሴ ትክክል ነኝ
- ~ - ~ - ~ - ~ -

እኔ ለራሴ ትክክል ነኝ የሚለው አባባል አውቀንም ይሁን ስናውቅ የምንገለገልበት አባባል ነው።

ብዙ ጊዜ አባባሎች የሆነን የሂወት ክፍል ለማበልፀግ ወይም ለመናድ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ናቸው እንደውም ብዙ አባባሎች የአንድ ማህበረሰብን ስልጣኔን ፍልስፍናን የሚያሳዩ መገለጫዎች ናቸው።

እኔ ለራሴ ትክክል ነኝ ወደሚለው አባባል ስንመለስ በፍልስፍና አለም ውስጥ ወጠ የሆነ እወነታ አለ ወይስ እወነታ አንፃራዊ (ተለዋዋጭ) ነው ወደ ሚለው የፍልስፍናና ክፍል ውስጥ ይከተናል ።

ሁሉም ለራሱ ትክክል ነው ኢስራኤል የፊሊስጢም ምድር ላይ የፈለገችውን ብታደርግ ለራሷ ትክክል ናት አሜሪካ የአረብ ሀገራትን ነዳጅ አሞጣ ስትዘርፍ ለራሷ ትክክልናት በየቦታው ሰውችን ያለ አግባቡ የሚጨፈጭፉ ቡድኖች ለራሳቸው ትክክል ናቸው የሚል አንድምታ ያለው እርኩስ የሆነ ፍልስፍና ነው።

እኔ ለራሴ ትክክል ነኝ የሚለው አስተሳሰብ ሃይማኖታዊ ይዘት የሌለው ከማህበረሰብ ወግ ያፈነገጠ የትኛውንም የሂወት መመዘኛን የማይቀበለ የወሮበሎች ከሰነ-ምግባር ከሃይማኖት ፣ከልበ -ህግ ያፈነገጡ ግለሰቦች የሚደበቁበት ከነቱ ምሽግ ነው።

#አልፈላሰፍ እኮ

ዘ.ሐ

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

02 Dec, 05:26


በባልደረቦቼ ( በሰሀቦች ) ጉዳይ አደራ አደራ ፤ እኔ ካለፍኩ በኃላ እነርሱን ኢላማ አታድርጏቸው ፤ የወደዳቸው ሰው ለኔ ባለው ውዴታ ነው እነርሱንም የወደደው ፤ የጠላቸው ደግሞ ለኔ ባለው ጥላቻ ምክንያት ነው እነርሱን የጠላቸው ፤ እነርሱን ያስቸገረ በርግጥ እኔን አስቸግሮኛል ፤ እኔን ያስቸገረ ደግሞ አሏህን አዛ እንዳደረገ ነው ( ለአሏህ የማይገባ ተግባር ፈፅሟል ) ፣ አሏህን አዛ ያደረገ ደግሞ ብዙም ሳይቆይ ይይዘዋል ።

ቲርሚዚይ

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

01 Dec, 18:40


ዝንቅ
- - ~ - -

ከሰለመ ቅርብ ጊዜያት የሆኑት ወጣት በጀለቢያ በጥምጣም ፏ ብሎ መስጂድ ይገባል እንደ አጋጣሚ ኢማሙ ሰላቱን ጨርሰው አሰለምተዋል።

ወጣቱም ሁለተኛ ጀማአ ለመስገድ ሰውችን ሲጠብቅ የተወሰኑ ሰውች ሰብሰብ አሉና ከመሀከል አንዱ ፈጠን ብሎ ኢቃም አለ።

ከሁሉም በተሻለ መልኩ በላይ ገፅታው ፏ ያለው እሱ ሰለነበረ ካለሰገድከን ብለው ሙጥኝ አሉበት
እሱም አዲስ ሰለምቴ ነኝ ምንም አላቅም ቢልም
ምእምናኑ ችክ ብለው ወደ ፊት ገፍትረው አስገቡት ።

እሱም በቅርቡ የተማራትን አሏሁ አክበር ካለ በኃላ ኢኒ ቢኒ ቲኒ ቀራላቸው ይባላል አሉባልታም ሊሆነ ይችላል።

ይህ ቀልድ ድሮ የሰማሁት ቢሆንም በዚህ ዘመን ያለ ቦታው የቁርአን አንቀፅ ያለ ቦታው ሀዲስ የሚጠቃቅሱ ሰውች ስመለከት ኢኒ ቢኒ ቲኒ ከሚለው የተለየ ትርጉም አይኖረውም የሚያቁትን አንቀፅ መጥቀስ መረጃ አምጥተሀል ማለት አይደለም ።

ዘ.ሐ

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

01 Dec, 16:24


ሁልግዜ ኦሬንታሊስቶች ለሚያነሷቸው ብዥታዎች መልስ በመስጠት ብቻ መብቃቃት የለብንም እኛም የክርስቲያኖችን እና የሌሎች ሀይማኖቶች ጭፍጨፋዎች እያነሳን ልካቸውን እንዲያውቁ ማድረግ አለበን

ዶ/ር ሸውቂ

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

01 Dec, 10:18


💎ዐቂዳ ደርስ - 30💎



     🎤 በኡስታዝ ዒሳ አብራር
          ( ሀፊዘሁሏሁ ተዐላ )

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

01 Dec, 10:18


💎ዐቂዳ ደርስ - 29💎



     🎤 በኡስታዝ ዒሳ አብራር
          ( ሀፊዘሁሏሁ ተዐላ )

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

01 Dec, 06:53


«አብዛኛው የኡመቱ ክፍል ስለሱፊዮች አያነሳም ይህ ደሞ ስህተት እንደሆነ ልታውቅ ይገባል። ምክንያቱም የሱፊያ ቃል በጥቅሉ አሏህን ወደ ማወቅ የሚወስድ መንገድ ሲሆን እሱም ከአካላዊ ግንኙነቶች መጽዳት እና መላቀቅ ማለት ነው። ይህ ደሞ ጥሩ መንገድ ነው» …♦️
በተጨማሪም እንዲህ አሉ፦ «ሱፊዮች በማስተንተንና ነፍስን ከአካላዊ ግንኙነቶች ለማላቀቅ በመጣር የተጠመዱ እንዲሁም ውስጣቸውም ሆነ ውጫቸው በሌሎች አድራጎቶቻቸውና ስራዎቻቸው ላይ አሏህን ከማውሳት እንዳይቦዝን የሚታትሩ ናቸው ፣ ከአሏህ ጋር በተሟላ ስነስርዓት ላይ ከመኾን የማይለዩ ፣ እነዚህ ከአደም ልጅ በላጭ ክፍሎች ናቸው»አሉ።♦️

🌹ታላቁ ሊቀሊቃውንትና ታዋቂው ሙፈሲር ኢማም ፈኽሩ ዲን አልራዚ رحمه الله🌹

📚اعتقادات فرق المسلمين والمشركين
በተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ በስምንተኛው ንዑስ ርዕስ ላይ "የሱፊዮች ሁኔታ"

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

01 Dec, 05:58


አሏህ ሱብሀነሁ ወተዐላ በጊዜያት መፈራረቅ የሚላበሰዉም ሆነ የሚያጣው ባህሪ የለም

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

30 Nov, 18:38


Live stream finished (37 minutes)

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

30 Nov, 18:20


ዛሬ እንደሚታወቀው የአራዳውች ቀን ነው
እኔም ከነሱ ጋር ለመመሳሰል የማናት ስሟ
ብቻ ወሀቢ ነኝ ፣ወሀቢ ነኝ ፣እኔም ወሀቢ ነኝ፣
ቁርአን የሚከተሉ ከተባሉ ወሀቢ እኔም ወሀቢ ነኝ፣ ወሀቢ ነኝ፣ እኔም ወሀቢ ነኝ፣ ተውሂድ የሚከተሉ ከተባሉ ወሀቢ እኔም ወሀቢ ነኝ ፣ ወሀቢ ነኝ ፣እኔም ወሀቢ ነኝ ፣ የሚለውን ሬጌ ራጋ እያደመጥኩ ነው መልካም ቅዳም ሲደመር የእሁድ ለሊት ይሁንላችሁ ።

ዘ.ሐ

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

30 Nov, 18:01


Live stream started

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

30 Nov, 17:59


ተንቢህ ኪታብና የአገራችን ዑለማዎች
ያላቸው ትስስር


⚡️ቅኝታችንን ዛሬ  የሰይዲ አብዱልጀሊል የሶለዋት ኪታብ #ተንቢሑል_አናም ላይ አድርገናል


ይህ ኪታብ ሲወሳ በአለም ደረጃ ይሄንን ኪታብ እውነተኛ የእውቀት ቀንጂል እና የፍቅር ጸዳል ያላበሱት ሐበሻዊ ዓሊም እና ሽሂድ አብረው ይታወሳሉ
💥ታላቁ ዓሊም ሽይኽ ሁሰይን ባሆች🍁


በአለም እውቅና ያለው የሶለዋት ኪታብ ተንቢሁል አናም ላይ የሚከተለውን ባብ እናገኛለን
باب فى إثم من ترك الصلاة عليه عند ذكره فى سره وجهره ﷺ
በዚሁ ባብ ውስጥ 19ኛው ሶለዋት 👇
🎤🎤🎤
❤️❤️اللهم صل وسلم على سيدنا ومولانا محمد وعلى آل سيدنا محمد الذي لا يكمل لأحد إسلامه حتى يصلي عليه صلوات الله عليه وسلامه❤️❤️

👉የሐበሻ ኩራት የሆኑት ታላቁ ዓሊም እና ሽሂድ በሆኑት ሽይኽ ሁሰይን ኢብኑ ሃቢብ ወረ-ሒመኖ ባለችው መንደራቸው  መጠሪያ ባሆች በሚለው ስም የባሆች ሽይኽ የሚባሉት በአለም በቀዳሚነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰይዲ አብዱል ጀሊል የሶለዋት ኪታብ  የሆነውን ተንቢሑል አናም ላይ ሽርህ አዘጋጂተው አለምን ጉድ ባስባለው ኪታባቸው ላይ ይሄንን ይላሉ
📚توضيح المرام ومسرح الافهام 
للعلامة الشيخ الشهيد حسين بن حبيب بن آدم
يقول فى كتابه
((لان كمال الايمان بكمال المحبة له صلى الله عليه وسلم ومن علامة المحبة إليه كثرة الصلاة والسلام عليه لأن من أحب شيأ أكثر من ذكره))
ትርጉም [[<<አንድ ሰው እስልምናው ሙሉ አይደለም በነብያችንﷺ ላይ ሶለዋት እስካላወረደ ድረስ የተባለበት>> ምክንያቱ የኢማን ምሉእነት የሚገኘው ነብያችንን ﷺ ከመውደድ ጋር በመሆኑ ነው።
ነብያችንን ﷺ የመውደድ ምልክቱ ደግሞ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ አብዝቶ በማውረድ ነው።
ምክንያቱም  አንድን ነገር የወደደ ሰው የወደደውን ነገር አብዝቶ ያወሳል]]
ሲሉ ያብራቱታል

🍁የሐበሻ ዑለማዎች የሶለዋት ኪታቦች እውነተኛ ፍቅራቸውን በብእር ጠብታ ለማስፈር መታተራቸው የነብያችንን ዓለይሒ ሶላቱ ወሰላም የስብእና ልዕልና መውደድ በትውልዱ ውስጥ የገዘፈ አሻራ ጥሎ ተራማጂ እንዳደረገው ያሳያል።

አሏህ የአለማቱ ፈጣሪ ተወዳጂ የሆኑትን ነብያችንን ዓለይሒ ሶላቱ ወሰላም እውነተኛ መውደድ ይወፍቀን🤲
فخر الرازي

https://t.me/sufiyahlesuna

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

30 Nov, 14:32


"ከደደቦች ጋር አትጣላ በቁጥር ብዙ ናቸው።"📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌

ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

30 Nov, 05:49


ዝንቅ
= = =
#አንድ ሽማግሌ በሁለተ ወጣቶች መሀከል ይቀመጣል ልጆቹም መዘባበት ፈለጉና አንተ ሰውይ አላዋቂ ነህ ወይስ ሞኝ ብሎ ይጠይቁታል እሱም በሁለቱ መሀል ነኝ ሲል ይመልሳል ።


#በአንዲት ከተማ ውስጥ በጎባጣነቱ የሚታወቅ ሰው ነበር ከእለታት አንድ ቀን ጉዳጓድ ውስጥ ይወድቅና ጎብጥናው ይስተካከል ነገር ግን ሁለቱ ፍሬውቹ ያብጣሉ።ጎሮቤቶቹ እንዃን ደስ አለህ እያሉ ብስራተቸውን ሲገልፁ ። እባካችሁን አቁሙ አሁን የደረሰብኝ ከበፊቱ የባሰ ነው አለ።


#ኢብኑ ሀቢብ እንደጠቀሱት የኡስማን ኢብኑ ሰኢድ ወንድም ጉድጓድ ውስጥ ገባና ወንድሙ
ጉድጓድ ውስጥ ገባህ ሲል ጠየቀው ?ወንድምም አዎ አትመለከተኝም እንዴ ሲል ይጠይቀዋል ኡስማን በቃ የሚያወጣህ ሰው ይዤ እስክመጣ ከዚህ የትም እንዳትሄድ አለው።


ዘ.ሐ

11,036

subscribers

2,965

photos

379

videos