========================
ውድ ተማሪዎች:
የመጀመሪያው ትምህርት ተጥናቅቆ ወደ ሁለተኛው ደርሰናል:: ይህ ትምህርት ለአንድ ሳምንት ብቻ ይቆያል:: አርብ ለት ፈተና ይሰጣል:: መልካም ጥናት
ትምህርት 2 መግቢያ:
========================
“እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
— ዮሐንስ 17:3
ስለ እግዚአብሄር ያለን ግንዛቤ በሌላው የህይወታችን አቅጣጫዎች ሁሉ ባለን አስተያየት ላይ ፣ እንዲሁም የህይወትን ጥያቄዎች እንዴት እንደምንረዳና እንደምንመልስ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳድርብናል፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ ስለእግዚአብሔር ማንነት ሊታወቅ የሚችለውን በትክክል ካልተረዳን ራሳችንን ለመረዳት አዳጋች ይሆንብናል፤
ስለ እግዚአብሄር ያለን መረዳት የተሳሳተ ከሆነ ስለራሳችን ያለን መረዳት የተሳሳተ ይሆናል!
በዚህች ትንሽ አዕምሮአችን ይህንን ጥልቅ ሀሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት መሞከር ውቂያኖስን በትንሽዬ ማንኪያ ጨልፎ ከመጨረስ ቢከብድም ልናውቀው የሚገባንን እና የምንችለውን ከቃሉ እናጠናለን፤ ደግሞም በመንፈሱ አማካይነት ሊያስተምረን ቃል ለገባልን ለመድሃኒያለም ምስጋና ይሁን!
በርግጥም ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሄር አለ? ካለስ እግዚአብሄር ማነው?
በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሄር በተለያየ ስሞች መጠራት ለምን አስፈለገው? እነዚያ ስሞችስ ምን ትርጉም ይኖራቸው ይሆን ?
የእግዚአብሄር ሊተላለፉ የሚችሉ እና ሊተላለፉ የማይችሉ ባህርያትስ ምን ምን ናቸው?
ስላሴ የሚለው ሀሳብ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ነውን ? ምን ማስረጃ አለ? ምን ማለትስ ነው?
ሰብዓዊውን ዘር በማዳን እቅድ ውስጥ ስለእግዚአብሄር አብ ሚና መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል?
እግዚአብሄር ወልድ ማን ነው? ሰውን ለማዳን ሰብዐዊውን ተፈጥሮ መውሰድ ለምን አስፈለገው? ከእግዚአብሄር አብ ጋርስ እኩል ነው? ከሆነስ በተለያዩ ቦታዎች አብ ከእኔ ይበልጣል ብሎ ለምን ተናገረ?
መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? መንፈስ ቅዱስ በእውነት አምላክ ነው ወይስ? ሰብዓዊውን ዘር በማዳን እቅድ ውስጥ ስለመንፈስ ቅዱስ ሚና መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል?