ፓራዳይም(የልቡና ውቅራችን) በተፈጥሮው ምክንያታዊ ሳይሆን ልማዳዊ ነው ! በምክንያት ህይወትን ለመቀየር መጀመር ይቻላል ያለ ልማድ ግን የፈለገ ብንጥር ጠብ የሚል ነገር የለም ምክንያቱም አእምሮ በምክንያት አይሰራም በድግግሞሽ በተገነባ እምነት እና ልማድ እንጂ።
ምን እፈልጋለው ? ለምን የምፈልገውን አይነት ሰው መሆን አቃተኝ ?
ምክንያታዊነት የሚሰራው ከእርሱ ጋር የሚዛመድ ውቅር ሲኖረን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ የሚገኝ ሳይሆን ሆን ብለን እራሳችን ላይ የምንገነባው አስተሳሰብ ፣ እምነት እና ልማድ ድምር ውጤት ነው።
ሆን ብሎ የሚፈልገውን እምነት እና ልማድ የማይገነባ በልጅነቱ በተቀረፀበት እና በዙሪያው በሚከናወነው ክስተቶች ህይወቱን ለመምራት የወሰነ ፍቃደኛ ነው። ብልህነት ግን ከመሻት ጋር የሚጣጣም ማንነትን በምርጫ መገንባት ነው።
"ለእድገት እና ለስኬት መርጠን እንስራ"
ህይወት ምርጫ ፣ ሂደት እና ውብ ናት !!!
https://t.me/BilinersNega