Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ @ddahbofficial Channel on Telegram

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

@ddahbofficial


Real time health information for the public

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ (Amharic)

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የወላጆች መንገድ ለአዲስ መንገዶች እና እርምጃዎች አሰጣጥጥሽ ባለሥልጣን ምርጥ መረጃዎችን በማስከበር አዝናኝ በተዘረቀ ምክንያት ከመጠቀም በፊት የሚገኝ እና ሁኔታ ነው። የድሬዳዋ አስተዳደረ ጤና ቢሮ ምንድን ነው? እንዴት እናከብርረዋለን? አስተዳደር ጤና ቢሮ ለምን እንተረብሽ? የሚናገረውን ስልኩ እናድርግ ፡፡ ddahbofficial አድርገን እና በአጭር ዳዊት ሊሆን የሚችል ሲሆን እንፈልግን!

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

25 Oct, 07:34


ዕለታዊ የኮቪድ-19 መረጃ
(15/02/2015 ዓ.ም)

ለፈጣን መረጃዎች!
Youtube:https://youtube.com/channel/UCiJE60dU1Gj3sjOMs_l_MPQ

Telegram:https://t.me/DDAHBofficial

Facebook:https://www.facebook.com/Dire-Dawa-Administration-Health-Bureau-1371606266279524/

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

03 Oct, 12:06


ዕለታዊ የኮቪድ-19 መረጃ
(23/01/2015 ዓ.ም)

ለፈጣን መረጃዎች!
Youtube:https://youtube.com/channel/UCiJE60dU1Gj3sjOMs_l_MPQ

Telegram:https://t.me/DDAHBofficial

Facebook:https://www.facebook.com/Dire-Dawa-Administration-Health-Bureau-1371606266279524/

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

02 Oct, 14:57


የማህበረሰብ ተሳትፎን በማሳደግ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን ማሻሻል እንደሚገባ ተገለፀ።

የገጠር ክላስተር አመራሮችና ባለሞያዎች፣አጋርና ባለድርሻ አካላትና የጤና ቢሮ አመራሮች የተገኙበት የማህበረሰብ ተሳትፎ ስልቶችን ለመተግበር የሚያስችል የትውውቅ መድረክ ተካሂዷል።

በትውውቅ መድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንደገለፁት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በርካታ የጤና ጉዳዮችን ለውጤት ያበቃንበት ስልት በመሆኑ ይህንን ፕሮግራም ማጠናከር የጤናውን ዘርፍ ውጤት ማሳደግ መሆኑን ገልፀው በአስተዳደራችንም ነባር የማህበረሰብ ተሳትፎዎችን በማጠናከር የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በመድረኩ የተገኙ አካላት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

ይህ በአዲስ መልክ የሚደራጀውና የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን የሚያሻሽለው የማህበረሰብ ተሳትፎ ስልቶች አተገባበር፣ዓላማና ተግባራዊ በተደረገባቸው የተለያዩ ክልሎች የተገኙ ውጤቶችን የተመለከቱ ፅሁፎች ከጤና ሚኒስቴር በመጡ ባለሞያዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በቀጣይ በአስተዳደራችን በቢዮአዋሌ ገጠር ክላስተር ይህ የማህበረሰብ ተሳትፎ አደረጃጀትና ትግበራ በፓይለት ደረጃ የሚጀመር ሲሆን ለዚህም ውጤታማነት በክላስተሩ የሚገኙ የጤናው ዘርፍ አመራሮች፣ባለሞያዎችና ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ በመድረኩ ጥሪ ቀርቧል።

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

25 Sep, 12:47


በተጨናነቀ ሁኔታ በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ይሰጥ የነበረውን የድንገተኛ አደጋ ህክምና ችግር የሚፈታ የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከል ተመረቀ፡፡
__
በምረቃ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሃር ማህበራዊ ልማት በተለይም ጤና አምራች የሆነውን ማህበረሰብ ከመጠበቅና ከልማት አቅም መጎልበት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ በመሆኑ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በአስተዳደራችን የጤና አገልግሎትን ተደራሽ እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር በተለይ ከፈጣን የከተማ ዕድገትና እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ድንገተኛ አደጋዎች በመበራከታቸው ድንገተኛ አደጋ ህክምና አገልግሎት ራሱን በቻለ ማዕከል ማስተናገድ አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል፡፡

ክቡር ከንቲባው አያይዘውም ዛሬ መርቀን ለአገልግሎት የምናበቃው የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና መስጫ ማዕከል በተሟላ ሁኔታ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር አቅም በፈቀደ ለተገልጋዩ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በመሆኑ ለዚህ የህክምና ማዕከል እውን መሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረገውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርንና ቀን ከሌት ለሠሩ ለአስተዳደራችን ጤና ቢሮና የድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል አመራሮችና ባለሞያዎች ምስጋና በማቅረብ ይህ ማዕከል ከአስተዳደሩ ነዋሪዎች ባሻገር ለአጎራባች ክልሎችም አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ጤና ጥበቃ ሚ/ር ለማዕከሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን እንዲደግፍ ጠይቀዋል፡፡

ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃርና የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ይህንን የድንገተኛ አደጋ ህክምና መስጫ ማዕከልን ለማስጀመር ለሰጡት አመራርና ላደረጉት ክትትል ምስጋናቸውን ያቀረቡት የ ኢ. ፌ. ድ. ሪ የገንብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ናቸው፡፡ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ድሬዳዋ በሕዝቦቿ መካከል ያለው አንድነት ለኢንዱስትሪ ልማት፤ ለሎጀስቲክ ማዕከልነትና የሀገራችን የሰላም ማዕከል አንዷ እንድትሆን ያደረጋት ሲሆን ይህንኑ አንድነትና መጠበቅ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በጤና ጥበቃ ሚንስቴር ሚ/ር ዲኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ይህ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማእከል ያለበት ቦታ አመቺ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሚቀጥሉት ጊዜያት በስፋት ከተሠራበት ለአስተዳደሩ ነዋሪ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ከድንገተኛ አደጋ ባሻገር ሌሎች መሰል የጤና አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋአስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በበኩላቸው ለአስተዳደሩ ነዋሪዎች የድንገተኛ አደጋ ህክምና ችግር ምላሽ የሚሰጠው የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከል ሥራ ለማስጀመር ዝግጅታችንን አጠናቀን ለዚህች ቀን በመብቃታችን እንኳን ደስ ያለን በማለት ይህንን ማዕከል አሁን ያለበት ደረጃ ለማድረስ አስተዳደራችን ትኩረት መስጠቱንና ለዚህም ስኬት ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩት ክቡር ከንቲባችንን አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

ኃላፊዋ አያይዘውም ይህ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከል በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ ይሰጥ የነበረውን የድንገተኛ አደጋ ህክምና አገልግሎት የሚያስቀር ሲሆን በጤና ጥበቃ ሚ/ር አገልግሎቱን ላማሻሻል በተሰጠ ዕድልና በተቀመጠው አቅጣጫ እና በተደረገ ድጋፍ ባለፈው አንድ ዓመት የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ለተደረገው ርብርብ የሆስፒታል የቦርድ አመራሮች፣ የማንጅመንት አባላት እና ሌሎችም አካላት ምስጋና እንደሚገባቸው ታናግረዋል፡፡

በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በ 2014 ዓ/ም ብቻ 12 ሺ 500 የሚሆኑ ድንገተኛ አደጋ የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አመቺ ባልሆነ ሁኔታ ህክምና ሲሰጣቸው እንደነበር ያስታወሱት ወ/ሮ ለምለም ይህ የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የአምቡላንስ ነፃ የስልክ መስመር እንደተዘጋጀለትና የነፃ የስልክ መስመር ቁጥሩም 9769 መሆኑንና የአምቡላንስ አገልግሎቱም ‹‹ኦተራይ›› የሚል ስያሜ እንደተሰጠው ይፋ አድርገዋል፡፡

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

25 Sep, 12:45


ለምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ግምታቸው 500 ሺ ብር የሚወጡ የመድሃኒትና የህክምና መስጫ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

የመድሃኒትና የህክምና መስጫ ቁሳቁስ ድጋፉን ያደረጉት ህይወት ማሞ መድሃኒት ማከፋፈያ፤ ኮኔል ቢላል ሆስፒታል እና ማክ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያዎች ጅምላ አከፋፋይ ናቸው፡፡

በድጋፍ አሰጣጡ መረሃ-ግብር ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ሀገሪቷ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ እንደ አስተዳደር የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን በዚሁም መሰረት በህክምና ዘርፍ የተሰማሩ አጋሮቻችን በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፎችን እያደረጉ ሲሆን አሁንም የምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ያለበትን ክፍተት በመለየት ግምታቸው 500 ሺ ብር የሚሆኑ የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ላደረጉት የግል ሆስፒታልና የመድሃኒት አከፋፋዮች በጤና ቢሮና በአስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበው ወደፊትም ሌሎች በተመሳሳይ ዘርፍ የተሠማሩ ሁሉ ወቅቱን የጠበቀ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለሆስፒታሉ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል አዛዥ ኮሮኔል ብርሃኑ ዘውዱ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ወያኔ በከፈተብን 1ኛውና 2ኛው ዙር ጦርነቶች ተመሳሳይ ድጋፎች በአስተዳደሩ፣ በጤና ቢሮና በጤናው ዘርፍ በተሰማሩ አካላት የተደረጉልን ሲሆን አሁንም የተከፈተብንን 3ኛው ዙር ጦርነትን ተከትሎ ለተደረገልን ድጋፍ እና ደጀንነት እያመሰገንን የናንተ ድጋፍና ደጀንነት ለሠራዊቱ የሞራል ስንቅ ከመሆኑም ባሻገር ያለችንን አንዲት ሀገር ሊበትኑ የመጡትን ጠላቶቻችንን በጋራ ሆነን እንድናሸንፋቸው ያግዘናል ብለዋል፡፡

ከዚህ ድጋፍ ቀደም ብሎ ሰሞኑን ዴልት ሆስፒታል ግምታቸው 75 ሺ ብር የሚያወጡ መድሃኒቶችንና የህክምና መስጫ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

21 Sep, 06:43


በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በቅርቡ የተጀመረው ሲቲስካን አገልግሎት እንግልታቸውንና ለአገልግሎቱ ይከፍሉ የነበረውን የክፍያ መጠን በብዙ እጥፍ እንደቀነሰላቸው ተገልጋዮች ተናገሩ፡፡

በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል የተሟላና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሲቲስካን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ በአገልግሎቱ መጀመር ምክኒያት አገልግሎቱን ለማግኘት የነበረባቸውን እንግልትና አቅማቸውን ያላገናዘበ ክፍያ እንዳስቀረላቸው ተገልጋዮች ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት መጥተው በሲቲስካን አገልግሎት መስጫ ክፍል ያገኘናቸው ተገልጋይ አቶ አብዲ አሜ ያላቸው የገቢ መጠን ዝቅተኛ መሆኑንና አገልግሎቱን በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ማግኘት ባይችሉ ያላቸው አማራጭ ብድር አሊያም ከወዳጅ ዘመድና ሊደግፋቸው ከሚችል አካል እርዳታን በማፈላለግ አገልግሎቱን ያገኙ እንደነበር በመናገር በተለይ ለብዙ ጊዜ ስንመኘው የነበረ የሲቲስካን አገልግሎት በመጀመሩ እጅግ እንደተደሰቱ ተናግረዋል፡፡

በድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙና ኢብራሂም በበኩላቸው የሲቲስካን አገልግሎት በሆስፒታሉ ሃምሌ 28/2014 ዓ/ም መጀመሩን አስታውሰው ይህ ዜና እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ለ 247 ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን በማውሳት የህብረተሰቡ የመገልገል ፍላጎት ዕለት ተዕለት መጨመሩንና ይህን አገልግሎት በማግኘቱ ተገልጋዩ ማህበረሰብ በሆስፒታላችን ላይ ያለው አመኔታ ከወትሮው ይለቅ እየተሻሻለ መምጣቱን ሥራ አስኪያጇ ተናግረው በተለይ የታካሚዎቻችን እንግልት መቀነሱ፤ የህክምና አገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረጉና ታካሚው ቀልጣፋና ፈጣን ውሳኔ እንዲያገኝ በማድረግ ታካሚውን ከህመሙ በቶሎ እንዲፈወስ የሲቲስካ መኖር ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ሙና ኢብራሂም አያይዘውም በሆስፒታላቸው ሲቲስካኑ በመጀመሩ አስተዳደሩን አመስግነው ይህን የሕዝብ ንበረት የሆነውን ሲቲስካን ሁሉም የሆስፒታሉ ማህበረሰብ በሚገባ በመንከባከብና በመጠበቅ የአገልግሎት ዕድሜውን ማስረዘም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

21 Sep, 06:40


ዕለታዊ የኮቪድ-19 መረጃ
(11/01/2015 ዓ.ም)

ለፈጣን መረጃዎች!
Youtube:https://youtube.com/channel/UCiJE60dU1Gj3sjOMs_l_MPQ

Telegram:https://t.me/DDAHBofficial

Facebook:https://www.facebook.com/Dire-Dawa-Administration-Health-Bureau-1371606266279524/

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

17 Sep, 08:49


የስራ እድል ማስታወቂያ

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

16 Sep, 16:49


በክረምት በጎ ፍቃድ በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከሚገነቡ ቤቶች በአንዱ የግንባታ ጉብኝትና በጉልበት ሥራ የማገዝ ተግባር ተከናወነ፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና ጤና ማበልፀግ የሥራ ሂደት ሠራተኞች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን አስመልክቶ በቢሮውና በገጠርና ከተማ ጤና ተቋማት ጤና ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ባደረጉት መዋጮ እየተሠሩ ካሉት በ 03 ቀበሌ ግንባታው የተጀመረውን የአቅመ ደካማ ቤት ያለበትን የግንባታ ደረጃ ከመጎብኘታቸውም ባሻገር የጉልበት ሥራ እገዛ አድርገዋል፡፡

በግንባታው ሥራ የጉልበት እገዛ ሲያደርጉ ያገኘናቸው የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የበሽታ መከላከልና ጤና ማበልፀግ የሥራ ሂደት መሪ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ እንዲህ ያሉ እርስ በእርስ የመደጋገፍ ተግባራት ሁሌም አቅም በፈቀድ መጠን ሊቀጥሉ እንደሚገባ በመናገር በተለይ ለበጎ ሥራ ገንዘብን ከማዋጣት ባሻገር በጉልበታችን እገዛ ማድረጋችን ለሌሎችም ምሳሌ መሆን የሚያስችል ከመሆኑም ሌላ አገልጋይነትና የበጎነትን መንፈስ በውስጣችን የበለጠ የሚያሰርፅ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

15 Sep, 12:27


የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች ‹‹ከሉዓላዊነታችን በተፃራሪ የቆመው የህውሃት ሸፍጥ›› በሚል ርዕስ በቀረበው ሰነድ ላይ ተወያዩ፡፡

በዚሁ በሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ በተደረገው ውይይት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ‹‹ከሉዓላዊነታችን በተፃራሪ የቆመው የህውሃት ሸፍጥ›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ዋና ኃላፊዋና ምክትል ኃላፊው አቶ ዩሱፍ ሰኢድ በቀረበው ሰነድ ላይ የተደረገውን ውይይት መርተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት አመራሮችና ሠራተኞች ለህግ ማስከበሩ ከጀግናው መከላያከያ ሠራዊታችን ጎን በሞያቸውና በሚያስልገው ሁሉ እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል፡፡

Dire Dawa Administration Health Bureau-የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

13 Sep, 16:17


"በጎነት ለጤናችን " በሚል መሪ ቃል የቢዮ አዋሌ ጤና ጣቢያ ሰራተኞች ለ50 አባወራዎች የማዕድ ማጋራት መርሀግብር አካሄዱ።

ጤና ጣቢያው እንደ እቅድ በያዘው የክረምት የበጎ ስራ አገልግሎት በቢዮአዋሌ ክላስተር ከአምስት ቀበሌዎች ለተወጣጡ 50 አባወራዎችና እማወራዎች የአስቤዛና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፉ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ የፕላንና ፕሮግራም ልማት ዳይሬክተር አቶ ሰይፈዲን አብዱረህማን እንዳሉት የቢዮአዋሌ ጤና ጣቢያ ሰራተኞች ከደሞዛቸው በማዋጣት ለሀምሳ አባወራዎችና እማወራዎች ማዕድ ማጋራታቸው የቅንታቸውንና በጎ ተግባራቸው ማሳያ ነው ብለዋል። እንደ ሀገርም እንደ አስተዳደር በተጀመረው የበጎ ስራ አገልግሎት የቢዮ አዋሌ ጤና ጣቢያ ሰራተኛች ላደረጉት አበርክቶ ሊመሰገኑ ይገባልም ብለዋል።

የቢዮ አዋሌ ጤና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ቀልቤሳ አባስ በበኩላቸው እንደገለጹት ጤና ጣቢያው ከጤናው አገልግሎት በተጓዳኝ በበጎ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልፀው በተለይ በቅርብ በተጀመረው አነስተኛ የቀዶ ጥገና አገልግሎት እና የማደንዘዣ ማሽኖችን በመጠቀም ለሚከናወኑ የጤና አገልግሎቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ እገዛዎችን በማድረግ ከጤናው ጎን ለጎን የበጎ ተግባር ስራዎችን ሲያከናውን የቆየ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ለጤና ጣቢያው ሰራተኞችና ለጤና ባለሞያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ለነዋሪዎቹ የተዘጋጀው ዘይት፣አልባሳትና ዱቄት በእንግዶቹ የተለገሰ ሲሆን በጤና ጣቢያው ግቢ ውስጥ የአቮካዶ ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።

ምንጭ:- የድሬዳዋ ብዙሃን መገናኛ ነው

1,469

subscribers

783

photos

5

videos