.
የሰዎችን የአዕምሮ ንብረት ያለምንም ሀፍረት በጠራራ ፀሀይ ለመዝረፍና በሰዎች ላብ በተገነባ መሰላል ላይ ከፍ ብሎ ለመታየት የመሞከር አባዜ በርካታ የትንሽነት ስነ ልቦና በተጠናወታቸው ድኩማን ዘንድ እንደ ትልቅ ሙያ የሚታይ የግብረ–ገብነት እንከን ሲሆን ተመልክተናል።
ይህ የትንሽነት ስነ–ልቦና ግን የጥበብ ቤትን የሚያህል ከታዳሚዎቿ የመግቢያ ክፍያ ለመጠየቅ አፍራ የመስራቾቿን ኪስ ስታጎድል የነበረች መድረክን በድፍረት ለመንጠቅ የመሞከር ድፍረት ይኖረዋል ብለን አስበን አናውቅም።
ለምን የሰውን የአዕምሮ ውጤት ያለፈቃዱ ትጠቀማላችሁ ሲባሉ «ልናሳድገው አስበን» የሚሉ ሰዎች ምሳሌ ሴት ልጅን ካሳደጋት እና ከተንከባከባት ወላጇ ፈቃድና እውቅና ውጪ አስገድደው ለመዳር እንደሚሞክሩ ሀፍረተ–ቢሶች ነው። ኒካሁም ውድቅ፤ ስራውም የከፋ!
የጥበብ ቤትን ከአላማና ከግቧ ውጪ የጥቂቶችን አለማዊ ጥቅም ማሟያ በማድረግ እንዲጠቀሙባትም ሆነ በፍፁም ማንም በስማችን እንዲነግድ አንፈቅድም።
በመሆኑም ውድ ቤተሰቦቻችን ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሀሳብ ድርቀታቸውን የወንጀላቸው መሸፈኛ ለማድረግ ከሚሞክሩ ግለሰቦች ራሳችሁን ትጠብቁ ዘንድ እናሳስባለን።
የጥበብ ቤት በቅርቡ ለማዘጋጀት ቀን የቆረጠችለት ምንም አይነት መሰናዶ አለመኖሩን በማወቅ፤ ራሳችሁን፣ ጊዜያችሁን እና ገንዘባችሁን ከዚህ አደገኛ እንቅስቃሴ እንድትጠብቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።
.
በቀለም ጠብታ ማንነት ሲረታ!
የጥበብ ቤት!
@tebeb