ጥቅሳ ጥቅስ @tksa_tks Channel on Telegram

ጥቅሳ ጥቅስ

@tksa_tks


እንኳን ደህና መጡ።
በቴሌግራም ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ማለትም
💥አርስቶትል
💥አብርሀም ሊንከን
💥አልበርት አንስታይን
💥ማህተመ ጋንዲ... እንዲሁም የሌሎችም አባባል የሚያገኙበት ቻናል🎯 ሲሆን አላማችንም ሰዎች በሚያነብቡት ጥቅስ የአስተሳሰባቸውን አድማስ ማስፋት ነው። ስለመረጡን እናመሰግናለን 🙏


Contact፦ @onajonah

ጥቅሳ ጥቅስ (Amharic)

ጥቅሳ ጥቅስ በቴሌግራም አርስቶት፣ አብርሀም ሊንከን፣ አልበርት አንስታይን እና ማህተመ ጋንዲ ወይም አስተሳሰባቸውን አድማስ ማስፋት እስከ እድሜ፣ የታዋቂ ሰዎች እንዲሁም አገኙበት ቻናልን ሰዎች የምርቃትን ብሔር በመረጡ፣ እናንተም መረጡን እና ታደለን። ለማህበረፅ እዚህ ላይ ላግኙ።

ጥቅሳ ጥቅስ

21 Nov, 11:44


⚡️ፊልም በነፃ ለማግኘት⚡️ ሶደሬ Tube 😍
ዝምብላቹ #Download ለማረግ 😍

Join😀 👇

ጥቅሳ ጥቅስ

21 Nov, 11:38


ት/ት ሚኒስቴር ድንገተኛ መግለጫ አወጣ ‼️
በመግለጫውም ስለ ዘንድሮ remedial እና 12ኛ ክፍሎች አዲስ መረጃ.....  Continue

ጥቅሳ ጥቅስ

20 Nov, 17:45


መጪው ጊዜ...

ጥቅሳ ጥቅስ

19 Nov, 16:55


ከዚህ በፊት ያልነበረህን ነገር እንዲኖርህ ከፈለክ......

ጥቅሳ ጥቅስ

17 Nov, 14:03


SHARE||@tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

17 Nov, 04:53


.........መከፋት ይሻላል።

SHARE||@tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

16 Nov, 19:00


ማይክ ታይሰን ለእኔ ቦክሰኛ አይደለም!
(አሌክስ አብርሃም)

ከህይወት ቡጢ ለማምለጥ ሲሮጥ ያቀረቡለት የቦክስ ጓንት ውስጥ የወደቀ ሚስኪን ወፍ ነው። እንደብዙ ጥቁር አሜሪካዊያን ገና በልጅነቱ ብዙ መከራ ተቀብሏል። አባቱን በእርግኝነት አያውቅም ነበር። አንድ ጀማይካዊ የታክሲ ሹፌር ነው ይባላል።ይሁንና እሱ አባቴ ብሎ የሚያስበው /የተነገረው/  ሴቶችን ለሴተኛ አዳሪነት የሚያቀርብ ሰካራምና ዱርየ ሰው ነበር። ያም ሆነ ይህ ከንቱ ነበሩ።  የሆነ ሁኖ የአባት ፍቅርም ይሁን ከለላ ሳይኖረው እናቱ ጋር መጠጥ አደንዛዥ እፅ ፣ወሲብና ወንጀል  በተሞላ በዘግናኝ ሰፈር ውስጥ ለመኖር የተገደደ ሚስኪን ህፃን ነበር። የባሰው አሳዛኝ ነገር እናቱ በሴተኛ አዳሪነት ስራ የተሰማራች ሴት መሆኗሲሆን  የምታሳድጋቸው  በዚሁ ስራ ነበር። ማይክ እናቱ በመጠጥና ድራግ በናወዙ ሰካራሞች እናቱ ላይ ብዙ ግፍ ሲፈፀም አይቷል።

በቤተሰቤ እንደተሳቀኩ ነው የኖርኩት ይላል በሀዘን።ብዙዎቹ  የተገፉ ህፃናት ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፣ ከሰው ያጡትን ፍቅር ከአሻንጉሊት፣ ከቤት እንስሳት ወይም በሃሳባቸው ከሚፈጥሩት ታሪክ  ለማግኘት ይጥራሉ. . .ማይክ ታይሰን ርግብ ነበረችው የሚወዳት ! አንድ የሰፈር ጉልበተኛ እርግቡን ገደለበት  . . .የማይክ ታይሰን የታፈነ ብሶት ለመጀመሪያ ጊዜ ቡጢ ሁኖ የተገለጠው እዚህ እድለቢስ ወጣት ላይ ነበር ይላሉ ታሪኩን የፃፉ! ከዛማ ምኑ ቅጡ ማይክ ከአንደበቱ ቡጢው የሚፈጥን የለየለት ተደባዳቢ የጎዳና ልጅ ሆነ። እስርቤትና ፖሊስ፣ ክስና መታሰር. . .!

በመሰረቱ ይሄ ባህሪው በዛ መንደር መሞቻው ነበር! ግን አንድ ጣሊያናዊ የቡጢ አሰልጣኝ ዓይን አረፈበት! የማይክን የጎዳና ቡጢ ከሞት ወደህይዎት፣ ከእስር ቤት ወደቦክስ ሪንግ አመጣው! እነዛን ቁጡና በብሶት የተሞረዱ የማይክን ሰንጢ ጥፍሮች በጓንት ሸፍኖ ስፖርት አደረጋቸው። ደም ሳይሆን ዝናና ገንዘብ አፈሰሱ። የምታዩት ማይክ ታይሰን ተፈጠረ። ስሙ በዓለም ናኘ። ግን ምን ዋጋ አለው ገና በ20 ዓመቱ የአለምን የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻንፒየን የተቆጣጠረው ማይክ የገንዘብ ጎርፍ አጥለቀለቀው፣ የልጅነቱን ስነልቦናዊ ህመም ፣ብቸኝነትና የውስጡን ረብሻ  የማያክም ገንዘብ። በ16 አመቱ በካንሰር ለሞተች እናቱ ያልደረሰ ገንዘብ ። እንደጉድ ብሩን ረጨው፣ ባለፈ ባገደመበት ሴት ነው፣ መጠጥ ነው፣ ድራግ ነው። ውድ መኪና ቅንጡ ቤት ... ከተራ ሰው እስከፖሊስ በውሃ ቀጠነ እየደበደበ ቅጣት ነው። ባዶውን ቀረ።

ይታያችሁ ፎርብስ አንድ ጊዜ የማይክን ሃብት 685 ሚሊየን ዶላር ገምቶት ነበር።  ዛሬስ? ከየኪሱ የቀሩትን ሳንቲሞች ጭምር ቆጣጥሮ የቀረው ሀብት 10 ሚሊየን ብር ቢሆን ነው።  ተራ በሚባሉ ፊልሞች ሳይቀር ተራ ገፀ ባህሪ ወክሎ  አሰሩኝ እያለ እስከመለመን ደርሶ ነበር። ማይክ ታይሰን ብዙዎች እንደሚያስቡት የሚንጎማለል አንበሳ ፣ ከአለት የጠነከረ የቡጢ ንጉስ አይደለም። ቤተሰብ እና ማህበረሰብ እንዲሁም ዘረኝነት የፈጠረው ጠባሳ ለዚህ ያበቃው የቦክስ ጓንት ውስጥ ጎጆውን የሰራ ሚስኪን ወፍ ነው። የልጅነት አዕምሮ ላይ የቆመ ጠባሳ በተጠቂው ቡጢ አይጣልም። ልጆች ላይ የሚሰነዘርን የህይወትን ቡጢ፣ የስነልቦና ፍላፃ  ይከላከል ዘንድ የተፈጠረ ጋሻ  ወላጅ ይባላል። ወላጅ ናችሁ? እንግዲያውስ ለልጆቻችሁ ህያው አጥር ሁኑ
!

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

SHARE||@ethio_tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

16 Nov, 17:29


...ጨለማን መጠበቅ ያስፈልጋል።



SHARE||@tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

14 Nov, 03:42


🤔እረስቼዋለሁ

#አንድ ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትዮዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ።

ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት ....

"እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ ሁለት የቤት ሥራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት!

ሴትዮዋም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! ፡

እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ ሁለት ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት።

ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው።

አባትም ጥያቄያቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ አንደኛው የቤት ስራሽ "አንዲት ሴት ከእኔ ዘንድ በተደጋጋሚ እየመጣች አንድ በጣም ህመም የሆነባትን ችግሯን እያነባች እየነገረቺኝ ትሄዳለች። እኔም ይሄ ችግሯ ይወገድላት ዘንድ እየጸለይሁላት ነው፡፡ እስቲ እውነት ፈጣሪ ካንቺ ጋር የሚያወራ ከሆነ ይህቺ ሴት ለኔ አንብታ የነገረቺኝ ችግሯ ምን እንደሆነ ጠይቂልኝ አሏት፡፡

ሁለተኛው የቤት ስራሽ "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሀ ገብቼ የተውኩት አንድ ከኃጢያት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሀ ገብቼ የተውኩት ኃጢያት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እነዚህ ሁለቱን ጥያቄዎች በትክክል ከነገርሺኝ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት።

ሴትዬይቱም ወደ ቤቷ ሄደች።

አባት ተመልሳ እንደማትመጣ ገምተው ነበር። ዳሩ ግን በንጋታው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው።

አባም ሴቲዮይቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደ እርሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ! ... እግዚአብሔርን የሴትቷን ችግር ምን እንደ ሆነና እኔም እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ኃጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ፤

"አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ...

"እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ...

"የሴቷ ችግርና ጭንቀት ልጅ መውለድ አለመቻሏ ሲሆን የእርስዎን ግን እረስቼዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡

እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት ሁኔታ እውነተኛውን የልጅቷን ጭንቀት ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና ለእርሳቸው ኃጥያት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደ ደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!

እ.. ረ .. ስ .. ቼ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!

ሰው እንጂ ፈጣሪ ያለፈ ስህተትህን አያስብም ወይም እንደ ፍርድ ቤት የሰራሃውን ነገር ፋይል አድርጎ መዝገብ ቤት አያስቀምጠውም.... በቃ ወደ እርሱ በንስሃ ስትቀርብ ጥፋትህን ሙሉ ለሙሉ ይረሳዋል። ይቅርታዉ ትላንትን አያስብም። የሰው ልጅ ግን ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብዬሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል! በአንድ ወቅት ያደረግከኝን የረሳሁት እንዳይመስልህ ይልሃል።

ፈጣሪ ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ!

ታዲያ ስንቶቻችን እንሆን ፈጣሪን በኛ መጠን መትረን ንስሀ በገባንበት ኃጢያት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን ፈጣሪ እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ያጠበውን ኃጢያታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት አለንጋ ራሳችንን የምንገርፍ? ... ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት አቤት በቀለለ!

 "ፈጣሪ ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበት እና ይቅርታን የሚያደርግ ልብ ይስጠን!"
አሜን!🙏


#LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት


ውብ ቀን ተመኘሁ🙏

SHARE @tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

13 Nov, 03:55


እንኳን በሕይወት ነቃችሁ!

በሰላም ስላደራችሁ ደስ ይበላችሁ!

በዓለም ላይ በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ አይሮፕላኖች እየተነሱ በሰላም ያሰቡበት በመድረስ ያርፋሉ፡፡ ከእነዚህ በረራዎች መካከል ግን የአንዱም እንኳን በሰላም መግባት በዜናዎች ላይ ሲነገር አንሰማም፡፡ ሆኖም፣ አንድ በረራ ላይ አደጋ ከደረሰ ግን ትኩረት ይስባል፣ ዜናውን ይሞላዋል፣ ወሬው ይሸጣል፡፡  

የአንድ ጤናማ ሰው ልብም ቢሆን በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ ይመታል፡፡ ይህንን ያህል ጠንክሮ የሚሰራው አካላችን ግን በቀን ውስጥ ትዝም አይለን፡፡ የምናስታውሰው መምታት ለማቆም ሲዳዳውና የምቱ ድግግሞሽ ሲለይብን ነው፡፡ ለምን? መልካሙ ነገር ተለምዷል፡፡ የምስራች የሆነው ነገር ትዝም አይለን፡፡ 

ዛሬ መልካም መልካሙን ላስታውሳችሁ፡፡ ዛሬ የምስራቹ ትዝ ይበላችሁ፡፡ በሰላም የመንቃታችሁ ጉዳይ፣ በሌሎች ላይ የደረሰ እናንተ ላይ ያለመድረሱ ጉዳይ፣ የደረሰባችሁ ነገር ከዚህ የከፋ ያለመሆኑ ጉዳይ . . . ትዝ ይበላችሁ፡፡

ከደረሰብን ክፉ ነገር የሆነልን መልካም ነገር ይበዛልና ደስ ይበላችሁ፡፡

ፈጣሪን አመስግኑ! ቤተሰቦቻችሁን፣ ጓደኞቻችሁንና በሕይወታችሁ ላይ መልካም ተጽእኖ ያደረጉ ሰዎችን አድንቁ!

መልካም ቀን!

ከወደዱት ይህን መልእክት ለወዳጅ ዘመድዎ ይላኩ።

@tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

12 Nov, 03:55


አንበሳ የጫካው ንጉስ የሆነው በክብደት: በቁመት: በፍጥነት አልያም በብልጠት አይደለም

በቁመት ቀጭኔ
በክብደት ዝሆን
በፍጥነት ጥንቸል
በብልጠት ጦጣ ይበልጡታል

👇🏾

አንበሳን የጫካ ንጉስ ያስባለው አመለካከቱ ወይም Mind-set ነው

ለአንበሳ ሁሉም እንስሳ የሚታየው እንደ ምግብ ነው: የአንበሳ የአስተሳሰብ ውቅር ይህ ነው - that is what makes a Lion King of the Jungle

👇🏾

አንበሳ ብዙ እድሜ አይኖርም: የብርታት እድሜውም ትንሽ ነው - ውስጡ ያለውን ብርታት ከሚያደክምበት ነገር ዋነኛው ደግሞ ጩኸቱ ነው/the Roaring Force

ድንበሩን ለማስጠበቅ ይጮሃል: ሀይሉን ለማሳየት ይጮሃል: ወገኖቹን ለመጥራት ይጮሃል: ለንግስናውም ይጮሃል - በዚህም የተነሳ አለአግባብ ሀይሉን አባክኖ ብርታቱ በጩኸት ይከስማል

ከፍ ስትል ዝም በል

“Privacy is power” እንዲል ❤️🙌🏼

Share @tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

11 Nov, 16:56


እነዚህ መድሀኒቶች የተከፈለባቸው ናቸው: መድሃኒት የሆኑ ሰዎች ቅን ልቦና ከፍለውባቸዋል

👇🏾

መድሃኒት ቤቱ የሚገኘው ሳር ቤት ነው

የመድሃኒት ቤቱ ስም ሃልተን ፋርማሲ ይባላል

እነዚህ የምታይዋቸው ደረሰኞች የተከፈለባቸው ናቸው: ቅን ልቦና ያላቸው ሰዎች የከፈሉት

መድኃኒት ለመግዛት አቅም ያነሳችው ሰዎች እዚህ ፋርማሲ ሄደው እነዚህን የተከፈለባቸው ደረሰኞችን በመጠቀም መድሃኒት መውሰድ ይችላሉ

👇🏾

ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው
!!!

❤️🙌🏼

SHARE||¶@ethio_tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

10 Nov, 19:42


ይህ ሰው ለማኝ ወይም ቤት አልባ ተቅበዝባዥ አይደለም።

ይህ ሊዮ ቶልስቶይ በ“war and peace” እና “anna karenina” ልብ ወለዶቹ የሚታወቀው ሩሲያዊ ደራሲ እና ፈላስፋ ነው። እሱ ከታላላቅ ደራሲያን አንዱ እና በሥነ ጽሑፍ ውስጥ በተጨባጭ እንቅስቃሴ ውስጥ ቁልፍ ሰው ተደርጎ ይቆጠራል።

ቶልስቶይ በ September 9, 1828 በሩሲያ ውስጥ ተወለደ እና በ December 20, 1910 ሞተ። ጽሑፎቻቸው ብዙውን ጊዜ ስለ ሥነ ምግባር እና የሰው ልጅ ሁኔታን ይዳስሳሉ እና ስራዎቹ ዛሬም በስፋት ይነበባሉ እና ይማራሉ።

ከታዋቂዎቹ ጥቅሶቹ መካከል፡- “ስለ ሃይማኖትህ አትንገረኝ፣ ሃይማኖትህን በተግባርህ ውስጥ እንዳየው ፍቀድልኝ” የሚሉት ይገኙበታል።

"ህመም ከተሰማህ በህይወት አለህ። ግን የሌሎች ህመም ከተሰማህ ሰው ነህ"

የቶልስቶይ ውርስ ከሥነ ጽሑፍም አልፏል። እሱ ፈላስፋ እና ማህበራዊ ለውጥ አራማጅ ነበር፣ እና ስለ ሰላማዊ ተቃውሞ እና ቀላል ኑሮ የሰጠው ሀሳብ እንደ ማህተመ ጋንዲ እና ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ያሉ መሪዎችን አነሳስቷል



SHARE @tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

10 Nov, 18:38


ድፍረት አለን ማለት አንፈራም ማለት ሳይሆን......


SHARE @tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

10 Nov, 17:16


📣[ታላቅ ቅናሽ]
★ ማስተዋወቅ የሚፈልጉት ነገር አለ?
📌 መልሶት አዎ ከሆነ ከእኛ ጋር በመስራት የፈለጉትን ማስታወቂያ በዚህ በማስተዋወቅ ስኬታማ መሆን ይችላሉ ::

🌟የድርጅት ማስታወቂያ
🌟የተለያዮ አልባሳት
🌟የፊልም ማስታወቂያ
🌟የ መድሀኒቶችን ማስታወቂያ
🌟የክፍት ስራ ቦታ ማስታወቂያ
🌟የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
🌟የስልክ እና የlaptop
🌟የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
🌟የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
🌟ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች
🌟የትምህርት ተቋማት....
🌟 የህክምና ማዕከላት
🌟የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች......
🌟 ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች....

ህጋዊነት ያለውን ማንኛውም ማስታወቂያ እዚህ ቻናላችን ላይ በቅናሽ ማስተዋወቅ ትችላላችሁ።
Đм нєяє  @onajonah

ጥቅሳ ጥቅስ

10 Nov, 15:47


እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ....
       
SHARE||@tksa_tks

ጥቅሳ ጥቅስ

09 Nov, 17:18


ለቀላል ሕይወት አትጸልዩ....

SHARE||@tksa_tks