PROUD_MUSLIM @proud_muslim Channel on Telegram

PROUD_MUSLIM

@proud_muslim


#ولا_تجعل_الدنيا_أكبر_همنا

PROUD_MUSLIM (Arabic)

تعد قناة PROUD_MUSLIM على تطبيق تيليجرام وجهة مثالية للمسلمين الذين يبحثون عن مصدر للإلهام والتشجيع في حياتهم اليومية. يهدف هذا المساحة الرقمية إلى توفير مضمون إيجابي وملهم يساعد المتابعين على تعزيز إيمانهم وتعزيز وجودهم كمسلمين فخورين. يتضمن المحتوى المشارك في القناة اقتباسات من القرآن الكريم والحديث النبوي الشريف، بالإضافة إلى نصائح وتذكيرات للتأمل والتفكير العميق في القيم الإسلامية. بالاضافة الى ذلك، تشارك PROUD_MUSLIM تجارب وقصص ناجحة لأفراد آخرين يعيشون حياة إسلامية ملهمة. سواء كنت تبحث عن دعم للحفاظ على علاقتك بالله أو تحتاج إلى دفعة للتفكير الإيجابي، فإن قناة PROUD_MUSLIM هي المكان المثالي للعثور على الموارد والدعم التي تحتاجها. انضم اليوم للحصول على جرعة إيجابية تدعمك في رحلتك الروحية كمسلم فخور.

PROUD_MUSLIM

20 Nov, 06:05


በአለማችን ውዱ መህር ኡሙ ሱለይም
ለ አቡ ጠለሃ የጠየቀችው እስልምናን
ነበር ።

ኡሙ ሱለይም መህሯን እስልምና
አድርጋ፣ ባሏን በእስልምና አንፃ
በመጨረሻም ለብቸኝነቷ ሳትሳሳ
ለእስልምና ስትል ውድ ባለቤቷን
አሳልፋ ሰጥታለች።


@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

19 Nov, 09:55


እንደ ጥላቻ ቀላል ነገር የለም
ውዴታ ትልቅ ነፍስና ትልቅ ትግስትን ይጠይቃል!
❤️
@Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

18 Nov, 10:56


@STRONG_IMAN

PROUD_MUSLIM

17 Nov, 18:46


ሕይወታችንን በተውበት እናድስ!
በኃጢዓታችን ምክንያት ተስፋ አንቁረጥ ፤
የሰው ልጅ በተፈጥሮ ተሳሳች ሲሆን
አላህ ደግሞ ንስሐ የሚገቡትን ይወዳል

فتوبوا الى الله ان الله تواب الرحيم

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

17 Nov, 12:07


ዓለም ውሸት ነች እኛ ደግሞ
በዚች ዓለም ውስጥ እውነት
ለመሆን የምንሞክር ተዋንያን ነን....

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

17 Nov, 06:27


#ሰው ሰውን አያኖርም
SO ለሰው ሳይሆን ለአላህ እንኑር❤️

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

16 Nov, 07:20


ነፃነት ይመስላት ነበር
ነገር ግን የሚጠብቃትን ነገር እንዳጣች አላወቀቺም...

@Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

16 Nov, 07:19


ህይወትህን ከራስህ ውጪ እንዲያስውብልህ አትፍቀድ
ምናልባት ከጥቁር ቀለም ውጪ ላይኖራቸው ስለሚችል!
@Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

16 Nov, 05:42


"በዚያ በአሸናፊው እና አዛኙ (ጌታ) ተመካ።"

ባለህበት ሁሉ ያይሃል፣
ይቆጣጠርሃል፣ ይከታተልሃል።

PROUD_MUSLIM

15 Nov, 18:09


የጠፋው አህያ

አንድ ጊዜ ነስሩዲን አህያዉ ጠፍቶበት ጫካ ዉስጥ ሲፈልጋት ቆየና የሆነ ነገር ትዝ ብሎት ድምፁን ከፍ አድርጎ ፈጣሪዉን አመሰገነ፡፡ ከዛም አጠገቡ የነበረዉ ጎረቤቱ ‹‹የት አለች አህያህ ተገኘች እንዴ?››ብሎ ሲጠይቀዉ ነስሩዲንም ‹‹አልተገኘችም የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ ነዉ፡፡›› አለዉ፡፡ ጎረቤቱም ‹‹ምን ትዝ አለህ?›› ብሎ ጠየቀዉ፡፡

ነስሩዲንም ‹‹እንኳንም ዛሬ በእግሬ ሄድኩ፡፡ አህያዬ ላይ ተቀምጬ ቢሆን ኖሮ እኔም አብሬ እጠፋ ነበር፡፡ እንኳንም ብቻዋን ጠፋች😁



@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

14 Nov, 17:01


የሙስሊሙ መመሸጊያ። የከፍታቸው መፍለቂያ። ልጆቿን በስደተኞች ካምፕ ታቅፋ በኢስላም ዕውቀት አንፃ ሸሂድነትን ደጋግማ የምታወሳ "በኢስላም የመጀመርያዋ ሸሂድ ማን ናት?!" ብላ ትጠይቃለች እየተሽቀዳደሙ "ሱመያ ሱመያ" ይላሉ። የማወራችሁ ስለነዚያ ብርቱዎች የተቸከለ ኢማን በልባቸው ስለታቀፉት ፍልስጤሞች ነው!

ደሜ ፍልስጤማዊ መኖርያዬም ጋዛ ነው ይላል ሊሳነል ሐላቸው። ከረጅም ሄል ጫማ ተራርቀው የዕውቀትን ዝናር ታጥቀው የወራሪዋን ወታደሮች ለመጋፈጥ በቸነፈር መሐል ይታገላሉ። በትጥቅም በዕውቀትም ይፋለማሉ።

ማንነቷን ለመነጠቅ ፈቃደኛ ያልሆነች... በጦርነት ታሪክ ያልተሰበረች... በጥንካሬዋ ቆማ ሚሳኤል ሳያሸብራት በንፁህ ልቧ ልጆቿን በዕውቀት ትጠብቃለች። አላህ አላህ በሉ እያለሽ ታስታውሳለች። ስለነፃነት እያስተማረች ስለፍትህ ሰብካ የመስጂደል አቅሳን ፍቅር በውስጣቸው ታሰርፃለች።

ሁሉም ያውቃታል! እርሷ ፍልስጤም ነች

አፈሯን በሸሂዶች ደም ያጠጣች... ጠላቶቿን ለመደምሰስ በድንጋይ ጥይት የሰራች... የፅናትና የትዕግስት ማማ! በቀይ የተነከረች አርማ! በአረንጓዴ መሬቷ ነጭ ጽጌረዳዎቿን ዘርታ በታማኝ ሙጃሂዶቿ እንክብካቤ፣ ከፍርስራሽ ስር በተቀበሩ ንፁሀን ልጆቿ ያደገች ፅኑ የማትበገር የማትሰበር ሀገር!

ሁሉም ያውቃታል...

ወድቃ መነሳት ታውቅበታለች። አፈር ልሳ መቆም ተክናበታለች። በችግር በቸነፈር ለማለፍ የአላህን ስም ትዘክራለች። ሥሯ በአውሎ ነፋስ እንኳ አይናወጥም ...

ፍልስጤም ሆይ...
ከሀገረ ሐበሻ እንባ ባቀረረው እይታ ዘወትር እየተመለከትንሽ አላህ ያፅናሽ ከማለት አልቦዘንም።

Mahi Mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇👇
@STRONG_IMAN

PROUD_MUSLIM

13 Nov, 18:48


አሰላሙ አለይኩም የቻናሌ  ቤተሰቦች❤️

እስካሁን አብሮን የቆየው  *መከረኛው ደንች ቤት  * የተሰኘው ታሪክ ተጠናቀቀ🤩🥳 እንዴት ነበር?  ምን ተማራቹበት ፡፡  በታሪኩ ላይ ያላቹን አስተያየት ኮሜንት ስር አስቀምጡልን
        🥰

PROUD_MUSLIM

13 Nov, 18:29


ቤተሰብም ላማክር ነገ ወደ ባህርዳር እመለሳለሁ አልኩት ፡፡ እነ ሀፍ ንግግራችንን ተጠባብቀው መጡ ቴክስት አድርጎላቸው ነበር ትንሽ ቆይተን ወደ ደሴ ተመለስን

ለነገ ወደ ባህርዳር የ አውሮፕላን ትኬት ቆርጠን ወደ ቤት ተመለስን ....አየር ማረፊያዉ ኮምቦልቻ ሲሆን የሚጠቀምበት ግን የደሴ ከተማ ነዋሪ ናቸዉ የአዉሮፕላን ትኬቱ የሚቆረጠዉ ደሴ ላይ ነዉ፡፡ደሴ እና ኮምቦልቻ የተያያዘ የሚወደዱ በትዳር የተጣመሩ የ25ደቂቃ መንገድ የሀገረጎ መንገድ ነዉ የሚለያቸዉ፡፡ የአዉሮፕላን ትኬቱን ሳዳም ነው የከፈለልኝ የዛሬዋን ቀን አድሬ ጠዋት ላይ ሳዳም እና ሀፍ ኮምቦልቻ አየር መንገድ ሸኝተዉኝ ወደ ባህር ዳር ተመለስኩ

ባህርዳር ከደረስኩ ቡሀላ ሳዳም ያለኝን በሙሉ ከልቤ ሁኜ መተግበር ጀመርኩ ግን ይቅርታ ለማድረግ ተቸገርኩኝ ግን ቀስ በቀስ ለአላህ ብየ ሁሉንም ነገር ስተውና ማድረግ ስጀምር ነገሮች እየቀለሉልኝ መጡ፡፡ አሁን ከደሴ ከተመለስኩ ዛሬ ስድስተኛ ወሬ ነው ከሳዳም ጋር ሁሌም ነው የምናወራው በጣም በሳል ልጅ ነው ፡፡

አንድ ቀን መጥፎ ሽታ ሸቶኝ አፍንጫየን ጥቅጥቅ ልቤን እፍን አደረገኝ፡፡ ህመሙን መቋቋም አልቻልኩም አባቴ ባህርዳር የሚገኘዉ ሪፈራል ሆስፒታል ወሰደኝ፡፡ ሁለት ቀን መተኛት አለብሽ ተብየ ተኝቼ መታከም ጀመርኩ .መድሀናቴን እየዋጥኩ ነዉ....
....ዶክተሩም ሙሉ ምርመራ አደረገልኝ፡፡ ከዛም ምን እንደተሰማኝ አላቅም እንደገና የHIV ምርመራ ማረግ እፈልጋለሁ አልኩት
....አባቴም አይ ሀሊማ ለምን ትጨነቂያለሽ አትሰቢ አላህ ያለዉ ሁኗል አለኝ
....እኔም እንደዉ ዝም ብየ ልመርመር ብየ ነዉ አልኩት
.......ዶክተሩም እሺ ብሎ የHIV ለመመርመር ደም ወሰደ

ዉጤቱ ሲመጣ ግን ያልታሰበ ነገር ሆነ የሚአጅብ ነዉ ሀላሊ HIV በደምሽ የለም አለኝ ዶክተሩ
....ማመን አቃተኝ በጣጣም የደስታ ጩኸት ጮህኩኝ
......እርግጠኛ ነህ?? አልኩት
......አዎ የለብሽም አለብሽ ያለዉ ሆስፒታል ዉጤት ተሳስቶባቸዉ ይሆናል አለኝ
.....ማመን አልቻልኩም በደስታ ልቤ ሊፈነዳ ሲወጣ ሲገባ ይታየኛል፡፡ ከዛም አባቴ ነገ ስንወጣ አለብሽ ያሉኝ ሆስፒታል ሄጄ እመረመራለሁ ብየ አንገቱ ላይ ጥምጥም አልኩበት፡፡ የደስታ እንቅልፍ አልወስደኝ አለ

የማይነጋ የለም ነጋ ቀጥታ HIV አለብሽ ወዳሉኝ ሆስፒታል ሄድኩ ፡፡ ሌላ ሀኪሞች አገኘሁ ...ከዛም ስመረመር ዉጤቴ ሲመጣ HIV የለብሽም አሉኝ....
.....ደስታየን መቆጣጠር አቃተኝ ተደሰትኩ አባቴ ጋር ተቃቅፈን ማልቀስ ጀመርኩ፡፡
አባቴ ተናዶ እንዴት በስነስርአት አይመረምሩም ብሎ የሆስፒታሉ ሀላፊ ጋር ሂዶ ተናገረዉ ሁሉንም አስረዳዉ፡፡
የሆስፒታሉ ሀላፊም ይቅርታ እንደዚህ ያለ የህክምና ስህተት አንዳንዴ ይፈፀማል ..ግን ይሄ ከባድ የህክምና ስህተት ነዉ ይቅርታ አለዉ
....ለሀፍ እና ለሳዳም ደዉየ ነገርኳቸዉ ደስታ፡በደስታ ሆኑ ...ሳዳም ግን ከነማንነቴ ተቀብሎኝ ነበር

ለማማና ባባም ስለሳዳም ነግሪያቸው ተስማምተውልኛል ፡፡ ሀምዛም ወደ ደሴ የሚሄድበት የጀመአ ፕሮግራም ነበር ሳዳም ጋር ተዋዉቀዉ ተግባብተዉ እነሱን መረጠልኝ፡፡ በዚ መሀል አንድ ቀን አዩብ ሱቅ ድረስ መጣ በተናገረው ንግግር እንደተፀፀተና መልሶ ሊያገባኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ
..... ለ ማይረባ ደም ብሎ እኔንና ቤተሰቤን አቁስሎን የሄደ ሰው መልሼ ላግባ ማለቱ ምን ያለ ድፍረት ነው?? ሰው እንዴት ተፍቶና ጥሎት የሄደውን ያውም ተጠይፎት የሄደውን እንዴት ሊመልሰው ይሻል??

የሳዳም ቤተሰብና የኔ ቤተሰብ ተነጋግረው ፈቲ በሁለተኛ አመቷ ህክምናዋን ጨርሳ ለኔ ሚዜ እንድትሆነኝ እፈልጋለሁ ስላልኩኝና መውጫዋ ጊዜ አራት ወር ስለቀረው በዛ ተወሰነ


አልሀምዱሊላህ ፈቲ ከአእምሮ ማገገሚያ ሆስፒታል ህክምናዋን ጨርሳ ከአዲስ አበባ መጣች፡፡ ፈቲ ስትወጣ አምሮባት የፈቲ ወዝ ተመልሷል፡፡ ፈቲም የተወሰነ ግዜ ተቸግራ እንደነበርና አሁን ከበፊቱ ለውጥ አምጥታ የማእከሉ ሁሉ ተሸላሚ ነበርኩ..ቁርአን መቅራት ሶላት መስገድ ጀምሪያለሁ አለችኝ

የእኔ እና የሳዳም ሰርግ ቀን ደረሰ ....ድል ባለ ሰርግ ደሴ ላይ ተደግሶ ዘመድ አዝማድ ከባህርዳር ደሴ ድረስ መጥተዉ ተጋባን ... ልቤ ሲመኘው ..የነበረን ልጅ አገኘሁ አልሀምዱሊላህ

ሙሸራችንን ከጨረስን ቡሀላ እኔ ፈቲ እና ዉዱ ባለቤቴ ሳዳም ሁነን ማማየን ልንዘይር ወደ አዳማ ከተማ ሄድን ፡፡ ማማየ ቤት ስንሄድ ደስታ አልጠበቀንም ማማየ ሙተው ነበር ያገኘናቸዉ አለቀስን ፈቲም ብታለቅስ ብታለቅስ ሊወጣላት አልቻለም ማማየ አሁን አንቱ የምፈልጓት ሰዉ ሁኛለሁ ተቀይሪያለሁ ብትል ማን ሰሚ አለ ወደ ማይመለስ አኼራ ሂደዋል፡፡ በጣጣም አዘን ለዚች ተራ ህይወት ነበር እንደዚህ የምንሆነው...ማማየ ሁሌም ቢሆን በልባችን አሉ ...ጥሩ የሰራ መቼም ቢሆን ከልብ አይወጣም አጂብብብብብብብብብብ
#መከረኛው_ድንች_ቤት
......#ተ....... #ፈ..........#ፀ........ #መ

@Proud_muslim
@Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

13 Nov, 18:29


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
     የመጨረሻዉ ክፍል


የማይታመን ተአምር ይሆናል ብየ ያልጠበኩት በፍፁም ያላሰብኩት ነገር ከመሸ ስለሆነ የገባነው ደክሞኛል ውስጤን ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ዋጠኝ ድንጋጤ,ደስታ,እቀፊው እቀፊው እቀፊው የሚል ስሜት እቅፉ ግቢና መልካም ጠረኑን አሽቺ ናፍቆትሽን አስወጪ የሚል የልብና አእምሮ ትዛዝ ብዙ ሰአት በድንጋጤ ደርቄ ቁሚያለሁ.... በስስት አይን አይኑን አያለሁ
.... ሀፍ ሀሉ ምን ሁነሽ ነው?? ንቂ እንጅ አንቀላፋሽኮ ብላ በኔና በሱ ሳቅ ብላ ይዛኝ ሄደች

ግን እንዴት ሳዳም እዚህ ቤት ተገኘ ለምን ዘመድ ነው?? ወይስ የሀፍ ወንድም ነው?? ምን ይሰራል እዚህ?? ቆይ ግን ያኔ ምንድን ነበር መልክቱ ሊሰጠኝስ የነበረው ??ወረቀቱ ምን ነበረ ??ቆይ ያልተፈታልኝ ሚስጥር ምንድን ነው ??ከኔ የተደበቀው ነገርስ ምን ይሆን ??ግራ በመጋባት ውስጥ ሆንኩኝ

ሀፍስን ስለ ሳዳም ልጠይቃት ፈለኩኝ ግን ገና ከመግባቴ ምን ይባላል ብየ ዝም አልኩኝ ..ሻወር ወስጄ ሰግጄ ራት ተብለን ሳሎን ገባን ሁሉም ተሰብስቧል ፡ታላቅ ወንድሟ አባቷ እናቷ ሁሉም አሉ

ሳዳም ግን ከእነሱ መሀል የለም ለምን የለም?? የዚህ ቤተሰብ አካል ከሆነ አሁንስ የት ሄደ?? ስለሱ ብቻ ማሰብ ጀመርኩ
ትንሽ ቆይተን በራፍ ተቆርቁሮ አሰላሙ አለይኩም ብሎ ገባ ሳዳም ነበር ... እናቷና ሀፍ ለኔ ሲሉ ለብቻችን ሱፍራ አድርገን መብላት ጀመርን ...ቀና እያልኩ ሳዳምን ሳላስባንን አይዋለሁ... ሁለታችንም ፊት ለፊት ተገጣጠምን ልቤ ስንጥቅ ልትል ደረሰች... የያዝኩትን የእንጀራ ጉርሻ ለቅቄው ትሪው ላይ ወደቀ እኔ ምን እየሆንኩ ነው እጄ መንቀጥቀጥ ጀመረ ...ሀፍሳ ለኬ ምሰራውን ነገር በደንብ እያየች ነበር ሌላ ጥፋት ሳላጠፋ በቃኝ ብየ ብነሳ የተሻለ ሀሳብ ነው ብየ ልነሳ ስል... የደሴ ሰዎች እንድትበሉላቸው ያላቸው ፍላጎት ልዩ ነው እነሱ ሳይበሉ ቢቀርባቸውና እንግዳቸው እንዲበላ ያላቸው ፍላጎት ልዩ ነው የምር የሆነ ፍቅርና ርህራሄ ነው የሚያሳዩት በሞተ ብላ አይሆንም አትነሺም አሉኝ እኔም ትንሽ በልቼ ተነሳሁ በቃ ፍቅር ናቸው

እኔም ደክሞኝ ስለነበር ተኝ አሉኝ ተነስቼ መኝታ ቤት ገባሁ ከ ሀፍ ጋር የሌለ ወሬ አወራን፡፡ ስለ አዩብም ነገርኳት ...በዛውም ትልቅ ሚስጥሬን የተፈጠረዉን Hiv እንዳለብኝ ነገርኳት፡፡ ሁለታችንም ተላቀስን በጣም ስለመሸ ተኛን፡፡ መተኛት ግን አይደለም የተኛሁት ሳዳምን አንድ ቤት ቁጭ ብለን በደንብ አየሁት እሱን እያልኩ እያሰብኩ ያላሰብኩት እንቅልፍ ወሰደኝ ፡፡ ሱብሂ ተነስተን ሰግደን አርፍደን ስለተነሳን ቁርስ በልተን ከቤት ወጣን እንደተለመደው አብረን ስንዞር ውለን የደሴን ናፍቆት አስወጥቼ ሀፍ የምትማርበትን ትምህርት ቤት ካየሁ ቡሀላ አሱር አካባቢ ተቋም የሚገኘዉ ኡስታዝ ጠልሀ መስጊድ ሰግደን .....ሻይ እንጠጣ ተባብለን ወደ ደሴ መውጫ አካባቢ ወዳለ መዝናኛ ወስዳኝ የደሴን ንፁህ አየር እየተቀበልን በመናፈሻው ውበት ተገርሜ የምታወራኝ ትልቅ ነገር እንዳለ አስረዳችኝና በ ትግስት እንዳዳምጣት ነገረችኝ
......በመስማማት በሚመስል መልኩ ራሴን ነቅነቅ አደረኩላት
......ከዛ በፊት ግን ስለ ሳዳም ጠየኳት ምንሽ ነው??? አልኳትከት
ከት ብላ ስቃብኝ እኔም ስለሱ ነው ማወራሽ እና አዳምጭኝ አለችኝ //////ሳዳም ታላቅ ወንድሜ ነው በጣም እወድዋለሁ ሚስጥሩን አይደብቀኝም እኔም አልደብቀውም እናም አንድ ቀን ያኔ ህመሜ ብሶብኝ ከግቢ የተመለስኩ ግዜ ፎቷችንን እያየሁ የአንችን ፎቶ አሳየሁትና ስለ አንች ብዙ ጠየቀኝ ፡፡ ቆንጆ እንደሆንሽና እንደወደደሽ ነገረኝ ....ከዛም ወደ አዳማ መቶ ሊያገኝሽ እንደሚፈልግ ነገረኝ

እኔም ራሴ የፃፍኩትን የጓደኝነት ደብዳቤ ሰጠሁት፡ አዳማ ሲገባ በስልክ እናወራ ነበር እና ድንች ቤቱ አካባቢ እንዲሄድ ስነግረው ቀጥታ ሄደ አንች ዜብራ ላይ መኪና ልትገጭ ብለሽ ራስሸን ስተሽ ስትወድቂ ወደ ሆስፒታል ወሰደሽ
....ከዛ ቡሀላ ያረገልሽና ያወራቺሁትን ነገር ይነግረኝ ነበር ....ያኔ ለኮንግራሽ የመጣን ቀን ሆቴል እንያዝ ሲባል ሳዳም የጋበዘሽ ሆቴል እንደምትጠሪልኝ ተስፋ አድርጌ ነበር ፡፡
ከዛ ቡሀላ አንች እኔንና ሴቱን ሁላ ከጥቅም ውጭ ስላደረገን ሄኖክ ነግሬው ነበር ተከታትሎ ደበደበውና ታሰረ...... ከዚ ቡሀላ የምትነግረኝን ነገር በ እንባ አጅቤው ነበር ማዳምጣት እሱ ለኬ ያውቀኝ ነበር ከዛ ታላቅ ወንድሜ ዋስ ሁኖ አስወጣው ለሄኖክ መታከሚያ ብርም ከፈልን ከዛw ቡሀላ በቃ ወሬው ሁሉ ስለ አንች ሆነ ፡፡ እናም ከፈቲ ሁሉንም መረጃ አግኝቷል በሄኖክ መደፈርሽን ጭምር ያውቃል፡ ፈቲን አሳምኖ በሱሷ ሰአት ሚስጥር አስወጥቷት ነበር ከዛ ቡሀላ ሊያገባሽ ወሰነ፡፡

እናም አሁን ያስመጣውሽ ልመረቅ ሳይሆን ከ ሳዱ ጋር እንድታወሩ ብየ ነው አለችኝ
......በፍፁም ምንም ማውራት አልፈልግም፡ እኔ ስንት ሚስጥሬን ነግሬሻለሁ በሽተኛ ነኝ ላገባው አልችልም አልኳት ፡፡ ያንች ወንድም መሆኑን ባውቅ ለራሱ አላወራም ነበር ወላሂ ወድጄዋለው ግን አይሆንም ብየ ለቅሶየን አባስኩት ቆይ እኔ ሚስጥሬን እየነገርኩሽ በሽተኛ መሆኔን እያወቅሽ እንዴት ለምትወጂው ወንድምሽ ትመኝኛለሽ ??በፍጹም አላደርገውም ሳዳምና አንችኮ ለኔ ከምንም በላይ ናችሁ ስለዚህ አላስበውም ህይወቴን ያተረፈልኝን ያንችን ወንድም ለኔ ደግሞ ልዩ የሆነን ወንድ አግብቼ ህይወት ማበላሸት አልፈልግም ለአላህ ስትሉ ተውት ይህንን ሀሳብ ሳዳምም ከኔ የተሻለች በጤናዋ ንፁህ እና ቢክራ ሴት ትገብዋለች እኔ ከምኑም የለሁበትም ከጤናየም በሽተኛ ከንፅህናየም ዝርክርክ ሰይባ ነኝ፡፡ ስለዚህ እኔ ለሳዳም አልገባም ብያት ተነስቼ መኪናው ውስጥ ገባሁ

ሰአቱ መሸ መግሪብ አካባቢ ወደ ቤት ገባን ምንም እንዳልተፈጠረ አስመስለን አመሸን ፡፡ሳዳም ኢሻ ሰግዶ ነው የሚገባው ቤት ገብቶ ሁላችንም ትንሽ አውርተን ተኛን፡፡ መኝታ ቤት ሁኜ ነገሮችን ማሰብ ጀመርኩ አዳሬን ሁሉ ስለ ሳዳም ብቻ ማሰብ ሆነ ስለ ሀፍ ንግግርና ህመምተኛ መሆኔን እያወቀች ለወንድሟ እኔን መምረጧ ገረመኝ ፡፡ ብቻ ባህር ዳር ሱፐር ማርኬቱን ዘግቼ ስለመጣሁ መመለስ አለብኝ አልኩኝ በተጨማሪም ማራዘሚያ መድሀኒቴ ሊያልቅብኝ ስለሆነ መመለስ አለብኝ ብየ አሰብኩ

ጠዋት ተነስተን ቁርስ በልተን ከቤት በሳዳም መኪና ወጣን ሀይቅ ዳር ወይም ኮንቦልቻ እንሂድ ሲባል ኮንቦልቻ ተመርጦ ሄድን ሀፍና ወንድሟ እኔና ሳዳምን ትተውን ሄዱ
...ኮምቦልቻ የሚገኘዉ ግሪን መስክ የተባለበት ቦታ ነበር ፡፡ ሳዳም ጋር ሰላምታ ተለዋውጠን ብዙ ነገር አወራን ስለአለብኝ በሽታ ጭምር
.....አንች በዱአ በርች ሲከፋሽና ስትቸገሪ ብቻ ሳይሆን መስገድ ያለብሽ በማንኛውም ቀን የለሊት ስግደትሽን ቀጥይ የበደሉሽን ሰዎች ሁሉ ይቅር በያቸው ለአላህ ብለሽ አውፍ በያቸው ሄኖክ ፈቲያ ባለ ድንች ቤቷ ሌሎቹንም ከልብሽ ይቅር በይ ሲቸግርሽ ብቻ ለይል አላህ ፊት አትቁሚ በሽታዉ ቢኖርብሽ ዋናዉ፡ፍቅሩ ነዉ እኔ blood O ነኝ ብቻ ወደምንወልደዉ ልጅ እንዳይተላለፍ ክትትል እናረጋለን.... ከዛ በፊት ግን ብንጋባና በአላህ መንገድ ላይ ብንጓዝ የተሻለ ይመስለኛል ብሎ ዝም አለ

ንግግሩ እንዴት ቀልብ ይስባል እይታውና ምክሩ እንዴት ይማርካል ምን አይነት ስብእናን ነው የተላበሰው?? አጂብ ይህ የንግግር ቺሎታ ግን በዘር የተላለፈ ይመስለኛል ከሀፍ ጋር ያመሳስላቸዋል

እኔም ሳዳም ፍቀድልኝ 👇

PROUD_MUSLIM

13 Nov, 18:23


የመጨረሻው ክፍል ከ 7 ደቂቃ ቡኋላ🤚

PROUD_MUSLIM

13 Nov, 09:25


መከረኛው ድንች ቤት
የመጨረሻው ክፍል ዛሬ ማታ ይጠብቁን
@STRONG_IMAN

PROUD_MUSLIM

13 Nov, 09:23


« የሆነ ሰዓት ይደክምሀል። ተነሳሽነትህ ይወርዳል። ጠብ እርግፍ ስትልላቸው የነበሩ ጉዳዮች ምንም ይሆኑብሀል። የስልቹነት በትረ ስልጣኑን ትቆናጠጣለህ። ምንም ለማድረግ ያስጠላሀል። ስለሚሰማህ ስሜቶች ለመግለፅም ለማስረዳትም ግራ ትጋባለህ።
የሆነ ጊዜ ላይ ለብዙ ዘመን የረሳኸውን ልብህን ስታገኘው፣ ሰዎችን ተደግፈህ ያለምከው ህይወት እንዳልሆነ ሲሆን፣ ብዙ ፍሬ ያፈራሉ ብለህ ባልካቸው ሩጫዎች ውስጥ ሮጠህ ውጤቱ እንዳሰብከው ሳይሆን ቀርቶ ፋይዳ የሌለው ነገር ሲሆንብህ የመጥፎ ስሜቶች መናኸርያ ትሆናለህ።
ይህ ህይወት ነው እራስህን እያስታመምክ ካልሆነ የማትኖረው። ጮክ ብለህ ለማልቀስ እንኳ ሰዎችን ልትሳቀቅበት የምትችልበት ይህ ህይወት ነው። ካላሰብከው፣ ካልጠበቅከው በኩል የምትጠገንበትና የምትደሰትበት ይህ ህይወት ነው። ፈፅሞ የማይገባህን እና ልታልመው የማትችለውን ማንነት ተላብሰህ ልትገኝ ትችላለህ።
በቃ ስትዝል፣ ስብርብር፣ ድክም ስትል እንደምንም ሞተህ ተሟሙተህ ወደ ጌታህ ሽሽ። ነፍስያህ ብትታገልህም እንደምንም እየዳህክ ወደ አላህ ተንፏቀቅ። አስቀያሚ ስሜቶችህን ነክሰህ፣ መራር እውነታዎችህን ውጠህ፣ ቁስሎችህን ይዘህ፣ አፈር ድሜ ልሰህም ቢሆን ወደ አለህ ለመሸሽ ሞክር።
አንዳንዴ ሰዎች መዛልህን መድከምህን ስታረዳቸው የበለጠ ሊቀብሩህ ይችላሉ። የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታልና ምንም እንኳ መጥፎ ስሜቶች ቢሰሙህም ጨርሰህ ሰዎች ላይ አትውደቅ። ለግራ መጋባትህ መፍትሄው ለመረዳት ግራ ካጋባህ ጌታህ ዘንድ ነውና እየተጨማለቅክም ቢሆን እርሱ ጋር ተሸሸግ። ወደድክም ጠላህም ፈልገኸውም ብትሄድ፣ ሳትፈልገውም ብትሄድ የሚያዝንልህ አላህ ብቻ ነው። የምወድህዋ አብሽሩ! ሰላም ለልብህ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@STRONG_IMAN
@STRONG_IMAN

PROUD_MUSLIM

12 Nov, 18:12


አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ላይ
ተሰፍ መቁረጥ አለባቹ እናንተ ሰለማታስብላቸው ሳይሆን እነሱ መረዳት ስላቃታቸው ነው 😔🥺

PROUD_MUSLIM

12 Nov, 17:54


እህህ who is ready for የመጨረሻው ክፍል

PROUD_MUSLIM

12 Nov, 17:50


ማንም ላይ ተማምነሽ
በሙሉ ልብሽ አትደገፊ
ዞር ሲሉብሽ ልትወድቂ ትቺያለሽ❤️‍🩹


@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

12 Nov, 16:26


ልብ ልብን ሲውድ አይን ነውርን አያይም 😔💔

PROUD_MUSLIM

12 Nov, 15:08


አንዳንዴ ከምንፈልገው ቦታ ለመድረስ
አሳማሚ እንቅፋቶችን ረግጦ ማለፍ
የግድ ይሆናል


@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

11 Nov, 17:01


የመጨረሻው ክፍል እሄ post 15 share ካገኘ ቶሎ ይለቀቃል

PROUD_MUSLIM

11 Nov, 17:00


🥰ተጀመረ   ተጀመረ   ተጀመረ  🥰

#መከረኛው ድንች ቤት ❤️

አብዛኛው ጊዜ በየቻናሉ ታሪክ ይደጋገማል በቃ ወሬ አላበዛም አዲስ በ PROUD MUSLIMS Channel ብቻ ያለ ድንቅ ታሪክ ....
ሰው ሁሉ በጉጉት እየጠበቀ ነው ሚያነበው መቼስ እንድታምኑኝ ወላሂ ምናምን አልልም ገብታቹ ብቻ አንብቡት ደስ ሚል ታሪክ ነው
OPEN የሚለውን ስትነኩ ወደ ክፍል 1 ይወስዳቹኋል✌️

PROUD_MUSLIM

11 Nov, 16:19


መጡም አይጠቅሙኝም ቀሩም አይጎዱኝም እኔ አላህን ይዤ እየሰራው ነው!🙌
@Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

11 Nov, 05:46


"የእናታችሁን ነገር አደራ"።

❪ረሱል ﷺ❫


@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

10 Nov, 17:50


የሳዳምን መኪና አየሁ ...ግራ እየገባኘ ምንም ሳልል እቤት ገባሁ......ቤት ገብቼ የሳሎን ቤት በራፍ ላይ ሳዳምን አገኘሁት...በጣጣጣም ደነገጥኩ የማይታመን ተአምር ሆነብኝ አፌ ተያያዘ የምለዉ አጣሁ ጭራሽ ማመን አልቻልኩም..........

#የመጨረሻዉ_ክፍል እና የታራኩ ማጠቃለያ ፁሁፍ

ከ 100👍 ቡኋላ
ይ............ቀ..............
..........ጥ...........ላ.................ል

@proud_muslim
@proud_muslim

    

PROUD_MUSLIM

10 Nov, 17:49


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 2⃣4⃣


ሁላችንም መተያየት ጀመርን ቤተሰብን ከቤተሰብ ለማለያየት ልጅን ከእናት እና ከአባት ለመለየት ወኔውና ድፍረቱ ኑሮት የሚያወራው ማነው በሂክማ የተሞላውና ንግግሩ ሽጉጥ ያቀባበለ ሠውን እንኳን አቀዝቅዞ ደስታና ተስፋ መሙላት ሚችለው የባባን ምላስ ማን ያዘው ??ምንስ ሲሆን ዝም አሰኘው?? ወንድ ነኝ ያለን ሰው በጉልበቱ ዝም የሚያሰኘው አትንኩኝ ባዩ ወንድሜ ሀምዛ ምንአይነት ጦረኛ ነገር አጋጠመው?? ማንኛው ሀሺም ዝም አስባለው ከፈቲ በላይ ልጇ እምመስለው እኔ ከ ማንም በላይ የምቀርባት እኔ ልጅሽ ፈቲ እንደዚ ነች የኔንም ህይወት አበላሸች ብየ እንዳልነግራት የትኛው ሸይጣን ዛሬ መልካምና ቅን አሳቢ ሁኖ ዝምታን አስመረጠኝ ከንግግር ይልቅ በተግባሯ ሰውን ታስተምራለች ምትባለዋ እናቴ በየተኛው የንግግር ተግባር እንደዚ ነው ብላ ትንገራት ሲበዛ ብልጥና ሩቅ አሳቢ ነች የምትባለዋስ የጀግናው ወንድሜ ሚስት ራውዳ ምን አስፈዝዟት ??ዝም አለች በየትኛው የብልህ ቋንቋ ትንገራት ምን ያለ ውዝግብ ያለ ቀን መጣ

የተደወለላትን ስልክ አውርታ ከጨረሰች ቡሀላ ወደኛ ዘወር ብላ አታወሩም እንዴ ??ምን ተፈጥሮ ነው በአላህ?? ዝም አላችሁ እኮ ብላ ወሬ በራሷ ግዜ ፈጠረች ብዙ ስናወራ ቆይተን ለዝሁር ሰላት ተነሳንና ሰግደን ምሳ በልተን ባባ ሊነግራት እየተዘጋጀ
____ፋጢማ አንድ የምናወራሽ ትልቅ ነገር አለ በትኩረት እንድትሰሚኝ እፈልጋለሁ የማወራሽን ነገር እስክጨርስ ድረስ እንዳታቋርጭኝ ብሎ ሲተነፍስ የትንፋሹን ግለት አስመስሎ ከነገራት ቡሀላ ምን ሊፈጠር እንደሚችል እያሳሰበኝ ይፈጀኝ ጀመር ውስጤ ምነው ባላወራ ብሎ ግማሽ የአካሌ ክፍል የሆነው ልቤ ሲመኝ አእምሮየ ግን ይንገራትና ከጭንቀቴ ልዳን ልገላገል ይላል ፡፡ የምነግርሽ ነገር ስለ ልጆቻችን ነው ቤተሰብ ሁነን ከዛም በተረፈ ጎረቤታሞች ሁነን በአንድ ሰፈርና በአንድ ጉርብትና ስንኖር የነበረው ለኛ ፍቅርና ለልጆቻችን የወደፊት ስኬት በማሰብ ነበር ፡፡ አንዷ ለአንዷ ከለላ ትሆን ዘንድም ዱአችን የላቀ ነበር ህይወትን እስከ መስጠት መስዋትነት እንዲከፍሉም ምክራችን ነበር..... አልሀምዱ ሊላህ ይህንን ሁሉ አልፈው ለዩኒቨርሲቲ በቁልን አዛም የቻሉትን ያክል ተጠባብቀዋል ሰይድና እኔ ከድሮ ጀምረን ስንጠባበቅ ኑረን እዚ ደርሰናል
ከናንተው ከእህት አማቾችም ልጆችን አፍርተን በዱንያችንና በዲናችን የተከበረውን ቤተሰብ አፍርተናል የኛም ልጆች ይህንን ነው ያደረጉት አሁን ግን ከምንግዜውም በላይ የከበደውን ፈተና ልንጋፈጥ ከፊት ለፊታችን ቁሞብናል ስለዚህ በአንድነት ልንጋፈጠው ግድ ይለናል..... ለሰይድም ቅድም ደውየለታለሁ እስካሁን ይመጣ ይሆናል ከማለቱ ሰይዴ በራፍ አንኳክቶ ገባ ፡፡ ማሻ አላህ ብሎ ፋዘር ተቀበለውና ከጎኑ አስቀመጠው ትንሽ በስልክ አውርቶት ስለ ነበር ማውራት አልፈለገም ቀጥታ ካቆመበት ቀጠለ
ሀምዛ ስላወራው ነገር አንድ በአንድ ይናገር ጀመር ማማና አክስቴ ማልቀስ ሲጀምሩ እኔም እንባየን መቆጣጠር አቅቶኝ አነባ ጀመር ሁሉም በለቅሶ ድምፅ ተዋጠ ከትምህርት ቤት መባረሯን አለመመረቋን በውሸት የተሰራ እውነተኛ የትምህርት መረጃ እንደያዘች እኔ ሳወራ ቤቱ ለቅሶ ብቻ ሆነ

ካሁን ካሁን ችግር ይፈጠራል ስል ያላሰብኩት ሆነ ምን እናድርግ ??ታዳ ወደሚለው መፍትሄ መጣን፡፡ ብዙ ሀሳቦች ተነሱ

ፈቲን ወደ ባህር ዳር እንድትመጣ እናትሽ ደክማለች ብለን የአዉሮፕላን ትኬት እናስቆርጣት በሚለዉ ተስማማን
.....አባቷ ሰይድ ለፈቲ ደውሎ እያለቀሰ አወራት፡፡ እናቷም እንደደከመች የልጄን አይን ልይ እያለች ስለሆነች ነይቶሎ ብሎ ነገራትና.....እናትሽ የታመመችዉ ህመም ከባድ ስለሆነ ነገ ቀጥታ አውሮፕላን በረራ እንድትመጣ ነግሯት ፡፡ ከዛም ወደ ድርጅቱ ስልክ ደውሎ ለፈቲ በአካውንቷ ብር እንዲያስገቡ ሰራተኞቹን አዞ ....ወደ እኔ ዙሮ የኔ ልጅ በኔው ልጅ በአንችው እህትሽ ይሄ ስለደረሰብሽ አውፍ በይኝ ብሎ አቀፈኝ
..... ልቤ በድንጋጤ ትርትር ልትል ደረሰች ያሰብኩት ሌላ ያላሰብኩት ሲሆን ለቅሶየ ገደብ አጣ፡፡ አክስቴም አቀፈችኝ በለቅሶ ያለፈ ቀን ምን አይነት ቀን ሆኖ አለፈ

ከዛም በመነገታው ጠዋት ላይ ባለፈው ከቤት ስወጣ ጥየው የነበረውን ስልኬን ፈልጌ አነሳሁት ብዙ ሚስኮሎችና ሚሴጆች አገኘሁ ሚሴጁ ጠቅላላ የሳዳም ናቸው ሳያቸው ደስ አሉኝ

ዛሬ አልቻልኩም ፍቅር እንደያዘኝ የገባኝ ስሸነፍለት ነው..ለሳዳም ደወልኩለት አነሳው ድምፁን ብቻ ሰምቼ ዘጋሁበት ውስጤ በሀሴት ተሞላ ምን እየሆንኩ ነው?? እኔንጃ መልሶ ደወለ በደስታ ብዛት ምን ላውራው እንደምንም ብየ አወራሁት በቃ ደስ አለኝ ልዩ ስሜት የተሰማኝ ልዪ ወንድ ስለሆነ ነው ብየ አሰብኩ ከዛ ቡሀላ ምን ላውራቹ በደስታ አበድኩ

ከቀኑ አራት ሰአት ላይ ፈቲ ባህርዳር በአዉሮፕላን መጣች እኔ እና ሰያና ሂደን ከአየር መንገድ ተቀብለናት፡፡ ቤት አመጣናት እናቴን አሳዩኝ ማለት ጀመረች ፡፡ ፈቲ ላያት በጣም ታሳዝናለች ጠቁራለች ከስታለች ራሷን ጥላለች ብቻ እሷ እሷ አትመስልም፡፡ ሀምዛ በጣም ተናዶባት ስለነበር ሊያገኛት አልፈለገም

ሁላችንም ተሰብስበን አክስቴ(የፈቲ እናት)የተቀመጥንበት ገባች
.....ፈቲ እንዴት ትዋሹኛላችሁ?? ብላ ቀወጠችው ፡፡ከዛ ቡሀላ አረጋግተናት ሁሉንም ነገር እንዳወቁና በጣም እንደተበሳጩባት ነገሯት በጣም ደነገጠች... ሁሉንም ነገር ለሷም ተነገራት

በሷ ምክንያት እኔም የHiv በሽተኛ መሆኔን ስትሰማ በጣም አለቀሰች፡፡ ወደ እኔ ተንደርድራ መጥታ ይቅርታ ከልቧ እያለቀሰች ጠየቀችኝ፡፡ ሁሉንም ሰው እግራቸው ስር እየወደቀች አውፍ በሉኝ ብላ ከዛም ስለ ህይወቷ ምንም ሳደብቅ አንድ ባንድ ነገረችን
...እኛም በተራችን አለቀስን ....

ከዛም ፈቲ ጋር አንድ ላይ አደርን፡፡ ገላዋን ተጣጥባ ልብስ ቀያይራ ሰላት ጀመረች.... ሁለት ግዜ እንዳስወረደች ነገረችኝ ብዙ ላይፏን አጫወተችኝ፡፡ እኔ ከማውቀው በላይ አስከፊ ህይወት አሳልፋለች

ፈቲ እኛጋር የተወሰነ ግዜ አሳልፋ በሁሉም ቤተሰብ ምክክር ወደ አዲስ አበባ እንድትሄድና የሱስ መዳኛ ተብሎ በተቋቋመ ሆስፒታል የአእምሮ ክትትል እንድታደርግ ተወሰነ ፡፡ ፈቲ እንደ ገና ከሁላችንም ስትለይ አለቀሰች ፡፡ እኛም አብሽሪ ለአንቺ ነዉ ከሱስ እንድትላቀቂ የበፊቷ ጠንካራዋ ፈቲ እንድትሆኝ ነዉ ብለን በዛ በዚብህ ብለን አሳምነን ወንድሜ ሀምዛ ይዟት አዲስ አበባ ወደ አእምሮ ማገገሚያ ሆስፒታል ለሁለት አመት ያህል ህክምና እንዲሰጣት ይዟት ሄደ የህክምና ወጩ የሁለት አመቱ ሙሉ በሙሉ ተከፈለላት ከዛ ሀኪም ቤት ከሁለት አመት በፊት በጭራሽ መዉጣት አትችልም፡፡

ለኔ ደግሞ ፋዘር ባህር ዳር ላይ ሱፐር ማርኬት ለብቻየ ከፈተልኝ ፡፡ ከ ሳዳም ጋር ልናብድ ደርሰናል በስልክ የፍቅር ቃላቶች ሳይቀር እያወራነ ነዉ ፡፡ ነጁ ደውላልኝ ልታገባ መሆኗን ነገረችኝና መብሩክ አልኳት .
.......ለሀፍ ደወልኩላት ደሴ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ትምህርት ተምራ ልትመረቅ መሆኑን ነገረችኝ
.....እኔም አንቺ አዳማ ድረስ እንዳስመረቅሽኝ ደሴ ድረስ መጥቼ አስመርቅሻለሁ አልኳት፡፡ ሳዳምም የደሴ ልጅ ስለሆነ አገኝዋለሁ ብየ አሰብኩኝ

የሀፍ መመረቃያ ሲደርስ አንድ ቀን ቀድሜ ወደ ደሴ አመራሁ ደሴ ንፍቅ ብላኝ ነበር
......ከዛም ደሴ መነሀሪያ ላይ ሀፍ ተቀብላኝ ..ወደ እነሱ ቤት ሄድኩኝ ....እነ ሀፍ ግቢ ውስጥ 👇👇

PROUD_MUSLIM

09 Nov, 18:11


እስከመቼ 🤦‍♂

PROUD_MUSLIM

09 Nov, 07:59


ደስተኛ ለመሆን
ብቸኛው  መንገድ ወደ አሏህ
መቅረብ ነው።


@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

08 Nov, 18:00


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 2⃣3⃣



ግን እንዴት ነው የምነግራት ??? የፈቲ ላይፍ ከታወቀ እኔም ከምወዳቸው ቤተሰቦቼ መጣላቴ አይቀርልኝም መልሼ ሌላ ችግር ውስጥ ልገባ ነው

ግን አንድን ነገር አሰብኩ ለሷ ህይወት መቀየር ሰበብ ይሆናል ብየ ልነግራት ወስኜ ተንደርድሬ ሄድኩኝ... የሳሎኑን በራፍ ወርውሬው ገባሁ ስገባ ሀምዛም ራውዳም ከመቀመጫቸው በድንጋጤ ተንደርድረው ወደኔ መጡ
....ሀምዛ ምን ሁነሽ ነው?? ምን ተፈጠረ ?? ብሎ በድንጋጤ አይን አየኝ አሁን ተኝተሽ አልነበር እንዴ ምን ሁነሽ ነው ??አለኝ ለካ ይጨነቅልኛል ለካ ያስብልኛል የዛኔ ለኬ የመታኝና የሰደበኝ ከልቡ አልነበረም በሁኔታው ደስ ቢለኝም ምንም አልሆንኩም ብየው እጄን ከእጁ ላይ በሀይል አላቅቄው ቁጭ አልኩኝ፡፡ ሀምዛ ፈቲን በጣም ይወዳታል እንደኔ ነው የሚያያት እና የምነግረውን ነገር እንዴት ያምነኛል ??ከባድ ነው ብቻ ደፍሬ ለማውራት ወሰንኩኝ
....ራውዲየ ለዚ ሁሉ መነሻውኮ አወኩት ክብሬን አሳጥቶ በሽተኛ ያደረገኝን ሰውኮ አወኩት አልኩኝ------ ማልቀስ ጀመርኩ
....ራዉዳም ተረጋጊና አውሪ አለችኝ
..... ለመረጋጋት እየሞከርኩ ሄኖክ ነው ለኛ ህይወት መበላሸት ምክንያቱ አልኳት
..... ለኛ ማለት አልገባኝም ??ንገሪኝ እናንተ እነማን ናችሁ ??? አለችኝ
..... ለኔም ለፈቲም ለሀፍስም አልኩኝ
....... ነገሩን አታወሳስቢብኝ ግልፅ አድርጊው አለኝ

ሀምዛ ነገሩን እነሱ በሚገባቸው መልኩ እያለቀስኩ ከ ሀ-ፐ አንድም ሳላስቀር ነገርኳቸው ፡፡ ይሄ ሁሉ እኔን ፍለጋ እንዳደረገው እና የፈቲንና የሀፍን ህይወት ያበላሸው ብየ እስከ ማንነቱ ነገርኳቸው ስለ ማማየም ጭምር ነገርኳቸው፡፡ ራውዳ አብራኝ ታለቅስ ነበር ሀምዛ እንባዎቹ በፂሙ ላይ ጭምር ያስታውቅ ነበር፡፡ ያን ቀን የፈቲ ተግባር ያናደደው ሀምዛ....እኮ ፈቲ ይህን በአንቺ ጨክና አረገች ??? ብሎ ማሰብ ጀመረ ሰአቱ ከለሊቱ 6ሰአት ሆነ
.....ለምን ፈቲ እንደዚ አይነት ችግር ውስጥ ስትገባ ለምን ዝም እንዳልኩ ለቤተሰብ ለምን እንዳላሳዉኩ ጠየቀኝ
....በሰአቱ ይህንን ነገር አስቤው ነበር ግን ቤተሰቧ ሊወስዳት ከመጣ ወይ ራሷን ታጠፋለች አለበለዚያ የማይሆን ውሳኔ ወስና እንዳላጣት ፈርቼ ነው አልኩት
..... ይህን ሄኖክ እገልዋለው ነገ ድሬ እሄዳለሁ አለ
.....በአላህ ይሁንብህ ይህንን ሀሳብ እርሳው ብየ ተንደርድሬ እግሩ ስር ወደኩኝ ብዙ ለመንኩት ሳይወድ በግዱ እሽ ብሎ አነሳኝ
....ለእናት እና አባቴ እንዴት ነው የምንነግራቸው?? አልኩት
... በመጀመሪያ ስለ ሁሉም ነገር አውፍ እንድትይኝ እፈልጋለሁ ምክንያትሽን ሳልጠይቅሽና እንደወንድም ሳልረዳሽ ስላጠፋሁት ጥፋትና ክብርሽን ዝቅ በማድረጌ ስሜታዊ በምሆኔ በጣም ይቅር በይኝ መልካም ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት ሚባለው ነገር ሀቅ ነው ራውዳ አርቃ ባታስብና አንችን እዚ እንድትመጭ ባታደርግ ኑሮ ከባድ ፀፀት ነበር የሚሆንብኝ ፡፡
.....ምንም ቢሆን ግን ፈትህያን አለቃትም ..እኔኮ ፈቲን ከአንች ለይቼ አላያትምኮ የሷ ላንች ያላት ፍቅርና ውዴታ አሳቢነቷና ተጨናቂነቷ ህይወቷን አሳልፋ የምትሰጥ ነውኮ የምትመስለው

ወንድሜ በማመንና ባለማመን ውስጥ ነው ራውዳ ስላመነችኝ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ በቃ እንተኛ ተባለና ሰባት ሰአት ተኩል ላይ ተለያየን እኔ ፍፁም ልረጋጋ አልቻልኩም

ሌላ ሀሳብ ደስታየን ሊያጠፋብኝ የፀሀይዋን መውጣት እየተጠባበቀ በማነፍነፍ ላይ ነው መተኛት ሳይሆን መስገድና ዱአ ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ ሙሉ ለይሉን በቁርአን በዱአና ሶላት አሳለፍኩት ሱብሂን ሰግጄ ትንሽ አረፍ አልኩኝ ፡፡ዛሬ በስንተኛ ቀኔ ምግብ ቀመስኩ ሰውነቴ እየተጎዳ እንደነበር ስበላ ታወቀኝ

ጠዋት ተነስተን ወደነ ባባ ጋር ሄድን ቤት ስገባ ማማ ሩጣ አቀፈችኝ እና ማልቀስ ጀመረች እኔም አብሪያት ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ ሀምዛ ባባ ጋር ገብቶ ሁሉንም ያወራሁትን አወራው ራውዳ እኛን ማረጋጋት ጀመረችና ወደ ሳሎን ተያይዘን ሄድን ስንገባ ባባ ነይ ወደዚህ የኔ ልጅ አለኝ..... የሰማሁትን መጠራጠር ጀመርኩኝ ይህ ንግግር እውነት ከ አባቴ አፍ ነው የምሰማው ነው ??ራሱ ነው ያለው ??ተወዛገብኩ ፡፡ ደግሞ ነይ እንጂ ሲለኝ እግሩ ስር ወድቄ አውፍ በለኝ አባቴ ብዙ አስከፍቼ አሳፍሬ አዋርጄካለው ይቅር ካላልከኝ አልነሳም አልኩት
..... ድምፆቹ ተያይዘው እንባወቹ እየወረዱ ተነሽ የኔ ልጅ እኔ ነኝ ጥፋተኛው ሁሉንም በተረጋጋ መንፈስ ልጠይቅሽና ልረዳ ይገባኝ ነበር አውፍ በይኝ ልጄ ብሎ ግንባሬን ስሞኝ እቅፍ አድርጎ ማልቀስ ጀመረ እኔም አለቀስኩ
..... ሀምዛ ባባ ለአክስቴ እንዴት ነው የምንነግረው ??አለ ለደቂቃወች የነበረ ዝምታ ተሰበረ ሁሉም ግራ ገባው በዚህ መሀል እጩኛየ አዩብ ቤት ቆርቁሮ ገባ፡፡ ሁላችንም ከመቀመጫችን ተነስተን ተቀበልነው እና ተቀመጥን በመካከላችን ሰላምታን ተለዋውጠን ስለ ስራና አፊያ አውርተን
...ባባም አዩብ ልጄ ባለፈው የተፈጠረውን ነገር እኔም አንተም እናውቃለን እንግዲህ የሁላችንም ምኞትና ፍላጎት አይሟላም አላህ በመረጠውና በፈቀደው መንገድ ይወስዳል ከ ወንጀል በስተቀር ወንጀልን ከሚሰሩት ደግሞ ተውበተኞቹ ከሁሉም የተሻሉና የበለጡት መልካምና ለአላህ ቅርብ የሆኑት ባሪያወቹ ናቸው አላህን ለመገዛት ከነሱ የተሻለን ባሪያ ማግኜት ከባድ ነው የሚሆነው ፡፡ሀሊማየም የኔ ልጅ አንተ በፈለካት መንገድና ቦታ አላገኘናትም ስለዚህ ከዚህ ቡሀላ ያንተ ውሳኔ ነው የሚሆነው ተውበተኛዋን እና አላህን ተገዢዋን የኔን ምርጧን ልጄን ከፈለክ ይቹትና፡፡ ካልተመቸህና የማትስማማ ከሆነ እንደ ድሯችን እንቀጥላለን ብሎ ዝም አለ
......ሳሊም ትንሽ ቆይቶ ጋሽ መሀመድ እኔ እርስዎን በጣም እወዳለሁ ቤተሰብወን በጣም አከብራለሁ ሀምዛ ወንድሜም ጭምር ነው ፡፡ ማማም እናቴ ናቸው ሀሊማም ሙስሊም እህቴ ነች ይህንን ስል ግን እያዘንኩ ነው .....በዚህ መስማማት አልችልም ንፅህናዋን የጠበቀች ጤነኛ ሴት ነው ማግባት የምፈልገው ብሎን አውፍ በሉኝ ብሎ ተነስቶ ወጣ

ክብሬን ማጣቴና መገፋቴ ቢያናደኝም እሱን እንደማላገባው ሳውቅ መሰለኝ ደስ አለኝ.. ሳዳምን ለምን መልሶ እንዳገረሸብኝ ባላቅም ናፈቀኝ አዩብ ከወጣ ከደቂቃወች ቡሀላ አክስቴ(የፈቲ እናት) ገባች ስትገባ በጣም አፈርኩ ስታየኝ ደስ አላትና ሰላም ብላኝ ቁጭ አለች

ሁላችንም በዝምታ ተዋጥን ምንድን ነው??? አውሩ እንጅ አለች ከፓርሳዋ ስልኳን እያወጣች እርስ በርሳችን መተያየት ጀመርን ማነው ሚያወራው በሚል መንፈስ ተያየን የጭንቅ ሰአት መጣ ቤተሰብን ከቤተሰብ ሚያጋጨው የውሳኔ ሰአት.......
Part ➋➍

ከ 70👍 ቡኋላ
ይቀጥላል......

join 👇👇


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

07 Nov, 12:19


ሐኪም ዘንድ እያንዳንዱን ህመምህን
በዝርዝር መናገር ግድ ይልሃል !!


ነገር ግን አላህ ዘንድ ያ ኢላሂ… 🤲
ማለቱ ብቻ ይበቃሃል።
الحمدلله

PROUD_MUSLIM

06 Nov, 06:46


እናም ተመልሰው ሲመጡ
እንዴት እንደሄዱ አትርሱ!

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

05 Nov, 18:51


ደረጃህ ከፋ ማለት ሲጀምር
ሰፈር ቀይር ትልቁ ጠላትህ
ምንም በሌለህ ጊዜ
የሚያውቅህ ሰው ነው።


@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

04 Nov, 17:29


ምንም ብር የለኝም ቀጥታ ሂጄ ገመድ ስጠኝ አሁን አመጣልሀለው አልኩት
....,በፍፁም አለኝ
........በጣም ለመንኩት አይሆንም አለኝ ከሱ ጋር ስጨቃጨቅ ከሇላየ ራቢና ራውዳ ያዙኝ ነይ ወደኛ ቤት እንሂድ አለች
.....ራውዳ እንቢ አልኳት እኔ አሳምኜዋለው ሀምዛን አለችኝ ለካ ቤት ከሄዱ ቡሀላ ሴት ልጅ ብቻዋን ስትሆን ሚያጋጥማትን አናቅም ተደፍራ ይሆናል ሌላም እኛ ማናቀው ነገር ተፈጥሮ ይሆናል ስለዚ ቤት አምጥተን እናውራት ብላው ነው የመጣችው እኔም ጭቅጭቃቸው ሲበዛ ቤት...

ሄድኩኝ ወደ መኝታ ክፍል ገባሁና ማልቀሴን ተያያዝኩት ....ውዱእ አድርጌ ሰግጄ መስገድና ማልቀስ ስራየ ብየ ተያያዝኩት

ራውዳም ነገሮችን ዩኒቨርስቲ በነበረች ሰአት እንዳስታውስና በጣም እንዳስብ ትገፋፋኛለች ምግብና ውሀ ባይኔ ከዞረ ቆየ አልበላም ብያት ተጨንቃለች ወንድሜን ራሱ አይቼው አላውቅም

በሶስተኛው ቀን በጣም ደከመኝ እንቅልፌ ራሱ በቁሜ ጣለኝ ከዝሁር ቡሀላ ተኝቼ አላህ በህልም አስመስሎ አስታወሰኝ

//////// በህልሜ ፈቲ ቤት ሁኜ ሄኖክ ሲገናኜኝ ተመለከትኩ ኢሻ አካባቢ ላይ በድንጋጤ ተነሳሁ ውዱእ አድርጌ ፈርድ ሰላቶችን ሰግጄ ለማስታወስ መጣር ጀመርኩኝ


አወ አስታወስኩኝ ያን ቀን ታምሜ ፈቲ ቤት ያደርኩ ቀን ፈቲ ሀሊማየ እንዳትፈርጂብኝ ግድ ሁኖብኝ ነው እያለች ስታነበንብና ለራሷ ስትለፈልፍ ነበር

የከፈተቺልኝን ለስላሳ እንድጠጣው ስትገፋፋኝና ሳልፈልግ እያመመኝ የተኛሁበት ቀን አስታወስኩ እኔም ጠዋት ላይ ስነሳ ጀንቤ ደም ሁኜ..... አይ የወር አበባ ይሆናል ያልኩት ትዝ አለኝ


ለራውዳ ልነግራት መንደርደር ጀመርኩ ግን ምን ብየ ነዉ የምነግራት ??? የፈቲን አሁን ያለችበትን ሂወት ሳስታውስ ቆምኩኝ......

#Part_23

ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል.......

Join👇👇


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

04 Nov, 17:28


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 2⃣2⃣



ከዛም ወደ ሆስፒታል አብረን ሄድን ....ካርድ ቆርጠን ከተወሰነ ደቂቃ ቡሀላ ለድንግልና ምርመራዉ ክፍል ገባሁ
አብረን በተቀመጥንባቸው ደቂቃወች ምንም ላወራው አልፈለኩም ንዴቴ ከውስጤ አልወጣም
የሄጅኩበት ሆስፒታል ባህር ዳር ላይ ትልቅእና ስመጥር ሆስፒታል ነው

ስገባ ሴት ዶክተር ነበረች በጣም ዘመናዊ ስለነበሩ ውጤት አይቆይም ....አብረን ገብተን ስለ ሁኔታው ካስረዳሆት ቡሀላ ደም እንድሰጥ አዛኝ ተመልሼ እንድገባ አዘዘችኝ
....ደም ሰጥቼ መጣሁ ስገባ የሆነ ማሽን እና አልጋ አዘጋጅታ ነበር ለምን እንደሆነ ባላቅም ገብቼ ተቀመጥኩኝ ብዙ ጥያቄና መልስ እንደዚሁም የምክር አገልግሎት ከሰጠችኝ ቡሀላ ልብሴን አውልቄ እንድተኛ አዘዘችኝ..... በማፈርና በመፍራት ውስጥ ሁኜ አደረኩት
አዱብ ለላብራቶሪ ስሄድ አብሮኝ ሂዶ ግን መልሶ አልገባም ነበር ፡፡ ምርመራየን ስጨርስ ለባብሼ ቁጭ አልኩኝ
...ውጤት ከሳምንት ቡሀላ መተሽ ውሰጂ ብላኝ ተመለስኩኝ

ከሳምንት ቡሀላ ባባና እኔ ሁነን ሄድን አዩብ ቀድሞን ነበር ፡፡ አብረን ገባን ባባና አዩብ ከኔ ፊት ለፊት ተቀመጡ
..... ከምንግዜውም በላይ ውስጤ ፈራ ለኔ ብቻ የሚያስታውቅ ስሜት ይነዝረኝ ጀመር ዶክተሳም ባባ ሲቀር አዩብን አስወጣቺውና ምንም ቢፈጠር ራሴን እንዳረጋጋ ነገረችኝ
.....እኔም እሺ አልኳት ግን ውስጤ የማላቀው ስሜት ወሮኛል
___\\\\\\\\\\ ዶክተሯም ሀሊማ ይህንን ዜና #ስነግርሽ_በጣም_እያዘንኩ_ነው_አንች_ድንግል(ቢክራ) አይደለሽም/////////// አለችኝ ውስጤ ሊፈነዳ ደረሰ መጮህ አቃተኝ የባባን ፊት ማየት ተሳነኝ እንባዎቼ የክረምት ጎርፍ ይመስል በዝምታ ያለማቋረጥ ይንዠቀዠቃል የሲቃ ድምፅ ጉሮሮየ ላይ ቁሞ ሊወጣ ይታገላል ግን በየት በኩል
ከዛም ጨመረችልኝ ሀሊማ አንዴ አድምጭኝ በጣም የሚያሳዝነው የ ኤች አይ ቪ ተጠቂ ነሽ በደምሽ ዉስጥ ኤች አይቪ ኤድስ አለብሽ ስትለኝ እግሮቼ ተንቀጥቅጠው ጉልበቶቼ ቀጭን ሰውነቴ ከብዶት ተርገፈገፈ ፊት ለፊቴ የነበረው መስታወት ጠረንጴዛ ላይ ፊት ለፊት ወደኩኝ
ከዛ ቡሀላ ምን እንደተፈጠረ የማቀው ነገር የለም ከተወሰነ ደቂቃ ቡሀላ ስነቃ አዩብ እና ባባ ፊት ለፊቴ ቁመዋል
..... ነርሷ ደህና እንደሆንኩኝ ነግራኝ ወደቤት ሄድን.. ባባ ምንም ነገር አላወራም እኔም እንባየ ዝም ብሎ ይፈስ ጀመር ማቆሚያው ምን እንደሆነ አላቅም የሚያሳስበኝና የሚያስለቅሰኝ ነገር የነባባን ደስታ ማጥፋቴ ነው ፡፡ በተከበሩበት አገር አዋረድኳቸው አዩብ ስለውጤቴ ምንም ነገር አያቅም ሁሉም ሰው አይቤን ያወቀ መሰለኝ በጣም ተሸማቀቅኩኝ
ወደ ክፍሌ ሩጬ ገብቼ በራፌን ዘግቼ ያለ ማቋረጥ አነባ ጀመር ባባም ማማም ሀምዛም አክስቴም በራፍ ላይ ቁመው ይቆረቁራሉ ላንዳቼውም ላለመክፈት ወሰንኩኝ ፡፡ ከተወሰነ ደቂቃ ቡሀላ የሀምዛ ሚስት(የወንድሜ ሚስት) በራፌን ቆረቆረቺው ራቢም ነበረች እኔ ሰማይና ምድሩ ተገለባብጦብኛል ስለምንም ነገር ማሰብ አልቻልኩም የባባን ደስታና ምኞት ሳጠፋው ይታወቀኛል የእናቴን ሚስኪን ልብ ቁርጥምጥም አድርጌ ስበላው ታወቀኝ ለራቢና

ለወንድሜ ሚስት ራውዲ ከፈትኩላቸው ሁለቱም ዘለው አቀፉኝና እንባየን መጠራረግ ጀመሩ ራውዳም ራቢአም ገና ሲያዩን እንባቸውን መቆጣጠር አቃታቸው አብረውኝ ያለቀሱ ጀመር፡፡ ወደ ሳሎን ሊወስዱኝ ቢፈልጉም አሻፈረኝ አልኩኝ ባባ ተንደርድሮ መኝታ ክፍሌ ገባና የማላቀውን ባባ ሆነብኝ በቃ ክብሬን ማንነቴን ደስታየን ምኞቴን ልጅነቴን የሰጠሁሽ አባትነቴን ዝቅ ያደረግሽ ከእንስሳ ያነሽ እንስሳ ነሽ፡፡
ልጄ አንች ሳትሆኝ ሀሊማ ነች ዩኒቨርስቲ ያልገባችው ያች ናት ያችኛዋ ጨዋዋ ልጄ ናት አንችን አይንሽን ላፈር ያድርገው ከቤቴ ውጭ አታቂኝም አላቅሽም ብሎ አንባረቀብኝ
.....በቃ አባቴ አባቴ አልመስለኝ አለ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ መልካም ፍቃዴ ነበር በህይወት ኑሬ የነሱን ሀዘን ከማየት በላይ ሞት የለም በየትኛው አቅሜስ ቁሜ አያለው ---------ሀምዛ ተከትሎት ገባና በጥፊ ሲመታኝ በጣም ስላመመኝ መሬት ላይ ወደኩኝ////// ወራዳ ነሽ አፌን ሞልቼ የማወራልሽ እህቴ አይደለሽም አንች የመጨረሻ ዝቃጭ ነሽ ባባንና ማማን እኔንም የሚተማመኑብሽን ሁላ ነው ዝቅ ያረግሽው በቃ ከዚ ቡሀላ ሚያወሩት ነገር በሰመመን ህልም መሰለኝ የማላቀው ቤተሰብ የገባሁ መሰለኝ እናቴም አክስቴም እያዩኝ ዝም አሉ ባባ ተነስተሽ ከቤት ውጭ ተመልሰሽ እንዳትመጭ አለኝ ሀምዛም ጮከብኝ ራቢአን እንዳትወጣ ከለከሏት አክስቴም ዝም አለች እናቴም ባዳ መሰልኳት መሰል እንባወቿ እየወረዱ ዝም አለች


ባባ እግር ስር ተንደርድሬ ወደኩኝ ይቅር እንዲለኝ ተማፀንኩት
.....አይሆንም አለ ጭራሽ ገፍትሮኝ ሄደ ሀምዛም ራውዳንና ራቢአን ወደ ሳሎን ወስዶ ሁሉም ረግጠውኝ አለፉ ፡፡ አማራጭ ሳጣ ከቤት ወጣሁ ለቅሶየ አላቋርጥ አለ እንባወቼ ማቆሚያ አጡ እንዴት ግን አባት በልጁ ላይ ወንድም በእህቱ ላይ ይጨክናል ??እናት ምን ቢያስቺላት ነው የልጇን ለቅሶ ቁማ የምታየው??? ይገርማል በጣም አንድ ቀን እንኳን ሳላጠፋ ቀርቶ አጥፍቼ ቢሆን እንኳን ከፊቱ መልካም ፈገግታ የማይለየው እንኳን ሊያሳፍረኝ አይደለም ሲመክረኝ እንኳን ድምፁን ቀንሶ የሚነግረኝ አባቴን ምን ነካው??? ምን ሆነ ምን አግኝቶት ነው????

እንኳን በጥፊ ሊመታኝ ሊሰድበኝና ሊቆጣኝ ቀርቶ ሲያየኝ እንኳን በስስት የሚያየኝ ወንድሜን ምን አስነኩብኝ?? ቤተሰቤ ወድየት እየሄደ ነው?? ግን
እንኳን አልቅሼ ይቅርና ዝም ብላ ራሱ ስለኔ የሚጨንቃት እናቴ በልቼ ያልጠገብኩ ጠጥቼ ያረካው ለብሼ የምደሰት የማልመስላትና ሁሌም ስለእኔ ሰላም የሚነሳት ብርቅየዋ የማትለወጠዋ እናቴ ምን ሁና ነው?? ቁማ የምታየኝ የሞትኩኝ መስሏት ይሆን ወይስ በህልሟ እያየችኝ መስሏት ይሆን ቁማ የምታነባው ከኔ በላይ እንዴት ሰው ሰራሽ ማሽንን ያምናሉ ንፁህነቴን ከኔና ከኔ ውጭ ማን የሚያውቅ አለ አላህ ሆይ ምነው እውነታውን ለኔ ብቻ ግልፅ አድርገህ ለሌሎች ጋረድክባቸው ??ምን በድየና አጥፍቼ ይሆን ??የአላህ ምነው ፈተናየን አበዛሀው ??በወንጀልና ሀራም ላይ ያሉትን አስደስተህ ምነው በሀላል መንገድ ላይ ያለሁትን ሚስኪን ባሪያህን ፈተናየንና ለቅሶየን አበዝሀው ???

መንገዴን ሳላውቀው እንባወቼን ሳላቆም በሰወች መሀልና በመኪና መንገዶች ተሻግሬ ከቤቴ በጣም ርቄ ሂጃለሁ ብዙ ግዜ የምንቀመጥበት ቦታ ሂጄ ቁጭ አልኩ ያለፉ ላይፎቼን ማሰብ ጀመርኩ ከየትኛውም ወንድ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም ካፌ ራሱ አብሬው ቁጭ ብየ ሻይ የጠጣውት ሰው ቢኖር ሳዳም ብቻ ነው እሱንም ነጁ ጋር አብረን ነው የገኜሁት ከማንም ጋር አልተኛሁም አንሶላም አልተጋፈፍኩም፡፡ ሌላው ይቅርና ለሰላምታ እንኳን እጄን ዘርግቼ አላቅም ታዳ በየትኛው መንፈስ ነው ሁለት በሽታ በአንዴ የሚመጣው??? በተለይ ኤች አይቪ ያለ ንክኪ አይመጣም ወይም በአንድ አይነት እቃ ካልተጠቀሙ በቀር እኔ ደግሞ መጠቀሚያየ ሁሉ የግሌ ናቸው ቢክራነቴንስ ቢሆን በቀላል ነገር የለሽም ማለት አልስማማበትም በስራ መብዛት ሊጠፋ ይችላል ግን ቁጭ ብየ ከመማርና ከመብላት ውጭ ይሄ ስራ ተብሎ አይጠራም የምሰራው ስራ ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ደረሰ

ቀኑ መጨላለም ጀመረ ፊት ለፊት ሱቅ አየሁ በቃ ራሴን መስቀል አለብኝ ብየ ሄድኩኝ በእጄም በኪሴም👇👇👇

PROUD_MUSLIM

04 Nov, 13:14


"መልካም ስራወች መጥፎ
አወዳደቅን ይጠብቃል"
ረሱል (ﷺ)

PROUD_MUSLIM

03 Nov, 17:51


ጨለማ ውስጥ ትተውን የሄዱት
ሰዎች ናቸው መትረፋችንን ለመጠየቅ
ሚመጡት!

PROUD_MUSLIM

03 Nov, 14:24


ህይወት ምንም ያህል ብትከብድ
እወቅ الله ነፍስን ከአቅሟ በላይ
አይጭንባትም::

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

02 Nov, 17:16


አላህ ብቻ ይበቃናል
ወላሂ አላህ ብቻ ይበቃናል☝️❤️‍🩹

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

01 Nov, 18:11


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 2⃣1⃣



ማማና ባባ ሲጨቃጨቁ እቤት ገባሁ መግባቴን ሲያውቁ ዝም አሉ በህይወት ዘመኔ ለመጀመሪያ ግዜ እንደዚ ሲያወሩ ሰማሁ የሁለቱንም አይን በየተራ እያየሁ ምንድን ነው የምትቸካኩት ??አልኳቸው
.....ሁለቱም ተያዩና ፈገግ ተባባሉ መደንገጤ ያስታውቅ ስለነበር ነው እኔን ግን የባስ ግራ አጋቡኝ

ባባ ቁጭ በይማ ሀሊማየ ጥሩ ዜና አለ የምነግርሽ እድሜ ልኬን ስጠብቃት የነበረችው ቀን ደረሰች አለኝ ምንድን ነው አልኩት?? ግራ እየተጋባሁ

...በዚህ መሀል አሰላሙ አለይኩም ብሎ ሀምዛ ወደቤት ገባ ፡ሀምዛ ታላቅ ወንድሜ ነው አግብቶ የራሱን ኑሮ ነው የሚኖረው ተንደርድሬ አቀፍኩትና ሳምኩት ብዙ ግዜ አገር ውስጥ አይቀመጥም ለምርቃኔም ፕሮግራም አልነበረም እቃ ሊያመጣ ቻይና ሂዶ ነበር በዛው ወደ ዱባይ ሚስቱን ይዞ ሂዶ ነው፡፡ ማማንም ባባንም ዘይሮ ቁጭ አለ ሁላችንም ቁጭ ባልንበት ከጀርባየ በኩል የሆነ ሰው መጥቶ በጣም የሚያምር ፈርጡ አልማዝ የሚመስል የአንገት ሀብል ተደረገልኝ .....ዘወር ስል የሀምዛ ሚስት ነበረች፡፡ በናፍቆት አቅፌ ሳምኳት እሷም ዘይራ ቁጭ አለች ስለነሱ ጉዞና ቆይታ ስናወራ አመሸን ..

ማታ መኝታ ክፍሌ ቁጭ ባልኩበት ሰአት እኛ ቤት ያለችዉ የቤት ሰራተኛችን መጥታ ባባ ይጠራሻል አለችኝ
....እኔም አቤት አባቢ አልኩት
..... ቁጭ በይ አለኝና ቁጭ አልኩኝ... ፈገግታውን ሳይነፍገኝ ስለአለዉ ሁኔታ ይነግረኝ ጀመር ፡፡ ለነገሩ እንኳን የሚያስደስተው አግኝቶ አይደለም ቢከፋው ቢቆጠጣኝ ቢናደድብኝ ራሱ ፈገግ ብሎ ነው የሚያወራኝ
እንደዚህ አለኝ--------== ሀሊማየ የኔ ልጅ አንችን ከልጅነትሽ ጀምሬ ሳሳድግሽ አንድም ቀን እንዳትከፊብኝ ምንም እንዳይጎልብሽ አድርጌ ነው፡፡ ሳስተምርሽ ደግሞ ተመርቀሽ ትልቅ ደረጃ እንድትደርሽልኝና በእውቀትሽ አንቱ እንድትባይልኝ ነበር አልሀምዱ ሊላህ ለዚህ በቅተሽልኛል በጉጉት ስጠብቀው የነበረው ቀን መጨረሻውን እዚሁ እናደርገዋለን ከዚህ ቡሀላ ይችን ቀን ጥበቃ ሌላ ቀን አያስፈልገንም እያለ አይን አይኔን ያየኛል ...

መጨረሻ ላይ የተናገረው ነገር ግራ አጋብቶኛል መጨረሻው ይሆናል ማለት ምን ማለት ነው??? ግራ እንደገባኝ አውቋል፡፡ የ ዘጠና አመት ሽማግሌ ይመስል ነበር ግንባሬ መጨማደዱ አይኔ ሊሸፈን መስለዋል አይዞሽ ሀሊማየ ግራ አይግባሽ ተምረሽ ከተመረቅሽ ቡሀላ አያት እንድታደርጊኝ እፈልግ ነበር የሆነ ነገር ሰውነቴን ነዘረኝ አግቢ እያለኝ እንደሆነ ገባኝ በጣም ደነገጥኩኝ ፡፡ ወሬውን እንዳላቋርጥ ብየ እንጅ የኔ አላማ ይህ አልነበረም በተማርኩበት ሙያ መስራትና ፈቲንና የሷን አይነት ሰወች ካሉበት ችግር ማስወጣትና መርዳት ነበር ከሄድኩበት ሀሳብ ያነቃኝ የባባ ወሬ ነበር
--------ሷሊህ ባል እንድታገቢ እፈልጋለሁ ዲኑ ላይ ጠንካራ የሆነ ሰው እፈልግ ነበር ስለ ዱኒያው የማይጨነቅ ሀቅሽን የሚወጣ ባል ሳፈላልግ ነበር አልሀምዱ ሊላህ ተገኝቷል፡ አኽላቁ ጥሩ የሆነ ባል አግኝቼልሻለሁ ከነገ ወዲያ ሽማግሌውቹ ይመጣሉ አለኝ

ፍላጎቴ የኔ ሌላ ነበር ነገር ግን ባባንና ማማን ለማስደሰት ስል ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ቤተሰብ ባመጣልኝ ባል ተስማማሁ ፡፡ እነሱ ለኔ የተሻለውን ነገር ቢሆን እንጅ አይመርጡልኝም ደግሞስ እኔ እንዳልከፋና ለደስታየ ሲሉ ስንት መሰዋትነትን ከፍለውልኛል እኔስ እነሱን ለማስደሰት ይህን ባደርግስ<<< ደግሞም ለሀላል ነገር ነው ያዘዙኝ

ደግሞ ከዚህ የበለጠ የሚያስደስተኝ ነገር ቢኖር ከነ ክብሬ ለሀላሌ መሆኔ እና ቤተሰቤን ክብሩን ላስጠብቅ መሆኔን ሳስበው ደስ አለኝ
...ግን ልጁን አውቀዋለሁ??? አልኳቸው
.... አዎ ታቂዋለሽ ብለው አዩብ ይባላል ብለዉ ነገሩኝ.. አዩብ የባባ ጓደኛ ልጅ ነበር ዲኑ ላይ ባለው አቋም ባህርዳር ላይ ብዙ ሴቶች ይመኙታል ፡፡ በዛም ላይ ቆንጆ ነው ግን የሚገርመዉ ሳዳም ግን ከሀሳቤ አልወጣም
...ትዳር ሲባል ባሌ ቢሆን ብየ የምመኘዉ ሳዳምን ነበር ..አሁንም ሳዳምን ብየ ተመኘሁ.. ግን ሳዳም አይሆንም

እኔም ጊዜ ሳልፈጅ ቤተሰቦቼን ለማስደሰት መስማማቴን ስነግራቸው ማማ አጠገብ ስለነበርኩ እቅፍ አረገችኝ ነይ እስኪ የኔ ልጅ ብሎ ባባ ደግሞ ግንባሬን ሳመኝ
.....ልተኛ አልኳቸው
.......ሂጂ ተኝ አሉኝና ወደ ክፍሌ ገባውና ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ሳዳምን ላወራው ወሰንኩኝ
....አሰላሙ አለይኩም ሳዳም እንዴት ነህ ??ብየ ላኩለት
.....መልስ የለም ዝም ጭጭ ያለ ነገር ፡፡ በቃ ተስፋ መቁረጥ አለብኝ አልኩና ስልኬን አጠፋፍቼ ተኛው

በተባለው ቀን ከሁለት ቀን ቡሀላ ሽማግሌወቹ መጡ፡፡ እኔም ለአዩብ ታጨሁ... ባባ እና ሽማግሌዎቹ የሰርግ ቀን ቆርጠው ኒካሁም ለሰርጉ ቀን እንዲሆን ብለዉ ተስማምተዉ ሆዱ ፡፡

ግዜወች ነጎዱ አንድ ቀን ባባ ተናዶ እቤት ገባ፡፡ የዛን ቀን አዲሱን ባሌን አግኝቶ አውርቶት ነበር
..... እናም እኔ ዩኒቨርሲቲ ደርሳ የመጣች ሴት አላምንም ንፅህነቷን ድንግል መሆኗን በህክምና ማረጋገጥ አለብኝ አለኝ እንዴት ልጄን እንደዚህይላል?? ብሎ መጮህ ጀመረ

በነገሩ አባቴ ቢናደድም ቢበሳጭም ገና ሳያገባኝ ሌላው ቀርቶ ኒካህ እንኳን ቀኑ ሳይደርስ በኔና በቤተሰቤ ክብር መቀለዱ አበሳጨኝ ፡፡ ጡሀራነቴንና ንፅህነቴን ከኔ በላይ ጀሊሉ ያቃል ቤተሰቤ እና የሚያቀኝ ሁሉ በአስሩም ጣቱ ስለ ጨዋነቴ ይመሰክራል... አዩብ ግን እንዴት ቢደፍረኝ ነው??? ብየ ተበሳጨሁ
አባቢን ለማረጋጋት እየሞከርኩ በቃ እንደዚህ አትሁን እኔ በራሴ 100% የምትማመን ልጅ ነኝ አዩብ ጋር ሂጄ ስለ ድንግል መሆኔ እመረመራለሁ አልኩት
..... በፍጹም አይሆንም አለ ባባ

ተነስቼ መኝታ ክፍሌ ገባሁ ቁጭ ብየ ማሰብ ጀመርኩኝ -------------ወንድ የሚባል ፍጡር በዛ ሸይጧን ሄኖክ ምክንያት አስጠልቶኛል፡፡ ወንድ ሲባል ሁሉም ለቢክራ ነው የሚሮጡት ቢክራዉን ግን የሚወስዱት እራሳቸዉ ወንዶች መሆናቸዉን ዘንግተዉታል ፡፡ ስለ ተውበቷና ስለ ጥሩ አኽላቋ የሚያስብ የለም ከሳዳሜ ውጭ ያሉ ወንዶች ሁሉ ሄኖክን ነው የሚመስሉኝ ፡፡ሳዳምንም በስንት ጉድ ነው ያመንኩት... አንዳንዴም ደግሞ በጥሩ ወንዶች ላይ መፍረዱ ከበደኝ_ ታላቅ ወንድሜ ሀምዛ መጀመሪያ ያገባት ሚስቱ ሸውዳው ነበር ቢክራ እንደሆነችና ከሱ ሌላ ወንድ እንደማታቅ አድርጋ አሳምናው አግብቷት ነበር፡፡ ግን ልጂቱ ቢክራ አልነበረችም... ይባስ ብላ እሱ ዱባይ ቻይና እቃ ለማምጣት ከሀገር ሲወጣ ቤት ድረስ ወንዶችን እያመጣች የገዛ አልጋው ላይ ትጨፍርበት ነበር ፡፡ሁሉም ሰው ንፁህ እና አዲስ ነገር ይፈልጋል ቢሆንም ይህን ያክል ሚያናንቅ ጥያቄ ግን መጠየቅ ተገቢ አይደለም

ለ ባባና ማማ ደስታ ስል ለማድረግ ተስማምቼ ...ለአዩብ ነገ ጠዋት እንገናኝ እና ባህርዳር ላይ ታዋቂ በሆኑ ሆስፒታሎች የድንግሎና ምርመራዉን አደርጋለሁ ብየ ቴክስት ላኩለት፡፡ ስፅፍለት ውስጤ በንዴት ቅጥል እያለ ነበር

ጠዋት ተነስቼ ሱብሂን ሰግጄ ዱአየን አድርጌ ቁርስ በልቼ ከቤት ወጣሁ እና ደወልኩለት
አዩብ ጋር ተገናኘን ..ከዛም ወደ ሆስፒታል አብረን ሄድን ....ካርድ ቆርጠን ከተወሰነ ደቂቃ ቡሀላ ለድንግልና ምርመራዉ ክፍል ገባሁ

የሀሊማ የምርመራ ዉጤት እንዴት ይሆን????በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን
#Part_➋➋
ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል....

Join👇👇


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

01 Nov, 04:28


"እወቁ ከመልካም ስራዎቻችሁ
ሁሉ በላጩ ሰላት ነው"

ረሱል ሰ.ዐ.ወ❤️

PROUD_MUSLIM

31 Oct, 18:19


ሰዎች የሞተን ሰው በምን ያህል
ፍጥነት እንደሚረሱ ብታቅ ሰዎችን
ለመማረክ መኖርህን ታቆም ነበር !



@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

31 Oct, 15:48


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 2⃣0⃣


ለውዷ ልጄ ሀሊማየ ይላል የእጅ ፁሁፉ የፈቲን ይመስላል ግን አይደለም ሀሊማየ የኔ ልጅ በመጀመሪያ ለዝች ቀን በመብቃትሽ ደስ ብሎኛል ግን ተመረቅሽ ማለት ሁሉም ነገር ተጠናቀቀ ማለት አይደለም እዚህ የነበሩብሽን ጭንቀት የሀሳብና መከራ ግዜ አለፍሽ ማለት ከአሁን ቡሀላ በድሎት ብቻ ትኖሪያለሽ ማለት አይደለም፡ እዚህ በነበርሽባቸው ግዜያቶች ያሳለፍሻቸው የደስታ የጭንቀት የህመም የአብሮነትና የብቸኝነት ግዜያቶች የህይወትሽ የመጀመሪያ ምእራፎች ናቸው በህይወትሽ መኖር የጀመርሽው ከቤተሰብ ተለይተሽ እዚ ስትመጭ ነበር እዚ ሁነሽ ከቀለሙ ትምህርት በላይ ህይወት ራሷ በተግባር ትምህርት ያስተማረችሽ ላንች የተሻለው ነበር ምክንያቱም ከኔ በላይ በአሁኑ ህይወትሽ ላይ የመጣውን ለውጥ አንች ታቂዋለሽ በፊት ምን ነበርሽ?? አሁንስ ምን ላይ እንደሆንሽ አንች ታውቂዋለሽ እርግጠኛ ነኝ ነገሮችን እንዴት እንደተለወጡብሽና እንዴት እንዳለፍሻቸው አየሽ? አንች ልዩ ሴት ነሽ ምክንያቱም ግዚያዊ ደስታ አልሸወደሽም ሱስ,ወንዶች,ሌላም ሌላም ነገሮች ሳያታልሉሽ እዚ ደረጃ ደርሰሽ ራስሽንም ቤተሰብሽንም ሚያውቅሽን ሠው በሙሉ አኩርተሻል እኔ በደስታ ብዛት አልቅሻለሁ፡ ሁሌም ልጄ ተመርቃ እኔ ስደሰት ማየት ምኞቷ ነበር በመጥፎ ጓደኛ ምክንያት ምኞቷም ቀርቶብኝ እሷንም ያጠዋት ስትመረቅ እንድሰጣት የምትፈልገውን ስጦታ ነው የሰጠውሽ
.....የኔ ልጅ ትምህርቷን ስትጨርስ እንድሰጣት የምትፈልገው ቁርአን ጅልባብና የወርቅ የአንገት ሀብል ነበር ይህንንም አድርጌዋለው አላህ ሀያት ከሰጠኝ ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሰሽ ልታይኝ እንደምትመጭ ተስፋ አደርጋለው ይላል ሁለት አይነት ስሜት ተሰማኝ የደስታ ይሁን በሳቸው ንግግር አዝኜ እንደሆነ ባላቅም እንባየ ፈሷል የንባየ አንዷ ጠብታ ከ ማማየ የሚለው ፁሁፍ ላይ አረፈች -----------ወረቀቱን በስነስርአት አስቀመጥኩት ሌላ የታሸገውን ስፈታው ቁርአን ጅልባብና የሚያምር የወርቅ ሀብል አገኜሁ,,, ወላሂ ስቅስቅ ብየ አለቀስኩ እንዴት ይህን ሁሉ አረጉ ገና ለገና መልኬ ልጃቸውን ስለመሰለ በጣም ደግሞ ደስ አለኝ እኔንጃ ግን የትኛው ስሜቴ ከፍ ብሎ እንደሚሰማኝ አላቅም
,,,,,ቁርአኑን ስከፍተው ፎቶየን አገኜሁት ደንግጬ ቶሎ አነሳሁትና አየሁት መቼ የተነሳሁት ፎቶ ነው?? ልብሱም የኔ አይደለም ግራ ገባኝ ....አሀ የማማየ ልጅ ነች ትዝ አለኝ ፡፡ ፎቶውና እኔ በደንብ ላየን ሰው እንጅ ልዩነታችን ሚያስታውቀው በጣም ተመሳሳይ ነን ተገረምኩኝ፡፡ ደጋግሜ አየሁት አጀበኝ በራፌ ሲቆረቆር ቶሎ ብየ እንባየን ጠራርጌ ወረቀቴን ደብቄ ከፈትኩት እንዳለቀስኩ አያስታውቅም ነበር ራቢ ነበረች
....ምንድን ነው የምርቃን ፕሮግራምሽ እንጅ ይሄኮ የሰርግሽ ቀን አይደለም አዲስ ሙሽራ ይመስል በራፍ ዘግተሽ ትሽኮረመሚያለሽሳ ብላ ወደ አልጋየ ጫፍ ሄደችና ቁጭ አለች ...ለኬ ፎቶውን ረስቼው አላነሳውትም ተናደድኩ ራቢ አነሳችው እና አንች ይሄ ልብስ ሲያምር መቼ ነው?? አለችኝ
.... የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ትምህርት ቤታችን ሲያከብር ለብሼው ነው አልኳት
...... ዋው ብላ ደጋግማ አየችው እኔ ከየት አምጥቼ እንደመለስኩላት ገረመኝ ፡ለኬ መደንገጥም ጥሩ ነው ያስመልጣል፡፡ አንዳንዴ ማሰብ ራሱ ያስባንናል

ማማ መጣችና ውይ እናንተ ልጆች በቃ ከተገናኛችሁ ማንንም አትሰሙም አይደል?? አለች ማማ ደግሞ ታቂ የለን'ዴ ምን አልባት ቤቴን በነፃ ዲዛይን ብታደርግልኝ ብየኮ እየተንከባከብኩ ነው አለች
....ማማ ፈገግ ብላ ኑ ምሳ እንብላ ብላ ሄደች ልክ ስወጣ በጣም ብዙ ሰው ተሰብስቦ አየሁ ሁሉም ቁመው ዘየሩኝ የማማ ጓደኞች ዘመዶቻችን ወንዶቹ እንኳን ደስ አለሽ ይሉኛል ፡፡ ወንዶቹን አልዘየርኩም ምሳ ተበላ እኔና ራቢ ወደ ክላስ ተመልሰን ማውራት ጀመርን ስላለፉ ግዜያቶች ማውራት ጀመርን ስንሳሳቅ ምናምን አሱር መግሪብ ኢሻ ደረሰ ራቢን ሸኚቼ ስልኬን መፈለግ ጀመርኩ ከትራሴ ስር አገኜሁት፡፡ ለኬ ዘግቼዋለው ተናደድኩ ስከፍተው ብዙ ሰው ደውሎ ነበር ፈቲ ሀፍና ነጁ ደውለውም ነበር መጀመሪያ ለሀፍና ነጁ ደወልኩ ፈቲን ረጂም ሠአት ላወራት ስለፈለኩ መጨረሻ ላይ ደወልኩላት ፡፡ ብዙ ሰአት አወራን ቤት ስለተደረገውም ፕሮግራም ነገርኳት ስለመጡላት ስጦታዎችም ነገርኳት ደስ አላት

አንች ግን እንድ ቀን ሳልተኛሽ ሄድሽ አይደል?? አለ ያ ቀፋፊ ሠው ሄኖክ ነበር፡፡ በተናገረው ብልግና ቃል ደንግጬ ዘጋሁት.... ተናደድኩ ግን መናደዱ ጥቅም የለው ብየ ተነስቼ እነ ባባን ተቀላቀልኩ እያወራን ሜሴጅ ገባ ሳዳም ይሆናል ብየ ፈጥኜ ከፈትኩት ግን ፈቲ ነበረች አንች(..........................)ለሴት ልጅ ማይላክ ሜሴጅ ነበር ከታች ግን
----------- አንች አስደብድበሽኝ አትቀሪም---------- እገድለዋለው ይላል

ግራ ገባኝ ሄኖክ በመደብደቡ ደስ አለኝ ፡ግን እኔ ማንንም አላኩም ማን ይሆን የደበደበዉ ???ብቻ ወደ ቤተሰብ ወሬ ተመለስኩ


ዳግም ቴክስት ገባ በቃ ሄኖክ ነው ብየ ሳላየው ቀረሁ ከብዙ ወሬ ቡሀላ ተኛው ፡፡ ጠዋት ሱብሂን ሰግጄ ስልኬን ስከፍተው ሳዳም ነበር ወዲያው ባለማየቴ ተናደድኩ
...... አሰላሙ አለይኩም ደህና ነሽ?? ሰው ሲጠፋ አትፈልጊም?? ይላል
....እኔም ወአለይኩም ሰላም አረ ሳዳም እዚህ በምርቃን ፕሮግራም ቢዚ ሁኜ ነዉ ብየ መለስኩለት፡፡ ግን message አልመለሰም
......ስልኩን ስጠባበቅ ዋልኩኝ
በዛ ሰሞን ቤተሰብ ዚያራ ከዚ ከዛ ስል ከረምኩ


ግዜውም ነጎደ ዛሬ ቤት ከመጣው ሁለት ወር ሆነኝ ወደ ሳሎን ልገባ ስል_____ ማማና ባባ ይጨቃጨቃሉ....... .

የሀሊማ እናት እና አባት ይጨቃጨቃሉ በምን ይሆን የሚጨቃጨቁት ???በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን
#Part_➋➊

ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል

join 👇👇

@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

29 Oct, 18:49


የተሰበረች ልብ ዳግም ሰውን ማመን
አትችልም ሁሌም በጥርጣሬ ትኖራለች

.💔

PROUD_MUSLIM

29 Oct, 17:52


ያን ጊዜያቶቾ 🥺🥹

PROUD_MUSLIM

28 Oct, 17:40


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣9⃣


ምን ለማለት ፈልገሽ ነው ?? እኔማ አልሄድም በቃ ሀፍስየን አላህ ይስጣት ስራ አግኝታለች ብላልኛለች አልሄድም አለች
....ማማየ ፊት እንደዚህ ማለቷ ቢያናደኝም ማማየ በቃ እኛ እንሂድ ብለን ተነሳን
.....ቆይ እንጅ የሚበላም ብሉ አሉን ሊያቀራርቡልን እየተነሱ ሁሌም ሳልበላ ወጥቼ አላቅም እሺ ብለን ትንሽ በላልተን ወጣን

ካፌ ቁጭ አልንና ከፈቲ ጋር መጨቃጨቅ ጀመርን ሂደን ትመለሻለሽ ብላትም አልሰማችኝም አማራጭ ስናጣ እኔና ሀፍስ ከናዝሬት ተነስተን አዲስ አበባ አደርን ፈቲም ሸኝታን ተመለሰች ፡፡ ለፈቲ ደውየ ለነ ባባ አልመጣም ብለሽ ንገሪ አልኳት
.....ደውላ ነገረቻቸው እኔና ሀፍሰ ጉዞ ወደ ደሴ ከተማ ሀፍስ የተወለደችበትን ያደገችበትን ለማየት ጉዞ ጀመርን መንገዱን ሙሉ ደስ ብሎኝ ደብረ ብርሀን ቁርስ በልተን ከደብረሲና ቆሎ እና ጦስኝ ገዝተን ምሳም በልተን ዋሻዉን አልፈን ኮንቦልቻን ጨርሰን ያንን ጠመዝማዛና አስፈሪውን የሀረጎን መንገድ ጀመርነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚ አይነት መንገድ ከባድ አልተገኘም፡፡ ሀረጎን እና የደሴ ቆንጆዎችን ገጣሚዎች ዘፋኞች ሲገጥሙ ..
እንደ ሀገጎ መንገድ ሽንጠ ጠመዝማዛ
ደሴ ቆንጆ ናቸዉ ሽቷቸዉ መአዛ
ይሏቸዋል፡፡ አንድ ግዜ ከቱርክ የመጡ ሹፌሮች መንገዱ ሲከብዳቸው ምነው ባይበላስ ቢቀር የተባለለት ዝነኛው መንገድ ጨርሰን ደሴ ከተማ ጠዋት ተነስተን ዙሁር ሶላት ተሰግዶ ደሴ ከተማ ገባን

ሀፍ የሰፈሮችን ስሞች ትነግረኝ ጀመር አራዳ.ሸዋበር.መንበረ ፀሀይ ሸልፍ ተራ ፒያሳ አውቶብስ ተራ ሼል መላኩ መናፈሻ ኧረ ብዛቱ ይህን ሁሉ አልፈን ዶልፊን ሰፈር ገባን..... የነሀፍም ቤት እዚሁ ነበር ፡፡ ወደ ቤት ስንገባ በጣም ሚያምር ግቢ ነው የቤቱ ውበት ይለያል አሱርን ሰግደን ምሳ ቀርቦልን በላልተን እስከ ኢሻ አምሽተን ተኛን የሚገርም ቤተሰብ ነው

ሳዳም ናፍቆኛል አረሳሁትም ሚሴጁን እጠባበቃለሁ ጠዋት ተነስተን ቁርስ በልተን ወጣን፡፡ እኔና ሀፍስ ሁነን በቤተሰቦቿ መኪና እራሷ እየነዳች ደሴን ከተማን እያሳየችን ስታዞረኝ ዋለች ፡፡ ፍቅር የሆነ ህዝብ ፍቅር የሆነች ሀገር በጣም ወደድኳት፡፡
በፊት ደሴን ጠባብ ከተማ አድርጌ ነበር ማስባት ግን ስህተት ነበር በጣም ሰፊ ነች በደሴ ከተማ ዉስጥ ከ1.4ሚሊየን ህዝብ በላይ አቅፋ ይዛለች፡፡ የወሎ መዲናም ነች ...ታላላቅ ሰዎችን ለኢትዮጵያ እንደ ደሴ ያበረከተ የለም በማንኛውም አይነት ለምሳሌ ዉዱ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ....እናም ብዙ መፅሀፎችን በማሳተም የምናቀዉ ሁለቱ መፅሀፍ ከአቅም በላይ ሁነዉ አንባቢ ትዉልድ አጥተዉ ገና ያልቀረቡ የፍልስፍና እዉቀት ያለዉ የዳዉዶ ሰፈር ልጅ ሙሀመድ አሊ ቡርሀን ከብዙዎቹ ሁለቱን መጥቀስ በቂ ነው ፡፡

ሀፍሷ ቁርአን የሚቀራባት ኡስታዝ ጦልሀ የሚገኝበት ተቋም ሰፈር ሄድን ከጠበኩት በላይ ውብ ስፍራ ነዉ መስጊዱ ለምለም አካባቢ ብቻ አእምሮን ያድሳል ፍፁም ደስታን ያላብሳል ለህመምተኞች ትልቅ መፈወሻ ቦታ ነው ፡፡ እንደውም ዘመናዊ ነን የሚሉ ሆስፒታሎች ከኡስታዝ ጦልሀ የአካባቢ ጽዳትና አእምሮን የማደስ ትልቅ ልምድ ሊማሩ ይገባል ኧረ እንደውም እነሱም እዚህ ድረስ መጥተው በግቢው ብቻ አእምሯቸውን ማደስ አለባቸው፡፡ አሱር ሰግደን ስንወጣ ኡስታዙን በአካል አገኜሇቸው
.... እኔ ኡስታዝ ጦልሀን በጣም ትልቅ ሠው አድርጊያቸው ነበር ግን ገና አርባዎቹ ውስጥ ያለ ወጣት ነው
.......ሀፍሷ እንዴት ነሽ ምነው ቆየሽሳ ??አላት በፍቃድ ስለነበር የወጣችው
.....ኡስታዝ ገና ትላንት መጣሁ ደግሞ እሷ ነች ያስመረኳት አለችው ወደኔ እየጠቆመች ቀና ብሎ ለማየት ሀይባው ያስፈራ ነበር congra ብሎን ሄደ፡፡ ኡስታዝ ጦልሀ ያገቡ ልጆች ሁሉ አሉት ፡፡ ከዛም ወሎ ዩኒቨርስቲን ላሳይሽ ብላኝ ደሴ የሚገኘዉ ካምፓስ ወስዳ አሳየችኝ በጣም ሰፊ ነዉ፡፡ ኮምቦልቻ የዩኒቨርስቲዉ ቅርንጫፍ ነዉ ሁለት ኮርስ ብቻ ነዉ የሚሰጠዉ ደሴ ደግሞ ዋናዉ ግቢ ነዉ፡፡ ከዛም ወደ ቤት ሄድን ....መግሪብ ኢሻ ሰግደን ራት በልተን ተሰብስበን ቁጭ አልን ተሰብስበን እያወራን ነገ እንደምሄድ ነገርኳቸው
..... እንድቆይ ቢፈልጉም እኔ መሄድ አለብኝ አልኳቸዉ.....እናም የሀፍስ ወንድምየው ስልክ እያወራ ነበር...... ባክህ የሰው ሰው ደብድቦኮ ታስሯል ዋስ ሁኜ አስፈትቼው አሁን አዲስ አበባ ነው ይላል መኪናውማ እዚህ ነው ያለው ሲል ወዲያው ሳዳም ትዝ አለኝ
..... ወንድሟ የያዘው መኪና የሳዳምን የሚመስል ነው ግን ቦታ ሳልሰጠው አለፍኩት፡፡ ሱብሂ ላይ ወንድሟ እና ሀፍስ አውቶብስ ተራ ሸኙኝ እና ከሀፍስ ጋር ተቃቅፈን ተሰነባብተን ጉዞ ወደ ተወለድኩበት የአማራ ክልል መቀመጫ ወደሆነችዉ በዉበት ከኢትዮ አንደኛ ወደ ሆነችዉ ባህርዳር ከተማ ጀመርኩ
....አጠገቤ ያለችዉ ልጅ እንደኔው ተመራቂ የሆነች ልጅ ነ ከ ወሎ ዩኒቨርስቲ (ደሴ ካምፓስ) ዩኒቨርስቲ የተመረቀች ልጅ ነበረች ፡፡ ስለ ደሴ ከተማ የህዝቡ ደግነት አውርታ አልጠገበችም የሚገርመዉ ስራዋ እዚሁ ደሴ ቢሆን ተመኘች ...ብቻ እየተጨዋወትን እያወራን ባህር ዳር ገባን
....ባባ መረሀሪያ መጥቶ ተቀብሎኝ ቤት አደረሰኝ፡፡ ቤቱ ደምቋል አምሽቼ ስለገባሁ ሰግጄ ብቻ ተኛው.... ለሱብሂ ተነስቼ ሰገድኩ ሴቶችና ወንዶች ከፎቅ ምድር ቤት ይሯሯጣሉ

አክስቴ አገኝሇትና በፈቲ መበሳጨቷን ነገረችኝ እኔም ተናድጄባታለው ግን ስራ ቶሎ መጀመር ሳይኖርባት አይቀርም አልኳት
.....በቃ አሁን የአንችና የሷን ድግስ አጣድፎናል በቃ ሂጂ ብላኝ እየተጣደፈች የያዘችውን ዘይት ወሰደች

እኔም ስለፈቲ ጥያቄ ስላላበዛችብኝ ደስ እያለኝ አብሮ አደጌ ቤት ልሄድ በራፉን ስከፍተው እሷ ልትቆረቁር ስትል ተገጣጠምን ....congra የኔ ውድ ብላ እቅፍ አደረገችኝ ፡፡ ራቢ ትባላለች በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበረች አጋጣሚ ሁኖ 12ሳይመጣ ቀረ እና እሷ ቀረች
.......ፈቲስ አለችኝ???
......እንዳልመጣች ነገርኳት
...... ቢደብራትም በቃ እንውጣ ብላኝ ይዛኝ ወጣች፡፡ የሰፈሩ ሰው መሄጃ አሳጣኝ እንኳን ደስ ያለሽ እያለ ሁሉም ያቅፈኛል ቤተሰቤ በጣም የተከበረ ነው፡ ሰወች ሁሉ ያከብሩናል የደስታየ ግዜ ስለነበር ስልኬ ራሱ ረፍት አጣ ፡፡ ራቢየ ስትቆጣ ስልኬን አጠፋውት

ከብዙ ደስ የሚሉ ሰአታቶች ቡሀላ ባል እንደመጣላትና በጣም በቅርቡ እንደምታገባ ነገረችኝ ሰርጉን ያራዘመችው እኔና ፈቲ ሚዜዎቿ እንድንሆን ፈልጋ ነው ፡፡ የፈቲ አለመምጣት ያስከፋትም ለዛ ነው ደስ አለኝ ልጁ የኛው ሰፈር ልጅ ነው ዲኑ ላይ በጣም ጠንካራ ነው በዚህም ይታወቃል በቃ ወደ ቤት እንመለስ ብያት ከራቢ ጋር ዝሁር አካባቢ ተመለስን ቤቱ በሰው ተጨናንቋል መኝታ ክፍሌ ስገባ በስጦታ አብዷል

እስካሁን ድረስ የማማየን ስጦታ አላየሁትም ልየው ብየ ከፈትኩት ስከፈተው በትልቁ ተጣጥፎ የተቀመጠ ወረቀት አገኜሁ ስገልጠው ለውዷ ልጄ ሀሊማየ ይላል....
#Part_➋O

ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል.....

Join👇👇👇

@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

28 Oct, 06:59


#አውቃለሁ_ያረብ
መታዘዜ ምንም አይጠቅምህም❗️
ባንተ ማመፄም ቅንጣት አይጎዳህም❗️
ብትቅጣኝ በፍትህ...
ብትምረኝ ለማርታ የተገባህ ነህ🙏

PROUD_MUSLIM

27 Oct, 19:05


የኔ ዱዓማ ይህን ሁሉ እንድታረግልኝ
አልነበረም🤍

አላህ ሆይ 🤲

ችሮታህ በዛብኝ የሚል ሰው
አጋጥሟችሁ ያውቃል?

PROUD_MUSLIM

27 Oct, 18:14


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣8⃣


በራፏ ገርበብ ብሎ ተከፍቶ አየሁኝ ያ ያየሁት የመሠለኝ ሰው ወደ ፈቲ ቤት የገባ መሠለኝ ቀስ እያልኩኝ መጠጋት ጀመርኩ የፈቲን ድምፅ መስማት ጀመርኩ በአላህ ተው እሽ በማሪያም ይሁንብህ ቀስ በል ግን ማንንም አልጎዳም ብለህ ቃል ግባልኝ አአ ቀስ ትላለች በቃ የሆኑ ሰወች እንደገቡ ገባኝ እሷ ያለምንም ማቋረጥ ትለፈልፋለች ፍርሀቴ ጨመረ ወደ ቤት መመለስ ፈለኩኝ ግን አልቻልኩም .....ልጮህ ፈለኩ አፌ ተያያዘ ደግሞም ፈራው ከፈቲ ድምፅ ውጭ ግን ምንም አይሰማም፡፡ ጎንበስ ስል ትልቅ ዲንጋይ አየሁና አንስቼ ቀስ ብየ ገባሁ.. ከሇላው ወገቡን ወይ አናቱን ለመምታት ፈለኩኝ

የስልኬን ፍላሽ አጥፍቼ ቀስ ብየ ገባሁ ይህን ድፍረት ከየት እንዳመጣሁ አልገባኝም
..... ስገባ ግን ማንም የለም፡፡ ፈቲ ልብሷን እንደለበሰች ነው ከላይ የደረብንላት ብርድልብስ ብቻ ስትወራጭ ከአልጋው ላይ ጥለዋለች እያቀባዠራት ነበር ፡፡ቤቱ ቡርቅስቅሱ ወቷል ማታ ትተነው እንደወጣነው ነው፡፡ ፈቲ ፈቲ ስላት ዝም አለች አኡዙ ቢላሂ ብየ አልብሻት ቁጭ ብየ አይን አይኗን እያየሁ ብርድ ልብሷን ተጋርቼ አልጋዋ ላይ ተጣጥፌ ማልቀስና ስለሷ ማሰብ ጀመርኩኝ ...የድሮዋን ፈቲ ማሰብና ማስታወስ ጀመርኩኝ የሄኖክ ክፋት የቤተሰቤ እዝነት የነሱ መጎዳት የኔ ውሸት ስንት ግዚያት በንደዚ አይነት ህመም ብቻዋን እንደተውኳት ሳስብ ብቻ ብዙ ነገር ራሴን በሷ ቦታ ላይ አስቀምጬ እኔ ብሆን እሷ ዝም ትለኝ ይሆን እያልኩ ሳስብ..... የሞት ታናሽ ወንድም እንቅልፍ ወሰደኝ

ጠዋት ስነሳ ፈቲ ቀድማኝ ተነስታ ቁጭ ብላ አይን አይኔን እያየችኝ ነበር Congra መንትያየ ተነስተሻል ዛሬ ምነው ሳትቀሰቅሽኝ??? አልኳት
.....ያው እንዳልቀሰቅስሽ ብየ ነዋ ስትለኝ ከልብ የመነጨ ፈገግታ ፈገግ አልኩኝ
....ሀሊማየ አለችኝ
......ወይየ ፈቲየ አልኳት የማታውን ነገር እንዳታነሳብኝ ከልብ ራሴን እየተማፀንኩ
.....ይሄ ሁሉ ነገር ምን ተፈጥሮ ነው ግን??? አለችኝ አጎንብሳ መሬት መሬቱን እያየች
....እኔ ራሴ የት እንዳደርኩኝ ስነሳ ነው ያወኩት አልኳት ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል
......ሀሊማየ ከምሬ ነውኮ አትቀልጂ ማታ ከነ ባባ ተለይተን ስንመጣ ብቻ ነው ማስታውሰው እዚ ቤት ውስጥ ምን እንደተፈጠረ የማቀው ታሪክ የለም አለችኝ ግን የማቀው ነገር ቢኖር ለሱሴ ማስታገሻ ሳጣ እንደዚ እንደሚያደርገኝ ነው ብላ ሲጋራዋን ለኮሰች
..... እኔ ፊት ይህን ያክል መዳፈሯ ቢያናደኝም የማታው አይነት እንዳይደገም ፈራሁ ወዲያው ግን ውርውር እያደረገችው ሀሊማየ ወላሂ ረስቼው ነው ይቅርታ አለችኝ
.....ችግር የለም ፈቲየ ብየ ወደ ማማየ ጋር ሄድኩኝና ሠላም ብያቸው ለመስገድ ውዱዕ ማድረግ ጀመርኩኝ፡፡ ሀሊማየ ስልክሽ እየጠራ ነው ሀፍስ ነች አለችኝ
..... አንሽዋ አልኳት
አንስታ ካናገረች ቡሀላ ቶሎ ኑ እየተባልን ነው አለች
.....ምነው ምን ተፈጠረ??? ስላት
.....እነ ማማ ሊሄዱ ነው የሰፈር ሰው ሳይሞት አይቀርም አለችኝ ፡፡ እኔ የሞተው ሰው ሳይሆን ያሳሰበኝ አሁን ስንሄድ ወደ ባህር ዳር እንውጣ እንዳይሉን ነው

...ፈቲን ለምን ማታ እንደዚህ እንዳደረገች ስጠይቃት
.....ሀፍ ስትመጣ ነው መድሀኒቴን የደበኩት እንደዚህ ይጠፋኛል እረሰዋለው ብየ አላሰብኩም ነበር አለች

ሱብሂን ሰግጄ ስጨርስ ፈቲ እንድታጨስ እንድፈቅድላት ጠየቀችኝ
.....እዛ ሂዳ ተወዛግባ ከምታወዛግበን ብየ እሽ አልኳት ሺሻዋንና ሲጋራዋን አከታተለችው ወዲያው ለሲጋራዋና መጥፎ ሽታዋ ማጥፊያ ዶዶራንትና ሺቶ ተቀባባችና ማስቲካ አላምጣ ሄድን

ስንሄድ ሁሉም ተነሳስተዋል የነጁም ቤተሰቦች ጭምር ባባ ወደኛ እያየ ልጆቼ በቃ እናንተ ከነገ ወዳ ድረስ እንድትመጡ መጨረስ ያለባችሁን ጨርሱ፡፡ ፈቲን ደግሞ ባንድ ግዜ ስራ ማገኜትሽን ምነው ሳትነገሪን ???ለማንኛውም ከባህር ዳር ተመልሰሽ ትጀምሪያለሽ አለ
....ሁላችንም ተያየን ሀፍስ ወዲያው ጠቀሰችን ምን አይነት ፈጣን አስተሳሰብ ነው ግን?? ሁሌም ሀፍ ያለችበት ነገር ይገራልኛል ፡፡ እኔ ምን ልላቸው ነው ብየ እያሰብኩ እሷ ግን አቅለዋለች ተሳሳቅን ፡፡ሀፍ ወድያው ያው እሷማ ሰርፕራይዝ ልታደርጋቹ ነበር አልተሳካም እንጅ እኔ ተነፈስኩት ስትል ሁላችንም ተሳሳቅን

ቤተሰቦቻችን ሁሉም ወደ ባህርዳር ሄዱ የሀፍ ወንድምም ወደ ደሴ ከተማ ተመልሶ ሄደ ፡፡ ሀፍ ከእነ ሀሊማ ጋር እመጣለሁ ብላ ቀረች ፡፡ ለአንዳንድ ወጭ ተብለን ብዙ ብር ሁሉም ሠጡን

ከሄዱ ቡሀላ ሁላችንም ወደ ሀፍስ አፈጠጥን
.... ምን ታፈጣላችሁ ??? በቃ የመሰለኝን ጥሩ ነው ብየ ያሰብኩትን ነው ያረኩት ብላ ዘወር ስትል ፈቲ ተንደርድራ እቅፍ አድርጋት አለቀሰች
.....አታልቅሽ ፈቲ አለቻትና እንባዋን ጠራረገችላት በቃ መመለስና መጨረስ ያለብንን እንጨራርስ አለች ፡፡እሺ ተባብለን ሄድን የመጀመሪያ ቀን በጣም ወረፋ ሆነብን ሀፍስ መምህሯን አግኝታ እሱ ጨራረሰልን ፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ምሳ ተሰብስበን ከዝሁር ቡሀላ በላንና ተሰብስበን ማማየ ቤት ሄድን
.....ልክ ማማየ ቤት ስንገባ ይህን ቤት አቅዋለው አለች ሀፍስ
.... ማማየ እና ሀፍ ገና ሲተያዩ ተሯሩጠው ተቃቀፉ ፡፡ልክ እንደተነፋፈቀ ሰው በጣም ተሰላለሙ እና ወደቤት ገባን
....ማማየን ታቋታለሁ እንዴ ??አልኳቸው
.... ውይ ይህችንማ ልጄን አንድ ግዜ አሟት አግኚቻት ነበር ከዛም ወደ ቤት አመጣሇት ስተረጋጋ ወደ ሰፈሯ እንድትሄድ ሸኜሇት አሉኝ

ሀፍ አንድ ግዜ ለብቻዋ ወጥታ ያጋጠማትን የነገረችኝን አስታወስኩ
.... እናንተስ እንዴት ተዋወቃችሁ??? አሉን ማማየ
....እኛማ አንድ ክፍል የምንማር ተማሪዎች ነበርን አለች ፈቲ ፡፡ ሀፍስ በተራዋ እሳቸውና እናንተ እንዴት ተዋወቃችሁ ???አለች
.....እኛማ የፈቲን ቤት ልንከራይ ስንመጣ ነው አልኳት
.........አሀ ፈቲ እዚህ ነዋ የተከራየችው ???በይ ቤትሽን አሳይኝ ብላ ተነሳች
ጠዋት ሳናዘጋጀው ስለወጣን እኔም ፈቲም ፈራን
.....ነያ አሳይኝ??? ስትላት ሁሉችንም ተነስተን ሄድን

ስንገባ ቤቱ ፅድት ተደርጓል፡፡ ደስ የሚል ሽታ አምጥቷል ፡፡ እኔና ፈቲ ገርሞን ማን እንደአዘጋጀዉ ተያየን
.....በጣም ያምራል አለች ሀፍስ

ተመልሰን ማማየ ጋር ገብተን ወደ ባህር ዳር ነገ ልንሄድ እንደሆነ ስነግራቸው
__ፈቲ ምን አላችሁ ??? ባህርዳር ልንሄድ ነው??? ትቀልዳላችሁ አለች
.......ሁላችንም አፈጠጥንባት.....


#Part_19

ከ 50👍 ቡኋላ

ይቀጥላል...

Join👇👇👇

@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

27 Oct, 12:47


"ዓለምን ያለሰይፍ የከፈታችሁ!
የኢስላምን ጦር ያሳረፋችሁ ብርቱዎች!
ስብስባችሁ ሁሉም ሥፍራ የደረሰ!
ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ጎናችሁ ያላረፈ!

በዘመናችሁ የኢስላም ጠላቶችን ረፍት ነሳችሁ!
ሚሽነሪዎችን አደከማችሁ!
ዱር ገደሉን አልፋችሁ እልም ካለው ገጠር መሐል ከተማችሁ!
ምቾታችሁን ትታችሁ ወንድሞቻችሁን ለማዳን ራሳችሁን ሰዋችሁ!

እናንተ የዳዕዋ ሰዎች ሆይ!
ማንም ጋር ያላየነው ሺህ ፍቅርና መውደድ በእርግጥም እናንተ ዘንድ ነበር። አኽላቅና ዙህድን የተማርነውም ከናንተው ነው። በር አንኳኩታችሁ ዘይራችሁ ተሰድባችሁ ተባራችሁ በትዕግስት እንደፀናችሁ ስንቱን ከመስጂድ ጋር አስተዋወቃችሁ"

በታላቁ ሙጃሂድ ዐብደላህ ኢብኑ አዛም ንግግር ፅሑፌን ልቋጭ
"ምርጥ ስነ ምግባርን የተላበሱ ሙጃሂዶች" ይሏቸዋል ስለነርሱ ሲያወጉ።
"ሰካራሞችን ከቡና ቤት ወደ መስጂድ እጃቸውን ይዘው እየተራመዱ ረጅሙን መንገድ አብረዋቸው ይጓዛሉ። መስጂድ አድርሰዋቸው እነርሱ ይመለሳሉ።
ልዩነታችን እንዳለ ሆነ በአንድ ነገር ውስጥ ያለውን መልካም ነገር እናጣጥላለን ማለት ግን አይደለም"

@STRONG_IMAN
@STRONG_IMAN

PROUD_MUSLIM

27 Oct, 11:41


አላህ

መጀመሪያውን ሳይሆን መጨረሻውን ያሳምርልን😊

PROUD_MUSLIM

27 Oct, 04:55


ስታለቅሱ አብሯቹህ ያለቀሰን ሰዉ
ስትስቁ ባይኖር እንኳን ፈልጉት ::

መልካም ትዝታንም ፍጠሩበት ::

PROUD_MUSLIM

26 Oct, 17:45


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣7⃣


እቃወቿን መወርወርና መስበር ጀመረች ፊቷ መለዋወጥና ጅማቶቿ መገታተር ጀመሩ
... ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ ፀጉሯን መንጨት ጀመረች ማማየ ጩኸቷን ሲሰሙ በራፉን ገፍትረው ገቡ እሷ ጩኸቷን ማቀዝቀዝ ጀመረች ልይዛትና ላቅፋት ፈልጌ ግን አልቻልኩም የመጠጦቹ ጠርሙሶች ለምልክት እንኳን መጥፋታቸው ከሷም አልፎ እኔንም እያስገረመኝ ነው

ሀሊማየ በራፉን ዝጊው አሉኝ ማማየ በጃቸው የያዙትን ነገር አውጥተው እየሰጧት ተንደርድራ ቀማቻቸውና ባፍንጫዋ መሳብ ጀመረች፡፡ አንድ ግዜም እንደዚሁ ስታደርግ አይቻታለው በማማየ ነገር ግን ግራ ተጋባው ምንድን ነው ያደረጉት እንዴት ምንድን ነው የሰጧት ግራ ገባኝና ሲወጡ እጠይቃቸዋለው ብየ ሀሳቤን ወደ ፈቲ መለስኩ፡፡ ፈቲ ማማየ የሰጧትን ነገር ካሸተተች ቡሀላ በትንሹም ቢሆን ወደ ራሷ ተመለሰች ተረጋግታ ማሰብ ስትጀምር
እሷ ቁም ሳጥን ብላ የምትጠራትን ትንሽየ የልብስ ማስቀመጫዋን ከፈተች ውስጥ የተቀመጡትን ልብሶች መወርወርና እጇ የገቡትን ስስ ልብሶች መቅደድ ጀመረች ሁሉንም አውጥታ እንደጀመረች ከልብሷ ስር የተቀመጠውን የትምህርት መረጃዋን ወረወረችው፡፡ እንዳትቀደው ፈርቼ ሩጬ አነሳሁት ለነገሩ ብትቀደውስ ከዚ ቡሀላ ህይወት አለኝ ብላም የምትማር አይመስለኝም ጭራሽ እንደውም ወረቀቶቹንም ባይኗም ማየት የምትፈልግ አይመስለኝም የሚገርመው ግን አስቀምጣዋለች

ወዲያው ከወረቀቶቹ ስር ሌላ ፌስታል አውጥታ ፈታችው ብዙ ሺሻና ሲጋራ ተቀምጧል ከዛ ሌላ በቢልቃጥ የተያዘ ፈሳሽ መዳኒትና መርፌ ተቀምጧል ወላሂ ፈቲ መሆኗን ረስቼ ፊልም እያየሁ ነው የመሰለኝ በቃ ምንም ሳልል ማየት ጀመርኩ፡ መርፌውን አውጥታ ከቢልቃጡ ላይ በመቀነስ ራሷን ሶስት ግዜ ወጋች እጄ ሲደነዝዝና ሺባ ሲሆን ይታወቀኛል እኔን የተሰማኝን ትንሽ ህመም እንኳን ራሷን ስትወጋ ተሰምቷት ይሆን??? እንጃ
በዚ ሰአት እንኳን ቢቆርጧትም የምትሰማ አይመስለኝም እንባየ ያለማቋረጥ ይፈሳል፡፡ ማማየ መተው አቀፉኝ ጥምጥም ብየ አለቀስኩኝ ማማየም ሲያለቅሱ ይታወቀኛል ግን አውቀውና እያስመሰሉ መሰለኝ ምክንያቱም ቅድም የሰጧት ነገር ሲያረጋጋት ተመልክቻለው ፈቲ እየተረጋጋች መምጣት ጀመረች

የሆነውን ሁሉ ቀስ እያለች ማየት ጀመረች ቤቱ ተበለሻሽቷል እቃወች ተሰባብረዋል እኔና ማማየ ተቃቅፈን እያለቀስን አየች ምን እየሆነ እንደሆነ አልገባትም ለምን ቤቱን እንደዚ እንዳደረግንባት አልገባትም ለምን ቁጭ ብለን እንደምናለቅስ የገባት አልመሰለኝም፡፡ በቃ ተቀየርንባት ሁሉም ግራ አጋብቷታል ይባስ ብላ ሄኖክ የሰጣትን የምትወደውን የቤት እቃ ለምን እንደሰበርኩባት የተሰባበሩትን የእቃውን ክፍሎች እያነሳች ትጠይቀኝ ጀመር በምሀል በምሀል ከት ብላ እየሳቀች ሀሊማየ ሁሉንም ስበሪው እሽ ካንች የሚበልጥ ነገር የለም ፡፡ ማማየ ያንን ሄኖክ ሚባል ውሻ ቤት እንዳያስገቡት እሺ... እሱ ነው ሀሊማየን እንደዚ የተጫወተባትና ህይወቷን ያበላሸው ብላ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች ....ትንሽ ቆይታ ደግሞ ሄኖክየ ምን ሁኖ ነው ቀረሳ ትላለች ፡፡ ወላሂ አንደዚህ ሁና አይቻት አላቅም ማንም እንደዚ አይነት ዝብርቅርቅ ያለ ንግግር ሲናገር ሰምቼ አላቅም ፡፡

ሠው ግን እንዴት ራሱን ይረሳል ?? የእውነት ግን ፈቲ ራሷን ነው እንደዚ ስትሆን ማያት እኔ ራሴ ሳብድ ይታወቀኛል፡፡ በሷ ሁኔታ ፀጉሬን ዳግም እንዳያበቅል አድርጌ ነቃቅየ ልጥለው ነው ሁሉም ነገር ፊቱን አዞረብኝ ማማየን እንኳን ፈራሁኝ ለምንድን ነው ግን እዚ ከመጣው ቡሀላ ሁሉም የከፋብኝ ??ያመንኳቸው ራሱ ለምንድን ነው የሚክዱኝ?? ለምን ጥፋቴ ምንድን ነው??? ከምንም በላይ የምወዳት ፈቲ ራሱ አይኔ እያየ አንደዚ ስትሆንብኝ እንዴት ነው ስለ ራሴ አለመለወጥና ራሴን አለመርሳት ያላሰብኩት?? ምን አይነት ፍጥረት ነኝ ግን??


ፈቲ ከብዙ ሳቅ ለቅሶና እንኳን ለሰሚ ለራሷ እንኳን ግራ ሚያጋቡ ወሬወች ቡሀላ ተኛች ፡፡

ሀሊማየ ተነሽ ከኔ ጋር እንሂድ ብለው አነሱኝ መራመድ አቅቶኝ ማማየ ደግፈውኝ ነው የሄድኩት ቤት ስገባ ሶፋቸው ላይ አስቀመጡኝ እና ጋቢ አለበሱኝ ሀሊማየ ከምን ምን ብየ እንደምጀምርልሽ አላቅም ቅድም ለፈቲ የሰጠሇት ነገር ልጄ ትጠቀመው የነበር ነው የልጄ ነበር ልጄም ስታጣ እንደዚ ነበር ሚያደርጋት እሷ ከሞተች ቡሀላ ብዙ ግዜ ልጥለው አውጥቸው ነበር ፡፡የመጀመሪያ ቀን አንችንና ፈቲን ሳያቺሁ ልጄን አስታወሳችሁኝ አንድ ቀን ታዳ ፈቲ ስታጨስ አየሇትና አስቀመጥኩት እና እንደዚ ሲያደርጋት ወስጄ አሰጣታለው አሉኝ
...... አለቀስኩኝ መተው አቀፉኝ እንዴት ግን ላልጠፋ ቀን ለስንት አመታት ስጠብቀው በነበረው የደስታየ ቀን የሀዘን ምሽት ላሳልፍ በቃ ደህ እደሪ ሀሊማየ ብለው ተረጋጊና ተኝ ብለው ወደ መኝታ ክፍላቸው ሄዱ፡፡ ሳስብ አደርኩኝ ለሊት ላይ ፈቲን ደህንነቷን ማወቅ ፈልጌ እንደምንም ተንገዳግጄ ተነሳው በራፉን ቀስ አድርጌ ከፍቼ መሄድ ጀመርኩ ......የሆነ ሠው ውልብ አለኝ አኡዙ ቢላሂ ብየ ወደ ፈቲ በራፍ አመራው በራፏ ገርበብ ብሏል......
#part_18

ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል.....

Join👇👇👇


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

26 Oct, 08:45


አላህ ቅርብ ነው🥰

PROUD_MUSLIM

26 Oct, 06:05


ወደኃላ መመልከታችን
ምን ያህል ትተን እንደመጣን
ለማወቅ እንጂ ለመመለስ እንዳይሆን!


@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

25 Oct, 17:42


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣6⃣



ሆቴል ደርሰን እኔና ሀፍ ነጁ እና ፈቲ ትተናቸው ወጣን እና ሀፍ ሁሉችንንም እያየች ወደ ፈቲ ዞረችና እና እንዴት ብለን ነዉ ለቤተሰቦችሽ ከዩኒቨርስቲ መጫርሽን የምናሳውቀው????? አለች.....

እንጃ ሀፍ እኔም ግራ ገብቶኛል አለቻት ነጁ ፡፡ ትንሽ አሰብ አደረገችና አንድ የማቀው ልጅ አለ እኛ እንደውልለትና እናናግረው ትንሽ ብር ከፍለነው ጋወንና የተሳሳተ መረጃ ይስራልን አለች ነጁ ፡፡
.....ይሄ ጥሩ ሀሳብ አይደለም መጥፎ ነገር ይዞ ይመጣል ባይሆን ሁሉንም እውነታ እንንገራቸው ነጁ ያልሽው ነገረ ግዚያዊ መፍትሄ ነው የሚሆነው ለነገሩ አሁን የተጋረጠብንን ችግር ማስወገዱ ይቀላል ስለዚህ እናድርገው ተባባልንና ደወልን ለልጁ
..... ሲደወልለት ከግቢ እንደተባረረ ነገረን ግን ሌላ መፍትሄ እንዳለው ነገረን ------- ሄኖክ የሚባል ጓደኛ አለኝ እሱ ያሰራላችሇል አለ..... ነጁ ቶሎ ብላ ስልኩን ዘጋችውና እኔ መቼም አላደርገውም ያ ሸይጧን አላህ ገላግሎኝማ ተመልሼ አልሄድም አለች

ሁላችንም ዝም አልን በቃ ሄኖክ ጋርማ እኔው ራሴ አናግረዋለው አትጨነቁ አለች ሀፍስ
....እሱ ጋር የነበራትን ግንኙነት ስለማታቅ ምን ብላ አፈጠጠችባት
... አወ አናግረዋለው ብላ ሄደች ሀፍ

እየሆነ ያለው ነገር አልገባትም ግራ ስትጋባ ሁሉንም ነገር ነገርኳት አንቺም የታመምሽዉ ያዘን ቀን ድንቹን ከበላሽ ቡሀላ እንደባሰባት እና የፈቲንም ሂወት ነገርኳት

በጣም አለቀሰች የጭካኔውን ጥግ አየችው የሰውን ብር አምላኪነት ተረዳችው፡፡ አዝናም ዝም አለች ከጠዋት ነበርና አዳማ የገቡት ለምሳ ተደወለልንና ወደ ሆቴል እየሄድን ሳለ ፈቲ ደወለችና አብረን ሄድን፡፡ በነገራችን ላይ ሀፍ መኪና ስለምትነዳ የወንድሟን መኪና ይዛ ነበር
....ፈቲ እሽ ብሏል አለች

ሀፍሳ ማውራት እየፈለገች ግን ዝምታ ዋጣት ተሰብስበን ምሳ ከበላን ቡሀላ የነጁም ቤተሰቦች አዳማ ገቡ እነሱንም ተቀብለን ይዘናቸው ከኛ ቤተሰብ ጋር ቀላቀልናቸው፡፡ የነጁ አባት የያዙት መኪና በጣም ያምራል ሄኖክም ላሰራበት ስራ 5000ብር ጠየቀንና ሠጠነው ከዛ ቡሀላ አይቼው አላቅም

የደረጃ ተመራቂ ነኝ ..ዛሬ ቀኑ የምረቃ ቀኔ ነው ዛሬ ሄኖክ ሁሉንም ነገር አመቻችቶላት ፈቲም በፎርጂድ መረጃ እና ጋወን እየተመረቀች ነዉ ፡፡ ፈቲ ትስቃለች ፎቶ በፎቶ ሆንን የውሸት እንደሆነ ቢታወቅ ምን ይባል ይሆን??? የውሸት ሳቅ መሆኑ ቢታወቅ ምን ይፈጠር ይሆን ????

ሀፍ በፈዘዙ እይታወች እኛን እየተመለከተች በሀሳብ ሂዳለች ፡፡ አሳዘነችኝ ይችን ቀን ስንት ዘመናት ጠብቃት ነበር ወንድሟ መቶ ሲያቅፈት ደረቱ ላይ እየተኛች እቅፍ አድርጋው አለቀሰች እንባየ መጣብኝና ፈሰሰ
.....ፈቲ ምነው አለቀሽሳ?? አለችኝ
... ሀፍን ሳሳያት ፈቲም አለቀሰች ውሏችን ያምር ነበር፡፡ ሳላስበው ማማየን አይሇቸው ደስ አለኝና ሄድኩኝ በእጃቸው የታሸገ ነገር ሰጡኝና ሀሊማየ የኔ ልጅ እደጊ ተባረኪ አላህ ይጠብቅሽ ትልቅ ደረጃ ድረሽ ውለጅ ክበጅ መንትያሽን ደግሞ ጠብቂ አሉኝ ፈቲን መሆኗ ነው
.....እሽ አልኳቸው በቃ የኔ ልጅ ደና ሁኚ እቤት መተሽ ደግሞ እይኝ አሉና ሄዱ በጣም ደስ አለኝ ወደነ ሀፍ ተመለስኩና ሀፍ ጋር ሂጄ ቁጭ አልኩኝ ውሎዋችንን በስጦታና በስልክ ስንጨናነቅ ዋልን

ሀፍ ከመጣች ጀምሮ አሟት አያቅም
.....ሀፍየ እንዴት ነው ያ የሚያምሽ ነገር ተሻለሽ ???አልኳት
......ያንንማ አልሀምዱ ሊላህ ኡስታዝ ጦልሀ ጋር እየተቀራብኝና በቁርአን ውሀ እየታጠብኩ ደህና ሁኛለው አለችኝ
.....ኡስታዝ ጦልሀ ደግሞ ማናቸው ???አልኳት
.... ......ኡስታዝ ጦልሀ ማለት ከደሴ ከተማም አልፎ ጎረቤት ከተሞች የሚታወቅ ታላቅ ዳኢና ኸይርን ብቻ የሚፈልግ ሠው ነው ፡፡ ከጦሳ ተራራ ስር ተቋም ሠፈር ነው የሚገኘው የራሱ ኢስላማዊ የሆነ አሊፍ የሚባል ትልቅ ት/ቤት መስጊድ አለው ፡፡ ት/ቤቱ ተምሪያለው መስጊዱና መማሪያ ግቢያችን በአጥር ነው ሚለያየው፡፡ አዳሪ መድረሳም አለው ቁርአን ሂፍዝ ሀዲስ ያስቀራበታል፡፡ በአመት ረመዳን ላይ ሙሉ የደሴ መስጊዶች በየራሳቸው የመረጧቸውን ድምፀ መረዋ የሆኑት ሁፋዞችን በመውሰድ እንዲያሰግዱ እድል ያሰጣቸዋል፡፡ በተለይ በተለይ አስርቱ የለይል ተሀጁድ ስግደቶች ላይ ጎልተው ይታያሉ፡፡ ሊላህ ብሎ የሚቀራባቸው ልጆችና ቁርአን ውሀ ላይ ቀርቶ የሚሰጣቸው ሰወች የፈወሳሉ፡፡ አሁን ላይ ለገንዘብ ብለው ከተቋቋሙ ሩቃ ቤቶች አስር እጅ ይበልጣል በጣም የታመሙ ሰወችን እዛው የራሳቸውን ክፍል ይዘው ይንከባከባቸዋል፡፡ አቅም የሌላቸውን በአቅማቸዉ ደሀ የሆኑ ሰወች ምግብ ሙሉ በሙሉ በመቻል ከህመማቸው እስኪፈወሱ ድረስ ያደርጋል፡፡ ይህንን ለአላህ ብሎ መስራቱን የተመለከቱ የደሴ፡ሀይቅ፡ኮምቦልቻ፡ኬሚሴ አዲስ አበባ ድረስ ይሄዳሉ፡፡ ቀን በቀን ግቢው በሰወች ይጨናነቃል፡፡ እኔም ለራሴ ክፍል ተሰቶኝ ነበር.... አሁን ራሱ ወደ አዳማ ስመጣ አቋርጨው ነዉ የመጣሁት..... እናም ወደ ደሴ ስመለስ እጀምራለው ከዛ ቡሀላ ብዙ አልቆይም ወደ ስራየ እመለሳለሁ አለችኝ
...... በጣም ተደሰትኩኝ


እኔና ፈቲ የመጡልንን የቴክስት መአቶች ስንመልስ አመሸን ወዲያው Congratulation የኔ ተናፋቂ ስለጠፋው ሶሪ አሁንም ላወራሽ ስለማልችል ባይ ሀሊማየ የሚል የሳዳም ቴክስት ገባልኝ ፡፡ በጣም ተደሰትኩኝ ግን ላወራሽ አልችልም ማለቱ አስከፋኝ ሙሉ ቀን ስጠብቀው ነበር እሺ ቢያንስ ትንሽ አውራኝ??? አልኩት ,....መልስ የለም


እራት ሰአት ደረሰ እራት ተሰብስበን በላን ይህን የሚያስጠላ ኑሮ ልገላገለው መሆኑን ሳስብ ደስ ይለኛል.... ግን ፈቲስ??? ብየ ትዝ ስትለኝ ይጨንቀኛል ሁላችንም ከእራት ቡሀላ ተለያየን

ፈቲ ሱሷ ሊገድላት ደርሷል አብሪያት እቤት ሄድን፡፡ ገና ከመግባታችን ሲጋራዋን የምታስቀምጥበትን ማተራመስ ጀመረች ምንም አይነት ነገር የለም መጠጧም የለም ሌላው ቀርቶ ምንጣፍ ስር የምታስቀምጠው ሺሻ ራሱ የለም

እቃወቹን መወርወርና መጮህ ጀመረች ማን ሊወስድ ይችላል???? ያውም በዚህ ቀን......
@part_17
ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል........


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

25 Oct, 15:14


ለሰዎች ደስታ ማሰብ ግን እንዴት ደስ ይላል።


@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

25 Oct, 13:04


በሰሜን ጋዛ ሰርጥ በሚገኘው ከማል ኡድዋን ሆስፒታል ውስጥ የነበሩ ፍልስጤማዊያንን የወራሪዋ ጦር ልብሳቸውን አስወልቀው በአደባባይ ሰብስበው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

እጅህን ከፍ አድረግ ዱዓ አድርግላቸው። አላህ አላህ ፊ ጋዛ!

#Mahi mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

PROUD_MUSLIM

24 Oct, 19:13


መልካም ስነ ምግባር
ሁሉንም መንገድህን ብርሀን ያረግልሀል!
:¨·.·¨: ❀
 `·. @Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

24 Oct, 10:37


ከሌላው ሪዝቅ ዐይንህን ዝቅ ስታደርግ ትረዘቃለህ።

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

23 Oct, 18:15


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣5⃣


ጠዋት ከወሰደኝ እንቅልፍ ስነሳ ጁኑብ ሁኛለሁ፡፡ አልጋዉ ላይ ተዘርሬ ተኝቻለሁ.... እንዲሁም ደም ታፋየ አካባቢ ፈሷል፡፡ እኔ ምንም ነገር ትዝ ሊለኝ አልቻለም ሀይድ ሁኜ ነው ብየ ዝም አልኩ......

ሀይዴ ግን ከዛን ቀን ቡሀላ ቀረ ፡በቃ የሆድ ህመሜ ምክንያት ነው ብየ ዝም አልኩ

ግዚያቶች ነጎዱ ፈቲም ሰሞኑን መድሀኒቷን አግኝታ መፍለቅለቅ ጀምራለች እንደእዛ ሁና ማየቴ ለኔ ትልቁ ደስታየ ነበር ፡፡ሳዳም የምር ናፍቆኛል በቃ ሁሌም ስልኬን ማየት የፃፃፍናቸውን ረጃጅም ቴክስቶች ማንበብ ስራየ ሆነ፡፡ ቴክስቶን ሳነብ ናፍቆቱ ይጨምርብኛል መመረቂያ ቀኔ በጣም ቀርቧል ሳምንት ነው የሚቀረው..... ባባ ደወለልኝና ወደ አዳማ እየመጡ እንደሆነና ያልጠበኩትም ሰርፕራይዝ ይዞ እየመጣ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ ምን ሊሆን ይችላል??? እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ ፡፡

ፈቲ ጋር ካፌ ቁጭ ብለን ነበር
.....ፈቲን እነ ባባ እየመጡ ነው ምንድን ነው ምናደርገው ???አልኳት
.....ለቤተሰቦቻችን ምን እንደምላቸው እየጨነቀኝ እኔም ግራ ገብቶኛል ሀሊማየ አለችኝ ፡፡በስራዋ እፍረት ውስጥ ገብታ እነሱ ወደ አዳማ እየደረሱ ነዉ አልኳት
..... .....በድንጋጤ ምን አለችና ተነሽ ተነሽ አለችኝ ደንግጬ ተነሳሁ ....ምን እየሆንሽ ነው??? ተረጋጊ እንጂ አልኳትና ጎትቼ አስቀመጥኳት ፡፡

በቃ እንደዚህ እናድርግ አሁን እነሱ ሲመጡ ሆቴል ነው የሚያርፉት ስለዚ ቀበጥነትሽን ተጠቅመሽ እናንተ ጋር ነው መሆን የምፈልገው በያቸው አልኳትና ለነጁ ደወልኩላት.... እዛው አካባቢ ስለነበረች መጣች ፡፡ለነጁ ሳማክራት ትንሽ ትጨናነቀች ፡፡ ከ ደቂቃዎች ቡሀላ አንድ ዘዴ መጣልኝ ለምን እንደዚህ አናደርግም??? ብላ አፈራርቃ አየችን
.......ሁለታችንም ለመስማት እየጓጓን ምን እናድርግ ???አልናት
____በቃ ቀን ቀን አብረናቼው ውለን ማታ እነሱን ሆቴል ካስገባችሁ ቡሀላ አንችም ወደ ግቢሽ አንችም ወደ ቤትሽ አለችን፡፡ አላህ ይስጣትና ከትልቅ ጭንቀት ገላገለችን ኡፍፍ ብየ የጭንቀት ትንፋሼን ገፋሁት፡፡ በጣም ቀለለኝ በነገራችን ላይ የደረጃ ጥሩ ዉጤት ካመጡት ተመራቂ ነኝ፡፡

የኔ ሌላው ጭንቀቴ የምረቃ ቀንና ከዛ ቡሀላ ያሉት ቀናቶች ናቸው፡፡ የፈቲ ስልክ ጠራ... ፈቲ ስልኳን እያየች ደስ ሲላት ተመለከትኩ
....ምን ነዉ የደወለዉ ??? ስላት
..... ሀፍስ ደወለች አለችኝ አንሽዋ ብያት ቀማሇት ወላሂ ናፍቃኛለች እኔ ላዋራት እያለች እንባ ባቀረሩ አይኖች አይን አይኔን እያየች እየተስለመለመች ስትለምነኝ አሳዘነችኝና ሰጠሇት
.....ወዲያው አንስታ እያለቀሰች አወራቻት ና ስልኩን ሰጠችኝ ማውራት ጀመርንና ኮንግራ ልበላችሁ ብየ ነው በቦታው ላይ ስላልተገኘሁ ይቅርታ በጣም እወዳችሇለሁ መልካም የምረቃ ግዜ ብላ ዘጋችው
ሀፍሷ አንጀቴን በላችኝ ወላሂ ባልመረቅ ደስተኛ ነኝ ፈቲንና ሀፍን አጥቼ አሁንኮ ሀፍ ከኔጋር የደረጃ ተመራቂ ኦር የዋንጫው አሸናፊ ትሆን ነበር ፈቲም እንደዛው ወላሂ ሶስታችንም ባንለያይ ኑሮ ትምህርት ቤቱ እኛን ለማበላለጥ ይቸገር ነበር እኩል ውጤት አምጥተን 4 ዋንጫ ማዘጋጀት ግድ ይለው ነበር፡፡ ሶስቱ የኛ አንዱ ደግሞ የሌላ ሌክቸር ተማሪ ይሆን ነበር

ሄኖክና ያች ገንዘብ አምላኪ አላህ የስራቸውን ይስጣቸዉእና ሁሉንም ነገር አበላሹት፡፡ መቼም ቢሆን እነዚህን ሁለት ሰወች ይቅር አልላቸውም የምወዳቸውን ሠወች ከጎኔ አርቀው የኔን ህይወት በጭንቀትና በሀሳብ በብቸኝነት የሞሉት ሰዎች የኔንም የምወዳቸውንም ሰዎች አላማና ሀሳብ ባጭር የቋጩ እርኩሶች ናቸው እና በየትኛው የርህራሄ ልቤ ይቅር ልበላቼው??? እንዴትስ ብየ ላስበው??? የማይሆንና ማይታሰብ ነገር ነው

እኔስ ተመረኩኝ ፈቲን ሱሰኛ የግዚያዊ ስሜቱ ማርኪያ አድርጓት ሀፍን ደግሞ በበሽታ ላይ በሽታ ጨምሮ ከምንም ውጭ ያደረጋት የሠው እርኩስ ነው የህይወቴ ሁለት ጥላሼቶች ናቸው


ከተወሰነ ሰአት ቡሀላ ባባ ደውሎ ናዝሬት እንደደረሱና ያሉበትን ቦታ ነገሩን በኮንትራት ባጃጅ ሶስታችንም ሄድን ...ቤተሰቦቻችን ያለንበት ቦታ ስንደርስ ሁሉንም ተራ በተራ ሰላም እየተባባልን ተቃቀፍን፡፡ ሁላችንም ደስ አለንና ኮንትራት ወደ ያዝነዉ ባጃጅ ልንገባ ስንል .......ከአንድ ጥቁር መኪና እኔንስ አታቅፉኝም??? ብላ ወጣች
....ዘወር ብለን ስንመለከት ሀፍስ ነበረች ሁላችንም ደርቀን ቀረን ተንደርድራ መታ አቀፈችኝ ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ማልቀስ ጀመርኩ ስቅስቅ አልኩኝ፡፡ ሀፍስ መሆኗን ራሱ ስታቅፈኝ ነው ያወኩት ነጁም ፈቲም እዛው አቅፈውን ማልቀስ ጀመርን ተላቀቅንና መልሰን ተቃቅፈን አለቀስን ፈቲ ጋር ተቃቅፈው ለረጅም ሠአት ተላቀሱ... ነጁም ጋር እንደዚሁ በጣም ገረመኝ፡፡ ለአላህ ብሎ የተመሰረተ ጓደኝነት ለካ እስከ ጥግ እንደሆነ ተሰማኝ ሀፍሷ ከደሴ ከተማ ጀምራ 500KM አቆራርጣ ለኛ ምርቃን መምጣቱ ወላሂ በህልሜም ትዝ ብሎኝ አያቅም፡፡
አክስቴ/የፈቲ እናት/እና ....የኔ እናት አብረውን አለቀሱ ሁሉም ሰው ያለቅስ ነበር ፡፡ ከነ ባባ በላይ የሀፍ መምጣት አስደሰተኝ ይህንን የሸይጣን ተግባር ባይፈፀም ኑሮ በለቅሷችን ፈንታ በሳቅን ነበር ፡፡እኔ በምደሰትበትና ቤተሰቤ ሁሉ አብሮኝ ሲስቅ ሀፍና ፈቲ በቁጭት ሊውሉ እንደሆነ ሳስበው ሀዘኔ በዛ ሀፍ ለኔ ደስታ ስትል ነው የመጣችው ፈቲ መጫሯን ታውቃለች፡፡ ግን ያለችበትንና ያሳለፈችውን ህይወት አታቅም ስታቅ ምን ይሰማት ይሆን??? እንጃ በጣም ታዝናለች

ሀፍ ከወጣችበት መኪና አንድ ልጅ ወጣ ሳየው ሳዳም መስሎኝ ደነገጥኩኝ... ግን ሳዳም አልነበረም በጣም ነው የሚመሳሰሉት በራሴ ተገርሜ የት እንረፍ ሲባባሉ ቶሎ ብየ የሆቴሉን ስም ጠራሁት ነጁ ፈገግ አለች ሀፍም እንደዛው ሆቴሉ ከ ሳዳም ጋር እራት የበላንበትና ነጁ የመረጠችልን ሆቴል ነበር፡፡ በአነጋገሬና በፍጥነቴ ተገረምኩኝ ሁሉም ተሳሳቁና በየመኪናው ገባ እኔም ሀፍስ ጋር ገባንና መሄድ ጀመርን


መኪናው የሳዳምን ነው የሚመስለው ተመሳሳይ ቦታ ላይ ተመሳሳይ ነገር ተለጥፏል፡፡ ይህ መኪና የማቀው የማቀው መሰለኝ አልኳት ለሀፍ
.... አንች ደግሞ ማመሳሰል ትወጃለሽ አለችኝ
....እረ ይሄ መኪና እርግጠኛ ነኝ አቀዋለሁ አልኳት
....ሀፍም ይሄ ትምህርት በቃ በችከላ አደበላልቆሻል ታርጋዉም እኮ አማ ነዉ ከደሴ ነዉ የመጣዉ አታቂዉም አለችኝ
........ሆቴል ደርሰን እኔና ሀፍ ነጁ እና ፈቲ ትተናቸው ወጣን እና ሀፍ ሁሉችንንም እያየች ወደ ፈቲ ዞረችና እና እንዴት ብለን ነዉ ለቤተሰቦችሽ ከዩኒቨርስቲ መጫርሽን የምናሳውቀው????? አለች.....

#Part_16
ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል.....,,

Join👇

@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

22 Oct, 18:42


ጥሩ አስትሳስብ ካለሽ ሁሌም አሽናፊ ነሽ

PROUD_MUSLIM

22 Oct, 17:22


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣4⃣



የፈቲ አባት ደጋግሞ ደውሏል ምን ሁኖ ነው?? ምን ተፈጠረ?? ብየ ልደውልለት ፈለኩኝ
.....ወዲያው ደወለና አነሳሁት
.....ሄሎ ሀሊማየ አለኝ የሀዘን ድምፅ ነበር
..........ሄሎ ሠይዶ አልኩት
......እንዴት ነሽ??
........አልሀምዱ ሊላህ ምነው ድምፅህ አመመህ እዴ?? አልኩት የተፈጠረውን ነገር ለማወቅ እየተጣደፍኩ
......ኧረ ደህና ነኝ ሀሊማየ እንደው አስሜ ተነስታብኝ ነው እንጂ ደህና ነኝ አለ በሀይለኛው የሚያስለውን ሳል አፈን እያደረገ
...... ሁሉም ደህና ናቸው?? ሁሉ ሰላም?? አልኩት ደህና ነን አትጨነቂ------------ ባይሆን ደጋግሜ የደወልኩት መመረቂያችሁ እየደረሰ ስለሆነ ከመምጣቴ በፊት ብር መላኬን ልነግርሽ ነው አለኝ
.....እሽ ሰይዶ በቃ እናወጣዋለን አልኩት
......ደግሞ የእህትሽ ስልክ አይሰራም አጠገብሽ አለች እንዴ??? አለኝ ክፍሉን ተዟዙሬ አይቼው አሁን ወደ ክላስ ሂዳለች አልኩት
.....እሺ ካነሰ እጨምርላችሇለሁ ደህና ዋሉ ብሎ ዘጋው

የሱን ስልክ ዘግቼ ሻወር ልወስድ ስል ሌላ አዲስ ስልክ ተደወለልኝ ማንሳት ባልፈልግም ግን አነሳውት ይሆናል ብየ ያልጠበኩት ሰዉ ሳዳም ነበር ትላንት ከሆስፒታል ጀምሮ ሲንከባከበኝ የነበረ ቆንጅየው ልጅ..... ደህንነቴን ጠይቆኝ __ፍቃደኛ ከሆንሽ ለትላንቱ ውለታየ ራቴን ጋብዥኝ አለኝ
ማታ መሆኑ ደስ ባይለኝም እሺ ብየው ስልኩን ዘጋሁት ሻወሬን ወስጄ ወደ ክላስ ሄድኩኝ ግን ስለ ሳዳም እያሰብኩ ነው እርጋታው ቁንጅናው ሳያውቀኝ ስላረገልኝ መልካምነቱ የድምፁ ውበት ድፍረቱ በቃ አጠቃላይ ደስ ብሎኛል፡፡ ለየትኛውም አይነት ወንድ ተሰምቶኝ የማያቅ ስሜት በሄኖክ የተነሳ ወንዶች ሁሉ አስጠልተውኛል ፡፡ ግን ለእሱ ለምን እንደዚ እሆናለሁ??? ሁሉም አስመሳይና ውሸታም ናቸዉ እሱም የበግ ቆዳ የለበሰ ቀበሮ ነው ብየ አሰብኩ፡፡ ደግሞ መልካምነቱ ትዝ ሲለኝ ሀሳብ እቀይራለሁ
.......ልደውልለት ፈለኩኝ ግን ሌላ ይመስለዋል ብየ ተውኩት፡፡ የተሰጡንን ነገሮች ሰራርቼ ምሳየን ከነጁ ጋር በላሁና ማታ አብራኝ እንድትሄድ ጠየኳት
......ነጁም እሺ አለችኝ ደስ አለኝ ሰአቱ ደረሰ የፈቲን ስልክ ብደውል አይሰራም አብራኝ እንድትሆን ፈልጌ ነበር ከሷ መለየቱ ስላስጠላኝ ሳዳምን ካገኘነው ቡሀላ ፈቲ ቤት ሄድን ለ አገሩ አዲስ እንደሆነ ያስታውቃል ለሀገሩ አዲስ የሆነ ሰው እኔን በመንከባከብ ተደምጧል፡፡ ፈቲ ጋር ስገባ ፈቲ እቤቷ ተኝታለች ምን ሁነሽ ነዉ ስልክሽም አይሰሪም አሁን ስመጣ ደግሞ ተኝተሻል ??? ስላት
......አይ መድሀኒቶቼን ጨርሼ ነው አለች
....ከግቢ ድረስ የመጣሁበትን ብነግራትም እንቢ አለች፡፡ እንቢ በማለቷ ብከፋም አልተቀየምኳትም ደህና እደሪ ብያት ማማየን ዘይሬ ወጣው

እራት ጋባዥ እኔ ስለነበርኩ አሪፍ ሆቴል ነጁ መርጣልን ሄድን እዛ ስናወራ ስንጫወት ቆይተን ነጁ እጇን ልትጣጠብ ተነሳች፡፡ የሚገርም ሰርፕራይዝ አለኝ ከእራት ቡሃላ እሰጥሻለሁ ብሎ ከኪሱ አንድ የታሸገ ፖስታ አውጥቶ መልሶ አስገባው.......>>>>>> ሲያወጣው #ሀፍሳ<<<<< የሚል ያየሁ መሰለኝ ግን በደንብ ግን አላየሁትም ምን አልባትም የሀፍሷ ሀሳብ እና ናፍቆቴ በዝቶ ይሆናል ፡፡ ግን ከሳዳም ጋር ፍፁም ደስተኛ ሁኛለሁ ምን እየሆንኩ ነው ግን ራሴን ታዘብኩት .....እራት በልተን በሱ ወሬ ተመስጨ ፖስታየንም ረስቼው ወጣሁ፡፡ አሁንም ግን ሂሳብ ቀድሞ እሱ ነው የከፈለው
.....ለምን ከፈልክ እኔ ነበርኩ ጋባዥ ??? ስለዉ
......ሌላ ቀን እኔና አንቺ ብቻ ስንሆን ትጋብዥኛለሽ አለኝ፡፡ እኔም ተስማማሁ

ወደ ዶርም ገብቼ ከፈቲ ጋር እያወራን ቴክስት ገባልኝ፡፡ ቴክስቱን ሳየው ፈገግ አልኩኝ
,,,,,,,, ነጁ አይታኝ ምነው ደስ አለሽ አለችኝ
.......ኧረ ምንም አይደል አልኩኝ እየተሽኮረመምኩ፡፡ ቁም ነገረኛ ነው እስከ 5:00 ስናወራ አመሸን በመጀመሪያ ቀን በመጀመሪያ ቀን ይህን ያህል ሰአት ማውራቴ ገረመኝ፡፡ ነገ ሆስፒታል ሂጄ የማስፈታበት ቀን ነው እንቅልፌ መጥቶብኝ ስለነበር ተኛሁ፡፡ ጠዋት አርፍጄ ተነሳሁ፡፡ ምንም ስላልነበረኝ ሆስፒታል ሂጄ አስፈታሁ ወደ ዶርም ተመልሼ ማሰብና መጨነቅ ሆነ ስራየ ለሊት ለሊት ማልቀስና መስገድ የግሌ አረኩት

መመረቂያ ግዜየ 2ወር ቀረው ለፈቲ ደወልኩላት ዛሬ ምንም ሠላም የለኝም በጣም አሞኛል ሳዳምም ከጠፋ ቆየ እየናፈቀኝ ነው መሠል አስሬ ስልኬን አያለሁ ግን ምንም የለም ፈቲን ሳገኛት ከስታለች ፊቷ ተቀያይሯል ሁለ ነገሯ ልክ አይደለም
.....ምን ሆነሽ ነው ???አልኳት
.....ደህና ነኝ ብላ ቆጣ አለችፈ
..... በቃ ሱሷ ነው ገባኝ ሄኖክ መድሀኒቱን እየሰጣት አይደለም ፡፡ ልብስና ጫማ ገዝተን ተለያየን ከተለየሆት ቡሀላ ህመሜ ባሰ ለፈቲ ደውየ ሆስፒታል ሄድኩ ፈቲ ከኔ ጋር ነው ማደር ያለብሽ አለችኝ
.....አማራጭ ስላልነበረኝ ሄድኩ የፈቲን ባህሪ አቃለሁ ፊት ለፊቷ የተጋረጠን ነገር ለማስወገድ ምንም ቢሆን ታደርጋለች ሄኖክ እንደከለከላት አውቂያለው ግን እኔን አሳልፋ እንደማትሰጥ ተማምኛለው

ፈቲ ሰፈር ስንደርስ ሄኖክን አየሁት ተደባድቦ ነው መሠል ፊቱ ተበላሽቷል፡፡ እንደዛ መሆኑን ሳውቅ ምነው ገለውት በነበር አልኩኝ ፡፡ ፈቲ እሱ ጋር ሂዳ ማውራት ስትጀምር ማማየን ሰላም ልበል ብየ ገባሁ ማማየ አልነበሩም ሌላ ቦታ ሂደዋል ፈቲ ከዛ ቀፋፊ ጋር ሳያት ውስጤ ተንጨረጨረ የሆነ ነገር ሲሰጣትም ስላየሁት ጥርጣሬየ ጨመረ ስትገባ ዝም ዝም ተባባልን ጨንቋታል እንደተናደድኩባት ገብቷት መሰለኝ

ሀሊማየ በቃ ይቅርታ ግድ ስለሆነብኝ ነው ተረጅኝ አለችኝና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
...... ፈቲ በአላህ ተይው አልኳት... ነገረ ስራዋ ግን ደስ አይልም በየሰአቱ በየደቂቃዉ እየደጋገመች #እንዳትቀየሚኝ_ግድ_ስለሆነብኝ_ነው እያለች በለቅሶ ብዛት አፏ ቃላት እንዳልፈታ ህፃን ልጅ ተያያዘ
....... ሽንት ቤት ደርሼ ስመጣ ለእኔም ለእሷም ኮካ ገዝታ ነበር....ኮካዉን እንድጠጣው ወተወተችኝ፡፡
...እኔም ኮካዉን አንስቼ ጠጣሁት.... ሀይለኛ እንቅልፍ ሲወስደኝ ታወቀኝ ...በእንቅልፌ ዉስጥ በህልሜ የሆነ ሰው ሲገናኘኝ ታወቀኝ ...........




ጠዋት ከወሰደኝ እንቅልፍ ስነሳ ጁኑብ ሁኛለሁ፡፡ አልጋዉ ላይ ተዘርሬ ተኝቻለሁ.... እንዲሁም ደም ታፋየ አካባቢ ፈሷል፡፡ እኔ ምንም ነገር ትዝ ሊለኝ አልቻለም ሀይድ ሁኜ ነው ብየ ዝም አልኩ......
#part_➊➎
ይቀጥላል
Join👇
ከ 50👍 ቡኃላ

@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

21 Oct, 18:00


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣3⃣


የማወራላትን ለመስማት እየጓጓች ወደኔ መጠጋት ጀመረች ምን እንደማወራላት ሁሉ ግራ ገባኝ
ፈቲ የማማየን ልጅ ታሪኳን ሰምተሻል ???አልኳት ወሬ ቢጠፋብኝ እንጅ ይህን አልነበረም ላወራላት የነበረው
.....አወ ሰምቻለው የምታሳዝን ልጅ ነች በተለይ ማማየ ያሳዝኑኛል አያታችንን ያስታውሱኛል አለችኝ፡፡ የኛም አያት እንደ ማማየ ሠው በጣም ነበር የምትወደው
......ብዙ ግዜ ደግሞ በረኪና ልትጠጭ ደርሰውብሽ ነበር አይደል?? አልኳት
.... ይህንንም ነገሩሽ ዴ??? አለችኝ እንደ ማፈር እያለች በቃ አሁን የምፈልገውን ማውሪያ መንገድ አገኜውና ወሬየን በጥያቄ ጀመርኩ ቅድም ማማየ ወንድምሽ ያሉሽ ማንን ነው?? ስላት አንገቷን ደፍታ ዝም አለች፡፡ ፈቲ አትፍሪኛ እኔኮ ነኝ ንገሪኝ አትፍሪኝ አልኳት
....... ሄኖክን ነው አለችኝ ሄኖክ ወንድሜ ነው ብለሽ በያቼው አለኝ የማማየን ባህሪ ያውቅ ስለነበር አለችኝ
...... እሳቸው ወንድምሽ አንዳልሆነ ቢያውቁብሽስ?? አልኳት
..... ነገርሻቸው እንዴ ?? አለችኝ ኧረ አትጃጃይብኝ ምን ብየ ነው የምነግራቸው ??ቢያውቁብሽ ምን ታደርጊያለሽ ነው ያልኩት አልኳት
...... እኔንጃ አላቅም ያዝኑብኛል እኔም ብሆን እሳቸውን የማይበት ድፍረቱም አይኖረኝም ፡፡ ሀሊማየ ማማየኮ ለኔ እንደናቴ ናቸው በግዜ መግባቴን አረጋግጠው ምግብ ቤታቸው ድረስ በልቸ፡ መክረውኝ እንደ እናት ተንከባክበውኝ ሌላው ቀርቶ የቤት ኪራይ ራሱ አይቀበሉኝም ላንች በጣም አስፈላጊ ይሆናልና ነው የሚሉኝ እና እንዴት አይነት አቅም ይኖረኛል??? አለችኝ

የኔን ጭንቀትና ሀሳብ የጨመረብኝ ነገር አሁን ማማየ ማወቃቸውን ካወቀች እኔም ሆንኩ ማማየ ማንፈልጋቸውን ውሳኔወች ትወስናለች ሳልነግራት ዝም ካልኩኝ ደግሞ እሷ በወንጀል ላይ ዘውትራ በአላህና በሠው ዘንድ ተወቃሽና ተጠያቂ ታደርገኛለች ከዛ በላይ ግን ለህሊናየ ምታወርሰኝ ህመም ከሁሉም በላይ ይከፋል ማማየስ ቢሆኑ እሷን በዚ ሁኔታ ማየትም አይፈልጉም እኔም ዝም እንድላት አይፈቅዱም ምን አይነት ፈተና ውስጥ ነው ግን የገባሁት??? ስለሷ ማሰቤ መጨነቄና መናፈቄ ሳያንሰኝ ስለሷ ቤተሰቧ ምን ይለኝ ይሆን?? በአላህስ ዘንድ እንዴት ነው የምጠየቀው ?? ወላሂ ፈቲ ለኔ ከምንምና ከማንም በላይ እወዳታለው ፈቲ ስጨነቅ ተጨንቃ ስከፋ ተከፍታ ስደሰት ከኔ በላይ ተደስታ ምትኖር ልጅ ነች ፡፡የኔ ራስ ወዳድነት ግን በዛ በጣም ከፋ በደስታዋ ግዜ አብሪያት ሁኜ በጭንቀቷና መጥፎ ግዜዋ ለብቻዋ ትጋፈጠው ዘንድ ፈረድኩባት
.....ምን አይነት ሴት ነኝ ግን በሀሳብ ተጓዝኩኝ ሀሊማየ ሀሊማየ ብላ ደጋግማ ስትጠራኝ ነቃሁ ወይ አልኳት ስለምን እያሰብሽ ነው??? አለችኝ
......ኧረ ዝም ብየ ነው በማለት ወሬ አስቀየስኩና ከልጅነት ጀምሮ ስላለፉ ታሪኮቻችን ማውራት ጀመርን በምሀል በምሀል ግን የሷ ነገር ያሳስበኛል ግማሽ ለሊት ድረስ አወራን ከዛ ተኛን እኔ ግን እንቅልፍ አጣሁ .....በምሀል አርግዛስ ቢሆን ?? ኤች አይቪና ሌላስ በሽታ ይዟትስ ቢሆን ??? ከንቅልፏ ቀስቅሼ ልጠይቃት አሰብኩ ግን ተውኩት የሆነ ሰአት ላይ እንቅልፍ ወሰደኝ ለሊት ላይ ሀይለኛ ሳል ቀሰቀሰኝ ፈቲ ነበረች ሲጋራ እያጨሰች መባነኔን ስታውቅ በድንጋጤ መሬት ላይ ጣለችው
....ኧረ ፈቲ ውሀ አፍሺበት ያቃጥልብሻል አልኳትና ተነስቼ አፈሰስኩበት ለምን እያልኩ ላልጠይቃት ወሰንኩኝ፡፡ ቀጥታ ሂጄ አቀፍኳት አለቀሰች ሀሊማየ ስላልቻልኩ ነው እንጂ እንድታይኝ አልፈለኩም እያለች ተንሰቀሰቀች
.....ፈቲዋ ይሄኮ ቀላል ነገር ነው አታካብጂው ደግሞም ምንም አልልሽም ትችያለሽ ደግሞም አስታውሽ ወደፊት ብዙ ፈተና አለብሽ ስለዚ ጠንከር በይ ብያት ተኛሁ መጥታ አጠገቤ ተኛች


ጠዋት ላይ ተነስቼ ውዱዕ እያረኩ ሳለ ሀሊማየ ደና አደርሽ አሉኝ ማማየ
.... ደና አደሩ ማማየ አልኳቸው
......እጂሽን ተሽሎሽ አደርሽ?? አሉኝ
...... አልሀምዱ ሊላህ ብየ ስመልስ በይ ያች መንትያሽን ቀስቅሻትና ቁርስ መታቹ ብሉ አሉኝ መተኛቷን እንዴት አወቁ ለነገሩ አለመስገዷንም ስለሚያቁ ይሆናል ብየ ገብቸ መስገድ ጀመርኩ

መሀል ላይ የለቅሶ ድምፅ ሠማሁ... ፈቲ ነበረች ቶሎ ብየ ጨርሼ ምን ሁነሽ ነው የምታለቅሽዉ??? አልኳት
....ሀሊማየ ከሰገድኩኮ ቆየሁ ናፍቆኛል መስገድ ግን ትዝ አይለኝም በቃ ልቤ ጠለሸ ቆሸሸ ማለት ነው?? እያለች አለቀሰች


በቃ በዚች ቅጽበት ቤት መደወል እንዳለብኝና ከባህርዳር ድረስ መጥተው እንዲወስዷት ወሰንኩ፡፡ አሁን ተነሽ ማማየ ቁርስ እየጠበቁን ነው ብየ ማማየ እንዳይጠብቁን ቀድሜ ወጣው ለማማየ ያሰብኩትን ልነግራቸው አልኩና እሚያስከፋቸው መስሎኝ ተውኩት፡፡ ቁርስ በልተን ማማየን ተሰናብቸ ወጣው ፈቲም ግቢ ድረስ ሸኝታኝ ልንለያይ ስንል ሀሊማየ ለባባና ለማማ ስለኔ አትነግሪያቸውማ ስላት ደነገጥኩ ማን ነገራት ማሰቤን እንዴት አወቀች ሁሌም ፈቲ የሆነ ነገር ሳስብላት ከኔ ቀድማኝ ትናገራለች ተናደድኩ ብናደድም ለማስመሰል አየሞከር ፊቴን ፈገግ አድርጌ እያቀፍኳት ኧረ አታስቢ አልኳት የክሀዲነት ስሜት ተሰማኝ ግን ለሷ ብየ ነው ግቢ ስገባ ለነጁ ደወልኩላትና ዶርሜ ገብቼ ለብቻየ ማውራት ጀመርኩ -------------አሁን ብነግራቸው ፈቲ ይህ ግብዝነቷና ሱሷ ተደማምሮ ጎዳና ላይ ትወድቃለች እኔንም ቤተሰቧንም ትርቃለች ይህ ከሚሆን ደግሞ ከነ ችግሯ እንዳትርቀኝ ፈልጋለሁ በዛ ላይ ደግሞ መመረቂያየ እየደረሰ ነው ከማንም በላይ ፈቲ አጠገቤ እንድትቆም እፈልጋለው እሷስ ይህንን የኔን ደስታ ለማየት አይደል በህይወት የቆየችው እያልኩ ከራሴ ጋር ሰጣ ገባ ገብቼ ስልኬ ሳይለንት ስለነበር አልሰማውትም ነበር እንደ አጋጣሚ ከአስቀመኩበት ሳነሳው የፈቲ አባት በተደጋጋሚ ደውሏል ምን ተፈጥሮ ይሆን???? አልኩኝ ለመደወል እየተጨነኩ የፈቲ አባት መልሶ ደወለ.....
@part_14

ከ 50👍ቡኋላ
ይቀጥላል
join 👇👇


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

20 Oct, 06:21


እናንተ ብቻ ምታውቁት
ደስ የሚላችሁን ቦታ
ብዙ ሰው እያወቀ ሲመጣ 😫😭

PROUD_MUSLIM

20 Oct, 04:10


የአንተ መገኘት
ተጽዕኖ ካላሳደረ።
የአንተ አለመኖርም
ለውጥ አያመጣም!

መልካም የዕረፍት ቀን🤗
:¨·.·¨: ❀
 `·. @Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

19 Oct, 15:54


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣2⃣



   በራፉ ተንኳኳ አንባዋን እየጠራረገች ማነው??? አለች እኔ ነኝ ፈቲየ አሉ ድክም ያሉ ባልቴት አከራያቸው ነበሩ ሂዳ ከፈተችላቸው እና ግቡ አለቻቸው
.....አይ ዛሬ በግዜ መግባትሽን ላረጋግጥ ብየ ነው በግዜ መግባትሽ ደስ ብሎኛል ወንድምሽ አልገባምሳ ??አሏት
.... አወ ዛሬ አይመጣም አለቻቸው ሄኖክን ነው ብየ አሰብኩኝ
.....ምነው ብቻሽን ታዳ?? አሉ ኧረ ብቻየን አይደለሁም ሀሊማየኮ አለች ግቡ ብልሁኮ እንቢ አልኩ አለቻቸው

ውይ ሀሊማየ መተሻል እንዴ እንዴ ??ብለው ወደውስጥ ገቡ ሲገቡ ቆም ብየ ተቀበልኳቸው ኧረ ቁጭ በይ ልጄ ብለው ቀጥታ ወደታሸገው ግራ እጄ እያዪ ምን ሆንሽብኝ ልጄ?? እያሉ በስስት ያዩኝ ጀመር ምንም አልሆንኩ ማማየ አልኳቸው ማዘር ሲሏቸው አይወዱም አንድ በጣም የሚወዷት ልጅ ነበረቻቸው ማማየ ብላ ነበር ምትጠራቸው እሷ ከሞተች ቡሀላ ነበር ሁሉም ሠው ማማየ እያለ የሚጠራቸው ቤታቸው የሚያከራዩት ሴት ብቻ ነው ባለ ትዳር ወንዶችን ሁሉ አያከራዩም የቤት ኪራይ ከሁሉም ያነሰ ነው እሳቸው ሚያስከፍሉት ሁሉንም እንደ ልጆቻቸው ነበር የሚያዩት
    ሁሌም ማታ ማታ እሳቸው ቤት ሁሉም ተሰብስቦ ያወራል ይጫወታል ቡና ጠጥተው ነው የሚለያዩት እኔና ፈቲ መልካችን በጣም ተመሳሳይ ነው ለነገሩ ፈቲ የአክስቴ ልጅ ናት ልዩነት የለንም፡፡
ማማየም እናንተ ሁለት ልጆች ልጄን ታስታውሱኛላችሁ በተለይ ሀሊማ ምንሽም  ከሷ አይለይም ልጄን ታስታውሽኛለሽ ይሉኛል፡፡ ሁሌም ወደቤታቸው በሄድኩ ግዜ እቤታቸው አስገብተውኝ በልቼና ጠጥቼ ነው የምወጣው በሉ ቶሎ ወደቤት እንድትመጡ ብለውን ወጡ ....እኔና ፈቲ ያመጣችውን ምግብ በልተን ለማማየ ይዘንላቸው ሄድን
    ቤታቸዉ ስንገባ ሁሉም ተሰብስቦ ቀድመውን እኛ አርፍደን ነበር ሁሉም ይስቃል ይጫወታል ስንገባ ቦታ ተሠጠንና ቁጭ አልን አብረን ስናወራ ስንጫወት ቆይተን ቡናችንን ጠጥተን ተመርቀን ስንወጣ ፈቲ ቀደመችኝ..እኔም ልወጣ ስል ሀሊማየ ቁጭ በይማ አሉኝ ሌሎቹ ወጡ ፡፡ ከዛም ማማየ ሀሊማየ አንች በጣም ጥሩ ልጅ ነሽ የፈቲ ነገር ግን ያስጨንቀኛል እዚህ የሚመጣው ሄኖክ የሚባል ልጅ ወንድሟ እንዳልሆነ አቃለሁ ማታ ማታ የሚሰሩት ስራ ያሳስበኛል፡፡ እስኪ ስለ እኔ ልጅ ታሪክ ላጫዉትሽ፡፡

የኔ ልጅ አባቷ በጣም ይወዳት ነበር ደግሞም ይቆጣጠራት ነበር የምትፈልገውን አያሳጣትም ነበር ግን አላህ ብሎ በመኪና አደጋ ሞተ  እሱ በመኪና አደጋ ከሞተ ቡሀላ የሷ ነገር ለኔ የተወሰነ ግዜ ጥሩ ነበር፡፡ ከዛም ዱርየ የሆነች ልጅ ጋር ገጠመችብኝና ከግዜ ግዜ ባህሪዋ ይቀየር ጀመር መጥፎ ጓደኞቿ በጣም በዙ እቤቴም ድረስ ይመጡ ጀመሩ ...ሲመጡ መጥፎ ፊት እንኳን አሳይቻቸው አላውቅም ነበር ፡፡ እዚ ሲመጡ የሚያወሩት ወሬ ይሰቀኝ ነበር ቀስ በቀስ ጓደኞቿ እቤት አንድ የተከራየ ባለትዳር ጋር ይማግጡ ጀመር
.....ልጄ ለዚህ ፍቃደኛ ስላልነበረች የተከራየዉ ልጅ እልክ ውስጥ ይገባ ጀምሯል የሚገርመው ደግሞ ሚስቱ ከሌላ ሴት ጋር እንዲማግጥ መፍቀዷና ማመቻቸቷ ነበር ፡፡ እሷም ሌሎች ጋር ትማግጥ ነበር ልጄ ቀስ በቀስ ሱስ ውስጥ ገባች መክሬም አልቅሸም አልመለስ አለችኝ በስተመጨረሻም ልጄን ተከራዩና ጓደኞቹ አስገድደው ደፈሯት ብለው ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ፡፡ ከዛ ቡሀላ ግን በህይወት አልቆየችልኝም ሞተችብኝ ፡፡ ፈቲም የልጄ ህይወት ላይ ነች በህይወት መቆየቷ ራሱ ለቤተሰቧ ትልቅ ነገር ነው ራሷን ልታጠፋ ብዙ ግዜ ደርሸባታለው መክሪያታለሁ እና እባክሽን ህይወቷን ታደጊው ሁሌም ማታ ማታ ቤቷ ሂጄ መኖሯን አረጋግጣለሁ ካመሸች ራሱ እጨነቃለሁ
..... የዚች ልጅ ህይወት ተስፋ ባንች ላይ ነው የሚታየኝ እኔ ልጄን ካጣሁ ቡሀላ ለተወሰነ ገዜ ራሴን አላቅም ነበር በአሏህና በቤተሰብ እርዳታ ነው ወደ ማንነቴ በከፊሉም ቢሆን የተመለስኩት ከዛ ቡሀላ ወንዶችን ግቢየ ላለማከራየት ወሰንኩኝ ፡፡ ሴት ልጆቼን በሙሉ ለመርዳት አሰብኩ ፈቲ ባየሆት ቁጥር ልጄን እያስታወሰችኝ ብናገራት አስከፋታለሁ ብየ እያሰብኩ ከኔ ጋር ጭቅጭቅ ይሰለቻትና መጥፎ ውሳኔ እንዳትወስንብኝና ሌላም ፀፀት እንዳላተርፍ ብየ ከነ ጥፋቷ ተውኳት፡፡  ስለ ልጁ ሄኖክ አጣርቼ በጣም መጥፎና ባለጌ ሠው መሆኑን አውቂያለሁ.... አንችንም እንደዚ አይነት ተግባር ውስጥ እንዳያስገባሽ እፈራለሁ ብቻ ምከሪያት አሉኝ፡፡

    እና እንባቸውን ጠራርገው ሸኙኝ እኔም ተክዝ ብየ ወደ ፈቲ ሄድኩኝ በራፉ ገርበብ ብሎ ስለነበር ሳልቆረቁር ገባሁ..... ስገባ ፈቲ ጠረንጴዛ ላይ አጎንብሳለች ፈቲ ብየ ተንደርድሬ ስሄድ ድንግጥ ብላ ተነሳች  ለካስ በአፍንጫዋ ሺሻ እየሳበች ነበር
 .......ይቅርታ ሀሊማየ ስላላስቻለኝ ነው አለችኝ
......ኧረ ችግር የለውም አልኳት ያልደነገጥኩ እየመሰልኩ ወደ አልጋው ሄድኩኝና ቁጭ ብየ ማሰብ ጀመርኩኝ ማማየ የነገሩኝን በሙሉ ማስታወስና በነገሩኝ ነገር ማዘን ጀመርኩኝ የአላህ ስራ ግን የአጅባል እንደሄኖክ አይነት ለግዚያዊ  ስሜታቸው ብለው የስንቱን ሰው ህይወት የሚያበላሹ ባሉበት እንደዛች ገንዘብን  ከሰው በላይ የሚያመልኩ ለሰው ህይወት ቅንጣት በማያስቡ  በበዙበት እንደነ  ማማየ አይነት ሠው መኖሩ እጅጉን  ያስደስታል የነሱ መኖር የሠውን ልጅ በአንድ አይነት ላለመፈረጅና ለውስጥ ሀሴት ይጠቅመናል እነሱ ባይኖሩ ኑሮ አላህ ሳንሞት በቀጣን ነበር


ፈቲን ምን ብየ እንደማወራት ጨነቀኝ ከየትኛው ልጀምርላት እያልኩ ሳስብ ሀሊማየ ምን ሆንሺብኝ??? አለችኝ ወደኔ እየተጠጋች ኧረ ምንም እንደው የማማየ ተግባር እየገረመኝ ነው እንጂ ምን አወሩሽ ግን አለች ለማዳመጥ በመጓጓት .....

#Part_➊➌
ከ 60 👍 ቡኋላ
ይቀጥላል
join 👇👇👇


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

19 Oct, 10:34


ሁሉም ሰው ለሰው የማይነግረው
ቢነግረውም ሰው የማይረዳው ህመም
በውስጡ አለ❤️‍🩹

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

18 Oct, 18:16


     የወሰደው ለጥበብ ነው ያቆየው ለእዝነቱ ነው ሙእሚን ደሞ ከሁለት አንዱን አያጣም

PROUD_MUSLIM

18 Oct, 18:11


ምናልባት ሊመጡ አይደለምና ሚሄዱት
አንተነትህን ከነሱ ማላቀቅህን እርግጠኛ ሁን😊


መቼም ጥሎህ ከማይሄደው ጌታህ ጋር ልብህን አቆራኝ❤️

@Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

18 Oct, 17:45


ያገባቹ ሴቶች ባሎቻቹ ኳስ ላይ ለሚያሳዩት ባህሪ ምን ትላላችሁ comment ላይ ሃሳብ

PROUD_MUSLIM

18 Oct, 15:09


ሰዎችን ለመምከር የግድ ቃላቶችህን ማራቀቅ አይጠበቅብህም..

ብዙዎቹ ቃላቶቻቸውን ሲያራቅቁ ; ተመካሪዎችን ሲያሳቅቁ አይተናልና..💔

@Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

18 Oct, 14:04


ውዷ ለራስሽ እራስሽ ነሽ መድኃኒቷ❤️

PROUD_MUSLIM

18 Oct, 07:34


እምቢ ብላ ኖራ ያን ሁሉ ዓመት
  ሙሀመድን ''ﷺ'" ስታይ
  ወሰነች ማግባት
''ኸድጃ🥰

@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

17 Oct, 17:16


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 1⃣1⃣


 ቤት ስገባ የቢራ ጠርሙስ አየሁ ማመን አልቻልኩም የእውነት ፈቲ ያች የማቃት ፈቲ አልሆንልኝ አለች ቀስ በቀስ የሲጋራና ሺሻ ሽታ ይሸተኝ ጀመር

 ፈቲ ገብቷታል ዶዶራንት እየረጨች ሀሊማየ ራት ምን ልስራልሽ ???? አለችኝ
..... ምንም አልፈልግም አልኳት
.....እንዴ መብላትማ አለብሽ ባይሆን ቴክ አወይ አሰርቼልሽ ልምጣ ብላ ከፓርሳዋ ሶስት መቶ  ብር ኖቶችን አንስታ ይዛ ሄደች

   እንደምንም ተነስቼ ቤት ውስጥ ያለውን ነገር ለማየት ከዚ ከዛ ማለት ጀመርኩ አልጋው ስር ብዙ የቢራ ጠርሙስ አየሁ በቃ ጥርጣሬየ በሙሉ እውነት እየሆነ መጣ፡፡  ተነስቼ መሳቢያውን ስከፍት እንቅጥቅጥ አረገኝ በጣም ብዙ ብዙ የተለያዩ የተላጡና የታሸጉ ኮንዶም...የእርግዝና መከላከያ ክኒን አየሁኝ.....ደንግጬ መሳቢያዉን ዘጋሁት

  አንድ ወንድ ከዉጭ ደህና አመሻችሁ ብሎ ሲገባ ደነገጥኩኝ... ሄኖክ ነበር ፡፡በእጁ የያዘውን አትክልት እያስቀመጠ እና ተሻለሽ ??? አለ በዛ ሰቃቂ ድምፁ
 ......አሁን እርይ ብየ ሳልጮክ ውጣልኝ አልኩት እንዳይጠጋኝ ብየ ወደግድግዳ ው እየሸሸሁ
.... ተይ እንጅ አሁን እንኳን ፀባይሽን አሳምሪ ሁሌም አስቸጋሪ ልጅ ነሽ ፡፡ >>>>>>>>ሳልነግርሽ የማላልፈው ነገር እስካሁን ከአገኘሆቸዉ ያስቸገርሽኝ ብቸኛ ሴት መሆንሽን ነው ..ግን አንድ ቀን እጄ እንደምትገቢ 100% አትጠራጠሪ ....ለዛ ቀን ደግሞ እንድትገኝ በህይወት መኖር አለብሽ በህይወት ትኖሪ ዘንድ ደግሞ በህመምሽ ሰአት ልንከባከብሽ ግዴታየ ነው እኔ ባንች መጨከን አልችልም <<<<<<<<<<ብሎ ትቶኝ ወጣ ፡፡
ጭንቀቴ ጨመረ መርበትበት ጀመርኩኝ ጨዋ ሊመስል ሲሞክር አለማፈሩ


     ትንሽ ቆይታ ፈቲ እጇ ላይ ቴክ አዌዬን  አስቀምጣ ገባች ልክ ስትገባ ምን ሊሰራ መቶ ነው ብየ ጮህኩባት
ማነው የመጣዉ ?? አለች እንዳላወቀ ለመሆን እየሞከረች
.....ባክሽ አታስመስይ እንድትዋሽኝ አልፈልግም እውነቱን ንገሪኝ ብየ አፈጠጥኩባት
....እሺ ሀሊማየ ተረጋጊና ምንም ሳልደብቅ ልንገርሽ አለችኝ እሽ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ፡፡  ከምን እንደምጀምርልሽ አላቅም ስለየትኛው ትክክለኛውም ስሜቴ ላስረዳሽ አልችልም ካሁን ቡሃላ ህይወት አስጠልታኛለች ፈቲ ያኔ እኔና ሀፍስ ያን ድንች ከበላንበት ግዜ ጀምሮ ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ሁሌም ለብቻየ ስሆን አለቅሳለሁ ህይወቴ ያስጠላኛል ማንነቴና ምንነቴ ይቀፈኛል በኔ ላይ ተስፋ የነበራቺሁንና ትወዱኝ የነበሩ ሰዎች የጠላቺሁኝ ያስጠላሇቺሁ ተስፋ የቆረጣቺሁብኝ ይመስለኛል በቃ ሁሉም ያስጠላኛል
  ያኔ ባህር ዳር እንድመለስ ስትመክሪኝ እንቢ ማለቴ ይቆጨኛል ፡፡ ሂጄ ብሆን አባቴ የሆነ ነገር ያደርግልኝ ነበር ሊሻለኝም ይችል ነበር እንባወቿ መቆሚያ የላቸውም ነበር ፡፡ ቀን በቀን የምበላው ድንች አያረካኝም ነበር
  አንድ ግዜ ታዳ ሄኖክ አጠገቤ ሲመጣ አይኔ እንዳያይህ አንተ ቆሻሻ ብየው ቦታ ቀየርኩ ተመልሶ መጥቶ መድሀኒቱ አለኝ አትሽሽኝ ልስጥሽ ብሎ ጠየቀኝ ምንም ሳልናገረው ተነስቼ ሄድኩኝ ማሰብ ጀመርኩኝ በተደጋጋሚ እየመጣ ይነግረኝ ጀመር በየቀኑ በዛብኝ እውነቱን ሊሆን ይችላል ብየ አሰብኩኝና እሽ ልለው አሰብኩ ግን ስጠኝ ብየ አልጠይቅም ብየ ለራሴ ነገርኩኝ፡፡  አንድ ቀን እኔና እሱ እያወራን ነበር ያኔ ግን እንደሌላው ቀን አልጠየቀኝም ሞክሪው ብሎ ሲሰጠኝ ነው የደረሽብንና የተጣላነው ከዛ ሞከርኩት እውነቱን ነበር በጣም ያረጋጋኛል ቀን በቀን እንዲሰጠኝ ፈለኩ የተወሰነ ቀን ሳልጠይቀው ይሰጠኝ ነበር ከዛ በጣም ተግባባን ግን አንድ ቀንም ከሱ ጋር መዋሌ ይቀፈኝ ነበር አሁንም ያስጠላኛል በሱ ደስተኛ አይደለሁም በቃ ሁሌም ከሱ ከተለየሁ ቡሀላ ስራየ ማልቀስ ነበር
.....እናም ከግቢ ሳልባረር በፊት አብሬው እንድተኛው ጠየቀኝ በፍፁም ብየ እንቢ ስለው መዳኒቱን ይቀንስብኝ ጀመር ለአንድ ቀን ከተለመደው ውጭ ቀንሶ ስጠቀም እንደ እብድ ያደርገኛል ሌላም መጨመር እፈልጋለሁ ምንም ነገር ይጠፋብኛል በቃ ከራሴ ጋር ሌላ አለም ውስጥ እገባለሁ፡፡ አንድም ቀን ግን እንድትጨነቂና እንድታስቢ አልፈልግም ነበር ለዛም ነበር ያኔ እንዳልባረር ስትለምኝልኝ እኔ ያለመንኩት ሁሌም ላላስቸግርሽ በማሰብ ነበር፡፡ አንችን ከራኩኝ ቡሀላ ግን ነገሮችን መቆጣጠር አቃተኝ ያኔ ያንች ጉድለት ገባኝ ግን ላለማስቸገር ነበርና የሄድኩት ምንም ቢፈጠር ላልነግርሽ ወሰንኩ
..........የኔም ህይወት ከሄኖክ ጋር ቀጠለ ሙሉ ለሙሉ ከለከለኝ ያኔ ማውራት ሁሉ እየከበደኝ ይመጣ ጀመር መንቀሳቀስ ሁሉ ግድ ሆነብኝ፡፡ አንድ ቀን እንድተኛው ሳይጠይቀኝ ጠየኩት ብጠይቀውም እንደገና ያለፋኝ ጀመር ..አንቺ ጋር ማደር አልፈልግም እለኝ..እኔም የሴትነቴ ትርጉም ጠፍቶብኝ አብረሀኝ እደር ብየ ብዙ ቀን ለመንኩት... በመጨረሻም እሺ ብሎ ተኛኝ ከዛም ክብሬን ለሄኖክ አስረከብኩ አለችኝ እሷም ታለቅሳለች እኔም አብሪያት ማልቀስ ቀጠልኩ

እዚሁ አልጋየ ላይ ነውኮ ይሄ ሁሉ ግፍ ያለፈዉ  ከዛ ቡሀላ ሄኖክ በቃ በፈለገው ሰአት እተኘዋለሁ በየመንገዱና አስሬ መሳሳም ለኛ ተራ ነገር ሆነ ሀፍረት ከውስጤ ወጣ ቀስ በቀስ ቢራ ጀመርኩ ከዛም ሲጋራ በቃ ከዛ ቡሀላ ህይወት መረረችኝ በምሀል ዝም አለችና ትንሽ ቆይታ ማውራት ጀመረች
.......በቃ ከዛ ቡሀላ ከሱ ጋር ለመተኛት ጠያቂዋና አሳሳቿ እኔው ሆንኩኝ ፡፡ የሄኖክ ገላ ለኔ መድሀኔቴ ሆነ አብረሀኝ እደር ስለዉ ሄኖክም ይንቀባረርብኛል .....ብዙ ግዜ ራሴን ላጠፋ ወስኜም ላደርገውም ነበር ...ግን አንችን ትዝ ትይኛለሽ እሷ ሁሌም ትወደኛለች እያስቸገርኳት ራሱ አራቀችኝም ቢያንስ እስክትመረቂ እያልኩ አስብ ነዉ፡፡
    ቅድም በራፌን ዘግቼ በረኪና ልጠጣ ስል ሄኖክ ደወለልኝና ሆስፒታል እንደሆንሽ ሲነግረኝ ነው እንደዚህ ሁኜ የመጣሁት አለች፡፡ ብዙ ግዜ አባቴና እናቴ ይደውሉልኛል ሲደውሉ ከሄኖክ ጋር ሁኜ ነው ያወቁ እየመሰለኝ እደነግጣለው ሀሊማየ በቃ የኔ ህይወት እዛ አወ አዛ #መከረኛ_ድንች_ቤት አብቅቷል፡፡ ሁሌም ቤት ሁኜ እኔ አንችና ሀፍስ ያሳለፍነው የፍቅር ግዜ ትዝ ይለኛል ብቻየን አለቅሳለሁ አሁንም ድረስ ሀፍ ታሳዝነኛለች አንች ታሳስቢኛለሽ ፡፡ እንኳንም ያኔ ከኛ ጋር ያን ድንች ያልበላሽ አለች ተቃቅፈን ማልቀስ ጀመርን
...... ፈቲየ እኔኮ በጣም ነው የምወድሽ መቼም ቢሆን ባንች ተስፋ ቆርጬ አላቅም ሁሌም እተማመንብሻለው ብየ ፊቷን መጠራረግ ጀመርኩ አስታውሽ ሀፍኮ ሁሌም ከፊታችሁ ፈተና አለ ዝግጁ ሁናቺሁ ጠብቁ ብላናለች ስለዚ መጠንከር አለብን አልኳት
.... እሽ አለች እምባዋን ከጉንጫ እያበሰች
.......ለነጁ ደውየ መግባቷን አረጋገጥኩኝ ለምን ለሀፍ አንደውልላትም ??አልኩ ተስማማች ለሀፍሷ ደወልኩላትና ረጂም ሰአት አወራናት ፈቲ ዛሬ ከልቧ ስትስቅ ሳያት ደስ አለኝ ስንት አላማ ነበራት በጨዋ አግብታ የልጆች እናት ሁና ታስብ ነበር በአጭሩ ቋጨው ስንቶች ናቸው ግን በሴቶች ህይወት ላይ ሚቀልዱት ???? ህብረተሰቡስ ቢሆን ለምን እኛ ላይ ሊፈርድ ድፍረቱን አገኜ ???? ሁሉም ቢሆን የሚታየውን ነገር ማውራት እንጂ እውነታውን ለመረዳት ሚፈልግ የለም እንደ ሄኖክ አይነት ወንዶች በበዙበት ላይ ለምን በዚ ሁኔታ በራፉ ተንኳኳ......,
#part_12

ከ 50 👍 ቡኋላ

join 👇👇


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

17 Oct, 14:00


አላህ አንተ ጋር መሆኑን ስትረሳ
የብቸኝነት ስሜት ይሰማሀል!
🪴
@Proud_muslim

PROUD_MUSLIM

17 Oct, 06:30


አንድ ነገር በቀላሉ አገኘኸው ማለት
ውድ አይደለም ማለት አይደለም።

PROUD_MUSLIM

16 Oct, 09:35


አንተ እንጂ ማንም የማያውቀው ጉዳይ አለኝ
የቀረበ ምላሹን እጠይቅሀለሁ ያ አሏህ❤️

PROUD_MUSLIM

15 Oct, 18:09


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 🔟



 ቤት እንከራያለን
.... እናንተም ሲደብራችሁ መጥታችሁ የምታድሩበት አለች ተናደድኩባት
... ለምን ባህር ዳር አትሄጅም ???አባትሽ ደግሞ ይረዳሻል ስለዚ ሁሉንም ንገሪው አልኳት
,,,,,,አለቀሰች አቀፍኳት እኔኮ መዳኒቱን አግኝቼዋለሁ ያለዛ መድሀኒት መኖር አልችልም አለች
.....ምንድን ነው መድሀኒቱ ??አልኳት
......... አግኝቼዋለው አታስቢ አለችኝ እኔና ነጁ ተያየን መድሀኒቱን ስጠቀምበት እረጋጋለሁ አለች
..... ....ተርበተበትኩ የጠረጠርኩትና የፈራሁት ነገር አሰማችኝ ደነዘዝኩኝ በቃ ነጁ አቀፈችኝ እሷንም ልክ እንደምሰማው ክብረ ንፅህናዋን አሳጣት የስሜቱ መጫወቻ አረጋት ምን አይነት ሠው ነው ግን በጣም አለቀስኩኝ፡፡ ለሷ መበላሸት እኔ ነኝ ተጠያቂዋ ያኔ እንደዛ ሲፎክር አለመጠርጠሬ የዛን ቀን ተደውሎልኝ ስመለስ ምን አለ አትሂዱ ብያቸው በነበር ፡፡ ግን ምን አይነት ራስ ወዳድ ነኝ ??ሲበዛ ጨካኝ ነኝ ??ሀፍምኮ  ያኔ ያንን ድንች ባትበላ ደህና ትሆን ነበር ፡ሀሳቤን ጭንቀቴን አማክራት ነበር ....በበሳል አንደበቷ ታጠናክረኝ ነበር ሳለቅስ አደርኩ
..... ፈቲም ቻት ስታደርግ ነው የምታድረው ጠዋት መምህሩ በነገረኝ መሠረት ቤሮ ሄድኩኝ የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ተሰጠኝ ትምህርትሽ ላይ ጎበዝ ባትሆኝ ኑሮ ባባረርኩሽ ነበር አለኝ፡፡

 ተመልሼ ከፈቲና ነጁ ጋር ቤት ፈለግን ብዙም ሳንለፋ አገኜን ለቤት ሚያስፈልጓትን አንዳንድ እቃወች ገዛን የመጀመሪያ ቀን አብረን አደርን ሱሷ ግን ሳያስቺላት ቀርቶ ድንች ቤቱ ሂዳ መጣች ተከታታይ ቀን አዳሬ ከሷ ጋር በጭቅጭቅ ውሎየ በሀዘንና በድብርት ግቢ ውስጥ ሆነ ከግዜ ግዜ በጣም ተራራቅን ብቸኝነቱን ሀዘኑን የግሌ አረኩት ሁሉም አስጠላኝ

    ለካስ ሁሉም የሚያምረው በጥሩ ሠወች መልካም አስተሳሰብና ለኛ በሚጨነቁ ሠወች ከጎናችን ስላሉ ነው እነዚህን መልካምና አስፈላጊውን ነገር  በንደነ ሄኖክና ያች ከሠው በላይ ለገንዘብ በሚጨነቁ ሠወች የዛሬን ብቻ በሚያስቡ ሰወች ነው እሷ ግን ስንት ቢከፍላት ነው ምንስ ቢያደርግላት ነው በኛ ህይወት ላይ የቆመረችው??? እውነት እሷ በምትወደው ሰው ቢሆን ትጨክን ነበር??? እኔንጃ ያኔ ከገንዘብና ከምትወደው ሰው የቱን ታስበልጥ ይሆን የእውነት ግን ሚዛን ላይ ግን ታስቀምጣቸውስ ነበር የኛስ ህይወት እንደዚ መበላሸቱን ስታይ ምን ትል ይሆን??? ይፀፅታታል ወይስ በሰራችው ትኮራና ተደሰት ይሆን??? እኔንጃ
ፈቲስ እሷጋር ስትውልና መብሰሉ ቀርቶ በቅጡ እንኳን ያልተላጠ ድንች ተስገብግባ ቀን በቀን ስትበላና ስትሄድ ስታያት ምን ብላት ይሆን ??ወይስ ቀን በቀን እያሰበች ስለምትቀበለው ርካሽ ብር ገበያዋን እያደራው ስለሆነ ተደሰተች እንደውም በዛ አድርጋ ለሌሎቹስ ልትሰጥስ አቅዳና አስባም ይሆናል

 የሄኖክ ነገር አይወራም ከሰው አልተፈጠረም ሁላቺንም ትምህርታችን ላይ ጎበዝ ነበርን ለግዚያዊ ስሜት ለደቂቃወች ብቻ ለሚቆይ ደስታ ተብሎ እንዴት ሠው በሰው ህይወት ላይ ይቀልዳል?? ፈቲጋርም ከተገናኘን ቆየን ከነጁ ጋር አንዳንዴም ቢሆን አብረን እንውላለን ....ሀፍ ሁሌም አብራኝ ያለች እስኪመስለኝ በስልክ እናወራለን

    ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ  ነው ከነጁ ጋር ፈቲን ልናያት ተስማምተን በተለመደው ሠአት ለመሄድ ከተቀጣጠርንበት ቦታ ሁኜ ደወልኩላት ጀመአቸው ሹራ ለማድረግ ድንገተኛ ስብሰባ ላይ ነበረች፡፡ በነገራችን ላይ ሄኖክ ነጁን ትቷታል ምን እንዳሰበ ጀሊሉ ይወቅ ወደ ድንች ቤቱ ማምራት ጀመርኩ ያለፉ ትዝታወች በአይነ ህሊናየ መምጣት ጀመሩ እኔና ፈቲ ተቃቅፈን ያለቀስነበት ሀፍ ታማ እኔ ወደ ነጁ ስጣደፍ ፈቲ ለሀፍ እያለቀሰች ብር ስትለምን አለፍ ስል የሀፍ ፈገግታ እርጋታዋ አረማመዷ አንድ ግዜ ፈቲ ስልኳን ቀምታት ስታሯሩጣት ብዙ ብዙ ትውስታወች መጡብኝ ለምን ግን ሀፍ ይህን ያህል ጭንቅላቴን ተቆጣጠረቺው ??? ቀልዶቿ ምክሯ ድምጿ እህህህህ ስንት ነገር አለ ከሀሳቤ ያባነነኝ ሀይለኛ የመኪና ክላክሶች ነበሩ በሀሳብ ብዛት መሀል መንገድ ላይ ቁሜ ነበር በጣም ደነገጥኩ ራሴን አመመኝ ከሆነ ቆይታ ቡሀላ በጆሮየ የሆነ ድምጽ ሲገባ ተሰማኝ >>>>>>ግር ግር አትፍጠሩ ለቀቅ አርጓት የሚል ረጃጅም ሩቅ ድምጾች እየቀረቡኝ መጡ
,,,,,,,አይኔን እንደምንም ቀስ አድርጌ ስገልጥ ነጭ ብቻ ነው ሚታየኝ የጣራውን ደማቅ መብራቶች ተለማመድኳቸው ለመነሳት ስሞክር አንዲት ነጭ የለበሰች ትሁት ልጅ ቆይ እዛው ብላ ትከሻየን ጫን አርጋ አስተኛችኝ እጄ ላይ ህመም ተሰማኝ የት ነው ያለሁት ??? ማነሽ አንች ምን ልሰራ ለምን መጣው አልኳት
.....አይዞሽ ነርስ ነኝ እኔ የሆኑ ልጆች አምጥተውሽ ነው አለች ልታረጋጋኝ እየሞከረች ቆይ እኔኮ ፈቲን እህቴን ላይ ናፍቃኝኮ እየሄድኩ ነበር እሷጋር ምን ሁኜ ነው ??አልኳት የተፈጠረውን ለማስታወስ እየሞከርኩ
...........የሆነ ቆንጅየ ልጅ እኔ ነኝ ያመጣሁሽ መሀል መንገድ ላይ ድንገት ቁመሽ ቀረሽ አንችን ለማዳን ብለው ሁለት መኪኖች ተገጫጭተው ወድቀዋል እኔ አንስቼሽ ይዤሽ መጣው ይሄ ሁሉ ሰው ያንች ጉዳይ አሳስቦት መቶ ነው አለና ክፍሉ ወደተሰበሰቡት ሰወች ጠቆመኝ
......አመሰግናለሁ አልኩኝ
........እኔ ግን ከሁሉም የገረመችኝ ከቅድሙ ሰአት ጀምሮ ምርር ብላ እያለቀሰች ነበር ስላንቺ ነው የምታለቅሰው አንድ ቀንም ሳላስደስታት ለኔ ስትጨነቅ አጥሇት እያለች እያለቀሰች ነው አለኝ
 .....የት ነች ??አልኩት
......መረጋጋት ስላልቻለች እውጭ ሰው ይዟት ነው አለኝ
..... ካላስቸገርኩህ አስጠራልኝ አልኩት
.... እሽ ግን እንዳትረብሽሽ ብለን ነው አለኝ ትህትና በሞላው ንግግር
...... ማን እንደሆነች ማወቅ ስለፈለኩና ስለጓጓሁ አስጠራት አልኩት
..... እሽ ብሎ ሄደና ይዟት ገባ ነጁን ስትገባ አይሇት በጣም ደስ አለኝ አንድ ቀን እንኳን የተለየ ነገር ሳናደርግ ብየ ነጁን ተከትላ ፈቲ ስትገባ ግን ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ ውስጤን ሀይለኛ ስሜት ፈነቀለኝ ነጁ ገድፋት ነበር የገባችው ተንደርድሬ ሂጄ አቀፍኳት እጄ ላይ ተሰክቶ የነበረው መርፌ እንዴት እንደነቀልኩት ፈጣሪ ብቻ ይወቅ ተቃቅፈን መላቀስ ጀመርን ነጁም አቅፋን ማልቀስ ጀመረች አቀፈችን አብዝሀኛው ሰው አለቀሰ እጄ አነቃቀሌ ስርአት ስላልነበረው ደም በደም ሆነ ስሜቱ ሀይለኛ ነበር
___ነርሷ መድሀኒትና የመጀመሪያ እርዳታ አድርጋልኝ ወጣን ሁሉንም አመሠገንኩ በኔ ምክንያት እኔን ለማትረፍ ብለው የነበሩትን ሠወች ስጠይቅ ደህና ናቸው አለኝ የሆስፒታሉን ሙሉ ወጭ ይዞኝ የመጣዉ የማላቀዉ  ልጅ ሸፈነልኝ ፡፡ ከዛም ወደ ፈቲ ቤት በራሱ መኪናው አደረሰንና ..ድንገት ቢያምሽ ደዉይልኝ ብሎኝ ስልክ ተለዋውጠን

  ስላደረገልኝ ነገር አመስግኜ ሸኘሁት ወደ ቤት ስገባ ብዙ አዳዲስ ነገሮች አየሁ ዘወር ስል የቢራ ጠርሙስ አየሁ እውነት ፈቲ ሱስ ቢራ መጠጣት ጀምራ ነው እንዴት????......

#part_11

ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል

join 👇👇


@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

15 Oct, 12:41


ምስጋናዎችን ደስ አይሉኝም ---- ይረብሹኛል ---ያደናብሩኛል🙂

PROUD_MUSLIM

15 Oct, 08:03


🥹🥺😍

PROUD_MUSLIM

15 Oct, 05:56


ጥሩ መሆን ማለት ሁልጊዜ የሌሎችን
መጥፎ ድርጊት መታገስ ማለት አይደለም

PROUD_MUSLIM

14 Oct, 15:55


❤️አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ❤️
 
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
      🌀 #Part 9⃣



ሀፍ ተዝለፍልፋ ወደቀች ሁላችንም ደነገጥን ስትወድቅ ደግሞ በጣም ትወራጫለች በኔና ፈቲ አትቆምም ሠወች ተረባረቡብን እሷን ያዙ እኔና ፈቲ ተቃቅፈን ማልቀስ ሆነ ስራችን ሀፍሳ ደም ከጭንቅላቷ በኩል ደም መፍሰስ ጀመረ በጣም መጮህ ጀመረች የአላህ ምን አጥፍቼ ነው?? ወንጀሌ ምንድን ነው ??አለቀስኩ ወዲያው ነጁ ትዝ አለችኝ ፈቲን አንች ሀፍን ጠብቂ እኔ ነጁ ጋር ልሂድ እያልኳት ሀፍስ ነቃች ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ስታየው አለቀሰች የተመታው ጭንቅላቷን ስትነካ ደም በደም ሁናለች በጣም አለቀሰች ገባሽ ወይ ብየ ለነጁ ቴክስት አረኩላት room5negn alech
....እኔም ሀፍስ መታመሟን ነገርኳት መምጣቴን እንድታውቅ አልፈለኩም ግን በእጄ ብር ስላልነበር ሆስፒታል መሄጃ አልያዝኩም መሄድ ግድ ነው አልኳት ያለንበትንን አካባቢ ነገርኳት ግን መልስ አልሰጠችኝም ዝም አለች ፈቲ ድፍረቷ ለዚ ጠቀመን እሷ ባትጠይቅ ሀፍስ ተጎጂ ነበረች እዛ ለተሰበሰበው ሰው እያለቀሰች ሆስፒታል መሄጃ አልያዝንም እባካችሁ ተባበሩን አለች ሁሉም የቻለውን አወጣ ኩንትራት ባጃጅ ይዤ ወደ ሆስፒታል አደረስኳቸው

ለፈቲ ያለውን ብር ሰጥቼ ወደ ሆቴል መሮጥ ጀመርኩ ምን አይነት የተረገመ ቀን ነው ልቤ መንገዱ ላይ ልትወጣ እየታገለች ነው ትንፋሼ አስር አስሬ እየወጣ እየገባ ቦታ አሳጣት እንጅ መንገድ ላይ አንድ ፓሊስ አገኜሁ ነገርኩትና አብሮኝ መሮጥ ጀመረ ምነው ግን ባጃጁ ምን ግዜ ነው ይህን ያህል የነዳው አናደደኝ ፓሊሱም ሌላ ጓደኛውን ጨምሮ ደረስን ወደ ሩም 5አመራን፡፡

 በራፍ ላይ ቁሜ አዳመጥኩ የልመና ድምፅ ይሰማኛል እባክህን ተው ትላለች ...በራፉን ሰብረን ገባን ላፕቶፑ ወሲብ ቀስቃሽ ፊልም ተከፍቶበት ሁለታቸውም ራቁታቸውን ሁነው ሲታገላት ደረስን ሩጠው ያዙት፡፡  ቶሎ ብየ ነጁን ብርድልብስ አልብሼ ሁለታችንም አንገታችንን ደፍተን ተኛን ልበስ ብለው ካስለበሱት ቡሀላ ውጭ እንጠብቃችኀለን ብለው ወጡ ነጁ እቅፍ አድርጋኝ ማልቀስ ጀመረች አልቻልኩም በጣም አለቀስኩ ልብሷን ለብሳ ወጣን ነጁ ጥንካሬዋ ገረመኝ ስነልቦናዋ ጠንካራ ነው ጓደኛየ በመሆኗ ደስ አለኝ ተያይዘን ፓሊስ ጣቢያ ሄድን

   ሁሉንም ነገር ለፓሊሶቹ ነግረን ወጣን እሱ ተያዘ ቀጥታ ወደ ሆስፒታል ሄድን ሀፍ ጨርሳ ነበር ተቃቅፈን እንደገና አለቀስን ተያይዘን ወደ ዶርም ሄድን ትንሽም ቢሆን የረፍት ስሜት ተሠማን ፡፡ በአሸናፊ ስሜት ተሳሳቅን ግዜያቶች ነጎዱ የነጁንም እህት ከመታሰሩ በፊት ማንም እንዳይነካት ነግሯቸው ስለነበር ደስ ብሎናል
 ....ስጋታችን ግን አሁን በዋስ ሊወጣ ነው ያኔ እንዳይጎዳቸው ነው እስከዛ ግን ረፍት ላይ ነን ፡፡ግን ከጓደኞቹ የሚደርሠን ብዙ ማስፈራሪያወች አሉ ዛሬ ተጠባቂው ቅዳሜ ነው ሀፍስም የተሰፋላትን ተከታትላ አስፈትታለች ሙሉ ጤናዋ ተመልሷል ድንች ቤታችን ተመግበን እየተመለስን ሄኖክ መጣ ሶስታችንንም አስፈራርቶን ሄደ ትምርት መዝጊያው ግዜ እየደረሰ ነው exam በዝቶብኛል ግዜዎች ከ ሄኖክ ጋር ቀጠሉ የወራችን ቀን ነው መንገድ ላይ ተደወለልኝ ከክላስ ነበር ተመለስኩ ፈቲና ሀፍስ ሄዱ ሄኖክም የሸረበውን ሴራ ከድንች ቤቷ ጋር በብር የተመሳጠረበት ቀን የምነበላው ምግብ ላይ መድሀኒት እንድትጨምርበት እኛ ስንገባ እንድትሰጠን ተስማሙ ፡፡ ሰው ግን እንዴት ከሰው በላይ ብር ያስበልጣል?? እነፈቲ በልተው ተመለሱ ባለመምጣቴ እያዘኑብኝ


  ከሳምንት ቡሀላ ግን ነገሮች ተለወጡ ሀፍስ ከበፊቱ በበለጠ መልኩ  ብዙ ግዜ ያማት ጀመር ሲህሯ ጋር ሲደራረብ ባሰባት፡፡  ፈቲም ቀን በቀን ድንች ቤት እንሂድ ማለት ጀምራለች እንቅልፍ አበዛች ፀባያቸው ይቀያየር ጀምሯል፡   ምንም ስላልገበኝ ማሰብ ጀምሪያለው ፡፡ ለእረፍት ወደ ባህርዳር ስንመለስ ፈቲ ያልተገባ ባህሪ ማሳየት ጀመረች ሀፍስም ህመሟ ጠናባት ፡፡ ለፈቲ ባህር ዳር ውስጥ የባህልም ቂርአትም ህክምናም ያልሄድንበት የለም


 የረፍት ገዜ አልቆ ወደ አዳማ ጉዞ እንደገና በናፍቆት ተቃቀፍን አዲስ አመት አዳማ ተከሰትን  ፈቲ በገባን በማግስቱ ጀምራ ውሎዋ ሁሉ ድንች ቤት ሆነ ትምህርት ተተወ ይባስ ብላ ድንቹን ሳይበስል በጥሬው ትበላው ጀመር ግን አላረካት ይላል፡፡ ሀፍስ በቀን ትምህርትም እየተማረች ሆነ የሚጥላት ግራ የሚያጋባ አመት ነዉ ለሀፍስ አዳማ ላይ ብዙ ቦታ ሄድን መፍትሄ ጠፋ፡፡ የሀፍስ ቤተሰቦቿ ከደሴ አተማ መጥተዉ ወደ ተወለደችበት ትምህርቷን አቋርጣ ወደ ደሴ መለሷት ....,እኔም ስትለየኝ ተላቀስን ...ከእሷ ተለይቼ ብቻየን ሁኜ አለቀስኩ በጣም ከፋኝ ሚስጥሬን ማወራት በሳሏ የተረጋጋችው ሀፍሳ ከጎኔ አጠሆት የብቸኝነት ስሜት ዋጠኝ ፡፡ ሩሙ ዶርሙ ትምህርቱ ሁሉም አስጠላኝ፡፡ ነጃትም ጓደኞቿ ጋር ፈቲም ድንች ቤቷ ይሄዳሉ ሀፍስ ከጭንቅላቴ መውጣት አልቻለችም ሀፍስ ደሴ ከተማ ላይ በሸዋበር መስጊድ በሚገኘዉ ኢቅራዕ ጀመአ እና በጦለሀ መስጊድ እና አሬራ መስጊድ ታዋቂ ሩቃ አገልግሎት የሚሰጡ አሉ እዛ እየተቀራልኝ ነዉ አለችኝ፡፡ ቀን በቀን እደውልላታለው ድምፇን ስሰማ እረጋጋለሁ ምክሯ አልተለየኝም .....አሁንም
ሀሊማ ከዚ በላይ ብዙ ፈተና አለብሽ ጠንክሪ ትለኛለች ስልኩን ስዘጋው ውስጤ ይጨልማል፡፡ በሀሳብ ብዛት ፈቲን ከድንች ቤቱ ሂጄ ማመጣበት ሰአት ረስዋለው ፈቲ ድንች ቤተ መዋል ከጀመረች ዛሬ አምስት ወር ሆናት ፡፡ ደግም የሚገርማችሁ በትምህርቷ በጣም ከመስነፋ ከመዉረዷ የተነሳ ከግቢ ተጭራለች ፡እኔም በድብቅ ነው የማስገባት


አንድ ቀን ድንች ቤቱ ሁና ላመጣት ስሄድ ከሄኖክ ጋር አይኀት ራሴን ማመን አቃተኝ ምን እየተሠራ እንደሆነ አልገባኝም ፡፡ ሂጄ እጇን ይዣት ወጣሁ መንገዱን ሙሉ መጨቃጨቅ ሆነ ለነገሩ መጨቃጨቅ መለያችን ከሆነ ሰነባበተ
   ወደ ግቢ ስንገባ ፈቲ ተያዘች ማደሪያ እንደለላትና ነገ ሻንጣዋን ይዛ ትሄዳለች ብየ ተንበርክኬ ለመንኩ
 ......እሽ ግን  አንችን ነገ ቢሮ እፈልግሻለሁ ብሎኝ ወጣ ይህን ያህል ሲሆን ግን እጇን አጣጥፋ ቁማ ታየኝ ነበር>>>>>> ምን ለመሆን ነው ይሄ ሁሉ ልመና ሀሊማ ግን እየተጃጃልሽ ነው የድሮዋን ሀሊማ አልሆንሽም ራስሽን ጥለሻልኮ አለችኝ
......እያበደች መሰለኝ ትኩር ብየ አይኀት ያች ፍልቅልቋ ፈቲ የት ገባች??? ግን ሄኖክ ምን አድርጓትና አስነክቷት ነው ??? ምርር ብየ አለቀስኩ ያጠፋሁት ወንጀል ካለ ብየ ለሊት ማልቀስና መስገድ ስራየ ነው....... እና ምን እናድርግ አለች ነጁ በጣም የምትወዳትን ፈቲ በስስት እያየች
...... ቤተሰብም ምንም አያቅም ቤተሰቦቻችን አቅም ስለነበራቸው ብር አንቸገርም ነበር ቤት እንከራያለን አለች
ከማን ጋር ነዉ የምትከራይዉ ???አልኳት ......

#Part_10

ከ 50👍 ቡኋላ
ይቀጥላል


join 👇👇

@proud_muslim
@proud_muslim

PROUD_MUSLIM

14 Oct, 09:02


ለጌታሽ ተደፍተሽ ያነባሽባቸው ሌሊቶች
ሁሉ ምላሻቸው ቅርብ ነው❤️‍🩹


@proud_muslim