BURAQ ISLAMIC ® @buraq_islamic Channel on Telegram

BURAQ ISLAMIC ®

@buraq_islamic


BURAQ ISLAMIC ® (English)

Welcome to BURAQ ISLAMIC ®, a Telegram channel dedicated to spreading the teachings of Islam and fostering a sense of community among its members. This channel serves as a platform for individuals looking to deepen their knowledge of the Islamic faith, connect with like-minded individuals, and engage in meaningful discussions. Whether you are a devoted follower of Islam or simply curious about the religion, BURAQ ISLAMIC ® offers a wealth of resources and insights to help you on your spiritual journey. From daily reflections and prayers to discussions on Islamic history and traditions, this channel covers a wide range of topics to cater to the diverse interests of its members. Join us today and be a part of a welcoming and inclusive community that is committed to promoting peace, love, and understanding through the teachings of Islam. BURAQ ISLAMIC ® - Where Faith Meets Community.

BURAQ ISLAMIC ®

11 Mar, 11:56


https://t.me/alanisquranacademy
ለወዳጅ ዘመደዋ ሼር በማድረግ ይጋብዙ

BURAQ ISLAMIC ®

11 Mar, 08:21


🎧👂 ረመዳን አላህ ዘንድ ያለው ደረጃ የተዳሰሰበት
👉 ረመዳንን የመሰለ እድል አጊኝቶ ያልተጠቀመበት ሰው መጨረሻ
👉 ረመዳንን እየናፈቁ ስንቶች ተለይተውናል
👉 አሁን የያዝነውን ረመዳን እንደምንጨርሰው ምን ዋስትና አለን
👉 ቀጥታ ስርጭቱን ነገ በአላህ
ፍቃድ እንጀምራለን

🎤 በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ
በ22 ደቂቃ ብቻ የተዳሰሰበት

https://t.me/alanisquranacademy
ሼር አንድን ኸይር ያመላከተ የሰሪውን ያክል ምንዳ ያገኛል ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም

BURAQ ISLAMIC ®

10 Mar, 07:40


👉ከአል አኒስ የቁርአን ትምህርት ቤት
👉ነፃ የተጅዊድ ኮርስ እና
👉ቁርአን ተፍሲር ቀጥታ ስርጭት በረመዳን ቀናቶች
👉የቁርአንን ትርጉሙን እንማር  ለዛውን እናጣጥም
👉ረመዳንን ከኛ ጋር እንዲያሳልፉ  ተጋብዘዋል
👉 ረመዳንን ተጠቅመንበት የምናሳልፈው ያድርገን

👉አላማች ቅን ባለ ራእይ ዲኑን የሚያውቅ ጤናማ ትውልድ መፍጠር ነው ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ
https://t.me/alanisquranacademy
ወዳጅ ዘመደዎን ይጋብዙ ሼር👆👆👆👆👆

BURAQ ISLAMIC ®

26 Feb, 12:13


ልብህ🫀ሲሰበር ወደ ፍጡር አትሩጥ ( አትሽሽ )
ወደ ፈጣሪህ الله ሽሽ

يزيد المخلوق هما فوق همك
وأما الخالق يرفعوا عنك همك
ፍጡር በሀሳብህ ላይ ሀሳብ ይጨርልሀል።ፈጣሪ ግን ሀሳብህን ያነሳልሀል።
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

25 Feb, 19:06


አስታውሽ!
- ባለ መልካም መአዛ አበቦችና ለምለም ቅርንጫፎች ላይ እንደምታርፍ ንብ ሁኝ
- የሰወችን ጉድለትና ነውር የምታነፈንፊበት ጊዜ አይኑርሽ
- አላህ ካንቺ ጋር ከሆነ ማንን ትፈሪያለሽ? እሱ ከራቀሽ ማን ተገን ይሆንሻል?
- ቅናትና ምቀኝነት እሳት ናቸው እራስን ይጎዳሉ
- ዛሬ ካልተዘጋጀሽና ካልሰራሽ የነገን የሚያውቀው አላህ ነው
- ክርክር ካለበት ቦታ ገለል በይ
- መልካም ስነምግባርን ባህሪሽ አድርጊ
- ጠላቶችሽን ችላ ብለሽ መልካምን ተመኝላቸው
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

24 Feb, 16:59


ክብር ይገባሻል!
# አንቺ አላህን ፈርተሽ የምትሰግጅና የምትፆሚ ሴት! ክብር ይገባሻል
# አንቺ ሂጃብሽን አሟልተሽ የምትለብሽ  ብልህና ራስሽን ጠባቂ ሴት! ክብር ይገባሻል
# አንቺ ተማሪዋና አንባቢዋ ሴት! ክብር ይገባሻል
# አንቺ ለጋስ እውነተኛ አደራ ጠባቂና ታማኝ ሴት! ክብር ይገባሻል
# አንቺ በትእግስት ከአላህ ምንዳን የምትጠብቂና በፀፀት ወደሱ የምትመለሽ ሴት! ክብር ይገባሻል
# አንቺ አላህን የምታስታውሺ የምታመሰግኝና ዘወትር የምትለምኝው ሴት! ክብር ይገባሻል
# አንቺ የአሲያን የመርየምንና የኸዲጃን ፈለግ የተከተልሽ ሴት! ክብር ይገባሻል
# አንቺ ልጆችሽን በተርቢያ የምታሳድጊ ሴት! ክብር ይገባሻል
# አንቺ የአላህን ድንበር የማታልፊና ከከለከላቸው ነገሮች የምትርቂ ሴት! ክብር ይገባሻል።
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

24 Feb, 11:58


አንዳንዴ .......
በቀረብናቸው ሰዎች ውስጣችን ይሰበራል።ጭራሽ ያልጠበቅነውን ነገር ከእነሱ እናስተናግዳለን። አዎ ህይወት እንደዚህ ነች። መሰበር መጠገን ማልቀስ መደሰት ማዘን መተከዝ ማቀድ መወሰን መውደቅ መነሳት ........
ግን የሆነ ቀን ላይ ማዘናችን መሰበራችን እና መውደቃችን ለሆነ ቀን ትምህርት ይሆነናል።
አላህ ከዱንያም ከአኼራም ፈተና ይጠብቀን🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲አሚን
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

21 Feb, 17:14


ቀልብህን
በሰላት  ==> አድሳት
በዚክር  ==> አርጥባት
በቀድር  ==>  አሳምናት
በቁርአን ==> አክማት
በየቂን   ==> አጠንክራት
በኢማን  ==> አበልፅጋት
በሞት    ==>  አለስልሳት
በቀብር  ==> አስፈራራት
በጀሃነብ  ==> አስጠንቅቃት
በጀነት   ==>አበሽራት🧡
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

20 Feb, 16:46


أفضل الأعمال
الصلاة على أول وقتها
ከስራ ሁሉ በላጩ ሶላትን በጊዜ መስገድ ነው።
ሶላትን የተወ የቤቱን ቁልፍ ጥሎ እንደወጣ ሰው ነው።
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

19 Feb, 05:05


السُّنَّةُ وَالۡبِدۡعَةُ

ሱንና እና ቢድዓ(ፈጠራ)

س١ - : هَلۡ فِي الدِّينِ بِدۡعَةٌ حَسَنَةٌ ؟

ج١ - : لَيۡسَ فِي الدِّينِ بِدۡعَةٌ حَسَنَةٌ وَالدَّلِيلُ قَوۡلُهُ تَعَالَى: ﴿ ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَـٰمَ دِينًا ﴾ (سورة المائدة).
وَقَوۡلُهُ ﷺ: (وَكُلُّ بِدۡعَةٍ ضَلَالَةٌ، وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ) (صَحِيحٌ رَوَاهُ أَحۡمَدُ وَغَيۡرُهُ).

ጥ.1 በዲን ላይ መልካም የሆነ ፈጠራ(ቢድዓ) አለን?

መ.1 በዲን ላይ መልካም የሆነ ፈጠራ(ቢድዓ) ሚባል ነገር ዬለም. መረጃዉም ካፍ ያለው የአላህ ቃል ነው:- “ ዛሬ ሀይማኖታቹን ለናንተ ሞላሁላቹ, በናንተ ላይም ጸጋዬን አደረግኩ` እንዲሁም ለናንተ እስልምና ሀይማኖትን ወደድኩላቹ. ” 
(ሱራህ አል-ማኢደህ 3:5)

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: “ሁሉም ቢድዓ(ፈጠራ) ጥሜት ነው. ሁሉም ጥሜት የእሳት ነው." (ሰሂህ አህመድና ሌሎች ዘግበውታል)

س٢ - : مَا هِيَ الۡبِدۡعَةُ فِي الدِّينِ ؟

ج٢ - : الۡبِدۡعَةُ فِي الدِّينِ هِيَ الزِّيَادَةُ فِيهِ أَوِ النُّقۡصَانُ. قَالَ اللهُ تَعَالَى مُنۡكِرًا عَلَى الۡمُشۡرِكِينَ بِدۡعَهُمۡ: ﴿ أَمۡ لَهُمۡ شُرَكَـٰٓؤُا۟ شَرَعُوا۟ لَهُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا لَمۡ يَأۡذَنۢ بِهِ ٱللَّهُ ﴾ (سورة الشورى).
وَقَالَ ﷺ: (مَنۡ أَحۡدَثَ فِي أَمۡرِنَا هَٰذَا مَا لَيۡسَ مِنۡهُ فَهُوَ رَدٌّ) (مُتَّفَقٌ عَلَيۡهِ) (رَدٌّ: غَيۡرُ مَقۡبُولٍ).

ጥ.2 በዲን ላይ ፈጠራ(ቢድዓ) ማለት ምን ማልት ነው ?

መ.2 በዲን ላይ ፈጠራ(ቢድዓ) ማለት በዲን ላይ የሌለን ነግር መጨመር ወይንም መቀነስ ነው, አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓለ በአጋሪያን ፈጠራቸውን በማውገዝ እንዲህ ይላል: “ለነሱ አላቸውን! ተጋሪ (በአምላክነት) አላህም በሱ ያልፈቀደበትን ከሀይማኖት ለነሱ የሚደነግጉላቸው. " (ሱራህ አሽ-ሿአራ 42:21)
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: “በዚህኛው ጉዳያችን(ዲናችን) ላይ ከሱ ያልሆነን አዲስን ነገር የጨመረ እሱ ተመላሽ ነው.” (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

س٣ - : هَلۡ فِي الۡإِسۡلَامِ سُنَّةٌ حَسَنَةٌ ؟

ج٣ - : نَعَمۡ فِي الۡإِسۡلَامِ سُنَّةٌ حَسَنَةٌ. قَالَ ﷺ: (مَنۡ سَنَّ فِي الۡإِسۡلَامِ سُنَّةً حَسَنَةً، فَلَهُ أَجۡرُهَا وَأَجۡرُ مَنۡ عَمِلَ بِهَا مِنۡ بَعۡدِهِ، مِنۡ غَيۡرِ أَنۡ يَنۡقُصَ مِنۡ أُجُورِهِمۡ شَيۡءٌ) (رَوَاهُ الۡبُخَارِيُّ).

ጥ.3 በኢስላም ዉስጥ መልካም የሆነ ፈለግ(ሱና) አለን ?

መ.3 አዎ, በኢስላም ዉስጥ መልካም የሆነ ፈለግ(ሱና)አለ. የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: “ በኢስልምና ዉስጥ ከዚህ በፊት ኖሮ የተረሳን የሆነን መልካም ፈለግ(ሱና) ሀይ ያደረገ ሰው ልሱ ምንዳ አለው እንዲሁም ከሱ በኋላ ሰዎች ሲሰሩበት ከነሱ ምንዳ ምንም ሰይቀነስ አሱም ምንዳ ያገኛል". (ሙስሊም ዘግበውታል)

س٤ - : مَتَى يَنۡتَصِرُ الۡمُسۡلِمُونَ ؟

ج٤ - : يَنۡتَصِرُ الۡمُسۡلِمُونَ إِذَا رَجَعُوا إِلَى تَطۡبِيقِ كِتَابِ رَبِّهِمۡ وَسُنَّةِ نَبِيِّهِمۡ ﷺ وَأَخَذُوا بِنَشۡرِ التَّوۡحِيدِ، وَحَذَرُوا مِنَ الشِّرۡكِ عَلَى اخۡتِلَافِ مَظَاهِرِهِ، وَأَعِدُّوا لِأَعۡدَائِهِمۡ مَا اسۡتَطَاعُوا مِنۡ قُوَّةٍ، قَالَ اللهُ تَعَالَى:﴿ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تَنصُرُوا۟ ٱللَّهَ يَنصُرۡكُمۡ وَيُثَبِّتۡ أَقۡدَامَكُمۡ ﴾ (سورة محمد).
وَقَالَ أَيۡضًا: ﴿ وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمۡ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ لَيَسۡتَخۡلِفَنَّهُمۡ فِى ٱلۡأَرۡضِ كَمَا ٱسۡتَخۡلَفَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمۡ دِينَهُمُ ٱلَّذِى ٱرۡتَضَىٰ لَهُمۡ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّنۢ بَعۡدِ خَوۡفِهِمۡ أَمۡنًا ۚ يَعۡبُدُونَنِى لَا يُشۡرِكُونَ بِى شَيۡـًٔا ﴾ (سورة النور).

ጥ.4 ሙስሊሞች መቼ ነው ከአላህ የሚረዱት/የሚታገዙት?

መ.4 ሙስሊሞች የሚረዱት የጌታቸውን መጽሃፍ(ቁርኣን) እንዲሁም የነቢያቸውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱና አጥብቆ ወደ-መያዝ ሲመለሱ, ተውሂድን በማሰራጨት በቆዩ ግዜ, ሽርክን ከተለያዩ አይነቶቹ ጋር ባስጠነቀቁ ግዜ እና ለጠላቶቻቸው ከሀይል በቻሉት ያክል

በተዘጋጁ ግዜ ነው። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል: እናንተ ያመናቹ ሆይ! (1)አላህን ከረዳቹት(የአላህን ዲን የምትረዱ ከሆነ), እሱ ይረዳቿል, ተረከዞቻቹንም ያጸናላቿል.” 
(ሱራህ ሙሃመድ 47:7)
(1)
አላህን ከረዳቹት ሲባል ከላይ መ.4 ላይ እንደተብራራው ከሆንን ማለት ነው።
በተጨማሪም ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:- “ ከናንተ ለነዚያ ላመኑት መልካምንም ስራ ለሰሩት ሰዎች አሏህ ከነሱ በፊት የነበሩ ሰዎችን እንደተካው ምድር ላይ ሊተካቸው፣ ያን ለነሱ የወደደውንም ሀይማኖት ሊያመቻችላቸው፣ ከፍርሃት በኋላም ሰላምን ሊተካላቸው ቃልን ገብቷል. እኔንም ይገዙኝ በኔም ምንም ነገር አያጋሩ።”. (ሱራህ አንኑር 24:55

BURAQ ISLAMIC ®

18 Feb, 06:29


የተስፋ መስኮቶች ሁል ጊዜ ለእኛ ክፍት ናቸው።
እኛ ነን በተስፋ መቁረጥ አቦራ የምናበላሸው።

ስለ ጥሩው ነገር ብሩህ አመለካከት ይኑርህ ና ታገኘዋለህና
መልካም ቀን
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

17 Feb, 13:19


https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

17 Feb, 04:25


አዎ!! ሰላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፣ሒጃብ የምትለብስ ሴት እና ተገላልጣ የምትሄደው አላህ ዘንድ ያላቸው ቦታ በጣም የተለያየ ነው፣የቀጣይቱ አለም ፀጋ ከቅርቢቱ አለም የተሻለ እና ዘውታሪም ነው።ሁሌም ቢሆን እግሮቹ መሬት ላይ ሆነው የማንነቱ ከፍታ ከከዋክብት ስር የሚሆን ሰው ለመሆን ጣር።ሕይወትህም ልዩ ትርጉም እንዲኖራት ቀጣዩ አለም ድረስ የሚዘልቅ አላማ ሊኖርህ ይገባል!!

✍️✍️ ከሰበዞች
https://t.me/sebezoch1212

       

BURAQ ISLAMIC ®

16 Feb, 14:21


🤍ህይወት የፈለገ ያህል ከባድ
ጭንቀተማና አድካሚ ብትሆንም
ሁለት ደስ የሚሉ ጣእምን የሚሰጧት
ነገሮች አሉ ‥ እንሱም
⇘ አላህን ማውሳት እና ለአላህ ብሎ
ከሚወድህ ልብ የሚመጣልህ ዱዓእ ነው ።
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

14 Feb, 06:17


አንዳንዴ ስሜቶቻችን ይቆጣጠሩናል።

ከውስጣችን ላይ እንደቀለጠ እሳተ ገሞራ የሚገላበጥ ብዙ የንዴት፣የሀዘን ፣የፀፀት ስሜቶች ይኖራሉ።።
እነዚህ ስሜቶች ገንፍለው እስካልወጡ ድረስ ውስጣችንን አቃጥለው ይጨርሱናል።ለዚህም ሲባል ለሚሰሙን ኔጋቲቭ ስሜቶች ከውስጣችን ላይ ቦታ አናስቀምጥ። የተሻለ ህይወት ለመኖር የተሻለ ማሰብ የሚል መፈክር ይዘን እንኑር
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

14 Feb, 04:44


🟥 እስቲ ስንተኛውን ይመርጣሉ ?

1 -አንድ ማንኪያ ስኳር የሻይን ጣዕም ትለውጣለች፤ ያንተ ጥሩ ንግግርህ ደግሞ  ሰዎች ስላንተ ያላቸውን እይታ ትቀይራለች!  በጥሩ ንግግርህም ሚን ዒንዲላህ በመልካም ትመነዳለህ

2 -ስህተትህን ለመሸፈን ብለህ ሌሎች ሰዎችን አትበድል፤ ሁልጊዜም ደስታህን ከሌሎች ሰዎች ህመም የራቀ አድርግ!

3 -ትልቅ ውድቀት ወድቆ መቅረት እንጂ ወድቆ መነሳት አይደለም!

4-በህይወት መንገድህ አታርፍድ፣ ካረፈድክም አትቅር፣ ምክንያቱም ካረፈድክ ትቀጣለህ፣ ከቀረህ ግን ታጣለህ!

5-አልሳካ ሲልህ መንገድህን እንጂ ዓላማህን አትቀይር፤ ዛፍ ቅጠሉን እንጂ ስሩን አይቀይርምና!

6-አስታውስ! የምትወድቀው ሌሎችን ለመጣል ስትሞክር ነው!

7-የወደቁትን ለማንሳት አቅሙ ከሌለህ፣ ቢያንስ ለሚወድቁት ምክንያት አትሁን!

8-አንተ ጎንበስ ካላልክ ማንም ጀርባህ ላይ አይወጣም!

9-ሦስት ነገሮችን እመን፦ የአላህን ውሳኔ ፣ ስህተትህንና ያየኸውን።

ስንተኛው ይበልጥ ጠቃሚ መልዕክትን ይዟል?


እንደናንተው ይሄ መልዕክት የሚያስፈልገው አካል
ይኖራልና ለቻላቹት ሁሉ ሼር ያድርጉ በዛውም
የሰዎችን ምርጫ በመመልከት ከሰዎች ይማሩ

ባረከላሁ ፊኩም

BURAQ ISLAMIC ®

13 Feb, 20:13


እናት ዱንያ ላይ ያለች ከንዝ(ውድ ሀብት) ናት
እናቶቻችንን አላህ ይጠብቅልን ያረብ🤲

https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

13 Feb, 09:16


2ኛ የትልቁ ሽርክ አይነት:- ከአላህ ውጭ ላለ መሳል(መነዘር)
ነዝር(ስለት) ማለት:- አንድ ሰው ሸሪዐ ግዴታ ሳያደርግበት በራሱ ላይ ግዴታ የሚያደርገው የኢባዳ አይነት ነው።

👉ስለት ሸሪዐ ግዴታ ባያደርገውም አንድ ሰው ባራሱ ላይ ግዴታ ካደረገ በኋላ ማሟላቱን ግን ግዴታ ያደርግበታል።
👉 ስለትን ከአላህ ውጭ አሳልፎ መስጠት ትልቁ ሽርክ ነው።
የስለት ክፍሎች
1 መፈፀሙ (ማሟላቱ ግዴታ የሆነ):- እሱም ሀላል በሆነ ነገር የተሳለ ሰው አላህ የጠየቀውን ነገር ካደረገለት ስለቱን ማሟላት ግዴታ ይሆናል።

2 መፈፀሙ( ማሟላቱ ) ሀራም የሆነ:- እንደዚህ አይነቱ የስለት አይነት አንድ ሰው ሀራም በሆነ ነገር ላይ የተሳለ ከሆነ ለምሳሌ:- አላህ ይህንን ቢያሳካልኝ ለአላህ ስል ይህን ያክል ሊትር ኸምር እጠጣለው..... ቢል ማሟላቱ ሀራም ነው። ይህንን የስለት አይነት አይፈፅፅም የስለቱ ከፋራ ያወጣል።

3 የተጠላ የስለት አይነት:- እንዲህ አይነት የስለት አይነት ደግሞ አንድ ሰው በማይችለው ነገር ወይም ራሱን በሚጎዳ ነገር ከተሳለ ለምሳሌ:- አላህ ይህንን ካደረገልኝ በአንድ እግሬ ፀሀይ ላይ ለሶስት ቀናቶች እቆማለው። እና የመሳሰሉት ከሆነ መፈፀሙ የተጠላ ነው። ይህ አይነት ስለት አይፈፀምም ከፋራ ይወጣበታል።

4 ያልተሰየመ(ልቅ የሆነ) እንደዛህ አይነት የስለት አይነት ደግሞ አላህ ይህንን ካደረገለኝ ተስያለው ሊል ነው።ምን አይነት ዒባዳ እንደሚሰራ አልጥራም እንደዛህ አይነት ስለት አይፈፀምም ግን ከፋራ(ማካካሻ) ይፈፅማል።

የስለት ከፋራ
1 ባሪያን ነፃ ማውጣት
2 10 ሚስኪን ማብላት ወይም ማልበስ
3 ሶስት ቀን መፃም

3ኛ የትልቁ ሽርክ አይነት ...........
https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

13 Feb, 09:16


ገድ ምንድን ነው።🤔

ገድ ማለት ከሽርክ አይነቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በአንድ ነገር ላይ ከአላህ ውጭ ተንጠልጣይ መሆን ማለት ነው።

ለምሳሌ ከቤታችን ወደ ስራ ለመሄድ በምንወጣበት ጊዜ አንድ ውሻ(ጥቁር ውሻ)፣ቁራ የመሳሰሉት በበራችን ላይ ቢያልፉ ወይም ደግሞ ቁራውን እያየነው ወደ ግራ ሲበር ዛሬ አይቀናኝም በቃ ልመለስ ጥሩ አይመጣም እያልን በቁራው ለይ ወይንም በዉሻው ላይ ገድ መጣል ማለት ነው።

ገድ ትንሹም ትልቁም ሽርክ ውስጥ ይገባል።

ትልቁ ሽርክ ውስጥ እሚገባው ውሻውን ወይም ቁራውን ከአላህ አሰበለጠን እነሱን መከተል ትልቁ ሽርክ ውስጥ ያስገባል።

ለምሳሌ ውሻው ዛሬ በቀኝ ካላለፈ ከቤቴ አልወጣም ሙሉ በሙሉ ውሻው ላይ ነው የተንጠለጠለው ይህ ደግሞ ትልቁ ሽርክ ውስጥ ያስገባዋል።

ትንሹ ሽርክ ውስጥ እሚገባው ደግሞ ውሻውን ምክንያት ሲያረግ ግን ሙሉ በሙሉ ሳይንጠለጠልበት።

ለምሳሌ ዛሬ ውሻው በግራ በኩል ነው ያለፈው አላህ ኸይር ያርገው።

ገዳችንን ሙሉ በሙሉ በአላህ ላይ ማረግ አለብን።

እንግዲ ረመዷንም እየደረሰ ነው ሻዕባንን እየፆምን እንጠባበቀው

አላህ ደርሰው ከሚፆሙት ያርገን

https://t.me/sebezoch1212

BURAQ ISLAMIC ®

11 Feb, 19:07


«ጥንቃቄ፦  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ብዙ ወጣት ሴቶች በሚዝናኑባቸው ቦታዎች ትላልቅ ከተማዎች ላይ GHB የሚባል ኬሚካል ተበራክቷል። "ጋባዦች" አንድ መጠጥ ውስጥ  የGHB ጠብታ ሲጨምሩበት ተጠቂዎች (አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች) በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ያሉበት፣ አብረዋቸው የነበሩበትን እና የተወሰዱበትን ቦታ አያስታውሱም። ገንዘብ ተከፍሏቸው የደነዘዙ ሴቶችን ለማስደፈር የሚያቀርቡ ውጣት ወንዶችም ሴቶችም ይሄንን እየሰሩ የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። በተለይ "የቤት ልጅ" አይነት የሚባሉ (ተማሪዎች) እና ሌሎች ወጣት ሴቶች የዚህ ወንጀል ተጠቂ እየሆኑ ነው። GHB ከሰውነታቸው ወጥቶ ሲነቁ በማይታወቅ ቦታ ብዙ ጉዳት ደርሶባቸው ራሳቸውን ያገኛሉ። ምን እንደተፈጠረ አያውቁም። GHB የሰው ሕይወት ሊያጠፋ ይችላል። በከተሞች መዝናናት እና መገባበዝ ደግሞ የተለመደ ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። እንዲህ አይነት ወንጀሎች በቅርብ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ውጪ ከኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው።»

https://t.me/sebezoch1212