ዘ Campus Life @zcampus_life Channel on Telegram

ዘ Campus Life

@zcampus_life


◉ WELCOME TO ዘ Campus Life◉

This channel is created to help freshman and Remedial students!
📚Short text notes in English with short
Amharic explanation
📚Hand writing notes by photo
📚 Voice explanations
📚 Campus life 😚🤔🥰

ዘ Campus Life (Amharic)

ለዛሬ በ በጣምነኛ ሰልካ የተለያዩ አይዲት እና በትምህርት የተመረጡ ተመልከተ አይዲት ተጠቃሚዎችን ድል እና በስነ ምግባራ አዲስ ገጽ ማስወገድ እንዴት ነው፡፡

በወቅታዊ ትምህርት ዙሩ Notes በእኛም በትምህርት ሳቅ ደረጃ ከእናንተ እንዲማሩ ያናግሩ፡፡
📚 ፍቃድወፍታዎች እና ትምህርት ስለማንኛውም ምሳሌ በ እርስዎ አማልክት ውስጥ እውቅን አዋልቃቸዋል፡፡
📚 ግምት መለያየትን በፎቶ ለአዲስ ማንኛውም ተቀብሎ እንቀመጣለን፡፡
📚 ትምህርት መልእክት
📚 የተንቀሳቃሽ እምነት እየወርዳችሁ መገንነት፡፡ 😚🤔🥰

ዘ Campus Life

21 Nov, 19:01


ዘ Campus Life pinned «📢 ግቢ ውስጥ አዲስ ሊሆኑባቹህ የሚችሉ የግቢ ቃላቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት!🆕 ⭐️ ካፌ-  ብዙሃኑ ተማሪ የሚጠቀምበት  የግቢው መመገቢያ ቦታ ⭐️ ላውንጅ - ግቢ ውስጥ የሚገኝ ተማሪን ባመከለ መልኩ ክፍያ የሚያስፈልግ ካፌ ነገር ነው  ፤ ምግብና መጠጦቹ(ለስላሳ ፣ ትኩስ ነገር ምናምን) ጥራት ያላቸው እና በዋጋም በጣም ቅናሽ ናቸው። ⭐️ ችከላ- ጥናት ⭐️ ቴንሽን- ጭለላ ፣ ውጥረት፣ መረበሽ፣…»

ዘ Campus Life

21 Nov, 18:59


📢 ግቢ ውስጥ አዲስ ሊሆኑባቹህ የሚችሉ የግቢ ቃላቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት!🆕

⭐️ ካፌ-  ብዙሃኑ ተማሪ የሚጠቀምበት  የግቢው መመገቢያ ቦታ

⭐️ ላውንጅ - ግቢ ውስጥ የሚገኝ ተማሪን ባመከለ መልኩ ክፍያ የሚያስፈልግ ካፌ ነገር ነው  ፤ ምግብና መጠጦቹ(ለስላሳ ፣ ትኩስ ነገር ምናምን) ጥራት ያላቸው እና በዋጋም በጣም ቅናሽ ናቸው።

⭐️ ችከላ- ጥናት

⭐️ ቴንሽን- ጭለላ ፣ ውጥረት፣ መረበሽ፣ መጨናነቅ

⭐️ 11  - ግማሽ እንጀራ በዳቦ ( የካፌ ምግብ ነው በተለይ እራት ላይ)

⭐️ Non-cafe - የግቢውን ካፌ የማይጠቀሙ ተማሪዎች

⭐️ Space - ባዶ ክፍል ብዙውን ጊዜ መማሪያ ክፍሎችን ለንባብ ስንጠቀምባቸው ስፔስ ይባላሉ

⭐️ Therefore- የካፌ ስጋ  ( ስጋ ሲባል ግን ሰፍ እንዳትሉ ! እንደስሙ ነው ማለት ትንሽ ስጋ ጣል ጣል የተደረገበት ገራሚ መረቅ )


⭐️ Cost -ካፌ ለማይጠቀሙ ተማሪዎች የሚሰጥ ወርሃዊ ክፍያ ፤ የሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ክፍያው ተመሳሳይ ነው።

⭐️ Add and drop - በትምህርት ሂደት ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ነገሮች ናቸው ፤ ይሰውራቹህና የሆነ ኮርስ ከፈላ(F) add and drop process ግድ ይሆናል

⭐️ ድድ ማስጫ- አላፊ አግዳሚውን ለማየት አመቺ የሆነ ቦታ ወይም መቀመጫ 

⭐️ ዛፓ - ጥበቃ ሰራተኞች

⭐️ GC- ተመራቂ ተማሪዎች

⭐️ Fresh፣ጦጣ ምናምን  - አዲስ ገቢ ተማሪዎች ( ግቢ ስትገቡ ፍሬሽ ምናምን እያሉ አዛ የሚያደርጓቹህ ብዙውን ጊዜ ሁለተኛ አመቶች ናቸው ሁሉም ሁለተኛ አመቶች ሳይሆኑ ፍሬሽነታቸውን ያልጨረሱት ወይም ገራሚ ፉገራ የተፎገሩት ናቸው

⭐️ በርጮሎጂስት- የፍየልን መኖ የሚጋፉ ጫት ቃሚዎች ማለት ነው

⭐️ ኦቨር- መጠጥ ቤት መሄድና ሰክሮ መምጣት

⭐️ ሻታ - ይቅርባቹህ እንዳያስመልሳቹህ ብዬ ነው


⭐️ ጥፊ- የዶርምን ላይፍ እንዳይረሳ ከሚደርግ ግሩም ጠረኖች ውስጥ አንዱ ነው፤ በተለይ በተለይ ወንዶች ጋር የተለመደ የካልሲ ጭስ ነው ( ወንዶችዬ ተዉ ግን አታሰደቡን? )

⭐️ Meal Card- የግቢው ካፌ ውስጥ ለመመገብ በግቢው የሚሰጣችሁ የመመገቢያ ካርድ።


"... የማናውቃቸው ድብቅ ስሞች ካሉ Comment'ቱ ክፍት ነው 😅

@Zcampus_Life

ዘ Campus Life

19 Nov, 15:30


በስተመጨረሻ😅

ዘ Campus Life

19 Nov, 15:30


WolkiteUniversity

በ2017 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 26 እና 27/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3x4 መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር በውጤታችሁ መሰረት ዳግም ቅበላ የተፈቀደላችሁ ተማሪዎች በተጠቀሱ ቀናት እንድታመለክቱ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@Zcampus_Life

ዘ Campus Life

19 Nov, 15:28


በተያዘው የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ከታቀደው የተማሪ ቁጥር የተመዘገበው በአስር ሚሊዮን ያነሰ እንደሆነ ተገለፀ።

በመላ ሀገሪቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ባሉ ትምህርት ቤቶች ከ32 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የተመዘገቡት ግን 21.7 ሚሊዮን ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከዕቅድ በታች የሆነው በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተቋማቸውን የሦስት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ይህን ለማስተካከል የመምህራን ባንክ ማቋቋምን ጨምሮ የተለያዩ የማትጊያ ስርዓቶች ይዘረጋሉ ብለዋል።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
@Zcampus_Life

ዘ Campus Life

18 Nov, 15:34


ዩኒቨርስቲዎች አዲስ ተማሪዎቻቸውን እየተቀበሉ ይገኛሉ።

እየተቀበሉ የሚገኙት :-
👉 WolaitaSodo University
           👉 Aksum University
           👉 Raya University
           👉 Madda walabu University

የ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛሉ።


ለበለጠ መረጃ:-
Official channel
      👇👇👇👇👇👇
@Zcampus_Life

ዘ Campus Life

14 Nov, 07:51


#MizanTepiUniversity

⭐️በ2017 ዓ.ም በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 11 እና 12/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ፡፡

✔️ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ብሄራዊ ፈተና ውጤት
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ዘጠኝ የቅርብ ጊዜ 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

🌟 @Zcampus_Life ⭐️

ዘ Campus Life

13 Nov, 11:48


✔️Bahirdar University
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መስጠት ጀምሯል፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚሰጠው ፈተና፤ ተማሪዎቹ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ጀማሪ መርሐግብር (Freshman) ለመግባት የሚያስችላቸውን ውጤት የሚለይበት ነው፡፡

በማኅበራዊ ሳይንስ (378) እና በተፈጥሮ ሳይንስ (950) በድምሩ 1,328 ተማሪዎች ፈተናውን በዩኒቨርሲቲው ሦስት ግቢዎች ማለትም በፖሊ፣ ፔዳ እና ሰላም ግቢዎች መውሰድ ጀምረዋል።

@Zcampus_Life

ዘ Campus Life

13 Nov, 06:13


✔️ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኅብረተሰብ ጤና የማስተርስ ፕሮግራም (MPH) መደበኛ እና የዕረፍት ቀናት አመልካቾች የቃል ፈተና አርብ ህዳር 6/2017 ዓ.ም ጠዋት 3:00 በተቋሙ አካዳሚክ ህንጻ እንደሚሰጥ ገልጿል።



@Zcampus_Life 💎

ዘ Campus Life

12 Nov, 18:21


✔️የወንዶች ከማን አንሼ✔️


@Zcampus_Life
@Zcampus_Life

ዘ Campus Life

12 Nov, 17:00


✔️#RayaUniversity

ለ2017 የትምህርት ዘመን ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@Zcampus_Life✔️

ዘ Campus Life

12 Nov, 14:36


✔️ freshman logic chapters save it you need it for later

@Zcampus_Life✔️