ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media @great_ethiopia_official Channel on Telegram

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

@great_ethiopia_official


This is ታላቋ ኢትዮጵያ - Great Ethiopia official Telegram channel

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media (Amharic)

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media ከእርሱን በፊት የሚያሰፋው መረጃ የምንለዋወጥ ሲሆን አገራችን አደረገ። ይህ ቅሬታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መንግሥትን እና የኢትዮጵያ ብሔርን መረጃዎችን መስራት ይችላል። የታላቁ ኢትዮጵያ እና አእምሮ ህዝቦችን ጠብቁ። ይህ አዳዲስ ታሪክ፣ የኢትዮጵያ ባንዳንን ወንድማማችን መካከል ይሆናል። በዚህ ቅኔታ ከመዋላት ያስፈልገዋል እና በዚህ አተሕዳሪዝም መዋላት ያናገራሉ። ይህ ታላቅ ኢትዮጵያን ከእንግሊዝኛው እርስዎ የሚያቀርቡት ሰውየትና መንግስትን በመምሪያ ላይ እንመለከታለን። ከዚህ በፊት፣ አብረን አል ወፍ እና የሰውየት እግር መኖሩን ለማየት የሚያደርገው እረት ነን። እንደመረፈ፣ በዚህ ታሪካዎ ላይ በሚበቀል ወንድማማችን ስራ እና እንዴት እንሰጣላለን።

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

09 Aug, 19:38


በእውነት ልብ ሰባሪ ውጤት ነው 😭🙏ተፅናኑ🙏
ኢትዮጵያ 6ተኛ ወጣች 😭😭😭ጣሊያን በአቅሟ 2ተኛ ወጣች 😭😭😭😭😭ያማል 😭😭😭ተበቀሉን😭
ኢትዮጵያ በ10 ሺህ የሴቶች ፍፃሜም አላሸነፈችም 🙏🙏 በጣም ያሳዝናል ዘንድሮ አቀባበል የለም 🚫🚫🚫 #ሼር
ዛሬም ያው ነው ሜዳሊያ ውስጥ አልገባንም።
👇👇👇👇
ኢትዮጵያ በ 10000ሜትር ምንም አይነት ሜዳሊያ ማግኘት ሳትችል ቀርታለች።

ኬንያ ወርቅ ፣ ጣልያን ብር እንዲሁም ኔዘርላንድ ነሐስ ማግኘት ችለዋል።

6ኛ ጉዳፍ ፀጋይ
7ኛ ፎቴን ተስፋይ
10ኛ ጵጌ ገብረሰላማ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

01 Aug, 15:36


https://youtu.be/_rQb5N4dOoQ

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

17 Jun, 15:03


የሚገርመው በታሪክ በአውሮፓ ዋንጫ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ሳይሸለም ቀርቶ ሪከርዱንም ሊሰብረው የሚችል ያልተገኘ ሲሆን የክብሩ ባለቤትም የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ኮኮብ የነበረው እና በ1984ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ላይ 9 ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ሚሼል ፕላቲኒ ነው።
ይህ ኮከብ በወቅቱ የኮኮብ ጎል አስቆጣሪ ሽልማት የሚሰጥ ባለመሆኑ ለመታደል ያልበቃ ሲሆን
በአውሮፓ ዋንጫ የኮኮብ ጎል አስቆጣሪነት ሽልማት የተጀመረው በ1996ቱ እንግሊዝ ባዘጋጀቺውና ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓን ዋንጫ ባነሳችበት ወቅት ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ በሽልማቱ በ5 ግቦች የደመቀው አለን ሺረር ነው።
በ2000ው የአውሮፓ ዋንጫ ላይ ኔዘርላንዳዊው ፓትሪክ ክላይቨርት በ4 ጎሎች ያሸነፈው ሲሆን
በ2004ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ያልተጠበቀቺው ግሪክ በአሰልቺው የመከላከል አጨዋወቷ ፖርቱጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን ስታነሳ በወቅቱ የክርስትያኖ ሮናልዶ ሜዳ ውስጥ ደም እምባ ማልቀስ አይረሴ ትዝታ ነበረ። ነገር ግን በወቅቱ ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ የነበረው የቀድሞው የሊቨርፑሉ አጥቂ ሚላን ባሮስ በ4 ግቦች ነበረ የተሸለመው።
በ2008ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ስፔን በኢኔስታ የመሳሰሉ ኮኮቦች ደምቃ ዋንጫውንም ስታነሳ አንቷን ግሪዝማን በ6 ግቦች ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ እንደነበር ይታወቃል።

የ2012ቱንም የአውሮፓ ዋንጫ በተከታታይ በመብላት ስፔን በታሪክ በተከታታይ በማንሳት ስትደምቅበት በወቅቱ 3 ተጫዋቾች ክርስትያኖ ሮናልዶ ፣ ፈርናንዶ ቶሬዝና ግሪዝማን በ4 ግቦች በጣምራ ሽልማቱን መውሰድ ችለዋል።

የ2016ቱን የአውሮፓ ዋንጫ ፖርቹጋል በክርስትያኖ እየተመራች የአውሮፓ ዋንጫን ስታነሳ ክርስትያኖ ኮኮብ ግብ አስቆጣሪም በመሆን በ2004 በግሪክ ዋንጫውን ሲነጠቁ ያነባው እንባው መታበሱ ይታወቃል።

የ2020ውን የአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ስታነሳ ከወርቃው የፈረንሳይ ትውልድ ውስጥ ኪሊያን ኢምባፔ በ5 ጎሎች የኮኮብ ጎል አስቆጣሪነቱን መውሰድ ችሏል።

የዘንድሮውንስ ማን ያነሳው ይሆን?? ኮኮብ ጎል አስቆጣሪስ ሆኖ ማን ይጨርስ ይሆን??? ጎበዝ ገማች ኮሜንት ላይ ያሳውቀን  🙏🙏

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

17 Jun, 14:06


ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ታፕ ታፕ በማድረግ ኮይኖችን የምትሰበስቡበት መተግበሪያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አግኝቶ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ በቅርቡ ለተጠራቀሙት ኮይኖች የዋጋ ተመን ይወጣለታል በመባሉ ብዙዎች በየቀኑ በሚሊዮኖች እያጠራቀሙበት ይገኛሉ።

በቅሩቡ Notcoin በዶላር የዋጋ ተመን ወቶለት የተጠራቀመው ወደ ክሪፕቶ ከረንሲ ተቀይሮ ዳጎስ ያሉ ገንዘቦችን ማስገኘት በመቻሉ ሀምስተር ኮምባትም የዋጋ ተመን ሳይወጣለት ብዙዎች በማጠራቀሙ መጠመዳቸው ታውቋል።

ስለ አጨዋወቱ ትንሽ መረጃ ለመስጠት ያህል መጀመሪያ ያልጀመራችሁ በዋናው በራሱ አድሬስ ገብታችሁ የምትጀምሩ ከሆነ ከ0 ስለሚያስጀምራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ ጆይን(start) ካደረጋችሁ 25k ኮይኖችን የምታገኙ ይሆናል
👇👇👇
👉ዝርዝር መረጃው
ከላይ በግራ በኩል Earn per tab የምትለዋ ታፕ ታፕ ስታደርጉ በየጣቱ የምታገኙት መጠን ነው። ነገር ግን ቀኑን ሙሉ ታፕ ታፕ እያደረጉ መዋል አይቻልም። ከታች በግራ በኩል 6000/6000 የሚለው አንደኛው ታፕ ታፕ ስታደርጉት እየቀነሰ መቶ 0/6000 ከመጣ ማቆም የምትችሉ ወይም ከፈለጋችሁ ፍጥነቱ ቀንሶባችሁ ታፕ ታፕ ማድረግ የምትችሉ ሲሆን ወታችሁ ከቆይታ በኋላ ስትመለሱ ግን እንደ ሌብላችሁ 6000/6000 ሙሉ ከሆነ በፍጥነት የሚሰራላችሁ ይሆናል።
ሲቀጥል ከታች Mine የሚለው ውስጥ በመግባት coins(ኮይኖችን) ባላችሁ ከላይ በቆጠረላችሁ ቁጥር እንደየቁጥራችሁ በመግዛት profit per hour የሚለው ቁጥር እንዲያድግላችሁ ማድረጋችሁ ጠቀሜታው እናንተ ታፕ ታፕ ባታደርጉም ከቆይታ በኋላ ተመልሳችሁ ስትገቡ እራሱ በየሰዓቱ ታፕ ታፕ አድርጎላችሁ ቁጥራችሁን የሚያሳድግላችሁ ይሆናል።
ከታች ሊንኩን በመጫን ተጠቀሙበት ነገ ላይ አይታወቅም የምትጠቀሙበት ይሆናል።


https://t.me/hamster_komBat_bot/start?startapp=kentId868068278
Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop!
💸  2k Coins as a first-time gift
🔥  25k Coins if you have Telegram Premium

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

17 Jun, 14:06


ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ታፕ ታፕ በማድረግ ኮይኖችን የምትሰበስቡበት መተግበሪያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አግኝቶ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ በቅርቡ ለተጠራቀሙት ኮይኖች የዋጋ ተመን ይወጣለታል በመባሉ ብዙዎች በየቀኑ በሚሊዮኖች እያጠራቀሙበት ይገኛሉ።

በቅሩቡ Notcoin በዶላር የዋጋ ተመን ወቶለት የተጠራቀመው ወደ ክሪፕቶ ከረንሲ ተቀይሮ ዳጎስ ያሉ ገንዘቦችን ማስገኘት በመቻሉ ሀምስተር ኮምባትም የዋጋ ተመን ሳይወጣለት ብዙዎች በማጠራቀሙ መጠመዳቸው ታውቋል።

ስለ አጨዋወቱ ትንሽ መረጃ ለመስጠት ያህል መጀመሪያ ያልጀመራችሁ በዋናው በራሱ አድሬስ ገብታችሁ የምትጀምሩ ከሆነ ከ0 ስለሚያስጀምራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ ጆይን(start) ካደረጋችሁ 25k ኮይኖችን የምታገኙ ይሆናል
👇👇👇
👉ዝርዝር መረጃው
ከላይ በግራ በኩል Earn per tab የምትለዋ ታፕ ታፕ ስታደርጉ በየጣቱ የምታገኙት መጠን ነው። ነገር ግን ቀኑን ሙሉ ታፕ ታፕ እያደረጉ መዋል አይቻልም። ከታች በግራ በኩል 6000/6000 የሚለው አንደኛው ታፕ ታፕ ስታደርጉት እየቀነሰ መቶ 0/6000 ከመጣ ማቆም የምትችሉ ወይም ከፈለጋችሁ ፍጥነቱ ቀንሶባችሁ ታፕ ታፕ ማድረግ የምትችሉ ሲሆን ወታችሁ ከቆይታ በኋላ ስትመለሱ ግን እንደ ሌብላችሁ 6000/6000 ሙሉ ከሆነ በፍጥነት የሚሰራላችሁ ይሆናል።
ሲቀጥል ከታች Mine የሚለው ውስጥ በመግባት coins(ኮይኖችን) ባላችሁ ከላይ በቆጠረላችሁ ቁጥር እንደየቁጥራችሁ በመግዛት profit per hour የሚለው ቁጥር እንዲያድግላችሁ ማድረጋችሁ ጠቀሜታው እናንተ ታፕ ታፕ ባታደርጉም ከቆይታ በኋላ ተመልሳችሁ ስትገቡ እራሱ በየሰዓቱ ታፕ ታፕ አድርጎላችሁ ቁጥራችሁን የሚያሳድግላችሁ ይሆናል።
ከታች ሊንኩን በመጫን ተጠቀሙበት ነገ ላይ አይታወቅም የምትጠቀሙበት ይሆናል።


https://t.me/hamster_komBat_bot/start?startapp=kentId868068278
Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop!
💸 2k Coins as a first-time gift
🔥 25k Coins if you have Telegram Premium

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

17 Jun, 13:03


ለጥንቃቄ 🚫🚫🚫🚫
በትግራይ ክልል ደቡብ ምስራቅ አከባቢ በቅርጫ ስጋ ምክንያት ከእንስሳ ወደ ሰዎች በተላለፈ እና ‹‹አባ ሰንጋ›› ሊሆን ይችላል በተባለ በሽታ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች አስተባባሪ የሆኑት አቶ መብርሃቶም ሀፍቱ ነግረውናል።

ስጋዉን በቅርጫ ወደ 30 የሚሆኑ አባወራዎች ተከፋፍለዉታል ያሉን ሲሆን በቁጥር ደረጃ ግን ከ5መቶ በላይ ሰዎች ስጋዉን መመገባቸዉን ጤና ቢሮዉ ማረጋገጡን ገልጸዋል፡፡

የእነዚህ 4 ሰዎች ህይወት ያለፈዉ በማህበረሰቡ ዉስጥ፣ ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ እና በአይደር ሆስፒታል መሆኑን ገልጸዉ ወደ አሁንም ማህበረሰቡ ዉስጥ ሌሎች ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ነዉ ያሉት፡፡

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

17 Jun, 13:02


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ከሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች መካከል 82ቱ ለቀጣይ አመት የትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዳይችሉ ማገዱን የከተማው ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ከ82ቱ ትምህርት ቤቶች መካከል የአፍ መፍቻ ቋንቋን ባለማስተማር እና በመሰል የፖሊሲ ጥሰት 40 የግል ት/ቤቶች እግድ እንደተጣለባቸው የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥር ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

ዝርዝር ምክንያቱን ለማጣራት እንደሞከርነው ከሆነ በካሪኩለሙ መሰረት አፍ መፍቻ ቋንቋ በሆነው በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ መፅሐፍቶችን ማስተማር ሲገባቸው ጭራሽ ከኬጂ ጀምሮ በራሳቸው ጀነራል ሳይንስ በማለት አዘጋጅተው እንደሚያስተምሩ አረጋግጠናል። ሲቀጥል ሌሎቹም ከስታንዳርድ ውጪ መገኘታቸውንም ተገልጿል ።
 
ብዙዎቹ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡
 
ቀሪዎቹ ደግሞ በራሳቸው ፈቃዳቸውን የመለሱ ናቸው ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፡፡

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

17 Jun, 12:06


የአልባንያ ቴሌቪዥን ዜና አንባቢ ሴት ጋዜጠኞቹን ያለ ጡ_ት ማስያዣ ዜና እንዲያቀርቡ መመሪያ አውጥቷል ።

ህዝቡ ፌስቡክ ላይ ተጥዶ የቴሌቪዥን ስርጭት መከታተል ማቆሙ ያሳሰበው ጣቢያ ፣ የተመልካቹ ቁጥር እንዲበዛ በሚል ነው ይህንን የወሰነው ።

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

16 Apr, 13:39


ትራምፕ በወሲብ ቅሌት ፍርድቤት ቀረቡ❗️

ትራምፕ የወሲብ ቅሌታቸው እንዲደበቅ ገንዘብ በመክፈል በቀረበባቸው ክስ ፍርድቤት ቀርበዋል። በበርካታ የወንጀል ክስ ፍርድቤት በመቅረብም በስልጣን ላይ ካሉ ወይንም ከቀድሞ ፕሬዝዳንቶች የመጀመሪያው ሆነዋል ሲል ኒዎርክ ታይምስ ዘግቧል።

ትራምፕ የዛሬው ክስ መዝገባቸው፤ በፈረንጆቹ 2016 ዓ.ም በነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር በሚያደርጉበት ወቅት ከዳንኤልስ ጋር ፈጽመውታል የተባለው ግንኙነት ከህዝብ እንዲደበቅ 130 ሺህ ዶላር መክፈላቸውንና ለማንም እንዳትናገር በማስፈራራት ያትታል።

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

08 Mar, 14:02


ሃሰተኛ መረጃ በቲክቶክ  በመልቀቅ እና ሃሰተኛ ቪዛ በማዘጋጀት በተለያዩ ሰዎች ላይ የማታለል ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመሰረተበት፡፡

ያለምንም ቅድመ ክፍያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚጓዙ ሰዎች ቪዛ እናስጨርሳለን የሚል ሃሰተኛ መረጃ በቲክቶክ  በማሰራጨት ከ25 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን ያታለለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል። ግለሰቡ ከ50 ሺ እስከ 600 ሺ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉንም ፖሊስ አረጋግጧል።

ግለሰቡ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ቆሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡  የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ጌታ ደረሰ እንደገለፁት ግለሰቡ ያለምንም ቅድመ ክፍያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ቪዛ እናስጨርሳለን በማለት በቲክቶክ ገፁ ያሰራጨውን መረጃ የተመለከቱ እና ወደ ካናዳ ለመጓዝ ፍላጎት አሳይተው ከተጠርጣሪው ጋር የተገናኙ ሰዎች አብዛኞቹ የወንጀሉ ሰለባ ሆነዋል፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ ያለምንም ቅድመ ክፍያ የቪዛ ፕሮሰስ እጨርሳለሁ ቢልም ጉዳይ እንዲያስፈፅምላቸው የተለያየ ቦታ እየቀያየረ በቀጠሮ ሲያገኛቸው ከነበሩ ባለጉዳዮች ቪዛ እንዳለቀላቸው እየነገረ እና ሌሎች ምክንያቶችን እየሰጠ ከእያንዳንዳቸው ከ50ሺ እስከ 600ሺ ብር የሚደርስ ገንዘብ ተቀብሏል፡፡

ተጠርጣሪው የማታለል ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ የታወቀው ቪዛ አልቆልሃል ተብሎ 600 ሺህ ብር የከፈለ  አንድ ግለሰብ ወደ ካናዳ ለመሄድ አየር መንገድ በተገኘበት ወቅት ቪዛው ሃሰተኛ መሆኑ ከተነገረው በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ነው፡፡

የግል ተበዳዮች መጠራጠር ሲጀምሩ ቤት ተከራይቶ የማታለል ወንጀሉን ሲፈፅም ከነበረበት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቆሬ አካባቢ በመሸሽ ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌላ ቤት ተከራይቶ ወንጀሉን መፈፀም እንደቀጠለ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል እንደተያዘ ረዳት ኢንስፔክተር ጌታ ደረሰ አስረድተዋል፡፡ 

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በህግ አግባብ ቤቱ ሲበረበር ሀሰተኛ ሰነዶች እና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ተገኝተዋል፡፡

ከ25 በላይ ግለሰቦች የወንጀሉ ሰለባ መሆናቸውን ያስታወሱት መርማሪው፤  በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የሚሰራጩ መረጃዎችን አምኖ ከመቀበል አስቀድሞ እነዚህን የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም እና ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን ተገንዝቦ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የመረጃዎችን ትክክለኛነት ሊያረጋግጥ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

29 Feb, 14:34


በተመሳሳይ ከፍታ ርቀት ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩት የኳታር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸዉ ተነግሯል።

ንብረትነቱ የኳታር አየር መንገድ የሆነዉ አዉሮፕላን ( ኳታር 6 ዩ) ከዶሃ ተነስቶ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ በ 38,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረ ቢሆንም በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አዉሮፕላኑ ወደ 40,000 ጫማ ወደ ላይ እንዲወጣ ተነግሮታል።

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6 : 32 ገደማ በተመሳሳይ በ39,000 ጫማ ከፍታ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ዱባይ ሲጓዝ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ( ኢቲ 602)
ጋር የተፋጠጠዉ የኳታር አዉሮፕላን ከመጋጨት ለጥቂት መትረፉ ተዘግቧል።

ሁለቱ ካፒቴኖች ስለ ክስተቱ ሲነጋገሩ የተቀረጹት ቅጂዎች ሁለቱም በሞቃዲሾ ከሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የተሳሳተ መመሪያ እንደተቀበሉ ያሳያል ተብሏል።

በሁለቱም አውሮፕላኖች ላይ የተገጠመው የግጭት ማስወገጃ ሲስተም (TCAS) ወዲያውኑ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፣ ይህም በታዘዘው ከፍታ ላይ ሌላ አውሮፕላን መኖሩን በማመልከቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት እንዲተርፍ ለማድረግ መቻሉ ዝግባዎች አመላክተዋል።

ይህን ተከትሎ በሞቃዲሾ የሚገኙት የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሆኑትን ሙባረክ ኑር አሊን በቁጥጥር ስር እንዲዉል አደርገዋል ሲል ካፒታል ነው የዘገበው።

👉👉ሼር ያድርጉ 🙏🙏 #ትኩረት #ሚዲያ #ሼር

ትኩረት ሚዲያ - Tikuret Media

29 Feb, 13:48


በሃላባ ዞን ህገወጥ የማርሻል አርት ስልጠና እየሰለጠኑ ነበር ያላቸውን በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደረገ
#ትኩረት #ሚዲያ #ሼር
በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በ2ኛ ጤፎ ቀበሌ በህገወጥ ማርሻል አርቲ ስልጠና እየሰለጠኑ የነበሩትን አካለት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገዋል።

የህገወጥ ማርሻል አርቲ ወርልድ ቴኳንዶ ስልጠና ያለፈቃድ ድንበር ተሻግረው ከህገዊ እውቅና ውጭ በቀበሌው በመንግስት ጤና ኬላ እና FTC ውስጥ ተደብቆ ሲያሰለጥን የነበሩ አሰልጣኝና ሰልጣኞችን ከወረዳው ፀጥታና ፖሊስ አካል ጋር በመሆን በህግ ቁጥጥር ስር ማድረግ ተችለዋል።

የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሁሴን ኢብራሂም በዚህ ወቅት እንደገለፁት በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና በቁሊቶ ከተማ መወቅሮች ህገወጦችን በመቆጣጠር ያለ ህጋዊ ፈቃድ ስሰሩ እና ስየሰሩ በተገኙ አካላት የለምንም ምህራት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስታውቀዋል።

ተግባሩ ቀጣይ ከህግ አካላት ጋር በማቀነጃት እስከ ውሰኔ እንዲያገኙ ተጠናክሮ እንደሚሰሩም የሀላባ ዞን ወጣቶችና ስፖርት የመምሪያው ሀላፊ አቶ ሁሴን ኢብራሂም በጥብቅ አሳስበዋል።