የዓለማችን የመጀመሪያው የግብረ ሰዶማዊ ኢማም ነው ተብሎ የሚታመነው ሙህሲን ሄንድሪክስ በደቡብ አፍሪካ ግቤርሃ ከተማ አቅራቢያ በጥይት ተመቶ መገደሉ ተነገረ ‼️
ትላንት ቅዳሜ ቀን ላይ ሙህሲን ሄንድሪክስ ከሌላ ሰው ጋር በመኪና እየተጓዙ ሳለ መኪናው ላይ ያልታወቀ ሰው ሰዎች የጥይት እሩምታ እንዳወረዱ ፖሊስ ተናግሯል።
ፖሊስ በሰጠው መግለጫ "ሁለት ፊታቸው ያልታወቁ ተጠርጣሪዎች ከተሽከርካሪው ወርደው በተሽከርካሪው ላይ ብዙ ጥይቶችን መተኮስ ጀመሩ" ብሏል። "ከዚያ በኋላ፣ ከቦታው ሸሹ። ከኋላ የተቀመጠው ሄንድሪክስ በጥይት ተመትቶ እንደተገደለ አውቀናል ።" ሲል ፖሊስ ተናግሯል።
ገዳዮችን ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ነውም ሲል ሲቲዝን የተባለ የሀገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA