የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT @yealemewuneta Channel on Telegram

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

@yealemewuneta


Welcome to

የዓለም እዉነታወችና
ድንቃ ድንቅ
#W/GALLERY ያገኛሉ 🌏

@brokenheartyy 👈 join

በቅርቡ ስለሚመጡት የUFOዎች 👽 እና
አለማችንን ሊያጠፏት የደረሱት አስትሮይዶች
ያልሰሙ ያላዩ ለማሜን
የምከብዱትን የዓለም 😱
እዉነታወችንና የተፈጠሩ
ድንቃ ድንቅ ያገኛሉ ።
#Peace_to_Ethiopia 🕊
@lijestifanos ✉️

ዋና ሕግ (Amharic)

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍 WORLD FACTnnለማንኛውም ሰው የምንጠፋውን ዋና ሕግ ትምህርት እንድናሠፍጽ ማግኘት ይችላሉ። በተለያዩ የUFOዎችና ሌሎች እባኮትም የአስትሮዎች እንዲሁም የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ እዉነታዎችን ይሰማሉ። እነሆ፤ ይግቡ።nnድንቃ ድንቅ #W/GALLERY ማንኛውም የተመረጠውን ዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ ሕግዎች ያወካሉ። የኢትዮጵያ ሕግን ገለጻ ጠበቁ።

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:04


ይቺ የምትመለከቷት ሴት ዝንብ ገድለሻል ብለው በእስርቤት 2 ቀን አቆይተው ፍርድ ቤት ደሞ 500 ዩሮ ቀጥቷታል !

በእኛ 68 ሺ ብር ማለት ነው.....

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:04


ዕለቱ አስገራሚ ታሪክ..

አሊያ አህመድ

በእንግሊዝ ምስራቅ ለንደን የምትኖር የ13 አመት ታዳጊ ሁለቱም ኩላሊቶቿ ስራ በማቆማቸው ምክንያት በሳምንት 3 ጊዜ የኩላሊት እጥበት ( dialysis ) እያደረገች አስቸጋሪ ህይወት የምትገፋ
የኢለመንተሪ ተማሪ ብትሆንም በህመሟ ምክንያት ግን ትምህርቷን በአግባቡ መከታተል የተሳናት ታዳጊ ናት።

ሬይ ኮይ ደግሞ የአሊያ አስተማሪ ነው።

የዓመቱ ትምህርት መጠናቀቂያ ወቅት ላይ የኢሊያ እናት ፋጢማ ወደ ትምህርት ቤቱ ስልክ ትደውላለች። ጥሪውን የተቀበለው የኢሊያ አስተማሪ ሬይ ነበር።

የአሊያ እናት ጭንቀት በተሞላበት ድምፅ ልጃቸው ህመሙ ስለጠናባት እና መቋቋም ስላልቻለች ትምህርት ቤት መምጣት እንደማትችል ለማሳወቅ ነበር ።

ሬይ፦ "ምነው አሊያ ሰላም አደለችም?"
እናት፦"ተደጋጋሚው የኩላሊት እጥበት ሰውነቷን አድክሟት ነው።" ሬይ እጅጉን ሀዘን ገባው በልጅነት አቅሟ ይህንን ፈተና መቀበሏ አንጀቱን በላው።
ሬይ፦ "ወ/ሮ ፋጢማ እኔ ልረዳት የምችለው ነገር ይኖራል?"
እናት፦"አመሰግናለሁ። የኩላሊት ተከላ በተጠባባቂ ላይ ያለች ስለሆነ ኢንሻአላህ ወደ ፊት እንደ እኩዮቿ ምትቦርቅበት ቀን ይመጣል።"

በሀዘን ልቡ እንደ ተሰበረ ንግግራቸውን አጠናቀቁ። ከስልክ ጥሪው ጀምሮ ብዙ ሲብሰለሰል የነበረው ሬይ መልሶ ስልኩን አነሳ፤ ለፋጢማ ደወለላት።

እናት፦ "ሃሎ"
ሬይ፦"እኔ አንደኛውን ኩላሊቴን ልሰጣት ፍቃደኛ ነኝ።"

እናት ፋጢማ በድንጋጤ ተዋጡ። የደስታ አይሉት የሀዘን እንባ ጉንጫቸውን አልፎ ይወርድ ጀመር። ለደቂቃዎች የሚሉት ግራ ገብቷቸው በዝምታ ቆዘሙ። ሬይ ደግሞ አወራ።

"ደም እና ሌሌች የምርመራ ውጤት ከአሊያ ጋር ተመሳሳይ ከሆነ በደስታ አንደኛውን ኩላሊት ልለግስ ፈቃደኛ ነኝ። ..

እናት ፋጢማ፦"እንደዚህ አይነት መልካም እና ቀና ሰው ይኖራል ብዬ አላሰብኩም።እንግሊዝ ውስጥ በቁጥር አነስተኛ ቤተሰቦች ነን። አብዛኛዎቹ ምስራቅ አፍሪካ ሶማሊያ ነው የሚኖሩት። ከቤተሰብ ተመሳሳይ ማግኘት አልቻልንም ነበር።" አለች በደስታ እና በመደነቅ።

በቀጣይ ቀናት ሬይ ወደ ሆስፒታል በማምራት ምርመራ አደረገ። እንደ ዕድል ሆኖ ሁሉም የምርመራ ውጤት ተመሳሳይ ሆኖ ተገኘ።

የኩላሊት ነቅሎ ተከላ ቀጠሮ ተያዘ። ለንደን በሚገኘው ታላቁ ኦርሞንድ ሆስፒታል የኩላሊት ልገሳው ቀዶ ጥገና ህክምና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ ..

" ህይወቴን ዳግም ያበራህልኝ ሁለተኛው አባቴ " ነበር፤ ያለችው አሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሬይን ስታገኘው።

መምህር ሬይ በበኩ፦ "የተማሪዬ የጤና ሁኔታ ተስተካክሎ ትምህርቷን በአግባቡ መከታተሏን ከማየት በላይ ምን ደስታ አለ። "

ሬይ ኮይ ባሳየው ወሰን ያለፈ መልካምነት የአመቱ ምርጥ አስተማሪ በመባል ፕራይድ ኦፍ ብሪትን አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:04


በጣም ብዙ የውሃ መጠንን ሊቆጥብ የሚችል በጃፓን እየተተገበረ ያለ የፈጠራ ስራ

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:04


የሚከተለው ታሪክ በህንድ አገር የተከሰተ አስገራሚ እና እውነተኛ ታሪክ ነው። በአለም ከተመዘገቡ አስገራሚ ክስተቶች አንዱ ነው።

ነገሩ ወዲህ ነው። የሁለት ሴቶች ታሪክ ነው፤ አንደኛዋ ከተማረ ሀብታም እና የከተማ ቤተሰብ የተወለደች፤ ሌለኛዋ ካልተማሩ ደሃ ቤተሰብ እና ገጠር የተወለደች። ከተማ የተወለደችው ሺቫ ስትባል ገጠር የተወለደችው ሱሜንትራ ትባላለች ።

ታሪኩ የሚጀምረው ሱሜትራ ወንድ ልጇን በወለደችበት ጊዜ ነው። ልጅ የመውለድ ህልሟ እንደተሳካ በከባድ ህመም መሰቃየት ጀመረች። የእጆቿ እና የእግሮቿ አጥንቶች በሙሉ መተጣጠፉ.... መቆረጣጠም ጀመረ፤ አጥቶቿ እስኪሰበሩ ድረስ። በመጨረሻም እንዲህ አለች።

"በሶስት ቀናት ውስጥ እሞታለሁ"

በተናገረች በሶስተኛው ቀን እንደተናገረችው ህመሟ አየለባት፤ ጭንቅላቷን ይዛ እየጮኸች ነብሷ አለፈ /ሞተች።/ እንደሞተችም አሟሟቷን ያዩ ሰዎች የሴይጣን ስራ እንደሚሆን ሲያወሩ ቆዩ።

በቀጣዩ ቀን ለቀብር ሲዘጋጁ የማይታመን ነገር ሆነ። ሱሜንትራ አይኗን ገልጣ ካስተኛት አይኗን ገለጠች። ህዝቡ በድንጋጤ ወደኋላ ገሸሽ አለ። ዶክተሮች ተመለከቷት ሱሜንትራ በህይወት አለች።

"እንኳን ደስ አላችሁ፤ በህይወት አለች"ብሎ ተናገረም።

የተፈጠረው ተዓምር ነው። ቤተሰቧ በሙሉ ባሏንም ጨምሮ በደስታ እንባ መራጨት ጀመሩ። ነገር ግን በነዚህ ሁሉ ደስተኞች መካከል አንድ ሰው የሚሆነው ነገር በቅጡ እየገባው አይደለም፦ እሷም እራሷ ሱሜንትራ ናት። አዎ ሁሉም ነገር እንግዳ ሆኖባታል። ሰዎችን አታውቃቸውም። ልጇን ባሏን ሁሉንም በፍፁም አታውቃቸውም።

"እኔ ሱሜንትራ አይደለሁም፤ የኔ ስም ሺቫ ነው። " ደጋግማ ትላለች።

"የገደለችኝ የወንድሜ ሚስት ናት"ትላለች።

***,
ቤተሰቦቿም የምትፈልገውን ነፃነት ሰጥተዋት ልጇን እነሱ መንካባከብ ጀመሩ። እሷም አንድ ክፍል ውስጥ በመግባት ደብዳቤ እየፃፈች ቤተሰቦቼ ወደምትላቸው ሰዎች "ከዚህ ገጠር እና ደሃ ቤተሰብ እንዲወስዷት፤ ወደ ቤቷ እንድትመለስ' ትልክ ጀመረች፤ እየሳለች ትልካለች፤ አየፃፈች ትልካለች።

የሚቀርብላትን አትመገብም ቤተሰቡን ትሸሻለች። ይኸ ነገር ለወራት ቀጠለ። ሆነም በወሩ መጨረሻ አንደ ቀን ወደቤታቸው ጎራ አለ።
**
ሰውዬው በእጁ ካርቶን ይዟል። ሱሙን 'ራም ትሪፖቲ' ይባላል ብሎ አስተዋወቀ። አስከትሎም "እዚህ ቤት ውስጥ ያልተለመደ ባህሪ የምታሳይ ሴት ልጅ ያለች እንደሆነ ጠየቀ። ሱሜትራ ሰውዬውን እንዳየችው "አባዬ" እያለች በሩጫ ሂዳ ተጠመጠመችበት። ለወራት ግራ ገብቷት በፀጥታ የነበረች ልጅ ሰውዬውን ስታይ ካሳየችው ደስታ እንና ፈንጥዚያ የማይገጣጠም ሆነ።

እንደተቀመጡ ራም የቤተሰቡን የፎቶ አልበም ከፈተ፤ እሷም አንድም ሳት ሳይለት ተናገረች። ሰማንታ በህይወቷ አይታ የማታውቃቸው ሰዎች ናቸው። አንድ ተለቅ ያለች ሴት ፎቶ ላይ ስትደርስ "ይህቺ ናት የገደለችኝ:ይህቺ ናት በጡብ አናቴን መትታ የገደለችኝ" ብላ መጮህ ጀመረች።

ራም ይኸን ሲመለከት የልጁን ነብስ በዚህች ልጅ ሰውነት ውስጥ አገኘው። ሁለቱም ተቃቅፈው ማልቀስ ጀመሩ።

"ሺቫ ልጄ ናት፤ሱሜትራ በሞተችበት ቀን የወንድሟ ሚስት በጡብ አንቷን መትታ ገድላ ራሷን ያጠፋች ለማስመሰል በባቡር መንገድ ላይ እንደጣለቻት ተናገረ። ሆኖም ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ደብዳቤዎች ወደ ቤቱ ይጎርፉ እንደጀመረ ጭምር...

በመጨረሻም ሺቫን ከተማ ወደቤቱ ወስዶ ከመላው ቤተሰቧ ጋር አገናኛት። ከዚያም በኋላ ተመልሳ ገጠር ከሱሜንትራ ቤተሰቦች ጋር እየኖረች ልጁንም አሳድጋ ለመጨረሻ ጊዜ በ1998 (እኤአ) አረፋለች።

ስለነገሩ ብዙ ሳይንትስቶች መልስ አላገኙለትም...ይኸ ታሪክ በ google ላይ ልታነቡ ትችላላችሁ።

ፎቶው የሱሜንትራ እና የራም ነው

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:04


ከ85% በላይ ሴቶች የግራና የቀኝ ጡቶቻቸው መጠን እኩል አይደለም። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ የአብዛኞቹ የግራ ጡታቸው ነው ከቀኙ በመጠን የሚተልቀው

ይሄ ትንሽ የመጠን መለያየት የበሽታ ምልክት አይደለም ሴቶች!

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:04


🔶ይህችን ጀግና እንስት ተዋወቋት Sabrina Gonzalez Pasterski ትባላለች። አሁን ላይ አዲሷ አንስታይን እየተባለች ትገኛለች።

🔸Sabrina ለሳይንስ ልዩ ፍቅር እንዳላት ትናገራለች ገና የ9 አመት ልጅ እያለች አውሮፕላን ማብረር እንደቻለች፤ በ10አመቷ ደግሞ በቺካጎ የአውሮፕላን ሞተር በቤቷ ውስጥ ሰርታ እንደነበር ቤተሰቦቿ ያስረዳሉ።

🔸Sabrina በኋላ ላይ በ12 አመቷ ሙሉ አውሮፕላን መስራቷም እንዲሁ አጀብ ያስባለላት ጉዳይ ነው። በኋላ ላይ በ14 አመቷ የሰራችውን አውሮፕላን ሙከራ በራራ እንዳረገችም የህይወት ታሪኳ ይመሰክራል።

🔹Sabrina አሁን ላይ የልጅነት ህልሟ ለሆነው Spacecraft ን ወይም መንኮራኩርን ለመስራትም ጥረት እያደረገች ትገኛለች። ከ Harvard University ሶስተኛ ዲግሪ ያላት ሲሆን በ Cambrige በሚገኘው MIT University ውስጥ ደግሞ በ ቲዎሮቲካል ሳይንስ ማዕከልም ዋና መርማሪ ናት። Quantum Gravity, Black hole, እና Space time ከምታጠናቸው ዋነኞቹ ናቸው።

🔹Sabrina የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት እንደሌላት ነገር ግን አንዳንድ ጥናቶችን በ PhysicsGirl.com ድህረገጽ ላይ ታጋራለች።ወደፊትም ብዙ የፊዚክስ ፈጣራዎችን ለአለም ታበረክታለች ተብሎላት በብዙዎች የምትጠበቅ ድንቅ እንስት ናት።

💬 እንግዲህ እኛም የአለም ህዝብን የሚጠቅም በጎ ፈጠራዎችን እንጂ ህዝብን የሚያጠፉ ነገር እንደማትፈበርክ(ልክ አንስታይን አቶሚክ ቦንብን ፈጥሮ እንደተፀፀተው) እንደማይሆን ተስፋ እናደርጋለን ይቅናት

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:03


በማሊ ወንድም ሆነ ሴቷም ሲሞቱ እና ሲገነዙ እጃቸው የሚቀመጠው ብልታቸው ላይ ነው።ይህን የሚያደርጉት በብልቴ የተነሳ ሳላውቅም ሆነ እያወኩ በድፍረት ለሰራሁት የዝሙት ሀጢያት ይቅር በለኝ ለማለት ነው።

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:03


✔️የሰው ልጅ ፕላስቲክ እቃዎችን እየተጠቀመ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ እ.ኤ.አ በ2050 በውቅያኖስ ውስጥ አሳዎችን እየዋጣቸው የአሳዎች ብዛት እየተመናመነ ሊያልቅ ይችላል።😔
በዚሁ አጋጣሚ ፕላስቲክ እቃዎችን የመጠቀም ባህላችንን እየቀነስን የውሀ ውስጥ ሀብቶቻችንን እንታደጋቸው ለማለት እንወዳለን👍

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:03


✔️በጠፈር ውስጥ ያሉት የኮከቦች ብዛት መሬት ላይ ካሉት የአሸዋ ቅንጣቶች ብዛት ይበልጣል።የኮከቦቹ ብዛት በቁጥር ከ10 የውሀ ጠብታዎች ሞሎኪዩሎች(Molecules) ጋር እኩል ነው።ይህም ማለት ወደ 15 Sextillion ድረስ ይደርሳል

ምንጭ :-Тяєєнυggєя

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:03


✔️ውሾች በአብዛኛው ጊዜ ደስተኛ በሚሆኑበት ወቅት ጭራቸውን ወደ ቀኝ ያስተኙታል።በተቃራኒው ወደ ግራ ካስተኙት ድንጋጤ እና ፍርሀት ውስጥ ናቸው ይለናል VCA Animals Hospital በዌብሳይቱ

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:02


✔️Tarantula ተብለው የሚጠሩት ሸረሪቶች ለሁለት አመት ያክል ያለ ምግብ መቆየት እንደሚችሉ ባዮሎጂስቶች አረጋግጠናል ብለዋል። አስቡት 2አመት ያለምግብ ሊሞላቸው ከጀርባቹ ባለው ከላይ ግርግዳው ላይ ብታገኙአቸው😁

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:02


ስለመሬት መንቀጥቀጥ ሲነሳ ትዝ ያለን የፈጠራ ውጤት ።
.....
ቻይናዊው Wang Wenxi ከጥቂት አመታት በፊት ዌንቹዋን እና ዩሹ በተባሉት የቻይና ግዛቶች ተከስቶ ጉዳት ያስከተለው የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት በቦታው ነበር ።

እና ይህ ክስተት ካለፈ በኋላ ፡ ለቀጣይ ይህ አይነት የተፈጥሮ አደጋ ቢከሰት የራሴንና የሌሎችን ህይወት እንዴት ማዳን እችላለሁ በሚል ነበር ወደዚህ ፈጠራ የገባው ።
....
እና የፈጠራ ሀሳቡ ተሳክቶለት ፡ የመሬት መንቀጥቀጥ የማይበግረው ( earthquake-proof bed ) ሰርቶ የፈጠራ ባለቤትነት ሆነ ።
.....
በመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ተነሳስቶ በ Wang Wenxi የተሰራው ይህ አልጋ ፡ በሰላም ጊዜ ሲታይ ፡ መደበኛ አልጋ ብቻ ይምሰል እንጂ በውስጡ የተወሳሰቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመድረሱ ጥቂት ሰከንዶች በፊት ማወቅ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች እና ሌሎች ነገሮች የተገጠሙበት ነው ።
....
እንደጥራቱና በውስጡ እንዳለው ምቾት ዋጋው የተለያየ ቢሆንም ፡ ከ4000 ዶላር ጀምሮ በሚሸጠው በዚህ አልጋ ላይ ተኝተው ፡ እንቅልፍ ላይ እያሉ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ፡ አልጋው በቅፅበት ውስጥ እኩል ይከፈልና የተኛውን ሰው በውስጡ በመደበቅ ፡ ከአልጋነት ወደ ግዙፍ ጠንካራ የብረት ሳጥንነት ይቀየራል ።
....
ከዚህ በኋላ ህንጻው ቢፈርስ ላዩ ላይ ፍርስራሽ ቢከመር ፡ ከውስጥ ያለው ሰው ያለስጋት መቆየት ይችላል ። ይህ ብቻ አይደለም ፡ በዚህ በግዙፍ የብረት ሳጥን ውስጥ ፡ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ቁሶች ፡ ምንም እንኳን fire proof ከሆነ ማቴሪያል የተሰራ ቢሆንም ፡ ድንገት በውስጥ እሳት ቢከሰት በሚል የእሳት ማጥፊያ ፡ በጭስ ምክንያት እንዳይታፈን ፡ የጋዝ ማስክ ፡ የታሸገ ውሀ ፡ ደረቅና የማይበላሹ ምግቦች ፡ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ጭምር በውስጡ ስላሉ ፡ ከመሬት መንቀጥቀጥ የተረፈው ሰው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አግኝተው እስኪያወጡት ሳይራብና ሳይጠማ ለቀናት መቆየት ይችላል ማለት ነው ።
....
እስከዛ ደግሞ ፡ በአልጋው ላይ የተገጠሙት የራዲዮ ሲግናሎች ፡ ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ምልክት እየሰጡ ፡ ሳጥኑ ያለበትን ቦታ ይጠቁማሉ ።
....
ክስተቶችን ፡ ወደ መፍትሄና አዘል፡ ፈጠራ ለሚለውጡ ባለ ብሩህ አእምሮ ሰወች 🙏

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:02


✔️በአለም ከፍተኛ የደን ስፍራን የያዙ ሀገራት በደረጃ:-

1ኛ ሩሲያ 🇷🇺..............814,848,460 ሄክታር

2ኛ ብራዚል 🇧🇷...........491,570,000 ሄክታር

3ኛ ካናዳ 🇨🇦..............346,975,800 ሄክታር
.
.
30ኛ ሱዳን 🇸🇩............18,861,120 ሄክታር
.
.
41ኛ ኢትዮጲያ 🇪🇹.......12,580,200 ሄክታር

Via WORLD🟢METER

🔴አስተውሉ:-ከላይ የቀረበው መረጃ በአንድ ሀገር ውስጥ ምን ያክል የደን ስፍራ በሄክታር እንዳለ እንጂ በFOREST/LAND Ratio አደለም።(ኢትዮጵያ ከነዚ ሀገሮች በቆዳ ስፋት እጅግ ታንሳለች)

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:02


✔️በጃፓን ሀገር ጥቁር ድመቶች መልካም እድል ወይም ጥሩ አጋጣሚ ምልክቶች ተደርገው ይቆጠራሉ።
እኛ ሀገርስ ጥቁር ድመት በመንገድ አቋረጠችኝ ብለን ቀናችን ተበላሸ እንላለን😁

የዓለም እዉነታና ድንቃ ድንቅ 🌍WORLD FACT

19 Oct, 09:01


✔️ከ800 አመታት በላይ እድሜ ያለው አሁንም ላይ በአገልግሎት ላይ ያለው የዴንማርክ ባንዲራ ነው።