Christian Mindset @christian_mind_set Channel on Telegram

Christian Mindset

@christian_mind_set


✞Destiny:-ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ግንባታ
☞ባለንበት የዘመን መጨረሻ እንጥፍጣፊ ሰዓት
በጥብቅ ከሚፈለገው ሀይል የመጀመሪያው የሆነው የወጣቱን ሀይል ካየበት ግብ የሚያሰናክሉትን ነገሮች በመለየት በመፍትሔው ላይ የተለያዩ መወያያ መድረኮች እና መንፈሳዊ ሰዎች በጉዳዩ ላይ የሠጡትን ምክር የምንዳስስበት እና የምንፈትሽበት መንፈሳዊ Channel ነው፡፡
😎ቤተሰብ + @cms_help_me

Christian Mindset (Amharic)

የክርስቲያናዊ አካባቢ እና መልካም ወገኖች ለምንጋሪ ነው፡፡ 'Christian Mindset' ተዘጋጀ የምንታመነኝበት መንፈሳዊ ቡድኑ ነው፡፡ ለምንመስለኝት ነው። የመንፈሳዊ ቤተሰብ ተመሳሳይ ዝርዝርን እና መረጃዎችን መዳብም የደረሱን መስራት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ይፋ ሕቅልና መረጃ የተገኘልን የመጀመሪያው ክርስቲያናዊ ፈላጊዎችን ትምህርት እና ማህበር ብቻ ለማህበረሰብ ያስችላሉ፡፡ ከዚህም በግንባታ በሚፈለገው ሀይል የመጀመሪያው ሀይል መከለከልን እና እንደምታስከፍሉት ሰዓትን እንጥል፡፡ 'Christian Mindset' እንዲህ ለሆነ እርምጃ ገለጹ፡፡

Christian Mindset

21 Nov, 18:19


ኔፍሊም እነማን ናቸው? በዚህ ቪዲዮ ቀርቧል
👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻

https://youtu.be/3B3jiPqp_OQ?si=Zp83pnqUqW18O2dR


〽️aranatha Digital Network
@Maranatha_MDN
@Maranatha_MDN2

Christian Mindset

20 Nov, 13:52


Christian Mindset pinned «🥵 #ጠኔ_ይያዛችሁ 🫠 🙂ሰው የሚጠጣው የጠማውን ያህል ነው። የሚበላውም የራበውን ያህል ነው። አንድ አንድ ሰው በጁ ውሀ ስለያዘ ብቻ በየደቂቃው ጎንጨት ይላል። ጉሮሮውን ለማራስ ያህል እንጂ እውነት ተጠምቶ አይደለም እርካታውም ቢሆን የዚያን ያህል ነው። ረሀብም እንደዛው ነው ስለቀረበ ብቻ የምንበላው እና ከቀናት ምግብ ፍለጋ በኃላ የምንበላው በመጠኑም ሆነ በርካታው ይለያያል። እኔ ሁለቱም አጋጥሞኝ ያውቃል…»

Christian Mindset

20 Nov, 13:50


🥵 #ጠኔ_ይያዛችሁ 🫠

🙂ሰው የሚጠጣው የጠማውን ያህል ነው። የሚበላውም የራበውን ያህል ነው። አንድ አንድ ሰው በጁ ውሀ ስለያዘ ብቻ በየደቂቃው ጎንጨት ይላል። ጉሮሮውን ለማራስ ያህል እንጂ እውነት ተጠምቶ አይደለም እርካታውም ቢሆን የዚያን ያህል ነው። ረሀብም እንደዛው ነው ስለቀረበ ብቻ የምንበላው እና ከቀናት ምግብ ፍለጋ በኃላ የምንበላው በመጠኑም ሆነ በርካታው ይለያያል። እኔ ሁለቱም አጋጥሞኝ ያውቃል የጠኔ ያህል እርቦኝ ያውቃል ምግብ መብላት ፈልጌ አጥቼ አውቃለሁ እሱ ሰዓት ታድያ እንዴት ከባድ መሰላችሁ ውሃ እንኳ ለተወሰነ ሰዓታት ካልሆነ አጥቼ አላውቅም።
ምን ልላችሁ ነው ታድያ ውፍረት እየቀነስኩ እና ግዴታ ሆኖብኝ የምበላው ምግብ እና በረሀብ ግዜ የምበላው አጎራረሱ እራሱ ይለያል ልክ እንደዛው መንፈሳዊ እረሀብም ይለያያል። መንፈስ ቅዱስን የምንፈልገው የራበንን ያህል ነው የምንፀልየው የፍለጋችንን ጥግ ነው። የናፈቀንን ሰው ለማየት ረጅም መንገድ የምንሄደው ቀጠሮው ሁሉ የማይደርስ የሚመስለን የናፍቆታችን ሙላት ስለሚበልጥ ነው። የሆነ አገር ተጉዘን ይሄ ነው የማይባል ተራራ እና ገደል አይተን ፎቶ አንስተን ተነስተን ሞኝ ይመስል ስቀን ወድቀን ተሰባብረን የምንመለሰው የአይናችንን ረሀብ ለመሙላት ነው። በተይ በበረሀ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እንዳወሩኝ ውሀ ጥማት እጅግ ከባድ ነገር ነው። ጌታ እየሱስም እኮ እንደዚህ አለ።

#ማንም_የተጠማ

የዮሐንስ ወንጌል 7
37፤ ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ እንዲህ ብሎ ጮኸ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።
አንድን ሰው ጠምቶሀል ብላችሁ በግድ ልታጠጡት እንደማትችሉ እንደዛው በርግጥ የተጠማን ሰው ደሞ ፍለጋውን ልታቋርጡበት አትችሉም። ሳይጠጣ አይረካምና።
በርግጥ እኔም ሆንኩ ከላይ የተጠቀሰው ቃል በስጋ ምድር ላይ ስለምናገኘው ውሀ አናወራም በርሱ ሊያምኑ ስላሉት ስለ መንፈስ ቅዱስ እንጂ።

ይሄን ፅሁፍ ከመፃፌ ከተወሱ ሰዓታት በፊት Daniel Tebebu የሚባል ጓደኛዬ ስለ እያሱ ቤተ መቅደስ ደጃፍ ላይ መቆየት በቪድዮ በጣም ጥሩ መልእክት ሲያስተላልፍ ነበር። እያሱም መንፈሳዊ ረሀብ በድንኳን ደጅ እንደሚያሳድረው አስቤ አላውቅም ነበር።

🤔መንፈሳዊ ረሀብ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ጌታም በተራራው ስብከት ላይ እንደተናገረው በመንፈስ ድሆች የሆኑ እነሱ መንግስተ ሰማያትን እንደሚወርሱ እንዲሁም ፅድቅን የሚራቡ እንደሚጠግቡ ይናገራል።

የማቴዎስ ወንጌል 5
3፤ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥
   መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
…………….
6፤ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥
   ይጠግባሉና።

😔ድህነት ሰውን ፍለጋ ውስጥ ይከተዋል ሰው ሁሌም የሚፈልገው የሌለውን ነውና።
በዚህ ፅሁፍ ላይ ማለት የምፈልገው አንድ ነገር ነው መፀሀፉ እንደሚነግረን
- እያሱ ከመቅደስ አይለይም ነበር
- ሳሙኤል በመቅደስ ውስጥ ያድር ነበር
- እግዚያብሔር ደሞ ለሚፈልጉት ይገኛል
- በመንፈስ ድሆች የሆኑቱ የተጠሙቱ ተሰብስበው እንደጠበቁት ሐዋርያቶች ይሞሉታል ይቀምሱታል

#ምን_ይሆን_የራበን ??

🤔ታድያ የዛሬ ጥያቄዬ ለኔም ለትውልዴም ይሄ ነው። ምን ይሆን በጣም የጠማን ? ምን ይሆን የጠኔ ያህል የራበን እርሱን የተራብነውን እናገኘዋለን። መፈለጋችን እና እረሀባችን ላመል ያህል ብቻ አለመሆኑን እርግጠኛ እንሁን እንጂ ከውስጥ የወጣ የምድረ በዳ አይነት ጥማት ይሁን እነጂ ከምንጩ ሊያጠጣን ዛሬም መንፈስ ቅዱስ ህያው ነው ረሀባችን ይጥና እንጂ ቤታችንን ሊያጠግብ ሙላታችን ሊሆን ቃሉ በደጃችን አለ። ብቻ ይራባችሁ።

#የማያረካ_ውሃ 

😏በጣም የሚገርመኝ ነገር ሁላችንም እንደምናውቀው በጣም የራበን ቀን የምንፈልገው ምግብ እንደኔ ከሆናችሁ ሞላ እና ጠቅለል ያለ በአፍ ሲበላ ጠንከር ያለ ምናምን ሊሆን ይችላል ግን በዚህ ዘመን እንደዛ አይደለም እዚህ ግባ የማትሉት የማይረቡ ምግቦች አሉን እንደ ፋንዲሻ ትሪውን ሞልተውት ምግብ መሰል መሸወጃዎች እንበላቸው ?? ብዙዎቻችን የራበንን ስለማናውቀው እነዛን መሰል ምግቦች እናግበሰብሰና ረሀባችን ከደቂቃዎች በኃላ ደሞ ይቀጥላል። መዝናኛው፣ ፊልሙ፣ የተደላደሉ ቀጠሮዎቻችን፣ አጠር ያሉ ስብከቶቻችን፣ የደህና እደር ያህል ፀሎታችን፣ የምንሰራቸው እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም መሰል ነገሮቻችን ተደማምረው ግዜያዊ ጥጋብ እየሰጡ ከትክክለለኛው ምንጭ እያራቁን ነው። እስኪ እዚህ ጋር ምንባባችሁን ገታ አድርጉት እና ስለራሳችሁ ትንሽ አስቡ
- የእውነት ምግብ ከበላችሁ ስንት ቀን ሆናችሁ ?
- የእውነት ምንጭ ስር ሄዳችሁ እንደ ሰማሪያዊትዋ ሴት ከቀዳችሁ ስንት ግዜ አስቆጠራችሁ ??
- መች ነበር ከድምፁ የጠገባችሁት መች ነበር ተሞልታችሁ እርፍ ያላችሁት።
እንደሚመስለኝ ሁላችንም እንደ ማርያም እና ዮሴፍ የፌስቲቫል ጋጋታ እየሱስን አስረስቶ አስጉዞን ሳይሆን አይቀርም  ወይም ደግሞ ፊታችን እየጠወለገ እንደ ኤማአኦስ መንገደኞች ጥቂት ምእራፍ ገሰገስን ??
እነዚህ የኔ ጥያቄዎች ናቸው መልሶቹ ደሞ ለናንተ።

#እኔ_ግን_ልንፀልይላቹ 
የርሀብ ጠኔ ልክ ስጋ የሚያከሳ መንፈስ የሚያወፍር ያግኛችሁ ብዬ
የሚያቅበዘብዝ ጥማት ከምንጩ የሚተክል ድንኳን የሚያስቀር ፍቅር መቅደስ የሚያሳድር ይያዛችሁ ብዬ
እናንተ አሜን በሉ።  🙏


⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_se

Christian Mindset

20 Nov, 13:47


አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። #ቅድሚያ #የእግዚአብሔርመንግሥት #አስቀድሞመፈለግ
Seek first the kingdom of God and all these things will be added to you. #Priorities #GodsKingdom #SeekFirst

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

19 Nov, 11:50


🥹 #ባንድ_ሌሊት_ዳንኩኝ ።🥰


🎵 🎶 በምን አይነት ፍቅር እንደነካኸኝ እኔንጃ ….)2x by Yidnekachew Teka

☺️እድገቴ ብዙ ነፃነት ስለነበረው የፈለኩትን የማድረግ የማሰብ ፣ የመሆንም መብት ነበረኝ ለምን የሄን አነበብክ ለምን እንደዚህ አደረክ የሚሉ ክሶች ብዙም አልነበሩብኝም፥ አባቴ በጣም እራሴን እንድፈልግ እና በመረጥኩት መንገድ እንድሄድ ረድቶኛል በጣም አመስግነዋለሁ። በተለይ ስለ Existence of God and thinking  logical lifestyle ያወራነውን መቼም አልረሳውም። የእናቴ ፀሎት ደግሞ መሬት ጠብ የማይል ነው። በዚህ አስቸጋሪ ዘመን ስለተሸከምሽኝ አመሰግናለሁ።

👉🏾 ብዙ የልጅነት ጥያቄዎች እና የማያጠግቡ መልሶች

🤔እግዚያብሔር የለም ወይም ቢኖር ኖሮ የሄ እና ያ ለምን ሆነ ?
ሰው መሆን ማለት ምንድን ነው ?
ሞት የመጨረሻችን ነው ?
እኔ እራሴ ሁሉን ለምን አላውቅም ?
ሃይማኖት ምን ድረስ ያስኬደናል ?
ሀይማኖት አምላክ ሰራሽ ነው ወይስ ሰው ሰራሽ ?
እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎች ከ13 አመቴ ጀምሮ እጠይቅ ነበር። እንደውም ከልጅነት ጏደኞቼ ጋር ወጣ ባለ መልኩ የማይረሱ አይነት ውይይቶችን እናደርግ ነበር። ለዚህም ደግሞ አንድ አንድ ግዜ ለማሸነፍ ሌላ ግዜ ለማወቅ ካለን ጉጉት የተነሳ የማናነባችው መፀሃፎች አልነበሩም።

👉🏾 ቀልድ የሚመስል ጉብኝት

🥺በፈረንጆቹ የጥቅምት ወር መጀመርያ ላይ ነበር ልክ የዛሬ 16 አመት ለመጀመርያ ግዜ ሙሉ ባዶ በሆነ ማንነት በአንድ በተባረከ አርብ ቀን በቤተስብ ውስጥ በሌለ ባልተለምደ ቤተእምነት (you go city church ) ውስጥ የተገኘሁት፥
ስባኪው( ፓስተር ሞ)  ስብከቱን ሲጀምር እንደዚህ አለ
“እግዚያብሄር አለ“ ቀጥታ ወደ እኔ ለእኔ በሚምስል መልኩ በልቤ ውስጥ ያለው ጥያቄ ሁሉ ተዳሰሰ  ስባኪውም ቀጠለ
“ ሰዎች በጣም ሰነፎች ነን አምላክን መፈለግ ሲያቅተን የለም እንላለን እሱ ግን አለ በተለያየ መንገድም እራሱን ሲያሳይ ኖርዋል ሰነፍ ግን በልቡ ሰነፍ ስለሆነ የለም ይላል እርሱ ግን ለሚፈልጉት ይገኛል” …….
እያለ በሰፊው አስተማረ ታድያ በዚህ መሃል ነበር ምን እንደነካኝ ሳላውቅ አንዳች የሆነ መረዳት በልቤ ውስጥ የገባው።  ለመጀመርያ ግዜ መፀሃፍ ቅዱስም ያነበብኩት በዚያን ቀን ነበር።

👉🏾 “ በምን አይነት ፍቅር እንደነካኸኝ እኔንጃ ..”

😭ያን ቀን በምን እና ምን እንደነካኝ ሳላውቅ ሰው እጁን ሳይጭንብኝ ፣ ማንም ይሄን በል ያንን ሳይለኝ  ፍቅሩ በልቤ መፍሰስ ጀመረ…….. ያላየሁት አምላክ እንደሚወደኝ እንድሚፈልገኝ ተሰማኝ……. አለቀስኩ ደግሜ አለቀስኩ ለሊቱን ሙሉ ግን ሊወጣልኝ አልቻለም ……. ድንገት በረደኝ ደሞ ሞቀኝ ደስታ እና ለቅሶ ተቀላቀሉብኝ …….. ደሞ መስቀል ታየኝ መኖር ፈለኩ……..ለምን እንደሆነ ሳላውቀው ደሞ ወዲያው ይቅርታ ጠየኩት….. የቆሸሽኩ ተሰማኝ ልጅነቴ ጥፋቶቼ ሁሉ ታዩኝ……..  ደሞ ውዲያው ይቅር ያለኝ መሰለኝ በውሃ ሳይሆን በደም አጠበኝ ……ብቻ ምኑ ቅጡ አንዳንዱን ስሜት የሚያውቅ ያውቀዋል …….. ባንድ ሌሊት ዳንኩኝ ።


👉🏾 ማን የለየኛል ???

🤗ይህው ድፍን 16 አመት ያ ስሜት ያ እንባ ያ ፍቅር አልበረደም ዛሬም  እግዚያብሄር ለኔ ሩቅ አይደለም በክርስቶስ ቅርቤ ሆኖልኛል። በመንፈሱ የእስትንፋሴ ያህል እሰማዋለሁ። “እናንተ ርቃችሁ የነበራችሁ … “ ኤፌሶን 2:13  እንድሚል ቃሉ በፊቱ፣ በቤቱ ዛሬም አለሁ። ፍቅሩ መልካምነቱ አባትነቱ እንክብካቤው እያደገ እንጂ ሲቅንስ አላየሁትም።  እርግጥ ነው ሮሜ 8፥39 “ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ:: “ ዛሬም በተለያየ ነገር ውስጥ እናልፋለን ከዚህ ፍቅር ግን ፀሃፊው  እንዳለው አንዳች ሊለየኝ(ን) እንዳይችል ተረድቼያለሁ።

🥰ብዙ መፃፍ ባስብም ብዙ ማለት ግን አልቻልኩም አንዳንዴ እኮ ቃላቶች እጅግ ትንሽ ናቸው። 

👉🏾 ይሄን ሁሉ ለምን አልከን ??

🤲አንድም ጌታ እየሱስን ስለወደደኝ ላመሰግነው
ሁለትም ምን አልባት በኔ አይነት የተሰላቸ ፍለጋ እና የስንፍና መንገድ ውስጥ ካላችሁ እግዚያብሔር ዛሬም እንደሚወዳችሁ ለማስታወስ እንዲሁም እርሱን በማወቅ እንድበረታ ያደረጉኝን ለማመስገን ነው።

😍ወንድማችሁ
አንተነህ ነኝ

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

19 Nov, 11:46


😍አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።| Do not keep talking so proudly or let your mouth speak such arrogance, for the Lord is a God who knows, and by him deeds are weighed.

📖 1 Samuel 2:3 (NIV) | 1ኛ ሳሙኤል 2:3
J
⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

16 Nov, 18:08


😒ሁሌ ከእራሴ ጋር የምሟገትበትን እውነት ልሞግታችሁ

🤔እስቲ ከራሳችሁ ህይወት አስተያዪት እድሜችሁ በጨመር ልክ የቱ እየበለጠባቹ የመጣ ይመስላችኋል ?

👆 ከላይ ያለው ምስል የሰው ልጅ በዘመናት መካከል ትኩረት ስለሚሰጣቸው በልብ እየነገሱ እና እየተቆጣጠሩት ያሉ ጉዳዮችን 1923 - 2024 ያለውን ጥናት በአሀዝ አቀረብኩላቹ ‼️ እናንተ ግን በቀን ውሏችሁ አስተያዪት

😎 መልካም ምሽት

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

15 Nov, 19:22


😊ከእኔ ተማሩ የቀጠለ ............


😐ከብዙ ቀናት ሙከራ እና ውትወታ በኋላ ከዚያም  በአክስቱ ልጅ በኩል እንዲያገኘኝ እናም ምን እንደተፈጠረ እንዲነግረኝ ስራ ቦታቸው አከባቢ የነበረው ካፌ ላይ እንድንገናኝ መልዕክት ላኩኝ የማይደርስ የለምና የቀጠሯችን ሰዓት ደረሰ እና ሄድኩኝ ትንሽ አርፍዶም ቢሆን ደረስ (ከዚህ በፊት በነበረን ግዜ አርፍዶ አያውቅም) ከዛም ከወትሮው ለየት ያለ ሰላምታ እጁን ዘርግቶ አቀረበልኝ ግራ ስለተጋባው ዝም ብዪ አየውት ቁጭ ብሎም እጄን ይዞ እየተርበተበተ አይኖቹ እንባ ቆጥረው ማውራት ጀመረ

ሰሉ አሁን በህይወቴ የማልቋቋመው ጭንቀት ውስጥ ነኝ ብዙ ጥያቄ እንድትጠይቂኝ አልፈልግም ግን ቤተሰቦቼ በእኔና በአንቺ ግንኙነት ደስተኛ አይደሉም አለኝ ምን አጠፍው ብዪ
ለምን ብዪ ጠየኩት ?

እርሱ፦ ቤተሰቦቼ ከእንናንተ ዘር(ጎሳ) ጋር መጋባት አይፈልጉም ንቀት አለባቸው አባቴ እና እናቴ ዘራችን አሰድበህ የዘመድ አዝማድ መሳለቂያ ታደርገን እና ልጅነትህ የዛን እለት ያበቃል ብለውኛል ብዙ ላስረዳቸው ሞከርኩ በጣም ለብዙ ቀናት ለመንኳቸው ግን ምንም ርህራሄ አልነበራቸውም ይባሱኑ  ዘመድ ሰብስበው ሁሉም ወይ እርሷን ወይ እኛን ምረጥ ብለው ነብሴን አስጨነቋት የልጅነት ፍቅሬን አንቺን እንድተው ነገሩኝ አለኝ

እኔም፦ በከባድ ግራ መጋባት ውስጥ ሆኜ እና ምን ወሰንክ አልኩት

😔መልሶም ብዙ ለማውራት አቅም የለኝም ግን በጣም እወድሻለሁ  ግን ካንቺ በላይ ለቤተሰቦቼ አስፈልጋለሁ ሳምንት ሙሉ ለብቻዪ አስቢያለሁ ተጋብተን ብንኖሮ የቤተሰቦቼ ሀዘን ብሎም መገለል  በህይወት አያቆየኝም ልጆችንም ባይተዋር ሆነው እንዲያድጉ አልፍም በሰቆቃ የተሞላ ኑሮ እንድንኖር አልፈልግም ስለዚህ አለሜ ያሳለፍናቸው እነዛ አመታት ሁሌም ልቤ ላይ  ይኖራሉ እወድሻለሁ አሁን አቅም የለኝም የምትይኝ ነገር ካለ በይኝ እና ልሂድ አለኝ
"ልብህ ወዳለህ ሂድ " አልኩት ከዛን ተነስቶ ሄደ  (የሚገርመው የዘላለም ቤተሰቦች ክርስቲያኖች አልፎም አገልጋዮች ናቸው😏)

😔 ለብዙ ወራት በህመም እና በለቅሶ በቤቴ ከረምኩ አያሌ ቀናት ተሰቃየው ወደዛ ወደጠላትውት ዝምታዪ ከአመታት በኋላ ተመለስኩ ብዙ ግዜ ምግብ አልበላም እነጫነጫለሁ ዝም ብዪ አለቅሳለሁ እራሴንም ለማጥፍት አስብ ነበር ህመሜን እና ጉዳቴን ካብራራው ቀናት አይበቁኝም ነገር ግን በዚህ ሁሉ አዝነው ልባቸው የወረደው ወላጆቼ ነበሩ አላለቀሱም እንጂ ደምተዋል  .....ብቻ ሆድ ይፍጀው ከዛም ሳሳጥረው ጌታ አበረታኝ እንደገና በረታሁ  የማያልፍ የመሰለኝ ያ ግዜ ብዙ ትውስታዎችን አሸክሞኝ አለፈ ብዙ ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር ቢኖረኝም በዚህ ልቋጭ  አሁን በህይወቴ ደስተኛ ነኝ ጌታ ትሁት በሆነ ባል ክሶኛል ደግሞም አንድ ቆንጅዪ ወንድ ልጅ ወልደናል ቁስሌን ከነ አካቴው እረሳ ዘንድ በልጅ ባርኮኛል ሁሉም  ለትምህርት ሆኗል....

እስቲ ልጠይቃቹ ?
ማን ነው መርጦ የተፈጠረ ? ማንስ ነው ተሽሎ የተወለደው?* ሁሉም አፈር አይደል?

😏 ከእኔ እንድትማሩ የምፈልገው የእግዘብሔርን ቃል እንደሚለው
“ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥30-31
እባካችሁ ሰዎችን በተወለዱበት ዘር ብሄር ጎሳ እየከፋፈላችሁ አትመልከቱ እንዲህ የሚያስብ ሰው ክርስቶስ አልበራለትም እኝደገና ወንጌል ሊመሰከርለት ይገባል አልዳነም ምክንያቱም ከክርስቶስ በላይ የጎሳ ትምክህት በልብ አለና

🤔ሌላው  በአስተሳሰብ ማነስ ምክንያት በወረዱ ሰዎች ህይወታችሁን አታስገምቱ ሁላችንም ስንሞት አፈር ነን + እንደ ክርስቲያን ኢየሱስ ከነገድ ከቋንቋ ከዘር ዋጀን እንጂ የጎሳ ተከራካሪ አላደረገንም ስለዚህ ለግንኙነታቹ ድንበር አበጁለት ለቤተሰቡ + ለባህል + ለጎደኛ .... ሁሉም በእናንተ ህይወት ገደብ ይኑራቸው ይህን ካረጋችሁ ጥሩ የሆነ ግንኙነት ይኖራችኋል የቀድሞ ህይወቴን ያፈረሰው ቤተሰብ ነውና

2, ለነገ ህይወታችሁ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ሁኑ🫡

3, የሚታይ ማታስነኩት  አቋም ይኑራችሁ (ከመጣው ጋር ሁሉ አትሂዱ😒 )

4, ጭንቀታችሁን ለጌታ ንገሩት 😔

ሁሉን ካወሩ ሆድ ባዶ ይቀራል ይባላል አይደል ስለዚህ ብዙ ምላችሁ ነገር ቢኖረኝም .... በዚሁ ልሰናበታችሁ በርቱልኝ 🙏

"ሁሉም ለትምህርታችን ሆነ"
እህታችሁ ነኝ❤️

‼️ለባለታሪካችን privacy ሲባል በስማቸው ላይ መጠነኛ ማሻሻያ አድርገናል



#ሼር

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

14 Nov, 12:31


Christian Mindset pinned «👩‍🦰ከእኔ ተማሩ..... 😐🙏 🙌ሰላም እንዴት ቆያቹ እኔ ደህና  ነኝ ብዙ ጊዜ በዚህ page ላይ የሚለቀቁ መልዕክቶች በጣም እከታተላለሁ ያፅናኑኛል በብዙ ተጠቅሜበታለሁ ዛሬ እኔን ያስለቀሰኝ እንዳያስለቅሳችሁ ከእኔ ብትማሩ ብዪ መጥቻለሁ 👩‍🦰 ስሜ ሰሎሜ ይባላል 29  አመቴ ነው የሀዋሳ ልጅ ነኝ ቤተሰቦቼም ሆኑ የሚያውቁኝ ሰዎች  ዝምተኛ እንደሆንኩ ይናገራሉ 😊 ይሄ ዝምታዪም ተከትሎኝ ወደ university…»

Christian Mindset

14 Nov, 12:29


👩‍🦰ከእኔ ተማሩ..... 😐🙏

🙌ሰላም እንዴት ቆያቹ እኔ ደህና  ነኝ ብዙ ጊዜ በዚህ page ላይ የሚለቀቁ መልዕክቶች በጣም እከታተላለሁ ያፅናኑኛል በብዙ ተጠቅሜበታለሁ ዛሬ እኔን ያስለቀሰኝ እንዳያስለቅሳችሁ ከእኔ ብትማሩ ብዪ መጥቻለሁ

👩‍🦰 ስሜ ሰሎሜ ይባላል 29  አመቴ ነው የሀዋሳ ልጅ ነኝ ቤተሰቦቼም ሆኑ የሚያውቁኝ ሰዎች  ዝምተኛ እንደሆንኩ ይናገራሉ 😊 ይሄ ዝምታዪም ተከትሎኝ ወደ university ሄዶ ነበር ብዙም ከ class ብሎም ከ dorm ልጆች ጋር አላወራም ነበር በጣም ዝምታ ይቀናኛል በነገራችን ላይ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ነበር ምማረው እናም ህይወትን በዝምታ እየገፋው በነበረ ወቅት 2ተኛ አመት ላይ ከእረፍት መልስ ከሀዋሳ ስመለሰ ግቢ ውስጥ የማውቀውን እንዲሁ በአይን የምንተያየውን   ልጅ መኪና ውስጥ አየውት (እውነት ለመናገር ዶርም ውስጥ ጎደኞቼ ብዙ ግዜ ስለእርሱ ሲያወሩ ስምቻለሁ ስለ ቁመናው ስለ ውበቱ በተለይ ስለ መንፈሳዊ ህይወቱ እና ተግባቦቱ አውርተው አይጠግብም ነበር ) 😊 እናም እርሱ ከተቀመጠበት አለፍ ብዪ ከበስተጀርባው ሄጄ ተቀመጥኩ ኤርፎኔንም አድርጌ መዝሙር እያደመጥኩ በዝምታ ረጅም መንገድ ተጓዝን ከዛም ለእረፍት ከመኪናው ስንወርድ ለሰላምታ እጁን ዘረጋ እርሱም፦ ሰላም ጎንደር አይደል ምትማሪው አለኝ
እኔም ፦ አዎን አልኩት
እርሱም ፦ ዘላለም እባላለሁ አለኝ ሰሎሜ እባላለሁ አልኩት

🤔ከዛም መኪና ውስጥ ገብተን ጉዟችንን ቀጠልን ጎንደር ገባን እስከ ግቢ የያዝኩትን ሻንጣ አግዞኝ ሀይስኩል ሀዋሳ ስለተማርንባቸው ትምህርት ቤቶች እያወራን ግቢ ደረስን እናም ስልክ ተለዋወጥን ሳሳጥረው በእዚህ መንገድ የእኔና የዘላለም ጎደኝነት ተጀመረ በጣም እየተግባባን መጣን ወደ ሀዋሳ ለእረፍት አንድ ላይ መመላለስ ጀመርን በግቢ ውስጥም ፌሎሽፕ ላይ አገልገሎት 😍አስጀመረኝ በህይወቴ የማልረሳውን የክርስቲያን ተማሪዎች አንድነት እንድካፈል ረዳኝ ስብእናው ማርኮኝ ነበር እንደተዋደድን ያሳብቅብን ነበር

🥰 አንድ ቀንም የፍቅር ጥያቄ አቀረበልኝ እኔም በደስታ ተቀበልኩት የፍቅር ህይወት ጀመርን እናም በግቢ በነበረን ቆይታ በጣም ተጠቅመን ነበር እናም በህይወቴ የማልረሳውን ጊዜ አሳለፍን ደግሞም ብዙ ስለወደፊት ህይወታችን እናወራ ነበር እንፀልያለን በትምህርታችን እንረዳለን ደግሞም ከተማ ውስጥ ያሉ ምግቦች አንዳቸው አይቀሩንም ነበር  በግቢ ውስጥ 3 አመት የፍቅር ህይወት አሳለፍን

😇 የግቢ ቆይታችንን አጠናቀን ወደ ሀዋሳ ከተመለስን በኋላ እኔ ባንክ ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ እርሱ ደግሞ የቤተሰቦቹን ንግድ ይሰራል ጥሩ ነበርን እንዋደድ ነበረ እንተሳሰብም ነበረ ሁሌ ከእናቱ ጋር እንደሚያስተዋውቀኝ ይነግረኝ ነበር ግን ጊዜው እስኪደርስ እንጠብቅ ነበር በድንገትም የአንድ ወዳጃችን ሰርግ ላይ እናቱን እና አባቱን እናም አክስቱን አስተዋወቀኝ በጣም ደስ የሚሉ ቤተሰቦች ነበሩ ከዛም ብዙ መቆየት ስለማይችል ተሰናብቻቸው ዞላ ሸኝቶኝ ወደ ቤት ሄድኩ ማታም በስልክ እያወራን አምሽተን የፀሎት ሰአታችን ሲደርስ እርሱ ፀልዮልን ተለያየን ነገር ግን በማግስቱ ስራ በዝቶብኝ ስለነበረ አልደወልኩለትም አመሻሽ ላይም ስልኩ ዝግ ነበር አላገኘውም 3 ቀን ሙሉ ሞላኝ text ሳደርግለትም አይመልስም  ስራ ቦታው ሄጄ ስጠይቅም የአክስቱ ልጅም  አልገባም አለችኝ ግን ሰላም እንደሆነ ነገረችኝ ግራ ገባኝ እንደ ቀልድ ሳምንት ሆነን በድንገትም ፀጉር ቤት ስሄድ መንገድ ላይ አየውት ዞላ ብዪ ስጠራውም እየሰማኝ አጠገብ የነበረ ባጃጅ ውስጥ ገብቶ ሄደ ..................

😍ይቀጥላል.......

#ሼር

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

12 Nov, 20:53


ጥያቄ
" እጮኛ ለመያዝ ምን ማድረግ አለብኝ? "

መልስ
ይህን ጥያቄ ስትጠይቀኝ ከነዚህ ሁለት አማራጮች አንዱ ላይ ልትሆን ትችላለህ።

1. እጮኝነት ለመጀመር ጊዜህ ደርሶ ትክክለኛ ሰው አተህ ምን ላድርግ በሚል አማራጭ ወይም
2. እጮኝነት ለመጀመር አማራጭ አግኝተህ ራስህን ዝግጁ የማድረጉ ምዕራፍ ላይ ልትሆን ትችላለህ።

••• አንድ ቁምነገረኛ ሰው በህይወቱ ሊወስናቸው ከሚችላቸው አንዱና ትልቁ ውሳኔ የፍቅር አጋር ምርጫ ነው። ታዲያ ይህን ውሳኔ ያዛቡ አንዳንዶች ሲጎዱ ጥቂቶች ደግሞ ደስተኛ ሆነው ሲቀጥሉ እናያለን።  አንተ ግን. . .

ትክክለኛውን ጊዜና ትክክለኛዋን ሴት ጠብቅ
••• ከላይ በፍቅር አጋር ምርጫ ወቅት የተሳሳተ ውሳኔ ወስነው የሚጎዱት ይህን አዛብተው ነው። ትክክለኛ ጊዜ ላይ ትክክለኛ ያልሆነች ሴት ብትመጣ ትርፉ ጉዳት ነው። ሌላው ደግሞ ትክክለኛዋ ሴት ትክክል ባልሆነ ጊዜ ብትመጣም ትርፉ ጉዳት ነው።
መጀመርያ ግን "የቱ ላይ ነኝ?" የሚለውን ለይ።

ትክክለኛ ጊዜ፡
••• አንድ ሰው እጮኝነት ለመጀመር ጊዜዬ ነው ለማለት ማየት ያለበት ብዙ ነገር አለ። ትክክለኛ ጊዜ ለመለየት መስፈርቶቹ ከሰው ሰው ሊለያይ ቢችሉም ግን የጋራ የሆኑ ነገሮችም አሉ። እነዚህን እኔ ብቁነት(መንፈሳዊ፣ስነልቦናዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብቁነት) በሚለው ጠቀልላቸዋለው።

መንፈሳዊ ብቁነት፡ እጮኝነት የስጋ ጉዳይ ብቻ አይደለም። የወደፊት የትዳር አጋርህ ምን እንድትሆን ትፈልጋለህ ብልህ "ጥሩ መንፈሳዊ ህይወት ያላት ብትሆን" ልትል እንደምትችል አልጠራጠርም። ስለዚህ አንተም በዛው ልክ ዝግጁ ሁንላት።
••• ሰይጣን በዚህ ዘመን የያዘው ትልቁ ትውልድን መጣያ መሳርያው እጮኝነት ላይ ያነጣጠረ ነውና ይህን ፈተና ለመቋቋም የሚረዳህን መንፈሳዊ ልምምድ(ፀሎት፣የቃል እውቀት፣ቅድስናን) ታጠቅ።

ስነልቦናዊ ብቁነት፡ እጮኝነት ውስጥ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አይደለም አለመግባባት ብሎም መለያየት ሊኖር ይችላል። መለያየት ደግሞ መጠኑ ከሰው ሰው ቢለያይም ስነልቦናዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል። ይህን የስነልቦና ቀውስ ታዲያ ብዙ ሳይጎዱበት የሚያሳልፉት አስቀድመው ራሳቸውን ያስታጠቁ ናቸውና  በእጮኝነት መሀል አለመግባባት ብሎም ለትዳር የማትሆን ከሆነች መለያየት እንዳለ አስቀድመህ ለራስህ ማወቁ መልካም ነው።
••• አስተውል ተጠራጣሪ ሁን እያልኩህ አይደለም።

ማህበራዊ ብቁነት፡ በዚህ ውስጥ ደግሞ ከሌላ ሰው ጋር ያለህ ተግባቦትህ፣ችግር አፈታትህና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ይጠቃለላሉ። ስለዚህ እነዚህ ጉዳዮች ላይ እንዴት ነኝ ብለህ ራስህን ጠይቅ ማስተካከል ያለብህ ነገር ካለም እርምጃ ውሰድ።

ኢኮኖሚያዊ ብቁነት፡ ይህን ለማብራራት እንዲረዳኝ ወደኋላ መለስ ብዬ በሰው ታሪክ ውስጥ ሰው እንዲህ በቴክኖሎጂ ከመከበቡ ምግብና ልብስ ቤት ድረስ Deliver ከመደረጉ በፊት የሰው ልጅ አዳኝ(hunter) ሆኖ የሚኖርበትን ጊዜን ላስታውሳችሁ። (በዛን ዘመንም ነበርክ እንዴ እንዳትሉኝ ደግሞ ገና ልጅ ነኝ እኔ😁)

••• በዛን ዘመን አንድ ወንድ አደን ላይ አሪፍ ከሆነና ለአደን በወጣ ቁጥር የሆነ ነገር በትከሻው ተሸክሞ ለቤተሰቡ የሚያመጣ ከሆነ ብዙ ሴቶች ይህን ወንድ ለባልነት ይፈልጉታል ምክንያቱም ወደፊት አግብተው ልጅ ቢወልዱ ልጆቻችንን መመገብ ይችላል ብለው ስለሚያስቡ። በተቃራኒው ደግሞ እንቅልፋምና አደንን ያልተለማመደን ወንድ እንኳን ለትዳር ሊያስቡት እንደ ወንድ ላይቆጥሩት ይችላሉ።
••• ብታምንም ባታምንም መለክያ መስፈርቱ ይለያይ እንጂ በዚህ ዘመንም እንዲህ አይነት አመራረጥ አለ። በዚህ ዘመንም አደን(hunting) አለ እንቅልፋም አዳኝ(hunter) ከሆንክ ለወደፊት ህይወታችን አይጠቅምም ትባልና ተፈላጊ ሳትሆን ትቀራለህ። የዚህ ዘመን አደን ደግሞ ቀለል ያለ ነው ሴትም አደን ላይ መሰማራት ስለጀመረች ከአንተ የሚጠበቀው ቢያንስ ግማሹን የአደን መንገድ መጓዝ ነው። በየት በኩል ነው ጫካውን አሳየኝና ማደን ልጀምር ካልክ ጫካው ውስጥ ነህና ተግተህ ስራ። ህይወት በጣም ከባድ ብትሆንም የወደፊት ልጆችህን እያሰብክ ኑሮህን እና ኢኮኖሚህን ለመለወጥ ትጋ።

••• ሌላው እጮኝነት ለመጀመር ኢኮኖሚያዊ ብቁነት አስፈላጊ የሚሆነው አንዳንድ ወጪ መኖሩ ስለማይቀር ነው። በትንሹ ለበአል ለልደት ምናምን ስጦታ ማሰብህ አይቀርም ታዲያ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኛ ተቀብሎ ከመግዛት በራስ ገንዘብ እንደመግዛት ያለ ነገር የለም። ይህን እንደምሳሌ አነሳው እንጂ ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎች መኖራቸው ግልፅ ነው ለዚህ ደግሞ አንተ በኢኮኖሚው ብቁ ብትሆን የተሻለ ነው የሚሆነው። ነገር ግን እንደ ግለሰቦቹ ይወሰናል ብዩ አስባለው ምክንያቱም በኢኮኖሚ እራሳቸውን ለመቻል በጋራ እየታገሉ ያሉ ወዳጆች ስላሉኝ (እናንተ አይመለከትም 😁)

ትክክለኛ ሰው
••• ይህ ከሰው ሰው ቢለያይም ግን እንደ ክርስቲያን ጌታን እንደግል አዳኝ አድርጋ የተቀበለች መሆኑዋ ትልቁ መስፈርት ነው። ሌላውን መስፈርት ለአንተ ብተወው መልካም ነው።

••• አንተ እጮኛ ለመያዝ ምን ላድርግ ያልከው ጊዜህ ደርሶ ከሆነ ትክክለኛዋን ሴት ጠብቅ። ነገር ግን ጊዜህ ሳይደርስ በዙርያህ ያሉ ሰዎች አዋክበውክ ወይም ጓደኞችህ ስለገቡበት ከሆነ ለመጀመር ያሰብከው ባትጀምር መልካም ነው።

••• ብዙ ጊዜ ልባችንን ለስብራት የምንዳርገው የእኛ ነው ብለን ያሰብነውን  ሰው ወደ ህይወታችን የሚመጣበትን ጊዜ ፈጠን አድርገን አልያም አዘግይተን ከማይሆን ሰው ጋር እጮኝነት በመጀመር ነውና አምላክ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛዋን ሰው ወደ ህይወትህ በማምጣት ይባርክህ።

                   ጨረስኩ! 😎

#ሼር

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

11 Nov, 18:27


🤔የካምፓስ ላይፍ ቴንሽን ወይንም
የኮሌጅ ውጥረት - የአን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትምህርት ላይ ስለሚያጋጥማቸው ውጥረት (ቴንሽን) እንዲህ ይላሉ፡

“የደም ስሮቼን በዕፅ ና በጫት ማጨናነቅን፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የፍትወተ-ሥጋ ባልንጀሮች ማስተናገድን ወይም እድሜዬ ወደ ሃምሳው ሲደርስ የነርቭ ቀውስ የሚያስከትሉብኝን ችግሮቼን አንደሌሉ ማስመሰልን ከመሳሰሉ ምርጫዎች ጋር በተፋጠጥኩበት በኔው ዓለም፣ ተስፋዎቼን ሁሉ በአንድ ከመንደር የዘለለ እውቅና በሌለው አናጢና አምላክ በሚባል እርባነ ቢስ ምስቅልቅል ላይ ማሳረፍ ትርጉም ይሰጣልን?”

የቀለሙ ጫና ደብዛዬን ሊያጠፋና ሊደፈጥጠኝ በተቃረበበት በዚህ ወቅት፣ በፊቴ የቆሙ ተራሮችን ከፊቴ ከማንከባለል ባሻገር እኔን የመፍጠር አቅም በሌለው ጣዖት ጉያ መሸጎጥ ትርጉም ይሰጣልን? ጨርሶ አላደርገውም! ማገልገልም ካለብኝ እኔ የማገለግለው አምላክ ከእንጨት የተቀረፀን ጥጃ ሳይሆን፣ የማይገደብ ኃይል ያለው፣ አምሳያ የማይገኝለት ውበት፣ ሉዓላዊ ሥልጣንና የማይነጥፍ ጸጋ ምንጭ የሆነውን ነው ከዚያ ባሻገር ግን ውድ ጊዜዬን በከንቱ ማባከን ነው፡፡

ምንም እንኳን ኢየሱስን ከሰባት ዓመቴ ጀምሮ የማውቀው ቢሆንም፣ ወኔ ቢስ፣ የማልረባና ባዶ የሓይማኖት ጀሌ መሆኔ እስካታከተኝ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እስከሆንኩበት ጊዜ ድረስ እምብዛም አልነበርኩም፡፡ እግዚአብሔር የሰዎች ትውፊት/ወግ ወይንም አስተሳሰብ ውጤት አሊያም እርባነቢስ የልማድ አምልኮ ውጤት አለመሆኑን ለመረዳት ይህንን ያህል ረጅም ጊዜ ወስዶብኛል፡፡ እርሱ ከእኛ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖረን ይሻል፡፡ (እውነተኛው አምላክ ከእኛ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖረው የሚፈልግ አምላክ ነው፡፡) ከትናት ዛሬም ከእርሱ ጋር የበለጠ እንድቆራኝ አድርጎኛልና ዛሬ፣ ስሙን እጅግ ከፍ አድርጌ አመሰግናለሁ ምክንያቱም በነዚህ ሁሉ ሻካራ ሁኔታዎቼ ውስጥ በድንቅ ሁኔታ እንደተሸከመኝ አይቻለሁ ፍቅሩንም አጣጥሜአለሁ ፡፡

በሁኔታችሁ በማያላግጥ፣ በማይስቅባችሁና ጀርባውን በማይሰጣችሁ ፊት ሁሉን ነገራችሁን ዝርግፍ ማድረግ ምንኛ የሚያጓጓ እፎይታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከእኔ ፍፅምናን አይጠብቅም፤ እርሱ ከእኔ የሚፈልገው ኀጢአቴን እንድናዘዝና እንድታዘዘው፣ ስለ እርሱም የእውነት ምስክር ሆኜ እንድኖር ብቻ ነው፡፡

በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት መመሥረት፣ ከሁሉ ልቆ እንዲወጣ ያደረገው ምኑ ነው? እፎይታው ድነት የአድርግ አታድርግ ዝርዝር ዶሴ ወይንም የማይቀረው የዘላለም ፍርድ ወይንም ኩነኔ ማስፈራሪያ አለመሆኑ ነው፡፡ በእኔም ላይ የተጫነ አሰቃቂ ሸክም አይደለም፡፡ ኢየሱስ ያለው፡

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”

ታዲያ ይህ ሁለንተናን የሚያድስ አይደለምን? ታዲያ ይህ ነፍስን የሚያስፈነድቅ አይደለምን?

ለደካሞች ምርኩዝ? እምብዛም ችግር የለበትም፣ ችግሮቹንም ያለ አንዳች እንከን ብቻውን ይወጣቸዋል የምትሉት አንድ ሰው ካለ አሳዩኝ፤ ሸክም ያላጎበጠው፣ የማያለቅስ፣ ጭንቀትና ውጥረት ያልከበበው አንድ ሰው ካለ እስኪ አምጡልኝ እንዲህ ዓይነት ሰው ካለ… ራሱን በገና አባት የማታለያ ቀልዶች ወይንም የፋሲካ ሰሞን ተረቶች የሚሸነግል ሰው ነው፡፡ የደካሞች ምርኩዝ? ኦ አዎን!

እርካታ የሞላበት ሕይወት በመጠጥ፣ በግሩም ውጤት፣ በመልካም ሥራ ወይንም በበጎ አድራጎት እንደማይገኝ አይቻለሁ፡፡ እኔ ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁም መጣሁ ብሎ (ኢየሱስ) ተስፋን ሲሰጥ ምን ማለቱ እንደሆነ የገባኝ ኀጢአቴን ስናዘዝ እና ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወቴ ጌታና አዳኝ አድርጌ ስቀበል ነው፡፡ አንድ ሰው ስለ አንድ ነገር ሕይወቱን ሊሰጥና ሌላውን ሰው ደስ ስለማሰኘት መጨነቅን ሊቆም የተገባ ነው፡፡ ሕመም እጅግ የምጠላው አላርጅኬ የመሆኑን ያህል፣ አንድ እምነት ሊሞትለት የሚገባ መሆኑን ራሱ ካላረጋገጠ በስተቀር እሞትለታለሁ ብዬ አልናገርም፡፡ እኔ፣ በዚህ በፕሪንስተን ኮሌጅ እንደሚገኙ እንደበርካቶች ሁሉ፣ ይህንን መሳዩን እምነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በጀመርኩት ኅብረት ውስጥ አግኝቼዋለሁ፡፡

ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ በቀኜ ነውና አልታወክም።
ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች
(መዝሙር 16፥8-9)


#ሼር

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

11 Nov, 11:11


Christian Mindset pinned «🤔ጥያቄ አሎት? 👋ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ ቤተሰብ + ለጥቂት ጊዚያት አቁመን የነበረውን ጥያቄ ተቀብሎ ለመመለስ መሞከር አሁን ስለጀመር ጥያቄቹን በዚህ ላኩልን @Yegorebet_meskot 👈👈👈👈👈 ⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️   •√ Christian Mindset •√    @christian_mind_set    @christian_mind_set»

Christian Mindset

11 Nov, 11:11


🤔ጥያቄ አሎት?

👋ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ ቤተሰብ + ለጥቂት ጊዚያት አቁመን የነበረውን ጥያቄ ተቀብሎ ለመመለስ መሞከር አሁን ስለጀመር ጥያቄቹን በዚህ ላኩልን @Yegorebet_meskot 👈👈👈👈👈

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

09 Nov, 20:30


በዩኒቨርሲቲ ሊገጥሙን ከሚችሉ የስሜት ቀውሶች ዕንዴት እናምልጥ?
ክፍል 4

በተቃረኒ ፆታ ስሜት ለወደቅነውስ?

ትላንትና ኣልፏል እና ልንቀይረው አንችልም። በትላንት እና በዛሬ መካከል ያለው ልዩነት ትላንት የእግዚአብሔር ብቻ ነው ሠው ትላንትናውን ማሸነፉ የሚችለው  ዛሬን  በመጠቀም ነው :: ያለፈው አልፏል ብሎ መቀበል መቻል እና ዛሬን መኖር ፀጋ ነው፡፡ በተቃራኒ ፆታ ስሜት ተሸንፈን የወደቅንም ማወቅ ያለብን  ነገር ወይኔ ባልወድቅ ኖሮ ብሎ ማሰብ እና ያለልክ መፀፀት ተገቢ አይደለም።  ባልወድቅስ ኖሮ ማለት ትላንትናዬን መልሱልኝ ብሎ  ዕንደማልቀስ ነው፡፡ ታዲያ ምን ተሻለ?

1. በእግዚአብሔር  ፊት  በየዕለቱ  በንሰሃ መመላለስ

እግዚያብሔር  በኃጢአት  ለወደቁት ሁሉ የንሰሃ በር አለው፡፡ ንሰሃ ማለት እግዚአብሔር ሓጢያት ያለውን ሀጢያት ነው ብዬ ተሰማምቻለው ማለት ነው። በተቃራኒ  ፆታ ስሜት በወደቅንበት አቅጣጫ ሁሉ ንሰሃ መግባት ያስፈልጋል። ሠይጣን አንድ በዚህ ወቅት ከሚሸውደን ነገር ውስጥ አንተ ንሰሃ መግባት አይሠለችህም? አሁንም ንሰሀ ገብተህ ተመልስህ እዛው ነህ ስለዚህ ለውጥ ለሌለው ነገር ለምን ንሠሀ ትገባለህ? ይለናል እግዚአብሔር ግን ዕንደማይሰለቸን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው:: 1000 ጊዜ ብንሣሣት አንድ ሺህ ጊዜ ንሠሀ መግባት ዕንዳይሰለቸን!!!!! እግዚአብሔር አዳም ሆይ ብሎ በስሙ ጠርቶ የፈለገው አዳም በተሸሽገ ቀን ነው፡ ፡ እግዚአብሔር  የሰውን ልጅ  490 ጊዜ ይቅር በሉ ካለ እኛንስ ምህረቱ ዕጅግ ታላቅ የሆነ አምላክ አይምረን? ስለዚህ ተግተን ያለ መታከት ንሰሃ መግባት አለብን ::


2 ወደ ተቃራኒ ፆታ ስሜት የሚገፋን ነገሮች ማስወገድ

አንዳዶቻችን ደካማ ስለሆንን አንዳዶቻችን በጋደኞቻችን ተገፈፍተን  ብቻ በአንድም በሌላ ምክንያት ዕዚህ ነገር ውስጥ ገብተናል። አሁን በንሰሀ ተመልሰን እየኖርን ወደነበርንበት ህይወት ዕንድን መለስ የሚያደርጉ ነገሮች ማስወገድ አለብን :: ለምሳሌ ፊልም በማየት ከሆነ ወደዚህ ነገር የምንገፋፋው ፊልም ማቆም አለብን በሌላ የጊዜ ማሳለፊያ መተካትም ይኖርብላናል :: መፀለይ መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ የስፖርት ዕንቅስቃሴ ማዘውተር ጓደኞቻችን ጋር መጫወት ብቻችንን በሆንን ሰዓት ደግሞ የምናሰላስለው የእግዘአብሔር ቃል መሆን አለበት። ራሣችንን በተቀደሠ ሃሳብ ማሸነፍ መለማመድ አለብን።


3. ለራሳችን ይቅርታ ማድረግ

ብዙ ጊዜ በዚህ አይነት ሀጢአት ተላልፈን የምንገኝ ንስሐ ስለ መግባት ዕንጂ ራሳችንን ይቅር  ስለማለት አልተማርንም :: የመጣንበት ጎዳና ላይ በጣም ብዙ ስህተት ዕንደሠራን እና ይህም ደግሞ በእኛ ጥፋት ዕንደሆነ ይሰማናል። ይህ የጥፋተኝነት ስሜት ነጋችንን ዕንዳናይ ያደርገናል። ስለዚህ በንስሀ ወደ ኢየሱስ ከመመለስ  በተጨማሪ  ራሳችንን ይቅር ማለት ኣለብን። ዕስከ መቼ ድረስ በትላንትና ጥፋት ዛሬያችንን አስረን ዕንኖራለን? ይቅርታ አላማድረግ ደግሞ እግዚአብሔር በእኛ ዕንዳይሠራ ያደርገዋል። በመሆኑም ራሳችንን ወቅሠን ይቅርታ ማደረግ ይኖርብናል

4. ፍላጎቱ በመጣ ጊዜ ማድረግ ያለብን ነገሮች
4.1 በመጀመሪያ ፍላጎቱ መኖሩን መልካም እና የጤነኝነት  ምልክት መሆኑን ተረድቶ መቀበል ያስፈልጋል። አስተውሉ ተሰማን ማለት ኃጢአት ነው ማለት አይደለም፡፡
4.2 ፍላጎቱ የመጣብን በአምሮዋችን እያሰብን ባለው ነገር፣ ብቻችን ስለሆንን ከጉዋደኛ  ጋር ያለስፈለገ ንኪኪ ወይም በሌላ ምክንያት ሊሆን ይችላል በዚህ ጊዜ ወድያው ቲቶ 2 ፥ 11 ማሰብ እና በውስጣችን ለራሳችን መንገር ተገቢ ነው::


ቲቶ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ድነት የሚገኝበት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና፤
¹² ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛት በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤

ይህ ፀጋ በእኔ በአንተ በአንቺ በሁላችንም ውስጥ አለ። ይህን የኃጢአት ፈተና ዕንዳልፍ የኃጢያት ምኞቴን ያሸንፍልኛል ብሎ መንገር ወዲያው በውስጣችን የተነሣውን የተቃራኒ ፆታ ስሜት ያሸንፍልናል ::

4.3 ስሜታችን ተሸነፈ ማለት አለቀ ማለት አይደለም ዕንደዛ ዕንዲሠማን ካደረገን ቦታ እና ሁኔታ ለመውጣት መወሰን አለብን። ለምሳሌ ብቻየን ስለሆንኩ ዕንደዛ የተሰማኝ ሀሳቤን ለመለወጥ ከሰው ጋር መቀለቀ አለብኝ። ስለዚህ ከሰው ጋር መሆን የኔ ውሣኔ ነው።


በመጨረሻም አስታውሱ ሴተኛ አዳሪ የነበረችው ትዕማርም የእምነት ደመና መካከል አንዱዋ  ናት። እግዚአብሔር ከምንም ከማንም አይነት ሁኔታ ያወጣል :: ለክብርም ያበቃል :: የያዝነው የ100 ሜትር ሩጫ አይደለም። ማራቶን ነው:: ገና በ8 እና 9 ኪ.ሜ ሩጫ ተስፋ አንቆርጥም። ለሽልማት እንሮጣለን ሽልማት ብናጣ እንኳን የጀመርነውን ሩጫ አጠናቀን ነው ምንሄደው። አሮን ሀጢያት ሠርቶ ህዝብ አስቶ ጣዖት በሠራ ጊዜ እግዚአብሔር በዚያው ተመሳሳይ ሰአት ለሙሴ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ሚያናግረኝ ካህን አሮንን ምረጥልኝ የሚለብሰውን ልብስ በጥበበኞች እኔ በሠጠውት ልኬት መሠረት ይሠራለት እያለው ነበር። የተቆረጠ ዛፍ ዕንያሚለመልም እኛም የወደቅን በዘፍኑ ፊት ተስፋ አለን። የምህረት አምላክ ሁሌም በደጅ ነው፡፡


በዚህ መዝሙር አበቃው👇👇👇👇👇
©teho
#ሼር

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

09 Nov, 20:25


🤯በዩኒቨርሲቲ ሊገጥሙን ከሚችሉ የስሜት ቀውሶች ዕንዴት እናምልጥ?
ክፍል 3

ማንኛውም ስሜት እግዚአብሔር በአላማ ነው ያስቀመጠው :: የተቃራኒ ፆታ ስሜትንም ዕንደዚሁ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ሲያስቀምጠው አላማ አለው። ይህ ስሜት ግን አላማውን ሲስት ኃጢአት ዕንድናደርግ ይገፋፋናል ፣ ተያያዥ ችግሮችን ያመጣብናል። መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚናግረን ለእያንዳንዱ ፈተና እግዚአብሔር መውጫን አዘጋጅቷል ታዲያ ከተቃራኒ ፆታ ስሜት ውስጥ ያለ አግባብ ወድቀን እንዳንገኝ ምን እናድርግ? የዚህን ጥያቄ መልስ በሁለት መልኩ ዕንየው አንድ ወደ እንደዚህ አይነት የውድቀት መስመር ያልገቡ እና ሁለት ገብተው መውጣት ለሚፈልጉ በሚል። ለዛሬ የመጀመሪያውን እንይ :: በተቃሪኒ ፆታ ስሜት ተታለው ያልሳቱ  በመጀመሪያ ሁል ጊዜ የሚጠብቃቸውን እግዚአብሔርን ማመስገን ተገቢ ነው፡፡
“ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥12 አይደለ መፅሀፍ ቅዱስ የሚለው ስለዚህ ራስን በንፅህና መጠበቅ መቻል ከእግዚአብሔር የተሰጠ የምህረት እና የቸርነት ፀጋ ነውና ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ስለዚህ ማመስገን የሚገባ ነገር ነው። በመቀጠል እነዚህ ቀጣይ ነገሮች ማደረግ ለዩኒቨርሲቲ ያለንን ቆይታ መልካም እና ያማረ ያደርገዋል።

1. ወደ እግዚአብሔር በዚህ ጉዳይ አዘውትሮ መፀለይ

ስሜት ለማሸነፍ ዋና የክርስቲያን መፍትሔ ወደ እግዚአብሔር መፀለይ ነው:: ፀሎት ማለት በምድራዊ ሁኔታችን ላይ ሰማያዊ እርዳታ እና ጣልቃ ገብነት ዕንድናገኝ ህይወታችንን ለጌታ አሳልፈን ምንሠጥበት ቦታ ነው። አንድ ነገር ማረጋግጥላቹ የማንፀልይ ከሆነ በዚህ ስሜት ብቻ ሳይሆን በህይወታችን ሁሉ ተሸናፊ ክርስቲያን ነን። ስለዚህ የሚስማን ስሜት እግዚአብሔር ወስዶ በእርሱ ፍቅር እና እርሱን በማገልገል ዕንዲተካው መፀለይ ኣለብን።

2. ስሜቱ ሲፈታተነን እና መመኝታችን ሲያይል በውስጣችን ያለዉን ስሜት በህሊናችን (በውስጣችንን) ወደ ክርስቶስ ግፉት።

ይህ ማለት የሰው ልጅ ነን በተጨማሪ ወጣቶች ነን እና በተለያየ መንገድ ስሜታችን ሊነሣሣ ይችላል። በዚህ ጊዜ ታዲያ ስሜቱን በግላችን ከመፍላም ይልቅ ስሜቱን አምነን ወደ ክርስቶስ  መግፋት ያስፈልጋል፡፡ ዕንዴት ?

ለምሣሌ የአንዲት ዕህት በለበሰችው አለባበስ ስሜታችን ለወሲብ ተነሣሣ :: በዚህ ጊዜ ወዲያውንኑ በውስጣችን ይህ ፀሎት መፀለይ ።

' 'እግዚአብሔር ሆይ በአሁን ሰዓት እዚህ ቦታ የፆታ ስሜቴ እየፈተነኝ ነው፡ ፡ እኔ ግን አንተን ማክበር እና ማስደስት እፈልጋለው :: በመሆኑም ይህን ስሜቴን እኔ ደካማ በመሆኔ መቆጣጠር አልችልም። አንተ ግን ትችላለህ እና አሁን ተቆጣጠረኝ፡፡

ይህ ፀሎት በውስጣችን ባለው ስሜት ላይ ኢየሱስ እንዲነግስ ዕንዲቆጣጠረን ያደርጋል። እግዚአብሔር ደግሞ በግልፅ ስናወራው ደስ ይለዋል፡፡ ይህ ፀሎት ከመጀመሪያው ሚለየው በህሊናችን በተፈተንን ጊዜ ወዲያው ነው የምናደርገው ነው:: ወዲያው በልብ ይጸለያል ወይ ለሚል ሰው የነህምያን ታሪክ ማሰታወስ በቂ ነው፡፡(ነህምያ2፡4-6) ይህን ፀሎት በተፈተንን ጊዜ መለማመድ ነጻ ያወጣናል። ደግሞ መፅሀፍ ቅዱስ ኃጢያተኝነትን እና የአለማዊ ምኞችን የሚያስንቅ የእግዚአብሔር  ፀጋ እንዳለን ይናገራል፡፡(ቲቶ 2) ስለዚህ በተፈተንን ሰአት ይህንን ፀጋ ስራውን ዕንዲሠራ መጣራት እና ይህንን የእግዚአብሔር ቃል ማሰላሰል ድል በስሜታችን ላይ ይሰጠናል።

3. የተቃራኒ ፆታ መሻትን የሚያነሣሡ ነገሮችን አስወግዱ

በዚህ ዘመን ፊልሞች ፣ መፅሄቶች ፣ ማስታወቂያዎች ፣ ዌብሣይቶች ሁሉ ስሜትን የሚቀሠቅሱ ናቸው። አለምን ሞልተዋል እና ከእነዚህ ነገሮች ወጪ ለመኖር ከባድ ነው:: ግን ህይወታችን ውስጥ ዘልቀው ዕንዲገቡ ማድረግ የለብንም። ሠይጣን አንድ ክርስቲያኖችን ከሚሸውድበት መንገድ አንዱ ዕንዲ አይነት ነገሮች ለአይናችን ለጆሮዎችን በቀረቡ ጊዜ ልናስወግዳቸው ብንል አንተ እኮ የጌታ ልጅ ነህ ፀጋው ይረዳሃል አንዴ እኮ ብታይ ብታደምጥ ከዛ በኋላ ትተወዋለህ በማለት ነው:: መፅሀፍ ቅዱስ ግን ስለ ስጋ ማሰብ ሞት ነው:: ማሰብ ሞት ነው ማለት ዕንዳስብክ ትምታለህ ሣይሆን ማሠብህ አድጎ ማየት ይሆናል ፤ ማየትህ መንካት፤ መንካትም ኃጢአት ፤ ኃጢአትም ከእግዚአብሔር መለየት ያም ሞት ይሆንብሀል ማለት ነው። ስለዚህ ስናይ ወደ ሞት መስመር ሰይጣን  እየመራን መሆኑን አውቀን ስሜታችንን ለእግዚአብሔር ማስገዛት አለብን። በተቻለ መጠን ዕንደዚህ አይነት ምስሎች እና ፊልሞችን አለመመልከት ግን እውነቱን ስንነጋገር ወጣት ነን በ እኔ ሁሉን እችላለው መንፈስ የምንመላለስ ስለሆንን ማየት ማቆም ባንችል እንኩዋን እነዚህን የወሲብ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ የፈልሞች part ላይ ስንደርስ ማሣለፍ ያስፈልጋል።

4. ከጋደኞቻችሁ ተፅህኖ ራቁ

በዚህ ዘመን የወሲብ ወሬ የማያወራ ፣ ድንግል የሆነ እና ብዙ ጊዜ በፍቅር ስም ሠውን ያልሸወደ እንደፋራ የሚታይበት ጊዜ ደርሰናል ::  ከአለማዊው ቤት ይልቅ ደግሞ በጌታ ቤት ሆነን የምንበድል እኛ ደግሞ በዝተናል። ዕንደውም በዩኒቨርሲቲ ቆይታው አንድ ጓደኛዬ የነገረኝ ነገር "አሁን ላይ ፉክክሩ ማን ብዙ ሴት / ወንድ አወጣ" ሆኑዋል ነበር ያለኝ። "እሧማ ልምድ አላት " እኮ መባል የማዕረግ ንግግር በሆነበት ወቅት ላይም ተገኝተናል። ይህ ሁሉ የሚመጣው አንዱ መንስኤ የጋደኛ ተፅህኖ ነው፡፡ ይህንን ማሸነፍ እና ልዩ ሆነን መውጣት ይኖርብናል፡፡ እነሡ አደሩ እና ልምድ😂😂😂 ኖራቸው ማለት እግዚአብሔር ተደስቶበታል ማለት አይደለም። እነሡ የወሲብ ወሬ አውሩ ማለት እኛ ከቡድንኑ ላለመገለል ስንል ወሬው ላይ መሣተፍ አለብን ማለት አይደለም። የራሣችን አቁዋም ከመፅሀፍ ቅዱስ ወስዳን ልንከተለው የሚገባን ሊኖረን ይገባል ::

“ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።”
  — መዝሙር 1፥1

ይቀጥላል

©teho
⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

09 Nov, 15:58


🤯በዩኒቨርሲቲ ሊገጥሙን ከሚችሉ የስሜት ቀውሶች ዕንዴት እናምልጥ?
ክፍል 2

1ኛ ነገሥት 19 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “በመጣህበት መንገድ ተመልሰህ ወደ ደማስቆ ምድረ በዳ ሂድ፤ እዚያ ስትደርስም አዛሄልን በሶርያ ላይ እንዲነግሥ ቅባው።
¹⁶ እንዲሁም የናሜሲን ልጅ ኢዩን በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ቅባው፤ ደግሞም ነቢይ ሆኖ በእግርህ እንዲተካ የአቤል ምሖላን ሰው የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ቅባው።
¹⁷ ከአዛሄል ሰይፍ ያመለጠውን ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ ሰይፍ ያመለጠውን ደግሞ ኤልሳዕ ይገድለዋል።
¹⁸ እኔም ጒልበታቸው ለበኣል ያልተንበረከከውንና አፋቸው ምስሉን ያልሳመውን ሰባት ሺህ ሰዎች በእስራኤል አስቀራለሁ።”

እግዚአብሔር ለኤልያስ ድብርት የሠጠው መፍትሔ

🙏1. ፀሎት

በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ኤልያስን በአንተ መገኘት አልፋለው እና ጠብቀኝ ሲለው እናያልን :: ታዲያ ኤልያስ እግዚአብሔርን በ 4 መንገድ ውስጥ ሲፈልገው እናም ሲያጣው በመጨረሻም እግዚአብሔርን ሲያገኘው እናያለን። ለእኛም ይህ ተምሣሌት ከገባንበት ቀውስ እስክንወጣ ድረስ እግዚአብሔርን በፀሎት መጠበቅ አለብን የሚለውን ይነግረናል። በእንደዚህ አይነት ቀውስ ወይም ህመም ውስጥ ያለ ሠው ለእግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ ዕውነተኛ ስሜቱን ለእግዚአብሔር ማቅረብ አለበት። ለዚህ ነው እግዚአብሔር ምንም እንኳን የኤሊያስን ሁኔታ እያውቀ ይህን ያለው፡

ከዚያም፣ “ኤልያስ ሆይ፤ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ።”
  — 1ኛ ነገሥት 19፥13 (አዲሱ መ.ት)

ስለዚህ በፀሎታችን ወቅት በግልፅነት ስሜታችንን ለእግዚአብሔር ማሳየት አለብን፡፡


👬2. ጓደኞችን ሠጠው

የድብርት አንድ መገለጫ የብቸኝነት ስሜት ነው። እግዚአብሔር ለኤሊያስ አብሮ የሚሆን አልሣዕን እና 7000 ለበአል ያልሰገዱ ሠዎችን ሠጠው፡፡ በዚህም ኤሊያስ ብቻውን አለመሆኑን ዕንዲያውቅ እና ዕንዲረዳ አደረገው። በድብርት ወቅት ወደ እግዚአብሔር  በፀሎት ስንቀርብ እግዚአብሔር ወደ እኛ ወይም እኛን ወደነሱ በመላክ ወደ ቀናው መንፈስ ዕንዲሚመሩ፣ ዕንዲያፀኑን እና ዕንዲያፅናኑን የሚያደርጉ ሰዎች ይወጠናል።በመሆኑም በፀሎት በእግዚአብሄር  ፊት ከማሣለፉ በተጨማሪ ወደ ሠላማዊ ስሜት ሊያቀርቡን የሚችሉ  ጉዋደኞቻችን ጋር በመሆን ስሜታችን ማጋራት አለማውራት ብንፈልግ እንኳን በዝምታ ውስጥ ሆነን አብረን የምናሣልፍቸው ጉዋደኞች ጋር መሆን ያስፈልገናል።

3🙂‍↔️ ለድብርቱ ምክንያት እግዚአብሔር መፍትሄ ሠጠው

ለኤሊያስ ዋነኛ የድብርት መንስኤ ኤልዛቤል ነበረች። እግዚአብሔር  እዪን  ቀባው እና ለእስራኤል ሆነ ለአንተ ችግር መፍትሔ ይሆናል አለው። በዚህ ዘመንም እግዚአብሔር በቃሉ፣ በመፅህፍት (መንፈሳዊም / አለማዊም) ፣ በተለያዩ የሚዲያ  መሳሪያዎች ፣ በተለያዩ  ሠዎች ..... ሌላም ሌላም  ለድ ብርቶቻችን መፍትሔ የሚሆኑ እዮዎች አሉት።

በመጨረሻው ድብርት ባጠቃን ጊዜ ዕንደ ክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር መሮጥ እና በቃሉ ውስጥ መፍትሔን መፈለግ አመለካከታችንን  እና ስሜታችንን ለማነፅ ይረዳናል።


2.👩‍❤️‍👨 የተቃራኒ ፆታ ስሜት

በወጣትነት በዕጅጉ ከሚፈትኑ ስሜቶች መካከል ዋነኛው ይሄ ነው:: የተቃራኒ ፆታ ስሜት ማለት በማንኛውም ሰው ላይ ያለ ከተቃራኒ ፆታ ጋር በማንኛውም መልኩ በወሲባዊ ሁኔታ መነካካት  ወይም  መገናኘት የመፈለግ  ስሜት ማለት ነው:: በእርግጥ ይህ ስሜት እግዚአብሔራዊ ነው። የስሜት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር የተፈጠረ በሙሉ መልካም ስለሆነ ይህ ስሜት መልካም የጤነኛነት ስሜት ነው:: ሠይጣን ግን ከፍጥረቱ ጀምሮ እግዚአብሔር መልካም ነው ያለዉን በሙሉ መጥፎ ዕንዲሆን ሲያደርግ ስለቆየ ይህንን ስሜት በመጥፎ ወስደነዋል።

ያዕቆብ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው።
¹⁵ ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ከዚህ የእግዚአብሔር ቃል ዕንደምናየው መመኘት (የስሜት ታላቅ ወንድም ) ዕንኳን በሀጢያትነት ሲፈረጅ አንመለከትም። የተቃራኒ ፆታ ስሜት መኖሩ በራሱ ኃጢአት ዕንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል :: ምክንያቱም የለበስነው ሥጋ ሁልጊዜ ይመኛል :: ሠይጣን ብዙ ወጣቶችን የሚያሠቃየን ሰሜቱ ስለ ተሰማን ኃጢያተኛ አድርገን ራሣችንን ዕንድቆጥር ያደርገናል። መፅሀፍ ቅዱስ ግን ይህንን አያስተምረንም። ስሜቱን ጎሽሙ ዕንጂ በኋጠያተኝነት መንፈስ ተመላለሱ አይለንም። ስለዚህ በሠፍው ከማየታችን በፉት ስለዚህ ስሜት ልናውቀው የሚገባው ነገር

1. ይህ ስሜት እግዚአብሔራዊ መሆኑን
2. ስሜቱ ተሰማን ማለት በራሱ የጤነኝነት ምልክት መሆኑን
3. ስለ ተሰማን ብቻ ኃጢአተኞች አይደለንም።

ይቀጥላል
© teho

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

08 Nov, 17:15


🤯በዩኒቨርሲቲ ሊገጥሙን ከሚችሉ የስሜት ቀውሶች ዕንዴት እናምልጥ?

ሰውን እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሲፈጥረው ብዙ አላማ ነበረው። ከእነዚህ አላማዎች መካከል ዋነኛው እግዚአብሔርን ዕንዲመስል ነው:: መፅሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በተለያዩ መልኩ የራሱ የሆነ ባህሪያት እና ስሜት ዕንዳለው ይነግረናል ::

እግዚአብሔር አብ  በብሉይ ኪዳን ሆነ በአዲስ ኪዳን ተቆጣ ፣ አዘነ፣ ተፀፀተ ፣ ደስ ተሰኘ ... ወዘተ እያለ ይነግረናል

“እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ ልቡም እጅግ አዘነ።”
  — ዘፍጥረት 6፥6  

በሌላ በኩል እግዚአብሔር ወልድ ስሜት ዕንዳለው ኢየሱስ በአላዘር ሞት ላይ ያፈሰሰው ዕንባ ዕውነተኛ ማስረጃ ነው።“ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።”
  — ዮሐንስ 11፥35 

እግዚአብሔር መንፈስ ስሜት ዕንዳለው በአዲስ ኪዳን ቅዱስን መንፈስ አታሳዝኑ

“ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።”
  — ኤፌሶን 4፥30   

በማለት መንፈስ ቅዱስ ስሜት ዕንዳለው መረዳት ይቻላል። ሰውም እግዚአብሔርን ለመምሰል ከመፈጠሩ አኳያ የገዛ ስሜት በውስጡ የያዙ ፍጡር ነው፡፡ የሰው ልጅ ስሜት በተለያዩ ሰዎች በተለያዩ  መንገድ ትርጒሙ ተሰጥቶታል።

ስሜት ማለት እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በነፍሱ ዙሪያ እየተከሠተ ያለዉን ዕንቅስቃሴ ዕንዲረዳ የሠጠው መጠቆሚያ ምልክት ነው:: ይህ ማለት ስሜት ምልክት መስጪያ ዕንጂ ዋናው ነገር ነው ማለት አይደለም፡፡ በዚህ ዙሪያ ትንሽ ማብራሪያ ልስጥ።

አንድ ሠው በጠና ይታመማል ::  ወደ ጤና ጣቢያ በሄደ ጊዜ የተለያዩ አይነት ምርመራ ይደረግለታል :: ደሙ  ቢወሰድ እና ደሙ የበሽታ ምልክት ቢያሳይ ይህ ሠው ደሙ ምልክት ሰጠ ዕንጂ በሽታው ደም ነው ማለት አይደለም። ስሜትም ዕንደዚሁ ነው አንድ ሰው ራሱን ማጥፋት ሲፈልግ ይህ ሠው በመፅሀፍ ቅዱስ ዕውነተኛ  ዕይታ ራሱን ማጥፋት መፈለጉ  ሣይሆን ችግሩ ነፍሱ የሆነችው፤ የተሰበረችበት ወይም ያዘነችበት ነገር አለ ማለት ነው።

መኪና የነዳጅ መጠቆሚያ (Fuel-gage) አለው። የዚህ መሳሪያ አገልግሎት በመኪና ውስጥ ያለውን የነዳጅ መጠን መጠቆም ነው፡፡ ለምሣሌ አንድ ሠው በጠዋት ተነስቶ መኪናው ነዳጅ ዕንዳለው ለማወቅ  መጠቆሚያውን ይመለከታል። ታዲያ ያለው የነዳጅ መጠን አንሶ ካገኘው መጠቆሚያውን ሣይሆን የነዳጅ መጠኑን ነው የሚያስተካክለው ። የዚህ የነዳጅ መጠቆሚያ ስራ ልክ ዕንደ ስሜት ነው:: ስሜትም በነፍሣችን ዙሪያ ምን ዕየተካሄደ ዕንዳለ ዕንድንረዳ እግዚአብሔር የሠጠን መጠቆሚያ ነው። አስተውሉ!! ስሜት ጠቁዋሚ ዕንጂ ዋነኛው ነገር አይደለም።

ወጣት ስንሆን በአብዛኛው የሚያስቸግረን ነገር ስሜታችንን መለየት፣ ማወቅ እና መግራት ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችን የተለያዩ የስሜት መፈራረቆች  በተለያዩ ምክንያቶች ይከሠቱ ብናል። ከልክ ያለፉ ጭንቀቶች ፣ ድብርት፣ የወሲብ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ  ዋነኞቹ ናቸው።


1. ድብርት☹️

ድብርት ማለት ቢይንስ ለ2 ሳምንት የቆዬ አስተሳሰብንና ባህሪን የሚያዛባ፤ የሰዎችን የእለት ተለት እንቅስቃሴንና ምርታማነትን የሚያውክ የአእምሮ ህመም ነው፡፡ በሌላ አባባል ድብርት ማለት ለራሣችን ለህይወታች ያለንን አመለካከት መቀነስ እና ከመጠን በላይ የደስታ መቀነስ የሚስተዋልበት ህይወት መኖር ማለት ነው:: ብዙ ጊዜ ድብርት ውስጥ መግባታችን ከዘገየ በኋላ ነው የምንረዳው። በመፅሀፍ ቅዱስ ድብርት ውስጥ ገብተው ከነበሩ ሰዎች መካከል ዳዊት፣ ኤልያስ እና እዮብ ዋነኞቹ ናቸው። ይህ ሚያሳየን ታላላቅ የተባሉ የእግዚአብሔር ሠዎች እንኳን በዚህ ስሜት ተጠቂ ናቸው:: ስለዚህ ድብርት ሲሰማን በእኛ ላይ ሲበረታ እኛን ብቻ ሚያጠቃ አድርጎ ማሰብ ኣስፈላጊ አይደለም :: በደብርት ወቅት የሚከሰቱ ዋነኛ ምልክቶችን እና የእግዚአብሔር መፍትሔዎችን ከኤልያስ ህይወት እንመልከት።


ኤልያስ በእግዚአብሔር እርዳታ ታላላቅ ተአምራትን ያደረገ 400 የበአል ነብያትን ያረደ ታላቅ የእግዚአብሔር ሠው ነው፡፡ ይህ ሰው ግን በአንዲት ሴት ዛቻ ግን ወደ ድብርት ህይወቱ ተቀየረ።

1ኛ ነገሥት 19 (አዲሱ መ.ት)
³ ኤልያስም ፈርቶ ስለ ነበር፣ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ሸሸ። በይሁዳ ምድር ወዳለችው ወደ ቤርሳቤህ እንደ መጣም አገልጋዩን በዚያ ተወው፤
⁴ በምድረ በዳም ውስጥ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዘ፤ ወደ አንድ ክትክታ ዛፍ እንደ መጣም፣ ከሥሩ ተቀምጦ፣ ይሞት ዘንድ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅቶኛል፤ እኔ ከቀደሙት አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰዳት” ብሎ ጸለየ።
⁵ ከዚያም ከዛፍ ሥር ተጋደመ፤ እንቅልፍም ወሰደው። በድንገትም አንድ መልአክ ነካ አደረገውና፣ “ተነሥና ብላ” አለው።
⁶ ዘወር ብሎ ሲመለከትም፣ እነሆ፣ በፍም የተጋገረ እንጎቻና አንድ ገንቦ ውሃ ከራስጌው አገኘ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ ተኛ።
⁷ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና መጥቶ ነካ አደረገውና፣ “ሩቅ መንገድ ስለምትሄድ ተነሥና ብላ” አለው።
⁸ ስለዚህም ተነሥቶ በላ፤ ጠጣም፤ በምግቡም ብርታት አግኝቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ እስኪደርስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተጓዘ፤

¹⁰ እርሱም፣ “እኔ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ እስራኤላውያን ኪዳንህን ትተዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና። የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አሁንም እኔን ለመግደል ይፈልጋሉ” አለ።

¹³ ኤልያስም ይህን ሲሰማ፣ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፍኖ ወጣና በዋሻው ደጃፍ ቆመ። ከዚያም፣ “ኤልያስ ሆይ፤ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ።
¹⁴ እርሱም፣ “እኔ ሁሉን ለሚችል ጌታ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ እስራኤላውያን ኪዳንህን ትተዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና። የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አሁንም እኔን ለመግደል ይፈልጋሉ” አለ።

የድብርት ምልክቶች

1.🤢 የምግብ ፍላጎት መቀነስ
ኤልያስ ምግብ መብላት ዕንኳን ዕንዳለበት ምግብ የማይመገቡ የእግዚአብሔር መልአክቶች ናቸው ኣስታውሰው የመገቡት

🫤2. ከሠው ሁሉ ተለይቶ ብቻ መሆን መፈልግ
ኤልያስ በደረሠበት ድብርት የሆነው ነገር ከሰው ሁሉ ተለይቶ ብቸኛ መሆን ፈለገ። ለዚህም በእግሩ አንድ ሙሉቀን ተጓዘ :: የተጉዋዘው ግን ወይ ምድረ በዳ ነው:: ውሃ ምግብ ሠው ወደሌለበት :: ድብርት በሠው ላይ የሚያመጣው ዋነኛ ተፅህኖ አንድ ሠውን ብቸኛ ማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ ሁለተኛ ማስረጃ የሚሆንን የኤልያስ ብቻዬን ቀረው የሚለው ፀሎት ነው፡፡

3. 🫣የምናየው እና የምንሠማው ሁሉ ይዛባብናል

ኤልያስ ሰማይን 3 አመት ተኩል በፀሎቱ ዘግቶ ያስከፈተ ሠው ዛሬ ግን በሠማው ዛቻ በአካባቢው ያለው መረጃ የትላንት የእግዚአብሔር የተአምራት ዕጅ ሁሉ በተዛባ መልኩ ዕንዲረዳ ሆነ። ድባቴ ወይም ድብርት በገጠመን ጊዜ ስለራሣችን ስለ ሁኔታችን የምናየው የምንሠማው ሁሉ ይዛባብናል

4. 🕯ሞት መመኘት ራስን ለማጥፋት መሞከር

ኤልያስ የፀለየው እግዚአብሔር ሆይ ሁኔታውን ቀይር ሣይሆን መሞት ለእኔ የተሻለ ነው ብሎ ውሰደኝ አለ። ኤልያስ ሞትን ይመኝ ዘንድ ያደረገው ከወር በላይ በቆየበት የድብርት ስሜት ነው::

ይቀጥላል
©teho


⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

07 Nov, 09:15


🤷‍♀የመጀመርያ አመት ተማሪዎች እና የፍቅር ግንኙነት

🤔 እንዲህ አምናለሁ "ነፃነት እና ውሀ አንድ ናቸው እያሳሳቁ የመውሰድ ክህሎት አላቸው።"
ከቤተሰቦቻቹ ጋር በነበራችሁ ቆይታ ቁጥጥር የበዛባችሁ እና የት ገባክ/ሽ የት ወጣክ/ሽ እየተባላችሁ አድጋችሁ ከሆነ እመኑኝ ወደ ጊቢ ገብታችሁ የሚያጋጥማችሁ ደስታ ሊያሳብዳችሁ ሁላ ይችላል። እንዴት ማለት ጥሩ...
"ጓኛዬ ከቤተሰቦችሽ ጋር እያለሽ ስልክሽ በጠራ ቁጥር ደንብረሽ ወደ ጓዳ ሮጠሽ ገብተሽ ትመልሺ ነበር ብንል እመኚኝ ጊቢ ስትገቢ ቤት የለመድሽው ተግባርሽ ሆኖ ወደ ውጪ ሮጠሽ ካልወጣሽ በስተቀር እንደዛ አይነት ቁጥጥር የለም።"
፠ በዚህ ነፃነትሽ ሰክረሽ በሚመራሽ አቅጣጫ ፈሰስሽ ማለት..."ተበላሽ!" እመኚኝ የቴሌ operator የሆንሽ ያክል የጊቢው ጎረምሳ ሁሉ "ሀሎ ውዴ..." እያለሽ መፈናፈኛ ያሳጣሻል።ደሞዝ አልባ operator ሆነሽ ቀረሽ ማለት ነው።
፠ "መልክ ሳይኖረኝ የምን operator አመጣክብኝ!" ካልሽ እሱን ገብተሽ "አሀሀሀሀ ለካ ልክ ነበር።" ብለሽ ከስህተትሽ ከመማርሽ በፊት ላሳውቅሽ። እየነገርኩሽ ጎረምሶቹ ዶርማቸው ቁጭ ብለው "ስልኬን ታነሳዋለች አታነሳውም" ቁማር ሊጫወቱብሽ ሁላ ይችላሉ።
"አንትስ ስልኬ ፓኬጅ ጨረሰ እያልክ እየተሳቀክ ኢንተርኔት ተጠቅመክ ይሆናል ጊቢ ስትገባ የመጀመርያው ናላክን የሚያዞረው የ wifi (ኢንተርኔት) ነፃነት ነው።"
፠ አሰብከው ያ የሌሊት የቀን ፓኬጅ እያስባለክ ብርክን ሲሞጨሙጭ የነበረው ኢንተርኔት እንደ ነፋስ በጊቢክ በነፃ ሲነፍስ..."ዶርም የራሱ ጉዳይ!!" ሊያስብልክ ሁላ ይችላል። እመነኝ ከዚህ የነፃነት ነፋስ ጋር ነፈስክ ማለት ከ4 ወር በኋላ ነፋሱ ሻንጣክን አስጠቅልሎ ከቤተሰቦችክ በር ጋር ነው የሚያላትምክ። አዎዎዎ ከጊቢ ሊያስጭርክ ሁላ ይችላል።(ለሰይጣንክ ነው ይህን የምመኘው።)
ርእሴን ረስቼ አይደለም ዝምብዬ የምዘላብደው... ከፍቅር ግንኙነት ጋር በተያያዘ በሁለት ከፍዬ ዛሬ እተነፍስባችኋለሁ።
፠ እጮኝነት ላልጀመሩ ወዳጆቼ!!
፠ እጮኝነት ለጀመሩ ወዳጆቼ!!

                          
🪩እጮኝነት_ላልጀመሩ
እባካችሁን እናንተን አንድ ነገር እንድል ፍቀዱልኝ..."እድለኞች ናችሁ!!" የምሬን እኮ ነው። እስቲ ለእናንተ ስለ እጮኝነት የሆነ ነገር ልበላችሁ።
፠ እጮኝነት ብቸኛ ስለሆናችሁ የምትገቡበት ነገር አይደለም።
  - እመነኝ ብቸኝነት ተሰምቶክ እጮኝነት ከመጀመር ይልቅ ብቸኛ ሆነክ(ክርስቶስ እኮ አለክ ኣ?) የትምህርት ዘመንክን ብትጨርስ የተሻለ ነው።
፠ እጮኝነት ጊዜ የሚፈልግ ነገር ነው።
  - የጊቢ ነፃነት ጊዜ አለችሁ ሊል ይችላል። ግን በእኔ ይሁንባችሁ ከ1 ሴሚስተር በኋላ ነፃነት እና የጊዜ አጣቃቀም እንደሚለያዩ  ከማስተዋላችሁ በፊት አሁን የምላችሁን እመኑኝ።
፠ እጮኝነት ሁለት ጥንዶች አንድ ወደሚሆኑበት ትዳር ከመግባታቸው በፊት የሚጠናኑበት ህብረት ነው እንጂ ፈታ ብለክ ዞር የምትልበት የመዝናኛ ክበብ አይደለም።
  - ግባችን ትዳር እስካልሆነ እጮኝነት ማሰቡ ትንሽ ሞኝነት አይመስልም?(መቼም አሁን ላይ አላማዬ ትዳር ነው አትለኝም። እንደሱ ካልክ የጋብቻ ትምህርት ቤት ነክ ማለት ነው።)
፠ ትምህርታችሁን አትዘንጉ ያለበለዚያ ነፃነት የተባለው ማእበል ከርስክ ጋር አጣልቶክ ህይወቴ እኮ ናት ካልካት እጮኛክ ጋር አጣልቶክ... "ሰራሁለት!" ይላል!!

🎈ማስታወሻ፦
      ፠ በዩኒቨርሲቲ ቆይታ እጮኝነት ጀምረው ትዳር የመሰረቱ የሉም አልወጣኝም።
      ፠ ደግሞ ከ80% በላይ በተሳሳተ እጮኝነት ተሰብረው ከትምህርታቸውም ከአምላካቸው ሳይሆኑ የቀሩ እንዳሉም አስተውሉ።
                                    እጮኝነት_ለጀመሩ
፠ ምን ያህል በእጮኝነት ህይወት እንደቆያችሁ ባላውቅም ግን በነበራችሁ አጭርም ይሁን ረጅም ጊዜ የፍቅር ግንኙነት እንደሚነገርለት ቀላል እንዳልሆነ የተረዳችሁ ይመስለኛል። ካሰባችሁት በጣም ቀላል ሆኖ አግኝታችሁ ከሆነ ሁለት ነገር መገመት አያቅተኝም
1. ጌታ በጣም ረድቷችኋል ማለት ነው።
2. የጀመራችሁት ግንኙነት እውነተኛ ፍቅር መሆኑ ያጠራጥረኛል

💯ግድ የላችሁም በዚህ እንስማማ ጌታ ካልረዳ እጮኝነት መጀመር በጊቢ ቆይታ ሌላ ዩኒቨርሲቲ መግባት ነው አ?(እንተማመና! እንደውም በጊቢ ቆይታው የእጮኝነት ህይወቱን ሳያበላሽ የወጣ ሁለት ዲግሪ እንደመስራት ነው።ለእኔ!!) 
ማስፈራሪያ በዛበት አ? እኔ እንዲህ አምናለሁ። " ትዳር የእግዜአብሔር ስጦታ ከሆነ እጮኝነትም ከእርሱ ዘንድ የተሰጠን ስጦታ ነው።" ስለዚህ ሰው ከሰው የተሰጠውን ስጦታ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ከጠበቀ ከጌታ ለተሰጠው ስጦታ ደግሞ የፈለገ መስዋትነት ቢከፍል ሞኝ አያስብለውም።

   🤔  እጮኝነት ከጀመራችሁ እንዲህ ብታደርጉ መልካም ነው።
፠ ፀልዩ!!(አዎዎዎ የተለያየ ስፍራ ሆናችሁ ቢሆን እንካን አብዝታችሁ ፀልዩ።)
፠ የፍቅር አጋራችሁ ከጌታ የተሰጣችሁ ስጦታ ነውና ታማኝ ሁኑለት።
፠ አይናችሁ እጃችሁ ባለው ስጦታ ይሁን እንጂ በሌላ አትሸወዱ።
፠ በመካከላችሁ ክፍተት እንዳይፈጠር ነገሮችን በግልፅነት ተነጋገሩ።
፠ ከጊቢው ጋር ተያይዞ የሚሰማችሁን ስሜት በሌላ አትረዱ።

‼️ማስጠንቀቅያ፦
      ፠ እጮኛሽ ወዳለሽበት ከተማ አንቺን ለመጠየቅ ሊመጣ ይችላል እና በዚህ ጊዜ እኔን ብሎ እኮ ነው የመጣው ብለሽ አብረሽው ቤርጎ ያዝሽ ማለት "ተበላሽ!!" እናንተ ከብረት የተሰራችሁ አይደላችሁም ውስጣችሁ የሚፈሰው ደም እንጂ ፈሳሽ ሜርኩሪ አይደለም። እመኑኝ ስሜታችሁን መቆጣጠር ተስኗችሁ ሌላ መዘዝ ውስጥ ትገባላችሁ።(ጌታ ከዚህ ይሰውራችሁ!!)

🧔🏾ብዙ ፀጋ ይብዛላችሁ

⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

06 Nov, 09:20


🗯 የቀጠለ…
10 ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሚጠቅም ምክር

6. 🤔በግቢ ቆይታችሁ ምን ማድረግ ዕንደምትፈልጉ አስቀድማቹ አስቡ

🧠አንድ ተማሪ ወደ ግቢ ሲሄድ ማድረግ ያለበት ነገር አንዱ ነገር በግቢ ቆይታው ምን ማድረግ ዕንዳለበት ከመሄዱ በፊት መወሰን ነው:: አስቀድሞ ምን ማድረግ ዕንደሚፈልግ? በምን መልኩ ጊዜውን ዕንደሚያሣልፍ ፣ ከ እግዚኣብሔር ጋር በምን መልኩ እና በምን ሠአት ዕንደሚገናኝ፣ ለራሱ የሚሰጠውን ጊዜ ኣቅዶ መሄድ ጠቃሚ ነው፡፡ የግቢ ህይወት ራሳችን በራሳችን ማስተዳድር የምንማርበት ሠፊ ህይወት በመሆኑ ማቀድ ተገቢ ነው። ብዙ ወጣቶች የሚለወጡበት በመሆኑ ግቢ ልክ ዕንደሌላው ወጣት ክርስቲያንንም ስለሚፈትን አስቀድሞ ማቀድ አስፈላጊ ነው።

7. 😎የመዝናኛ ምርጫዎቻችን በቅድስና መነጽር ምረጡ

🧠ማንኛውም ወጣት ግቢ ከቤተሰብ ነፃ ሆኖ የሚኖርበት ቦታ ነው:: ታዲያ በግቢ ህይወት ከትምህርቱ ውጪ በተጨማሪ ሌላ ህይወት ያለ ነው፡፡ ከዚህ ህይወት አንዱ መዝናኛ ነው። በግቢ ቆይታችን ዕንዴት መዝናናት ዕንዳለብን በቅድስና መምረጥ አለብን። በኢንተርኔት አጠቃቀማችን ፣ ለመዝናናት ለምንሄደው ቦቻዎች ፣ በምናያቸው ፊልሞች፣ ለመዝናናት በምንመርጣቸው ተግባራት ላይ የመጀመሪያ ነገር እግዚኣብሔርን ያከብራል በመቀጠል ዕኔንስ ጠልፎ ይጥለኛል ወይ? የሚለውን ማየት አለብን።

“ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥12

እዚህ ጋር አንድ ነገር ልጨምር አትኩሮትም ይሠጥልኝ።

ለመዝናናት እና ለጊዜ ማሣለፊያ ብላችሁ የፍቅር ጓደኝነት ዕንዳትጀምሩ!!!


8. 🫡እርዳታ መጠየቅ ልመዱ

🧠ብዙ ጊዜ ዩኒቨርሲቲ ከቢሮ መገኛ ቦታ ጀምሮ ውስብስብ ያለ ቦታ ነው:: ከተለያዩ ቦታ የሚመጡ አዳዲስ ተማሪዎች ድንግርግር ሲሉ ይስተዋላል። በክፍል ውስጥም ልክ እንደዚሁ በአለመተዋወቅ እና በፍርሃት ምክንያት ያልገባቸውን የማይጠይቁ ብዙ ናቸው። ይህ ግን ተገቢ አይደለም። ሲከብደን ፣ ያልገባን ነገር ሲኖር ለመጠየቅ መድፈር እና መልመድ አለብን :: ''ጠያቂ አዋቂ " ይላሉ አበው ሱተርቱ በመሆኑ መጠየቅ በተገባን ቦታ መጠየቅ አለብን።


9.🏃‍♀‍➡️ የሰውነት ጤንነታችሁን ጠብቁ

🧠ጥናት አልተደረገም ዕንጂ አንድ ተማሪን ከግቢ ትምህርት የሚያሠናክል ነገር የሥጋ ጤንነት ነው:: የቤት ምግብ፣ የለመዱትን አየር መቀየር፣ ብዙ ብዙ ምክንያቶች የውስጥ ጤናን ያውካሉ። ታዲያ በዚህ ወቅት በአግባቡ አለመማር ፣ ክላስ ማምለጥ አልፎም “withdraw” እስከመሙላት ስለሚያስደርስ  ጤናችንን መጠበቅ ያስፈልጋል። በመሆኑም ስለ ጤናችንን እያመሰግንን ከመፀለይ በተጨማሪ የምንበላውን ምግብ በንፁህ ውሃ ታጥበን መመገብ፣ የማይስማሙንን ምግብ በተቻለ አቅም የምንወስድበትን መጠን መቀነስ ፣ ሠውነት እንቅስቃሴ ማደረግ ያስፈልጋል።

10. 👨‍❤️‍👨ስለ ፍቅር ህይወታችሁ ተግታችሁ ፀልዩ

🧠ግቢ ሲገባ አንድ በአብዛኛው ወጣት የሚታሰበው ነገር የፍቅር አጋር ወይም ጓደኛ  መያዥያ ቦታ ተደርጎ ነው የሚታሰበው፡ ፡ ዕንደው የልባችንን ዕንነጋገር ከተባለ ፌሎ ለዚህ ትልቅ ሚና እየተጫወታ ያለ የክርስቲያን ጓደኛ መፈለጊያ ቦታ ነው። ታዲያ በዚህ መሃል የፍቅር ግንኙነት ሣይታሰብበት ይጀመራል። ወጣት መሆናችን ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሰሜት ተጋላጭ ያደርገናል። በዚህ ጊዜ ስላልታሰበበት ከቅድስና መውጣት፣ ትምህርት ማቋረጥ ፧ መጨነቅ ......ሌላም ሌላም ሊመጣ ይችላል። በመሆኑ የፍቅር ጓደኝነት ከመጀመራችሁ በፉት በእግዚኣብሔር  ፊት ፀልዩ ፤ ፁሙ :: በደንብ አስቡበት! ከመጀመራች በፉት ይህን ጥያቄ ለራሣችሁ መልሱ!

1. ዕዉነት ለትዳር ዝግጁ ነኝ? ( አስተውሉ! ለትዳር ነው ያልኩት)
2. ዛሬ ምወስነው ነገር ነገ ላይ ዞር ብዬ ስየው ይጸጽተኝ ይሆን ወይ?
3  የእግዚኣብሔር ፍቃድ በሁኔታዬ ላይ ምንድነው?


🫡እግዚኣብሔር ሁላችሁንም ረድቶን ደግሞ ከጥቂት አመታት በኋላ ለከበረ ደረጃ ዕንደምትደርሱ ትልቅ እምነት አለኝ። ጌታ በነገር ሁሉ ለዘመናችሁ ሁሉ ኣብሮ ይሁን ፀጋ ይብዛላችሁ ።

©teho
⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

05 Nov, 10:39


👩‍⚕10 አዲስ ክርስቲያን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የሚጠቅም ምክር.....🧠

1. 🙏በነገር ሁሉ እግዚኣብሔርን አስቀድሙ (ማቲ 6፥33 / ምሣሌ 3፥5-6 )

🧠በዚህ ምድር ላይ የተጠራነው በዋነኝነት እግዚኣብሔርን ለማክበር እና ከእርሱ ጋር ሰራተኞች ሆነን ልንሠራ ነው:: በእርግጥ አንድ ተማሪ ወደ ግቢ ሲሄድ ዋነኛ አላማው መማር ቢሆንም ለክርስቲያን ግን በህይወት ዘመን ሁሉ እግዚኣብሔርን ማስቀደም አለበት :: ስለዚህ ቃሉን ለማንበብ እና ለማሠላሠል ፣ ለመፀለይ እና እግዚኣብሔርን ማወቅ ማስቀደም አለብን :: ይህ ማለት ግን  የትምህርት ሰአትን ተጋፍተን መሆን የለበትም። አንዳንድ ተማሪዎች ክለስ ቀርተው፣ ማጥናት እየኖረባቸው ፌሎ ብለው ይሄዳሉ ይህን ተገቢ አይደለም ::

2.🥰 በተቻለ መጠን ኢየሱስን የሚወዱ ጋደኞች ይኑሩን

🧠ሠው በተለያየ መልኩ ከእግር ይቀርባል ደግሞሞ ይርቃል :: ከእነዚህ መንገድ መካከል ዋነኛው ጓደኛ ነው:: መጽሃፍ ቅዱስ በ2ተኛ ጢሞ 2፥22 ላይ
“ከወጣትነት ክፉ ምኞት ሽሽ፤ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋርም ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ተከታተል።”
  — 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22 (አዲሱ መ.ት)
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን በተግባር የሚያደርጉት ጋር አብሮ መሆን ጠቃሚ ነው

3.🤔 ስለ መጨናነቅ አታሰቡ

🧠የመጀመሪያው አንድ ተማሪ ግቢ ገባ ሲባል ወደ ሁሉም ሀሣብ ሚመጣው በቀድሞው አጠራሩ "Christmas test " ወይም " የገና ግርግር " የሚባለው በአሁኑ freshman ወይንም Remedial ፈተና ነው:: በእርግጥ የመጀመሪያ የማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥበት ወቅት ቢሆንም የዩኒቨርሲቲ ውጤት እና ህይወት ማብቂያ ተደርጎ መታሰብ የለበትም :: በዚህ ወቅት ራስን አረጋግቶ ፈተና ላይ በማተኮር አቅም በፈቀድ መጠን መስራት እና ውስጥን ማረጋጋት አስፈላጊ ነው።

“እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።”
  — 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7 (አዲሱ መ.ት)

4 🏃‍♀‍➡️ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙ

🧠ሌላው በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚስተዋለው ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም ነው፡፡ አንዳንዴ በጣም ብዙ የሚሰራ ነገር ይኖር እና በተማሪ ላይ መጨናነቅ ይታያል። አንዳንዴ ደግሞ ሠፊ የሆነ ነፃ ጊዜ ስለሚኖር ምን ዕንደሚደረግ ይጠፋል። ታዲያ በሁለቱም ወቅት የራስን፣ የውስጥን ስሜት ማረጋጋት እና በእቅድ መመራት ተገቢ ነው። ብዙ አሣይመንቶች በተሠጡ ጊዜ አግባብነት ባለው ወቅት መስራት በተደራረበብን ወቅት ተራ በተራ ለመስራት እና ለመጨረስ መሞከር ተገቢ ነው፡፡ ነፃ ጊዜ በሚገኝበት ወቅት በእቅድ ማሣለፍ መለማመድ ተገቢ ነው።

“ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤”
  — መክብብ 3፥1 (አዲሱ መ.ት)

5. 🤯ትምህርታቹን ላይ አተኵሩ ግን አታምርሩ

🧠በኢትዮጲያ አብዛኛው የማህበረሠብ ክፍል የወደፊት ህይወቱን በትምህርት ላይ ብቻ የተመሰረት እና የነገው ተስፋ በትምህርት ብቻ ይገኛል ብሎ የሚያምን በተጨማሪ የሀገራችን ስርአት ለዚህ የተጋለጠ ነው፡፡
ትምህርት አንድ የዕውቀት መገቢያ መንገድ ነው:: መጽሃፍ ቅዱስም ትምህርታችን በአግባቡ ዕንድንማር ይመክረናል።

“ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።”
  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥16


🧠ይህ ማለት ግን ትምህርት የህይወታችን መሠረት ነው ፤ ትምህርት ካልተሣካልን የህይወት መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ እግዚኣብሔር በእርግጥ በአንድም በሌላም መልኩ ይሥራል። በዚህ ዘመን የታወቁ ሰዎች ፣ የእግዚኣብሔር አገልጋዮች፣ እና ሌሎች ሠዎች በቀለም ዕውቀታቸው የበለፀጉ ነበሩ ፤ናቸውም፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ፊደል ያልቆጠሩ፣ የቀለም እውቀትን የማያውቁ በእግዚኣብሔር ቤት የኖሩ በአለም በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው  ታላቅ ተፅህኖ ያመጡ ሠዎች አሉ። በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ጥበበኞች ብሎ ዳንኤል፣ ሠለሞን ወዘተ ...... ይጠቅሣል። በሌላ በኩል ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ ራሱ ሐዋሪያትን ያልተማሩ እና ማንበብ የማይችሉ ዕንደ ነበሩ ይነግረናል።

🫀አስተውሉ!

" ትምህርትን አያስፈልግም እያልኩ ሣይሆን ዕንደ ክርስቲያን እግዚኣብሔር ላይ ነው ተስፋችን መሆን ያለበት ፣ ስለዚህ ትምህርታቹ ላይ አተኩሩ ግን አታምርሩ"

ይቀጥላል...

teho
 
⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

04 Nov, 19:39


UNIVERSITY እና ክርስትና
ቅድመ ዝግጅት አዲስ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለሚቀላቀሉ ክርስቲያን ተማሪዎች
 
አንድ ነገር አውቃለሁ... "እግዜአብሔር መልካም እንደሆነ!!" ስለዚህ እንዲህም ስላችሁም እግዜአብሔር መልካም ነው..."university የሚያስገባ ነጥብ መጣ አልመጣ እርሱ መልካም ነው!!" በዚህ ከተስማማን እንቀጥል።
ይህ ነገር ሁላችንንም ያስማማናል "ዛሬ ጌታ ቢመጣ 12ኛ/10ኛ ክፍል ሆነን የተፈተንነው የፈተና ውጤት አይደለም የዘላለም ህይወት የሚሆነን!!"
፠ ስለዚህ በፈተና ያለፍንም የወድቅንም አንድ የሚያደርገን ነገር አለ..."መማራችን ጌታ እንዲከብርበት ነው።
አዎዎ ወድቀንም ጌታ እንዲከብርበት ነው። ስንፍናን  እያበረታታው አይደለም።
ስለዚህ ይህን ፅሁፍ ስታነቡ ወድቂያለሁ...አልፍያለሁ...ነጥቤ አነሰ በዛ እያላችሁ ሳይሆን ነገ ላይ በትምህርቴ... በህይወቴ ጌታን እንዴት ላስከብር እያላችሁ መሆን አለበት።
ወደ ዋናው ርእሳችን እንመለስ...
አውቃለሁ የዘንድሮ የተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደ ባለ 100million ሎተሪ ቆራጭ ባለ እጣ ልባችሁን አንጠልጥሎ አልቀረም ወቷል ። እየደነገጡ ከመሸበር እና ግራ ከመጋባት እንደ ክርስቲያን እናንተ ግን ጌታን እንደሚያውቅ አስተዋይ ሰው እንዲህ ብትዘጋጁ መልካም ነው!!!

፠ በቅድሚያ አንድ ነገር እወቁ ጊቢ/ኮሌጅ ሰው እንደሚስልላችሁ አይነት እይታ ሳይሆን ያለው እናንተ ገብታችሁ የምትካፈሉት አይነት ገፅታ ነው ያለው።አንዳንዴ የዩኒቨርሲቲ ህይወት ምን እንደሚመስል የማያውቅ ሰው "ኡኡኡኡኡ እዛ ነው የደረሰህ/ሽ?...ተበላሽ!!!!" ሲል ልታደምጡ ትችላላችሁ ግን ምንም ይሁን ምን ከ15 ቀን በኋላ እራሳችሁ ገብታችሁ ታዩታላችሁ...ያኔ እንደ ገነት ተስሎ የተነገራችሁ ጊቢ በተቀራኒው ልታገኙ ትችላላችሁ። ክንፍ እንዳለው መልአት ተስለው የተነገራችሁ መምህር ቀንድ ያወጡ ሰይጣን ሊመስሏችሁ ይችላሉ። ስለዚህ እኔ እንዲህ እመክራችኋለው ምንም ይነገራችሁ ምን ለሁለቱም ነገር ራሳችሁን አዘጋጁ።
ከዚህ በተረፈ ብርድ ልብስ አንሶላ የእስፖርት ትጥቅ ስለነዚ ነገሮች እኔ አላስታውሳችሁም። TV ላይ ተከታተሉ እስኪሰላችሁ ትሰማላችሁ ነገር ግን እንደ ክርስቲያን ምን ሊገጥማችሁ እንደሚችል እና እንዴት ማድረግ እንዳለባችሁ ላውራችሁ እወዳለሁ።


[ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ለእናንተ ይጠቅማሉ ብዬ ያሰብኩትን ፅሑፍ ይዤላችሁ ስለምመጣ ፅሑፉን ይጠቅማል ለምትሉት ሰው ሼር ያድርጉ። ]


                         ⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

01 Nov, 20:36


⚡️#አጽንዖት⚡️

ድኀነት:- እግዚአብሔር ለኃጢአተኛው የሰራለትን የማዳን ሥራ እንጂ ማንም ራሱን ነፃ ለማድረግ የሰራውን ሥራ አያመለክትም❗️

ኤፌሶን 2
8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።

#ጸጋና_ምህረት_ይብዛልን

Christian Mindset

01 Nov, 18:45


❤️ሰላም እና ፀጋ ይብዛላችሁ ቤተሰብ + ዛሬ ትንሽ ወጣ ባለ ሀሳብ ነው የመጣውት የአመቱ ምርጥ የጥበብ ስራ ነው ከላይ ያጋራዋችሁ ሀሳብን ለመረዳት ሙሉውን ጨርሳቹ ተመልከቱ ይሄ በእግዜሩ አምሳል የተፈጠረ ሰብአዊ ፍጡር የሚሰማው አንድ ስሜት እንጂ ሌላ ምንም አጀንዳ የለውም እባካችሁ ተመልከቱት እንዲህ አይነቱን ስራ ያብዛልን ተዋንያን ይልመድባችሁ 🤩 ተመልክታችሁ ስትጨርሱ ከዛም በዚህ ፅሁፍ ላይ መታችሁ የተሰማችሁን comment አሰሙን ክበሩልኝ🙏

Christian Mindset

01 Nov, 18:38


https://www.youtube.com/watch?v=E0WGPyJp7w8

Christian Mindset

29 Oct, 22:17


ከእንቅልፋችን እንንቃ
" ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።" (ሮሜ  13:11 ) 

》ከእንቅልፍ እንንቃ ሲባል ባጭሩ እንቅልፍ አራት ደረጃዎች እንዳሉት ሳይንሳዊ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች ከመንፈሳዊ እንቅልፍ አንጻር በማየት የኛን ሁኔታ ስንመለከት:-

ደረጃ_1: አይን መጨፈን የሚጀመርበት
》ንቁ ሆነን ስናከናውናቸው የነበሩ ነገሮችን ማከናወን የምናቆምበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ጊዜ በቀላሉ ለመንቃት የሚቻልበት ደረጃ የመሆኑን ያህል በፍጥነት ወደ ቀጣዩ እንቅልፍ ደረጃ የሚታለፍበት በመሆኑ ብዙ በዚህ ደረጃ የመቆየት እድል የለውም፡፡ ይህን ከመንፈሳዊ እንቅልፍ አንጻር ስናየው በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ አማኝ ቀደም ሲል  በንቃት የሚጸልየውን ጸሎት  በፍቅር ለእግዚአብሄር የሚያቀርበውን አምልኮ እንዲሁም በመሰጠት ያነበው የነበረውን የእግዚአብሄር ቃል  ለማንበብ ሃይል የሚያጣበት እና በሃጢያት ላይ ማመቻመች የሚጀምርበት ደረጃ ነው፡፡ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?( ገላ.3፡1 )  

ደረጃ_2: ቀላል እንቅልፍ
》 በዚህ ደረጃ አይንን ከመጨፈን ባለፈ ወደ ቀላል እንቅልፍ የሚገባበት ደረጃ ሲሆን በዚህም የልብ ምት እና ሰውነት ሙቀት የሚቀንስበት ወቅት ሲሆን በዚህም ሰውነታችን ወደ ጥልቅ እንቅልፍ ለመግባት ዝግጅት የሚያደርግበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ልባችን ለክርስቶስ የነበረውን መቃጠል (ፍቅር) የሚያጣበት እና ያለን መንፈሳዊ መነቃቃት የሚቀዘቅዝበት ደረጃ ነው፡፡ …የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና። እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፡፡ (ራእ.2፡4-5)

ደረጃ_3_እና_4: ከባድ እንቅልፍ
》 በዚህ ወቅት ሰውነታችን ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ የሚገባበት በመሆኑ በዙሪችን እየተከናወኑ ያሉ ነገሮችን ማስተዋል አንችልም፡፡ ንቁ በሆንበት ጊዜ የሚታዘዙን ጡንቻዎቻችን ፓራላይዝድ የሚሆኑበት የእንቅልፍ ደረጃ ነው፡፡ በዚህ የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ከመንፈሳዊ አለም ያለን ቁርኝት የሚቋረጥበት እና ለመንፈሳዊ ነገር ባዳ የምንሆንበት ይልቁንም ስንጸየፋቸው የነበሩ አለማዊ ልምምዶች  ምንም እንዳለሆኑ ተቆጥረው በቤተ ክርስቲያን ስፍራ የሚይዙበት ፣ ከአለም ጋር መዳቀልና መቀላቀል የተለመደ የሚሆንበት ደረጃ ነው፡፡ ወገኞች ሆይ በየትኛውም የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ  ላይ እንገኝ ያው እንቅልፍ ላይ በመሆናችን እንንቃ እንመለስ! ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ (ሮሜ.13፡11)

.   ⬇️ ይቀላቀሉን ⬇️
  •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

28 Oct, 21:01


🤔ምን አስተውላችሁ

👇👇የተሰማችሁን comment ላይ አሰሙን👇👇

Christian Mindset

25 Oct, 15:49


ልቤን በአፍሪካ ቅበሩ።
ዴቪድ ሊቪንግስተን(1813----1873).
ለአፍሪካ የወንጌል ብርሃን እንዲበራላት ሕይወቱን፣ትዳሩን፣ምቾቱን፣ዕድሜውን፣ዘመኑን፣መስዋዕት ስላደረገው ታላቅ ባለራዕይ ሚስዮናዊ ዴቪድ ሊቪንግስተን።

ከዛሬ 138 ዓመታት በፊት ዴቪድ ሊቪንግስተን የተናገረ ንግግር "ኤኔ "ከሞትኩ ልቤን አውጥታችሁ በአፍሪካ ቅበሩ፣ሬሳዬን ወደ እንግሊዝ ውሰዱ"።ዴቪድ ሊቪንግስተን አፍሪካ የጨለማው ከፍለ አህጉረ ተብላ የምትታወቅበት ዘመን በወንጌል ብርሃን የጨለማውን  ሊገፍ በነብሱ ተወራርዶ ራሱን ለተጋለጡት መለኮታዊ ራእይ የሰጠ ባለራዕይ ነበር።

ዴቪድ ሊቪንግስተን ከሜድካል ትምህርት ቤት እንደተመረቀ፣ጓዙን ሸክፎ በጊዜው የጨለማ ምድር ትባል ወደ ነበረችው አፍሪካ ወንጌልን ይዞ ዘመተ።በወንጌል ብርሃን ሊሆንላት የራሱን መልካም ኑሮ፣ዕድገት፣ትምህርት፣ወዳጆች፣በብዙ ዕድሎች የተሞላች የታላቋ ብሪታንያ አካል የሆነችውን ስኮትላንድ እርግፍ አድርጎ ተወ።

በራእይ ጉልበት፣በፍቅር ተገዶ ንጹህ ውሃ ለማግኘት ወደሚቸገረበት፣የሰዎችን ቋንቋና ባህል ወደማያውቅበት፣በሰፈርና በጎሳ ተከፋፍሎ ይተላለቁ ወደነበሩት፣ከእሾህና ከዱር አራዊት ጋረ እየተፋጠጠና በእግሩ ከአገር ወደ አገር እየተጓዘ ወደሚኖርበት ፣ባዕድ አምልኮና አጋንንታዊ አሠራር፣የሰዎችን አዕምሮ ምድሪቷን ወደ ገዛበት አፍሪካ፣በወንጌል የምስራች ዜና ተስፋ ሊሆንላት መጣ።ወደ አፍሪካ በደቡብ በኩል ለመግባት ያደረገው ሙከራ ባይሳካለትም ተስፋ ሳይቆርጥ ወደ ምዕራብ አፍሪካ በማቅናት፣ከብዙ ትግልና ትግስት በኋላ ወደ መሀል አፍሪካ የሚዘልቅበት በር ተከፈተለት።

“ጌታ ሆይ ከባድ ሸክምህን ሁሉ በእኔ ለይ ጫነው”ብሎ ይጸልይ እንደነበር፣ጸሎቱም መልስ ይዞ መጣ።ዴቪድ በራእይ ኃይል ወደ መሀል የአህጉሪቱ ክፍል በእግሩ ስጓዝ አንድ ትልቅ አንበሳ ሰፍሮበት በእግዚአብሔር ከሞት ቢያመልጥም ግራ እጅ ሽባ ሆኖአል።ዴቪድ ማርያም የምትባል ቆንጆ ሚስት ነበር።ማርያም ከዴቪድ ጋር ብዙ የመከራ መራራ ጽዋዎችን የጨለጠች ጠንካራ ሴት ነበረች።በተለይ ከሁሉም ልባችውን የሰበርው፣የአፍሪካን በረሃ ሲያቋረጡ ከልጆቻቸው መካከል አንድ በእጃቸው ላይ መሞቱ ነበር።

መከራው ከቀን ወደ ቀን እያየለ ስመጣ፣ለራሱ ወደ ኋላ ለመመለስ ስላልፈለገ ሚስቱንና ልጆቹን ወደ ኢንግላንድ ሲልክ ቤተሰቡን ከራሱ የለየው ሰለማይወዳቸው ነው የሚል ብርቱ ትችትም እንደተሰነዘረበት ታሪኩ ያወሳል።ዴቪድ ከውጪው አለም ጋረ የነበረው ግኑኝነት ለ16 ዓመታት ከተቋረጠ ና ከቤተሰቡ ጋር ለ5 ዓመት ከተለያየ በኋላ ከአፍሪካ ወደ እንግሊዝ አቀና።ተወልዶ ወዳደገበት ቀዬ ሲያመራ መንደሩ ወና ሲሆን የአባቱን ሞት የሰማውም ሠፈሩ ሲደርስ ነው ።

ዴቪድ ልቡን ለአፍሪካ የወንጌል አገልግሎት ስለሰጠ ከቤተሰብ ጋር ብዙ ለመቀመጥና የእንግሊዝን መልካም ኑሮ ለማጣጣም ለራሱ ዕድል አልሰጠም።እነዚያ በሺ የሚገመቱ የክርስቶስን ወንጌል ያልሰሙ መንደሮች ራእይ እረፍትና እንቅልፍ ስለነሣው ወደ አፍሪካ ጫካ ወዲያው ተመለሰ።ዓመታት ተቆጠሩ ልጆቹም እራሳቸውን ወደ መቻል ሲመጡ ባለቤቱ ሜሪ ዴቪድ እንዲመጣ ደብዳቤ ብትልክለትም የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ።እርሱ ባይመጣ እኔ ልፈልገው በማለት አስቸጋሪውንና ረዥሙን ጉዞ ከእንግሊዝ ወደ አፍሪካ ጫካ በመርከብ ጀመረች።

ለወራት  በውቅያኖስ ላይ ተጉዛ ባለቤቷ ወደለበት አፍሪካ ጫካ እንደደረሰች በብጫ ወባ ታማ የአልጋ ቁራኛ ሆነች።
ዴቪድ እርሱን ፍለጋ ብዙ ለደከመችውና ለሚወዳት ሜሪ ከበሽታዋ እንድታገግም የተቻላቸውን ሁሉ ቢያደርግላትም ከሞት መንገድ ሊመልሳት አልቻለም።ቀንና ሌሊት በእንባ ይታጠብ ነበረ።በመጨረሻም እጁ ላይ እያለች እስከ ወዲያኛው አሸለበች።በአንድ ዛፍ ሥር ቀበራት።በጭቃ ላይ ቁጭ ብሎ አለቀሰላት።

በመጨረሻም ዴቪድ ሊቪንግስተን ዓይኖቹም ደከሙ፣ሁሌ የሚበላው ደረቅ የበቆሎ ቆሎ ስለነበር ጥርሶቹም የማድቀቅ ሥራቸውን እያቆሙ መጡ።ሰውነቱም መልፈስፈስ ጀመረ፣በሁሉም ሰው ተረሣ መቆምም መቀመጥም ተሳነው ፣ይህም የባለራዕይ የመጨረሻው የክብር ጊዜ ነበር።

ወደ አንድ ጎጆ ሲያስገቡት እንዲህ ብሎ ተናዘዘ "እኔ ከሞትኩ ልቤን አውጥታችሁ በአፍሪካ ቅበሩት ቀሪው አካሌ ወደ  አገሬ ይወስድ"ብሎ ከላይ የሚዘንበው ዝናብ በተኛበት ቦታ እያበሰበሰው ለመጨረሻ ጊዜ ከበሽታው ጋር ይተጋል ነበር።በመጨረሻም አዳምንም ታግሎ ተንበርክኮ እየጸለየ ባለበት ሥፈራ ወደ ቀጣዩ ሕይወት ተሻገር።
   የባሪያ ንግድ እንዲቆም ተጽእኖ  የፈጠረው ሰው ነበር።
           •√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

24 Oct, 19:41


😞ፀሎት

አታድነኝም ወይ?!😔

🥹አባቴ ዛሬም እኔ ነኝ የምትሳሳልኝ ልጅህ እንደ ወትሮዪ መጥቻለሁ
አንተ ሁሉን አዋቂ ነህ። የማታውቀውን አዲስ ድካሜን አልነግርህም። ግን ትግሉ ከብዶኛልና ተማጽኖዬን አሰማሃለሁ። 🥹 እኔን ከእኔ እንድታስጥለኝ ልመናዬን ወደአንተ አደርሳለሁ። በአንድ እኔ ውስጥ ሁለት ተቃራኒ እኔነቶች እንዳሉ ይሰማኛል። በአንድ በኩል፤ እኔ አንተን ላከብርህ፣ የሰጠኸኝን ተልዕኮ ከግብ ላደርስና ለሰዎች ጥቅም ልኖር እፈልጋለሁ። ደግሞ በሌላ በኩል፤ እኔው ራሴ ከዚ በተቃራኒ የራሴን ክብር የምወድ፣ ለራሴ ፈቃድ በመኖር የምደሰትና ለግል ጥቅሜ እንጂ ስለ ሌላው ግድ የማይሰጠኝ ሆኜ ራሴን አገኘዋለሁ። ታዲያ እኔ የቱ ነኝ? መቼስ ነው በውስጤ የሚደረገው ይህ ትግል የሚያበቃው? በጸሎት ስፍራዬ ሕልውናህ ተሰምቶኝ በቃልህ ስበረታ ከዚህ ትግል የተገላገልኩ ይመስለኝና ምድር ላይ መሆኔንም እስክረሳ እሆናለሁ። ደግሞ ሌላ ጊዜ በልቦናዬ ዝው የሚሉትን የክፉ ሀሳቦች ብዛት ስመለከት የማስበውን ሀሳብ እኔ እያሰብሁ እንዳለ እንኳን ማመን ይከብደኛል። እራሴን እጠላለሁ። ወዳንተ እንድሰበስበኝ እመኛለሁ። ታዲያ እኔ የቱ ነኝ? ታዲያ ከዚህ ትግልስ መቼ ይሆን ድል አድርጌ የምወጣው ? አባቴ ሆይ አልደብቅህም ከብዶኛል። የእውነቴን ነው ከብዶኛል። ለዚህ ለሞት ከተሰጠ ስጋ አንተ ካላዳንኸኝ ማን ሊታደገኝ ይችላል? እኔን ከራሴ አንተ ካላዳንክ ማን ሊያድነኝ ይችላል?
የዚህ ትግል መቋጫው ወይ አንተ ዳግም ስትመለስ ወይ ደግሞ እኔ ወዳንተ ስሰበሰብ እንደሆነ አልዘነጋሁትም። ትግሉን እንድታስቆምልኝ እንድጸልይም ቃልህ አይነግረኝም። ታዲያ ጸሎቴ፤ አጋዤ አንተ ብቻ በመሆንህ እጄን እንድትይዘኝ፣ በዕለት ዕለት ፍልሚያዬ ውስጥ በድል እንዳሸገር እንድትረዳኝና ከፍጻሜው እንድታደርሰኝ ነው።

 "ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም" ዕብራውያን 4:15

አሜን🤲

•√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

23 Oct, 10:09


🤔ጥያቄ ለ ኢትዮጵያ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን  መሪዎች
የመርሐግብሩ ድምቀቶች ወይስ...?

  ጁላይ 27 2024፣ የ2024 ዓ ም የEGST ተማሪዎች የምርቃት ቀን ነበር።  ትምህርት ቤቱ በፌስቡክ ገፁ በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙትን እንግዶች ከመዘርዘሩ በፊት "The event was graced by esteemed dignitaries" የሚል ዐ/ነገር ተጠቅሟል (ሊንኩ በኮመንት ሳጥን ተቀምጦላችኋል)፤ ለመሆኑ እነዚህ ለዕለቱ ፕሮግራም "ድምቀት" ናቸው የተባሉት እንግዶች እነማን ነበሩ?

1. አርክቢሾፕ ማርቲን ሞደስ ከሲዊዲን ቤተክርስቲያን
2. ቢሾፕ ኤልሳቤጥ ኢተን ከአሜሪካ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን
3. ሪቨረንድ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንትና የEGST ባለድርሻ አካላት ሊቀመንበር
4. ዶ/ር ጣሰው ገብሬ የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት
5. መጋቢ ፃዲቁ አብዶ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ፕሬዚዳንት

  ከነዚህ እንግዶች ውስጥ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱት የ"Church of Sweden" አርክቢሾፕ ናቸው። የእኚህ ሰው ቤተክርስቲያን እ.ኤ.አ. ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ተመሳሳይ ፆታዎችን በጋብቻ ታጣምራለች፤ በቤተክርስቲያኒቱ ደንብ መሠረት "Gay" ወይም "Lesbian" ሆኖ የቤተክርስቲያኒቱ አባል መሆን ይቻላል፤ እንዲያውም እ ኤ አ በ2009 በቢሾፕነት የተመረጠችው "Eva Btunne" በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ "Lesbian" ቢሾፕ ነች።

   በተ.ቁ. 2 የተጠቀሱት ቢሾፕ ኤልሳቤጥ ኢተን ደግሞ በአሜሪካ የወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን ቢሾፕ ናቸው። የዛሬው ፅሁፌ ትኩረት ሶደማዊነትን በተመለከተ በዋናነት ቢሾፕ ኤልሳቤጥና ቤተክርስቲያናቸው ያላቸው አቋም ምን እንደሚመስል መፈተሽ ነው፦

1. "Bishop Elizabeth Eaton" እግዚአብሔር "Gay" የሆኑ ሰዎችን ለመጋቢነት አገልግሎት እንደሚጠራቸው ያምናሉ። ቢሾፗ ለዚህ አቋማቸው ጉልበት የሆነላቸው ቤተክርስቲያናቸው...  Evangelical Lutheran Church of America(ELCA)...እ. ኤ.አ በ2009 ዓ. ም. ግብረሰዶማዊነትንና የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ተቀብሎ ማፅደቁ ነው ይላሉ። እናም ግብረሰዶማዊ "ጌዮች" ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥሪው ይኑራቸው እንጂ የቤተክርስቲያናቸው ምስባክ ለግብረሰዶማውያን ክፍት ነው። መቼም ዘይገረም ነው፤ ሰዶምና ጎሞራ ላይ እሳት የዘነበባቸው ግብረሰዶማዊያን በእኛ ዘመን ከኃጢአታቸው ንስሃ ባልገቡበት ሁኔታ እግዚአብሔር ለወንጌል አገልግሎት ሊጠራቸው እንደሚችል በቢሾፕ ኤልሳቤጥ እየተነገረን ነው፦

"The decision we took in 2009 to say that if called by God and if having the gifts to serve, partnered gay people can serve, I think that was the right decision..."(Bishop Elizabeth Eaton, source : Toledo newspaper)

2. እ ኤ አ በ2024 የ"United Methodist Church" ግብረሰዶማዊነትን በተቀበለች ጊዜ ቢሾፕ ኤልሳቤጥ ደስታቸውን የገለጡት እንደዚህ በማለት ነበር፦

"The ELCA rejoices and gives thanks to God for the opportunity to proclaim together (with United Methodists), from this point forward, that Christian teaching is for all people and that the gifts of all are welcome and needed to serve Christ's church."

ግብረሰዶማዊነት ያለአንዳች ከልካይ  ወደ ቤተክርስቲያን ሰተት ብሎ በመግባቱ ቢሾፗ ጭራሽ "እግዚአብሔር ይመስገን" እያሉ ነው! እግዝኦ ማረነ እንጂ ሌላ ምን ይባላል?

3. የ2024 የ"EGST" ምሩቃን "ድምቀት" እንደሆኑ የተነገረላቸው  ቢሾፕ ኤልሳቤጥ ፆታ መቀየርንም (Transgenderism) በብርቱ ከመደገፍም ባሻገር በቤተክርስቲያኒቱ በጀት በቀዶ ሕክምና ወንድ ወደ ሴትነት፣ ሴትም ወደ ወንድነት እንደየፍላጎታቸው ፆታቸውን እንዲቀይሩ ድጋፍ የሚያደርጉ ሴት ናቸው። ታዲያ የቤተክርስቲያኒቱ በጀት የሚመደበው ለፆታ ለውጥ ብቻ አይደለም፤ ለውርጃም(abortion) በጀት ይመደባል።

"The ELCA even pays for hormone blockers for children in the denomination’s healthcare plan. That’s right, your ELCA offering dollars at work, destroying children’s sexuality before it can develop. ELCA offering dollars also pay for abortion for any reason in the denomination’s healthcare plan."

4. ቢሾፕ ኤልሳቤጥ ኢተን በገሃነም መኖር አያምኑም፤ ቢኖር እንኳ ባዶ ሆኖ ነው የማገኘው ትለናለች።

"Elizabeth Eaton, head Bishop of the ELCA, has said that if hell exists, she believes it is empty. So, if everybody is going to heaven, what will the ELCA do with its time and money? Promote liberal politics."

5. ቢሾፗ ቀላል የሚባሉ ሴት አይደሉም። ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል 28 ፤19 ላይ በእንግሊዝኛው "Father, Son, and Holy Spirit" በማለት የተናገረውን እሷ  “Parent, Child, and Holy Breath” and as “Rain, Estuary, and Sea" በማለት የቀየሩ ደፋር ሴት ናቸው። ቢሾፗ ይህን ያሉት አንድ ፆታውን የቀየረ ቢሾፕ ለአገልግሎት ተሹሞ ከማህበረ ምዕመናኑን ጋር ሲተዋወቅ  ነበር።

"We must never forget the language Jesus gave us for God: Father, Son, and Holy Spirit (Matthew 28:19).  But at the installation service of the ELCA’s first transgender bishop, Eaton also referred to God as “Parent, Child, and Holy Breath” and as “Rain, Estuary, and Sea”(Pastor Tom Brock)

6. ከላይ ከተ ቁ 1-5 ያካፈልኳችሁን መረጃ ያገኘሁት ከ"Pastor Tom Brock" ፅሁፎች ነው(የዚህን ሰው Tom Brock  የፌቡ ገፅ ተከታተሉ)። በመጨረሻም ፓስተር ቶም የEGST ምሩቃን "ድምቀት የነበረችውን የቢሾፕ ኤልሳቤጥን መንፈሳዊ አቋም ከካቶሊኩ "Pope Benedict" ጋር ያነፃፀረው እንደዚህ በማለት ነበር፦

"I got to thinking. Pope Benedict believed abortion is a sin. Bishop Eaton works for abortion rights. Pope Benedict believed homosexual behavior is a sin. Bishop Eaton has produced gay pride videos. Pope Benedict believed in Hell. Bishop Eaton has said that, if Hell exists, she believes it is empty"

መልስ እንፈልጋለን ?
   👇
   @christian_mind_set

Christian Mindset

21 Oct, 19:39


😔#ቱርካዊው

😞ከቀናት በፊት አከራዬ ያለ ቅጥ የኪራይ ገንዘብ ጨመረብኝ ተው ብዬ ጥቂት ልሟገተው ሞከርኩ  አሻፈረኝ አለ  ካልሆነም ቤቴን ልቀቅ አለኝ ። ለዚህ የሚሆን ገቢ ስላልነበረኝ በብስጭት እያዘንኩ ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ።
   ታዲያ ከቀናት በኋላ ሰቅጣጩ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ።
     ዛሬ እኔና የቀድሞ አከራዬ አብረን በመጠለያ ውስጥ የእርዳታ ምግብ እየጠበቅን ጎን ለጎን ተቀምጠን እሳት እየሞቅን እንገኛለን።
  #ቱርካዊ
#ቀን #የሚያመጣውን #አታውቅምና #አትመካ
#ህይወትህን ቀለል ያለ አድርገው አትቆይም እና ቢያመንም የምንቀበለው መራራ እውነት ነው

🙃ህይወት እንዲህ ናት


•√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

15 Oct, 11:58


🥰የአውግስጢኖስ እናት(ሞኒካ)😘

ስለዚህች ድንቅ ሴት መጋቢ ጆን ፓይበር ሲያወራ ሰምቼ አውቃለሁ። በአንድ መጻሐፉ ላይም ሳያነሳት አይቀርም። ነገር ግን አሁን እያነበብኩት ባለሁለት የአውግስጢኖስ ዜና-ሕይወት መጽሐፍ ላይ ስለሷ የሰፈረውን ነገር ሳይ ታሪኳን ሰምቶ እንደማያውቅ እንደ አዲስ ሰው ነው የሆንኩት። አለመደነቅ አልቻልኩም። ይህን ለሰዎች ለማጋራት መጻሐፉን እንኳን አንብቤ እስክጨርስ አልጠበቅሁም። ይኸው ላስነብባችሁ ተከሰትኩ።
ብቻ ምናለፋችሁ ሞኒካ ድንቅናት።

ከዚህች ሴት ሕይወት የተገረምኩባቸውና አስተማሪ ናቸው ብዬ ያሰብኳቸው ጥቂት ነገሮች እነሆ:-
1. ሞኒካ በጣም ባሏን የምታከብርና በጥበብ በመያዝ የተካነች ሴት ናት።
በጊዜው ባሎች ሚስቶቻቸውን በጭካኔ ነበር የሚያስተዳድሩት። ነገር ግን ሞኒካ እንደሌሎች ሴቶች የባሏ የችካኔ ዱላ እምብዛም አላረፈባትም ነበር። ታዲያ ይሄን ያዩ ጓደኞቿ እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደቻለ በመገረም ሲጠይቋት፣ ከተጋቡበት ጊዜ አንስቶ ባለቤቷን Patriciusን እንደ ቤቱ አለቃ ትቆጥረው እንደነበርና ተበሳጭታበች ወይም ተቋቁማው እንደማታውቅ ይልቅ ባህሪው ምክንያታዊ ሆኖ አልታይ ካላት እስኪረጋጋ ጠብቃ ነገሩን እንደምታብራራለት ነበር የነገረቻቸው። ምናልባት ይህም ይሆናል ፓጋን የነበረውን ባሏን ከጊዜ በኋላ ወደ ቤተክርስቲያን ሊያመጣው የቻለው(ምንም እንኳን ለውጡ የሚያረካ ባይሆንም)።
2. ሞኒካ ከጌታ ጋር ያላት ህብረት ጠንካራ ነበር። በየሳምንቱ በጾምና ጸሎት የምታሳልፍባቸው የተመረጡ ቀናት ነበሯት። ቤተክርሰቲያን በቀን ሁለቴ ነበር የምትሄደው። ሰዎችን መርዳት ደስታን የሚቸራት አይነት ሴት ነበረች። ደግሞ ለጌታ ያላትን ቆራጥነት ይጨምር ዘንድ በየጊዜው እየሄደች የሰማዕታትን ሀውልቶች ትጎበኝ ነበር። ጌታን ስትወድ ከልቧ ነው።
3. ልጇን አውግስጢኖስን ከሳተበት ለመመለስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል የምትተጋ ሴት ነበረች። አውግስጢኖስ የሕይወቱ የመጀመሪያ እድሜዎች ብሎም በወጣትነት ጊዜው የነበረው ስነ ምግባርና የሚከተለው ሀይማኖት ጥሩ አልነበረም። ታዲያ ሞኒካ አውግስጢኖስን ይዛ በየዕለቱ በእግዚአብሔር ፊት በእንባ ትቀርብ ነበር። ምንም እንኳን አውግስጢኖስን በሙግት እንደማትረታው ጠንቅቃ ብታውቅም፣ የእውነትን ቃል በየጊዜው ለርሱ ከመናገር አትቆጠብም ነበር። ከ ሀገር ሀገር ሲቀይር ተከትላው ያለበት ድረስ ዋጋ ከፍላ ትሄድ ነበር(የውነት መፈናፈኛ ነው ያሳጣችው😅)። በየሄደችበት ሊረዱት ይችላሉ ብላ የምታስባቸውን ሰዎች አንዳች መፍትሄ እንዲያበጁላት ከመለመን ቦዝና አታውቅም። እንደውም በአንድ ወቅት አውግስጢኖስ የ Manichaeismን አስተምህሮ በሚከተልበት ጊዜ ሊረዱት ይችላሉ ብላ ያሰበችውን አንድ አባት በእንባ ብትማጸናቸውም እሳቸው ግን እንዲህ ያለ ለእውነት አሻፈረኝ ያለን ሰው እግዚአብሔር ራሱ ካልመለሰው በስተቀር ማነጋገር ረብ እንደሌለው ነገሮአት ጥያቄዋን ለማስተናገድ አልፈቀዱም ነበር። ሞኒካ ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ ተስፋ አትቆርጥም ነበር። እግዚአብሔር ጸሎቷን እንደሚሰማና በአንድ ወቅት በህልሟ አይታ እንደነበረው ልጆ እርሷ ወደምትከተለው ወደ እውነተኛይቱ ሀይማኖት እንደሚመለስ እርግጠኛ ነበረች። ይህም እንዲሆን በእግዚአብሔር ፊት እንባዋን ማፍሰስ የዘወትር ተግባሯ ነበር።
ይህች ሴት ድንቅ ሴት ናት። ይኸው በስተመጨረሻም ጸሎቷ ተሰምቶ መሻቷ ሰምሮላት እንደ አውግስጢኖስ ያለ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ታላቅ አሻራን ያሳረፈ ሰው ማፍራት ችላለች።

"እኔ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም እኖር ዘንድ ስለኔ ዓያሌ ዓመታትን ላነባችው፣ አሁን ስለሞተችውና ከእይታዬ ለራቀችው እናቴ አለቅሳለሁ።"
ቅ. አውግስጢኖስ (St. Augustine) እናቱን በሞት ሲያጣ የተናገረው ንግግር ነው።


😎Natyy

•√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

10 Oct, 10:19


"...የትዳር ጥያቄህን ከመቀበሌ በፊት፣ ስትሰብክ ማየት እፈልጋለሁ.."

በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ነው፤ አንድ ወጣት ከC.F. W. Walther ጋር በጋራ ሆነው ዛሬ LCMS በመባል የሚታወቀውን ቤተክርስቲያን ለመመስረት መነጋገር ይጀምራሉ። በጊዜው ዋልተር ሚዙሪ ሲሆን፣ ወጣቱ ደግሞ ሚቺጋን ነበር የሚኖረው።  ወጣቱ እንዳላገባ የተገነዘበው ዋልተር፣ ወጣቱን ወደ ሚዙሪ መጥቶ ሲኖዶሱን ስለመመስረት በስፋት እንዲነጋገሩ፣ እንዲሁም ያላገባች የቅርብ ዘመዱን ለትዳር ይተሳሰቡ ዘንድ ሊያስተዋውቀው እንዳሰበ ነገረው። ወጣቱም የዋልተርን ሃሳብ በደስታ ተቀብሎ ወደ ሚዙሩ ይመጣል። በዚያም ዋልተር ያሰበለትን እህት ያገኛል፤ ይወዳትማል። ሁለት ሳምንታት ያህል አብሯት አሳልፎ፣ የመጣበት የሲኖዶስ ምስረታ ውይይቱንም አጠናቆ መመለሸው ሲደርስ፣ ልጅቱን " ስለ እኔ እና አንቺ ምን ታስቢያለሽ እኔ በጥቂት ቀናት ውስጥ ልመለስ ነው?" ብሎ ሲጠይቃት፤ የሷ ምላሽ የነበረው "የትዳር ጥያቄህን ከመቀበሌ በፊት፣ ስትሰብክ ማየት እፈልጋለሁ" የሚል ነበር። እሱም ቅድመ ሁኔታውን ተቀብሎ እሷና እነ ዋልተርን ጨምሮ ሌሎች በታደሙበት ሰበከ፤ ለትዳርም በቁ😁

🤔ታሪኩን ስሰማ በጣም ተገርሜም አስፈግጎኝም ነበር። ነገር ግን ከመፈገግም አለፍ ብዬ በቤተሰብ ውስጥ የባልን የመጋቢነት ድርሻ እንዳስብ አድርጎኛል። መጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ፣ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ከበለሲቱ እንዳይበላ ያስጠነቀቀው አዳምን ነበር። ይህም ማለት ባለቤቱን ማስተማር የአዳም ሃላፊነት ነበር ማለት ነው። እንዲሁም በሌሎች የብሉይ መጽሐፍት ውስጥ ብንመለከት፣ አባት ቤተሰቡን የእግዚአብሔርን ሕግ የማስተማር ሃላፊነት አለበት (ዘዳ 6፥ 6 - 7፤ ዘጸ 13፥8)።ይህንንም ትዕዛዝ በማክበር በአይሁድ ባህል በፋሲካ የመጀመሪያው ምሽት በቤተሰብ የሚከበር Passover Seder ተብሎ የሚጠራ ስነ ሥርዓት አለ። በዚህ ወቅት አባት ለቤተሰቡ ከግብጻውያን እጅ እግዚአብሔር እንዴት እንደታደጋቸው ይተርካል። ሊበሉ ያሉት ምግብ እንዴት በምሳሌነት ያንን የእግዚአብሔርን ትድግና እንደሚያሳይ ያስረዳቸዋል። እሱ ብቻ አይደለም፣ Mah Nishtanah በለማል የሚታወቁትን ይህን የእግዚአብሔር ማዳን ቤተሰቡ እንዲወያይ የሚጋብዙትን  ጥያቄዎች ("ይህ ምሽት ከሌሎቹ ምሽቶች በምን ይለያል?" እና መሰል ጥያቄዎች ናቸው) የቤቱ ታናሽ ልጅ እንዲጠይቅ ያደርጋል። በዚህ መልክ ቤተሰቡ በዚህ የመጀመሪያው የፋሲካ ምሽት የእግዚአብሔርን ማዳን ያስታውሳል፤ እርስ በእርስ ይማማራል ማለት ነው። እንግዲህ በዚህ ውስጥ ትልቁን ሚና የሚጫወተው አባት ነው።

በአዲስ ኪዳንም አባት ልጆቹን በፈሪሃ እግዚአብሔር የማሳደግ ሃላፊነ እንዳለበት እናነባለን (ኤፌ 6፥4)። እንግዲህ ይህ ማለት አባት እንዲህ የቤተሰብ መጋቢ ለመሆን የበቃ መሆን አለበት ማለት ነው። ለባለቤቱም ቢሆን ራስ እንደመሆኑ ቃሉን ሊያስተምራት የሚችል መሆን አለበት።

ይህ ማለት፣ ሁሉም ወንድ ሰባኪ አሊያ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የገባ መሆን አለበት ማለት አይደለም። ነገር ግይ ለቤተሰቡ የሚተርፍ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ያስፈልገዋል። ምክንያቱም ቤተሰብ ሲመሰርት ዓላማው ቤተሰቡን በቃሉ እውነት አስታጥቆ በዚህ ምድር የክርስቶስ ወኪል አድርጎ ማብቃት ነው።

ይህንን እውነት Dietrich እንዲህ በማለት ይገልጻል "For this reason, children are born into this world and given to parents so that they will be given back to God, who created them; that they be instructed in his knowledge; improved; and brought up in true religion and the fear of God, that they will recognize and follow him alone."(Lives and Writings of the great Ftahers of the Lutheran Church, 123)

እንዲሁም በመጽሐፍ ንባብ ቡድናችን በጋራ ስናነበው በነበረው መጽሐፍ ላይ Francis Chan እንደባልነቱ ለሚስቱ ያለውን ሃላፊነት እና መሻት እንዲህ በማለት ይገልጻል "Because I am crazy about Lisa, I want her to have a great life. But more than that, I want her to have a great eternity. I want her to look back at her life without regret. I want her to be confident that the time she spent on earth prepared her for heaven. Most importantly, I want her to hear God say, “Well done, good and faithful servant. You have been faithful over a little; I will set you over much. Enter into the joy of your master” (Matt. 25:23). " (You and me Forever, pp. 10)

ስለዚህ፦

1. ወንድሞች ሆይ ይህ ዓላማ ገብቷችሁ ለእግዚአብሔር የጦር እቃ የሚሆን ትውልድ ከአብራካችሁ ለማብቃት የበቃችሁ እስክትሆኑ ድረስ ለትዳር እህቶችን ከማየት ተቆጠቡ። አግብታችሁ የሚስታችሁን መንፈሳዊ ሕይወት ለመኮትኮት የበቃችሁ አድርጋችሁ ራሳችሁን ካላሰባችሁ፣ ከትዳር በፊት በቃሉ ለማገንባትና ለማደግ ጊዜ ውሰዱ።

2. እህቶች ሆይ፣ ለትዳር ለምታስቡት ወንድ የመጀመሪያ መመዘኛችሁ "ይህ ሰው አብረን የምንመሰርተው ቤተሰብ መጋቢ መሆን ይችላል ወይ? ሳጠፋ በቃሉ ሊገስጸኝ ብቁ ነው ወይ? ከእርሱ ጋር አበሬ ብሆን አሁን የእግዚአብሔርን መንግስት ከማገለግለው በላይ ማገልገል እችላለሁ ወይስ ቀመንፈሳዊ ሕይወቴ እደክማለሁ?" ብላችሁ ጠይቁ። ይህን ስል፣ አንዳንድ እህቶች እግዚአብሔር ጸጋውን አብዝቶላችሁ በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ በስላችሁ ሙክክ ያላችሁ እንደሆናችሁ አውቃለሁ። ታዲያ የዚህን ጊዜ ከእናንተ በበለጠ የሚተጋ ካልሆነ በስተቀር ለትዳር አታስቡት እያልኩ አይደለም። ነገር ግን ምንም እንኳን አንቺ በመንፈሳዊ ብስለት እና እውቀት ከእርሱ የተሻልሽ ብትሆኚም፣ እርሱም አብሮሽ ለማደግ ፍላጎት ያለው፣ ከጌታ ጋር ያለሽን ሕብረት የሚያበረታታ እና በዛ መስመር ውስጥ ያለ መሆን አለበት። ካልሆነ ግን እኔ ቀይረዋለሁ ብሎ ትዳርም ሆነ ጓደኝነት አይጀመርም። ከፈለግሽ ከቀየርሽው በኋላ ለጓደኝነት ልታስቢው ትችያለሽ።

እንደሁል ጊዜው ይህ እኔ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ብዬ ማምነው ምልከታዬ ነው እንጂ ዶግማ አይደለም። ስለዚህ ለአስተያየት እና ለውይይት ክፍት ነው።

😎ክበሩልኝ።

•√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

08 Oct, 19:25


🥹አይዟችሁ

'እኔ ያረገዝኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው።''
~~~
“አንድ ዘመን ዝሆን እና ውሻ በአንድ ጊዜ ፀነሱ ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ደግሞ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ደግሞ ሌላ ዘጠኝ ወር ፤ሌሎች አስር ቡችላዎችን ወለደች፡፡ የውሻዋ መውለድ ቀጥሏል፡፡ በ 18 ኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆን ቀርባ ጥያቄ ጠየቀች ፤ “እርግጠኛ ነዎት እርጉዝ መሆንዎን ዝሆን? በተመሳሳይ ቀን እርጉዝ ሆነን እኔ ደርዘን ቡችላዎች ሦስት ጊዜ ወለድኩ እናም አሁን ትላልቅ ውሾች ሆነው አድገዋል ፣ ግን አሁንም እርስዎ እርጉዝ ነዎት ፡፡ ምን አየተካሄደ ነው? ዝሆኗ መለሰች: - “እንድትገነዘቢ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፤ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው ፡፡ እኔ የምወልደው በሁለት ዓመት ውስጥ አንድ ብቻ ነው፡፡ ልጄ መሬቱን ሲረግጥ ፍጥረት ይሰማዋል ፡፡ መንገዱን ሲያቋርጥ የሰው ልጆች ቆም ብለው በአድናቆት ይመለከታሉ፡፡ የተሸከምኩት ትኩረት ይስባል፡፡ ስለዚህ እኔ የምሸከመው ነገር ታላቅ እና ታላቅ ነው ፡፡

አንዳንዶች ለጸሎታቸው መልስ ቶሎ ሲቀበሉ የሌሎቹ ደግሞ ይዘገያል ። ያንተ የዘገየው ግን እመነኝ እግዚአብሔር ትልቅ ነገርን ለመሰጠት አጭቶሀል ማለት ነወ። በመዘግየቱም ተስፋ አትቁረጥ ፡፡ በሌሎች ስጦታ አትቅና ፡፡ የራስህን በረከቶች እስክትቀበል ድረስ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ለራስህም እንዲህ በል“የእኔ ጊዜ ይመጣል እናም በምድር ላይ ሲራመድ ሰዎች በአድናቆት የሚመለከቱት ዝሆን አይነት በረከት እገኛለሁ" ያ ግን ቶሎ አይሆንም ፅናት ያስፈልጋል፡፡
ፅናት!
አይዞህ!!


•√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

05 Oct, 18:43


             🤔ምክር ቢጤ!!
             

1- ከመጥፎ ጓደኛ ተለዩ
▪️የቅርብ ጓደኛ የትዳር ጓደኛ መሆን አለበት ።
▪️የትዳር ጓደኛችሁን ትታችሁ ከመጥፎ ጓደኛ ጋር አብራችሁ የምትውሉ እና የምታመሹ ከሆነ ከነሱ መጥፎ ባህሪይ ወይም ፀባይ ትቀስማላችሁ። ስለዚህ ከነሱ ተጠንቀቁ ቢቻልም እራቁ  (1ኛ ቆሮንቶስ 15:33 2ቆሮንቶስ 6:17)በሩቁ ያዙዎቸው ማለት ነው

2- የተቃራኒን ፆታ ሁለት እና ሦስት ጊዜ ከማየት ተጠንቀቁ። ለምን ብትሉ የመጀመሪያው ማየት ማን እንደሆነ ለማወቅ ነው ። ይህ አይነት ማየትን ማንም ማስቀረት አይችልም ። ሁለተኛው እና ሦስተኛው አጥብቆ  ማየት ግን ነገር የሚስከትል ስለሆነ ተቆጠቡ ። ስለዚህ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ 5:27-30 ላይ"ወደሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮል ያለው "። በተጨማሪ  ሮሜ 3:11-18 አንብቡ።

3- ንግግራቹን በልክ አድርጉ
▪️የአሮጊቶችን ተረትየመሰለ (1ኛ ጢሞ ፡ 4:7  2ጢሞ 2:16) እንዲሁም መጥፎ የልጆች ቀልድ መስማትም ሆነ  ወይም መልሶ ከማስተጋባት ተቆጠቡ (1ቆሮ 15:33)።

4- ስለልብሳችሁ እና ጌጣችሁ ተጠንቀቁ
▪️ከልክ በላይ ማጌጥ እና ማስጌጥ ለናተም ሆነ ለሌላው ወጥመድ መሆኑን አትዘንጉ። አለባበሳችሁ እና አጋጌጣችሁን በውስጣችሁ ያለው መንፈስ ቅድስ እንዲቆጣጠር ፍቀድለት።(1 ጴጥ  3:3-4) የውጪ ቁንጅናን ሳይሆን አጥብቃችሁ የውስጥ ቁንጅናን ፈልጉ ። ከሰው በላይምሆመሆንንም  ከሰው በታች መሆንን አትፈልጉ። አባባላቹ በልክ ይሁን (ፊልጵ 4:11-13)።

5- የምታነቧቸውን መፅሐፍ ስትመርጡ ተጠንቀቁ!!
▪️ሰው አብኛውን ጊዜ የሚመስለው የሚያደርገውን ፣የሚያየውን እና የሚሰማውን ስለሆነ ፣የምታነቡት መፅሐፍ ውስጣዊ ህይወት የሚያቆሽሽ ሊሆን ስለሚችል የምታነቡትን መፅሐፍ በጥንቃቄ ምረጡ።

6- ከተቃራኒ ፆታ ጋር መላፋትን (መዳራትን) አትልመድ!!
▪️የራሳችሁ ካልሆነ ተቃራኒ ፆታ ጋር ከመሆናችሁ በፊት ወደ ፈተና አታግባን ብላችሁ ፀልዩ። ፀሎት ወደ ፈተና ላለመግባት ይረዳናል ። የእግዚአብሔር ጥበቃ ይመጣላችኋል ። ሰው እየፀለየ ሀጢያት አይሰራምና ። ከሁሉም የሚመረጠው ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለብቻ አለመሆን ነው ። በራስ ጥበቃ ከመረዳት በተጨማሪ ከሌሎች ሀሜትም ያድናል ።
(ገላትያ 9:19-20)
7- ብዙ ጊዜያችሁን በእግዚአብሔር ቃል አለማሳለፍ ፣ አለማንበብ!!
▪️ ኢያሱ 1:8:-9 በየ ቀኑ የእግዚአብሔርን ቃል መፅሐፍ ቅዱስን አንብብና ያነበብከውን ወይም የሠማኸውን ቃል አሰላስል።
   መዝ (119):11-16 ተመልከት።
ዮሴፍ ከጲጥፋራ ሚስት ፈተና ያመለጠው እና ትቶ ሸሽቶ የሄደው ከአባቱ የሰማውን የእግዚአብሔር ቃል በማሰብ እና እግዚአብሔር ማሳዘን አልፈልገም በማለቱ ነው ።እኛም በእምነት ክርስቶስ በልባችን ፣ በኑሮአችን ካለ ትዕዛዙን እንጠብቃለን  (ዮሐ 14:15) በየቀኑ የእግዚአብሔር ቃል ማንበብ አለብን ።

8- ከሚያሰክር መጠጥ ተጠበቁ
▪️ሰዉ የሚያሰክር ነገር ከወሰደ ራሱን መቆጣጠር ወይም ስላለበት ሁኔታ ማስተዋል ይሳነዋልና::
9- መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጓደኛኞች  ይኑራችሁ::

  በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ የታቀፋችሁ ሁኑ ። በቤተ ክርስቲያንም ልዩ ልዩ አገልግሎት ስለሚኖር ተሳተፉ  (ሮሜ 12:1፣2)
▪️ በቤተ ክርስቲያን ፅዳት ተሳተፉ
▪️በሰንበት ትምህርት ቤት
አስተምሩ
▪️በምስክርነት ቡድን ውስጥ ተሳተፉ
▪️በመዘምራን መሪነና አገልግሎት ተሳተፉ
▪️በፀሎት ቡድን ውስጥ በመግባት አገልግሎት ስጡ
▪️በድቁና አገልግሉ
▪️በማስተናገድ አገልግሉ
▪️በሴቶች ኮሚቴ መሪነት አገልግሎት አበርክቱ
▪️በወጣቶች ኮሚቴ መሪነት አገልግሉ
▪️ በሽምግልና አገልግሉ
▪️በወንጌላዊነት (በሰባኪነት) እና በሌሎችም በማስተማርና የማማከር አገልግሎቶች ውስጥ መግባትና ማገልገል አለባች ሁ::
▪️ለሰይጣን ስፍራ አትስጡ፡ ለእግዚአብሔር ወንጌል አገልግሎት ጊዜ ስጡ። ጌታ ጋብቻችሁን ይባርካል።
▪️በጌታ የፀኑትን አማኝ ጓደኞችን በጥንቃቄ ፈልጉና ያዙ ።
▪️ሰይጣን እንዳይፈትናችሁ ባልና ሚስት አብራችሁ ኑሩ እንጂ ተለያይታችሁ ወይም በተለያየ ቦታ አትኑሩ።

•√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

05 Oct, 16:54


https://youtu.be/Ez_9oDLGHAc

Christian Mindset

03 Oct, 12:56


#እኔ ምለው እዚህ ቤት #ያዕቆብ #የለም እንዴ?????????
  *,*
  
   በብዙ የቀድሞ የክርስቲያኖች ቤት ውስጥ ልማድ እንደሆነው  ሁሉ እኛም ቤት ሊጠይቀን የመጣ አማኝ እንግዳ ከጥቂት ጭውውት ቦኋላ ቃል እንዲያካፍለን መጽሐፍ ቅዱስ ይሰጠዋል።
                       አንድ ቀን በጣም የማከብረው የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ ሊጠይቀን መጣ።
       ልጆች መጠበቅ ከጓዳ ስራ ጋር ተዳምሮ ቢያባክነኝም ጥቂት ካጫወትኩት ቦኋላ በቤትና በጎረቤት ያሉትን ሁሉ ሰብስቤ ቃል እንዲያካፍለን መጽሐፍ ቅዱስ ሰጠሁት።
               ጊዜው ሁለተኛ ልጃችን በእግሩ መሄድ ጀምሮ ቤቱን በአንድ እግሩ ያቆመበት፣ ያገኘውን እቃ የሚሰብርበት፣ያገኘውን መጽሐፍ ላይ የሚቸከችክበት፣ ካሻው ድምጽ ሳያሳማ የሚቀድበት ጊዜ ነበር............ሆኖም ለአገልጋዩ የሰጠሁት መጽሐፍ ቅዱስ የልጃችን የመቅደድ አደጋ ሰለባ መሆኑን ፈጽሞ አላወኩም ነበር።
         አገልጋዩ የሰጠውትን መጽሃፍ ቅዱስ ይዞ ቆመና የሚናገርበትን ክፍል ለማውጣት ያገላብጥ ጀመር።
     በቤት ውስጥ የነበርነው ሁላችን በፊቱ ተኮልኩለን ካሁን ካሁን ይጀምራል በማለት አይን አይኑን እያየን አንጠብቃለን።
      እሱ ግን የያዘውን  መጽሃፍ ቅዱስ አንዴ ወዲህ አንዴ ወድያ ማገላበጡን ስራዬ ብሎ ተያያዘው..........በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀቱ የማልደራደርበት የበሰለ አገልጋይ ስለሆነ እንዲህ የሚያገላብጠው ሊናገር የፈለገው ክፍል ጠፍቶት ነው?🙄 ብዬ ማሰብ አልቻልኩም ።
           ከጥቂት ቆይታ ቦኋላ ማገላበጡን ትቶ መጽሃፍ ቅዱሱን ዘጋና.................ግራ በተጋባ ስሜት ፣ በለሰለሰ ድምጽ  " #እኔ #የምለው እዚህ ቤት #ያዕቆብ የለም እንዴ ??????
         ሲል ጠየቀ።
ለካ ሊናገርበት የፈለገው ሀሳብ የያዕቆብ መልዕክት ላይ ያለ ሆኖ መልዕክቱን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲያጣው ማመን ተስኖት ነበር አንዴ ወደ ግራ አንዴ ወደቀኝ ሲያገላብጥ የቆየው።
           ዳሩ እጁ ላይ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ልጃችን እንዳጋጣሚ የያዕቆብን መልዕክት በመለየት ገንጥሎ ያወጣበት ነበር።
         በዚያው "የያዕቆብ መልዕክት በቤታችን ይኑር!" በሚል ተግባራዊ ክርስትና ሰብኮንና ጸልዮልን ሄደ።
            #የያዕቆብ መልዕክት ከአዲስ ኪዳን መልዕክቶች ሁሉ ልዩ የሚያደርገው #እምነት ላይ ብቻ ሳይሆን #ስራ ላይ ፣ #ንግግር ላይ ብቻ ሳይሆን #ተግባር ላይ፣  #ፀጋ ላይ ብቻ ሳይሆን #ሥነ-ምግባር ላይ የሚያነጣጥር #ውጤት ተኮር መልዕክት መሆኑ ነው።
   👉  ጸሃፊ:ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን
   👉የመጽሐፉ ዕርስ:እፎይ-ታ ሳልሳይ
   👉  ገጽ:132
•√ Christian Mindset •√
   @christian_mind_set
   @christian_mind_set

Christian Mindset

20 Sep, 18:33


አንድ ወቅት  አንድ ባልና ሚስት  በየቀኑ  ይጣላሉ ።

ከዚህም   ለመታረቅ  ሽማግሌዎችን  ይጠራሉ ።

ባል ችግሩን  ለሽማግሌዎች  አስረዳ ።

ሚስት የራሷን  ችግር ዘክዝካ በሽማግሌዎች  ፊት ተናገረች።

አንዱ ጥበበኛ  ሽማግሌ  እንዴህ አሉ ሁለታችሁም  ችግራችሁን ተናግራችኋል ፤ አስቲ አሁን ደግሞ መልካም ጎን የሆነውን  ብቻ ተናገሩ  በማለት ጊዜ ሰጡአቸው ።

ሁለቱም  ለመናገር  ረዥም ስዓት  ተገደረደሩ።( ወሰደባቸው )

ሽማግሌዎች  ሚስት  የባልዋን መልካም  ጎን እንድትናገር  ዕድል  ሰጧት።

ሚስት  መናገር ስትጀምር  እርሱማ ...እ...እ ጀግናዬ  ነው!ጉበዝ

ነው!   ብርቱ ለቤቱ ሟች ያገኘውን  ይዞ ለቤቱ የሚመጣ  ጠንካራ

ሰው ነው።እ...እ...ርሱማ የሚያስፈልገውንን  የሚያሟላልን፤

ከሰው በታች እንዳንሆን  ቤቱን የሚደግፍ  ጀገና ነው! አለችና

ታዲያ ምን ያደርጋል  ስትል

ሽማግሌዎች ያልሺው ይበቃል  ብለው አስቆሟት።

ባል ፈገግ  አለ ፤ ፊቱ ላይ ውስጣዊ ደስታ እየተነበበት።

አንዱ ሽማግሌ  በል አንተ ደግሞ በተራህ ተናገረ  እንጂ አሉት

አይ...አይ...አይ...ተውኝ  እስቲ አለ። የደስተኝነት ፊት እያሳየ።

ግድ የለም  ተናገር አሉት ሽማግሌው

ባተሌ ናት ከጠዋት  እስከ  ማታ ለትዳሯ የምትባዝን። ነጋ ጠባ ሩጫ  ለልጆቿ ሟች ቤቷን የምትሠራ  ቁምነገር ዐዋቂ ወይዘሮ ደርባባ ደግሞስ  ቁንጅናዋስ ቢሉ የቀይ ዳማ መልከኛ  ናት እንዴት  እንደምወዳት እኮ  ግን ምን ዋጋ አለው  ሲል

ሽማግሌው በቃ በቃ አሉ።

ሚስት  በቧላ ንግግር  በጣም ቀመደስቷ ፊቷ ፈገግ አለ። ከተቀመጠችበት  ብድግ ብላ ሆሌ እንዲህ አትልም  ነበር በል  ተነሥ ወደ ቤታችን እንሄድ  ብላ ሽማግሌዎችን አመስግነው  በሰላም  ሄዱ
  
   @christian_mind_set

Christian Mindset

28 Aug, 17:14


♨️ ኢየሱስ አትፍረዱ ሲል ምን ማለቱ ነው? አማኞች ሞራላዊ ፍርድ ልንሰጥ አይገባምን? የዚህን ጥያቄ ምላሽ ከታች ባለው ቪዲዮ ሊንክ ያገኛሉ፡፡

👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/Ez_9oDLGHAc

〽️aranatha Digital Network
å @Maranatha_MDN å
.| @Maranatha_MDN2 |.

Christian Mindset

26 Aug, 08:22


ሰላም ❤️ቤተሰብ + እንደምን ሰነበታችሁ፣ እስኪ ይህን ጽሁፍ ታነቡ ዘንድ ጋበዝኩ!!

♨️የክርስትና ሕይወት እድገት #መጨረሻ #መቋጫ #ማቆምያ #ማብቂያ #የለውም። ሁል ጊዜ #የማያቋርጥ እና #የሚቀጥል ነው።እኔ #አድጌአለሁ #ትምህርት #ጸሎት #ምክር #ቃል #ማጥናት #ቃሉን #መማር #በቃኝ የሚባልበት #ጊዜ #አይመጣም።

▫️ የክርስትና ህይወት እድገት ከውስጥ ወደ ውጭ የሚደረግ እንጂ ከውጭ ወደ ውስጥ የሚደረግ አይደለም፤ በውስጥህ ታድጋለህ እድገትህም ወደ ውጭ ይገለጣል።

♨️እናቶች ሲጸንሱ ጽንሱ በውስጥ እንደሚያድግ እድገቱ ግን ለሰው ሁሉ በግልጽ እንደሚታይ እነርሱም መጸነሳቸውን እኛም በእነርሱ ሆድ መግፋት እንደሚናውቀው፤

▫️ የክርስትና ሕይወት እድገት እንዲሁ ነው፤ እድገት የተመጣጠነ ለውጥ እንጂ በአንድ ነገር ብቻ የምታድግበት ሾጣጣ፣ ሞላላ መሆን አይደለም።

♨️ የክርስትና ህይወት እድገት ደግሞ የሌላ የምንም አይደለም የአስተሳሰብ እድገት ግሪኩ "#ኢኘግኖሲስ" የሚለው እውነተኛ እና ጥልቅ፣ግልጽ፣ቅርብ እውቀት ነው።(ቆላ1:10-11፣ኤፌ 1:17)

▫️ በክርስትና የምታድገው በክርስቶስ ውስጥ ያለ ሀሳብ ባንተ ውስጥ እስኪኖር (ፋልጱ 2:5)፤ወደ እርሱ ፍጽም ሙላት እስክትደርስ(ኤፌ 3:18-19) ነው፤የአስተሳሰብ እድገት የሚጀምረው አዲስ አዕምሮ በክርስቶስ እንደተሰጠህ ስታውቅ ነው። ስለዚህ ለእድገቱ መሰረት የሆነውን ተንኮል የሌለበትን የቃሉን ወተት(1ኛ ጴጥ 2:2-3) ቀን ከሌሊት መመገብ ያስፈልጋል።

•√ Christian Mindset •√
@christian_mind_set
@christian_mind_set

Christian Mindset

04 Aug, 08:13


🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
       #ስዊፍት እና #አቢ
       [ካንሰርን እምቢ !!]
#ስዊፍት ከ 7ኛ ክፍል ጀምሮ ነበር በካንሰር ህመም መሰቃየት የጀመረው::ቤተሰቦቹ በብዙ ነገር በመርዳት ሁሌም ከጎኑ አይለዩም ነበር::ታድያ አንድ ቀን ጠዋት ሲነቃ ቤተሰቦቹ ፍፁም ያልጠበቁትን ነገር ይጠይቃቸዋል::ለሁለት አመት በእጮኝነት አብራው የቆየችውን #አቢን ማግባት እንደሚፈልግ::ታድያ ይሔን የሰሙት የሆስፒታሉ ሰራተኞች እና ቤተሰቡ ማቀድ ይጀምራሉ:: #ስዊፍት የሚታከምበትን ክፍል ለሰርግ እንዲሆን አድርገው ዲኮር አደረጉ::ካሜራ እና ቪዲዮ የሚቀርፅ ሰው አዘጋጅተው #ስዊፊት የዚህ ምድር ኑሮው ሳያበቃ ሚስቱ እንድትሆን ከሁለት አመት በፊት አጭቷት ያስቀመጣትን #አቢን ይዘውለት ሊመጡ ሁሉንም ነገር ጨረሱ::
#ስዊፍት ይህን ሁሉ ሲያደርጉ ብዙ የሚያውቀው ነገር አልነበረም::
ከቀናትበሁዋላ አንድ ሌላ ክፍል አስገብተው ልብሱን ቀይረው በሽታው በጣም ስለጠናበት መንቀሳቀስ ስለማይችል ከነአልጋው እየገፋት ወደ ለመደው ክፍሉ እየገፋት ሲወስዱት #ስዊፍት አንዳች መልካም ነገር እዲፈጠር አምኖ ዙርያውን በጉጉት ይቃኝ ነበር::ወደ ክፍሉ እየቀረበ በመጣ ቁጥር ለየት ባለ አለባበስ የሚያያቸው  የቤተሰቡ አባላት ጥርጣሬው ልክ እንደነበር አረጋገጡለት::በሆስፒታሉ ያሉ ሰራተኞች ሌላ ታካሚ የሌለ እስኪያስመስልባቸው ነፍስን በሚያድስ ፈገግታ ይመለከቱታል::ትንሽ እየገፋት ሲያስጠጉት የክፍል ጓደኞቹ የተለየ አቀባበል አደረጉለት::አሁን #ሲዊፍት ያቺን "ከነፍሴ አፈቅርሻለሁ!!" ሲላት የነበራትን በነፍሱ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ሆኖ ሆስፒታሉን ከሞሉ ህዝብ መሀል #አቢን መፈለግ ጀመረ::ብዙም ሳይለፋ ነበር ከጎኑ የነበረው የቸርቻቸው ፓስተር ነካ አድርጎት ፍፁም አምራና አሸብርቃ ቃሏን አክብራ በሽታውን በሚያስረሳ ፈገግታ ታጅባ ወደ እሱ የምትመጣውን #አቢን የጠቆመው::በሽታው አልጋ ላይ ባያስተኛው #አቢን በሩጫ ሄዶ እቅፍፍ ቢያደርጋት ምንኛ ደስ ባለው::ደስታው በቃል የሚገለፅ አልነበረም:: አጠገቡ ቆማ የነበረችውን እናቱን በምስጋና እና ፍቅር ባዘለ እንባ ታጅቦ ቀና ብሎ አያት እናቱም አለሁልህ ከዚህ በላይ የሚገባክ ነክ በሚል እይታ እያየችው ትከሻውን ነካነካ አደረገችለት::
ወዲያው ሁሉም ከተሰበሰቡ በዋላ ፓስተሩ ንግግሩን ጀመረ::
"በመጀመርያ የማሳይህ ነገር አለ::" ብሉ አጠገቡ ያለውን መጋረጃ ገለጥ አደረገ:: #ስዊፍት ከሆስፒታሉ ውጪም ሰርጉን ሊታደም የመጣ ሰው እንዳለ ሲያይ በጣም ደስስ ተሰኘ:: ፓስተሩ ቀጠለ "የሰርጋቹን ቅለት በጣም ወድጄዋለሁ::ጋብቻ  እግዚአብሔር በሚገኝበት የተወሰኑ ሰዎች  ባሉበት የሚደረግ ሲሆን አንተ ደግሞ ለዚህ እድል የታጨክ ነክ::ከብዙ ጊዜ በፊት ጀምሮ የሰው ልጅ በተለያየ ሁኔታ እና ቦታ የሰርግ ስነ ስርዐት ሲፈፅም ቆይቷል:: ለዛ ሁሉ ግን ትርጉም የሚሰጠው እግዚአብሄርን ማወቅ እና የእርሱ መገኘት ነው::እኛ ያለንበት ሁኔታ ጥሩም ይሁን መጥፋ እግዚአብሔርን ሊያግደው አይችልም:: ደስታ ሊኖር አይችልም በሚያስብል ሁኔታ ውስጥ ሆነን እንኳን ፍፁም ሰላም እና ደስታ ይሰማናል::" በዚህ ንግግር በየመሀሉ የአረፍተነገሩን መጨረስ እየጠበቀ ከአልጋው ላይ ሆኖ አንገቱን በአዎንታ የሚነቀንቀው #ስዊፍት ከግማሽ በላይ ታዳሚዎችን በእንባ እንዲያዝ አደረገ:: "እኔ ምለውን ከእኔ በመቀጠል ትደግመዋለክ::" የፓስተሩ ንግግር ነው:: "በዚህ ቀለበት...."  #ስዊፍት ደገመ አጠገቡ የቆመችው #አቢ ደስታዋ ምንም አልቀነሰም:: "እስከ ህይወቴ ፍፃሜ ላልለይሽ ሚስቴ አድርጌሻለሁ::" ቀለበቱን አንስቶ አጠለቀላት:: #አቢም በተራዋ ቃለ መሀላውን ፈፅማ ቀለበት ጣቱ ላይ አጠለቀችለት:: አሁን ህልማቸው እውን ሆነ::እነዚህ ሁለት ፍቅረኛሞች ባል እና ሚስት ከመሆን በሽታው አላገታቸውም::በሁለቱም ዘንድ ፍፁም ደስታ ይነበብ ነበር::

    👉    "ፍቅር ታማኝ ነው!!! "
    👉    "ፍቅር ተስፋ አይቆርጥም!! "
    👉    "ፍቅር ሁሌም አሸናፊ ነው!!"
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

"ትርጉም ያለው ፍቅር ምንጩ ክርስቶስ ነው!!"

•√ Christian Mindset •√
@christian_mind_set
@christian_mind_set

Christian Mindset

04 Aug, 08:13


#ስዊፍት እና #አቢ
       [ካንሰርን እምቢ !!]

Christian Mindset
@christian_mind_set
@christian_mind_set

Christian Mindset

01 Aug, 13:00


☹️ጥያቄ አለኝ ?

▫️Jx እባላለሁ ጥያቄ ነበረኝ በቤተክርስቲያናችን የወጣቶች አስተባባሪ ነኝ እጮኛ መያዝ እፈልጋለሁ ግን በህይወቴ ምንም አይነት ጥያቄ ቀርቦልኝ አያውቅም ጓደኞቼ ብሎም ታናናሾቼ ጭምር እጮኛ ይዘዋል ቀናት በሄዱ ቁጥር ፍርሀቴ እየጨመረ መቷል እውነተኛ እጮኛ ለማግኘት ምን ላድርግ?

መልስ

▫️ፍርሀትሽ ጤናማ ፍርሀት ነው እውነተኛ እጮኛ ለማግኘት:-

1) ከስጦታው በላይ ሰጭው ላይ ትኩረትሽን አድርጊ ምክንያቱም ስጦታው የሚመጣ ከሰጪው ነውና ስለዚህ ከጌታ ጋር ያለሽን ህብረት አጠንክሪ ብዙ ክርስቲያኖች በቅጡ ከጌታቸው ጋር ፍቅር ሳይዛቸው (የፀሎት🙏 እና የቃሉ ሕይወት ) ሳይኖራቸው እግዚአብሔር የሚከብርበትን የፍቅር ህይወት ፈልገው ይጀምራሉ መጨረሻቸውም የልብ ስብራት ይሆናል::

2) በፀሎትሽ🙇‍♀ ወቅት ሁሌም እውነተኛውን ጓደኛ ጌታ እንዲሰጥሽ ጌታን ጠይቂው እርሱ ቸር ነውና በጎውን ነገር ያደርጋል::

3) በአቅራቢያሽ ያሉ ወንድሞችን🙎‍♂ ሁሉ ጋር ተመሳሳይ እና ልዩነት የሌለው አቀራረብ አይኑርሽ::

4) በምትችይው ልክ ተግባቢ የማትከብጁ ፊትሽ የማይጨማደድ ለመሆን ሞክሪ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አትኮሳተሪ🙂)

5) በቤተክርስቲያን , በትምህርት ቤት, በስራ ቦታ ካሉ ወገኖች ጋር ያለሽን ንግግር + መቀራረብ አጠንክሪ በተለይ (በቤተክርስቲያን⛪️ )

6) ለሰይጣን ክስ እና ወቀሳ ቦታ አትስጪ አንቺ የእግዚአብሔር መለኮታዊ አጀንዳ የሚፈፀምብሽ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የምትኖሪ የተመረጥሽ ሴት🙍‍♀ ነሽ ምንም ሰይጣን ዋጋሽን አራክሶ ቢጠራ የማይለወጠው እውነት የተገዛሽበት ዋጋ ውድ ነው፤ ምንም ማድረግ አይቻልም::

7) በመልካምም ሆነ በክፉ አስበው ሀሳብ በሚሰነዝሩ ወገኖች አትደናበሪ ያንቺ ፍጥነት ሆነ መዘግየት በእግዚአብሔር ፍቃድ ላይ እንጂ በሰዎች🧍‍♀🧍🧍‍♂🕺 ሀሳብ ላይ አይመሰረትም ይህን ስል የወገኖችን ምክር አትስሚ እያልኩ አይደለም።

8) እግዚአብሔር ለሚያመቻቻቸው የተለያዪ የትውውቅ አጋጣሚዎች ንቁ👀 ለመሆን ሞክሪ ችላ አትበያቸው።

9) እውነተኛ እጮኛ ከመፈለግሽ በፊት እውነተኛ እጮኛው ለመሆን ተሰሪ ( መፅሐፍትን ማንበብ📚 + በትዳር ውስጥ ካሉ ሰዎች ልምድ መቅሰም + ምስክነቶች መስማት +ለእራስሽ ጊዜ🕙 መስጠት (መንከባከብ ) + ከሚበልጡ ሽ ሰዎች ጋር መዋል )።

😐ቤተሰብ + በጥቂቱም ቢሆን የመለስኩ ይመስለኛል በመጨረሻ ግልፅነትሽን ሳላደንቅ አላልፍም የብዙ እህቶችን ፍረሀት እና ጥያቄ ነው የጠየቅሽው በቀጣይ ስትወጪ በምስክርነት እንደሚሆን አልጠራጠርም::

ፀጋ እና ሰላም ይብዛልሽ!!

•√ Christian Mindset •√
@christian_mind_set
@christian_mind_set

Christian Mindset

31 Jul, 10:44


#ሃይ_ባይ_ያጣው_ፌሚኒዝም

♨️ሀሳቦን እርሶም በcomment ያስፍሩ

•√ Christian Mindset •√
@christian_mind_set
@christian_mind_set

Christian Mindset

30 Jul, 12:14


"ሃይ ባይ ያጣዉ ፌሚኒዝም!!"

♨️እንደማህበረሰብ በብዛት ከሚነወሩ ሃሳቦች ቀዳሚዉ ፌሚኒዝም ነዉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያዎች ቀዳሚ የመነጋገሪያ ጉዳይ ከመሆኑ አኳያ የሃሳቡ ቀዳሚ አቀንቃኞች በተደጋጋሚ "ፈሚኒዝም የሚጠላዉ በያዘዉ ሃስብ ሳይሆን ሰዉ ስለፍልስፍናዉ ባለዉ የተዛባ መረዳት ነዉ" ሲሉ እንሰማለን። ይሄ ምን ያህል እዉነት ነዉ? ሃሳቡን ልክ አይደለም ብሎ እንደሚያምን አንድ ሰዉ ፌሚኒዝም ለምን መነቀፍ አለበት ከምልባቸዉ ምክንያቶች ቀዳሚዉን በዚህ ጹሁፍ በጥቂቱን ለማቅረብ እሞክራለሁ።

GENDER ROLE ( ጾታዊ ሃላፊነት)

▫️ፌሚኒዝም ነባሩ ጾታዊ ስርዓት በወንድና በሴት መካከል ባለዉ ተፈጥሯዊ የአካልና ስነልቦናዊ ልዩነት ላይ መሰረት ማድረጉን ይክዳል። ታሪክን ብሎም አሁን ያለዉ የማህበርሰብ መዋቅር በጨቋኝ የአባታዊ ስርዓት የሚፈርጅበት መሰረታዊዉ ምክንያትም የጾታ ስርዓት የማህበርሰብ ፈጠራ ነዉ ብሎ መደምደሙ ነዉ። (Considering Gender as a social construct)

ይሄ ግን ልክ አይደለም። ሴትና ወንድ እንደሰዉ አንድ ቢሆኑም። የተለያየ የአይምሮ እና የአካል ተፈጥራዊ ባህሪ አላቸዉ። ፌሚኒዝም ያን አቅሎ በደምሳሳዉ ያየዋል።

ለምሳሌ - ሴቶች ከወንዶች ፍጹም የማይነጻጸር ሌሎች ሰዎችን የመረዳት ፣ ልጆችን nurture የማድረግ ጸጋ አላቸዉ። ወንዶች ደግሞ ከሴቶች የተሻለ አደጋ ለማጋፈጥ ዝግጁ የመሆን ( risk taking behaviors) ያን ለመጋፈጥ የሚያስችልም አካልዊ አቅም አላቸዉ። ከዉልደታቸዉ ጀምሮ ተፈጥሮ ለዛ ዝግጁ ታደርጋቸዋለች። ያ ብቻ ሳይሆን በ Aggression, Emotional Expression , በ Interest እና preference ይለያየሉ።

ያም ከወንድና ከሴት የሚጠበቀዉ ባህሪና ሃላፊነት የተለያየ ያደርገዋል። ባህል ደግሞ እሱን ያጸናል። እንጂ እንደነሱ መከራከሪያ ወንድ የተሻለ ሊደርግ የታሰበ ስርዓት ያመጣዉ ክፍፍል ስለሆነ አይደለም።

▫️ተፈጥሮ ለማንም ፍትሃዊ አልነበረችም። ዛሬ ላይ ከመድረሱ በፊት የሰዉ ልጅ ቀዳሚ ግብ በህይወት መትረፍ ነበር። የባህል ሃላፊነት ደግሞ የማህበርሰቡ ቀጣይነት ማረጋገጥ ነዉ። የአንድ ህብረተሰብ ቀጣይነት የሚረጋገጠዉ በጤነኛ እና ዉጤታማ ህጻናት ላይ ነዉ። በሌላ አማርኛ በጤናማ ትዳር ላይ። ያን ማድረግ የሚያስችለዉ ብቸኛዉ መንገድ ለሁለቱም ( ባልና ሚስት) ተፈጥሯቸዉ የተስማማዉን ሃላፊነት ሲጫሙ ነዉ። ማህበርሰብ እንደሚለዉ ወንድ የወንድን ሃላፊነት ሲይዝ ( protector and provider ) ፣ ሴት የሴትን ሃላፊነት ስትይዝ ( Caring and Nurturing)።

እዚህ ጋር ግን በመግባባት ባል እና ሚስት በትዳራቸዉ አንተ ይሄን አድርግ አንቺ ይሄን አድርጊ ተባብለዉ የሚስማማቸዉን ሃላፊነቶች ሊከፋፈሉ ይችላሉ። ማህበርሰብ ግን ማጽናት ያለበት ለሁለቱም ተፈጥሮ የሚስማማዉን ባህሪ ነዉ።

▫️ በጊዜ ሂደት የቴክኖሎጂ መምጣትና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዉ ሁነቶች መቀየር ተፈጥሯዊ ልዩነቶችን በሚቻል ደረጃ ለማጥበብ ሞክሯል። በቴክኖሎጂ ረገድ የወሊድ መቆጣጠሪያ ፣ የቤት ስራ አጋዥ መሳሪያዎች ፥ በኢኮኖሚዉ በአለም ጦርነቶች ምክንያት የሰራተኛ ወንዶች ማነስ ሴቶችን ወደ ስራ እንዲሰማሩ ገፍቷል። ( ልብ በሉ የአባትዊዉ ስርዓት ተጠቃሚ የተባሉት እነዚሁ ወንዶች ናቸዉ ወደ ሞት ቀድመዉ የሚጋዙት። Sadly we are still in that déjà vu as a country)። ወዲፊትም ተፈጥሯዊ ልዩነቶችን ማጥበብ ቢቻል የጻታዊ ሃልፊነቶች እየተቀየሩ ሊመጡ ይችላሉ።

ነገር ግን ስርዓተ ጾታን ከተፈጥሮ ለይቶ ማየት ማህበራዊ መሰረቶችን የሚንድ ግልብ አስተሳሰብ ነዉ። ጾታዊ ሃላፊነቶች የምንረዳበት መነገድ ( ወንድ ማለት እንዲ ነዉ ፣ ሴት ማለት እንዲ ናት የምንለዉ ) የአንድ ህብረተሰብ የባህል እና የማንነት እምብርት ነዉ። እነዚህን ሚናዎች ማወክ ማህበራዊ ትስስርን ሊያዳክም እና የጋራ ማንነትን ወደ ማጣት ሊያመራን ይችላል።

▫️ደሞም የፌሚኒዝም ጾታን ከስርዓተ ጾታ ( sex and gender) ለይቶ የመረዳት ፍልስፍና "ሰዉ በተፈጥሮዉ አይደለም ወንድ ሴት የሚሆነዉ ራሱ መወሰን ይቻላል። ሁለት አይነት ጾታ ብቻ አይደለም ያለዉ" የሚሉ የግብረሰዶማዉያን እና የትራስን ጀንደር ሃሳቦች መንገድ የጠረገ ነዉ። ያ ደግሞ ባህልን ብቻ ሳይሆን ሰዉ የመሆንን መሰረታዉ እዉነቶች ነዉ የሚንደዉ።

ከሌላ ቦታ መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎበት የተወሰደ

ስለ ጉዳዩ የናንተንም ሀሳብ በcomment ላይ አስፍሩልን

√• Christian Mindset •√
@christian_mind_set
@christian_mind_set

Christian Mindset

28 Jul, 19:19


#በመንፈስ የመመላለስ ምስጢር
==========================

♨️እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት ማየት የሚፈልገውን ፍሬ ለማፍራት መንገዱ ሃይማኖታዊ ጥበብና ሰዋዊ ጥረት ሳይሆን በመንፈስ መኖርና መመላለስ ብቻና ብቻ ነው።

❄️መንፈሳዊ ድልን የምንቀዳጀው በየእለቱ ራሳችንን ለመለወጥ በምናደርገው ቁርጠኛ ውሳኔ እና ትግል ሳይሆን ራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ሃሳብ ስናስገዛ ብቻ ነው። ገላ 5:22-24,ሮሜ 8:14,ኤፌ 5:18

♨️እግዚአብሔር የጠራን እንድንኖርለት ሳይሆን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ እንዲኖር ነው። ክርስቶስ ወደ ህይወታችን የመጣው ከመሞት ብቻ ሳይሆን ከመኖርም ሊያድነን ነውና።
ገላ 2:20,ሮሜ 5:10

📌በክርስቶስ ኢየሱስ ላላችሁ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

🟩Christian Mindset🟩
@Christian_Mind_Set
@Christian_Mind_Set

Christian Mindset

25 Jul, 19:10


🤔 የተሳሳት አጥንት ማንሳት ? 🤔

😍 ሰላማችሁ ይብዛ ቤተሰብ + ከተወሰነ ቀናት በፊት ጭንቅላቴ ውስጥ አንድ ሀሳብ ያለማቋረጥ ይመላለስ ነበር። ይህም ሀሳብ ሰዎች ወደ ትዳር አለም ብሎም ወደ እጮኝነት ሲገቡ እንዴት የተሳሳተ የግራ ጎን አጥንት እንደሚያነሱ የሚያሳይ ነበር።

🤔በሰመመን 5 ወንዶች ከቀረበላቸው ስምንት(3 ትናንሽና 5 ትላልቅ) አጥንት መሐል በጥንቃቄ ሲመርጡ የሚያሳይ ነበር።  አምስቱ ወንዶች በመንፈሳዊ ህይወት ጠንካራ የሚባሉ ናቸው። ነገር ግን በጣም የበረቱ አልነበሩም። ወዲያው አጥንት እየመረጡ የማንሳቱ ሒደት ተጀመረ።

😶የመጀመርያው ወንድ ለምርጫ ከቀረበለት አጥንት መሐል ከትላልቆቹ አንድ አነሳ። ሁላተኛው፡ ሶስተኛው፡ አራቱም ወንዶች ከመጀመርያው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ውሳኔ ወሰኑ ሁሉም የመረጡት አጥንት ከትላልቆቹ መሐል ነበር። አምስተኛው ወንድ ግን ለራሱ እንዲህ ሲል ተናገረ 'ምንም እንኳን የመጨረሻው መራጭ ብሆንም መልካሙ ይደርሰኛል'ብሎ ከቀረበለት አጥንት መሃል ወደ ትንሿ አጥንት ተመለከተ። ነገር ግን ወደ ትንሿ አጥንት ሲጠጋ ልቡ ግን ከነዚያ ከአምስቱ የቀረውን ትልቁን አጥንት ለማንሳት ሸፈተ። 'እነዚህ ሶስት አጥንቶች አራቱ ጓደኞቼ ካነሷቸው ያንሳሉ። ስለዚህ ልክ አንደ ጓደኞቼ ትልቅ አጥንት ማንሳት አየቻልኩ ለምን ትንሽ አነሳለሁ?' ሲል ራሱን አሳምኖ ትልቁን አጥንት አነሳ። አሁን አምስቱም ወንዶች ከቀረበልቸው ሶስት ትናንሽ እና አምስት ትላልቅ አጥንቶች ሁሉ ትላልቆቹን መረጡ። በመጨረሻም እጃቸው ላይ ካለው ትላልቅ አጥንት አንድ እንከን አስተዋሉ። አጥንቶቹ የተሰነጠቁና በጣም የደረቁ ነበሩ። አጥንቱን አንደስጦታ ያቀረበላቸው ሰው በምርጫቸው ተገርሞ እያሾፈ ሳቀባቸው። ነገር ግን ሶስቱን ትናንሽ አጥንቶች እነሱ ባሉበት ሰበረና በውስጣቸው ህይወት እንዳለ አሳያቸው። "

🤔ታድያ ከነዚህ ሰዎች ምርጫ ይህን እውነት አስተዋልኩ። አራቱ ወንዶች በአጥንቶቹ ትልቅነት ተሸውደዋል። አምስተኛው ግን ከአጥንቱ ትልቅነት ይልቅ በብዙኃኑ ምርጫ ተሸውዷል።

💠 የህይወት አጋር በምንመርጥበት ወቅት አብዛኞቻችን ምንም በመንፈሳዊ ነገር በሳል ብንሆን ልባችን ወደትላልቆቹ አጥንት(ሃብታም፥ ቆንጆ፥ ዝነኛ ወንድ እና ሴት) ይሸፍታል። ገንዘብ ያላቸው ነገር ግን መልካም ስብዕና፥ ፍቅር የሌላቸው ከላይ የሚያሳዩን ገጽታ ብዙዎቻችንን ያስተናል። በእንደዚህ አይነት ምርጫ ላይ የተመሰረተ የፍቅር ግንኙነትም ሆነ ትዳር መጨረሻው ጸጸትና የማይጠገን ስብራት ነው።

💠 ማስተዋል ያለብን ግዙፍ ጭንቅላት ሁሉ በቅጡ ላያስብ እንደሚችል ነው። ስለዚህ ከየትኛውም ነገራችን በላይ አጥንታችንን ስንመርጥ ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።

💠በምንም ሆኔታ ሀብትን የትዳር አጋር መምረጫ መስፈርት አታድርጉ!!
   ❇️ ሀብት ብለው የተጋቡ ግን ሰላም አጥተው የተለያዩ አሉና!!
  ❇️ ፍቅርን ብለው የተጋቡ ሀብትን ያስከተሉ አሉና!!

💠 ውበትን እንደ ዋና የትዳር አጋር መምረጫ መስፈርት አያድርጉ!!
 
❇️ ጊዜያዊ መልክ ወቅቱን ጠብቆ ሲጠፋ የመሰረታችሁት ትዳር ደብዛው እንዳይጠፋ!!

❇️ ላስተዋለ ፍቅር ማንም ሊያስተውል የማይችል ውበት በጥንዶች መሐል ይፈጥራልና!!

😎 ፀጋ ይብዛላችሁ
kibreab_x
                         
Christian Mindset
^| @Christian_Mind_Set |^
^ | @Christian_Mind_Set |

Christian Mindset

25 Jul, 19:03


❤️የእውነተኛ ፍቅር መሰረት እግዚአብሔራዊ ፍቅር (አጋፔ) ፍቅር ስለሆነ የህንፃው ጥንካሬ በመሰረቱ ላይ ነውና እውነተኛ ፍቅር ከግለሰቦች ስሜት አለፍ ብሎ በዘላለማዊው በክርስቶስ ላይ ይደገፍል❤️

Christian Mindset
^| @Christian_Mind_Set |^
^ | @Christian_Mind_Set |^

Christian Mindset

24 Jul, 07:38


https://www.youtube.com/watch?v=7gVEwTC6d_M