አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN @addis_tv Channel on Telegram

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

@addis_tv


አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN (Amharic)

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN በቦሌ, አዲስ ወረሳ, ኢትዮጵያ ድጋፍ እና ኢንተርቡት መረጃዎችን ከፍተኛ ለማስተካከል ያስችለዋል። addis_tv በታላቅ የቴሌግራም ምርጫዎ ከታላቅ የቲቪ እና የንባቡቡን የማህፀን መረጃውን ተከትሎ ያገለግላል። አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN እናጀምሮ ኢትዮጵያውያን ለምንድን ምንም ወሬዎችን ማቅረብ እየተከፈለ በማለት እንደሚገኝ ለምን አስተዋወቅ? እንዲሁም የትኞቹን እና ትናንትዎቹን ጣልቃ ማህፀን መረጃዎች እና መዋብሪያዎች እንድናፈቅር በዚህ የቢሮ ምርጫ ላይ ደስታ ይመልከቱ።

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

15 Nov, 20:00


የስም ዝርዝሮቹ ብዛት ስላላቸው
በቀላል መንገድ ሚፈልጉትን ስም
ለማግኝት search 🔍 የሚለውን
በመጫን ሚፈልጉትን ስም ያስገቡ::

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

01 Apr, 14:06


500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ትግራይ ክልል ደረሰ

500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ በዛሬው እለት ትግራይ ክልል መድረሱን የአለም ምግብ ድርጅት ገለጸ።

ወደ ክልሉ በየብስ የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ እንቅስቀሴ መጀመሩን ተከትሎ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።

በዛሬው እለትም 500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ በድርጅቱና
አጋር አካላትአማካኝነት ወደ ክልሉ መድረሱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መንግስት በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ድጋፍ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል የግጭት ማቆም ውሳኔ ማድረጉና በየብስ የሚደረገው ድጋፍም እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወቃል።

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

31 Mar, 13:40


በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ ጀመረ

በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል የሰብዓዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የሰብዓዊ እርዳታን ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

ውሳኔው ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ የመድኃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ገንዘብና አልሚ ምግቦችን ረጂ ድርጅቶች በቻሉት መጠን በአየር ትራንስፖርት በየዕለቱ ማጓጓዝ መጀመራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል፡፡

በዛሬው ዕለትም በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል የሰብዓዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመራቸውን ነው ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በተሟላ ሁኔታ ለማስኬድ ከተባበሪና ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ዛሬም ቁርጠኛ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

31 Mar, 13:38


ከነገ ጀምሮ ለነባር እና ለአዳዲስ የሃይማኖት ቴሌቪዥን አመልካቾች ፈቃድ መስጠት ሊጀመር ነው

ከመጋቢት 23 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለነባር እና ለአዳዲስ የሃይማኖት ቴሌቪዥን አመልካቾች ፈቃድ መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ገለጸ።

ባለስልጣኑ በሃይማኖት ብሮድካስት ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ ውይይት እያደረገ ነው።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ፥ ቀደም ሲል በነበሩት የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ እና ህጎች መሰረት የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት ብሮድካስት እንዳያቋቁሙ ህጋዊ እውቅና እና ፈቃድ እንዳያገኙ ተከልክለው መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡

በህብረተሰቡ ዘንድ የሃይማኖት መርሃ ግብር በቴሌቪዥን ለመከታተል ከነበረው ፍላጎት ጋር በተያያዘ ሃገራዊ ለውጡን ተከትሎ የሃይማኖት ብሮድካስተሮች በህግ ዕውቅና እንዲያገኙ፤ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲውም ሆነ የአዋጅ ማሻሻያ በመደረጉ ባለስልጣኑ ፈቃድ አውጥተው እንዲንቀሳቀሱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋልም ነው ያሉት ።

በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሰረትም ከመጋቢት 23 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለነባርም ሆነ ለአዳዲስ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ፈቃድ አመልካቾች ፈቃድ መስጠት የሚጀምር መሆኑን ተናግረዋል።

በተደረገው ጥናት መሰረት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ50 በላይ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በስርጭት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፥ ጣቢያዎቹ ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ለተከታዮቻቸው አማራጭ የመገናኛ ዘዴ በመሆን እያገለገሉ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

በአንጻሩ ጥቂት የሚባሉ በሃላፊነት ስሜት እና በጥንቃቄ የማይንቀሳቀሱ የሃይማኖት ሚዲያዎች በመኖራቸው በሚያሰራጯቸው መረጃዎች ከህብረተሰቡ የሚደርሱ ቅሬታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ እንደሚገኙም አንስተዋል።

ከነዚህ ቅሬታዎች ውስጥም ከሕግ፣ ከሞራል፣ ከጤና ጋር የሚቃረኑ ንግግሮችን የማሰራጨት እና ሌሎች ሃይማኖቶችን የመንቀፍ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

በመሆኑም የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ለሃገር አንድነት፣ ለህዝብ መፈቃቀር ፣ አብሮነት፣ መረዳዳት፣ ሰላም እና መሰል በጎ ሃይማንታዊ ዕሴቶችን በማጠናከር የበኩላቸውን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

31 Mar, 13:30


የነዳጅ ስርጭት ችግር የሚፈጥሩ የነዳጅ ማደያዎችን እንደማይታገስ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በየጊዜው በሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት ዙሪያ በከተማው ካሉ የነዳጅ ማደያ ባላቤቶች ጋር የተወያየ ሲሆን በውይይቱ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንዳሌለ ነገር ግን ከስርጭት ጋር ተያይዞ እጥረት መከሰቱ ተገልጿል፡፡

ሆኖም ከስርጭት ጋር ተያይዞ አንዳንድ ማደያዎች የሚፈጥሩትን እንግልትና አሻጥር ፈር ለማስያዝ ጠበቅ ያለ እርምጃ እንደሚወስድና ብልሹ አሰራርን እንደማይታገስ መግለፁን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ÷ከስርጭት ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ማደያዎች የሚፈጠረው ብልሹ አሰራር የምርት ስርጭት ፈተና መሆናቸውን አብራርተው ፤ያልተገባ ጥቅም በመፈለግ እጥረቱን በሚያባብሱ የነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስረድተዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከልም የነዳጅ አቅርቦትን በማሳደግ እና ቁጥጥሩን በማጠናከር ሌሊት ነዳጅ በሚሸጡት ላይ የመጠን ማሻሻያ እንደሚደረግና በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ ማደያዎች እለታዊ መረጃን ለቢሮው እንዲያሳውቁ ማድረግ የሚያስችል አሰራር የሚዘረጋ መሆኑንም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በከተማዋ ከ134 የነዳጅ ማደያዎች 117 ማደያዎች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን ÷ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በፈጠሩና በምሽት በበርሜል ነዳጅ ሲሸጡ የተገኙ ሶስት ማደያዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ መቻሉን አቶ አደም ኑሪ ተናግረዋል፡፡

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

31 Mar, 09:00


በኢትዮጵያ በአሰላና ኢተያ አካባቢ የ50 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ሀይል ማመንጫ ግንባታ ለማከናወን የ100 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የቱሉ ሞዬ ሀገር በቀል ድርጅትና ሚትስቡሽ ኮርፖሬሽን ሲሆኑ ፕሮጀክቱ የሚከናወነው ከፈረንሳይ መንግስት በተገኘ ፈንድ ነው ተብሏል።

ከእንፋሎት የሚገኝ የሀይል አማራጭ ከአከባቢ ብክለት የፀዳና ዘላቂ በመሆኑ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያም በዘርፉ እምቅ ሀይል ስላላት ማልማት እንደሚገባ ተመላቷል፡፡

“የእንፋሎት ሀይልን በሀገራችን በስፋት መጠቀም እንፈልጋለን” ያሉት የማዕድን ሚንስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ አማራጭ የሀይል ምንጮችን ለማስፋፋት መንግስት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

የበለጸገችና ገናና ሀገር ለመገንባት የሃይል አቅርቦት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለዚህም መንግስት የሚቀጥሉትን 10 አመታት የሚያገለግል ፖሊሲ ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

ኢንጅነር ታከለ አክለውም በሀይል አቅርቦት ዘርፉ ላይ የግል ዘርፉ እንዲሳተፍ እንደሚፈለግና በዚህም መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

30 Mar, 12:26


በጥቆማ የተያዘ 46 ሺሕ ሊትር ዘይት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል ነው

በኅብረተሰቡ ጥቆማ በህገወጥ መንገድ በመኪና ተጭኖ የተያዘ ከ46 ሺሕ ሊትር በላይ ዘይት በመሰረታዊ ሸማች አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል መሆኑ ተገለፀ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር በመኪና ጥበቃ ላይ በተሰማሩ ነዋሪዎች ጥቆማ ከ2 ሺሕ 300 ካርቶን በላይ ዘይት ጭኖ የነበረ መኪና በኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል ተወርሶ በወረዳው መሰረታዊ ሸማች ማኅበር አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ሊከፋፈል መወሰኑን ወረዳው አስታውቋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ትዝታ ነጋሽ ኅብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ተግባራትን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

28 Mar, 17:56


ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው።

በአሜሪካ መንግስት መቀመጫ ‘ካፒቶል ሂል’ ፊት ለፊት እየተካሄደ በሚገኘው ሰልፍ ላይ ከአሜሪካ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በተጨማሪ ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳትፈዋል።

‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎች የኢትዮጵያን ሕልውና የሚጎዳ እንዲሁም የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት የሚያበላሽ በመሆኑ ሊሰረዝ ይገባል የሚል መልዕክት በሰልፈኞቹ እየተላለፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡

“ማዕቀብ መጣል ለኢትዮጵያ ጉዳትን እንጂ ምንም ጥቅም አያስገኝም ፤ ጎጂ የሆኑት ረቂቅ ሕጎች ውድቅ መደረግ አለባቸው” የሚሉ መፈክሮችም እየተላለፉ ነው።

በአሜሪካ የኮንግረስ አባል ቶም ማሊኖውስኪ (ኒውጀርሲ) ዋና አርቃቂነት፣ በያንግ ኪም (ካሊፎርኒያ)፣ ግሪጎሪ ሚክስ (ኒው ዮርክ)፣ ዴቪድ ሲሲሊን (ሮድ አይላንድስ)፣ ብራድ ሼርማን(ካሊፎርኒያ) እና ማይክል ማካውል (ቴክሳስ) ደጋፊነት የተዘጋጀው ‘ኢትዮጵያ ስታብላይዜሽን ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ አክት’ ወይም ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ በኮንግረሱ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ውይይት እንደተደረገበት የሚታወስ ነው።

የ‘ኤችአር 6600’ ተጓዳኝ ወይም አጋዥ (ኮምፓኒየን ቢል) የሆነው የኢትዮጵያ ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ ፕሮሞሽን አክት ኦፍ 2021’ ወይም ‘ኤስ.3199’ በአሜሪካ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርዚ) ዋና አርቃቂነት፣ በሴናተር ጀምስ ሪስች (ኢዳሆ)፣ በሴናተር ክሪስ ኩንስ (ዴልዌር) እና በሴናተር ቶም ቲሊስ (ኖርዝ ካሮላይና) ደጋፊነት የተዘጋጀ ነው።

የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ በ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕግ ላይ ነገ ውይይት እንደሚያደርግ ኢዜአ ዘግቧል።

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

28 Mar, 17:56


በሀገር ውስጥ የዘረ-መል ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር ተገለጸ

በሀገር ውስጥ የዘረ-መል (ዲ ኤን ኤ) ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እንደገለጹት ፥ አዳዲስ የፎረንሲክ ምርመራ ማሽኖችን ተቋሙ ወደ ሀገር አስገብቶ ጥቅም ላይ እያዋለ ነው።

በአስር ዓመቱ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ከአፍሪካ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት አንዱ ሊሆን በለውጥ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሰራሮቹን በቴክኖሎጂ እያዘመነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ከዚህ ቀደም ወደ ሌላ ሀገራት ተልኮ ይደረግ የነበረው የዲ ኤንኤ ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ይደረጋል ብለዋል።

ከቴክኖሎጂ ባለፈ ፖሊስ ውጤታማ ስራ ለመስራት ያስችለው ዘንድ አዳዲስ አደረጃጀቶች ማዋቀሩን ኮሚሽነር ጄነራሉ ገልጸዋል።

አዳዲሶቹ አደረጃጀቶች እያደገ የመጣውን የአየር እና የየብስ ትራንስፖርት ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ናቸው ተብሎላቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎችንና ዩኒቨርሲቲዎችን ትኩረት አድርገው መዋቀራቸውን አስታውቀዋል።

አዳዲሶቹ አደረጃጀቶች የአቪየሽን ፖሊስ፣ የምድር ባቡር ፖሊስ፣ የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች ናቸው።

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

28 Mar, 14:26


በአዲስ አበባ የተሰረቁ የተለያዩ ዕቃዎችን እየተቀበሉ በሚሸጡ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በመዲናዋ የተሰረቁ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን በሚቀበሉ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በመዲናዋ ልደታና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የተሰረቁ ዕቃዎችን በመግዛት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ፥ የንብረቶቹ ማከማቻ የነበሩ ሱቆች ላይም እርምጃ ተወስዷል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3፣ ወረዳ 4 እና ወረዳ 7 አካባቢ አንዳንድ ሱቆች በስርቆት የሚመጡ የተለያዩ ዕቃዎችን እንደሚቀበሉ ተደርሶባቸዋል።

በመሆኑም ፖሊስ በክፍለ ከተማው መጋቢት 15 እና 16 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ ሱቆች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ይዟል።

ፖሊስ በልደታ ክፍለ ከተማ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 80 የሞባይል ስልኮች፣ 24 ሲም ካርዶች፣ ሁለት ላፕቶፕ፣ አንድ ህገ-ወጥ ሽጉጥ እና በርካታ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ተይዘዋል።

ከተያዙት ዕቃዎች ጋር 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽኑ በመግለጫው አመልክቷል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማም መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ አካባቢዎች በንግድ ሱቆች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 618 የሞባይል ስልኮች፣ አምስት ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ 45 ሲም ካርዶች እና ሌሎችም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ተይዘዋል።

በተመሳሳይ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የንብረት ዓይነቶች በተለያየ አጋጣሚ የጠፋባቸውና የተሰረቀባቸው ባለንብረቶች ባስመዘገቡት መሰረት እየተመሳከረ በመረጋገጥ ላይ መሆኑ ታውቋል።

በአዲስ አበባ በስፋት እየተስተዋለ የመጣውን ሌብነትና ዘረፋ ለመቆጣጠር በቀጣይም ቁጥጥሩን በማጠናከር እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

28 Mar, 14:24


የብልፅግና ፓርቲ ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች የሚመልሱ እቅዶች ተዘጋጅተው እንዲተገበሩ አቅጣጫ አስቀመጠ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ በቅርቡ ባካሄደው አንደኛ ጉባዔው ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችና ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች አስመልክቶ በመላ ሀገሪቱ ከህዝቡ ጋር ሲያደርግ የነበረውን ውይይት አጠናቋል፡፡

የውይይቶቹን መጠናቀቅ ተከትሎም በዛሬው እለት በማእከል ደረጃ የመድረኮቹ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በተገኙበትና የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በመሩት የዛሬው መድረክ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደር መድረኮች የተነሱ ዋና ዋና ሃሳቦች ተገምግመዋል፡፡

በህዝቡ የተነሱትን የህዝብ ጥያቄዎች ለመመለስና ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ዝርዝር እቅዶች ተዘጋጅተው እንዲተገበሩ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በመሆኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅዶች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር እንዲገባ ፓርቲው አቅጣጫ ማስቀመጡን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

27 Mar, 14:02


የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሁለቱ አገራት መሪዎች በሁለትዮሽ አገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያና ጂቡቲ ለረጅም ዘመናት የቆየና የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው አገሮች ናቸው።

የሁለቱን አገሮች የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በተለይም በፖለቲካና ኢኮኖሚ መስኮች ይበልጥ ተቀራርበው በመስራት ላይ ይገኛሉ ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያና ጂቡቲ በባቡር፣ በመንገድ፣ በውሃ፣ በቴሌኮም፣ በኤሌክትሪክ ሃይል እና ሌሎችም የልማት መስኮች የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል።

@Addis_Tv

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

27 Mar, 14:01


አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በስፔን የ10 ኪሜ የጎዳና ሩጫ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ።

አትሌቱ 28:34 በሆነ ሰዓት በመግባት የቦታውን ሪከርድ ጭምር ሰብሮ ውድድሩን ማሸነፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

@Addis_Tv