Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners @riqichaoromoogrammar Channel on Telegram

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

@riqichaoromoogrammar

"ቋንቋ ወንዝ ያሻግራል።"
Riqicha=ድልድይ
"Afaan laga ceesiisa."

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners (Amharic)

ብሔራዊ እና ግንብሽ አስተማሪ ቋንቋ ኦሮምን እና ኦሮሞን አሰራርን በተለያች መረጃዎችን ብቻ ለመጠቀም የሚዳራሉን ሥራዎችን እና ቋንቋዎችን በተመለከተ ቋንቋ ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች ቡድን ከነማ እና እናመሽር የሚፈልጉ። ይህ ቡዳውያን በሚታወቀው ቋንቋ ኦሮሞን በመመለስ ውሂቡን ለመማር ከተነበሩት ከፍተኛ የባህል መረጃዎች ጋር የሚከተሉትን ሰዎች እና አዋጅ ተረአቦችን ለመቀነስ ከእርሱ ጋር የአገልግሎት ዕቅድ ለመዘጋጀት ኶ስት በሚያስገቡ እና በሚዳረግ አጠቃላይ ዙሪያዎች ላይ ያሉትን መረጃዎች ለእኛ የትዕይንሽ አቅም አንጭደሹ።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

25 Dec, 14:33

...s =........illee፡"...ም"= too
Fakkeenya/ምሳሌ
1. Anis =እኔም= Anillee
2.  Nutis ፡እኛም= Nutillee
3. Isaanis ፡እነሱም=Isaanille
4.Isinis ፡እናንተም= Isinillee፡
5. Atis ፡አንተም፣አንቺም= Atillee
6. Innis ፡እሱም= Innillee 
7.Isheenis፡እሷም= Isheenillee
8. Ijoolleenis፡ልጆችም 
9.  Ammas ፡አሁንም

....n
= or to indicate a subject in asentence.
Fakkeenya/ምሳሌ
1. Ani baasiin dhufe.
   በባስ መጣሁ።
2. Nuti taaksiin deemne.
    በታክሲ ሄድን።
3. Ati cileen bilcheessita.
      አንቺ በከሰል ታበስላለሁ።
4.  Isaan bishaanin bashannanu.   
      እነሱ በዉሃ ይዝናናሉ።
5. Namni miilaan tarkaanfata. 
    ሰው በእግሩ ይራመዳል።
6.  Baacaan kormee dha.
    ባጫ ጎበዝ ነዉ።
  Bacha is clever
7. Caaltuun deesse.
   ጫልቱ ወለደች።
    chaltu gave birth.
.....hoo ...."ስ" =what about...
Fskkeenya/ምሳሌ
1.  Ani hoo?=እኔስ?= what about me?
2. Nuti hoo?=እኛስ?= what about us?
3.  Isaan hoo?=እነሱስ?= what about them?
4.  Isin hoo?=እናንተስ?= what about you?
5.  Ati hoo?=አንተስ/አንቺስ?= what about you?
6.  Inni hoo?=እሱስ?= what about him?
7.  Isheen hoo?=እሷስ? =what about her?

በዩቲዩብ: የመጽሐፉ ትምህርት በዚህ ቴሌግራም የሚቀርበውን ጨምሮ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እስከ አነባበቡ በድምጽ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ እና Join ያድርጉ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

15 Dec, 11:09

አፋን ኦሮሞን በራሰወ ይማሩ!

Riqicha/ሪቂቻ ለአፋን ኦሮሞ ጀማሪወች የቋንቋውን ህግ እና አጠቃቀም በአማርኛ:በእንግሊዝኛ እና በኦሮምኛ በቀላሉ ግን በጥልቀት ለማስተማር የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።

Riqicha/ሪቂቻ ብለው መጽሐፉን ይግዙ።

መጽሐፉን አዲስ አበባ ውስጥ በነዚህ መጽሐፍ ቤቶች  ያገኙታል፦

ለገሀር ተወልደ ህንጻ ስር-ጃፈር መጻህፍት

ለገሃር አመልድ ታወር -አይናለም መጽሐፍት

አምስት ኪሎ ብርሃን ሰላም ማተሚያ አጠገብ-ጃፈር መጻህፍት

ቦሌ ወሎ ሰፈር አካባቢ አለም ቡና አጠገብ-ደራሲው መጽሐፍት

በዩቲዩብ: መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ አነባበቡን ጨምሮ በድምጽ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

መጽሐፉን ግዙ።
የዩቲዩብ ቻናሉን subscribe አድርጉ።

ኑ ኦሮምኛን አብረን እንማር!
kottaa Afaan Oromoo waliin haa barannu!

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

14 Dec, 07:12

…ichi/icha/ittiin/itti

....itti indicates a specific object with feminine (female) grammatical gender.

... icha indicates a male object and goes  with the demonstratives kana and sana
Fakkeenya/ምሳሌ
1. Dinni manicha gube.
   ጠላት ቤቱን አቃጠለው።
   An enemy burnt the house.
2. Namichi mukicha mure.
  ሰውየው ዛፉን ቆረጠው።
The man cut down the tree.
3. Sarichi foonicha nyaate.
   ውሻው ስጋውን በላው።
   The dog ate the meat.
4. Tufaan ulicha (kana) cabse.
  ቱፋ ይህን ዱላ ሰበረው።
   Tufa broke this stick.
5. Caaltuun gurbicha (sana) jaallatti.
ጫልቱ ያንን ልጅ ትወዳዋለች።
Chaltu loved that boy.

...itti indicates a female object and goes with the demonstratives kana and sana
Fakkeenya/ምሳሌ
1. Qeerransichi re’ittii nyaate.
     ነብሩ ፍየሏን በላት።
    The tiger ate the goat.
2. Adurrittiin simbirrittii qabatte. 
      ድመቷ ወፏን ያዘቻት።
    The cat caught the bird.
3. Baacaan fardittii rukute.
    ባጫ ፈረሷን መታት።
    Bacha hit the horse.
4. Waraabeessi harrittii (sana) nyaate.
ጅብ ያቺን አህያ በላት።
  Hyena ate that donkey.
6. Namichi dubartittii (sana) gargaare.
ሰውየው ያቺን ሴትዮ እረዳት።
The man helped that woman.

በዩቲዩብ: የመጽሐፉ ትምህርት በዚህ ቴሌግራም የሚቀርበውን ጨምሮ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እስከ አነባበቡ በድምጽ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ እና Join ያድርጉ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

08 Dec, 05:31

…ichi/icha/ittiin/itti=the

These suffixes equate the definite article the. They are suffixed to the last consonanat of an Afaan Oromoo nouon to specify the subject or object of the sentence

...ichi indicates a specific subject with masculine (male) grammatical gender. 
...ittiin indicates a specific subject with feminine (female) grammatical gender
... icha indicates a specific object with masculine(male) grammatical gender.
...itti indicates a specific object with feminine (female) grammatical gender.

...ichi indicates male subject and goes with the demonstratives Kun and sun

Fakkeenya/ምሳሌ 1
1.Manichi gubate.
   ቤቱ ተቃጠለ።
The house burnt.
2. Namichi dhufeera. 
ሰውየው መጥቷል።
The man has come.
3. Kitaabichi guddaa dha.
  መጽሃፉ ትልቅ ነው።
   The book is big.
4. Mukichi dheeraa dha. 
    ዛፉ  ረጅም ነው።
   The tree is long.   
5. Kophichi (kun) haaraa dha.
   ይህ ጫማ አዲስ ነው።
  This shoe is new.
6. Ulichi (kun) cabeera. 
  ይህ ዱላ ተሰብሯል።
This stick is broken.
7.Mukichi (sun) dheeraa dha.  
    ያ  ዛፍ ረጅም ነው።
     that tree is long.
...ittiin indicates a femal subject and goes with with the demonstratives Kun and sun.

Fakkeenya/ምሳሌ 2
1. Harrittiin garbuu sana nyaatte.
   አህያይቱ ገብሱን በላችው።
   The donkey ate the barley.
2. Dubartittiin diimtuu dha
   ሴትዮዋ ቀይ ናት።
The woman is red.
3. Biyyittiin badhaatee jirti. 
  ሃገሪቱ በልጽጋለች።
The country has prospered.
4. Harrittiin (kun) garbuu sana nyaatte. 
ይህቺ አህያ ገብሱን በላችው።
This donkey ate the barley. 5.Gaangeettiin (sun) hiidhamteertti.
   ያቺ በቅሎ ታስራለች።
 That mule has been arrested.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

07 Dec, 08:42

Itti aanee፡በመቀጠል፡next to
Fakkeenya/ምሳሌ
1.Har'a roobi , boru kamisa, iftaan jimaata, itti aanee sanbata dha.
ዛሬ እሮብ፣ነገ ሃሙስ፣ከነገ ወዲያ አርብ ቀጥሎ ቅዳሜ ነው።
2. Ani fixee jira, itti aanee eenyu?  
  እኔ ጨርሻለሁ፤ ቀጥሎ ማን ነው?

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

06 Dec, 14:34

ውድ ኢትዮጵያውያን የሃገሬ ልጆች እንደምን አላችሁልኝ?
Riqicha/ሪቂቻ ለአፋን ኦሮሞ ጀማሪወች የቋንቋውን ህግ እና አጠቃቀም በአማርኛ:በእንግሊዝኛ እና በኦሮምኛ በቀላሉ ግን በጥልቀት ለማስተማር የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።
መጽሐፉ ከታተመበት አንስቶ ላለፉት ሁለት ዓመታት   በዚህ ቴሌግራም ፣ላለፈው  አንድ ዓመት በዩቲዩብ የመጽሐፉን ትምህርቶች ያለመታከት   እያጋራሁ እገኛለሁ።
Riqicha/ሪቂቻ ብለው መጽሐፉን በመግዛት ቻናሉን ይደግፉ።

መጽሐፉን አዲስ አበባ ውስጥ በነዚህ መጽሐፍ ቤቶች   ታገኙታላችሁ፦

ለገሀር ተወልደ ህንጻ ስር-ጃፈር መጻህፍት

አምስት ኪሎ ብርሃን ሰላም ማተሚያ አጠገብ-ጃፈር መጻህፍት

ለገሃር አመልድ ታወር -አይናለም መጽሐፍት

ቦሌ ወሎ ሰፈር አካባቢ አለም ቡና አጠገብ-ደራሲው መጽሐፍት

በዩቲዩብ: መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

መጽሐፉን ግዙ።
የዩቲዩብ ቻናሉን subscribe አድርጉ።

ኑ ኦሮምኛን አብረን እንማር!
kottaa Afaan Oromoo waliin haa barannu!

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

06 Dec, 13:18

Hanga/haga/hamma፡እስከ፡untill
Fakkeenya/ምሳሌ
1.Ganamaa hanga ammaa hojjechaan jira.
ከጠዋት እስከ አሁን እየሰራሁ ነው። 
I am working from morning until now.
3. Isheen hanga dhuftutti eessayyu hin deemu.
እሷ እስከ ምትመጣ የትም አልሄድም።
I  go no where until she comes.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

02 Dec, 13:31

Ala፡ውጭ፡out
Fakkeenya/ምሳሌ
1. Kutaa ala kaa'i. 
  ከክፍል ውጭ አስቀሞምጥ።
  Put it out of the room. 2.Konkoolaataan ala.
ከመኪና ውጭ፡outside the car.
3. Manaa ala=ከቤት ውጭ= outside the house.
4. Gamoon ala
  ከህንጻ ውጭ
  outside the building. 
5. Manaa alatti na eegi. 
   ከቤት ውጭ ጠብቂኝ።
  Wait me out of the house.
6. Biyya alaa hin deemu.
    ውጭ ሃገር አልሄድም።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

01 Dec, 07:43

Yookiin/yookan=ወይም=or
Used in statements.
Fakkeenya/ምሳሌ 1
1. Har’a yookiin boru ni gahu
   ዛሬ ወይም ነገ ይደርሳሉ።
  They will arrive today or tomorrow.  2. Konkolaataa yookan xiyyaaraan deemi.
  በመኪና ወይም በአውሮፕላን ሂድ።
  Go by car or by plane. 
3. Daabboo yookiin biddeena  biti.
    ዳቦ ወይም እንጀራ ግዛ። 
   Buy either bread or enjera

...moo=or=ወይስ
Used in question 
Fakkeenya/ምሳሌ 2
1. Dhalaamoo dhiira
  ሴት ናት ወንድ?
    Is she female or male ?
2. Mirga moo bita?
   ቀኝ ነው ገራ?
  Is it right or left?
3. Lubbu qabeeyyi  moo lubbu dhabeeyyii?
ህይወት ያለው ነው ወይስ ህይወት የሌለዉ?  
   Is it living or non living ?
4. Shawaa lixaa moo shawaa bahaa?
ምዕራብ ሸዋ ወይስ ምስራቅ ሸዋ? 
West shewa or east shewa?

Ammoo/immoo:ደግሞ/ደሞ
Fakkeenya/ምሳሌ 3
1.Baqqalaan ammoo maal gochuuf as dhufe?
  በቀለ ደግሞ እዚህ ምን ሊያደርግ መጣ? 2.Loltuun ammoo magaalaa keessa maal godha?
ወታደር ደሞ ከተማ ውስጥ ምን ያደርጋል? 3.Caaltuun ammoo garam deemte?  
    ጫልቱ ደሞ ወደየት ሄደች?

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

30 Nov, 07:05

Haa ta'uyyu malee፡ቢሆንም ቅሉ፡even though
Fakkeenya/ምሳሌ
1. Dargaggoo dha;haa ta'u malee bay'ee beekaa dha.
  ወጣት ነው ቢሆንም በጣም አዋቂ ነው።  
  Even though he is too young he is wise.
2. Ciree nyaanneerra, haa ta'u malee ammas beelofneerra.
  Though we ate breakfast we are hungry now too.
   ቁርስ በልተናል ሆኖም አሁን እርቦናል።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

28 Nov, 17:26

Utuu/osoo/otoo/yoo፡ከሆነ፡if
Fakkeenya/ምሳሌ

1.Utuun beeke, nan deema ture.
    አውቄ ቢሆን  ሄጄ ነበር።
2. Soddomii shan osoo hin taane, digdamii shan ta'uu qaba.
ሰላሳ አምስት ሳይሆን ሃያአምስት መሆን አለበት።
3.Amma otoo hin taane sa'aa booda wayya. 
አሁን ሳይሆን ከሰዓት ይሻላል።
4. Isheen yoo dhageesse, natti himti. 
  ከሰማች ትነግረኛለች።
5. Yoon argadhe siif nan bita. 
ካገኘሁ  እገዛልሻለሁ።
6. Qormaata yoon darbe, nan gammada. 
  ፈተና ካለፍኩ እደሰታለሁ።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

27 Nov, 10:55

Garuu፡ነገር ግን፡but
Fakkeenya/ምሳሌ

1.Jirbiin adii dha cileen garuu  gurraacha.
ጥጥ ነጭ ከሰል ግን ጥቁር ነው።
  Cotton is white but charcoal is dark.
2.  Nan dhufa garuu hedduu hin turu.
እመጣለሁ ነገር ግን ብዙ አልቆይም።
I will come but I won’t stay long. 3.Eebbifamaniiru garuu hojii hin arganne.
ተመርቀዋል ነገር ግን ስራ አላገኙም።
They are graduated but they didn’t get work.
4.Geenyeerra sagantichi garuu hin jalqabne.
ደርሰናል ፕሮግራሙ ግን አልጀመረም
We have arrived but the program didn’t start.
5. Erga deemanii turaniiru garuu hin geenye.
ከሄዱ ቆይተዋል ነግር ግን አልደረሱም።
It has been long since they went but they didn’t arrive yet.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

26 Nov, 13:36

Akka ፡እንደ፡as/like
Fakkeenya/ምሳሌ

1. Simbirroon akka nama haasa'u maal jedhama?
    እንደ ሰው የሚያወራ ወፍ ምን ይባላል?   
    what is the bird that talks like humans?
2. Akka fedhii keessanii ta'uu dandeessu.
እንደፍላጎታችሁ መሆን ትችላላችሁ።
  You can be as you wish.
3. Akka oggeessatti kana si hin gorsu.
እነደ ባለሞያ ይህን አልመክርህም።
As a professional I don’t advice you this.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

24 Nov, 06:29

Gidduu፡መካከል፡between

Fakkeenya/ምሳሌ

1.Isaan gidduu walii galteen jira.  
   በእነሱ መካከል መግባባት አለ።
   There is harmony between them.
2. Saba fi sab lammoota gidduu jaalalli jira.
በብሄር ብሄረሰቦች መካከል ፍቅር አለ።
Ther is love among nations and nationalities.
3. Namoota gidduu walgargaaruun barbaachisaa dha.
በሰዎች መካከል መረዳዳት አስፈላጊ ነው።
Supporting each other is important among humans.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

23 Nov, 07:11

Bira/cina፡አጠገብ:near

Fakkeeny/ምሳሌ

1. Raagu'eel Anuwaar bira
  ራጉዔል አንዋር አጠገብ ነው።
  Raguel is near Anuar.
2.  Iddoon hojii koo mana koo bira 
     የስራ ቦታየ ቤቴ አጠገብ ነው። 
    My work place is near my home.
3. Mucayyoon hiriyaa ishee cinaa teesse
ልጅቷ ጓደኛዋ አጠገብ ተቀመጠች።
The girle sat near her friend.
4. Komboolchaan Dasee bira.
  ኮምቦልቻ ደሴ አጠገብ ናት። 
    Kombolcha is near Dese.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

16 Nov, 11:38

Gubbaa፡በላይ:above
Fakkeenya/ምሳሌ

1. Kitaabichi minjaalarra jira; dabatara koo isa gubbaa naaf kaa'i.
መጽሃፉ ጠረጴዛው ላይ አለ፤ደብተሬን ከሱ በላይ አስቀምጥለኝ።.
The book is on the table ;put my exercise book above it.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

15 Nov, 11:56

Duuba፡ኋላ፡behind
Fakkeeny/example
1. Balbala duubaan gali።
   በኋላ በር ግቢ/ግባ።
2. Gurbichi namicha duuba jira.
    ልጁ ከሰውየው በኋላ ነው።
   The boy is behind the man.
3. Manicha duuba dhokatteerti.
     ከበሩ ኋላ ተደብቃለች።
    She has hide behind the house.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

11 Nov, 16:26

Jala፡ከስር፡under

Fakkeenya/ምሳሌ
1. Qodicha minjaala jala kaa'i.
    እቃውን ከጠረጴዛ ስር አስቀምጥ።
     Put it under the table.
2. Saanduqa jala maaltu jira?
    ከሳጥኑ ስር ምን አለ?
    what is under the box?
3.  Dabtara keessan teessuma jala godha.
ደብተራችሁን ከዴስኩ ስር አድርጉ።
  Put your exercise book under the desk.
4.  Kopheen kiyya siricha jala jira:
    ጫማዬ አልጋው ስር ነው።
     My shoes is under the bed.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

10 Nov, 08:47

..f፡ለ፡for
Fakkeenya/ምሳሌ

1 Isiniif nyaata haa dhiheessinu. እናንተ ምግብ እናቅርብላችሁ።
Let us serve food for you.
2. Bu'aa argachuuf tattaaffiin dirqama. 
  ውጤት ማግኘት ጥረት ግድ ነው።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

09 Nov, 06:23

Malee፡ ከ...ውጭ:with out,except 
Fakkeenya/ምሳሌ
1.Ani ishee malee jiraachuu hin danda'u.
እኔ ከእሷ ውጭ መኖር አልችልም።
I can’t live without her.
2. Namni daabboo malee hin jiraatuu?
  ሰው ያለ ዳቦ አይኖርም ?
Does man live with out bread?
3. Aannan buna malee naa fidi.
ወተት ያለቡና አምጭልኝ።
  Bring me milk with out coffee. 
4. Tokkummaa malee filannoo hin qabnu.
ከአንድነት ውጭ ምርጫ የለንም።
  We don’t have option except unity.
5. Daa'imichi deeggarsa malee dhaabbachuu danda'a.
ህጻኑ ያለድጋፍ መቆም ይችላል። 
The baby can stand with out support.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

06 Nov, 10:47

Erga… Booda /Booddee =ከ…በኋላ፡after
Fakkeenya/ምሳሌ
1. Isheen erga beekte bodaa aarte. 
   ካዎቀች በኋላ ተናደደች። 
   She became angry after she knew.
2. Erga nyaadhe booda nan rafa.   
   ከበላሁ በኋላ እተኛለሁ።
   I will sleep after I eat.
3. Isaan  erga galani booda hin ba'an. 
እነሱ ከገቡ በኋላ አይወጡም ።
  They don’t go out after entering.

በዩቲዩብ: መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ እና Join ያድርጉ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

05 Nov, 16:19

Booda /Booddee :በኋላ፡after

Fakkeenya/ምሳሌ

1.Hojii booda boqochuun barbaachisaa dha.
ከስራ በኋላ ማረፍ አስፈላጊ ነው።
It is important to rest after work
3. Kana booddee as hin dhufin.
ከአሁን በኋላ እዚህ አትምጣ።
Don’t come here after.
4.  Sana booddee gabaa deemnee turre
  ከዛ በኋላ ገበያ ሄደን ነበር።
We had gone to the market then after.

በዩቲዩብ: መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ እና Join ያድርጉ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

04 Nov, 13:15

Dura፡በፊት፡before
Fakkeenya/ምሳሌ

1. Nyaachuun dura harka keessan dhiqadhaa.
ከመብላታችሁ በፊት እጃችሁን ታጠቡ። Wash your hands before eathing.
2. Qormaataa dura qo’adhu.
    ከፈተና በፊት አጥና።
    Study  before examination.
3. Ciisuun dura ibsaa dhaamsi. 
   ከመተኛትህ በፊት መብራት አጥፋ።
   Off the light before you sleep.
5. Isheen dhufuu dura haa deemnu.
እሷ ከመምጣቷ በፊት እንሂድ። 
Let us go before she comes. 
6. Murteessuun dura yaaduutu barbaachisa.
ከመወሰን በፊት ማስብ ያስፈልጋል።
It is important to think before deciding.

በዩቲዩብ: መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ እና Join ያድርጉ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

04 Nov, 09:58

https://youtu.be/Lvb8HDmqjv4

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

03 Nov, 08:20

Wajjin/waliin/faana፡ጋር፡with
Fakkeenya/ ምሳሌ

1 Marqaan dhadhaa waliin dhiyaata.
ገንፎ ከቅቤ ጋር ይቀርባል:
Porridge  is served with butter .
2.  Si faana namni jiraa?
   ካንተ ጋር ሰው አለ?
   Is there any one with you?
3.  Isheen isa waliin turte. 
     እሷ ከእሱ ጋር ነበረች።
      She was with him.
4.  Na wajjiin koottaa.
    ከኔ ጋር ኑ።
    Come with me.
5.  Ijoolleen maatii wajjiin guddachuu qabu.
  ልጆች ከወላጆች ጋር ማደግ አለባቸው።  
Children must grow with parents.

በዩቲዩብ: መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ እና Join ያድርጉ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

02 Nov, 05:46

Dabalatees፡በተጨማሪም ፡in addition 

1. Re'een baala nyaata, dabalatees marga ni dheeda.
ፍየል ቅጠል ይበላል በተጨማሪም ሳር ይግጣል።
Goat eats leaf; in addition to that it grazes.

2. Fuulli ishee ni hawwata, dabalatees mormi ishee dheeraa dha.
ፊቷ ይማርካል በተጨማሪም አንገቷ እረጅም ነው።
Her face is attractive ;in addition her neck is long.

3. Inni sooreessa dha , dabalatees beekumsa qaba.
እሱ ሃብታም ነው በተጨማሪም እውቀት አለው።
He is rich;in addition he is knowledgeable.

4. Dadhabeera, dabalatees hirribni na qabeera.
ደክሞኛል በተጨማሪም እንቅልፌ መጥቷል።
I am tired;in addition I am sleepy now.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

01 Nov, 09:27

Kanaaf/kanaafuu፡ስለዚህ፡therefore /so

Fakkeenya/ምሳሌ

Hojii fixneerra, kanaafuu haa deemnu.
  ስራ ጨርሰናል ስለዚህ እንሂድ።
  We have finished work so let us go.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

31 Oct, 12:05

ውድ ኢትዮጵያውያን የሃገሬ ልጆች እንደምን አላችሁልኝ?
Riqicha/ሪቂቻ ለአፋን ኦሮሞ ጀማሪወች የቋንቋውን ህግ እና አጠቃቀም በአማርኛ:በእንግሊዝኛ እና በኦሮምኛ በቀላሉ ግን በጥልቀት ለማስተማር የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።
መጽሐፉ ከታተመበት አንስቶ ላለፉት ሁለት ዓመታት   በዚህ ቴሌግራም ፣ላለፈው  አንድ ዓመት በዩቲዩብ የመጽሐፉን ትምህርቶች ያለመታከት   እያጋራሁ እገኛለሁ።
Riqicha/ሪቂቻ ብለው መጽሐፉን በመግዛት ቻናሉን ይደግፉ።

መጽሐፉን አዲስ አበባ ውስጥ በነዚህ መጽሐፍ ቤቶች   ታገኙታላችሁ፦

ለገሀር ተወልደ ህንጻ ስር-ጃፈር መጻህፍት

አምስት ኪሎ ብርሃን ሰላም ማተሚያ አጠገብ-ጃፈር መጻህፍት

ለገሃር አመልድ ታወር -አይናለም መጽሐፍት

ቦሌ ወሎ ሰፈር አካባቢ አለም ቡና አጠገብ-ደራሲው መጽሐፍት

በዩቲዩብ: መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

መጽሐፉን ግዙ።
የዩቲዩብ ቻናሉን subscribe አድርጉ።

ኑ ኦሮምኛን አብረን እንማር!
kottaa Afaan Oromoo waliin haa barannu!

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

31 Oct, 09:27

Fi፡እና፡and
1.Risaa fi guchiin simbirroolee dha.  
   ንስር እና ሰጎን አዕዋፍ ናቸው።
    Eagle and ostrich are birds.
2. Arbi fi hardiidoon hoosistoota dha.
  ዝሆን እና የሜዳ አህያ አጥቢዎች ናቸው።   
  Elephant and zebra are mammals.
3. Leenci fi qeerransi adamsanii nyaatu.
  አንበሳ እና ነብር አድነው ይበላሉ።
   Lion and tiger eat by hunting .
4. Hantuutni  fi aduurreen wal hin jaallattu.
  አይጥና ድመት አይዋደዱም።
  Rat and cat don’t love each other
5. Harree fi fardi ni dheedu.
   አህያ እና ፈረስ ሳር ይግጣሉ።
    Donkey and horse graze.

Ti...and then
This is used to join two sequential actions.
1. Kana qabiiti achi taa'i.
    ይሄን ያዝና እዚያ ቁጭ በል።
   Have this and sit there.
2. Suuqii deemiti daabbo biti.
    ሱቅ ሂድና ዳቦ ግዛ።
   Go to shop and buy bread.
4. Nyaadhuti dhugi. 
  ብላና ጠጣ።
   Eat first and then drink .
5. Amma rafiiti barii dammaqi
    አሁን ተኛና በጊዜ ተነሳ።
   Sleep now and wake up early.

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

31 Oct, 09:24

ትምህርቱን ካቆምንበት እንቀጥላለን።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

04 Oct, 11:15

የኢሬቻ ታሪክ
• ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን እንደጻፉት
• ከ ግርማ ጉተማ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ; 2015 በፈረንጅ አቆጣጠር የተለጠፈ
• ምንጭ ኢትዮጵያን ስተዲስ
• ከእንግሊዝኛ የተተረጎመ
“ከ 12 ሺህ ዓመት በፊት የፀሃይ እና የሰማይ አምላክ ፥ የኩሽ ፈርኦኖች አምላክ የሆነው አስራ፡ ሴቴን ፣ ታናሽ ወንድሙን ኦራን እና እህታቸውን አሲስን (አቴቴ ወይም አድባርን) ፈጠረ።
ሴቴ ታናሽ ወንድሙን ኦራን ገደለው፤ አቴቴ ሟች ወንድሟን ኦራን ለማስታወስ ግድያው በተፈጸመበት ግብጽ ውስጥ በ አባይ ወንዝ ዳርቻ የኦዳ ዛፍ ተከለች፤የፀሃይ አምላክ የሆነውን አባታቸውንም በሴቴ እና በኦራ ቤተሰቦች መካከል ሰላም እንዲያወርድ ለመነችው ፤ዝናብም ዘንቦ የኦዳ ዛፏ አደገች፤ ይህም የለመነችው ሰላም በሴቴ እና በኦራ ቤተሰቦች መካከል መፈጠሩን ጠቆመ።
ኦራም በሱና በወንድሙ ቤተሰብ መካካል የወረደውን ሰላም ለማየት ከሞት ተነሳ(ኦራ-ኦሞ~ኦር-ኦሞ)
በኋላም በድንጋይ ዘመን ፡ የኦራ መታሰቢያ የሆነውን የኦዳ ዛፍ የሚተካ የድንጋይ ሃውልት ከ8 ሺህ ዓመት በፊት ተሰራ።
በየዓመቱ በመስከረም ወር ፡የአባይ ወንዝ በኑቢያ እና በጥቁር ግብጽ ምድር ሞልቶ መፍሰስ ሲጀምር የኦራ መታሰቢያ ሃውልት ክብረበዓል ይከበር ነበር ።
በኢትዮጵያም፡ በአክሱም እና በቅድመ አክሱም ዘመን አቴቴ ለኦራ መታሰቢያ ባቆመችው ሃውልት ዙሪያ ታላቅ በአል ይከበር ነበር። ከዚያ ወዲህ መታሰቢያው የፀሃይ እና የሰማይ አምላክን ችቦ በማብራት እና በማመስገን ይገለጽ ጀመር።
በኢትዮጵያ፡ በደመራ እና በአዲስ ዓመት የሚዜመው እዮ-ካ አበባዬ የተጀመረው ከዚህ በኋላ ነው።
"ካ" የእግዚአብሔር የመጀመሪያው ስም ነው። ከክርስትና እና እስልምና በፊት ፡ ኩሻዊ አባቶቻችን ያዎረሱን የአምላክ ስም "ካ" ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በተለይ ኦሮሞ፣ጉራጌ፣ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ እግዚአብሔርን ዋካ ወይም ዋቃ በሎ ይጠራል ።በአዲስ ዓመት ጊዜ እዮሃ ወይም እዮካ እያልን ስንዘምር "ካ" እግዚያብሔርን እያዎደስን ነው።
ገዳ ወይም ካዳ የእግዚያብሔር ህግ ማለት ነው፤ የዋቃ ህጎችና ትዕዛዞች የሚፈፀሙበት ስነ ስርዓት ነው።
ቻይና ፣ ጃፓን እና ህንድ አሁን ላሉበት ስልጣኔ የበቁት ከኣባቶቻቸው የወረሱትን ባህል እስልምና እና ክርስትና በተቀበሉበት ጊዜ እንኳ ሳይቀር ጠብቀው በመያዝ ነው።ባህል የብዙ ችቦዎች ወይም ደመራ ስብስብ ነው።
ኢሬቻ ወይም ኢሬሳ የገዳ አንዱ አካል ሲሆን የአዲስ አመት መጀመሪያ ተደርጎ ይወሰዳል ። መነሻውም አቴቴ ለኦራ ሃውልት ያቆመችበት ክስተት ነው።
በኦሮሞ ባህል የዝናቡ ወቅት የጨለማ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል ። በመስከረም መጀመሪያ ፡ ጨለማው ይገፈፋል ፣ወንዞች ጥልቀታቸው ቀንሶ ውሃው ጥርት ይላል፣ጭቃው ይደርቃል ።
ፀሃይ በምድር ላይ ስትነግስ ፡ አፍሪካዊ የኦሮሞ ህዝብ ይህን ታላቅ የተፈጥሮ ኡደት ለማክበር እና እግዚያብሔርን (ዋቃን) ለማምለክ ይወጣል ።
የውቢቷ አፍሪካ የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ በአንድ አምላክ ያምናል ። ኦሮሞ አምላኩን ዋቃ ይለዋል። እምነቱ ዋቄፈና ይባላል ፤ትርጉሙም የአለም ሁሉ ፈጣሪ በሆነው አንድ አምላክ(ዋቃ) ማመን ማለት ነው።
ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ተሰብስቦ ለአምላኩ ዋቃ አምልኮውን የሚፈጽምበት እና ምስጋናውን የሚያቀርብበት ክብረ በዓል ነው።
ዋቄፈና የገዳ ስርዓት አካል ሲሆን የአምልኮ ስነ ስርአቱ ከምንም ነገር የጸዳ ነው። የኦሮሞ የእምነት አባቶች እና ህዝቡ በእጃቸው ለምለም ሳር እና አበባ ይዘው ወደ ተራራ ፣ ወደ ወንዝ ወይም ወደ ሃይቅ ዳርቻ በመሄድ አምልኳቸውን ይፈጽማሉ ፡ ዋቃንም ያመሰግናሉ ።
ወደ ተራራ ፣ ወደ ወንዝ ወይም ወደ ሃይቅ ዳርቻ የሚሄዱት ተራራውን ፣ ወንዙንና ሃይቁን ለማምለክ አይደለም። ይልቁንም ፦አንድም ከምንም አይነት ጫጫታ ርቀው በተመስጦ ዋቃን ለማምለክ ፣ ሁለትም እነዚህ ቦታዎች ሰላም የሰፈነባቸው በመሆናቸው የዋቃ መንፈስ በዚያ እንደሚገኝ ስለሚያምኑ ፣ ሶስትም አረንጓዴ የቅድስና ውሃም የህይዎት ተምሳሌት ስለሆኑ ወደዚያ ይሄዳሉ ።”

የእንግሊዝኛው ጽሑፍ አድራሻ ይኸውላችሁ ፡https://yeroo.org/2019/09/03/the-story-of-irrecha-by-poet-laureate-tsegaye-gebremedhin-robba-qawessa/

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

04 Oct, 11:15

Ayyaana Irreechaa kan kabajjaniif, ayyaana gaarii!
የኢሬቻን በዓል ለምታከብሩ መልካም በዓል!

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

27 Sep, 00:19

Masqalaa=መሰቀላ
Ayyaana masqalaaf baga isiin gahe;baga nu gahe.
እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

28 Jun, 10:00

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች እንደምን አላችሁልኝ?
Riqicha/ሪቂቻ ለአፋን ኦሮሞ ጀማሪወች የቋንቋውን ህግ እና አጠቃቀም በአማርኛ:በእንግሊዝኛ እና በኦሮምኛ በቀላሉ ግን በጥልቀት ለማስተማር የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።
መጽሐፉ ከታተመበት አንስቶ ላለፉት ሁለት ዓመታት   በዚህ ቴሌግራም ፣ላለፈው  አንድ ዓመት በዩቲዩብ የመጽሐፉን ትምህርቶች ያለመታከት   እያጋራሁ እገኛለሁ።
Riqicha/ሪቂቻ ብለው መጽሐፉን በመግዛት ቻናሉን ይደግፉ።
መጽሐፉን አዲስ አበባ ውስጥ በነዚህ መጽሐፍ ቤቶች   ታገኙታላችሁ፦

ለገሀር ተወልደ ህንጻ ስር-ጃፈር መጻህፍት
 
ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንጻ ስር ጃፈር መጻህፍት

ብሔራዊ ጀርባ-አይናለም መጻህፍ ቤት

አራት ኪሎ-  እነሆ መጽሐፍ ቤት  ታክሲ  መያዣው ፊት ለፊት

ቦሌ ወሎ ሰፈር አካባቢ አለም ቡና አጠገብ-ደራሲው መጽሐፍት

በዩቲዩብ: መጽሐፉ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እየቀረበ ይገኛል። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፦
https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8

መጽሐፉን ግዙ።
የዩቲዩብ ቻናሉን subscribe አድርጉ።

ኑ ኦሮምኛን አብረን እንማር!
kottaa Afaan Oromoo waliin haa barannu!

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

26 Jun, 20:26

https://youtu.be/U8pY_sk7JSo

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

26 Jun, 09:14

Sababni isaa/ሰበብኒሳ:ምክናያቱም ፡ because

1. Nuti hin dhufnu,sababnisaa  hin waamamne./ ኑቲ ሂን ዱ"ፍኑ, ሰበብኒሳ ሂን ዋመምኔ
እኛ አንመጣም፤ምክንያቱም አልተጠራንም።
We don’t  come because we were not called/invited.
2. Inni fayyeera, sababnisaa yaalameera./ኢኒ' ፈየ'ራ, ሰበብኒሳ ያለሜራ
እሱ ድኗል፤ምክናያቱም ታክሟል።
He has improved ,because he was treated.
3. Isheen gadditeerti, sababnisaa qormaata kufteerti./ኢሼን ገዲቴርቲ, ሰበብኒሳ ቆርማተ ኩፍቴየርቲ
She is sad,because she has fallen exam.
አዝናለች፤ምክናያቱም ፈተና ወድቃለች።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

22 Jun, 06:30

Waa'ee/ዋኤ ፡ስለ፡about

1. Waa'ee gaa'ila kee natti himi./ዋኤ ገኢላኬ ነቲ' ሂሚ
ስለ ጋብቻህ ንገረኝ፤ ስለጋብቻሽ ንገሪኝ።
Tell me about your marriage.
2. Waa'ee Itoophiyaa maal beektu?/ዋኤ ኢቶጵያ ማል ቤክቱ
ስለ ኢትዮጵያ ምን ታውቃላችሁ?
What do you know about Ethiopia ?
3. Mee waa'ee jireenyaa yaa haasoofnu./ሜ ዋኤ ጅሬኛ ያ ሃሶፍኑ
እስቲ ስለኑሮ እናውራ።
Let us talk about life.
4. Waa'ee ofii kee maal beekta?/ዋኤ ኦፊኬ ማልቤክታ
ስለራስህ ምን ታውቃለህ?
What do you know about yourself

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

17 Jun, 16:03

Conjunction and prepositions in Afaan Oromoo

1. Waa'ee/ዋኤ፡ስለ፡about
2. Sababni isaa/ሰበብኒሳ:ምክናያቱም/ because
3. Maalifi/ማሊፊ :because :ምክናያቱም
4. Fi/ፊ፡እና፡and ..., ti=and then . ...
5. dhaan/ዳ"ን ፡በ፡by
6. Kanaaf/kanaafuu/ከናፍ፡ስለዚህ፡therefore
7. Dabalatees/ደበለቴስ፡በተጨማሪም ፡in addition
8. Wajjin/waliin/faana(ወጅ'ን/ወሊን/ፋነ) ፡ጋር፡with
9.Dura/ዱራ፡በፊት፡before
10. Booda /Booddee/ቦዳ/ቦዴ :በኋላ፡after
11. Erga… Booda /Booddee/ኤርጋ ቦወዳ :ከ…በኋላ፡after
12. Erga/ኤርጋ፡ከ...ዎዲህ፡since
13. Malee/መሌ፡ ከ...ውጭ:with out,except ..
14. ...f/ፍ፡ለ፡for
15. Duuba/ዱውበ፡ኋላ፡behind
16. Jala/ጀለ፡ከስር፡under
17. Gajjallaa/ገጀ'ላ'፡ከስር፡beneath
18. Gubbaa/ጉባ'፡በላይ:above
19. Gararraa/ገረራ'፡ከላይ፡over Irra፡ላይ፡on
20. Irraa/ኢራ'፡ከ:from
21. Bira/cina/ቢረ/ጭነ፡አጠገብ:near
22. Ammoo/immoo/አሞ'/ኢሞ':ደግሞ/ደሞ
23. Haa ta'uyyu malee/ሃተኡ መሌ፡ቢሆንም ቅሉ፡even though Kan፡የ፡of/’
24. Ala/አለ፡ውጭ፡out
25. Hanga/haga/hamma=(ሀንገ/ሀገ/ሀመ')፡እስከ፡untill
26. Utuu/osoo/otoo/yoo=(ኡቱ/ኦሶ/ኦቶ/ዮ)፡ከሆነ፡if
27. Itti aanee/ኢቲ' አኔ፡በመቀጠል፡next to
28. Gidduu/ጊዱ'፡መካከል፡between
29. Keessa/ኬየሰ'፡ውስጥ፡in
30. Keessatti/ኬየሰ'ቲ'፡ወደ ውስጥ:into
31. Akka/akkuma/አከ'/አኩ'መ፡እንደ፡as/like
32. Garuu/ገሩ፡ነገር ግን፡but ...
33. moo/ሞ፡ወይስ፡or
34. Yookiin/yookan/ዮኪን/ዮካን፡ወይም፡or

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

16 Jun, 11:05

Ayyaana Arafaaf baga isiin gahe!
እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ!

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

10 Jun, 13:45

download ማረግ ይቻላል👆

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

10 Jun, 13:36

ከላይ በስድስት ክፍል የቀረበውን ማብራሪያ እነሆ አሁን ደግሞ በ PDF በነጻ ሰጠኋችሁ። መክፈል የሚፈልግ ቢኖር አንድ Riqicha/ሪቂቻ መጽሐፍ ይሸምት እላለሁ። ይኸው PDF👇download አድርጋችሁ አንብቡ።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

10 Jun, 13:30

ክፍል ስድስት
ማጠቃለያ

• ስለተነባቢወች መጥበቅና መላላት የምንከተለው ህግ ቀላል ብቻ ሳይሆን አሻሚ ነገር የለውም። ህጉ በደንብ ከገባችሁ በኋላ ተነባቢወችን ስታነቡ እና ስትጽፉ ስህተት መስራት የለባችሁም! ስለተነባቢወች በዚህ ደረጃ የራስ መተማመን ካላዳበራችሁ ህጉ አልገባችሁም ማለት ነው። በሌላ በኩል የአናባቢወችን አጻጻፍ እና ንባብ በተመለከት የምንከተለው ህግ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ቀላል ቢሆንም በተግባር የሚረዝም እና የሚያጥር ድምጽን የሚወክል አናባቢን በትክክል ለመጻፍ በሚነገረው ቃል ውስጥ ረዝሞ እና አጥሮ የሚጠራውን ድምጽ ቀድሞ መገንዘብ ይጠይቃል። ይህን በቀላሉ የሚገነዘቡት አፋቸውን በአፋን ኦሮሞ የፈቱ ሰወች ናቸው። ስለሆነም እንደ እኔ አፋን ኦሮሞን እንደሁለተኛ ቋንቋው የሚማር ሰው አጥረው እና ረዝመው የሚጠሩ ድምጾችን መገንዘብ ስለሚያዳግተው አናባቢወችን አሳስቶ ሊጽፍ ይችላል። አናባቢወችን በትክክል ለመጻፍ ህጉን በተክክል መገንዘብ ብቻ በቂ አይደለም፤ በሚነገረው ቃል ውስጥ የተኞቹ አናባቢ ድምጾች እንደሚያጥሩ እና እንደሚረዝሙ መለየት አለብን። ለምሳሌ ሃብታም በኦሮምኛ [ሶሬሳ'] ነው። ይህን ቃል በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ጻፉት ብላችሁ፡ ቃሉ [ሶሬሳ'] ሲጠራ የሚጠብቀው ተነባቢ ሳ' ብቻ መሆኑን መለየት ምንም አያዳግትም፤ ሌሎቹ ተነባቢወች( ሶ እና ሬ) አይጠብቁም። ስለዚህ የመጀመሪያው s እና r በነጠላ የመጨረሻው s ተደርቦ እንደሚጻፍ በቀላሉ ትገነዘባላችሁ። ቀጥሎ ከተነባቢወቹ ጋር ያሉት አናባቢወች ከ ሶ/s ጋር ኦ/፣ ከ ሬ/r ጋር ኤ/e፣ ከ ሳ'/s ጋር አ/a መሆናቸውንም መለየት አያዳግትም። ከነዚህ አናባቢወች ውስጥ አ/a አጥሮ መጠራቱን መለየትም ይቻላል። የሚያስቸግረው ኦ/o እና ኤ/e በ [ሶሬሳ'] ውስጥ አጥረው ወይ ረዝመው መጠራታቸውን መለየት ነው። ይህን ከግምት አስገብታችሁ [ሶሬሳ']ን ከሚከተሉት በአንዱ እንደምትጽፉት እገምታለሁ። [soressa], [sooressa], [soreessa],[sooreessa]። በመሰረቱ የቋንቋው ተናጋሪወች [ሶሬሳ']ን ሲጠሩ ኦ/o ን አስረዝመው፣ ኤ/e ን እና አ/a ን አሳጥረው ስለሆነ በአማርኛ ሲጻፍ ወደ [ሶወሬሳ] ይጠጋል። በዚህ መሰረት ትክክለኛው አጻጻፍ [sooressa] ይሆናል ማለት ነው። ቃላትን በለቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ስንጽፍ በእንግሊዝኛ ስንጽፍ እንደሚፈጠረው ሁሉ የአናባቢወች አጻጻፍ ስህተት/spelling error የማይቀር መሆኑን መካድ አይቻልም።
• ሌላው ብዙ ሰወችን ሲያሰቸግር የማየው አማርኛ ቃላትን በእንግሊዝኛ ፊደል ለመጻፍ የምንከተለውን አካሄዳ ከላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ጋር ማምታታት ነው። ለምሳሌ [ገዳ] የሚለውን ቃል በተለምዶ በእንግሊዝኛ ስንጽፈው [geda] ብለን ነው። በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ሲጻፍ ትክክለኛው አጻጻፍ [gadaa] ሆኑ ሳለ እንደጀማሪ ከአማርኛውን አካሄድ ጋር ማምታታት ሊከሰት ይችላል፤ ልብ ማለት ያስፈልጋል። አበቃሁ!

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

10 Jun, 04:41

ክፍል አምስት

በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ጽሁፍ አናባቢወችን ለመጻፍ የመንከተለዉህግ፡ መርዘም እና ማጠር

የሚረዝም አናባቢም ረዝሞ መነበቡን ለማሳየት አናባቢው ተደግሞ ይጻፋል። አጥሮ የሚነበብ አናባቢ ድምጽን የሚወክል አናባቢ አንድ ጊዜ በቻ ይጻፋል። በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የተጻፈ ቃል አነባበቡ በአማርኛ ሲጻፍ በላቲኑ ተጽፎ የሚታየዉን ሙሉበሙሉ ባይተካም [ee] ረዝሞ መነበቡን ለማሳየት ከሃምስ ፊደሉ ቀጥሎ “የ” ን፣ [oo] ረዝሞ መነበቡን ለማሳየት ከሳብእ ፊደሉ ቀጥሎ “ወ” ን፣ [uu] ረዝሞ መነበቡን ለማሳየት ከካልእ ፊደሉ ቀጥሎ “ው” ን በትንሹ ጽፌያለሁ። ለምሳሌ [guuffee] የሚለውን ቃል [ጉዉፌ’የ] ብላችሁ አንብቡት። በተመሳሳይ [Ijoollee]ን [ኢጆወሌ’የ] ብላችሁ አንብቡት።የአናባቢወችን መርዘም ለማሳየት የገቡትን “ው”፣“የ” እና “ወ” ተጭናችሁ አታንብቧቸዉ። [u], [e] እና[o] በነጠላ ሲጻፉ አጥረዉ ስለሚነበቡ በካልእ፣ በሃምስ እና በሳብእ ተነባቢ ፊደል ብቻ ይጻፋሉ።ለምሳሌ [kufe]=[ኩፌ]፣ [tole]=[ቶሌ] ተብለዉ ይነበባሉ። የሚከተሉትን ተጨማሪ ምሳሌወች ተመልከቱ።
[Lafa]=[ለፈ]
[Laafaa]=[ላፋ]
[Sooressa]=[ሶወሬሳ']
[Dureessa]=[ዱሬየሳ']
[Miti]=[ሚቲ]
[Niitii]=[ኒቲ]
[Dhufe]=[ዱ"ፌ]
[Dhuufe]=[ዱ"ዉፌ]
[Bona]=[ቦነ] በጋ
[Boona]=[ቦወነ]
[Boonaa]=[ቦወና]
[Gosa]=[ጎሰ]
[Gosaa]=[ጎሳ]

ሶስት ተመሳሳይ አናባቢወች ወይም ሁለት የተለያዩ አናባቢወች በመደዳ ተከታትለው አይጻፉም። እንዲህ ሲሆን ['] እናስገባለን። ለምሳሌ [re'ee] = [ሬኤ] ፣ [mo'uu] = [ሞኡ] የሚሉትን ቃላት አስተውሏቸው። ቀደም ብየ በክፍል ሁለት ተራቁጥር 9 ላይ ስለ አናቂ ድምጽ/sagalee hudhaa የሰጠሁትን ማብራሪያ ተመልከቱ።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

09 Jun, 10:28

ክፍል አራት

በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ጽሁፍ ተነባቢወችን ለመጻፍ የምንከተለዉ ህግ፡ መጥበቅ እና መላላት

በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ተነባቢወች ላልተው እና ጠብቀው ይነበባሉ። የሚጠብቅ ተነባቢ መጥበቁን ለማሳየት ተነባቢው ተደግሞ ይጻፋል። ለምሳሌ [በቀ'ለ]፣[ዱባ']፣[ጡጫ']፣[ጡጦ']፣[ጸጋ'] እና [ኮዳ']
በሚሉት የአማርኛ ቃላት ውስጥ አናታቸው ላይ የ['] ምልክት ያለባቸው ፊደሎች ጠብቀው መነበበ አለባቸው። እነዚህን ቃላት በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ስንጽፋቸው የሚጠብቁትን ተነባቢወች የሚወክሉት የላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ፊደሎች እንደሚከተለው ተደርበው ይጻፋሉ።
[በቀ'ለ]= [baqqala]
[ዱባ']= [dubbaa]
[ጡጫ']= [xuccaa]
[ጡጦ']= [xuuxxoo]
[ጸጋ']= [tseggaa]
[ኮዳ']= [koddaa]
በግልባጩ [qeerroo] = [ቄሮ'] እና [ijoollee] = [ኢጆሌ'] በሚሉት የኦሮምኛ ቃላት ውስጥ "r" እና "l" ተደግመው ስለተጻፉ “ሮ” እና “ሌ” ጠብቀው መነበብ አለባቸው። በአማርኛው ንባብ ውስጥ ጠብቆ የሚነበብን ተነባቢ ለማሳየት የ ['] ምልክት ጠብቆ በሚነበበው ፊደል አናት ላይ አስቀምጣለሁ። የሚከተሉትን የኦሮምኘኛ ቃላት ወስደን- ተጨማሪ ምሳሌወች እንመልከት ።
[Abbaa]=[አባ']-ባ' ይጠብቃል
[Carraa]= [ጨራ']-ራ' ይጠብቃል
[Guddaa]=[ጉዳ']-ዳ' ይጠብቃል
[Waggaa]=[ወጋ']--ጋ' ይጠብቃል
[Jijjiiruu]= [ጅጅ'ሩ]-ሁለተኛው ጅ' ይጠብቃል
በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ላልቶ የሚነበብ ተነባቢ አንድ ጊዜ ብቻ ይጻፋል። የሚከተሉትን ምሳሌወች ተመልከቱ።
[Dargaggoo]=[ደርገጎ']- ገ አይጠብቅም፤ ጎ' ይጠብቃል
[Ijoollee]=[ኢጆሌ']- ጆ አይጠብቅም፤ ሌ' ይጠብቃል።
[Adaadaa]=[አዳዳ]- የትኛውም ተነባቢ አይጠብቅም
[Barreeffame]= [በሬ'ፈ'ሜ]-ሬ' እና ፈ' ይጠብቃሉ፤ ሜ አይጠብቅም።
[Obbooleessa]=[ኦቦ'ሌሳ']--ቦ' እና ሳ' ይጠብቃሉ፤ ሌ አይጠብቅም።
በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የተነባቢወችን መጥበቅና መላላት በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተዋል ይገባል።
1. የሚጠብቅ ድምጽ በነጠላ ፡ የሚላላ ድምጽ ደግሞ በሁለት ተነባቢ ከተጻፈ ቃሉ ወይ ትርጉም አልባ ይሆናል አሊያም ከፍተኛ የትርጉም ለውጥ ያመጣል። የሚከተሉትን ምሳሌወች ተመልከቱ
[Sodaa]= [ሶዳ]-ዳ ሳይጠብቅ ትርጉሙ ፍርሃት
[Soddaa]=[ሶዳ']-ዳ ሲጠብቅ ትርጉሙ አማት
[Madaa]=[መዳ]-ዳ ሳይጠብቅ ትርጉሙ ቁስል
[Madda]=[መዳ']-ዳ' ሲጠብቅ ትርጉሙ ምንጭ ይሆናል
2. የትኛውም የቃል መጀመሪያ ተነባቢ እና [h] ተደርበው አይጻፉም።
3. ቁቤ ደቻ ቢጠብቅም ተደርቦ አይጻፍም። ለምሳሌ [qoopheessuu]=[ቆጴ'ሱ'] በሚለው የኦሮምኛ ቃል ውስጥ ጴ' እና ሱ' ጠብቀው መነበብ አለባቸው። ነገር ግን ጴ' መጥበቁን ለማሳየት ph በድጋሚ "phph" ተደርጎ አይጻፍም። [ch] እና [ny] ሁልጊዜ በሚባል ደረጃ (by default) ጠብቀው ይነበባሉ። [nyaachuu]=[ኛቹ']፣ [gaafachuu] =[ጋፈቹ']፣... [Jireenya]=[ጅሬኛ']፣ [keenya] =[ኬኛ']፣... ወዘተ በሚሉት የኦሮምኛ ቃላት ውስጥ ቹ' እና -ኛ' ይጠብቃሉ። ከ[ch] ቀደሞ ሌላ ተነባቢ ሲኖር ግን [ch] by default ላልቶ ይነበባል። [tolchuu]=[ቶልቹ]፣ [garagalchuu]=[ገረገልቹ]፣ [bulchuu]=[ቡልቹ]፣... በሚሉት የኦሮምኛ ቃላት ውስጥ ከ ch በፊት l በመኖሩ በነዚህ ቃላት ውስጥ [ch]/ቹ ላልቶ ይነበባል። [sh] በአብዛኛው ላልቶ ብቻ ይነበባል።[warsha]=[ወርሻ]፣ [oomishuu]=[ኦሚሹ] በሚሉት የኦሮምኛ ቃላት ውስጥ -ሻ እና ሹ አይጠብቁም። [dh] እና [ph] ላልተው ወይም ጠብቀው ሊነበቡ ይችላሉ። የሚከተሉትን ምሳሌወች ተመልከቱ።
[Badhaadhaa]=[በዳ"ዳ"]-ሁለቱም ዳ" ወች ላልተው ይነበባሉ
[Hodhuu]= [ሆዱ"] ፡ በዚህ ቃል ውስጥ dh (ዳ") ላልቶ ሲነበብ የቃሉ ትርጉም መጥባት ነው፤ dh (ዳ") ጠበቆ ሲነበብ የቃሉ ትርጉም መስፋት ይሆናል።
[Cuuphuu]=[ጩጱ]-ጱ ላልቶ ይነበባል
[Suphee]= [ሱጴ]-በዚህ ቃል ውስጥ ph (ጴ) ላልቶ ሲነበብ የቃሉ ትርጉም ሸክላ ነው፤ ph (ጴ) ጠበቆ ሲነበብ የቃሉ ትርጉም ጠገነ ይሆናል።
4. ከሁለት በላይ ተነባቢወች በመደዳ ተከታትለው አይጻፉም። አንድን ቃል ስናረባ(during word conjugation)ከሁለት በላይ ተነባቢወች በመደዳ ተከታትለው በሚመጡበት ጊዜ ቀድመው በነበሩት ሁለት(አንድ አይነት ወይም የተለያዩ) ተነባቢወች እና በሚጨመረው ተነባቢ መካከል “i” እናስገባለን። ለምሳሌ [kennuu]=[ኬኑ'] የሚለውን የኦሮምኛ ቃል ተመልከቱ። ቃሉ በሁለት ተመሳሳይ ተነባቢወች(nn) ይጨርሳል።የቃሉ ትርጉም መስጠት ነዉ። ከዚህ ቃል (እኛ) ሰጠን የሚል ትርጉም ያለው ሌላ ቃል ለመመስረት በ ምንከተለው ህግ መሰረት በ[kennuu] መጨረሻ ላይ ያሉትን አናባቢወች (uu) አጥፍተን የቃሉ መጨረሻ ተነባቢ ላይ (ne) መጨመር አለብን። ይህን ስናደርግ የምናገኘው ቃል kennne ይሆናል። ሶስት n ተከታትሎ መጻፍ ስለማይችል ቀደሞ በነበሩት ሁለት nዎች እና በተጨመረው n መካከል i ስናስገባ ሰጠን የሚል ትርጉም ያለው የኦሮምኛ ቃል ትክክለኛ አጻጻፍ [kennine]=[ኬኒ'ኔ] ይሆናል። በተመሳሳይ መንገድ የተጻፉትን የሚከተሉትን ተጨማሪ ምሳሌወች ተመልከቱ።
[Kennite]=[ኬን'ቴ]
[Gaddine]=[ገድ'ኔ]
[Tolchine]=[ቶልችኔ]
[Ergitu]=[ኤርጊቱ]

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

09 Jun, 10:04

ክፍል ሶስት

በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ቃላትን መጻፍ እና ማንበብ

የላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ፊደላት ለብቻቸው እንዴት እንደሚጠሩ(እንደሚነበቡ) ካወቅን በኋላ በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ለመጻፍ እና ለማንበብ የሚቀረን የመጨረሻ ቁምነገር የላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ተነባቢወችን እና አናባቢወችን በማቀናጀት እንዴት ቃላትን እንደምንጽፍ እንዲሁም በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የተጻፈን ቃል እንዴት እንደምናነብ መገንዘብ ነው። በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የጽሁፍ ስርዓት ተነባቢወች እና አናባቢወች ሁለቱም በጽሁፉ ውስጥ ይወከላሉ። ይህን አጻጻፍ ከአማርኛ አጻጻፍ ጋር ስታነጻጽሩት በአማርኛ ጽሁፍ ስርዓት አናባቢወች አይጻፉም። ላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞን ከእንግሊዝኛ አጻጻፍ ጋር ብታነጻጽሩት በሁለቱም አናባቢወች ስለሚጻፉ ተመሳሳይነት አላቸው።
በጽንጸ ሀሳብ ደረጃም ሆነ በተግባር በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ መጻፍና ማንበብ ከእንግሊዝኛ አንጻር ቀላል መሆኑን ለመናገር እደፍራለሁ። በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ጽሁፍ ስርዓት እንደ እንግሊዝኛ የሚዋጥ(silent) አናባቢም ሆነ ተነባቢ የለም፤ በቃሉ ውስጥ ያሉ አናባቢወችና ተነባቢወች ሁሉ ይነበባሉ። የላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ጽሁፍ ስርዓትን ቀላል የሚያደርገዉ ሌላዉ ምክንያት የተነባቢዉ ድምጽ ሁልጊዜ ተከትሎት በሚጻፈው አናባቢ ላይ ብቻ መወሰኑ ነዉ። እንበልና ከላይ ዘርዝረን ያየናቸውን የላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ 28 ተነባቢ ፊደሎች በአንድ ተነባቢ ፊደደል "T" አንወክላቸው። ከዛ ተነባቢውን ("T") ከአምስቱ የላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ አናባቢዎች ጋር ስናጣምረው የሁሉም ተነባቢወች ድምጽ እና ንባብ ከታች ለ "T" እንደምናየው ይሆናል።
1. [Ta]=[ተ]-a ሲያጥር
2. [Tu/Tuu=[ቱ]
3. [Tii]= [ቲ]-i ሲረዝም
4. [Taa]= [ታ]-a ሲረዝም
5. [Te/Tee]=[ቴ]
6. [Ti]=[ት]-i ሲያጥር
7. [To/Too]=[ቶ]
[a] እና [i] ሲያጥሩና ሲረዝሙ በተነባቢዉ ላይ የተወሰነ የድምጽ ለዉጥ ያመጣሉ። [a] ሲያጥር ተነባቢዉ ከሞላጎደል እንደ አማርኛዉ የመጀመሪያ ፊደል፡ [a] ሲረዝም ተነባቢዉ እንደ አማርኛዉ አራተኛ ፊደል ተደርጎ የነበባል። [i] ሲያጥር ተነባቢዉ ከሞላጎደል እንደ አማርኛዉ ስድስተኛ ፊደል፡ [i] ሲረዝም ተነባቢዉ እንደ አማርኛዉ ሶስተኛ ፊደል ተደርጎ የነበባል። ለሶስቱ አናየባቢወች (e,o,u) የአናባቢወቹ ማጠርና መርዘም በተነባቢው ላይ የድምጽ ለውጥ አያመጣም። ለምሳሌ [Tee] ረዘም ተደርጎ ከመነበቡ ውጭ [Te] እና [Tee] ሁለቱም ሲነበቡ [ቴ] ተብለው ነው። በነዚህ ሁለት ምክንያቶች ማለትም በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የጽሁፍ ስርዓት የሚዋጥ ድምጽ ባለመኖሩ እና የተነባቢው ድምጽ ሁልጊዜ ተከትሎት በሚጻፈው አናባቢ ላይ ብቻ መወሰኑ ላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የተናገርነውን (ያነበብነውን) እንድንጽፍ፡ የተጻፈውን(ያየነውን) እንድናነብ ያስችላል። በእንግሊዝኛ የተነባቢው ድምጽ ሁልጊዜ ተከትሎት በሚጻፈው አናባቢ ብቻ አይወሰንም። ለምሳሌ [come], [cook] እና [cod] የሚሉትን የእንግሊዝኛ ቃላት ተመልከቱ። [come]=ካም፣[cook]=ኩክ፣ [cod]= ኮድ ተብለው ይነበባሉ። "co" በ [come] ውስጥ "ካ" በ [cod] ውስጥ ደግሞ "ኮ" የሚሉ ሁለት የተለያዩ ድምጾችን ይሰጣል። በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ግን “coo” ረዘም ተደርጎ ከመነበቡ ውጭ "co" ም ሆነ "coo" ሁልጊዜ "ጮ" ተብሎ ነው የሚነበበው።
ቃላትን በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ለመጻፍ እና ለማንበብ የምንከተለው ህግ አጭር እና ቀላል ነው። በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ቃላትን ስንጽፍ እና ስናነብ በቃሉ መሃል እና መጨረሻ ላይ ጠብቆ የሚጠራን ድምጽ የሚወክሉ ነጠላ ተነባቢወች ከ [h] በስተቀር ተደርበው ይጽፋሉ፤ ተደርቦ የተጻፈ ነጠላ ተነባቢ ፊደልም ጠብቆ ይነበባል። በተመሳሳይ ረዝሞ የሚጠራ አናባቢ ድምጽን የሚወክሉ አናባቢወች ተደግመው ይጻፋሉ፤ ተደግሞ የተጻፈ አናባቢም ረዝሞ ይነበባል።

Riqicha/ሪቂቻ ኦሮምኛ ሰዋስው ለጀማሪወች/ seerlugaa Afaan Oromoo/ Afaan Oromoo grammar for beginners

08 Jun, 15:18

9. [']: ይህ ምልክት በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ አናቂ ድምጽን (sagalee hudhaa) ይወክላል። ለምሳሌ [ማእረግ] እና [ጸባኦት] በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ሲጻፉ በተከታታይ [maa'irag] እና [tsabaa'ot] ተብለው ነው። በተመሳሳይ በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የተጻፉት [danda'aa] እና [bal'aa] በተከታታይ ሲነበቡ [ደንደአ] እና [በል'ኣ] ይሆናሉ። በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ ሁለት የተለያዩ አናባቢወች ወይም ሶስት ተመሳሳይ አናባቢወች በመደዳ ተከታትለው አይጻፉም። የተለያዩ አናባቢወች በመደዳ ተከታትለው ከመጡ በመጀመሪያው እና በሁለተኛው አናባቢ መካከል ['] ይቀመጣል። ምሳሌ [ari'u]=[አሪኡ] በሚለው ቃል ውስጥ i እና u የተለያዩ አናባቢወች ተከታትለው ስለመጡ በመካከላቸው ['] ተቀምጧል። በተመሳሳይ ሶስት አንድ አይነት አናባቢወችም በመደዳ ተከታትለው ከመጡ በመጀመሪያው እና በቀጣይ አናባቢወች መካከል ['] ይቀመጣል።ምሳሌ [re'ee]=[ሬኤ] በሚለው ቃል ውስጥ ሶስት ተመሳሳይ አናባቢወች ተከታትለው ስለመጡ በመጀመሪያው e እና ቀጥሎ በመጡት ሁለት eዎች መካከል ['] ተቀምጧል። አስተውሉ! እንደ እንግሊዝኛው ['] በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የ ስርዓተ ነጥብ አገልግሎት የለውም፤ መጥበቅና መላላትን ለማመልከት የሚቀመጥም አይደለም። በላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ የተጻፈ ቃል በውስጡ አናቂ ድምጽ/sagalee hudhaa ሲኖረው የቃሉ አነባበብ በአማርኛ ፊደል ሲጻፍ ከ['] ቀጥሎ የሚመጣው የአፋን ኦሮሞ አናባቢ ተነባቢ ሆኖ ይጻፋል። ከላይ ያሉትን ምሳሌወች ተመልሳችሁ አስተዉሉ።

የላቲን ቁቤ አፋን ኦሮሞ አናባቢወች ለብቻቸው ሲነበቡ የአማርኛውን የ[አ] ዘሮች ድምጽ ይሰጣሉ። a/አ ወይም ኣ፣ e/ኤ፣ i/ኢ፣ o/ኦ፣ u/ኡ ተብለው ይነበባሉ። አንድ አናባቢ ብቻ (a,e,i,o,u) አጭር ድምጽን ሁለት ተመሳሳይ አናባቢወች (aa,ee,ii,oo,uu) ረጅም ድምጽን ይወክላሉ። አምስቱም አናባቢወች አጭር እና ረጅም አናባቢ ስለሚኖራቸው በቅርጽ አምስት ብቻ ቢሆኑም አጭር እና ረጅም አናባቢዎችን ጨምሮ ላቲን ቁቤ አፋን አሮሞ አስር አናባቢወች አሉት ሊባል ይችላል።