✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️ @getemegn1991 Channel on Telegram

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

@getemegn1991


ይህ ቻናል በዋነኝነት በዘር፣በራስ ሐጢያት እንዲሁም በቅንአትና በምቀኝነት በሰውነታችን ሸምቀው ፍልሚያ ለገጠሙን ጠላቶቻችን እርኩሳን መናፍስት የመልስ ምት የምንሰጥበት እግዚአብሔርን አምነን ከእስራታቸው የምንወጣበት ድንግል ማርያምን አማላጅ አርገን የምንክድበት መላእክትን ተራዳኢ አርገን ቅዱሳንን ይዘን ከመንገዳችን የምናስወጣበት ከስም ወደ ተግባር ኦርቶዶክሳዊነት የምንመጣበት የተግባር ቤታችን ነው።

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️ (Amharic)

ተግባራዊ ክርስትና ቻናል (✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️) በየእግዚአብሔር ምት የምንመጣበት ሰፋ ላይ ይመከራል፡፡ ይህ መልሱ የሚታወቅ በተግባር ኦርቶዶክስ ከተማ ዩኒቨርሲቲ አባላት ጥንቃቄያዎች እና ቁምፊዎች የሚኖሩበት መንፈሳቸው ነው፡፡ በብልጣር ሁሉ የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ መምሪያን ለማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲ አባላት ጥቅም ጋር የተግባር መምሪያ ቤታችንን ማህበረሰብ አሰፋለው፡፡ የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ መምሪያ ቤት መካከለነ መልእክቶችን በጽሑፎቻቸው ስለሚያደርግ ብልጽግና ስሙን መጠቀም ይችላሉ፡፡ ለተመደቡበት ተማሪ ትምህርት መንግሥት ላይ የብልጣሩ ህግ በውሳኔ እና በትግል መቆጣጠል ተዘጋጅተዋል፡፡ ደንቆናና ተበጁን ቤተክርስቲያን እና እናቴን በአንደኛው የውጭ ገጽታ አማራጭ ሳይከተለው ተቀማጭን ለመመረዝ ይህ ቻናሉ የተፈጥሮን ለውጥ ሲል በቅንአትና በምቀኝነት የሚዋልን ኁናታችንን ማርያምን መንፈስ ለመሰነብ አስብላለሁ፡፡

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

13 Jan, 21:10


እንኩዋን ለእናታችን ለሰማዕቷ ለቅድስት አርሴማ ወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን የሰማዕታት በረከቷ በኛ ላይ ይደርብን🌸🌺

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

13 Jan, 19:30


🔴ስግደት 6🔴
1,የአምልኮ ስግደት
2,የፀጋ ለድንግል ማርያም
3, የቅድስት አርሴማ ስግደት
4, የንስሐ ስግደት
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

13 Jan, 16:27


             ጥር ፮ (6) ቀን

          እየሱስ/ግዝረቱ ለእግዚእነ/ እየሱስ ገዳም ፣ ነቢዩ ኤልያስ የተሰወረበት ቀን

እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ ለግዝረት [ ለኢየሱስ ] ዓመታዊ በዓል ፣ ከአዳም ዐሥረኛ ትውልድ ለሆነው ለታላቁ አባት ለጻድቁ ለቅዱስ ኖኅ ለዕረፍቱ መታሰቢያ ፣ ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ኤልያስ በሕይወት ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ለዐረገበት [ ከሞት ለተሰወረበት ] በዓል ፣ ለታላቋ ሰማዕት ለቅድስት አርሴማ ለልደቷ በዓልና ለከበረና ለታላቁ አባት ለቂሣርያ ኤጲስቆጶስ ለአቡነ ባስልዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
🌺🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

13 Jan, 16:14


https://youtu.be/NwYPZX2shpU?si=xLF4t8XOOBojN6AM

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

13 Jan, 10:24


ገብረመንፈስ ቅዱስ ርዕሰ ባህታዊ | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

@https://t.me/getemegn1991
@https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

12 Jan, 22:57


በሰርጋችን ዕለት እንድትባርከን ጌታ ጠርተንሃል በእምነት ሆነን ከእናትህ ጋር.......

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

12 Jan, 21:40


እንኳን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን 🌺🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

12 Jan, 19:30


🔴ስግደት 5🔴
1,የአምልኮ 28
2,የአምልኮ 41
3,የፀጋ ለድንግል ማርያም
4,የፀጋ ለአቡዬ ገብረመንፈስ ቅዱስ
5,የንስሀ እና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

08 Jan, 09:41


✞ ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ

ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ (2)
ምስክሩ ነህ የኢየሱስ
ባማረው ቃልህ ልቤን አድስ

ጌታ የሚወደው ትሁት ወንጌላዊ
ምድራዊ አይደለ ክብሩ ሰማያዊ
በወንጌል የተካ የአሣውን መረብ
አደገ በፊቱ ተሞልቶ በጥበብ

ወንጌል ናት ሕይወቱ የተሰወረባት
በርሷ እየነደደ ለአለም ያበራባት
ተነጥፎ ያነባ በአምላኩ ፍቅር
ሳለው በውስጣችን የወንጌልን ክብር

የአይሁድ ጭካኔ ቢወራ ቢነገር
ከእራት ብቻ አይደለም ቀራንዮም ነበር
ፊቱን አላዞረም በዚያች የጭንቅ ቀን
ዮሐንስ አልቻለም በጌታው መጨከን

አምደ ቀራንዮ ከአስራ ሁለቱ አንዱ
አስራ አንዱ ሸሽተው በመንገድ ሲሄዱ
ዮሐንስ ነው ስሙ ጅራፍ ያላሸሸው
የክርስቶስ ፍቅር ውስጡን ያሸነፈው

ከአይሁድ ዛቻ ይልቅ ፍቅሩ ይሰማዋል
ገዳዮቹን ሊያድን ለሚሞተው አዝኗል
እንዲህ ያለ ፍቅር ለማንም የለውም
አለና ጻፈለት ብዕር ባይችለውም
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

07 Jan, 21:31


እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ወረሐዊ መተሰቢያ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🌺🤲🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

07 Jan, 19:30


🔴ስግደት 30🔴
1,41 ስግደት
2,ረጅሙ የፀጋ ስግደት ለድንግል
3,የቅዱስ ዮሐንስ ስግደት
4,የንስሀ እና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

07 Jan, 15:38


ቅዱስ ላሊበላ🙏🌺❤️

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

07 Jan, 09:53


ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ።

ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ኾኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ። ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚኾን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ። ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት። ይህን ወዷልና፤ (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ 66፥17)።

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ።
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

07 Jan, 09:21


✝️ይኸው ተወለደ✝️
    
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት (፫)
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት (፫)


ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ (፫)
 አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ (፫)

አዝ___

ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ (፫)
የእስራኤል ንጉስ ተወልዷል እያሉ (፫)

አዝ___

ሰብአ ሰገል መጡ እጅ መንሻ ይዘው (፫)
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው(፫)

አዝ___

ምእመናን እንሂድ ከልደቱ ቤት(፫)
ውሃው ሆኗልና ማርና ወተት (፫)

አዝ___ 

በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ(፫)
ብሥራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ(፫)
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

06 Jan, 20:54


እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን ፫ 🌺🤲

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

06 Jan, 19:30


🔴ስግደት 29🔴
1,የምስጋና የሰልስቱ ደቂቅ
2,መዝ 22 እና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

01 Jan, 10:07


ታሕሳስ ፳፫ /23/

በዚችም ቀን የእሴይ ልጅ ንጉሥ ዳዊት አረፈ።

ንጉሥ ዳዊት ቤተልሔም የሆነች ከይሁዳ ነገድ ነው። ሳሙኤልም በእግዚአብሔርን ትእዛዝ ዳዊትን ከእረኝነት አስጠርቶ ቅብዐ መንግስትን ቀብቶ አነገሰው። ከፍልስጤማውያንም ጋራ ሰልፍ በሆነ ጊዜ ብርቱ ሰው ስሙ ጎልያድ የሚባል ከጌት ሰዎች የተወለደ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ ከኢሎፍላውያን ሰፈር ወጣ።

በዚያም ወራት ዳዊት ወንድሞቹን ሊጐበኝ ወጣ ጎልያድንም በአየው ጊዜ አምላካዊ ቅናትን ቀና ሳኦልንም እንዲህ አለው እኔ ሔጄ ይህን ያልተገረዘ ቈላፍ ገድዬ ዛሬ ከእስራኤል ሽሙጥን አርቃለሁ አለው። ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔርን አርበኞች ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን ቁም ነገር ነው ከድብ አፍና ከአንበሳ አፍ ያዳነኝ እርሱ እግዚአብሔር ከዚህ ካልተገረዘ ኢሎፍላዊ እጅ ያድነኛል።ሳኦልም ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን አለው።

ዳዊትም ዛሬ የእስራኤልን አርበኞች የተገዳደርክ አንተን ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ይጥልሃል እገድልህምአለሁ ራስህንም እቆርጣለሁ አለው። ዳዊትም አንዲት ደንጊያ አውጥቶ ወነጨፋት ያንንም ኢሎፍላዊ ግንባሩን ገመሰው በግንባሩም ተደፋ። ዳዊትም ሩጦ የገዛ ሰይፉን አንሥቶ ራሱን ቆረጠው ከእስራኤልም ልጆች ስድብን አራቀ።

የዳዊትም መላው ዕድሜው ሰባ ነው መንግሥትን ሳይይዝ ሠላሳ ዓመት ኖረ ከዚያ በኋላ አርባ ዓመት ኖሮ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለ እግዚአብሔር
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

01 Jan, 09:33


ዛሬ ማታ አንድ አንድ ሰው ይዘን እንገኝ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

31 Dec, 21:09


እንኳን አደረሳችሁ ለሊቀ ሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሀዊ መታሰቢያ በዓል የሰማዕቱ በረከቱ ረድኤቱ አይለየን🌸🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

31 Dec, 19:30


🔴ስግደት 23🔴
➡️➡️➡️➡️➡️
1,የአምልኮ ስግደት 41
2,የፀጋ ለድንግል ማርያም
3,የቅዱስ ጊዮርጊስ ስግደት
4,የንስሐና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

31 Dec, 17:28


የፊልሞና ጥናት ጥያቄ እና መልስ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

31 Dec, 14:09


🌺ማታ🌺 1/30 ለጓደኞቻችሁ ሊንክ ሼር ሼር እያደረጋችሁ  አንድ አንድ ሰው የያዛቸው ኑ በሰዓታችን እንገናኝ https://t.me/getemegn12 🌻🌼

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

31 Dec, 04:59


https://youtu.be/gapyk8Sx5lA?si=KXBqeSsZKq8YEobB

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

31 Dec, 04:02


https://youtu.be/qjNBYXrO81A?si=QWZjalEZftwkDYdN

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Dec, 22:09


<አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ እንዲህ ይሉናል ስለ አንደበት> አንደበታችንን እንጠብቅ!
አፉ ውስጥ ያለችውን ይህችን ትንሽዬ ብልት መቆጣጠር የማይችል ሰው ህይወቱ በመከራ እና በብስጭት የተሞላ መሆኑ የማይቀር ነው። ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላቶች ከሰይፍ የላቀ፣ ከፈንጂ የባሰ ጉዳትን የማስከተል አቅም አላቸው።
➵ *ማሳበባችንን እንተው!*
ማንኛውንም ውድቀት ላለመቀበል ሁሉንም ዓይነት ሰበቦች እና ምክንያቶችን እናመጣለን። ይህም ከስህተታችን እንዳንማር ያደርገናል። ለማሳበብ ለማሳበብማ አዳም ሔዋን ላይ አሳቧል፤ ሔዋንም እባብ ላይ አሳባለች… ታዲያ ማን ከእርግማኑ ተረፈ?።

➵ ፀሎት አየራችን ይሁን*
ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ዋነኛው መንገድ ነው… ከፀሎት ጋር ያልተቆራኘ ህይወት አየር በሌለበት ቦታ ላይ እንደመኖር ይቆጠራል! የጭንቀት እና የስጋት ሰንሰለት የትም እንዳንሄድ፣ ምንም ብሩህ ነገር እንዳናስብ ተብትቦ ይይዘናል፤ ፀሎት እንዴት ይህንን የብረት ሰንሰለት ማቅለጥ እንደሚችል እንማርበታለን።

➵ጭንቀት በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ ነው።*
አምላካችን እግዚአብሔር ጭንቀታችንን ሁሉ ለእሱ እንድንተው መክሮናል። እኛ ግን ብዙ ጊዜ በጭንቀት ራሳችንን ስናሳምም ነው የምንገኘው። የታዘዝነውን ከማድረግ ይልቅ በተፈጠረብን ችግር አማካይነት ሳናውቀው በተቃውሞ ውስጥ እንገባለን። የጭንቀት መድሃኒቱ የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ ለአምላካችን መተው ነው።
➵ ➵ *መድኃኒታችንን እንዋጥ።*
ይቅርታ ከብዙ በሽታዎች የሚፈሰው መድኃኒት ነው፡፡ ራሳችንን ከመመረዝ ነጻ ማውጣት የምንችለው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ልክ የተቀደደ ልብስን እንደሚሰፋ የሚያውቅ መርፌ ዓይነት ነው። በየቀኑ የይቅርታን መድኃኒት እየዋጥን መፈወስ ስንችል ለምን ይሆን ራሳችንን የምንመርዘው?

📝አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Dec, 21:18


እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል ወረሐዊ መታሰቢያ እና ለአብሳሪ ድንግል ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ መታሰቢያ አደረሰን አደረሳችሁ 🌺

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Dec, 19:31


🔴ስግደት 22🔴
1,መናፍስትን የሚቀጠቅጥ ስግደት
2,የፀጋ ለድንግል ማርያም
3,የቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ዑራኤል
4የንስሀ እና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

28 Dec, 21:48


https://youtu.be/_LzxFM-1vRM

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

28 Dec, 20:43


እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የጻዲቁ አባ ዮሐንስ ሀፂር በረከታቸው ይደርብን አሜን 🤲🌺

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

28 Dec, 19:30


╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ስግደት ለ ታህሳስ 18
1️⃣የአምልኮ 28
2️⃣41 የአምልኮ ስግደት
3️⃣ረጅም የአምልኮ ስግደት
4️⃣አባታችን ሆይ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

28 Dec, 09:38


+ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ኢትዮጵያውያን እሳት ውስጥ ከገባን ቆይተናል:: የሠለስቱ ደቂቅ እምነት ግን የለንም::

+ እንዲያውም ከእኛስ ናቡከደነፆር ሳይሻል አይቀርም:: ከእሳት እንዳወጣ እርስ በእርሳችን እየተባላን ከእሳቱ በላይ ጥላቻ እያቃጠለን ነው:: አንዱ በሌላው ሞት እየዘበተ አንዱ የሌላው ለቅሶ እያሳቀው የኢትዮጵያ ሠለስቱ ደቂቆች ለፈጣሪም አልመች ብለን ተጨካክነናል::

+ አንዴ አናንያና አዛርያ ሚሳኤል ላይ ሲወርዱበት አንዴ አዛርያ ከአናንያ ሲጣላ እየዋልን እርስ በእርሳችን ተራ በተራ እየተናከስን በእሳት ውስጥ ሆነን እንኳን መደማመጥ አልቻልንም::

+ ናቡከደነፆርና ወዳጆቹ በጥላቻ ዓይናቸው እያዩን እንኳን መስማማት አቅቶናል:: ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እንደ ሠለስቱ ደቂቅ ከእሳት ሳታወጣን በፊት እኛን ከእኛ ውስጥ አውጣን::

+ ራሳችን እያራገብን ከምንቃጠልበት እሳት አድነን:: ናቡከደነጾርን ግራ ያጋባ መገዳደላችንን እና መበሻሸቃችንን በምልጃህ አስቁምልን:: ከሞትህ ሞቴ ከደምህ ደሜ ይበልጣል ከዕንባህ ዕንባዬ ይበልጣል ብለን ልናልቅ ነውና ለኢትዮጵያውያን ድረስልን:: በግፍ የረገፉትን ንጹሐን በክንፎችህ ነፍሳቸውን ጋርድልን:: ተሰድደው ተፈናቅለው ያሉትን ሰብስብ::

+ ለኢትዮጵያም ድንግልን ባረጋጉ ቃላትህ፦
"ዕንባን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው" ብለህ አረጋጋት
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

28 Dec, 04:50


ገብርኤል መላከ ራማ

ገብርኤል (፪)
ገብርኤል መልአከ ራማ (፪)
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ
ድምጽህን እናስማ

ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሰውን መሆን ለአለሙ ሰበክ(፪)

ከውኃ እና ከሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለውም ሞትና መከራ(፪)

የመንገድ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለአገራችን ምስራች ይዘህ ና(፪)

አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ
ስለአንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳተ ነህ ገብርኤል ነባልባልባ አስወጋጅ
የአምላክ መወለድ ለአለም ምታውጅ(፪)

መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

27 Dec, 21:52


የቅዱስ ገብርኤል ድርሳን በእውነት ለወንድማችን ቃል ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልህ 🤲🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

27 Dec, 21:12


እንኳን ለሊቀ መላኩ ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን  ቅዱስ ገብርኤል የዓመት ሰው ይበለን አሜን🤲🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

27 Dec, 20:15


ተአምረ ኢየሱስ፣ ተአምረ_ማርያም፣_ድርሳነ_ቅዱስ_ገብርኤል_የታሕሣሥ_እና_ስንክሳር_የታሕሣሥ_19.pdf

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

27 Dec, 19:29


══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ስግደት ታህሳስ 1⃣9⃣
1️⃣የአምልኮ 28
2️⃣41 የአምልኮ
3️⃣የመንፈስ ቅዱስ ስግደት
3️⃣መዝ 22 እና አባታችን ሆይ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

03 Dec, 04:30


https://youtu.be/rtJwyj13c-w?si=E3BhX6DVEeQePQUv

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

03 Dec, 00:40


https://youtu.be/oyCAgKTu0Fk?si=SrOfEbCgIIYw55gq

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

02 Dec, 21:34


እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወራዊ መታሰቢያ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🤲🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

02 Dec, 19:30


🔴ስግደት 24🔴
➡️➡️➡️➡️➡️
1,የአምልኮ ስግደት
2,የፀጋ ለድንግል ማርያም
3,የአቡነ ተክለሃይማኖት
4,የንስሐና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

02 Dec, 13:50


🌼ማታ🌼 1/30 ትምህርት አለ ለጓደኞቻችሁ ሊንክ ሼር ሼር እያደረጋችሁ  አንድ አንድ ሰው የያዛቸው ኑ በሰዓታችን እንገና እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ https://t.me/getemegn12

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

02 Dec, 10:10


እውነት ነው ✞

እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው [፪]

ወደ እግዚአብሔር አብ የምንደርስበት
አንድያ ልጁን የምናምንበት
የህይወት መንገድ እርሱ ብቻ ነው
የባህሪ አምላክ  ብለን ስናምነው
        አዝ =======
በማርያም ስጋ የተገለጠው
ወልድን ስናውቅ ነው አብን ያወቅው
አብ በእርሱ እንዳለ እርሱም በአብ አለ
በሀይል በስልጣን የተካከለ
        አዝ =======
ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ
ህይወት የሰጠን በደልን ክሶ
እኛም ዳሰስነው በላን ጠጣነው
በዝግ ቤት ሳለን ገብቶ ያየነው
        አዝ =======
ፈቅዶ ቢወሰን በአጭር ቁመት
ረቂቁ ቢገዝፍ በጠባብ ደረት
መንሹ በእጁ ነው ሁሉን ያጠራል
በአለም ሊፈርድ ዳግም ይመጣ
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

01 Dec, 21:09


እንኳን አደረሳችሁ ለሊቀ ሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሀዊ መታሰቢያ በዓል የሰማዕቱ በረከቱ ረድኤቱ አይለየን🌸🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

01 Dec, 19:30


🔴ስግደት 23🔴
➡️➡️➡️➡️➡️
1,የአምልኮ ስግደት 41
2,የፀጋ ለድንግል ማርያም
3,የቅዱስ ጊዮርጊስ ስግደት
4,የንስሐና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

01 Dec, 06:55


https://youtu.be/Yd9Ll_MnBPA?si=Vj4KxoOBEIr8OyMQ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Nov, 21:57


https://youtu.be/vs8ifG2-_g8?si=NBdf5TczRLAmmgGP

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Nov, 20:53


እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል ወራዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ //የቅዱስ ዑራኤል በረከቱ አይለየን አሜን//🌺🌺

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Nov, 19:30


🔴ስግደት 1🔴ቅዳሜ🔴
1,የአምልኮ ስግደት
2,ለክቡር መስቀሉ አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Nov, 15:39


🥀ስለ እመ ብርሃን ስለ ወላዲተ አምላክ ፀበለ ፃድቅ ይቅመሱ እመ ብርሃን ወላዲተ አምላክ ከርሞ በሰላም በጤና ታድርሰን ለሀገራችን ፅኑ ሰላምን አንድነትን ትስጥልን አሜን 🤲🥰🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Nov, 10:55


ቅድስት ሆይ ለምኚልን🤲

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

30 Nov, 09:37


ሶበ ተዘከርነሀ ለጽዮን ✞

ሶበ ተዘከርነሀ ለጽዮን [፪]
ውስተ አፍላገ ባቢሎን እየ
ነበርነ ወበ ከይነ እንዚራቲነ
ሰቀልነ ውስተ ኩይሀቲያ [፪]

ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን [፪]
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠናል አለቀስን
መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ [፪]

ጽኑ መከራ ተቀበልን ተጨንቅን በፈተና
የደውይ ሞት በላያችን እንደ ዝናብ ወርዷልና
አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ
ዘመሩለት ለአምላካችን ቢያድናቸው ከመከራ
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግሥቱ መርጧታልና ማደርያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤቴ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን

    
የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለ ፍርሀት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረን የማረኩንን በትኖ
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግሥቱ መርጧታልና ማደርያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤቴ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
    
ስጋችንን ይገል ዘንድ የሞት ጥላ ቢያጠላ
እናልፋለን ሁሉን ባ'ንቺ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን እንድናለን ከድዌአችን
ለስጋና ለነፍሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን

እግዚአብሔር ጽዮንን....
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን.....https://
t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

29 Nov, 21:45


እንኩዋን ለእናታችን ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን ፫ 🤲🌺🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

29 Nov, 20:22


ተአምረ ኢየሱስ፣ ተአምረ_ማርያም_ም_11፣_ድርሳነ_ማርያም_የኅዳር_እና_ስንክሳር_የኅዳር_22.pdf

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

29 Nov, 19:30


╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ስግደት ለ ህዳር 21
1️⃣የአምልኮ 28
2️⃣41 የአምልኮ ስግደት
3️⃣ረጅም የአምልኮ ስግደት
4️⃣አባታችን ሆይ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

29 Nov, 15:28


ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፡፡ አእምሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን

©🥀አሜን አሜን አሜን🥀

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

29 Nov, 14:21


https://youtu.be/QtVcP6pUF5g?si=s6i-87OSrkPuoMGc

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

29 Nov, 14:07


🌼ማታ🌼 1/30ትምህርት አለ ለጓደኞቻችሁ ሊንክ ሼር ሼር እያደረጋችሁ  አንድ አንድ ሰው የያዛቸው ኑ በሰዓታችን እንገና እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ https://t.me/getemegn12

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

21 Nov, 16:44


"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል :ያድናቸዉማል "::(መዝ 33:7 )

"መጽናናት ሲነሳኝ እንባ ባአይኔ ቀድማ

ደርሰህ ብርታት ሆንከኝአቆምከኝ ከማማ

የስደት ስንቄ ነህ ያንደበቴ ጣዕም

ክብርና ሞገሴ የኔነቴ ሠላም

ዛሬም እንደትናት እላለሁ ሚካኤል

አማላጅነትህ ሞትን ያሻግራል

ከክፉ ጠብቆ ሠላምን ያለብሳል

አንተን የተሰጠ ፍቅርህ የገባው ሰው

የሚያመሰግንህ የታደለ ሰው ነው"::

#ቅዱስ_ሚካኤል_በእለተ_ቀኑ_ከክፉ_ይጠብቃችሁ🙏

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

21 Nov, 09:43


የቅዱስ ሚካኤል ድርሳን ዘወራዊ ህዳር🌺

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

21 Nov, 09:43


ይለይብኛል ሚካኤል


ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል(2)
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል (2)

አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን

ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል===ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል===የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል===መነሻዬ ሆነሀል

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ

ሚካኤል===እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል===ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል===ለኔ አይኔ ነው መከታዬ
ሚካኤል===የዘለዓለም ጠባቂዬ

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ 
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

21 Nov, 04:51


"በዚች በኅዳር 12 ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሁል ጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኀይላት ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ ነው ::

እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ የባርነት ኑሮ ነጻ አውጥቶ መና አውርዶ ደመና ጋርዶ አለት ሰንጥቆ ውኃ አፍልቆ ጠላት ገድሎ ባሕር ከፍሎ እየመራ ምድረ ርስት ያስገባቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው በዚህም ‹‹ መጋቤ ብሉይ ›› የሚል ቅጽል ተሰጥቶታል ።

ቅዱስ ያሬድ ስለዚህ ገናና መልአክ ሲመሰክር ‹‹ ሚካኤል ቀን በደመና ሌሊት በብርሃነ እሳት መራቸው ፤ በእስራኤል በጎዳናቸው ፊት ፊት እየሔደ ሕዝቡን በደስታ አወጣቸው ! መልአኩን ላከ አዳናቸው ፡፡ ›› በማለት ታዳጊነቱን ዘምሯል ።

እንዲሁም በዚህ በኅዳር_12_ቀን የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ሚስቱ ቴዎብስታ ትባላለች ሁል ጊዜ ያለ ማቋረጥ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉ መታሰቢያ ያደርጉ ነበር በሚኖሩበትም በሀገር ውስጥ ችግር ሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚሆን  የሚያደርጉበትንም ገንዘብ አጡ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ተመስሎ ለዱራታዎስ ተገለጠለት ።

የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልም የበዓሉን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ታላቅ ቸርነትን አደረገላቸው ቅዱስ ሚካኤልም ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ እኔ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁንና ምፅዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት የሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር  እንድታጡ አላደርጋችሁም አላቸው ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ ።እርሱ :ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መልአክ ነው  ሥልጣኑም ታላቅ  ነው  በችግራችን ጊዜ  ይለምንልን ዘንድ  ረዳትም  ይሆነን  ዘንድ ክንፎቹንም ዘርግቶ : ይጋርድልን አሜን በእውነት🙏😥

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Nov, 21:49


እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ መታሰቢያ አደረሳችሁ አደረሰን🌺

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Nov, 20:52


የየራሳችሁን ብቻ የክርስትና ስም ጻፉ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Nov, 20:17


ድርሳነ ሚካኤል የኅዳር፣ ገድለ አቡነ ሳሙኤል የኅዳር እና ስንክሳር የኅዳር -12.pdf

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Nov, 19:30


╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ስግደት ለ ህዳር 12
1️⃣የአምልኮ 28
2️⃣41 የአምልኮ ስግደት
3️⃣ረጅም የአምልኮ ስግደት
4️⃣አባታችን ሆይ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Nov, 15:27


ወዳጅ_ነህ_ለሁሉ ❖

ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ
ዛሬም ቆመሀል በኪዳንህ ላሉ

ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፊቴ
ምራኝ መንገዴን እንዳይመሽ ልድረስ ካባቴ
እንዴት ይገፋል ጎዳናው ካላንተ እርዳታ
ጥሜን ቁረጠው በበትርህ ጭንጫውን ምታው (2)


ተጠመጠመ ጠላቴ በእሳት ሰንሰለት
የጌታ መልአክ ሚካኤል በሰይፍ ወድቆበት
የለም ከቦታው ስመለስ አጥቼዋለው
የሚረዳኝን ተሹሞ አይቼዋለው (2)


ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሀል
ስለረዳኸዉ ዳንኤል እጅግ ወዶሀል
ይነዋወፃል ባህሩ አንተ ስትመጣ
እግዚአብሄር ይንገስ ዳቢሎስ መድረሻ ይጣ (2)


አለኝ ትዝታ በቤትህ ከልጅነቴ
ስትሳሳልኝ እያየው ፀንቷል ጉልበቴ
ልዘምር እንጂ ላመስግን ታላቁን ጌታ
አንተን የሰጠኝ ጠባቂ በቀን በማታ (2)

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Nov, 12:32


ማታ  1/30 ጥያቄ ያላችሁ ጥያቄያቸውን በውስጥ ላኩ ጓደኞቻችሁ ሊንክ ሼር ሼር እያደረጋችሁ በሰዓታችን እንገናኝ  https://t.me/getemegn12 🌻🌼

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Nov, 03:50


ማታ  1/30 ጥያቄ ያላችሁ ጥያቄያቸውን በውስጥ ላኩ ጓደኞቻችሁ ሊንክ ሼር ሼር እያደረጋችሁ በሰዓታችን እንገናኝ  https://t.me/getemegn12 🌻🌼

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

19 Nov, 21:25


እንኮን ለእናታችን ቅድስት ሐና አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🌺🤲

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

19 Nov, 19:42


ስግደት ደርሷችሁ የማያቅ የያዙ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

19 Nov, 19:30


🔴ስግደት 15🔴
➡️➡️➡️➡️➡️
1,የመንፈስ ቅዱስ መሳቢያ
2,የፀጋ ለድንግል ማርያም
3,የፀጋ የቅዱስ ገብርኤልና ሚካኤል
4,የንስሐና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

04 Nov, 21:52


እንኳን አደረሳችሁ ለአባታች ለፃዲቁ አቡነ ሀብተ ማርያም ወራዊ  ክብረ በዓል
የአባታችን በረከታቸው ረድኤታቸው አይለየን
🌸🌺

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

04 Nov, 19:49


🔴ስግደት 26🔴
➡️➡️➡️➡️➡️
1,የአምልኮ ስግደት
2,የፀጋ ለድንግል ማርያም
3,የቅዱስ ሚካኤል ና ገብርኤል
4የንስሐና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

03 Nov, 21:08


እንኳን ለታላቁ ሊቀ ሰማዕት ቅዱስ መርቆርዮስ ወርኀዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። 🌸🌺

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

03 Nov, 19:31


በጣም ይቅርታ የቀጠርኩት መስሎ ለቅቄዋለሁ የኔ ነገር😭

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

03 Nov, 19:30


🔴ስግደት 25🔴
➡️➡️➡️➡️➡️
⓵,ረጅሙ የአምልኮ ስግደት
⓶,የፀጋ ለድንግል ማርያም
⓷,የፀጋ ለቅዱስ ሚካኤልና ለቅዱስ ገብርኤል
⓸,የቅዱስ መርቆሬዎስ የክብር ስግደት
⓹.የንስሐና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

03 Nov, 14:04


🌼ማታ🌼 1/00 ትምህርት አለ ለጓደኞቻችሁ ሊንክ ሼር ሼር እያደረጋችሁ  አንድ አንድ ሰው የያዛቸው ኑ በሰዓታችን እንገና እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ https://t.me/getemegn12

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

02 Nov, 20:53


እንኳን ለፃድቁ ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ወረሐዊ መታሰቢያና ለቅድስት ፀበለ ማርያም አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🤲🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

02 Nov, 19:30


╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ስግደት ዘ ሰንበት
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
1️⃣የአምልኮ 28
2️⃣የምስጋና ስግደት
3️⃣ አባታችን ሆይ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
           ✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
          ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

02 Nov, 10:07


ሰማዕተ ኢየሱስ የእውነት ምስክር
ህያውን ነው በሰማይ
ብፁዕ ነው በምድር
ደራጎንን በጦር ወግቶ ገደለና
ከሞት አዳነኝ ጊዮርጊስ ደረሰና


የሀዘን ማዕበል እንዳያንገላታኝ
ታምር ሰሪው ሰማዕት ፈጥኖ አረጋጋኜ
በእግዚአብሔር ጣዕም በፍቅሩተጠምዷል
ይህን አለም ንቆ በክብር አጊጧል
አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ


እርሱ ለምጠራው ሲመሽም ሲነጋ
ዋስ ጠበቃዬ ነው በነፍስም በስጋ
ድንቅ የሚፈፅም ሀያል ሰማዕት ነው
በቅድመ እግዚአብሔር ለእኔ የሚቆመው
አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ


የምስጋናን አውታር የታጠቀ ሰማዕት
ስሙን ተሸክሞ የታመነ እስከሞት
ሙታንን የሚያስነሳ ስልጣን ተቀብሏል
በአባቱ መንግስት እንደ ፀሐይ ደምቋል
አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ



https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

02 Nov, 07:43


https://youtu.be/tBElbARGqWQ?si=mXlbI9u_oipgOe2S

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

01 Nov, 20:50


እንኳን አደረሳችሁ ለሊቀ ሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሀዊ መታሰቢያ በዓል የሰማዕቱ በረከቱ ረድኤቱ አይለየን🌸🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

01 Nov, 19:35


የህማማት መቁጠሪያ ያዙ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

21 Oct, 19:30


╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ስግደት ለ ጥቅምት 12
1️⃣የአምልኮ 28
2️⃣41 የአምልኮ ስግደት
3️⃣ረጅም የአምልኮ ስግደት
4️⃣አባታችን ሆይ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

21 Oct, 10:57


"ትሑት ሰው ምንጊዜም ቢሆን የእርሱን ድካም ስለሚያውቅና የእግዚአብሔርን እርዳታ ስለሚሻ የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ ላይ ያደርጋል።

💪በክንዱ ሳይመካ በእግዚአብሔር እርዳታ🙏ስለተመካም ያሸንፋል።"

✍️....ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌸መልካም ቀን ይሁንልን
🤲🌷

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

21 Oct, 09:28


ያሬድ ካህኑ ዘመረ✞

ያሬድ ካህኑ ዘመረ(፪)
ዘመረ ያሬድ ዘመረ
አምላኩን አመሰገነ

አርያም በማለት  - - - ያሬድ ዘመረ
ማኅሌት ጀመረ - - - ያሬድ ዘመረ
ዜማውን ከመልእክት እያስተባበረ
ምስጋና አቀረበ - - - ያሬድ ዘመረ
በዜማ መሣሪያ - - - ያሬድ ዘመረ
ጸናጽል አነሳ ከበሮ መቋሚያ
      
በግዕዝ በዕዝል - - -  ያሬድ ዘመረ
በአራራይ ዜማ - - -   ያሬድ ዘመረ
ከብሉይ ከሐዲስ ምስጢር እያስማማ
በዜማው ምልክት - - -  ያሬድ ዘመረ
የአምላክን መከራ - - - ያሬድ ዘመረ
የመስቀሉን ነገር የማዳኑን ስራ
      
ደሙ እየፈሰሰ - - -   ያሬድ ዘመረ
በጦር ተወግቶ - - - ያሬድ ዘመረ
ሊቁ ማኅሌታይ በመንፈስ ተቃኝቶ
በጥዑም ልሳኑ - - -  ያሬድ ዘመረ
በተሰጠው ጸጋ - - - ያሬድ ዘመረ
ለንጉሥ እግዚአብሔር ለአልፋ ዖሜጋ
      
ድጓ ጾመድጓ  - - - ያሬድ ዘመረ
ምዕራፍ መዋሲት - - - ያሬድ ዘመረ
ምሥጢር ተገልጦለት በሰማይ መላእክት
የዜማ መሠረት - - - ያሬድ ዘመረ
ፈልፈለ ዝማሬ - - - ያሬድ ዘመረ
የኢትዮጲያ ኩራት የተዋህዶ ፍሬ

              
21 መዝሙር
ተጨማሪ  ለማግኘት
ይቀላቀሉ  ➟
ለሌሎች ያጋሩ 
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

21 Oct, 02:55


https://youtu.be/TTweH4__d38?si=pXPfCnRH0k7XF7o2

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Oct, 21:54


እንኳን ለቅዱስ ያሬድ ወርሀዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን🌺🌸

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Oct, 19:30


🔴ስግደት 11🔴
➡️➡️➡️➡️➡️
1,የመንፈስ ቅዱስ መሳቢያ
2,የፀጋ ለድንግል ማርያም
3,የፀጋ የቅዱስ ገብርኤልና ሚካኤል
4,የንስሐና አባታችን ሆይ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
@getemegn12
@getemegn1991
@lemelame_4
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
https://youtube.com/@yosef_welde_hawareyat?sub_confirmation=1

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Oct, 19:26


በስህተት ነው የተለቀቀው ከ30 ጠብቁ

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Oct, 16:11


                          †                          

  *_<<የኖህ የቃልኪዳኑ ምልክት>>_*

"ቀስተ ደመና ማርያም ትእምርተ ኪዳኑ ለኖህ
ዘእግዚአብሔር ሤመኪ ለተዝካረ ምሕረት ወፍትሕ
ህየንተ ቀሰፋ ለምድር ወአማሰና በአይኀ፡፡
በእንቲአኪ አሠርገዋ በጽጌ ኲሉ አቅማሕ
ከመበከዋክብት አሠርገዎ ለሰማይ ስፉሕ፡፡"

[ ለምሕረትና ለፍርድ መታሰቢያ አድርጎ ያኖረሽ የኖህ የቃልኪዳኑ ምልክት ቀስተ ደመና ማርያም ምድርን በጥፋት ውሃ ስለመታትና ስለ አጠፋት ፈንታ ፤ ሰፊ ሰማይን ስፍር ቁጥር በሌላቸው ከዋክብት እንደ አስጌጠው ሁሉ በአንቺ ምክንያት ልዩ ልዩ በሆኑ አበባዎች ፍሬዎች ምድርን አስጌጣት ፤ በአንቺ ምክንያት በምድር በጎ በጎ ተዓምራት ተደረገ፡፡ ]

*[ አባ ጽጌ ድንግል ]*

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

20 Oct, 11:03


*በአንተ ማረፍ ማን ይሰጠኛል* ? ልቦናዬ ይጥለቀለቅ ዘንድ ፥ ክፋቴን እረሳ ዘንድ ፥ አንተን ብቸኛው ሀብቴን አቅፍ ዘንድ! ወደ እኔ መግባትህን ማን ይሰጠኛል ? አንተ ለእኔ ምንድነህ? እንድናገር በርኅራኄህ አንደበቴን ዳስሰው ፥ እንዳፈቅርህ ግድ የምትለኝ ፥ ምላሽ ባልሰጥ ቁጣህ የሚነደውና ከለላ የሚያሳጣኝ ፥ እኔ ለአንተ ምንድነኝ ? አንተን አለማፍቀር ራሱ ጉስቁልና አይደለምን ? ኦ ! አቤቱ ጌታዬ አምላኬ ፥ በርኅሩኅነትህ መልስልኝ ፥ አንተ ለእኔ ማን ነህ ? እሰማህ ዘንድ ተናገረኝ ፥ እነሆ በፊትህ የልቦናዬ ጆሮዎች ተከፍተዋልና፥ *አቤቱ ጌታዬ ክፈትና ለነፍሴ "እኔ ነኝ መድኃኒትሽ" በላት* ይህን ድምፅ በሩጫ ተከትዬ በመጨረሻም አንተን ልይዝህ እፈልጋለሁ፤ ሰምቼህ ወደ አንተ ልሩጥ ፥ በአንተም ላይ ራሴን ልጣል ፥ እባክህ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ላለመሞት ልሙት ብቻ ፊትህን ልይ።"

*(ሊቁ አውግስጢኖስ)*

መልካም ዕለተ ሰንበት
https://t.me/getemegn1991

✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️

19 Oct, 21:11


እንኳን አደረሳችሁ🌺

3,267

subscribers

3,373

photos

598

videos