💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞 @menta_lboch Channel on Telegram

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

@menta_lboch


🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ

ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤

HBD ለማለት፤ 🎂

ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀

ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂ & Cross

━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @MENTA_LBOCH ይላኩለት።

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞 (Amharic)

አሁንም በሽታችን ተደፋሁልን። የእኛ የቴሌግራም ቻናሎች ዲስክ አፓላይሲይችን የተከፈቱ ለውጥ ማንበብ እና ሌሎች እንደምንችል ዋጋ እንድናውቀው አይደረስን። ያሀድ ወይም በጣም አአዪል ያስተምር የተወጋ ልቦችና መንታዎችን በብቻ እናመሰግናለን። ስለዚህ በሰርተኛው ማርያም ላይ እንገናኘዋለን። እንዲሁም በአሁኑ ባለ ምዕራፍ እናልብሽሽ ሆኖ የተወደደ ሊሆን እንችላለን።

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

29 Jun, 17:02


🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

29 Jun, 16:51


🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

30 Apr, 16:34


በጣም ሚዋደዱ ሁለት ፍቅረኛሞች ለመጋባት
ይወስናሉ፡፡ ቀለበት ሊያስሩ ጥቂት ወራት
ሲቀራቸው ልጅቱ የመኪና አደጋ ይደርስባት እና
ፊቷ ሙሉ በሙሉ ተበላሸ፡፡ "ቀሪ ህይወቴን መልከ-ጥፉ እና አስጠሊታ ሁኜ መኖሬ ግድ ሆኗል፡፡ ከእንግዲህ ላንተ የምገባ ሴት አደለሁም፡፡ ሌላ ቆንጆ ወጣት ሴት ፈልገህ አግባ፡፡" ብላ ለልጁ ፃፈችለት፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንዲህ ሚል ደብባቤ ደረሳት... "ውዴ ማፈር ያለበት ሰው ካለ እኔ ነኝ ማፈር ያለብኝ፡፡ በአይን ህመም ምክንያት ማየት እንደማልችል ዶክተር ነግሮኛል፡፡ እንዲህ ሁኜ የምታገቢኝ ከሆነ እኔ አንቺን ለማግባት እፈልጋለሁ፡፡" ወዲያው ተጋቡ፡፡ ልጁ ጭራሽ ማየት አይችልም ነበር፡፡

ለ 20 አመታት በፍቅር በደስታ በመተሳሰብ ኖሩ፡፡
እሷ የአይኑ ብርሃን ሁና እየመራችው ፍቅራቸው ፈክቶ በሀሴት ኖሩ፡፡ ከ20 አመት ቆይታ በኋላ ሴቷ በጠና ታመመች፡፡ በባዶ ጨለማ ትቼው ልሞት ነው ካለኔ ማን አለው እያለች ትጨነቅ ነበር፡፡  ሞት አይቀርምና ወደማይቀርበት አለም ሄደች፡፡ ሚስቱ የሞተችበት እለት ሰውየው አይኑን ገልጦ ማየት ጀመረ፡፡ ሰው ሁሉ ተገረመ ደነገጠ "አይነ ስውር አልነበርኩም.... የተበላሸውን ፊቴን አየብኝ ብላ እንዳትሳቀቅ ብዬ ነው አይነ ስውር መስዬ የኖርኩት፡፡" አለ፡፡ የታሪኩ "ሞራል" እዉነተኛ ፍቅር አካላዊ ውበትን ሳይሆን ሚመለከተው ውስጣዊ ውበትን ነው፡፡ ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው ሚመለከተው፡፡



            𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
            💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
             ,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
                •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

30 Apr, 16:28


ታላይነትን.....

ገፅታሽ ማራኪ አንደበትሽ ጣፋጭ
ፈገግታሽም ገዳይ የማይሰጥ አማራጭ

የውበትሽ ብርሃን ከሰማዩ ሚልቅ
የውብ አይንሽ ጨረር የማያነቃንቅ 

ከርቀት ሲታዩ ...
ጥርስና ከናፍርሽ አቤት ማማራቸው
ሰረቅ ሰረቅ አርገሽ በፈገግታ መልኩ ሁሉን ስታያቸው

አንገትሽ መለሎ
አዳም ሚከተልሽ በገላሽ ተታሎ

በሁሉም ተወዳጅ ገፅታ እያለሽ
ሞናሊሳን ሚያስንቅ ፈገግታም እያለሽ
አታላይነትን   ማ'ነው  ያስተማረሽ ?
🤔


𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
       ❤️

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

30 Apr, 16:25


             ባለታክሲው
            
              ክፍል 3

በምን ቅፅበት ከቤት ውስጥ
ተወርውሬ እንደወጣሁ አላውቅም
ብቻ ወንድሜን ፍለጋ ወደቤት ገሰገስኩ...... ጊቢውን ማንኳኳት አይበለው እየደበደብኩ እስኪከፍቱልኝ
ተጣደፍኩ እናቴ ነበረች የከፈተችው አልፌያት ወደውስጥ በሩጫ ገባሁ ምን ሆነሻል ልጄ እናቴ እየተጣራች
ተከተለችኝ ቀጥታ ወንድሜ ወደተኛበት ክፍል አመራው በሩን በርግጄ ገብቼ በተኛበት እላዩ ተከመርኩ ያለየሌለ
ሀይሌን ተጠቅሜ አነቅኩት እናቴ ኡኡታዋን አቀለጠችው ወንድሜ እጄን ካንገቱ ለማስለቀቅ ይታገላል እኔ።
ግሩሜን አንተ ነህ የደበደብከው አንተ ነህ ልትገለው የነበረው እያልኩ ይባስ እጄን እያጠበኩ ታገልኩት እንደምንም መንጭቆ አስለቀቀኝና ከላዩ ላይ ሲወረውረኝ ከግርግዳ ተጋጭቼ ወደኩ ግን ምንም አልመሰለኝም ድጋሜ ተነሳሁና ወደሱ ተንደረደርኩ የእናቴን ጩኸት የሰሙ ጎረቤቶች ቤቱን አጥለቀለቁት እኔንም ወንድሜንም
ያዙን እኔ እጮሀለሁ እሳደባለሁ ወንድሜ ትናንት ላወቅሽው ጎረምሳ እኔን ብቸኛውን ወንድምሽን ልትገይኝ
ልትገይኝ ይላል እናቴ ጥግ ላይ ሆና ታለቅሳለች ጎረቤት ይንጫጫል በቃ
ቤቱ በአንድ እግሩ ቆመ እኔን
ክፍሌ አስገብተው በር ዘጉብኝ ከዛ ቀጥታ ልብሴን በትምህርት ቤት ቦርሳዬ ውስጥ መሰብሰብ ጀመርኩ የቀረውን በፌስታል አድርጌ በመስኮት ዘልዬ ወጣሁ እናቴ አንዷ ጎረቤት አይታ ያዘችኝ ልቁቀኝ እዚ ቤት አልቀመጥም
አልኩኝ ብለመን ብሰራ ማንም አልሰማም አልኩ ወደቤት
ከመለሳችሁኝ እራሴን አጠለፋሁ ያለዛ ልሂድበት ልቁቀኝ ብዬ እሪ አልኩኝ ወንድሜ ከውስጥ ወጣና  ተዋት ትሂድ
ጎረምሳ ከበለጠባት ትሂድ ግን እወቂ እሬሳውን ባላሳቅፍሽ እኔ እዮብ አይደለሁም  አለኝ  እሬሳውን አታሳቅፈኝም ከገደልከውም አብረህ ነው
የምትገለን ከዚህ በኃላ እንኳን ቀን ለሊት እራሱ ከግሩም አጠገብ አታጣኝም  ብዬው እናቴ ደንግጣ ቁጭ ባለችበት በረንዳ ላይ። ሄጄ  እማ አንቺ ግን ይቅር
በይኝ አልኳትና ጉንጯን ስሜያት ወጣሁ ወደ ግሩም ሄድኩኝ የሆነውን ሁሉ አጫወትኩት በጣም አዘነ እንዲ
ማድረግ እንደሌለብኝ ነገረኝ ሆኖም አብሬው ልኖር በመምጣቴ ደስ አለው አባቴ ማታ ከስራ ሲገባ የሆነውን
ሰምቶ ደወለና ልጄ አንገቴን አስደፋሽኝ በተከበርኩበት ሰፈር
አዋረድሽኝ ካሁን በኃላ አባት አለኝ ቤተሰብ አለኝ ብለሽ እንዳታስቢ  ብሎ ስልኩን ዘጋብኝ ለጊዜው አባባሉ
ቢያስጨንቀኝም ትክክለኛ ውሳኔ እንደወሰንኩ ስለተሰማኝ ተውኩት ኑሮዬም ከግሩሜጋር ሆነ እሱም ድኖ ተነሳ ላዳው ታክሲውን ሽጧት አብነት አከባቢ ሰፋ ያለ ቤት ተከራይተን የቤት እቃ አሟልተን እሱም በሚኒባስ ታክሲ
ላይ በሹፍርና ተቀጥሮ እየሰራ እኔም ማትሪክ ውጤቴን እየጠበኩ ሽማግሌ ሰርገኛ አጃቢ በሌለበት ፍቅር ደግሶ
ፍቅር ሞሽሮ ፍቅር አፈራርሞ ዳረንና የአብሮነትን ህይወት ተካፍለን መኖር ጀመርን።
አቤት እንዴት ደስ ይል ነበር.... ያየን ሁሉ ካይን ያውጣችሁ እስከሚለን ድረስ በፍቅር ከነፍን እኔም ማትሪክ ውጤት አልመጣልኝም ነበር ከምቀመጥ የፀጉር
ሞያ ተምሬ ኑሮዋችንን ለማገዝ ተነጋግረን መማር ጀመርኩ እናቴን ወንድሜና አባቴ ሳይኖሩ በድብቅ እየሄድኩ አያታለሁ እሷም በድብቅ ቤቴ ትመጣለች እኔና ግሩሜን
አይታን ትሄዳለች።
በዚህ መልኩ ህይወት ቀጠለ ከ6 ወር በኃላ በፀጉር ሞያ ተመረቅኩኝ ከምርቃቴ ጋር ሌላ የምስራች ተፈጠረ
አረገዝኩ በወቅቱ የነበረን ደስታ እንዲ ተፅፎ የሚያልቅ አልነበረም። ግሩሜ ከቤተሰብ ጋር እርቅ እንዲወርድ
አግባባኝ አባቴ ተለምኖ እርጉዝ መሆኔ ተነግሮት ይቅር አለኝ ከወንድሜም ታረቅን በቃ ይባስ ቤታችን በደስታ
ተጥለቀለቀ የማናውቀውን ልጃችንን መናፈቅ ጀመርን እንዳይደርስ የለ መውለጃዬም ደርሶ ሴት ልጃችን ይህቺን
አለም ተቀላቀለች። ስሟን  ሀሴድ አልናት። ሀሴድ የመፀሀፍቅዱስ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ተዝቆ የማያልቅ ፍቅር ማለት ነው። አቤት የነበረን ደስታ............ ታድያ ይህን ደስታ ያጠቆረ አንድ መፍፎ ቀን ተፈጠረ.........
ገና ወልጄ ከተኛሁ 2 ወሬ ነበር ያን ቀን ግሩሜ ከምሽቱ 2 ሰዓት አከባቢ ደወለልኝና ማማዬ የሆኑ የደብረዘይት
ሰዎች መኪና አጥተው ደብረዘይት ካደረስከን አንድ ሺህ ብር እንከፍልሃለን አሉኝ ደግሞ 6 ናቸው እና ገንዘቡ
ከመጣ ይጠቅመናል ይሄን እድል ማሳለፍ የለብምኝ አድርሻቸው እልለልለሁ ላሳውቅሽ ብዬ ነው አለኝ
ውስንጤ ደስ ባይለውም እሺ አልኩት ከዛም ግን 5 ሰዐት አለፈ አልመጣም ስልኩ ላይ ደወልኩ ይጠራል አይነሳም....... ደግሜ ሞሞከርኩ...........


   🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
      

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

28 Apr, 09:35


🥀🌹አንድ አጭር የፍቅር ታሪክ ልጋብዛቹ

       በአንድ ወቅት ሁለት እጅግ የሚዋደዱ ፍቅረኛማቾች💃 ነበሩ፡፡ በፍቅራቸው ሙሉ አካባቢው ይቀናባቸዋል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ግን በአንድ ሆቴል  ልጆቷ በድንገት ከሌላ ወንድ ጋር ትታያለች፡፡ በዚህ ሰአት የሆነ ሰው ደውሎ "ና የፍቅረኛህን ቅሌት ተመልከት" ብሎ ይነግረዋል፡፡ ልጁም ካለበት በፍጥነት ሲመጣ ክፍል ይዘው ገብተዋል፡፡ ገቡ ወደተባለበት ክፍል ቀርቦ ሲያዳምጥ ከውስጥ ይሳሳቃሉ፡፡ እስከመጨረሻው የመታገስ አቅም አልነበረውም፡፡
        በኔ ላይ ሌላ ወንድ ? ሲል ይናደዳል😡፡፡ በዚህ ግዜ የሷ ጉዋደኛ የሆነች ልታፅናናው ትቀርበዋለች፡፡ እሱም አጋጣሚውን በመጠቀም እንደውም ላስቀናት በሚል እሷ በምታየው ቦታ ጓደኛዋን እየወሰደ ያዝናናታል እንደፍቅረኛ አድርጎ ለሰው ያወራል፡፡
      ከ ወር ቡሀላ ፍቅረኛው ሞተች፡፡ በዚህ ግዜ በእናቷ በኩል አንድ ደብዳቤ አስቀምጣለት ነበር፡፡ እሱ የኔ ግፍ ነው ብሎ በቀብር ስርአቱ ላይ እንኳን አልተገኘም፡፡ እናትየዋ ባለበት ሄዳ የልጇ አደራ የሆነውን ደብዳቤውን ሰጠችው፡፡ ደብዳቤው ይህን ይላል፡፡
       😍😍   "ውዴ የኔ ፍቅር አንተ አዝነክብኛል እኔ ግን ተደስቻለው፡፡ ያን ቀን ሆቴል ደውዬ እንድትመጣ ያደረኩት እኔ ነኝ፡፡ በዛ ክፍል ውስጥ ምንም አልተፈጠረም፡፡ አንተ በኔ ተናደክ ወደሌላ ሴት እንድትሄድ የሰራውት ድራማ ነበር፡፡ በሀዘንህ ሰአት ያፅናናችክ ጉዋደኛዬ እኔ ነኝ የላኳት፡፡ እሷ በጣም ትወድካለች ፡፡ እንዳትተዋት፡፡ አንተ እኔን ለማስቀናት ፍቅር ስትሰጣት ሳይ እኔ እደሰት ነበር፡፡ ያንን ፍቅር ከልብህ አድርገው፡፡ ደስታህን አይቼ በመሞቴ እድለኛ ነኝ፡፡ ቢያንስ ብቻክን አልተውኩህም፡፡ ይሄንን ያደረኩት ለመሞት 30ቀን ብቻ እንደቀረኝ ሳውቅ ነው፡፡"

"ፍቅር ማለት አብረው ላሉት ብቻ ሳይሆን ትተውት ለሚሄዱትም ደስታ መጨነቅ ነው፡፡"


⭐️𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑⭐️🌹

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕❤️

,,,,,,,,,,,🌹❣️🌹❣️🌹❣️,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,✉️ @menta_lboch
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
       ❤️

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

28 Apr, 09:28


ግጥም

💔 ልቤ ምን አጠፋ💔



እኔስ መስሎኝ ነበር ካንጀት ያፍርከኝ
ልቤን አብከንክነህ ምነው ጉድ አረከኝ
መውደዴን ነግሮህ የሆዴን አውጥቼ
መዋል ማድር አልችል ካንተ ተለይቼ
ሃሳቤ ጭንቀቴ ቢገባህ ምን አለ
ሌላ ብትቀይር ምን የተለዬ አለ?


ልቤን ብቻ ይዘህ ለምን ትዞራለህ
ተመልሰህ ጨርስ ነፈሴነው የቀረህ
ያንተው ህመምተኛ ባይተዋር ሆኛለሁ
ህመምተኛ አደርኸኝ ለማን እሆናለሁ


እንግዲህ ኑሮዬ በዱር በገደል ነው
ከሰው መኖር አልችል ልቤ ካንተ ጋር ነው
አልበላም አልጠጣም ልድረቅ ልሁን እንጨት
የልቤን ከተማ ብቻ አንተ ኑርበት፣



አላስገድድህም ና ተመለስ ብዬ፣
ሁለተኛ ብትሄድ ምን ዋስትና ጥዬ
ያሁኑም ስራህ ምን ይታወቅሃል
የጊዜው ይርዘም እንጂ ልቤ ይፈርዳል
ጊዜው ይርዘም እንጂ እንባዬ ይፈርዳል 💔

𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕❤️
,,,,,,,,,,,🌹❣️🌹❣️🌹❣️,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,✉️ @menta_lboch
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
       ❤️

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

27 Apr, 17:15


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
            
​ ባለታክሲው🚕

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
            
         
⭐️ክፍል 2️⃣

እኔ በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ ትናንትና ነው ያየሁት እሱ እንዴት ስለኔ ይሄን ያህል ሊያውቅ ቻለ? ይሄን
እያሰብኩኝ ተከፍቶ ወደሚጠብቀኝ በር ገባሁ። መንገድ ጀመርን ስለራሱ እንዲነግረኝ ጠየኩት ተወልዶ ያደገው
ጨርቆስ አከባቢ እንደሆነና የወንድ አያቱ እጅግ ይወዱት ስለነበረ ሲሞቱ መሬት አውርሰውት ሞቱ መሬቱ ተሽጦ
እቺን ላዳ ታክሲ ገዝቶ ስራ መጀመሩን አጫወተኝ ግሩም ደስ የሚል ልጅ ነው ከውበቱም በላይ በዚች 2 ቀን ውስጥ ያሳየኝ መልካምነትና ስነምግባር በጣም የሚገርም ነበር እኔን የት እንደሚያውቀኝ ጠየኩት ሁሌ ታክሲ ስጠብቂ አይሻለሁ ደግሞ ሁሌ ብቻሽን ስለማይሽ
ይገርመኝ ነበር ከዛ አንድ ቀን የተሳፈርሽበትን ታክሲ ተከተልኩት አለምባንክ ስትወርጂ አየሁሽና መኪናዬን
ጥግ ላይ አቁሜ በእግሬ ተከተልኩሽ ከዛ ቤታቹ ስትገቢ አየሁሽ በራቹጋ የሆነ ጩጬ ሰላም ስትይ ስላየሁሽ
ጠራሁትና ያሁኗ ልጅ ስሟ ማነው ስለው ሊዲያ አለኝ ከዛ በቃ ሁሌ አንቺን መከታተል ስራዬ ሆነ አለኝ
አሁን የቅድሙ ጭንቀቴ ለቀቀኝና ዘና ብዬ ማውራት ጀመርኩ እየተጨዋወትን ትምርት ቤት ስለደረስኩ አውርዶኝ ከትምህርት መልስ እንደሚጠብቀኝ ነግሮኝ ሄደ እሱን እያሰብኩ አይደርስ የለ ትምርት አልቆ ስወጣ አገኘሁት ደስ አለኝ ደስታዬ ዉደር አልነበረውም።
በዚህ መልኩ ጠዋት ጊቢያችን በር ላይ ከሰዓት ትምህርትቤት በር ላይ መገናኘት ስራችን ሆነ የፍቅር ጥያቄ ከማናችንም አፍ ሳይወጣ በፍቅር ከነፍን እኔማ
ትምህርቴ ግሩም ስራዬ ግሩም ውሎዬ ግሩም ህልሜ ግሩም በቃ እስትንፋሴ ይመስል የሱን ስም ሳልጠራ
የማወራው ወሬ ጠፋ እሱን ሳላስብ የምታልፍ ደቂቃ ጠፋች እራሴን እስክረሳ ድረስ ወደድኩት።
በዚ መሀል ታላቅ ወንድሜ ሰማ እንዴት ምን ሲደረግ እንኳን አንቺ አንድ ፍሬዋ ልጅ እኔ ታላቅሽም ፍቅር
አልጀመርኩም አሁኑኑ ይሄን ነገር አቁመሽ ትምህርትሽ ላይ ብቻ አተኩሪ ድጋሜ ከዛ ልጅጋር እንዳላይሽ አለኝ
እኔ ግን ማንንም የምሰማበት ሰዓት አልነበረም ከግሩሜጋር እንዳላይሽ ከምትለኝ በህይወት እንዳላይሽ
ብትለኝ ይሻለኛል  አልኩት በቃ ሁሌ ቤቱ ውስጥ ጭቅጭቅ ሆነ ሁኔታችን ግራ ያጋባት እናቴ ምንድነው ብላ
ስትጠይቅ ወንድሜ ሁሉንም ነገር ነገራት እናቴ በተራዋ እሪ አለች እኔ ግን ህይወቴ ታልፋታለች አላቆምም አልኩኝ
እንዲ እንዲ እያለ ጊዜውም ሄዶ ማትሪክ ተፈትኜ ት/ት ተዘጋ የትምህርት መዘጋት ለኔና ለግሩሜ ይባስ ምቹ ሆነልን ጠዋት ከሰፈር ይወስደኛል አዲስ አበባን ከሲኒማ ቤት እስከ ሆቴል ስናስሳት እንውልና ማታ ወደ ቤት ይመልሰኛል። የወንድሜና የእናቴ ጭቅጭቅ ከቀን ወደ
ቀን እየባሰ መጣ እኔ ግን ጆሮ አልነበረኝም ግሩሜ እስከዛሬ እንዴት ያለሱ ኖርኩኝ ብዬ እስከማስብ ድረስ
ህይወቴን በደስታ ባህር አጥለቀለቃት።
ታድያ አንድ ቀን እንደተለመደው አብረን ውለን ደስ የሚል ቀን አሳልፈን እቤት በር ላይ አውርዶኝ ተለያየን ሁሌም
ማታ ማታ ከተለያየን በኃላ እቤት ሲደርስ በሰላም መግባቱን ደውሎ ይነግረኛል ያን ቀን ግን ብጠብቀው ብጠብቀው አልደወለም እኔ ስደውል ስልኩ ዝግ ነው
ትንሽ ብጨነቅም ምናልባት ባትሪ ዘግቶበት ይሆናል ብዬ ተኛው ጠዋት ስነሳም አልደወለም ስሞክርም ዝግ ነው
አሁን በጣም አሳሰበኝና አንድ ብሩክ የሚባል ጓደኛውጋ ደወልኩ ከብዙ ጥሪ በኃላ አነሳው ሰላምታ እንኳን
ሳልጠይቀው ቀጥታ ወደጉዳዬ ነው የገባሁት ብሩክ ግሩሜ ምን ሆኖ ነው ስልኩ ማይሰራው?
አልኩት ብሩክ እየፈራ
ሊዱ ግሩሜ ማታ አንቺን ሸኝቶ መኪናውን ማደሪያ ቦታ
አቁሞ ሲመለስ ሌቦች ገንዘብ የያዘ መስሏቸው ደበደቡት አሁን እዚ አለርት ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ተኝቷል እኔም
አጠገቡ ነኝ ከዚህ በኃላ የተናገረውን አልሰማሁትም ከአልጋዬ ተወርውሬ ተነስቼ ጠረቤዛ ላይ ያገኘሁትን ብር
አንስቼ እሮጥኩኝ በምን ፍጥነት ከሆስፒታሉ እንደደረስኩ አላውቀውም ከብዙ ፍለጋ በኃላ ግሩሜ የተኛበትን ክፍል አገኘሁት እላዩ ላይ ተጠምጥሜ አለቀስኩ አበድኩ እንደምንም ብሎ
አይዞዞሽ ማሬ ደና ነኝ እኮ አለኝ በቃ ውሎዬ እዛ ሆስፒታል ሆነ እቤት የምገባው ለማደር ብቻ ነው እሱንም
አባቴን ፈርቼ እንጂ ከግሩሜ ባልለይ ደስታዬ ነበር።
ከሳምንት በኃላ እቤት ሆኖ ህክምናውን መከታተል እንደሚችል ተነግሮት ከሆስፒታል ወጣ እኔም እቤቱ
እየዋልኩ ማስታመም ጀመርኩ
ታድያ አንድ ቀን ጠዋት እቤት አድሬ ወደሱ ቤት ስመጣ ጓደኞቹ ተሰብስበው እያወሩ ደረስኩ በሩ ክፍት ስለነበረ
መግባቴን ማንም አላየም አንደኛው ጓደኛው ቆይ ለምን እንሷን መደበቅ አስፈለገ ገሎህስ ቢሆን
ኖሮ? ፈጣሪ ነው ያተረፈህ እንጂ እሱማ የሞትክ መስሎት ነው ጥሎህ የሄደው ነገስ ቢጨርስህ ምን ይታወቃል?
ብሩክ ከሱ ተከትሎ እኮ እኔም ያንን ቀን ይነርራት ስል አይ ተው ብለህ አስዋሸኸኝ ቆይ እሱ ወንድሟስ ቢሆን
እንናተ ከተዋደዳቹ ምን አግብቶት ነው የሚያለያያቹ? የሰማሁትን ማመን አልልቻኩም በቆምኩበት መንቀጥቀጥ
ጀመርኩ ብሩክ ምንድነው የምታወሩት ግሩሜን ማን ነው የደበደበው? አልኩኝ ሁሉም ደንግጠው ወደኔ ዞሩ
መልስልኝ ብሩክ ማነው የደበደበው? ብሩክ ፀጉሩን እያሻሸ.....
ሊዱ ያኔ እኔ እውነቱን ልነግርሽ ስልእሱ ነው ተው ከወንድሟ ትጣላለች ብሎ ያስዋሸኝ እንጅ ግሩሜን
ወንድምሽ ነው ልጆች ቀጥሮ ያስደበደበው አለኝ በምን
ቅፅበት ከቤቱ ውስጥ ተወርውሬ እንደወጣሁ አላውቀም ብቻ ወንድሜን ፍለጋ ወደቤት ገሰገስኩ......



    ‌‌‌‌‌‌‌     

🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

        
𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕❤️
,,,,,,,,,,,🌹❣️🌹❤️🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️ 🍃🌺🍃♥️•••═•
  
@menta_lboch @menta_lboch
   
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
​​

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

27 Apr, 17:04


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
             ‍ ባለታክሲው🚕

💟

          ⭐️ክፍል 1️⃣

ሊዲያ ሀጎስ እባላለሁ ተወልጄ
ያደኩት እዚሁ አዲስ አበባ
በተለምዶ አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ነው።
እንዳብዛኛው ኢትዮጵያዊ መካከለኛ
ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ነው የተወለድኩት ታድያ የዛሬው ታሪኬ የሚጀምረው የ10ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነበር።
የምማረው አየርጤና ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ነበር (ምናልባት እዛ አከባቢ የሆናችሁ ታውቁታላችሁ) እናም ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድም
ለመመለስም ግዴታ ታክሲ መጠቀም አለብኝ ምክንያቱም ት/ቤቱ ከሰፈሬ በጣም ይርቃል ከዛ እንደልማዴ ትምህርት ጨርሼ ወደ ሰፈሬ የሚሄድ ታክሲ እየጠበኩኝ እያለ አንድ ላዳ ታክሲ መቶ አጠገቤ ቆመና ሹፌሩ በመስኮት በኩል ተንጠራርቶ አለምባንክ ነሽ አይደል ነይ ግቢ አለኝ እኔም ትንሽ
ተናድጄ  አመሰግናለሁ እኔ ታክሲ ነው የምጠብቀው ለላዳ የሚሆን ሳንቲም የለኝም አልኩት አውቃለው
ባክሽ ነይ ግቢ እኔም ወደዛው ስለሆንኩ እግረ መንገዴን ላድርስሽ ብዬ ነው ምንም አላስከፍልሽም አለኝ
አልገባም አልኩት ከመኪናው ወርዶ ወደኔ መጣ በጣም ቆንጆ ነው እዚ ከምትቆሚ ብትገቢ ይሻልሻል ታክሲ
አታገኚም አለኝ የገቢናውን በር ከፍቶ በእጁ ወደውስጥ እያመለከተኝ እውነትም ረጅም ሰዓት ቆሜያለሁ በዛ ላይ እርቦኝ ነበር ገባሁ መንገድ ጀመርን ግን ሰፈሬ አለምባንክ መሆኑን እንዴት አወክ? አልኩት
ምን እዚ ታክሲ ተራ አይደል እንዴ እንደ አደባባይ ሀውልት ቆመሽ ምትውይው  አለኝ ከት ብዬ ሳኩኝ
ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው እያወራን ሰፈር ደረስን ልወርድ ስል ግሩም እባላለሁ ስልኬ እዚ ላይ አለልሽ በማንኛውም ሰዓት ብትደውይ እገኛለሁ አለኝ ቢዝነስ ካርዱን እየሰጠኝ አመስግኜው ወደ ቤት ገባሁ ግን በጣም ደስ ደስ እያለኝ ነበር ሁሉ ነገሩ ጨዋታው ቀልዱ ውበቱ ያቺን ትንሽ ልቤን አሸበራት።
እሱን እያሰብኩ ነጋ ጠዋት ላይ እንደልማዴ ወደ ትምህርት ለመሄድ ዩኒፎርሜን ለብሼ ቦርሳዬን አንግቼ እየተጣደፍኩ ከቤት ስወጣ ልክ የግቢ በራችን መውጫ ላይ ግሩም ላዳ
ታክሲውን ተደግፎ ቆሟል።
እሱ መሆኑን ሳአለቀቀኝም ነበር የደነገጥኩት  ምን ትሰራለህ እዚ  አልኩት መጀመርያ እንዴት አደርክ አይቀድምም? አለኝ ረጋ ብሎ
እሱማ ደና ብታድር አይደል እንዴ ያገኘሁክ ይልቅ ምን ትሰራለህ?ድንጋጤዬ አለቀቀኝም
አረ ተረጋጊ ሴትዮ ባልሽ ቤት የመጣሁ አስመሰልሽው እኮ እኔ እዚ የታመመ ሰው አምጥቼ በዛው በበራቹ በኩል
ሳልፍ ትዝ ብለሽኝ ቆይ እስኪ እቺ ልጅ ደሞ እንዳመሏ ታክሲ አታ እንዳትንገላታ ብዬ እየጠበኩሽ ነበር አለኝ
እየሳቀ ቤታችንን እንዴት አወቅከው? አፈጠጥኩበት እንኳን ቤታቹን የትምህርት ቤት ክፍልሽን ሁሉ
አውቀዋለሁ አረ እንደውም የምትቀመጪበትንም ቦታ
አውቀዋለሁ ይልቅ ነይ ግቢ ትምርት እንዳይረፍድብሽ አለኝ የገቢናውን በር እየከፈተ አሁን የባሰ ግራ ተጋባሁ
እኔ በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ ትናንትና ነው ያየሁት እሱ እንዴት ስለኔ ይሄን ያህል ሊያውቅ ቻለ?
ይሄን እያሰብኩኝ ተከፍቶ ወደሚጠብቀኝ በር ገባሁ........


🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕❤️
,,,,,,,,,,,🌹❣️🌹❤️🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️ 🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,, @menta_lboch
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

26 Apr, 17:26


የፍቅር ታሪክ ይጀመር የምትሉ 👍

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

26 Apr, 17:16


❤️. . . . ❤️ለምንስ አጣሁሽ❤️ . . . .🫥

ለስንት አመት ሙሉ ልቤ በሩን ዘግቶ
ሠውንም ለመቅረብ አሻፈረኝ ብሎ
ሠላም እየኖረ ሁሉንም ረስቶ
ድንገት ሳያስበው አንቺ መጣሽና
በሩን ስታነኳኪ ክፈትልኝ ብለሽ
እሱም ግራ ገብቶት ትንሽ ተርበትብቶ
እስኪ ይሁን ብሎ ዝጉን ከፈተና
ተቀብሎሽ ነበር ሁሉንም አየና
ውዴ ግን ከምን ጊዜው ሀሳብሽ ጠፋና
ሁሉንም ረስተሽ መለየት አመጣሽ
ለምንስ ቀረብሽኝ ለምንስ አጣሁሽ??

🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

31 Dec, 00:29


አንዳንዴ የሁሉም ሰው ችግር ፈቺ ስትሆን ላንተ ሰው ታጣለህ ሀሳብ አዳማጭ ..ለሰዎች መፍትሄ ፈላጊ.. ሰው ለልቡ ሰው ሲያስፈልገው አያገኝለትም..
   ከህይወት አንድ እርምጃ ከፍ ማለትኮ የነገሮች መጨረሻ አይደለም.. ህይወት አይደል እንዴ?? ከፍ ስትል ፈተናዎችህም በደረጃህ ልክ ከፍ ይላሉ.. ነገር ግን ከፍ ላለው ችግርህ ተመጣጣኝ መፍትሄ የሚያመጣ ሰው አይገኝም.. ሁሉም በራሱ ልክ ነው መፍትሄ ያለው.. በደረጃው ፣ በልኩ ነው ሊያስብ የሚችለው።

𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

29 Dec, 19:00


እኔ ሰው የምመክረው ከራሴ ተነስቼ ነው ወጣትነት በጣም ከባድ ነው ብዙ ነገሮች የሚያምሩን የኑሮ ፈተናን የምንጀምርበት ነው ሞቴን የተመኘውበት ቀን አለ ማንም አደለም ያስቆመኝ ፈጣሪ እንጂ እና ጉድለታችንን ፈጣሪ ይሙላልን እያልኩ አሳቤን አቀርባለው ሁላችንም ያለንን ነገር ብንናገር በዚ ቻናል የጎደለንንም በንገልፅ ጉድለታችንን ብንሞላላ ህይወታችንን ማቅለል እንችላለን ከፈጣሪ ጋር ለምሳሌ እኔ የስነፁፍ ተሰጦ አለኝ ግጥም ፣ድርሰት ፣ዜማ ፣እሰራለው ድምፅ እናሙዚቃ የመስራት ፍላጎት አቅም ላላቸው ግጥም ዜማ ላጣ መስጠት እችላለው አንድ ጉድለት ሞላው ማለት አደለ ሌላው ድርሰቴን ደሞ ፕሮዲውስ የሚያደርግልኝ ባገኝ ጉድለቴን ሞላልኝ ማለት ነው እንደዚ በየአለን ነገር እየተረዳዳን ወደ ስኬት እና ወደ ደስታ እንጓዝ ዘንድ እኔ ፍቃዱ እባላለው ፣፣፣፣ስለህይወት አንድ ግጥም ልጋብዛችው እና እንለያይ አስተያየት ፃፉልኝ የግጥሜ እርዕስ፣ ህይወት ፣ስኖር እንደኖርኩኝ ፣ስሞት እንደሞትኩኝ ፣ሰው ማውራቱ ላይቀር ፣ህይወትን ስንኖራት አይቀርም መቸገር፣ችግር ግንብርታት ነው ስንት ችግር አለፍኩ ፣ማመስገንን ትቼ ራሴን እያስጨነኩ፣በግዜው ሊሰጠኝ የሚያስፈልገኝን ፣አላማርረውም እኔየፈጠረኝን፣ያሰብነው ነገር ባይሆን ምናልባት፣መጉደሏ አይቀርም ህይወት እንደዚ ናት፣ሰው ስላለ እንጂ ምድር ምድረ በዳ ፣ህይወት እንድትቀለን እኛ እንረዳዳ፣እራሳችንን ብናይ ብዙ ነገር አለን ፣ለሌለንም ነገር ፈጣሪ ይመስገን ፣ሀላችውም አሜን ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

26 Nov, 13:21


Questions To ask

#ወሬ_እየጠፋባችሁ_ተቸግራችኋል_እንግዲያስ_አይጨነቁ_እነሆ_መፍቴሄውን_በትንሹ_ይዘንላችሁ_መተናል

እኛ አንድላይ ስንሆን ደስ የሚልሽ ነገር ምንድን ነው ?

የሆነ ምክንያት ልትነግሪኝ ትችያለሽ ለምን እንደምወድሽ ?

አሁን ከንፈሮችሽን ብስምሽ ምን ታደርጊያለሽ ?

እንዴት ይሄንን ቁንጅና ተጎናፀፍሺው ?

ከኔ ጋር Date ማድረግ ትፈልጊያለሽ ?

ወደፊት በሕይወትሽ ውስጥ ልታይኝ ትፈልጊያለሽ ?

ከኔ ደስ የሚልሽ ነገር ምንድነው ?

የት መሳም የበለጠ ያስደስትሻል ?

ከኔ መጀመሪያ የተደነቅሽብኝ ነገር ምንድን ነው ?

ሶስት ቃላት ተጠቅመሽ እኔን ግለTsiኝ ?

ምን ታስቢያለሽ ፍቅር ( ወሲብ ) የትኛውም ቦታ መስራት ወይም አልጋ ላይ ብቻ መስራት ?

ሰው በበዛበት ቦታ መሳሳም እንዴት ታዪዋለሽ ?

ምን ማድረግ ትፈልጊያለሽ እኔ አሁን አንቺ ቤት ብሆን ?

ስለ አንቺ ምን እንደሚሰማኝ ማወቅ ትፈልጊያለሽ ?

ስለ እኔ ምን እያሰብሽ ነው አሁን ?

ተጨማሪ የፍቅር ጥያቄ ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@MENTA_LBOCH

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

19 Nov, 19:13


ምን ሆነሻል🥺🥺🥺

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

18 Sep, 02:24


ከጨለመ አይደል...
          ኩራዝ ትዝ ሚልህ
መሸት ሲል አይደል...
     የብርሃን ጥቅሙ የሚገለጥልህ
ሲበርድህም አይደል...
          ፀሀይ ምትናፍቀው
     [እንግዲህ እሷንም]
ያጣሃት እለት ነው...
       ፍቅሯን እምታውቀው

🥰🥰 😘😘  🌷🌷😍🙏🙏🥀🥀

   🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,📩 @joon_vision
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

18 Sep, 02:22


 😢 አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል😔

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛


            🌹ክፍል አንድ (1)❤️

     ሂክማ እባላለሁ ተወልጀ ያደኩት በመዲናችን አዲስ አበባ ገርጂ አካባቢ በሚባለዉ ሰፈር ሲሆን ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ሴት ልጃቸው ነኝ፡፡ ቤተሰቦቼ ለኔ ያላቸው ፍቅርና ስስት በቃል የሚገለፅ አይደለም! ፍላጎቴ ሳይዛነፍ አቀማጥለው ነው ያሳደጉኝ፡፡ በጥሩ ስነምግባር በኢስላም ተርብያ ዲኔን እያስተማሩ የአንድ ብቁ እና ንቁ እሆንላቸው ዘንድ ተንከባክበው አሳደጉኝ፡፡ የኔም የዋዛ አልነበርኩም በትምህርቴም ሆነ በቂርአቴ ስለጉብዝናየ ኡስታዞቼ እና መምህራኖቼ ምስክር ናቸው፡፡ ቦሌ መድሀኒያለም preparatory school የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡ ጓደኞቼ ስለኔ መልካምነት አውርተው አይጠግቡም፡፡
     መምህራኖቼ ገና በዛ የአፍላነት እድሜ 1 ብሎ በሚጀምርበት fire age ተብሎ በሚጠራው እድሜ ክልል ውሰጥ ሆኜ የባህሪ ለውጥ ያለማሳየቴ ለመምህሮቸ ትንግርት ሆኖባቸውም ነበር፡፡ ከዛም በኃላ ለኔ ያላቸው ውዴታም ክብርም ከፍ ያለ ነው! እንደ ትልቅ ሰው ጓደኛቸው አርገው ያዩኛል፡፡
       አባቴ የመንግስት ሰራተኛ ሲሆን  ሸዋሮቢት በምትባለዉ ከተማ  ነበር የሚሰራው ብዙ ጊዜ ፊልድ ስለሚበዛበት ከሸዋሮቤትም ወደ ሌላ ሀገር ይሄድ ነበር እቤትም  እማ ብዙ ጊዜዋን ከኔ ጋር ታሳልፍለች፡፡ አሁን ላይ ሰወች ለሚወዱት ማንነቴ ግንባታ ኡሚ ከፍተኛውን ድርሻ ትወስዳለች! ወደ መልካም ነገር የምታመላክተኝ መንገድ መሪየ ኡሚ ናት፡፡  አባቢ ለእማ ልዩ ፍቅርና ክብር አለው መልካምነቷና ብልህነቷን ያደንቃል፡፡ በተለይ ደግሞ የአይኑ ማረፊያ የሆነችውን አንድ ልጅን ዲኗን እንድታውቅ መንገድ መሪ ሆናት ልጅም በሰወች ዘንድ ተወዳጅ እንድትሆንለት ከፍተኛውን ድርሻ ለወሰደቾው እናቴ አድናቆቱ ከልብ ነው፡፡

    እኔም "አላህ ኸይርን ሽቶልኝ ዲኔን አስገንዝቦኛል! አንድ ስህተት እንዳለኝ አቀዋለሁ የሰዉ ልጅ ነኝ እና መሳሳቴ አይቀርም ጓደኞቼ ሁሉም profile pictur የራሳቸዉን ፎቶ ስለሚያረጉ በጓደኞቼ ግፊት እኔም profile የራሴን ማረግ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ፡፡ ፎቶ መነሳቱ ሀራም መሆኑን እያወኩ ግን ጓደኞቼ ጋር ሰርግ በሚኖረን ሰአት ትምህርት ስንሄድ የማስታወሻ ፎቶ እየተባለ እየተነሳን profile ለማረግ እንቸኩል ነበር፡፡
       በዛም ላይ የማላቀዉን ለማወቅ በተለያዩ social media ላይ የዳእዋ ጥሪ የሚያረጉ ግሩፓች ላይ ተሳታፊ ሆንኩኝ፡፡ whatsap እና telegram የኔ የዳእዋ ጥሪ መገልገያ ከሆኑ ሰነበቱ፡፡ ብዙ group ላይ እኔን add ያረጉኛልበትምህርት ቤት የሚከፈቱ የሰፈር ልጆች የሚከፍቱት group ላይ ብዙ group ገብቻለሁ አገለግላለሁ፡፡ በቦሌ priparatory scholl አንዱ ልጅ group ከፍቶ በጣም ብዙ ተከታታይ ያለዉ ኢስላሚክ group ሁኖ ነበር ከዛም ዉጭ ሌላ group ነበሩኝ፡፡ ፎቶየን እቀያይር ነበር የትዳረ ጥያቄ በቤተሰቦቼ እየመጣ ትምህርቴን ልጨርስ እያልኩኝ አሳልፊያለሁ፡፡
      እናቴም ግን የዩኒቨርስቲ ዉጤት ቢመጣልሽ አትማርም ወደ ትዳር ነዉ የምገቢዉ ልጅ ወልደሽ ማየት እፈልጋለሁ እንጂ ዩኒቨርስቲ ገብተሽ ጊዜ እንድፈጂ አልፈልግም ብቻ ትምህርት እንደጨረሽ ከተቻለ አንቺ ያመጣሽዉን ባል እቀበላለሁ ግን ኢማን የሌለዉ ከሆነ እኔ የጠየቁኝ ያዘጋጀሁልሽ ትምህርቷን ትጨርስ ብየ የመለስኳቸዉ ስላለ እኔ የወደድኩትን እንደምወጂ እርግጠኛ ነኝ አለችኝ፡፡
...እናት ወልይ ናት አይደል የሚባለዉ እኔም እሺ ማሚ ነበር መልሴ፡፡እኔም ተፈትኜ ዉጤት ቢመጣም ዩኒቨርስቲ ላልገባ ወስኛለሁ፡፡
ብዙ  የሚያወሩኝ የማላቃቸዉ ልጆች ቁጥሬን ከየት አገኛችሁ ብየ ስጠይቅ ከGroup አድራሻሽ ነዉ ቁጠርሽ የለንም ይሉኝ ነበር ከዛ በblock አሰናብት ነበር፡፡
     
    ከእለታት አንድ ቀን ግን ከወትሮው ለየት ያለ ነገር አጋጠመኝ፡፡ ከማላውቀው ሰው በእኔ በtelegram ቁጥር የድምፅ መልእክት ተልኮልኝ አየሁ፡፡ መልእክቱን ስሰማ ቀጥታ ወደ ፕሮፍይሉ በመሄድ ስለሱ ማንነት ለማወቅ እንዲረዳኝ ማየት ጀመርኩኝ በጠቅላላ ኢስላማዊ ፎቶወች እና ዱአ ይበዛበታል፡፡፡ እኔም ለማጣራት ያህል ነበር ፕሮፍይሉን የፈተሽኩት፡  የድምፅ መልእክቱ ከአምስት ደቂቃ የበለጠ ሲሆን profile ባረኩት ፎቶ አላህን እንድፈራ ፎቶ ሀራም መሆኑን የካተተ record ነበር አነጋገሩ በጣም አስተማሪ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ እሱ ነበር ተይ ያለኝ የማላቀዉ ቁጥሮች profile እያዩ ቆንጂት ሀይ የማይለኝ የለም telegram ስገባ የማላቀዉ ቁጥር ይበዛብኝ ነበር እኔ ግን አጂ ነብይ ጋር አላወራም ብየ ማንንም አላወራም ግን ምን ዋጋ አለዉ profile ከgroup እያዩት መሆኑን የተረዳሁት ዘንግቼ ነበር፡፡

     በፁሁፍም ከሀዲስ ከቁርአን ማስረጃ እያቀረበ ብዙ ትምህርቶችን ላከልኝ እኔም ጀዛ ከሏህ ብየ ፎቶየን profile ያረኩትን እንዳለ አጠፋሁ፡፡
ከዛም ግን ጎበዝ ዲነኛ እንደሆንሽ አቃለሁ profile ፎቶዉ የአንቺ መሆኑን ሳይ በጣም ነዉ የገረመኝ ሂክማ መቼ ጀምራ እንደዚህ ሁነች ብየ ግራ ገብቶኝ ነዉ አለኝ
....እኔም በመደንገጥ እንዴ ከአሁን በፊት ታቀኛለህ እንዴ ????? አልኩት
እሱም........

ይቀጥላል...


✎ ክፍል ሁለት (2) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
         
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ

🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
@menta_lboch    ,,📩 @joon_vision
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

12 Sep, 05:19


 ዘረኝነት፣ በሽታ፣ ጥላቻና ችግር ከምድራችን ጠፍቶ የምናይበት የፍቅር፣ የደስታና
የሰላም ዓመት ይሁንልን!🙏

🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌼
          🌼 

🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹,,,,,,,,,,
        •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    @menta_lboch    ,,📩 @joon_vision
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
     

💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

08 Sep, 18:30


ሌላ አዲስ ታሪክ ይለቀቅ የምትሉ


😉😉😉😉😉😉😉😉😉

1,587

subscribers

176

photos

53

videos