✞ማርያም አማላጅ ናት✞ @maryam_maryam2127 Channel on Telegram

✞ማርያም አማላጅ ናት✞

@maryam_maryam2127


✝️•✞•ከገነት የመውጣታችን ምክኒያት ሔዋን እንደሆነች ሁሉ•✞•✝️

✝️•✞•ዳግመኛ ወደ ገነት የመግቢያ በራችን ድንግል ማርያም ናት•✞•✝️

✝️ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘለዓለም ትኑር✝️
❥ማርያምን የሚወድ ሁሉ ይቀላቀል
☟-☟-☟-☟-☟
https://t.me/Maryam_Maryam2127

ጥቆማ አስተያየቶች ካሉዎት👇 @MARYAM_amalaj_bot

✞ማርያም አማላጅ ናት✞ (Amharic)

ማርያም አማላጅ ናት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አዝናኝ ቅኝት የሚሆነው፣ ገነት የመውጣታችን ምክኒያት ሔዋን እንደሆነች በእኛ ማርያም አማላጅ ናት ማህበረሰብና ክርስቲያን ህዝብን የሚዋጋ በተለያዩ መረጃዎች እና ተጨባጭ የተመረጠ ጽሑፍ፣ ለእኛ ተዘርናል። ማርያም እኖዳቸውን ብንልም ወደ ገነት እንገናኛለን፣ ድንግል ማርያም ናት ከፍተኛ እና ስለሆነች ይህንን ተረካብ እሳት ለማግኘት ከፍተኛዎቻችንን እንወስዳለን።

✞ማርያም አማላጅ ናት✞

21 Nov, 17:53


የከርሞ ሰው ይበለን🙏🏻🤗

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል 🙏🏻❤️‍🩹

የታመሙትን ፈውሶ፡፡
የወጡትን በሰላም መልሶ፡፡
ያለቀሱትን እንባቸውን አብሶ፡፡
የወደቁትን አንስቶ፡፡
በግፍ የታሰሩትን ፈትቶ፡፡
የሞቱትንም ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡
ለሀገራችን ሰላሙን ፍቅሩን ይላክልን።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን🙏🏻❤️‍🩹


🤲💚💛❤️🤲
እግዚአብሔር ሆይ! ተመስገን 🤲🥀

✞ማርያም አማላጅ ናት✞

21 Nov, 17:00


የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች
ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉ @m_ezmur21

✞ማርያም አማላጅ ናት✞

21 Nov, 03:27


" ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም። " ዳን፡10፥21

"የተጨነቀውን የተጨቆነውን ነፃ የምታወጣው ሚካኤል ሆይ፦ ሰላም ላንተ ይሁን ፡ ሠራተኛው ሠርቶ እንዲበላ ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡

ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል ዘንድ የምትላክ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አዳኝነትህን በማመን የለመነህን በክንፈ ረድኤትህ የምትሠውረው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡

በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን የሚንፈራገጠውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው ሚካኤል ሆይ ፤ አንገትህን ዘንበል ቀለስ አድርገህ በፈጣሪ ፊት ሰግደህ እኛ ባሮቹን በቸርነቱ ይጎበኘን ዘንድ የማናዊት እጁን ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ ለምን አማልድ ለዘላለሙ አሜን፡፡"
🌺 [መልክአ ሚካኤል] 🌺

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ምልጃውና ረድኤቱ ጥበቃው አይለየን አሜን ! 🙏🏻

✞ማርያም አማላጅ ናት✞

20 Nov, 18:09


🔔 የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ሼር👉
💚💛❤️
@Maryam_Maryam2127
@Maryam_Maryam2127

✞ማርያም አማላጅ ናት✞

20 Nov, 18:07


🔔 የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ሼር👉
💚💛❤️
@Maryam_Maryam2127
@Maryam_Maryam2127

✞ማርያም አማላጅ ናት✞

20 Nov, 15:58


​​💛 እንኳን ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏🏻❤️

ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ❤️

ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል:: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን እንደ ረዳው ታስተምራለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 5 ላይ እንደ ተጻፈው ቅዱሱ መልአክ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: እሥራኤልን በምድረ በዳ የመራ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ሲያርፍ ታላቅ ሐዘንና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር:: እግዚአብሔር ግን ኢያሱን አስነስቶ አረጋግቷቸዋል:: ቅዱስ ሚካኤል 40ውን ዘመን እሥራኤልን ደመና ጋርዶ: መና አውርዶ: ክንፉን ዘርግቶ: ጠላትን መክቶ ከሙሴ ጋ እንደ መራቸው ከኢያሱ ጋርም ይሆን ዘንድ ከሰማይ ወረደ::

በኢያሪኮ አካባቢም የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በግርማ ለኢያሱ ታየው:: ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ "አንተ ከእኛ ወገን ነህን? ወይስ ከጠላቶቻችን?" ሲል ጠየቀው:: ቅዱስ ሚካኤልም መልሶ "እረዳህ ዘንድ እነሆ የሠራዊት አለቃ ሆኜ ተሹሜ መጥተቻለሁ" አለው::
ያን ጊዜ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰገደለት:: ቅዱሱ መልአክም አክሎ "ፍታሕ ቶታነ አሳዕኒከ እም እገሪከ: እስመ ምድር እንተ ትከይዳ ቅድስት ይዕቲ - የረገጥካት ምድር የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ" አለው::

ኢያሱም የተባለውን አደረገ:: ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን "ለመላእክት የጸጋ (የአክብሮ) ስግደት ይገባል: በቅዱሳኑ ፊትም ጫማ ተለብሶ አይቆምም" የምትለው:: ያ መሬት ሊቀ መላእክት ቢቆምበት ተቀድሷል:: ዛሬም ቤቱ በታነጸበት: ታቦቱ በተቀረጸበት ቦታ ሁሉ ቅዱሱ መልአክ አለና ጫማን አውልቆ: ባጭሩ ታጥቆ መግባት ይገባል::

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከኢያሱ ጋር ሆኖ አማሌቅን ጨምሮ የእሥራኤልን ጠላት አጥፍቷል:: ጥቅመ ኢያሪኮን (ቅጥሩን) አፍርሷል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: በገባኦን ፀሐይን: በቆላተ ኤሎምም ጨረቃን ሲያቆም ከእርሱ ጋር ሆኖ ረድቶታል::

         ዱራታኦስና ቴዎብስታ❤️
ቅዱሳኑ ዱራታኦስ (ዶርታኦስ) እና ቴዎብስታ (ቴዎብስትያ) የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ:: በድርሳነ ሚካኤልና በመጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ እንደምናገኘው 2ቱ ቅዱሳን በተቀደሰ ትዳር ተወስነው: ሕጉን ትዕዛዙን ፈጽመው: ለነዳያን ራርተው: ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለው የሚኖሩ ነበሩ:: ይልቁኑ ግን የጌታችን: የእመቤታችንን እና የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ያለማስታጐል ያደርጉ ነበር:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ሐብት ንብረታቸው አልቆ ተቸገሩ:: ግን የጨነቃቸው መቸገራቸው ሳይሆን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ሊያቆሙ መሆናቸው ነው::

አማራጭ ሲያጡ ተቀምጠው ተመካከሩ:: የቅዱሱ መልአክ ዝክር ከሚቀር ልብሳቸውን (ያውም የክብር ልብሳቸውን) ሊሸጡ ተስማሙ:: በዚህ መሰረት ቅዱስ ዱራታኦስ ወደ ገበያ ሲሔድ ወዳጁ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወረደለት:: መንገድ ላይም የጦር መኮንን ሃገረ ገዢ መስሎ ተገናኝቶ አጫወተው:: ችግሩን ጠይቆም መፍትሔውን ነገረው:: "እኔ እዋስሃለሁና ለበዓል የሚያስፈልጉህን ነገሮች ሁሉ ገዝተህ አሰናዳ" አለው::

"እኔ ወደ ቤትህ መጥቼ ስለምስተናገድ አንድ አሣ አምጥተህ አቆየኝ:: እኔ ሳልመጣ ግን አትረደው" አለው:: ቅዱስ ዱራታኦስ የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ ወደ ቤቱ ሲሔድ ድንቅ ነገርን ተመለከተ:: ሚስቱ ቅድስት ቴዎብስታ በቤቱ መካከል ሁና ቤቱ በበረከት ሞልቷል::
ማሩ: ቅቤው: እሕሉ ሁሉ በየሥፍራው ሞልቷል:: ባልና ሚስቱ ደስ ብሏቸው:: ነዳያንን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ዋሉ:: በሁዋላ ያ መኮንን (ቅዱስ ሚካኤል) በቤታቸው መጥቶ ተስተናገደ::

በእርሱ ትዕዛዝ የአሣው ራስ (ሆድ) ሲከፈት በውስጡ 300 ዲናር ወርቅ (እንቁ) ተገኘ:: ቅዱሳኑ ይህን ተመልክተው ሲደነግጡ ቅዱስ ሚካኤል ክንፉን ዘርግቶ ራሱን ገለጸላቸው:: ደንግጠው በግንባራቸው ተደፉ:: እርሱ ግን "በተገኘው ሃብት እዳችሁን ክፈሉ:: ከዚህ በሁዋላ ግን በምድር አትቸገሩም:: በሰማይም ክፍላችሁ ከእኔ ጋር ነው" ብሎ ባርኩዋቸው ወደ ሰማይ ዐረገ:: እነርሱም በሐሴትና በበጐ ምግባር ኖረው ዐርፈዋል:: ለርስቱም በቅተዋል::

          ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ❤️
የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ::
በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ::
በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ::
በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ::
ምጽዋትን ያዘወተረ::
አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

         አፄ በእደ ማርያም❤️
በዕደ ማርያም" ማለት "በማርያም እጅ" እንደ ማለት ነው:: እኒህ ሰው የኢትዮዽያ ንጉሥ ሲሆኑ የነገሡትም በ1460 ዓ/ም ነው:: ደጉ አባታቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሲያርፉ በመንግስቱ ተተክተው ሃገራችንን አስተዳድረዋል:: ድርሰት ደርሰዋል:: አብያተ መቃድስ አንጸዋል::
በተለይ ለቅኔ ትምሕርት ማበብ ልዩ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ይነገራል:: ልክ በነገሡ በ10 ዓመታቸው ግን መንግስተ ምድር በቃኝ ብለው በምናኔ በርሃ ገብተዋል:: በዙፋናቸውም አፄ እስክንድር ተተክተዋል:: ጻድቁ ንጉሥ ግን ቅዱስ ሚካኤልን ይወዱት ነበርና በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

አምላከ ቅዱሳን በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን:: ከቅዱሳኑ በረከታቸውም አይለየን
🌺💚💛❤️🌺
@Maryam_Maryam2127
@Maryam_Maryam2127

✞ማርያም አማላጅ ናት✞

20 Nov, 04:33


ቅድስት ሐና ልጅሽ ድንግል ማርያም አማላጃችን!❤️
የልጅ ልጅሽ መድኃኔዓለም ደግሞ አምላካችን !❤️

እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ እያቄም ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።

🤍 በድጋሚ እንኳን ለቅድስት ሐና አመታዊ የዕረፍት መታሰቢያ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ ❤️