Day To Day @etco122 Channel on Telegram

Day To Day

@etco122


እንኳን ወደ ቻናላችን በደህና መጡ😍👋

Ethio News (Amharic)

እንኳን ወደ ቻናላችን በደህና መጡ😍👋nnኢትዮ ቴሌግራም ዜና እንዴት እንደ ሃገር ሃገሮች የሚያዩ አዳዲስ ዜናዎችን በማቅረብ ከአስቸኳይ ምህረት በሚገኘው ቴሌግራም ላይ ይመዝገቡ። ዜናዎች ከማዶ ፈላጊዎች እና ትክክለኛ ስነልቦች ጋር ከሚኖሩ የተወሰነ ግሌ መረጃዎችን እንመለከታለን። በተጨማሪም ከቶ ተቀበሊ ያለ ዜናን ለማሳይ ከአዲሱ ቅንብሮች በሃሳብ ቅንብሮች ጋር ከኖሩ ትእዛዝ እንደሚለዋወጥ የሚያሳውቁ ሰዎች መሆኑን ማስቻሉን በቴሌግራሙ ላይ።

Day To Day

29 Oct, 10:08


https://t.me/BitgetWallet_TGBot/BGW?startapp=sharetask-2w3jLqbPjz9hYQNdD
🎁 You’re invited to unlock a mystery gift! 🎁

First 1,000,000 only! Clicking this link guarantees your qualification.

First come, first served, do not wait!

Join me on Bitget Wallet Lite now!

Day To Day

28 Oct, 15:20


t.me/hexn_bot/app?startapp=ce786d3a-5b25-43b7-a990-fa0d8d636f79

Day To Day

22 Oct, 16:04


#ኦርቶዶክስተዋሕዶ

" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን ጀምሯል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባኤውን መጀመረ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

Day To Day

21 Oct, 16:32


#ደመወዝ : የደመወዝ ጭማሪ ተፈቅዶና በጀቱም ጸድቆ ክፍያው ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም.  ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዛሬ አሳውቋል።

ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደው በጀት፣ የአፈጻጸም መመሪያውንና የክፍያ ትዕዛዙን ለ12ቱ ክልሎች፣ ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና ለፌደራል ተቋማት ዛሬ መተላለፉም ተገልጿል።

(ከጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ይፋዊ የደመወዝ ስኬል ከላይ ተያይዟል)

#CivilServiceCommission
#MekuriaHaile

@tikvahethiopia

Day To Day

20 Oct, 15:59


https://t.me/+ODoSXlNENlNlNWNk

Day To Day

20 Oct, 08:31


የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የቀበሌ መታወቂያን አይተካም፦ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት

#Ethiopia | የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የቀበሌ መታወቂያን መተካት እንደማይችል እና ሁለቱም የተለያየ አገልግሎት እንደሚሰጡ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ዮዳሄ ዓርኣስላሴ ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት ስራ አስኪያጁ የብሔራዊ ዲጂታል ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታሉ ዓለም እንድትቀላቀል የሚረዳት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ተቋማትን ከተቋማት ክልልን ከክልል ከተማን ከከተማ እርስ በእርስ እንዲናበቡ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የቀበሌ መታወቂያን አይተካም ያሉት ስራ አስኪያጁ የቀበሌ መታወቂያ አላማው ነዋሪነትን የሚያረጋግጥ እንጂ ማንነትን የሚያረጋግጥ አይደለም ብለዋል፡፡

አገልግሎቱ ገና ጅማሬ ላይ ያለ ነው፤ ስርዓቱ እየተለመደ ሲመጣ ከቀበሌ መታወቂያ እና ከብዙ አገልግሎቶች ጋር እንደሚተሳሰርም ገልጸዋል፡፡

በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የኦፕሬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ሄኖክ ጥላሁን በበኩላቸው መታወቂያ በሁለት አይነት እንደሚከፈል ገልጸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ እና መሰረታዊ መታወቂያ በሚል በሁለት እንደሚከፈሉ ገልጸዋል፡፡

በዚህም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት የሚጠቀሙ ነዋሪዎች "ማን ናቸው" የሚለውን አስተማማኝ በሆነ መልኩ ያረጋግጣል ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ወደ አስገዳጅ ሁኔታ ምዝገባ እንደማይካሄድ ገልጸው አገልግሎት ሰጪዎች አገልግሎታቸውን እንዲያቀላጥፉ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

Day To Day

19 Oct, 17:05


#ደመወዝ

" የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " - የገንዘብ ሚኒስቴር


የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ፤ ከመስከረም ወር 2017 ጀምሮ የሚጨመር ደመወዝ በካቢኔ መፅደቁን አሳውቀዋል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ትኩረት ያደረገ የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉን አመልክተዋል።

አቶ አህመድ " የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ በካቢኔ ፀድቋል ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ ይደረጋል። የደመወዝ ጭማሪው ከ91 እስከ 92 ቢሊዮን ብር መካከል ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ ይሆናል " ብለዋል።

በነባሩ በጀት የተወሰነ መግባቱን ፤ በተጨማሪ በጀትነትም የሚታወጅ መኖሩን ጠቁመዋል።

" ሲቪል ሰርቫንቱ አጠቃላይ የመንግሥት ሰራተኛው በሁሉም መስክ በፀጥታም በሌሎችም ዘርፍ ያሉትን የኑሮ ጫና ለመቋቋም የሚያስችለውን ድጋፍ ለማድረግ መንግሥት በከፍተኛ ቁርጠኝነት ተገባበት ነው " ሲሉ አቶ አህመድ ተናግረዋል።

" የባለፉት ሁለት ወራት የኢንፍሌሽን አፈጻጸም በሚታይበት ጊዜ እንደተሰጋው አይደለም። የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የተወስነ ጭማሪ በአንዳንድ እቃዎች ላይ እንጂ በአብዛኛው የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። " ብለዋል።

" እንደዛም ሆኖ የደመወዝ ጭማሪው እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ የሰራተኛውን ቋሚ ደመወዝተኛ ገቢ ያለውን ዝቅተኛውን ትኩረት አድርገን የዝቅተኛውን በጣም ከፍተኛ ጭማሪ አድርገናል የላይኛውን ዝቅተኛ ጭማሪ አድርገን ነው የተሰራው ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

Day To Day

19 Oct, 09:57


" በተፈጸመባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታለች፤ የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " - የቤተሰብ አባል

በኦሮሚያ ክልል ፣ በምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ' የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም ' በሚል ከዛፍ ጋር ታስራ በባለቤቷ ክፉኛ የተደበደበችና የተገረፈች የ3 ልጆች እናት በአስጊ ጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የቤተሰብ አባሏ ተናገሩ።

በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ የምትገኘው ኩሹ ቦናያ የተባለችው እናት በደረሰባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታ " የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " በማለት የቤተሰብ አባሏ ገልጸዋል።

የአካባቢው አቃቤ ሕግ በበኩላቸው ግርፋቱን መፈጸማቸው የተጠረጠሩ ባለቤቷን ጨምሮ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ መካሄዱን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፈዋል የተባሉት ሽማግሌዎች የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልጸዋል።

Day To Day

19 Oct, 09:05


"ባለቤትሽ ጋር ለምን አልመለስም አልሽ በማለት በባለቤቷ ህዝብ ፊት እንድትገረፍ የተወሰነባት የልጆች እናት"

ጉዳዩ እንዲህ ነው... ወ/ሮ ኩሹ ቦናያ ምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ቃቀሎ ቀበሌ ነዋሪ ናት። ወ/ሮ ኩሹ ከአቶ ገልገሎ ዋሪዮ ጋር ትዳር ከመሰረቱ 12 አመታት አስቆጥሯል ሶስት ልጆም ወልዷል።

ወ/ሮ ኩሹ ሶስተኛ ልጃቸውን ነፍስጡር ሆነው ባለቤታቸው የሀገር መከላከያ ተቀላቅለው ለግዳጅ 4 አመት ሌላ ቦታ ቆይቷል።

አራት አመታትን ሶስት ልጆችን ብቻቸውን ያሳደጉት ወ/ሮ ኩሹ ከአራት አመታት በኋላ ባለቤታቸው ከመከላከያ ተሸኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ጉዳዩን ለፋስት መረጃ ያስረዱት የቤተሰብ አባል አቶ ገለግሎ ሲመለሱ የተለያዩ ሱሶችን ስለለመዱ ትዳሩ እንደቀድሞ ሰላማዊ ሊሆን አልቻለም ጭቅጭቅ እና ግጭት ተከሰተ ይላሉ።

ወ/ሮ ኩሹ ትዳራቸው እንዳይፈርስ በተደጋጋሚ በሽማግሌ ብታስመክርም ባለቤቷ ሊስተካከል ስላልቻለ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ወደ ቤተሰቦቿ ትሄዳለች።

ይህን ጊዜ ባል ሀገር ሽማግሌዎችን በመላክ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ያስጠይቃል፣ ወ/ሮ ኩሹ የእኔ ጉዳት አልታየም በፍፁም አልመስም በማለት የሽማግሌዎቹን ጥያቄ ውድቅ ታደርጋለች።

ሽማግሌዎቹም የምንልሽን ስሜ ቶሎ ወደ ቤትሽ ተመለሺ ካልሆነ ቅጣት እንጥልብሻለን በማለት ሲያጠነቅቋት እንደቆዩ ተበዳይ ትናገራለች።

በእምቢታ የፀናችው ወ/ሮ ኩሹ በሽማግሌዎቹ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባት በገመድ ከግንድ ጋር ታስራ በልጆቿ እና በህዝብ ፊት በባለቤቷ እንድትገረፍ ተደረገ።

ይህን ውሳኔ አስተላልፏል የተባሉት ሽማግሌዎች ጃርሶ ቦሩ፣ ገልገሎ ጃተኒ፣ ዲዳ ዋሌ፣ ዲዳ ጃተኒ፣ አለካ ጃርሶ፣ ባርጪ ኢያ፣ ዲባ ጎሊቻ የተባሉ ሲሆኑ ፋስት መረጃ በደረሰው መረጃ እነዚህ ሽማግሌ የተባሉ ግለሰቦች 5 ቀን ታስረው በዋስትና መለቀቃቸውን ሰምተናል።

Day To Day

19 Oct, 08:19


#ከፍተኛትኩረት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍል በቅርብ አመታት ታይቶ የማይታወቅ የወባ ወረርሽኝ ተከስቶ ህዝብ እየረገፈ ነው

በአካባቢው ያሉ የጤና ባለሙያዎች እንደነገሩኝ በወላይታ፣ በከምባታ፣ በጉራጌ ዞኖች እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ እና ዙርያው ወረርሽኙ ተባብሷል።

ፈጣን ትኩረት ያሻዋል፣

@Elias_Meseret

Day To Day

18 Oct, 08:52


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶች መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።

በዚሁ መሠረት፦

1. ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ፦ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር
2. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፦ የቱርዝም ሚንስቴር ሚንስትር
3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ፦ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር በመሆን ተሹመዋል።

Day To Day

17 Oct, 17:06


" ታፍኖ ከተወሰደ ከ5 ቀናት በኋላ ተገድሎ አስክሬኑ ወንዝ ተጥሎ ተገኝቷል " - የትግራይ ነፃነት ፓርቲ

የትግራይ ነፃነት ፓርቲ የአመራር አባሉ ታፍኖ ከተወሰደ በኃላ ተገድሎ አስከሬኑ ወንዝ ተጥሎ እንደተገኘ ገለፀ።  

ፓርቲው ታፍኖ የተወሰደውን የአመራር አባሉን ላለፉት ከ5 ቀናት ሲፈልግ የቆየ ቢሆን ተገድሎ አስክሬኑ ወንዝ ተጥሎ ማግኘቱ አሳውቋል።

የፓርቲው ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደጀን መዝገበ " አሰቃቂ ድርጊቱ የተፈፀመው በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ነው " ብለዋል።

ተገድሎ የተገኘው የፓርቲው አመራር አባል በወረዳው የፓርቲው አስተባባሪ መሆኑን ገልጸው ፥ " ታፍኖ ከተወሰደ ከ5 ቀናት በኋላ ተገድሎ ሬሳው በወንዝ ተጥሎ ተገኝቷል ይህ ጭካኔ የተሞላበት አረመንያዊ ድርጊት ነው " ሲሉ አውግዘውታል። 

ሊቀ-መንበሩ በዞኑ የሚገኙ አባላቱ " ' ፓርቲው መደገፍ ህወሓት መቃወም አቁሙ አለበለዚያ ትገደላላችሁ ' የሚል ማስፈራርያ ደርሶዋቸዋል " ሲሉ ' ህወሓትን ክሰዋል።

ህወሓት ለቀረበበት ክስ እስካሁን የሰጠው መልስ የለም። 

" ተግባሩን የህወሓት አባላት ነው እየፈፀሙ የሚገኙት " በማለት ያቀረቡትን ክስ ያጠነከሩት የፓርቲው ሊቀመንበር " በ19 የፓርቲው አባላት አፈና ፣ ደብደባና ግድያ ደርሷል " ማለታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TiikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tiikvahethiopia

Day To Day

17 Oct, 16:29


#AddisAbaba

ትናንት ምሽት 5 ሰዓት ተኩል ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ወረዳ 7 ኢንዱስትሪ መንደር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሰብ በማሽን ተይዞ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።

እንደ አዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መረጃ ፤ ከሜድሮክ ድርጅቶች በአንዱ ውስጥ ሰራተኛ የሆነው ሟቹ ትናንት ምሽት አሸዋ በሚፈጭ ማሽን ላይ ስራውን እያከወነ በነበረበት ወቅት በማሽኑ ተይዞ ወዲያው ህይወቱ አልፏል።

አስከሬኑን ከማሽኑ ለማላቀቅ አልተቻለም ነበር፡፡

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን ከማሽኑ አላቀው ማውጣት የቻሉት ለ2 ሰዓት ከፈጀ ጥረት በኋላ ነው።

የትናንቱ በማሽን ላይ የደረሰው አደጋ ጉዳይ በህግ ተይዟል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ትላንት በሸገር ከተማ አሸዋ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወና ወሀ ባቆረ ጉድጓድ ውስጥ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አልፏል።

ሟቾቹ ዕድሜያቸዉ 19 እና 23 ነው።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አንደኛውን ወጣት አስክሬን አውጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን እድሜው 19 ዓመት የሆነው ወጣት አስክሬን የአካባቢው ህብረተሰብ አስቀድሞ አውጥተውታል።

ክፍት የተተወው ጉድጓድ ውሃ ያለበት በመሆኑ አንደኛው ግለሰብ ለመታጠብ ብሎ ገብቶ ተንሸራትቶ ወደ ውሃው ውስጥ ይገባል ፤ የዚህን ሰው መግባት የተመለከተው ሌላው ግለሰብ ደግሞ እርሱን ለማውጣት ሲል ወደ ጉድጓዱ በመግባቱ የሁለቱም ህይወት ወዲያው አልፏል፡፡

#ShegerFM102.1