ትምህርተ ኦርቶዶክስ @orthodox_tewahedooo Channel on Telegram

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

@orthodox_tewahedooo


ትምህርተ ኦርቶዶክስ (Amharic)

ትምህርተ ኦርቶዶክስ (Orthodox Tewahedo) አዲስ ተናጋሪ ቦታ ለወቅታዊ ትመልከትና ትእዛዝ የሚሰጡበት ቦታ። ከትናጋሪ ከፖሊስ ከተንበስታል ለመከራ የሚሆነው፣ ታስታውሱልና ተመልኳል። ዓምፂራ ወይም ትምህርተ ኦርቶዶክሲቲ ቤተ-መንበር ነው ትህርተ ኦርቶዶክስ ፣ ትህርተ ደብረ ፊት ተከተለው። በትምህርተ ኦርቶዶክስ ቤተ-ሰብ የተሳተፈውን ማህበረሰብ, ትናንተር ለአባቶችና ቤተ-መንበር የሚገኝ መጽሐፍ ወረቀትንና የማሽከርኪያዎችን በረረት ያዳምጡ። በሚኒ እስኪቀረፍም የሚሆኑ ዜናዎችን ተገኝቷል፣ ለሚሳቅ በሃገራችን ላይ እንዲኖሩ፣ ልዩ እና የሳምንት ፈቃድን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፈጻሜዎችን ማግኘትን እንጠቀማለን።

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

14 Apr, 17:37


ንሴብሖ

ንሴብሖ /2/ ለእግዚአብሔር /2/ 
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4 
እናመስግነው /2/ እግዚአብሔርን /2/ 
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/ 

ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ህይወት የሚሰጠን መና ነው ምግባችን

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራም ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ነው የዓለም ቤዛ

ከአለት ላይ ውሃ ፈልቆ እንደጠጣነው
ይህን ታላቅ አምላክ ኑ እናመስግነው
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

13 Feb, 18:48


††† የካቲት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ
2.አባ ቴዎድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
3.አባ እለ እስክንድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
4.ቅዱስ አባዲር

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

12 Feb, 19:10


††† የካቲት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት
2.የዓለም ኁሉ መምሕር ቅዱስ አቡሊዲስ (ብዙ መንፈሳዊ ድርሳናትን የደረሰ ሊቀ ዻዻስና ሰማዕት)
3.ቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ (ሰማዕታት)
4.ቅድስት አትናስያና 3ቱ ሰማዕታት ልጆቿ (ቴዎድራ : ቴዎፍናና ቴዎዶክስያ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

11 Feb, 18:24


††† የካቲት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
2.ቅዱስ አባ ብሶይ ጻድቅ
3.አባ አክርዽዮስ
4."49" አረጋውያን ሰማዕታት (ፍልሠታቸው)
5.ቅዱስ አሞኒና ሚስቱ ቅድስት ሙስያ (የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች)
6.አባ ኖብ ጻድቅ : መነሳንሱ ዘወርቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

10 Feb, 17:21


††† የካቲት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አጋቦስ ነቢይ: ሐዋርያና ሰማዕት
2.አባ ዘካርያስ ትሩፈ ምግባር

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ነጎድጓድ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፊያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

10 Feb, 07:34


የካቲት ፭ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ከሀይማኖታችን እና ከአባቶቻችን ጎን በመቆም አንድነታችንን እና የደረሰብንን በደል ለ አለም እናሳያለን።
🖤🖤🖤🤍🤍🤍

አንድ መንበር
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፖትሪያልክ

በአሁኑ ሰዓት መንግስት ኔትወርክ በማጥፋት, ከ social media ላይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ eotc ሚዲያ የካቲት 2 ዓ/ም አባቶች የሰጡትን መግለጫ በማጥፋት
በተጨማሪም ት/ቤቶችን በመዝጋት መረጃ ልውውጥ እንዳይኖር በማድረግ እሁድ የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስቀረት ታስቧል።

Share በማድረግ ለብዙዎች እንድረስ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

10 Feb, 07:17


Telegram
Tiktok እና ሌሎች social media አልሰራ ላላችሁ ይጠቅማቹሀል

share በማድረግ ለብዙዎች እንድረስ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

09 Feb, 18:28


✞ የካቲት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት-በዓለ ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
3.አባ ያዕቆብ መስተጋድል

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

08 Feb, 19:12


አስቸኳይ

በነገው ዕለት በዓለም ገና ሚካኤል አቶ አካለወልድን ለመቀበል ዝግጅት ተደርጓል። አካለ ወልድ በዚህ ሰአት ዓለም ገና ዓለም ሆቴል ውስጥ ይገኛል። ሰበታ፣ ወለቴ፣ ዓለምገና እና በዙሪያው ያላችሁ ምእመናን ተባብራችሁ ይህንን ሴራ አክሽፉ።

🖤🖤🖤🖤🖤

አንዲት ቤተ ክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትርያርክ

Share በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

08 Feb, 18:42


✞✞✞ የካቲት 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (የባሕታውያን ሁሉ አባት)
፪.ቅዱስ አባ ለንጊኖስ ሊቀ ምኔት (ደብረ ዝጋግ)
፫.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ

††† ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ (የሃይማኖት ጠበቃ)
፬.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ
፭.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፮.አባ ሕርያቆስ ዘሐገረ ብሕንሳ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

07 Feb, 18:59


✞✞✞ የካቲት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."150"ቅዱሳን ሊቃውንት ዻዻሳት (በቁስጥንጥንያ ተሠብሥበው መናፍቃንን ያወገዙበት: ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ያፀኑበት /ጉባዔ ቁስጥንጥንያ/ በ381 ዓ/ም::
ከወቅቱ ቅዱሳን ሊቃውንት እነዚህ ይጠቀሳሉ:-
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ
*ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት
*ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም)
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
3.ታላቁ ቴዎዶስዮስ ጻድቅ (ንጉሠ ቁስጥንጥንያ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም እግዝእትነ
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
5.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

Share በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

07 Feb, 17:01


"…በገዳሙ የሚኖር ማንኛውም መነኩሴ ከሊቅ እስከ ደቂቅ 150 መዝሙረ ዳዊት በቀን እንዲደግም። ከደገመ በኋላም መጸሐፉን መሬት ላይ ደፍቶ ያስቀምጥ። መቁጠሪያውንና መቋሚያውን ጸሎት ከጨረሰ በኋላ መሬት ላይ ይጣል። ምግብን በተመለከተ በቋርፍ ቤትም ሆነ ብእህል ቤቶችና  በአትክልት ቦታዎች ጨው፣ በርበሬ፣ ያለበት ምግብ ከሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀን እንዳይመገብ። በማንኛውም ቦታ የገዳማችን መነኮሳት ባእት እሳት እንዳይነድ። ከቤተ እግዚእብሔር የሚሰጠውን ብቻ እንዲመገብ። የተመገበበትን ፋጋ ከጨረሰ በኋላ ባፉደፍቶ እንዲያሳድር። ከምሽቱ 12 ሰዓት ውጭ የመቁንን ደውል እንዳይደውል። ውኃ ከአንድ ብርጭቆ በላይ እንዳይጠጣ። ሻይ እንዳይፈላ። ጭልቃ እንዳይጨለቅ ወስኗል። 

"…ይህ ትእዛዝ በሁሉም የቋርፍ ቤት፣ የአትክልት ቦታ፣ የሞፈር ቤቶች፣ በየዋሻው እና በየፍርኩታው ላሉ ባህታውያን አባቶች መልክቱ ይተላለፍ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በሀገራችን የመጣው አደጋ ቀላል አይደለም በሚል ተወስኗል። ይህ ውሳኔ ከትናንት ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል።


https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

06 Feb, 18:54


#የነነዌ_ጻም_የመጀመሪያ_ቀን_ውሎ

ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተክርስቲያንላይ የደረሰው መከራ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የነነዌን ጾም በምሕላ እና የሐዘን ልብስ በመልበስ ምእመናን እንዲያሳልፉት አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። ይህንን አዋጅ ተከትሎ ዛሬ ጥር 29/2015 ዓ.ም ምእመናን በሌሊት ወደ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመሄድ የምሕላ ጸሎት ላይ የተሳተፉ ሲሆን በተጨማሪም ጥቁር ልብስ በመልበስ ሐዘናቸውን ሲገልጹ ውለዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ግን የጸጥታ አካላት ጥቁር ልብስ የለበሱ ምእመናንን እና ካህናትን ሲያዋክቡ የነበረ ሲሆን በተወሰኑ አካባቢዎች ደግሞ ለእስር የተዳረጉ እንዳሉ መረጃዎች እየደረሱን ይገኛሉ። በተለይ በኮልፌ፣ በለገጣፎ፣ በአዳማ እና በቢሾፍቱ ምእመናን እና ካህናት የታሰሩ ሲሆን በእነኚሁ አካባቢዎች ምእመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው የምሕላ እና የቅዳሴ ጸሎትን እንዳይከታተሉ በጸጥታ አካላት ተከልክለዋል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች ሥር ባሉ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ ኦርቶዶክሳውያን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሆነውን ጥቁር ልብስ ለብሰው እንዳይገቡ ከፍተኛ ክልከላ ሲደረግባቸው የዋለ ሲሆን በዝግጅት ክፍላችን በደረሱት መረጃዎች መሠረት አንዳንድ ተቋማት ሠራተኞቻቸውን እስከማገድም እንደደረሱ ለማወቅ ተችሏል።

በመጀመሪያው የጾመ ነነዌ ዕለት የተፈጠሩ እነኚህ ችግሮች በቀጣዮቹ ቀናት እንዳይደገሙ እና መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ያጋጠማትን ሕገወጥ ድርጊት የሚያባብሱ ነገሮችን እየተመለከተ ችላ ማለት እንደሌለበት ስለ ውሏቸው ያነጋገርናቸው አባቶች ገልጸውናል።

ሼር በማድረግ ለብዙዎች እንድረስ
https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

06 Feb, 18:48


#ከለሊቱ_8_ስዓት ሽንት ቤት አስገብተው ቆለፉብኝ በክላሽ ሰደፍ እና በዱላ ደበደቡኝ ፊኛዬን ሲመቱኝ ወደቅሁ ቆቤን እና መቁጠሪያዬን ቀምተው ሸንትቤት ጨመሩት ማጅራቴን ይዘው የሽንት ቤቱ ትቦ ላይ በመዘቅዘቅ ምግብህ እሄ ነው ላስ አሉኝ።

የያቤሎ_ደብር_አስተዳዳሪ

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

06 Feb, 10:57


https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

06 Feb, 10:54


የሰሜን ጎንደር ዞን መቀመጫ በሆነችው በደባርቅ ከተማ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ወደ አደባባይ በመውጣት የመንግሥት የጸጥታ አካላት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እያሳደሩ ያሉትን ተጽእኖ ተቃውመዋል።

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

06 Feb, 10:49


ለድፍን 18 ዓመታት በኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት ጳጳስ የነበሩት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ አጭር የአገልግሎት ታሪክ

እኚህ ሰው Ex አባ ሳዊሮስ በቀድሞ ስማቸው #ደምመላሽ #ሞገስ በምንኩስና ስማቸው አካለወልድ ሞገስ ቤተክርስቲያን ኦሮሚኛ የምችሉ መነኮሳት ጵጵስና ይሰጣቸው ብላ በ1997 ጵጵስና ሾማቸው ነበር።

ላለፉት 18 ዓመታት ኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ተመድበው ነበር። ተጨማሪ ሌሎች 4 በውጪ ያሉ ሀገረ ስብከቶችን ደርበው ያስተዳድሩ ነበር። ነገር ግን በዚህ በ18 ዓመት ሀገረ ስብከት የማስተዳደር እድሚያቸው አንድም የAfaan Oromoo አብነት ትምህርት ቤት አልከፈቱም። አንድም የAfaan oromoo የካህናት ማስልጠኛ አልከፈቱም። አንድም በAfaan oromoo መጻህፍ አልጻፉም። አንድም ቀን በAfaan oromoo ቀድሰው አያውቁም።
የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከትን እንዲያስተዳድሩ ሲጠየቁ ''ልታስገድሉኝ ነው ወይ? እዛ መሄድ አልፈልግም'' ብለው የቀሩ ሰው ናቸው።

እኚህ ሰውዬ ውሏቸውም አዳራቸውም 4ኪሎ ባለው መኖሪያ ቤታቸው ነበር። በዚህ 18 ያህል የጵጵስና ዘመናቸው አንድ የAfaan oromoo መጽሃፍ ያልጻፉ ሰውዬ የቋንቋን ችግር እነሰደ ክፍተት ተጠቅመው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የመክፈል፣ መፈንቅለ ፓትርያርክ የማድረግና ስልጣን የመያዝ እንጂ አንድም ለህዝቡ የማዘንና በቋንቋ የማስተማር ዓላማ የላቸውም።

https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

05 Feb, 19:30


ጥቁር መልበስ አዲስ ክስተት አይደለም። ቀድሞም ቅዱሳን ነቢያት ክፉ ዘመን ሲመጣ በዘመኑ ለነበረው ንጉሥና ለሕዝቡ ጥቁር ለብሰው፣ በጥቁር ፈረስ ሆነው፣ ጥቁር መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበር። በፈረስ መሆናቸውም ፈረስ ፈጣን ነው። ፈጥኖ መቅሰፍት ይደረጋል ሲሉ ነው።


በሰላሙ ጊዜ ደግሞ ነጭ ለብሰው፣ ነጭ መነሳንስ ይዘው በአሕያ ተጭነው ይመጣሉ። በአህያ ተጭኖ መምጣት የሰላም ምልክት ነው። ጌታም ሰላምን አመጣሁላችሁ ሲለን በአሕያ ተቀምጦ መጣ። እንኳን ለነነዌ ጾም በሰላም አደረሳችሁ። አባቶቻችን ባዘዙን መሰረት በፍጹም ፍቅርና ትሕትና ሆነን ምሕላውን እንከታተል።
https://t.me/orthodox_tewahedooo

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

05 Feb, 17:31


ስለ ፆመ ነነዌ በጥቂቱ . . . .


https://t.me/orthodox_tewahedooo