መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በክልሉ የንግድ እንቅስቃሴ መስተጓጎሉ የሚታወቅ ሲሆን ይህም በማህበረሰቡ ላይ የተፈጠረውን የኢኮኖሚ ጫና ለመፍታት ሚኒስቴሩ ኮሜቴ በማቋቋም ወደ ክልሉ መላኩ ታውቋል፡፡
የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ የማነ ወረደ እንደተናገሩት በመቐለ ከተማ የንግድ እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ገልጸው ሸማቹ ህብተረሰብም የሚፈልጋቸውን ዕቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እየተገበያየ ነው፡፡
ይህን ተከትሎም በከተማዋ በአሁኑ ወቅት ነጭ ጤፍ በኪሎ 45 ብር ፣ ቀይ ጤፍ 38ብር፣ ሠርገኛ 38 ብር ፣ስንዴ 28 ብር ፣ ሽንኩርት 15ብር ፣ ቲማቲም 10 ብር ፣ ድንች 20 ብር እየተሸጠ መሆኑን የኮሚቴው አባላት በእይታ ማረጋገጣቸውን አመላክተዋል፡፡
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ከህግ ማስከበሩ ጋር ተያይዞ የአንዳንድ የምግብ ሸቀጦች ላይ ማለትም በሞኮሮኒ፣ በሩዝ፣ በምስርና በአተር ክክ እና በቡና ምርቶች ላይ አንጻራዊ የዋጋ ንረት መከሰቱን አቶየማነ ተናግረዋል፡፡
ከዚህም በተጓዳኝ በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ የቤንዚን እጥረት በሃገሪቱ ችግር እንደተከሰተ በማስመሰል ቤንዚን በከተማዋ በሊትር እስከ 50 ብር በህገ-ወጥ መልኩ እየተሸጠ እንዳለ የገለጹት የኮሚቴው ሰብሳቢ ይህም ትልቅ እልባት ያሻዋል ብለዋል፡፡
እንደተናገሩት በክልሉ በአሁኑ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መሠረታዊ የሸቀጥ የአቅርቦት ችግር እንዳይከሰት አሁን በጊዚያዊነት ጉና እነዚህን ምርቶች እንዲያከፋፍል ሃላፊነት የተሰጠው መሆኑን ሃላፊው ገልፀው ይህንን ሃላፊነት ለጉና ብቻ የመስጠት ፍላጎት እንደሌለውና በቅርቡ ሌሎች በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙ የንግድ ድርጅቶች የማከፋፈል ሃላፊነቱ እንደሚሰጥም አስረድተዋል፡፡
እነዚህን ምርቶች በማከፋፈሉ ተግባር ላይ በአሁኑ ወቅት ዩኒየኖች የማከፍፈል ስራ እየሰሩ መሆኑን እና በቀጣይ ግን ዘይትና ስኳር በመንግስት ለማከፋፍል ዕቅድ መያዙንም አቶ ዮሴፍ መግለፃቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
@Tigrai_Tv