Abu Furat @abufurat Channel on Telegram

Abu Furat

@abufurat


🌴በዚህ ቻናል በዋናነት የሸይኽ ሷሊህ #ኢብኑ_ዑሰይሚንና የሌሎች ታላላቅ ዑለሞች ፈታዋዎችና ትምህርቶች በአማርኛ ይቀርባሉ።
🕋🕋🕋
በተጨማሪም ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎች ይቀርቡበታል።🌴
ለአስተያየትና ለጥቆማ @YunusHassen ይጠቀሙ!
🏝️ما كان لله سيبقى🏝️

Abu Furat (Amharic)

አቡ ፉራት - ዑለሞች እና ትምህርቶችnnአቡ ፉራት በዚህ ቻናል በዋናነት የሸይኽ ሷሊህ #ኢብኑ_ዑሰይሚንና የሌሎች ታላላቅ ዑለሞች ፈታዋዎችና ትምህርቶች በአማርኛ ይቀርባሉ። በተጨማሪም ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎች ይቀርቡበታል። ለአስተያየትና ለጥቆማ @YunusHassen ይጠቀሙ! የትምህርት መልእክታችንንና ዑለሞችን በአማርኛ ታሪካቸውን ይምረጡ።

Abu Furat

18 Nov, 04:54


⚠️ከፊል ሰው ካልተወደሰ ጀግና ካልተደረገ ዳዕዋ [ማድረግ] ይተዋል/ያቆማል።

ይህ ወደ ነፍሱ እንጂ ወደ አሏህ ጥሪ እያዳረገ እንዳልሆነ ማስረጃ ነው።

ሙስሊም ይንቃ‼️

ዳዕዋ ሲያደርግ ኒያው ለአሏህ ፊት ብሎ ማጥራት፡ ሰዎችን መጥቀምና እነሱን ከሺርክ ከቢድዓና ሸሪዓን ከሚፃረሩ ነገሮች ማጥራት ይሁን።

ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አሏህ ይጠብቃቸውና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

18 Nov, 03:01


ዝምታ የዓሊም ጌጥ፡ የጃሂል ደግሞ መስሰተሪያ ነው።

ሱፍያን ቢን ዑየይናህ አሏህ ይዘንለትና።

ምክነያቱም ዓሊም ሲናገርም ዝም ሲልም በዕውቀት ነው።

ጃሂል ደግሞ በማያውቀው ነገር ገብቶ በነገር ቢዋኝ/ቢያወራ፡ ጃሂልነቱ ይፋ ይሆናል።

ስለሆነም በዝምታው ነውሩን ይሸፍናል።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

18 Nov, 01:09


የፈጅር ሶላት የቀንና የለሊት መላኢካዎች የሚቀያየሩበት ወቅት ነው።

መላኢካዎች ባረያህሱጁድ ሩኩዕ ኢስቲግፋር ተስቢህ ተህሊል ተክቢር ተህሚድ... ላይ ሁኖ ትተነው መጥተናል የሚል ሪፖርት ለጌታችን እንዲያደርሱልን በዒባዳ እንጠንክር።

ለይልዊትርሱሁርፈጅር

እንንቃሌሎችንም እናንቃ

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 19:14


የፈጅር ሶላት ሱናዋ ብቻ ከዱንያና በውስጧ ከያዘቻቸው ነገሮች ሁላ ትበልጣለች።

ሱናው እንዲህ ከሆነ ታዲያ ፈርዱ ምን ሊሆን ነው

የፈጅር ሶላት የሰገደ ሰው በአሏህ ጥበቃ ስር ነው።

ለይልዊትርፈጅር በአግባቡና በወቅቱ ለመስገድ በጊዜና በአዝካር እንተኛ።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 19:09


ቀልድ፡ ሳቅ፡ እንቶ ፈንቶ ወሬዎች፡ የማይመለከቱን ጉዳዮች ያበዛን ጊዜ፡

ልባችን ይደርቃል፡
ክብራችን ይገፈፋል፡
ባላሰብነው ሁኔታና ባልገምተነው ሰው እንዋረዳለን።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 18:48


💜ሰኞና ሀሙስ ስራዎች ወደ አሏህ ይቀርባሉ።

ፆመኛ ሁነን ስራችን ወደ አሏህ እንዲቀርብ ነገ ሰኞ ነውና እንፁም።

እንፁም፡
እናስፈጥር፡
እናስታውስ፡

💜ሙእሚን ከመልካም ነገር አይጠግብምና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 14:21


[ሱረቱ ነህል፡66]

[ግመል ከብት ፍየል] ሳርና መሰል ነገሮች ይበላሉ፡ ውሀን ይጠጣሉ።

ከተመገቡት ምግብ ደም የሚሆነው ወደ ጅማት፡ ወተቱ ወደ ግት ሽንቱ ወደ ፊኛ ይኼዳል።

አንዱ በአንዱ አይቀላቀልም አይደባለቅም!
በዚህ በደምና በፈርስ መካከል ትኩስ ጣፋጭ ለጠጪ ምቹ የሆነ ወተት ይወጣል

ሱብሃነሏህ!
የትኛው ቴክኖሎጂ ነው ሳርና ውሀን አደባልቆ ወተት የሚፈጥረው⁉️

የምሽት አዝካር።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 13:32


⚠️ብዙ ሰው ዘንድ የምመለከተው ስህተት፡

ከሩኩዕ ሲንነሱ ሰሚዐ-ሏሁ ሊመን ሀሚደሕ ይላሉ።

ይህ ስህተት ነው። /و የለም!

ትክክለኛው ሰሚዐ-ሏሁ ሊመን ሀሚደሕ

سمع الله لمن حمده
ማለት ነው።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 11:36


በኛ ላይ ያለፉ ነገሮች ሁሉ [ታሪክ ሁነው] እናስታውሳቸዋለን።

ከፈተናው በኋላ ጌታችንን እናመሰግናለን።

ብቻ ከታጋሾች እንሁን።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 11:27


ረሱልﷺ በነዚህ 5️⃣ተህሊሎች ላይ ሁኖ የሞተ ሰው እሳት አትነካውም ብለዋል።
لا إله إلا الله والله أكبر.
لا إله إلا الله وحده.
لا إله إلا الله لا شريك له.
لا إله إلا الله له الملك وله الحمد.
لا إله إلا الله ولا حول ولا قوه إلا بالله.

በሁሉም ተህሊሎች ወቅት አሏህ ባረያዬ ዕውነት ብሏል ይላል።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 11:20


🚫ኢንሻላህ በጀነት እንገናኛለን አትበል።
✔️ይልቁንስ በጀነት እንድንገናኝ አሏህን እንጠይቃለን በል።

ኢማሙ ኢብኑ ባዝ አሏህ ይዘንላቸውና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 10:56


💜ሱጁዱ-ሰሕዉን ረስቶ ያሰላመተ ሰው፡ ካሰላመተ 4 ወይም 5 ደቂቃ አካባቢ በሆነ አጭር ጊዜ ካስተወሰ ሱጁዱ-ሰሕዉው ይሰግዳል።

ሆኖም ግን በጣም ከቆየ በኋላ ከሆነ ያስታወሰው፡ እኔም የሚታየኝ የአብዛኛው ዑለማኦች አቋምም ሱጁዱ-ሰሕዉው ከሱ ላይ ይወድቃል [መስገድ የለበትም] የሚለው ነው።

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ግን ባስታወሰው ሰአት መስገድ አለበት። ሀታ ከ1 ሰአት ከ2 ሰአት በኋላም ቢሆን ያስታወሰው መስገድ አለበት ብሏል።

ሸይኽ ሷሊህ ኢብኑ ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና።

💥حكم من نسي السجود للسهو!

🔹السؤال:
إذا نسي الإنسان سجود السهو ثم تذكر بعدما فرغ من الصلاة ماذا يفعل؟

🔸الجواب:
إذا نسي الإنسان سجود السهو حتى سلم فليسجد.

أما إذا طال الفصل، فإنه يسقط عنه عند أكثر العلماء،
وقال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله: متى ذكر سجد، حتى لو مضت عليه ساعة أو ساعتان فإنه يسجد،

ولكن الذي يظهر لي: أنه لا يسجد إذا طال الفصل
أما إذا كان أربع أو خمس دقائق فيسجد ويسلم.

🔸الشيخ ابن عثيمين رحمه الله

📓لقاء الباب المفتوح (126)

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 07:47


ወንበር ላይ ተቀምጦ የሚሰግድ ሰውን በተመለከተ በጣም ወሳኝ ነጥብ፡

ሰውዬው ከመጀመሪያው ጀምሮ ቁጭ ብሎ የሚሰግድ ከሆነ፡ የወንበሩን የኋላ እግር ሶፍ ላይ[ከሰዎች ተረከዝ እኩል ] ያደርገዋል፡ ትከሻውም ከሰዎች ትከሻ ትይዩ ይሆናል። በዚህ መልኩ ቁጭ ብሎ ሶላቱን ይጨርሳል።

ሰውዬው መጀመርያ ሶላቱን ቁሞ የሚጀምር ከሆነና ለሩኩዕና ለሱጁድ የሚቀመጥ ከሆነ፡

ሲቆም ወንበሩን ወደ ኋላ አድርጎ ትከሻው ከሰዎች ትከሻ እኩል አድርጎ[በመደበኛው አቋቋም] ይቆማል፡

ለሩኩዕ/ለሱጁድ መቀመጥ ሲፈልግ ወንበሩን ወደ ፊት ስቦ ሶፍ ውስጥ ያስገባውና ይቀመጥበታል፡

ሱጁድ/ተሸሑድ ጨርሶ ሲቆም ደግሞ ወንበሩን ወደ ኋላ ያደርግና ሰውዬው ሶፍ ውስጥ ተስተካክሎ ይቆማል፡
ሆኖም በእርጅና ወይም በሌላ ምክንያት ሰውዬው ወንበሩን ወደ ፊት ወደ ኋላ ማድረጉ በጣም የሚያስቸግረው/የማይችል ከሆነ፡

ወንበሩን ሶፍ ላይ አድርጎ እሱ ከሶፉ ትንሽ ወጣ/ቀደም ብሎ ቁሞ ሶላቱን ይጀምራል ባለበት ሁኔታ ሶላቱን ይጨርሳል። ይህ ትንሽ ከሶፍ ቀደም ማለቱ ከአቅም በላይ በሆነ ምክነያት ስለሆነ ኢንሻላህ ዐፍው ይባላል።

ሸይኽ ዶ/ር ዐዚዝ ቢን ፈርሃን አሏህ ይጠብቃቸውና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 04:07


ዱንያ የሸይጧን ኸምር ናት። በሷ የሰከረ ሰው፡

በሙታን ካምፕ ውስጥ ከከሰሩ ሰዎች ጋር የተቆጨና የተፀፀተ ሁኖ እንጂ አይነቃም።

የህያ ቢን ሙዓዝ አሏህ ይዘንለትና።

⚠️በዱንያ አንሸንገል፡ አኼራን አሻግረን እንመልከት፡ ተውበትና ኢስቲግፋር እናብዛ!

ያማረ ውሎ ይሁንልን።

📌 قال يحيى بن معاذ :

✍🏻 الدنيا خمرُ الشيطان من سَكِرَ منها لم يُفِقْ إلا في عسكر الموتى نادماً مع الخاسرين.

📖 جامع العلوم والحكم (٧١٣).

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

17 Nov, 01:29


ጣፋጭ ዕንቅልፍህንና የምትወዳት ባለቤትትህን ትተህ ተነስተህ ለይል ስትቆምና፡

ልክ ለጌታህ በሩኩዕና በሱጁድ ዝቅ ስትል፡ ስትተናስ፡ ስትደፋ

⚙️በአሏህ ፈቃድ ጭንቀት ትካዜና ሀዘኑ ተጠራርጎ ይውወገዳል።

ንቁአንቁ
ለይልዊትርፈጅር

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

16 Nov, 19:46


በአሏህ ፈቃድ ለይልዊትርፈጅር ለመስገድ አስበን አላርም ሞልተን እንተኛ።

والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته.

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

16 Nov, 19:43


እህቶች እያነበባችሁ።

ባልን መታዘዝ ጂሃድ ነው፡ ትዕግስት ያስፈልገዋል።

ለሴት ልጅ ባልዋን ልታከብር፡ በስርአት ልታናግረውና በሱ ላይ ድምፅ ከፍ ላታደርግ የተገባ ነው።

ሸይኽ ሷሊህ ኢብኑ ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና።

طاعة الزوج جهاد يحتاج الصبر؛ ينبغي للمرأة أن تحترم زوجها ؛وأن تخاطبه بأدب وأن لا ترفع صوتها عليه..

الإمام ابن عثيمين رحمه الله .

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

16 Nov, 19:34


ዱንያ፡

ትንሽ ሁኖ ያብቃቃ፡ ብዙ ሁኖ ካዘናጋ ይሻላል።

ባለን እንብቃቃ።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

16 Nov, 19:17


الحمد لله!
تمت بالخير.

Abu Furat

16 Nov, 19:16


Live stream finished (45 minutes)

Abu Furat

15 Nov, 05:29


🤎🔠🔤🔠🔤'🔤' 💜

አንድ ባረያ በስትንፋሱ ቁጥር በሳቸው ﷺ ላይ ሶለዋት ቢያደርግ እንኳ ሀቃቸውን የሚውወጣ/የሚሞላ አይሆንም

ኢማሙ ኢብነል ቀዩም አሏህ ይዘንለትና!

🌸صلوات ربي وسلامه عليه 🌸

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

15 Nov, 01:48


🔘ወንድሜ ንቃ! ትክክለኛ ወንድ ሁን!🔘

ወንድነትህን ሚስትህን በማሰቃየት ሳይሆን ዕንቅልፍና ሸይጧንን በማሸነፍ አሳይ!

ሱረቱ ኑር ላይ አሏህ ወንዶች ብሎ የጠራቸው፡ እሱን ከመገዛት ንግድም ይሁን ምንም ነገር የማያዘናጋቸው ቆራጦችን ነው።

እህቴ አንቺስ ለይል ለመቆም ምን ከለከለሽ?

ባረከሏሁ ፊኩም ‼️
በዱንያ ያማረና ፅድት ያለ ህይወት ለመኖር፡ በአኼራ ደግሞ ጀነትን ለመውረስ የለይል ባልደረባ እንሁን!

ለይልዊትርፈጅር
ንቁአንቁ

🌸صلوات ربي وسلامه عليه🌸

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 19:00


🔈አያመል ቢድ መፆም ለሚፈልግ ሰው፡ ቀኑ ነገ ጁሙዓ ቅዳሜና እሁድ ነው።

በወር 3️⃣ቀን መፆም የአመት ፆምን ምንዳ ያስገኛል።

ለይልዊትርፈጅር በአግባቡና በወቅቱ ለመስገድ በጊዜና በአዝካር እንተኛ።

ደህና እደሩ።
صلوات ربي وسلامه عليه.
https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 18:01


ሰለፎች እንዲህ ናቸው

ታላቁ ታብዕይ ሀሰን አል-በስርይ አሏህ ይዘንለትና አንድ ለሊት፡

"ያ አሏህ! የበደለኝን ሰው ይቅር በለው" የሚለውን ዱዓ አበዛ፡

ከዛም አንድ ልጅ፡
አባ ሲዒድ ሆይ! የበደለህ ሰው እኔ በሆንኩኝ ብዬ እስክመኝ ድረስ፡ ለሊቷ ለበደለህ ሰው ዱዓ ስታደርግ ሰምቼሀለሁ!

ለዚህ ነገር ምን አነሳሳህ? አለው።

ሀሰነል በስሪይም፡
﴿فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُ‌هُ عَلَى اللَّـه﴾
[ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአሏህ ላይ ነው]

የሚለው የአሏህ ቃል አለው።

كان الحسن البصري يدعو ذات ليلة:
اللهم اعفُ عمن ظلمني فأكثر في ذلك..
فقال له رجل: يا أبا سعيد لقد سمعتك الليلة تدعو لمن ظلمك حتی تمنيت أن أكون فيمن ظلمك
فما دعاك إلى ذلك؟
قال:
قوله تعالى:
﴿فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُ‌هُ عَلَى اللَّـه﴾

📖 شرح البخاري «لابن بطال» (6/575).

የሙግት ሰለፍይ አንሁን፡ ባረከሏሁ ፊኩም።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 14:02


💜በሰው ላይ ከመንጠልጠል፡ በዛፍ ላይ መንጠልጠል ይሻላል፡

ቢያንስ የዛፉን ጥላ ታገኛለህ፡ ፍራፍሬም ልታገኝ ትችላለህ።

በሰው ላይ መንጠልጠል የጀመርክ ጊዜ ግን፡

⚙️ከአሏህ ጋር ያለህ ግንኙነት ይቋረጣል፡ የውርደትና የበታችነት ቁልቁለት ትጀምራህ!

በመኽሉቅ ላይ ተደግፎ ክብርና ልቅና ከመፈለግ በአሏህ እንጠበቃለን።

አቡ ፉራት 💧

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 11:15


ወላጆቻችን ለኛ ምን ያክል ዋጋ እንደከፈሉ በትክክል የምናውቀው፡

እኛም አሏህ ልጆች ሰጥቶን ለልጆቻችን መሥዋዕትነት መክፈል ስንጀምር ብቻና ብቻ ነው
رَبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 11:03


ሌባ እናት ልጇን አታምንም እንደሚባለው፡
አጭበርባሪ ሁሉም ሰው አጭበርባሪ ይመስለዋል።
አስመሳዩም ሁሉም ሰው አስመሳይ ይመስለዋል።
ሙናፊቁም ሁሉም ሰው ልክ እንደራሱ ባለ 2️⃣ፊት ይመስለዋል።

ሙእሚን ግን ከውጭ በሚያየው ነገር ይፈርዳል እንጂ፡ በሰዎች ላይ መጥፎ ጥርጣሬን አይጠራጠርም።

የውስጣቸውን ጉዳይ ደግሞ ወደ አሏህ ያስጠጋል።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 10:49


💜የድብቅ ወንጀሎች ...

🎙ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ حفظه الله ورعاه

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 05:14


ድሀን ሀብታም ያደርጋል፡ የተሰበረን ይጠግናል!
ሰዎችን ይሰጣቸዋል፡ ሌሎችን ደግሞ ይከለክላል!
ይገድላል፡ ህያውም ያደርገዋል!
አንዱን ከፍ፡ አንዱን ዝቅ ያደርጋል!
አንድ ጉዳይ ከአንዱ ጉዳይ አያዘናጋውም አያሳስተውም!

💜كُلَّ يَوْمٍ هُوَ فِى شَأْنٍ💜

💜በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡💜

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 05:00


ከሰዎች መገናኘት ተባለ አለ በማለት ፡ ወሬ ከመተብተብና ከመቃዠት ውጭ ምንም አይጠቅምም።

ዕውቀትን ለመቅሰም ወይም ሁኔታን ለማስተካከል ካልሆነ በስተቀር፡ ሰዎችን መገናኘት አሳንስ [ብዙ አትገናኝ]!

لِقَاءُ النّاسِ لَيسَ يُفِيدُ شَيئًا سِوَى الهَذَيَانِ مِنْ قِيلٍ وَقَالِ➪ ، فَأَقلِلْ مِن لِقَاءِ النّاسِ إِلّا لِأَخْذِ الْعِلْمِ➪ ،ِ أَو إِصلَاحِ حَالِ➪  .

سير أعلام النبلاء •|

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 03:14


🔘በትንሽ ስራ በየቀኑ 1️⃣0️⃣0️⃣0️⃣ ሀሰናት የምታገኙበትን፡ ወይም 1️⃣0️⃣0️⃣0️⃣ ወንጀል የምታሰርዙበትን ነገር ልጠቁማችሁ፡

1️⃣0️⃣0️⃣ ጊዜ سبحان الله በሉ፡ በአሏህ ፈቃድ ይህንን ምንዳ ታገኛላችሁ።

ሙስሊሙ ዘግቦታል።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 02:53


🆘ከዚህ ታሪክ ትምህርት እንውሰድ፡ ሌሎችንም እናስጠንቅቅ🆘
===
" መኪናው አስፓልት ዳር ቆሞ ቢገኝም ውስጥ የነበረው እቃ ግን ተዘርፎ ተወስዷል " - አመልካቾች

ከሰሞኑን አንድ ዝርፊያ በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።

ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው ታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 - 00434 አ.አ የሆነ እቃ ጫኝ አይሱዙ መኪና ከነጫነው እቃ በተደራጁ ዘራፊዎች ተወስዶባቸው እንደነበር ባለቤቶቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከጫነው እቃ ጭምር የተዘረፈውን መኪና ያዩ ወገኖችም እንዲያፏልጓቸው ብዙ ሲጥሩ ከቆዩ በኃላ ንብረቱ ተወስዶ መኪናው ግን ሃና ማርያም አካባቢ መንገድ ዳር ቆሞ ተገኝቷል።

ዝርፊያው እንዴት ተፈጸመ ?

መኪናው ከቀናት በፊት ከኮዩ ፈጬ የንግድ እቃ ጭኖ መርካቶ ለማራገፍ መንገድ ይጀምራል።

ሳር ቤት ኪንግስ ሆቴል አከባቢ ሲደርስ ግን የወታደር ሬንጀር ልብስ የለበሱ እና የታጠቁ
ሰዎች በአባዱላ መኪና መንገድ በመዝጋት መኪናውን ያስቆሙታል።

በተጨማሪም ልክ የህግ አስከባሪ አካላት (ወታደር) እንደሆኑ በማስመሰል ሹፌሩን " መንጃ ፍቃድ አምጣ " ብለው ጠይቀው ህገወጥ እቃ እንደጫነ ጥቆማ ደርሷቸው ያስቆሙት መሆኑን እና መኪናው ለፍተሻ የሚፈለግ መሆኑን ይገልጻሉ።

ሹፌሩም የጫነው እቃ መርካቶ የሚራገፍ የንግድ እቃ መሆኑን ገልፆ እቃው የተገዛበትን ደረሰኝ በማሳየት ጭምር ለማስረዳት ይሞክራል።

ይሁንና ግን ልክ እንደ ህግ አስከባሪ / ወታደር ልብስ ለብሰውና ታጥቀው እና ተደራጅተው የመጡት ዘራፊዎች " መኪናው ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ መፈተሸ አለበት " በማለት ሹፌሩን እያዋከቡ እና እየደበደቡ አውርደው ወደያዙት አባዱላ መኪና ያስገቡታል።

የእነርሱ ሹፌር ደግሞ ወደ አይሱዙው ገብቶ መኪኖቹ ፊት እና ኋላ ሆነው እየተከታተሉ ይሔዳሉ፡፡

ይሁንና ግን ቡልጋሪያ አከባቢ ሲደርሱ አይሱዙው ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲያመራ ሹፌሩን የጫነው አባዱላ ደግሞ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይዞራል።

በዚህ ሰዓት ሹፌሩ " ህግ ቦታ እየወሰድንህ ነው አላላችሁኝም ወይ ? ለምንድነው መኪናው ወደ ሌላ አቅጣጫ የሚሔደው ? " የሚል ጥያቄ ሲያነሳ ውስጥ ያሉት ዘራፊዎች ሹፌሩን እራሱን እስከሚስት ድረስ በመደብደብ እና በማፈን ጭምብል አልብሰው በፍጥነት እየነዱ ይጓዛሉ።

በዚህ ሁኔታ ለረጅም ርቀት ከተጓዙ በኋላ ኃጫሉ መንገድ ወደ ጋርመንት መሔጃው ጋር ሹፌሩን ከመኪናው አውርደው ጥለውት ይሰወራሉ።

ሁኔታው ከተፈጠረ በኋላ አከባቢው ላይ የደረሱ ሰዎች ሹፌሩን አፋፍሰው ጤና ጣቢያ ያደረሱ ሲሆን ሹፌሩም አራሱን ከመሳት ከነቃ በኋላ ጉዳዩን ወንጀሉ ለተፈፀመበት አከባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክቷል።

ከቀናት በኃላ በተደረገ ፍለጋ መኪናው ሃና ማርያም አስፓልት ዳር ቆሞ ሊገኝ ችሏል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መኪና ከጫነው እቃ ጭምር እንደተዘረፈባቸው የገለጹት አመልካቾች ፥ " ምንም እንኳን መኪናው ቆሞ ቢገኝም ውስጥ ተጭኖ የነበረው ከ3.4 እስከ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት እቃ ተዘርፎ ተወስዷል " ብለዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እስካሁን የተያዘ ሰው እንደሌለ ጠቁመዋል።

ሌሎች ወገኖች መሰል ነገር እንዳይፈጸምባቸው በማለት ይህንን ጉዳይ ለጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ ማጋራታቸውን ገልጸዋል።

©TIKVAH

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

14 Nov, 01:40


🟢በድቅድቅ ጨለማ የምንሰግደው የለይል ሶላት በአሏህ ፈቃድ የዱንያን ጭንቀትና የቀብር ጨለማን ያስወግዳል።
የሁለት ሀገር ስኬትን ያጎናፅፋል።

🟢ፆመኞች ትንሽም ቢሆን ሱሁር ብሉ፡ ሱሁር መብላት ዒባዳ ነው በውስጡም በረካ አልለ!

ለይልዊትርሱሁርፈጅር

ንቁአንቁ

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

13 Nov, 18:49


በዓቂዳህ ጠንካራ ከሆንክ ጂንና ሸይጧን ካንተ ይፈራሉ

በዓቂዳህ ግን የምትወለጋገድና ቀጥ ያላልክ ከሆንክ፡ ምናልባት ጥላህንም ልትፈራ ትችላለህ።

ሸይኽ ሙቅቢል ዋድዒይ አሏህ ይዘንላቸውና።

💐ገራሚ አገላለፅ ነው፡ ደህና እደሩ💐
- فإذا كنت قوي العقيدة
● الجنّي
● والشيطان سيخافا منك

وإذا كنت مزعزع العقيدة
>>> ربما تخاف من ظلّك .

العلامة مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله .

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

13 Nov, 18:39


ዛሕራ 130 ሓዲሶች ክፍል 3
ዛሕራ መስጂድ ላይ እየተሰጠ ያለው (የእውቀት መጀመሪያ 130 ሓዲሶች ክፍል 3 ደርስ)
ይህ ኪታብ በድጋሚ የተቀዳ አዲስ ሪከርድ ነው፡፡
ከዚህ በፊት ከነበረው ቅጂ ይለያል
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

ሀቂቃ ይህ ክፍል በጣም ገራሚ ደርስ ነው፡ የባለፈው ሳምንት ደርስ ነው ይደመጥ!

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

13 Nov, 18:36


💜ፂም ለወንድ ልጅ ጌጡ/ውበቱ፡
💜ለፊቱ ኑር/ብርሃን፡
💜ከሴት ልጅም የሚልለይበት ነው።

ኢማሙ ኢብኑ ባዝ አሏህ ይዘንላቸውና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

13 Nov, 18:31


🆘ፂሙን የሚልጭ ሰው ፋሲቅ ነው፡ ምስክርነቱም ተቀባይነት የለውም።

🆘በመጅሊስ/በሹራ ላይም የሱን ሀሳብ አይያዝም።

ኢማሙ ማሊክ አሏህ ይዘንላቸውና።

ለይልዊትርፈጅር በወቅቱና በአግባቡ ለመስገድ፡

በጊዜና በአዝካር እንተኛ

📌حالق اللحية فاسق لا تُقبل شهادتـه!
ولا يُؤخذ برأيه في المجالس.

-الإمام مالك رحمه الله🎙

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

13 Nov, 18:08


አንድ ሰው ረሱልﷺ ዘንድ መጣና በህልሙ አስደንጋጭ፡ አስፈሪ ነገሮች እንደሚያይ ነገራቸው፡

እሳቸውም ፍራሽህ ላይ ልትተኛ ስትል ይህን ዚክር በል አሉት፡

[‏أعوذُ بكلماتِ اللَّـهِ التامَّةِ ،من غضبِهِ وعقابِهِ، ومِن شرِّ عباده ،ومن همزاتِ الشياطينِ ،وأنْ يحضرون .]

‏جاءَ رجلٌ إلى النبيِّ ﷺ فشكَا إليهِ أهاويلَ يراها في المنامِ ( يعني أشياء مخيفة مفزعة ) .

‏فقال له النبي ﷺ :

‏إذا أويتَ إلى فراشِك فقلْ :

‏أعوذُ بكلماتِ اللَّـهِ التامَّةِ ،من غضبِهِ وعقابِهِ، ومِن شرِّ عباده ،ومن همزاتِ الشياطينِ ،وأنْ يحضرون .

📖 ‏السلسلة الصحيحة ٢٦٤٤.

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

13 Nov, 17:49


🔘ነገ ሀሙስ ነው እንፁመው 🔘

ጌታችን አሏህ ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለራሱ ነው ፆም ግን ለኔ ነው እኔው በሱ እመነዳዋለሁ ብሏል፡
የፆመኛ የአፍ ጠረን አሏህ ዘንድ ከሚስክ የበለጠ የተወደደ ነው፡
1️⃣ቀን በአሏህ መንገድ የፆመ ሰው ፊቱ ከእሳት 7️⃣0️⃣ አመት ይርቃል
በወር 3️⃣ ቀን የፆመ ሰው አመቱን ሙሉ እንደ ፆም ሰው ምንዳ ይስሰጠዋል፡
ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት በር አልለ፡
ፆም በዱንያ ከሀራም፡ በአኼራ ደግሞ ከእሳት መጥጠበቂያ ጋሻ ነው፡
🔤🔤🔤

ነገ ሀሙስ ነው፡
🤎እንፁም
🤎እናስፈጥር፡
🤎የምንወዳቸውን እናስታውስ❗️

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

13 Nov, 17:28


በመኪና አደጋ፡ በቃጠሎ፡ በመስመጥና መሰል ድንገተኛ አደጋዎች የሚሞት ሰው የሸሂድን ምንዳ ያገኛል።

በምጥ ወቅት ስትወልድ የሞተችም ሴት የሸሂድን ምንዳ ታገኛለች።

💜ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አሏህ ይጠብቃቸውና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

13 Nov, 03:37


🔘በአንድ ዚክር ጀነትን ግቡ🔘

ይህንን ዚክር አለማለት ሀቂቃ ትልቅ ኪሳራ ነው።
ሰይዱል ኢስቲግፋር

ረሱል ﷺ አንድ ሰው ይህን ዚክር እርግጠኛ ሁኖ[የቂን ብሎ] ቀን ላይ ካለና በዛው ቀን ሳይመሽ ከሞተ የጀነት ነው

በለሊት ላይ [በዚክሩ] እርግጠኛ ሁኖ ይህንን ዚክር ካለና በዛው ለሊት ሳይነጋ ከሞተ የጀነት ሰው ነው ብለዋል። ቡኻሪ ዘግቦታል።

የጠዋት አዝካር

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

12 Nov, 18:19


ከኡስታዝህ ዕውቀትን ቅሰም እንጂ፡ በኡስታዝህ አትንጠልጠል አትደገፍ

ረሱል ﷺ ለውዱ ልጃቸው፡

አንቺ ፋጢማ ቢንት ሙሀመድ ሆይ! ነፍስሽን ከእሳት አድኚ። እኔ ላንቺ ከአሏህ ምንም ነገር አላደርግልሽም ብለዋታል።

🆘አንተስ? አንቺስ? ኡስታዝህ ያድንሀል? ያድንሻል?

ኡስታዜ ኡስታዜ በልኩ ይሁን።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

12 Nov, 17:03


💜አብዛኛው ሰዎችን እሳት የሚያስገባው አፍና ብልት ነው።

💜ረሱል صلوات ربي وسلامه عليه 🌴

💜ከአፋችን መጥፎ ንግግር እንዳይወጣ፡ ሀራም ምግብ/መጠጥ ደግሞ እንዳይገባ እንጠንቀቅ።

አስተውል❗️
በሀራሙ ስሜትህን ስትወጣ ከባድ ወንጀል እንደሆነው ሁሉ፡ በሀላል ኒካህ ካገባሀት ሚስትህ የምታደርገው ግንኙነት ደግሞ ሶደቃ ነው።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

12 Nov, 16:02


🔘ይነበብ🔘

የታመመን መጠየቅ ትልቅ ምንዳ አልለው፡ ኢስላማዊም ሀቅ ነው።

😉ሆኖም ዝም ብለን የቱጋ ፈለጠህ? የቱጋ ቆረጠህ? ና መሰል እርባና ቢስ ነገሮች እያወራን ልብ ከምናወልቅ፡ የበለጠ በህመም ላይ ህመም ከምንጨምር

ይህንን ትልቅ ዱዓእ እናድርግለት፡

[أسأل الله العظيم، رب العرش العظيم أن يشفيك]
ረሱል ﷺ የታመመን ሰው ሲጠይቁ የታመመውን ሰው ራስጌ ቁጭ ብለው ይህንን ዱዓ 7️⃣ጊዜ ያደርጉ ነበር።

በሌላ ሶሂህ ሀዲስ እንደተረጋገጠው ደግሞ ረሱል ﷺ አንድ ሰው አንድን አጀሉ ያልደረሰ የታመመን ሰው ጠይቆ ለታመመው ሰው ይህን ዱዓ 7️⃣ጊዜ አያደርግለትም፡ ሰውዬው ዓፍያ ቢሆን እንጂ ብለዋል።

ህይወታችን በዕውቀት ብርሃን ላይ ይሁን

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

12 Nov, 15:42


ሶላት ላይ የተሸሑድ አደራረግ በዚህ መልክ ነው።

ሸይኽ ዶ /ር ዐብዱ-ረዛቅ አል-በድርን እናዳምጣቸው።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

12 Nov, 14:46


🔘ዕወቅ❗️ልብ ልክ እንደ ምሽግ ነው።

ሸይጧን የጠባቂን ዝንጋቴ እየፈለገ በዚህ ምሽግ ከመሽከርከር አይወገድም!

ጠባቂው ለቅፅበት እንኳን ቢሆን ከመጠበቅ ሊዘናጋና ክፍተት ሊፈጥር አይግገባም።

ምክነያቱም ጠላት ላፍታም እንኳን አይዘናጋምና!

🤎ኢማሙ ኢብኑ ጀውዚይ አሏህ ይዘንለትና።

የምሽት አዝካር

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

12 Nov, 13:24


🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤 
🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤

💜 #Gumer 💜

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

12 Nov, 09:21


🌸ጨዋ የሆነች ሴት ከአጅነብይ ወንድ ጋር ስታወራ ጠንከር ኮስተር ማለት አልለባት!

መቅለስለስ ድምፅን ማለስለስና ማለዘብ መሽሞንሞን ተገቢ አይደለም፡ የፊትና በር መክፈት ነው።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

11 Nov, 14:20


💜የምሽት አዝካሮችን በተደቡርና በአግባቡ እንዘክር።

💜የፆመኛ ዱዓ ሙስተጃብ ነውና ፆመኞች ዱዓ አብዙ፡ በተለይ በኢፍጧር ወቅት።

💜በዱዓችሁ ሌሎችም የኢማን ወንድምችና እህቶችን አስታውሱ፡ የመላኢካ ዱዓ ታገኛላችሁ

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

11 Nov, 11:05


ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር ገፅ የተወሰደ!
ቴሌግራም ገፁን የሚፈልግ በዚህ ሊንክ መቅቀላቀል ይችላል👇
https://t.me/sultan_54

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

11 Nov, 10:22


የታላቁ ታብዕይ ሀሰን አል-በስርይ ድንቅ ንግግር፡

በቁርአን 9️⃣0️⃣ ቦታ ላይ፡ አሏህ ሪዝቅን እንደቀደረና ለፍጡራኖቹም [ለሪዝቃቸው] ሀላፊነት እንደወሰደ ቀርቻለሁ።

1️⃣ቦታ ደግሞ ሸይጧን [እንዳትለግሱ] ድህነትን ያስፈራራችኋል የሚል ቀርቻለሁ።

9️⃣0️⃣ ቦታ ላይ ያልለውን የእውነተኛውን ንግግር ተጠራጥረን፡ በ1️⃣ቦታ ላይ ያልለውን የውሸተኛውን ንግግር አመንን❗️

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

11 Nov, 05:44


በሀላሉ ስትሰራ ጀርባህ ሊስሰበር ጉልበትህ ሊዝል ይችል ይሆናል።

ነገር ግን ሁሌም የትም አንገትህን ቀና አድርገህ እንድትራመድ ያደርገሀል።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

11 Nov, 05:10


ጌታውን ሚግገዛ በተውሂድ በሱና
ተደላድሎ ገብቷል በስኬት ጎዳና

ማጣት አይበግረው ማግኘት አያኮራው
የዱንያ ኮተቶች፡ ስላልሆነ ዓላማው

የሱ ትልቁ ግብ፡ ትልቁ ዓላማ
ጌታውን ማየት ነው በዳረል ከራማ

አቡ ፉራት 💧

ካሰብነው በላይ ተሳክቶልንና ተደስተን የምንውልበት ውብና ያማረ ውሎ ይሁንልን።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

11 Nov, 00:54


በለሊት ጨለማ፡ ሶላቱን የሚሰግድ
በ'ርግጥ ጀምሯል የደጋጎች መንገድ


ለይልዊትርሱሁርፈጅር

ንቁአንቁ

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

10 Nov, 18:58


ለሴት ልጅ ባልዋ እሷ ዘንድ እይያለ [መንገድ ካልወጣ]፡

ባልዋ ሳይፈቅድላት ሱና ፆም መፆም አይፈቀድላትም።

ላጤዎች አሏህ ይዘንላችሁና ማግባት ካልቻላችሁ ፆም አብዙ፡ አይናችሁ ለመስበርና ከሀራም ለመጥጠበቅ ይረዳችኋል ብለዋል

💜ውዱ ነብያችን صلوات ربي وسلامه عليه 🌴

ደህና እደሩ።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

10 Nov, 18:49


ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ረሱል ረሱልﷺ፡

በጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አልለ። ፆመኞች የውመል ቂያማህ ይገቡበታል። ከነሱ ውጭ ማንም ከሱ አይገባም!

ፆመኞች የት አልሉ? ይባላል። ይቆማሉ ከነሱ ውጭ ከሱ ማንም አይገባም። ልክ እንደ ገቡ ይዝዘጋል፡ ከሱ ከነሱ ውጭ ማንም አይገባም ብለዋል።

💜ነገ ሰኞ ነው እንፁመው ባረከሏሁ ፊኩም!

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

10 Nov, 18:37


ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ረሱልﷺ፡

በአሏህ መንገድ ላይ አንድን ቀን ለፆመ ሰው፡ አሏህ ፊቱን ከእሳት 7️⃣0️⃣ አመት ያርቀዋል ብለዋል።

ነገ ሰኞ ነው

🌸እንፁም፡
🌸እናስታውስ፡
🌸እናስፈጥር፡

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

09 Nov, 14:51


💜ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ💜

ጣኦታትን በመሰባበሩ ምክነያት ጣኦት አምላኪዎች ወደ እሳት የጣሉት ነቢይ ማን ይባላል⁉️

⭐️ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና⭐️

🌸መልሱን በመንካት  ውሰዱ🌹

ሀ❳ ሙሀመድ [ﷺ]

ለ❳ ሙሳ [عليه السلام]

ሐ❳ኢብራሒም [عليه السلام]

መ❳ ዒሳ [عليه السلام]

መልካም እድል

Abu Furat

09 Nov, 14:45


የአሏህን ፍጥረት ለመቀየር የሚጥር ሰው ወንጀሉ ምንኛ ከፋ!

ከአሏህ የበለጠ አሳማሪ አለ?
ወደ አፈር እንደምንመለስ ተረሳ?

በተለይ እህቶች አሏህን ፍሩ!

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

09 Nov, 12:20


ጌታችን አሏህ የምንፈልገውን ነገር ከሰጠን በእዝነቱ ነው

ከከለከለን በጥበቡ ነው

እኛ ግን ሁሌም እስትንፋሳችን እስካለ፡ ውዴታውን ከጅለን በዱዓእ ከማንኳኳት አንወገድም!

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

09 Nov, 12:01


የሰው ልጅ ልክ ሩሁ ሲወጣ አይኑን ወደ ላይ ይገልጣል፡ ከፍ ያደርጋል።

አይኑ ሩሁን ይከተላል።

ለዚህም አንድ ሰው ሲሞት አይኑን መሸፈን ይወደዳል።

ዛሬ ቁርአን ለመቅራት፡ መልካም ነገር ለመመልከት እምቢ ብሎ፡ ሀራም ነገር በመመልከት የተጠመደው ዐይናችን፡

ልክ ሩሀችን ከጀሰዳችን ሲወጣ፡ ይመለከተዋል ዕውነታው ይርረዳል።

‏عن أبي هريرة رضي الله عنه قال:

قال رسول الله ﷺ :

" ألم تروا الإنسان إذا مات شخص بصره ؟ " قالوا : بلى. قال : " فذلك حين يتبع بصره نفسه ".

📚رواه مسلم 921

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

09 Nov, 10:02


ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ርብርብ ነው! ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የሚችለውን እያደረገ ነው። በዚህ የመስጂድ ግንባታ ላይ የሶደቀቱን ጃሪያ ድርሻ እንዲኖረው የሚሻ ያቅሙን በማገዝ ለኣኺራው ስንቅ ያስቀምጥ።
መስጅደል ፉርቃን በወረባቦ ወረዳ ዋና ከተማ ቢስቲማ ላይ እየተሰራ ያለ መስጂድ ነው። መስጂዱ ለከተማው ድምቀት ነው። ከዚያ በላይ ግን ለከተማውም በዙሪያው ላሉ ቀበሌዎችም ጥሩ የደዕዋ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፣ ኢንሻአላህ።

መርዳት ለምትፈልጉ ከታች በተለጠፈው አካውንት ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ወረባቦ ፉርቃን መስጂድ
ንግድ ባንክ - 1000401221957
አቢሲኒያ - 64828638
ዳሽን - 2935824167011

መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን። ምናልባት በናንተ በኩል ተሳትፎ የሚያደርግ ቢኖር ከአጅሩ ተካፋይ ትሆናላችሁ።
{ مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }
"ሌሎችን ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።"
=
ቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Abu Furat

09 Nov, 08:45


ለሁሉም ኡመት/ህዝቦች የሚያመልኩት ጣዖት አልላቸው።

የዚህ ኡመት/ህዝብ ጣዖት ዲናርና ዲርሃም ነው።

ታላቁ ታብዕይ ሀሰን አል-በስርይ አሏህ ይዘንለትና፡

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

09 Nov, 06:54


ስለ ዲን ስለ ሸሪዓ የመጠቀ የጠለቀ ዕውቀት ያልለው ዓሊም ሲናገር እንዴት ደስስስስ ይላል!

የተቸገርነው በግብርና ተመርቆ የግል ሀኪም ቤት እንደሚከፍተው ሰው አይነት፡

ያለ ዕውቀት በዲን ላይ የሚፈተፍቱ ተናጋሪዎች በዝተውብን ነው።

🩵عليكم بالدليل من الكتاب والسنة على فهم السلف الصالح.

🎙 الشيخ الفاضل أ. د/ صالح بن سعد السحيمي -حفظه الله-.

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

09 Nov, 05:53


ዕውቀት በዱንያም በአኼራም ወደ መልካም ነገር ይመራል።

ሙቀት ግን ወደ ዋናው ሙቀት [የጀሃነም እሳት] ነው የሚመራው።

ከዛሬው ከወንድሜ ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ደርስ የተወሰደ!

ሙቀትና ዕውቀትን እንለይ!

ዕውቀት ወደ ልቀት ሲሆን፡ ሙቀት ግን ወደ ውድቀት ነው።

አቡ ፉራት 💧

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

08 Nov, 19:24


ሱብሃነሏህ!
ምንኛ ጣፋጭ ምክር ነው።
ደህና እደሩ።
ثنائية هي أصل الفتنة في الدين

لفضيلة الشيخ /
د. صالح بن عبدالله العصيمي

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

08 Nov, 13:39


ወንጀላችን እንዲሰረዝልን አንፈልግም

مَن قال: سُبْحانَ اللَّهِ وبِحَمْدِهِ، في يَومٍ مِائَةَ مَرَّةٍ؛ حُطَّتْ خَطاياهُ وإنْ كانَتْ مِثْلَ زَبَدِ البَحْرِ.

ረሱል ﷺ በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሃነሏሂ ወቢሀምዲሂ ያለ ሰው፡ ወንጀሉ የባህር አረፋ ያክል እንኳን ቢሆን ይስሰረዝለታል ብለዋል።

ዑለሞች ይህን ዚክር በቀኑ መጨረሻ ማለቱ የተሻለ ነው ብለዋል።

*️⃣እንዘክር|እናስታውስ❗️
*️⃣የምሽት አዝካር ❗️

صلوات ربي وسلامه عليه.

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

08 Nov, 11:32


⚠️ረሱልﷺ ያለፈውም የመጪውም ወንጀል ተምሮላቸው ሳለ፡ በተቀመጡበት አንድ መጅሊስ ብቻ ከ100 ጊዜ በላይ ጌታቸውን ምህረት ይጠይቁ ነበር።

ትልቁ ዒባዳ/ሶላትን እንደሰገዱ ወዲያው 3ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ ነበር፡ ከዛም ሌሎች ዚክሮች ይሉ ነበር።

በጣም የሚያሳዝነው እኛ ግን ልክ ሶላት እንዳለቀ፡ እንኳን ለኢስቲግፋርና ለዚክር ልንቀመጥ ቀርቶ፡

ልክ ከእስር እንደተለቀቀ ሰው ግር ብለን፡ ሰጋጆችን አቋርጠን፡ ተንጋግተንና ተገፈታትረን ከአሏህ ቤት እንወጣለን!

ለምን⁉️ እስከመቼ⁉️

ሀቂቃ እራሳችንን እንፈትሽ፡ ኢስቲግፋር እናብዛ፡ በዒባዳችን ላይ ዕርጋታና ደስታ ይኑረን።

🌸صلوات ربي وسلامه عليه🌸

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

08 Nov, 10:32


ሱረቱ-ዛሪያት ከቁጥር 17-18 ጌታችን አሏህ ስለ ጥንቁቆቹ 2️⃣ ባህሪያት እንዲህ ይለናል።

ከለሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበር።
በለሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ።

እኛም የነዚህ ሁለት የላቁ ባህርያት ባለቤት ለመሆን ጥረት እናድርግ።

صلوات ربي وسلامه عليه.

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

08 Nov, 01:11


መጥፎዎችን ከመቅቀላቀል፡ በብቸንነት ውስጥ ራሀ/ዕረፍት አልለ።

አሚረል ሙእሚኒን ዑመር رصي الله عنه

ይህን ዕውነታ አሏህ ገጥሞት ብቻውን የጌታውን ውዴታ ከጅሎ ለይል የቆመ ሰው ያውቀዋል፡ ያጣጥመዋል!

ለይልዊትርፈጅር
ንቁአንቁ

صلوات ربي وسلامه عليه

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

07 Nov, 18:55


የበደሉንን ሰዎች ለአሏህ ብለን ይቅር ብለን፡

ለወንጀላችን ደግሞ ምህረትን ጠይቀንና ልባችንን አፅድተን፡

🔘ለይል🔘ዊትርና🔘ፈጅር በወቅቱና በአግባቡ ለመስገድ በጊዜና በአዝካር እንተኛ።

ደህና እደሩ

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

07 Nov, 17:48


በሁሉም ሁኔታ ላይ በነብዩ ﷺ ሶለዋት ማብዛት እወዳለሁ። በጁሙዓ ዕለትና በለሊቷ ደግሞ እጅግ በጣም ማብዛትን እወዳለሁ።

ኢማሙ አሽ-ሻፊዒይ አሏህ ይዘንላቸውና።

صلوات ربي وسلامه عليه

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

07 Nov, 17:39


💜ዐብደሏህ ኢብኑ ሙባረክ አሏህ ይዘንለትና፡

ሙሲባ አንድ ናት! ባለቤቱ ከተበሳጨ ግን ሁለት ትሆናለች።

አንዱ ሙሲባው እራሱ ሲሆን፡ ሁለተኛው ደግሞ [በመታገስ የሚገኘው] ምንዳ መወገዱ ነው።

ይህ [ምንዳው መወገዱ] ደግሞ ከመጀመሪያው ሙሲባ የባሰ ነው ብሏል።

💛ሶብር|እንታገስ💛

ለይለተል ጁሙዓ ነው ለአለማቱ እዝነት በተላኩት ነብያችን ላይ ሶለዋት እናብዛ🌴

صلوات ربي وسلامه عليه

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

04 Nov, 01:28


🤎(وَبِالأَسحارِ هُم يَستَغفِرونَ)🤎

💚أستغفر الله العظيم وأتوب إليه💚

ለይል|ዊትር|ፈጅር

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

03 Nov, 10:15


🔠🔠🔠🔠 🔠🔠🔠🔠🔠❗️

በሰላማዊ መንገድ የኒቃብ ጥያቄ ያቀረቡ
2️⃣ መተነቂብና 3️⃣ወንድ የአዲስ ከተማ ት/ቤት ተማሪዎች፡

ከጁሙዓ ጀምሮ እንደታሰሩና የት እንደታሰሩ እንደማይታወቅ ሀሩን ሚዲያ ከተማሪዎቹ ወላጆች ሰምቶ ዘግቧል።

🔴ሚስማር ሲምመታ የበለጠ እንደሚጠነክር ሁሉ፡ ሙስሊሞች ሲታሰሩ፡ ጭቆና ሲበዛባቸው ከአለት በበለጠ ይጠነክራሉ እንጂ አይስሰበሩም።

ተማሪዎቹ ይፍፈቱ!

ሀገር ተረካቢ ተማሪን በማሰር ሀገር አይግገነባም!

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

03 Nov, 08:47


አንድ ሰው ሱጁድ ሲወርድ #መጀመርያ በጉልበቶቹ መውረድ አለበት፡

ከዛም የእጅ መዳፎቹን ከዛም ደግሞ ግንባሩና አፍንጫውን መሬት ማስነካት አለበት።

ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አሏህ ይጠብቃቸውና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

03 Nov, 01:27


🔘ለአሏህ ብለን በለሊት ጨለማ የምንሰግደው የለይል ሶላት፡

የህይወት ምስቅልቅን ያስተካክላል፡
የቀብር ጨለማን ያበራል፡
የአኼራ ህይወትን ያሳምራል፡
የሲሯጥ ጉዞን ቀላል ያደርጋል፡
...

ያ አኺ! ያ ኡኽቲ! ጌታችን እኮ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ወርዶ

ሊምረን፡ የፈለግነውን ሊሰጠን፡... እየተጣራ ነው።

እንንቃ|እናንቃ!

🔴ለይል|ዊትር|ፈጅር።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

02 Nov, 18:54


የአንድ ባረያ በልቁ ምርጡና በላጩ ቀኑ፡

ወደ አሏህ ተውበት ያደረገበትና አሏህ ተውበቱን የተቀበለው ቀን ነው።

ኢማሙ ኢብነል ቀዩም አሏህ ይዘንለትና።

ወደ አሏህ እንመለስ፡ ደህና እደሩ።

أحبكم في الله جميعا.

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

02 Nov, 18:43


በረባ ባልረባው እንደፈለገ ከአጅነብይ ሴት እየተገናኘ እየተደባለቀ፡ እኔ በሴት አልፈተንም የሚል ወንድ፡

ወይ ውሸቱን ነው ወይም የጤና ችግር አለበት።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

02 Nov, 18:21


ፊትና የማይፍፈራ ከሆነና በተለመደው ሰላምታ በቃላት ማለስለስ/ማለዘብ እስከሌለ ድረስ፡

አጅነብይ የሆነችን ሴት በሰላምታ መጀመር ወይም ሰላምታ መመለስ ችግር የለውም።

🔴ሰላምታ መጀመር ሱና ነው፡ መመለሱ ግን ዋጂብ ነው።

🔴ሆኖም ግን ፈተና የሚከተል ከሆነ ይህን ነገር ይተወዋል።

ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አሏህ ይጠብቃቸውና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

02 Nov, 18:06


ኒቃብ የሚልለበሰው የአሏህና የመልዕክተኛው ትዕዛዝ ስለሆነ እንጂ፡

ለቁንጅና/ለውበት ተብሎ፡ ኒቃብ ውበት ነው በሚል መፈክር አይደለም‼️

ይልቁንስ ኒቃብ መልበስ የአሏህ ትዕዛዝ ነው‼️
ኒቃብ መልበስ ዒባዳ ነው‼️

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

02 Nov, 17:13


🌸ሷሊህ ሴት ባልዋ ደጋግ/ሷሊህ ከሆኑ ወላጆቹ እንዲያስበልጣት አትወድም፡ አትፈልግም🌸

ሸይኽ ሙቅቢል ዋዲዒይ አሏህ ይዘንላቸውና።


🌸الصَّالِحَة لَا تَدْفَعُ الزَّوْجَ إِلَى العُقُوقَ🌸

‏قَالَ العَلّامَة مُقْبِل الوَادِعِي رَحِـمَهُ الله- :

‏ «المَرْأَةُ الصَّالِحَةُ لَا تـَرْضَى بِـأَنْ يُفَضِّلَهَا زَوْجـُهَا عَلَى أَبـَوَيْهِ الصَّالِحَـيْنِ»

الرحله الأَخـِيرَة ص: (٢٤٠)

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

02 Nov, 14:47


🩷የመርሳት ሱጁድ [ሱጁዱ-ሰሕዉ] ከማሰላመት በፊትም በኋላም ማድረግ ይቻላል።

ነገር ግን #በማጉደል ከሆነ፡ ለምሳሌ የመጀመሪያው ተሸሑድ በመርሳት ወይም በሩኩዕና በሱጁድ ተስቢህ መርሳትና በመሳሰሉት ምክነያት ከሆነ ከማሰላመት በፊት ማድረጉ በላጭ ነው፡

#በመጨመር ከሆነ፡ ለምሳሌ ረስቶ አንድ ረከዓ ቢጭጨመር ካሰላመቱ በኋላ ይደረጋል።

ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አሏህ ይጠብቃቸውና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

02 Nov, 12:34


🔘ትኩረት ይስሰጠው🔘

ሶላት በጀመዓ ሲሰገድ መስጂድ ገብተን ከፊት ያለው ሶፍ ከሞላና ከኛ ጋር አብሮን የሚቆም ሰው ካላገኘን፡

የግድ አብሮን የሚቆም ሰው እስኪመጣ መጠበቅ አለብን እንጂ ለብቻችን ቁመን መስገድ የለብንም።

ሀታ ኢማሙ እስኪጨርስ ድረስ ጠብቀን ሰው ባይመጣ እንኳ፡ ኢማሙ ሲጨርስ ለብቻችን እንሰግዳለን፡ በኒያችን የጀመዓ ምንዳ እንመነዳለን።

ረሱልﷺ ከሶፍ በኋላ ለብቻ መስገድ ከልክለዋል፡ በአንድ ሶፍ ለብቻው የሰገደ ሰውን ሶላቱን እንዲደግም አዘዋል።

ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አሏህ ይጠብቃቸውና እናዳምጣቸው።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

02 Nov, 01:12


የለይል ጓዶች እንዴት ናችሁ?

ባላችሁበት ሁሉ አሏህ ሰላማችሁን ያብዛው።

በርቱ ተበራቱ ጠንክሩ ታገሱ ቆራጥ ሁኑ!

በአሏህ ፈቃድ ቀጠሮው ጀነት ነው።

ለይል|ዊትር|ፈጅር

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

01 Nov, 18:33


በሂጃብ እንቅፋት የሚሆን ሁሉ የሸይጧን ሰራዊት ነው።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

01 Nov, 18:20


🔡የኸይር ነገር መንገዶች ብዙ ናቸው።

እኔ እንደማስበው አሏህ ከደነገጋቸው ፈርዶች በኋላ በላጩ የሸሪዓ ዕውቀትን መፈለግ ነው።

ምክነያቱም በአሁን ወቅት ወደ'ሱ[ዕውቀት] በጣም ፈላጊዎች ነንና [በጣም ያስፈልገናልና] ! 🔣

ሸይኽ ሷሊህ ኢብኑ ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና።

«‏إنّ طُرق الخير كثِيرة، وأفضلُها فيما أرى بعد الفَرائض التي فرضَها الله هو طَلب ‌العِلم⁩ الشّرعي، لأننا اليوم في ضرُورة إليهِ».

  الشّيخ ابن عُثِيمين -رحِمهُ الله-.

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

01 Nov, 17:32


በወንበር ላይ ቁጭ ብሎ የሚሰግድ ሰው ሩኩዕና ሱጁድ ሲያደርግ፡

#በጭንቅላቱ_ብቻ ያመላክታል እንጂ ጀርባውን ከፍ ዝቅ እያደረገ ማንቀሳቀስ የለበትም!

ሸይኽ ዶ/ር ዐዚዝ ቢን ፈርሃን አሏህ ይጠብቃቸውና እናዳምጣቸው።

طريقة الركوع والسجود للمصلين على الكرسي .
الشيخ الدكتور عزيز بن فرحان العنزي حفظه الله .

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

01 Nov, 14:13


بسم الله الرحمن الرحيم

በዘህራ መስጂድ ውስጥ በኡስታዝ በሳዳት ከማል የተጀመረው "የዕውቀት መጀመሪያ 130 ሀዲሶች" የሚለው ኪታብ ቂርአት:

በአሏህ ፈቃድ የነገው ቅዳሜም ከጠዋቱ 12፡15 እስከ 1፡15 ድረስ ይኖራል።

ቂርአቱ ሁሌም ቅዳሜ ከጠዋቱ 12፡15 እስከ 1፡15 ድረስ ይስሰጣል።

ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል።

ኪታቡ ለሌላቸው ሰዎች በወቅቱ በነፃ የሚታደል ሲሆን ፡ ለበለጠ መረጃ በ
@YunusHassen ማናገር ይቻላል።

🔵ኑ! አምልኮአችንን በዕውቀት ላይ የተመሰረተ እናድርግ!

ዘህራ መስጂድና መድረሳ!

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

01 Nov, 10:31


🔴ሰውን ማነወር፡ በሰው ማሾፍ፡ በሰው ላይ ማላገጥ አይገኝም፡

🤔#ጎደሎ ከሆነ ሰው እንጂ!

ከዛሬው ኹጥባችን የተወሰደ።

صلوات ربي وسلامه عليه 🌴

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

01 Nov, 07:42


ማስታወስ ብቻ ሳይሆን እኛም እንተግብር፡

በጁሙዓ ዕለት ተገቢ ከሆኑ ነገሮች፡

💜ገላን መታጠብ፡
💜ጥሩ ልብስ መልበስ፡
💜ለወንዶች ሽቶ መቀባት፡
💜በጊዜ ወደ መስጂድ መኼድ፡
💜ሶለዋት ማብዛት፡
💜ሱረቱል ከህፍ መቅራት፡
💜መስጂድ ሲገቡ ሰዎችን ለያይቶ አለመቀመጥና በሰዎች ትከሻ አለመረማመድ፡
💜ኹጥባ ሲደረግ ምንም ነገር አለማውራት፡
💜በተለይ ከዐሱር ሶላት በኋላ ዱዓእ ማብዛት ይገኙበታል፡

#ጁሙዓ_ሙባረክ መባባል መሰረት የሌለው #ቢድዓ መሆኑን ዑለሞች ተናግረዋል።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

01 Nov, 06:30


በአሁን ወቅት ከሙስሊም ጠል ግለሰቦች ባልተናነሰ ኒቃብ ላይ እንቅፋት የሆኑ 2️⃣ ነገሮች ይታዩኛል፡

🔴ያለ ዕውቀት በኒቃብ ጉዳይ ፈትዋ የሚሰጡ "ሙተከሊሞች"ና፡

🔴አሏህ ይምራቸውና ኒቃብ ለብሰው አየር ላይ የሚነጥሩ፡ ከስነምግባር የተራቆቱ፡ የአይናቸው ኩልና የጥፍራቸው ቀለም የሚያሳዩ፡ የኒቃብን ክብርና መስፈርት ያልተረዱ እህቶች ናቸው።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

Abu Furat

31 Oct, 19:34


🤎ኒቃብን የለበሰች ሴት በዱንያ እንኳ ከቦዘኔዎችና ከወሮበሎች "ለከፋና" ጉንተላ ሰላም ሁና ትራመዳለች።

⭐️የትኛውም ሰው ቢያከብራት እንጂ በመጥፎ ነገር ሊያዋራት አይሞክርም።

ደህና እደሩ።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

3,314

subscribers

1,440

photos

658

videos